ተጠያቂዎቹ በከፊል ቄሶች ናቸው

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ተጠያቂዎቹ በከፊል ቄሶች ናቸው

Postby shebellawiye » Sat May 16, 2009 6:04 am

እንደምን ከረማቹ''

ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍተዋል <<<<<<<<<<ይላል መጽሀፍ ቅዱሱ;;

95% የኢትዪጵያ ኦርቶዶክስ ምእመን የእግዚያብሄር ቃል እውቀት የለውም;; ለምን የለውም?

1=አስተማሪዎቹ ቄሶቹ መጽሀፍን ከሚሰብኩ ይልቅ የሚዘበዝቡት ነገር ጭራሽ አንዳንዱማ ተቃራኒ ነው;; መጽሀፍ ቅዱስን ማሳለም እንጂ ውስጡን ከፍተው ለማስተማር አልደፈሩም;; ከመጽሀፉ ይልቅ ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ የሚሸጡትን ድርሳነ ሚካኤል ክርስቶስ ሳምራ ......ወዘተ ይተርካሉ;;ሀይማኖታችን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ከማለት ያለፈ እና የጥላቻን ዘመቻ የሚያስፋፋ ስብከት መሳይ ነገር ከመጽሀፍ ቅዱስ አንድም ሳይጠቀስ ይሄንን ህዝብ በደመነፍስ እንዲሄድ ያደርጉታ;; ለዚህም ማስረጃ አንድን ምእመን ስለመጽሀፍ ቅዱስ ብትጠይቁት ቤተክርስቲያን ስሞ ከመመለስ ያለፈ ነገር መጽሀፉ እንዲህ ይላል ብሎ የሚናገር አታገኙም;; እዚህ ፎረም ላይ እንክዋን ጥያቄ ሲጠየቁ እውቀቱ ስለሌለ ወይ ወደ ስድብ ይሄዳሉ አለበለዚያም ጥያቄውን ለማረሳሳት መልስ መስጠት ሳይችሉ ሲቀሩ ሌላ ጥያቄ በመጠየቅ ወደ ንትርክ ጭቅጭቅ ሲገቡ ይታያሉ;; እውቀት ማጣት;; ይሄ ታዲያ የቄሶች ስንፍና ብቻ ሳይሆን ምእመኑም መጽሀፍ ቅዱስ ገልጾ ለማንበብ ትልቅ ችግር አለበት ያውም ማንበብ እየቻለ;; አባት እናቶች በነሱ ጊዜ ምናልባት ብዙሀኑ ማንበብ ስለማይችሉ ቄሶች የነገሯቸውን ብቻ በየዋህነት ተቀብለዋል;; እግዚያብሄር የዋሆችን ስለሚወድ እንደልባቸው ተቀብሏቸዋል;; የነሱ የዋህነት ነው እኛን የሚያኖረን;; ይህ ሲባል ግን ጥሩ አባቶች መጽሀፍ ቅዱስን የሚያስተምሩም እንዳሉ ሊተኮርበት ይገባል;; ብቻ አንዳንዴ መጽሀፉን ገልጸው ሲያስተምሩ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ሆኑ ተብሎ ስም ይሰጣቸዋል ምክንያቱም ስላልተለመደ በእምነቱ;;

2=የኛ ትውልድ ግን ማንበብ እየቻለ መጽሀፍ ቅዱስን ከማንበብ ሌላ ነገር ማንበብ ይቀለዋል;; ባጭሩ የምእመኑም ስንፍና አለበት;; መጽሀፍ ቅዱስን ለማንበብ ይፈራል;; ይሄም ለእውቀት ማነስ አስተዋጾ አድርጎአል;;


የተለየ ሀሳብ ካላቹ አስተያየት መስጠት ይቻላል;; ጽሁፉ ግን ይቀጥላል;; ንትርክ ጭቅጭቅ ስድብ አይፈቀድም;;
shebellawiye
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Sat Oct 21, 2006 9:32 pm

Postby ዋሕድ » Sat May 16, 2009 10:25 pm

23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።
ብሎ አስተምሮን ነበር መድዓኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ስጋዌው........

