የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ወርቅነሸ » Mon Aug 02, 2010 3:25 pm

ዘ ተዋሕዶ wrote:ለሶስተኛ መደብ (ለነጠላና ለብዙ ፆታዎች ) የሚያገለግሉ

ለነጠላ ወንድ
. ዝንቱ :
. ዝክቱ : ይህ : እሱ
. ዝ ይህ

ለብዙ ወንዶች
. እሙንቱ
. እሉ
. እሎንቱ
. እልክቱ : እነሱ : (እነሱ )

ለነጠላ ሴት (ፆታ)
. ዛቲ
. ዛ : ያች

ለብዙ ሴቶች
. እማንቱ
. እላ
. እላንንቱ
. እልኩ
. እንትኩ : እነዚህ : እነዛ : (እነሱ)

ከላይ እንደገለጽነው

"ውእቱ " ማለት : "ነው " : ማለት ሲሆን
በአሥሩም መደቦች ያገለግላል :

ነገር ግን :
. ለሩቅ ሴት
. ለሩቅ ወንዶች ና
. ለሩቅ ሴቶች ሲሆን : የተለየ ጸባይ አለው ::

ለምሳሌ

1, ለሩቅ ነጠላ ሴት

ዛቲ : ይህች (ያች ) : ናት : ለሚለው :
የሩቅ ሴት : ውእቱ በማለት ፋንታ :
ዛቲ : ይእቲ : ይህች ናት ይላል ::

2ኛ , ለሩቅ ወንዶች

እሙንቱ
. እሉ
. እሎንቱ
. እልክቱ : ለሚሉት : ውእቱ : ሳይሆን :
ውእቶሙ (ናቸው ) ይሆናል ::

3ኛ , ለሩቅ ሴቶች

. እማንቱ
. እላ
. እላንንቱ
. እልኩ
. እንትኩ :: ለሚለውም : ውእቱ ሳይሆን :

ውእቶን : (ናቸው ) ይላል ::

ስለዚህ

""ውእቱ "" : ከአሥሩ መደቦች ውስጥ

1. ለሩቅ ወንዶች
2. ለሩቅ ሴት እና
3. ለሩቅ ሴቶች : እንደማያገለግል : በጥንቃቄ ማስተዋሉ ጥሩ ነው ::

ይቀጥላል ::


1, ለሩቅ ነጠላ ሴት

ዛቲ : ይህች (ያች ) : ናት : ለሚለው :
የሩቅ ሴት : ውእቱ በማለት ፋንታ :
ዛቲ : ይእቲ : ይህች ናት ይላል ::


እርማት... ዛቲ ይህች (ያች) ናት ለሚለው ዳቲ ተብሎ ይነበብ...በል ዛ...ዛ..ዛ..ዛ.. ብለህ የተንዛዛሀው ቦታ ሁሉ ዳ...ዳ..ዳ..ዳ.. ብለህ አስተካክለው :lol:

ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
ወርቅነሸ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 467
Joined: Tue Oct 06, 2009 12:20 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Tue Aug 03, 2010 6:38 am

አንዳንድ አገባቦችን
በአስሩ መራህያን እያስገባን ለማየት እንሞክር ::

በእንተ - ስለ

ውእቱ.........> በእንቲአሁ ......... ስለሱ
ውእቶሙ....> በእንቲአሆሙ .... ስለነሱ
ይእቲ........ > በእንቲአሃ .......... ስለሷ
ውእቶን......> በእንቲአሆን ...... ስለነሱ

አንተ....................> በእንቲአከ ...... ስላንተ
አንትሙ...............> በእንቲክሙ .... ስለናንተ
አንቲ....................> በእንቲአኪ ....... ስላንቺ
አንትን.................> በእንቲአክን .... ስለናንተ

አነ..............> በእንቲአየ ....... ስለኔ
ንህነ...........> በእንቲአነ ........ ስለኛ

-----------------------------------------------

መንገለ - ወደ

ውእቱ ...................... መንገሌሁ ........... ወደሱ
ውእቶሙ ................. መንገሌሆሙ ...... ወደነሱ
ይእቲ ........................ መንገሌሃ ........... ወደሷ
ውእቶን ..................... መንገሌሆን ....... ወደነሱ