ታዲያ እንዚህ የትንቢት መፈጸሚያዎች.... የአለም ጉዶች... ከ2000 አመት በኃላ ጠፍጥፈው የሰሩትን የሱስን ተቀበሉ ይሉናል.... ታዲያ መልሳችን አሁንም እንዲህ ተብለን ነበር ነው 23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።100% የፕሮቴስታንት ድርጅት ተከታይ የሚያምነውን አያቅም........ ግን ሁሉም አንድ ነገር ይቃወማሉ......ተዋህዶን.... ይቃወማሉ እንጂ የሚቃወሙትን ግን አያቁም....... የአህዛብ አለማመን ሆዳቸውን ሲቆርጣቸው አይታይም.... ግን የተዋህዶ ነገር እንደ ፖሊዮ ሽባ አርጓቸው አሰልሏቸዋል...... መጽሃፍ ቅዱስን ተሸክመው ይዞራሉ ግን አያውቁትም..... እርሱም ይመሰክርባቸዋል...... እራሳቸውን በራሳቸው አጽድቀው ያንቆለጳጵሳሉ ግን ክርስቶስ የመረጣቸውን ቅዱሳንን ያንኩዋስሳሉ...... ስለክርስትናቸው ክርስቲያኑን ሊጭኑት ይፈልጋሉ ግን አህዛብን ስለክርስትና ሲያናግሩ በስህተት እንኳን አይታዩም...... ለምን ቢሉ የመሀመድና በእነርሱ ላይ የሰፈረው ጋኔን ግባቸው አንድ ስለሆነ!.....


ዋሕድ
ዋሕድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 415
Joined: Fri Apr 03, 2009 6:01 pm

Postby ማህለይ » Sun May 17, 2009 5:16 am

ዋሕድ wrote:[color=red]

100% የፕሮቴስታንት ድርጅት ተከታይ የሚያምነውን አያቅም........
ያብዬን ወደምዬ ማለት እንዲህ ነው! እናንተ ተህዋዶዎች መጻፍቅዱስ ምን እንደሆነ ያስተማርናቹ እኛ ጴንጤ ክርስያኖች ነን! ዘር ማንዘራቹ ዳዊት ሲያነበንብ መጻፍቅዱስ ያወቃቹ መሰላቹ እንጂ...... ዋህዴ የኔ ቆንጆ አንዲትም ነገር አታውቂም!አታውቁም!

ግን ሁሉም አንድ ነገር ይቃወማሉ......ተዋህዶን.... ይቃወማሉ እንጂ የሚቃወሙትን ግን አያቁም.......
ሰይጣንን ተቃወሙት ብሎ መጻፍቅዱስ ስለሚያዝ ነዋ! እስቲ ሄደሽ አንብቢው! አንቺ መጻፍቅዱስን እንደቄሶችሽ መንተራስሽ ቀርቶ የቡና ገበታ ነው ያረክሽው መሰለኝ! እስቲ ገለጥ አርጊና ስለሴጣን/ስለተዋህዶ/ የተጻፈውን አንብቢው


የአህዛብ አለማመን ሆዳቸውን ሲቆርጣቸው አይታይም....
እና የቄሶችሽን ነው የሚቆርጠው? አዎ የ40 የ80 የሙት አመት ገለመሌ በማለት እየዘረፉ በሚበሉት ምግብ በቁንጣን ሲታመሙ-ለአህዛብ ሆዳችንን ቆረጠን ትያለሽ! መጀመርያ አህዛብ ማለት ተዋህዶና አማኞችዋ መሆናቸውን እወቂ::

ክርስቶስ የመረጣቸውን ቅዱሳንን ያንኩዋስሳሉ......

ሳምራን ክርስቶስ መረጣት? ተክልዬንም እንደዛው? እነሱ ጠንቅዋዮች ቅዱሳን ናቸው? :P

ስለክርስትናቸው ክርስቲያኑን ሊጭኑት ይፈልጋሉ ግን አህዛብን ስለክርስትና ሲያናግሩ በስህተት እንኳን አይታዩም...... ለምን ቢሉ የመሀመድና በእነርሱ ላይ የሰፈረው ጋኔን ግባቸው አንድ ስለሆነ!.....


ድንጋይ እየወረወርሽበትና እየሰደብሽ የምታሳድጅው በየመንገዱና በየቤቱ እየዞረ የሚሰብከውን ጴንጤ ክርስትያን እንዴት ትዝ አላሉሽም ከላይ ያለውን ስትጽፊ? ነገረ ስራቹ ሁሉ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ክስ ብቻ የሞላባቹ ናቹ! ዛሬ ያላቹን ነገ የምታፈርሱ የዜሮ ድምር ሁላ :P :P :P

ዋህድ እስቲ ለቅልቂው መልስሽን! በዛውም ቄስ ትምህርት ቤት እያለሽ ያስተማሩሽን ስድብ ጭምር!
ማህለይ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1067
Joined: Wed Sep 26, 2007 8:13 pm

Postby NATHRATHE » Sun May 17, 2009 6:04 am

+++

95% የኢትዪጵያ ኦርቶዶክስ ምእመን የእግዚያብሄር ቃል እውቀት የለውም ;; ለምን የለውም ?

መናፍቃን ተራ ወሬ ማውራት ማንም አይችላችሁም:: እስቲ የትኛው ጥናት ላይ ነው የጠቀስከውን Data ያገኘህው:: እንደ ዲያብሎስ ሀሰት ከራስህ አመንጭተህ ስትጽፍ ትንሽ ቅር አይልህም::

ይቆየን
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

Postby ዋሕድ » Sun May 17, 2009 7:14 pm

ማህለይ wrote: ያብዬን ወደምዬ ማለት እንዲህ ነው! እናንተ ተህዋዶዎች መጻፍቅዱስ ምን እንደሆነ ያስተማርናቹ እኛ ጴንጤ ክርስያኖች ነን! ዘር ማንዘራቹ ዳዊት ሲያነበንብ መጻፍቅዱስ ያወቃቹ መሰላቹ እንጂ...... ዋህዴ የኔ ቆንጆ አንዲትም ነገር አታውቂም!አታውቁም!


አንተ እኮ አቴይስት ነህ! ስለመጽሃፍ ቅዱስ ከማውራትህ በፊት መጀመሪያ በእግዝሃብሔር መኖር ማመን አለብክ እኮ!.... አንተ እኮ የነፍስን ዘላለማዊነት የማታምን በስብሰክ የምትቀር ብስብስ ነህ!.... ለጴንጤዎች ጥብቅና የምትቆመው የሰፈረባቹ ጋኔን ግባቸው አንድ ስለሆነ ነው አይደል?....

ከመቼ ወዲ ነው ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስን ጴንጤ ማስተማር የጀመረው?.... ደፋር እኛ ነን ያስተማርናቹ ትላለክ ደግሞ እንዴ?... አንድ ቀን እንኩዋን ተሳስታችሁ ቃሉን አስተምራችሁ አታውቁም!... ተዋህዶን ስትሰድቡ መሸባችሁ እንጂ!.... ስማ አማኙን ሕዝብ መጽሃፍ ቅዱስን እንዲጥል ጡል ጡል ማለታችሁን ሀገር ያወቀው ጉዳቹ ነው.... መዝሙረ ዳዊትን መጥላታችሁ አንዱ ጸረ-መጽሃፍ ቅዱስ መሆናችሁን ያሳያል..... ትላንት መጥታችሁ ዱንኳን ተክላቹህ የሱስን እንደ ግል አዳኝ ተቀበል ስትሉ ቅዱሳን አባቶቻችን ለአንድዬ ከቋጥኝ አለት ፈልፍለው ቤተ-መድዓኒአለም ብለው የአለም አዳኝነቱን ጥንት መስክረው ዛሬም ለዚህ ዘመን ትውልድ ተርፈዋል..... የት እና የት እኮ ነን! በፍጹም ለንጽጽር እንኳን አትቀርቡም::

ሰይጣንን ተቃወሙት ብሎ መጻፍቅዱስ ስለሚያዝ ነዋ! እስቲ ሄደሽ አንብቢው! አንቺ መጻፍቅዱስን እንደቄሶችሽ መንተራስሽ ቀርቶ የቡና ገበታ ነው ያረክሽው መሰለኝ! እስቲ ገለጥ አርጊና ስለሴጣን/ስለተዋህዶ/ የተጻፈውን አንብቢው


ድሮም እኮ ሰይጣን "እኔ ሰይጣን ነኝ" ብሎ በፊት ለፊት አይመጣም እንዲህ በእንዳንተ አይነቱ ላይ አድሮ ልብክን ዙፋኑ እጅክን ደግሞ ንዋያተ ቅዱሳንን መስረቂያ; እግርክን ወደ ርኩሰቱ ስፍራ መሄጃ እና መምጪያ; ምላስክን ቅዱሳንን መስደቢያ አርጎ ይጠቀምበታል እንጂ... ለዚህም ነው ከእናት ልጅ በላይ ውድ የሆነው መድህን አለም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ያስተማረን:
23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


እና የቄሶችሽን ነው የሚቆርጠው? አዎ የ40 የ80 የሙት አመት ገለመሌ በማለት እየዘረፉ በሚበሉት ምግብ በቁንጣን ሲታመሙ-ለአህዛብ ሆዳችንን ቆረጠን ትያለሽ! መጀመርያ አህዛብ ማለት ተዋህዶና አማኞችዋ መሆናቸውን እወቂ::


እናንተ የድኽነቱን ሕያው ቃል ለሃብት ድህነት መቀነሻ የምትጠመዝዙ... የብልጽግና "ወንጌል" ሰባኪዎች.... ሐሰተኛ ወንድሞች... እምነት የጎደላችሁ ተጠራጣሪዎች ስለሆናችሁ መናፍቃን የምትመጥን ስማችሁ ነች..... ክርስቶስን ፈጽሞ የማያውቁት አህዛብ ጣዎት አምላኪዎች በአንድ የዲያብሎስ ግንድነት አንድ ስለሆናችሁ ስለ እነርሱ አይገዳችሁም!.... መጀመሪያ ክርስቶስን አላወቅህ ስለ 40 እና 80 ትቀባጥራለክ... ሆድ አምላኩ! ሕጻናት በ40 እና በ80 ቀን ሲጠመቁ ስለሚገኝው ከእግዝአብሔር ጸጋ ይልቅ ሰዎች በፍቃዳቸው ተደስተው ስለሚደግሱት ድግስ ሆድህን ቆረጠክ አይደል?!