አንተ ............. መንገሌከ ............ ወዳንተ
አንትሙ ........ መንገሌክሙ ....... ወደናንተ
አንቲ .............. መንገሌኪ .......... ወዳንቺ
አንትን ............ መንገሌክን ........ ወደናንተ

አነ ........... መንገሌየ ........... ወደኔ
ንህነ ......... መንገሌነ ........... ወደኛ

ይቀጥላል
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Aug 04, 2010 5:09 pm

ጥቂት ዐረፍተ ነገሮች በግዕዝ ቋንቋ

ዝንቱ ብዕሲ : ሄር ውእቱ - ይህ ሰው ደግ ነው

ዛቲ ብዕሲት : ሰናይት ይእቲ - ያች ሴት ቆንጆ ናት

አነ ውእቱ : ገባሬ ሰናይ ዘእንበለ አስብ
እኔ ያለ ደመወዝ : በጎ ሥራ የምሰራ ሰው ነኝ

አብርሐም አቡነ ወጽአ እምሀገሩ ሰሚኦ ቃለ እግዚአብሔር
አብርሐም አባታችን : የእግዚዐብሔርን ቃል ሰምቶ ከሀገሩ ወጣ :

አነ እሜህር ልሳነ ግዕዝ : ውስተ ዝንቱ አምድ ::
እኔ በዚህ አምድ ውስጥ : የግዕዝ ቋንቋን አስተምራለሁ ::

በካልዕ እለት እዌስክ : ካልዓነ ቃላተ
በሌላ ቀን ሌሎች ቃላትን እጨምራለሁ
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

ጳጳስ ?

Postby እንሰት » Fri Aug 13, 2010 10:19 am

ሰላም ለመምህር እና ለአረዳው

ጳጳስ ኤጲስ ቆጶስ እና ዲያቆን ከግሪክ የተወረሱ የቤ/ክ/ ማእረጎች እንደሆኑ አውቃለሁ

ካህን ደብተራ እና ቄስስ? አሁን አሁን ደግሞ ቀሢስ ም ይባላል:: እነዚህ ቃላት ምንጫቸው ምንድን ነው?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዘ ተዋሕዶ » Mon Oct 31, 2011 7:17 pm

ጤና ይስጥልኝ ይህን መልእክት ለምታነቡ ሁሉ

ጊዜ ሲኖራችሁ እስኪ ይህን ትከልከቱት
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Nov 03, 2011 3:41 am

ሰላም 'ዘ-ተዋሕዶ' :-

ስለ ግእዝ ቋንቋ ያለኝ ዕውቀት እጅግ በጣም ውሱን ነው :: ነገር ግን በግሌ የግእዝ ቋንቋን ለመማር ለማደርገው ጥረት እንዲረዳኝ ከገዛኋቸው መጻሕፍት መካከል ለጊዜው ለመገንዘብ የቻልኩትን ለማካፈል እጥራለሁ ::

ለዚህ አስተያዬት በምንጭነት የተጠቀምኩበት ሟቹ ዶክተር ዶክተር ለይኩን ብርሃኑ በ1998 ዓ.ም. 'የግእዝ ቋንቋ መማሪያ' በሚል ርዕስ ያሣተሙት መጽሐፍ ነው ::

ስለ ግእዝ ቋንቋ ፊደላት ባቀረብኸው ትምህርት ላይ ተጨማሪ የሚሆኑ ኃሣቦችን ለማከል ያህል :-

ፊደል የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን ምንጩም 'ፈደለ' ከሚለው ግሥ የወጣ ነው :: 'ፈደለ' የአማርኛ አቻ ቃሉ 'ጻፈ' ማለት ሲሆን 'ፊደል' ደግሞ የአማርኛ ትርጉሙ 'ጽሑፍ' ማለት ነው ::

ዶክተር ለይኩን ሃያ ስድስቱን የግእዝ ቋንቋ ፊደላት በሦሥት ክፍሎች ይመደቧቸዋል :- ቅደም ተከተላቸውም በቁጥር ከ 1 እስከ 800 ነው :: ፊደላቱ ከእነ ትርጓሜያቸው እንዲህ ያቀርቡታል :: [እንግዲህ የዋርካ ባለቤቶች የግእዝ ቁጥሮችን መጻፍ እስኪያስችሉን ድረስ በአረቦች ቁጥሮች እንጠቀም ::]

ፊደላቱ _____________ መለያ ቁጥር ____ ትርጓሜ
ክፍል 1

ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ ________ 1 ____ ሀለወቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ::
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ _______ 2 ____ ለብሰ ሥጋ :: እምንድንግል ::
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ _____ 3 ____ ሐመ ወሞተ ::
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ ____ 4 ____ መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ::
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ _____ 5 ____ ሠረቀ በሥጋ ::
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ _______ 6 ____ ረግዓት ምድር በቃሉ ::
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ________ 7 ____ ሰብአ ኮነ እግዚእነ ::
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ _______ 8 ____ ቀዳሚሁ ቃል ::
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ _______ 9 ____ በትሕትናሁ ወረደ ::
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ ______ 10 ____ ተሰብአ ወተሰገወ ::

ክፍል 2
ኅ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ ______ 20 _____ ኃያል እግዚአብሔር ::
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ ________ 30 _____ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ::
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ _____ 40 _____ አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ::
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ ______ 50 _____ ከሃሊ እግዚአብሔር ::
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ _____ 60 _____ ወረደ እምሰማይ ::
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ _______ 70 _____ ዐርገ ሰማያተ ::
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ _______ 80 _____ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ::
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ _______ 90 ______ የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ::

ክፍል 3
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ______ 100 _____ ደመረ ሥጋነ ምስለ መለኮቱ ::
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ _______ 200 _____ ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ::
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ ___ 300 _____ ጠዐሙ ውታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ::
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ ______ 400 _____ ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ::
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ ______ 500 _____ ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ::
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ _______ 600 _____ ፀወነ ኮንከነ ::
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ ______ 700 _____ ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ::
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ _____ 800 _____ ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ::

ከአማርኛ ፊደላት ውስጥ ያልጠቀስኸው ሆሄ 'ቨ' ነው :: በእርግጥ በቅርብ ጊዜ የተጨመረ ስለሆነ እኔ ፊደል በቆጠርሁበት ዘመን በፊደል ገበታ ላይ አልነበረም ::

በሚቀጥለው ክፍል ስለ ግእዝ ግሦች ርባታ ያገኘሁትን አካፍላለሁ ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Mar 23, 2012 9:53 pm

ሰላም ዘ-ተዋሕዶ :-

ስለ ግእዝ ትምህርት ከስምንቱ አቢይ የግሥ ቤቶች አረባብ ጀምሮ በ'ደበሎ' ድረ-ገፅ አለ :: ከዚያ ጥሩ ትምህርት ማግኘት ይቻላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ::

ምንጭ:- ደበሎ : ስምንቱ አርእስት ከነ አርስቶቻቸው ::

ሀ ..... የ'ቀተለ' ሠራዊት:- ቀተለ ..... ገደለ (በአማርኛ)
ለ ..... የ'ቀደሰ' ሠራዊት:- ቀደሰ ..... አመሠገነ (በአማርኛ )
ሐ ..... የ'ባረከ' ሠራዊት:- ባረከ ..... ባረከ (በአማርኛ )
መ ..... የ'ገብረ' ሠራዊት:- ገብረ ..... አደረገ (በአማርኛ )
ሠ ..... የ'አእመረ' ሠራዊት:- አእመረ ..... አወቀ (በአማርኛ )
ረ ..... የ'ሤመ' ሠራዊት:- ሤመ ..... ሾመ (በአማርኛ )
ሰ ..... የ'ብህለ' ሠራዊት:- ብህለ ..... አለ (በአማርኛ )
ሸ ..... የ'ቆመ' ሠራዊት: ቆመ ..... ቆመ (በአማርኛ )

ከዚህ መጀመር ይቻላል ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት

Postby Gragn ahmed » Fri Mar 23, 2012 11:43 pm

ዘ ተዋሕዶ wrote:በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

ውድ ወገኖች እንደምን አላችሁ ?