ሳምራን ክርስቶስ መረጣት? ተክልዬንም እንደዛው? እነሱ ጠንቅዋዮች ቅዱሳን ናቸው? :P

በምድር ላይ እኔ ጻድቅ ነኝ የማይል እንድም ጴንጤ የለም!... ሁሉም እራሱን አጽድቋል.... ታዲያ እናንተን ክርስቶስ ነው የመረጣችሁ?!.... እንዳውም አንዳንዴ በየትኛው ቴክኖሎጂ ተጠቅመው እንደሆነ እኔንጃ ብቻ ከጀምሳቸው ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲሆልን እና ገነትን ተዟዝረው አይተው እንደመጡ ሲናገሩ በፈጤ ነው!.... ሰዎች አልተረዱላችሁም እንጂ ባለ 4 ዲያሜንሽናል ፍጡሮች ናችሁ እኮ!.... ታዲያ ዛሬ ቅዱሳንን ለመሳደብ አፋችሁ ቢከፈት ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነውና አይደንቀንም.... እንዲህ ተብሎ ተስጽፎልናልና.... ለእናንተ ደግሞ ተጻፈባችሁ!
5 ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።6 እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።7 ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።

ድንጋይ እየወረወርሽበትና እየሰደብሽ የምታሳድጅው በየመንገዱና በየቤቱ እየዞረ የሚሰብከውን ጴንጤ ክርስትያን እንዴት ትዝ አላሉሽም ከላይ ያለውን ስትጽፊ? ነገረ ስራቹ ሁሉ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ክስ ብቻ የሞላባቹ ናቹ! ዛሬ ያላቹን ነገ የምታፈርሱ የዜሮ ድምር ሁላ :P :P :P


ተው እንጂ በግድማ አታስቀኝ እንጂ!... በየሰፈሩ የሚሰብኩ አልከኝ?!.. ቂ ቂ ቂ.... "ና አንተ ሰይጣን ያልበራልክ የሱስን ተቀበል!" የሚሉትን ነው ሲሰብኩ ያልከው.. ቂ ቂ ቂ.... ታዲያ መንፈሳውያን የተዋህዶ ልጆች ካልሆኑ እንዲህ ሲሰደብ እግዝአብሔር ይቅር ይበልክ ብሎ ዝም ብሎ የሚያልፍ የትኛው ሰው ነው?!.... አንተ እራስክ እንኳን በግል እዚህ ዋርካ ላይ አጸያፊ ስድብ ሲሰድቡክ ስንት ግዜ እኩል ስትመላለስ አልነበረም?!... ሲበዛ ግብዝ ነህ!
እኔን የሚገርመኝ በግል ሲሰድቡት ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው ግና ቅዱሳንን ሲሰድቡበት ጆሮ የሚሰጠው ኦርቶዶክስ ባይ ነኙ ነው እንጂ!.... ቢያንስ እነዚህን የአውሬው መንገድ ጠራጊዎችን በሕጋዊ አግባብነት መጠየቅ ሲችል በዝምታ መደንዘዙ ይገርማል!....

ዋህድ እስቲ ለቅልቂው መልስሽን! በዛውም ቄስ ትምህርት ቤት እያለሽ ያስተማሩሽን ስድብ ጭምር!


እግዝአብሄር እንዲያዝን አባትክ ዲያብሎስ እንዲደሰት ነው አይደል? አልሳደብም!

ዋሕድ
ዋሕድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 415
Joined: Fri Apr 03, 2009 6:01 pm

Re: ተጠያቂዎቹ በከፊል ቄሶች ናቸው

Postby ብርኃናዊት » Sun May 17, 2009 7:48 pm

shebellawiye wrote:እዚህ ፎረም ላይ እንክዋን ጥያቄ ሲጠየቁ እውቀቱ ስለሌለ ወይ ወደ ስድብ ይሄዳሉ አለበለዚያም ጥያቄውን ለማረሳሳት መልስ መስጠት ሳይችሉ ሲቀሩ ሌላ ጥያቄ በመጠየቅ ወደ ንትርክ ጭቅጭቅ ሲገቡ ይታያሉ;; እውቀት ማጣት;;


በጣም! :lol:

ለዚያ እኮ ነው ፕሮቴስታንቶች 1.5 ከ 34 ያመጡት?

:lol: :lol:
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby shebellawiye » Mon May 18, 