በዚህ ርዕስ ሥር : ለመግባቢያነት ያህል ግዕዝ ቋንቋ እንማማራለን

ለጊዜው ቀለል ባለ መንገድ እንጀምረውና ሁኔታውን እያየንም በጋራ እንዲሰፋ እናደርጋለን

ትምሕርቱ በቋንቋው ላይ ብቻ ያተኮረ ስለሆነ : ሌሎች አርዕስቶችን አያስተናግድም ::

የግዕዝ ቋንቋን ስናጠና በቅድሚያ ማወቅ ያለብን ፊደላቱን ነው ::

ከ ሀ እስከ ፐ ያሉት ፊደላት : ሁሉም የግዕዝ አይደሉም ::
ይህም ማለት {የሰው እና የቦታ ስሞች ካልሆኑ በቀር } በግሥ አረባብም ሆነ በዐረፍተ ነገር አመሰራረት ላይ የማይገኙ ማለት ነው

የግዕዝ ያልሆኑት ፊደላትም የሚከተሉት ናቸው

1. ሸ ሹ .......
2. ቸ ቹ ......
3. ኘ ኙ ......
4. ኸ ኹ .....
5. ዠ ዡ .....
6. ጀ ጁ .......
7. ጨ ጩ .....: ናቸው ::

ሌሎች ግን ሁሉ {ኰ - ጐ - ቈ - ኈ } የሚባሉትን ጨምሮ የግዕዝ ፊደላት ናቸው ::

ለዛሬው ከላይ በመግቢያዬ ላይ የጠቀስሁትን የግዕዝ ሐረግ {ዐረፍተ ነገር } ላብራራ

በ -ስመ አብ ወ -ወልድ ወ -መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ


{በ} የሚለው ቃል በዚህ ንባብ ትርጉሙ አይለውጥም ያው {በ} ነው ::

{ስመ} - የሚለው ቃል : ሰመየ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም : ስም አወጣ - ሰየመ ማለት ነው : {ስም} ::

{አብ} - ተአበወ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አባት ሆነ ማለት ነው :: {አባት}

{ወልድ} - ወለደ {ለ : አይጠብቅም } ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ወለደ {ለ : ይጠብቃል } :: {ልጅ}

{መንፈስ} - ነፍሰ : ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ነፈሰ ማለት ነው :: {ረቂቅ}

{ቅዱስ} - ቀደሰ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም {በዚህ ቃል ብቻ } አመሰገነ : አከበረ ማለት ነው :: {ክቡር : ምስጉን}

{አሐዱ} - አሐደ : ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም አንድ አደረገ ማለት ነው :: {አንድ}

{አምላክ} - መለከ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ገዛ ማለት ነው : {ገዥ}

{ወ }. ወልድ ወ .መንፈስ ቅዱስ {ወ የሚለው በዚህ ዐረፍተ ነገር ብቻ } {እና } ተብሎ ይፈታል ::

{የመጀመሪያው የግዕዙ ቃል} ሲሆን {የመጨረሻው ደግሞ የአማርኛ ቀጥተኛ ትርጉሙ} ነው ::

ጠቅለል ያለ ትርጉሙ

በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ
ወይም
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማለት ነው ::

ስለ አቀራረቡ ማኛውንም ዓይነት አስተያየትም ሆነ ጥያቄ በደስታ እቀበላለሁ ::

በሚቀጥለው ትምሕርታችን
{የግዕዝ} ፊደላት ለግዕዝ ቋንቋ ያላቸውን መሰረትነት እንማማራለን

ስብሐት ለእግዚአብሔር - ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
አሜን

ይቆየንስራ ፈት ነህ ልበል ?
እንደው በዚህ በሞተ ቁንቃ ጊዜቸንን እናባክን ????????????
Gragn ahmed
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Wed Jul 20, 2011 7:29 am

Re: የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Mar 24, 2012 12:04 am

Gragn ahmed wrote:
ዘ ተዋሕዶ wrote:በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

ውድ ወገኖች እንደምን አላችሁ ?

በዚህ ርዕስ ሥር : ለመግባቢያነት ያህል ግዕዝ ቋንቋ እንማማራለን

ለጊዜው ቀለል ባለ መንገድ እንጀምረውና ሁኔታውን እያየንም በጋራ እንዲሰፋ እናደርጋለን

ትምሕርቱ በቋንቋው ላይ ብቻ ያተኮረ ስለሆነ : ሌሎች አርዕስቶችን አያስተናግድም ::

የግዕዝ ቋንቋን ስናጠና በቅድሚያ ማወቅ ያለብን ፊደላቱን ነው ::

ከ ሀ እስከ ፐ ያሉት ፊደላት : ሁሉም የግዕዝ አይደሉም ::
ይህም ማለት {የሰው እና የቦታ ስሞች ካልሆኑ በቀር } በግሥ አረባብም ሆነ በዐረፍተ ነገር አመሰራረት ላይ የማይገኙ ማለት ነው

የግዕዝ ያልሆኑት ፊደላትም የሚከተሉት ናቸው

1. ሸ ሹ .......
2. ቸ ቹ ......
3. ኘ ኙ ......
4. ኸ ኹ .....
5. ዠ ዡ .....
6. ጀ ጁ .......
7. ጨ ጩ .....: ናቸው ::

ሌሎች ግን ሁሉ {ኰ - ጐ - ቈ - ኈ } የሚባሉትን ጨምሮ የግዕዝ ፊደላት ናቸው ::

ለዛሬው ከላይ በመግቢያዬ ላይ የጠቀስሁትን የግዕዝ ሐረግ {ዐረፍተ ነገር } ላብራራ

በ -ስመ አብ ወ -ወልድ ወ -መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ


{በ} የሚለው ቃል በዚህ ንባብ ትርጉሙ አይለውጥም ያው {በ} ነው ::

{ስመ} - የሚለው ቃል : ሰመየ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም : ስም አወጣ - ሰየመ ማለት ነው : {ስም} ::

{አብ} - ተአበወ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አባት ሆነ ማለት ነው :: {አባት}

{ወልድ} - ወለደ {ለ : አይጠብቅም } ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ወለደ {ለ : ይጠብቃል } :: {ልጅ}

{መንፈስ} - ነፍሰ : ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ነፈሰ ማለት ነው :: {ረቂቅ}

{ቅዱስ} - ቀደሰ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም {በዚህ ቃል ብቻ } አመሰገነ : አከበረ ማለት ነው :: {ክቡር : ምስጉን}

{አሐዱ} - አሐደ : ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም አንድ አደረገ ማለት ነው :: {አንድ}

{አምላክ} - መለከ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ገዛ ማለት ነው : {ገዥ}

{ወ }. ወልድ ወ .መንፈስ ቅዱስ {ወ የሚለው በዚህ ዐረፍተ ነገር ብቻ } {እና } ተብሎ ይፈታል ::

{የመጀመሪያው የግዕዙ ቃል} ሲሆን {የመጨረሻው ደግሞ የአማርኛ ቀጥተኛ ትርጉሙ} ነው ::

ጠቅለል ያለ ትርጉሙ

በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ
ወይም
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማለት ነው ::

ስለ አቀራረቡ ማኛውንም ዓይነት አስተያየትም ሆነ ጥያቄ በደስታ እቀበላለሁ ::

በሚቀጥለው ትምሕርታችን
{የግዕዝ} ፊደላት ለግዕዝ ቋንቋ ያላቸውን መሰረትነት እንማማራለን

ስብሐት ለእግዚአብሔር - ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
አሜን

ይቆየንስራ ፈት ነህ ልበል ?
እንደው በዚህ በሞተ ቁንቃ ጊዜቸንን እናባክን ????????????

Gragn ahmed:

Everybody in the Warka Forum knows that you are one of the representatives of Al-Qaeda in Warka. You may use different pseudonames: Worknech, Jemila, Ethio-Mujahidin, Dr Zaker, Selemtew, Woldiya, etc., but you are the same person. Your master and evil-doer, Usama Bin-Laden, was killed for good by the brave SEALS of the USA. Rest assured, you will be caught too. You cannot keep yourself in hiding behind a pseudoname forever.

Tedla
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Dec 01, 2013 4:51 am

ሰላም ወገኖቼ:-

ይህንን ድረ-ገፅ እስከዛሬ ባለማወቄ ...
ግእዝ በመሥመር-ላይ

እንበርታ: ግዕዝ አልሞተም: አይሞትምም::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ወርቅነች » Sun Dec 01, 2013 5:19 am

እንበርታ : ግዕዝ አልሞተም : አይሞትምም ::


ቅቅቅቅቅ...ፈዛዛው..በወርቅነሸ ወርቁ ዘመኔ ኒክ ሰም ከመታገዴ በፊት ጎልጉለህ የወርቅነሸን ትዝታዮን ብትቀሰቅሰውም ግእዝ ቢሞትም ባይሞትም አንተ ሞተሀል ትላለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol: :lol:

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ወገኖቼ:-

ይህንን ድረ-ገፅ እስከዛሬ ባለማወቄ ...
ግእዝ በመሥመር-ላይ

እንበርታ: ግዕዝ አልሞተም: አይሞትምም::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests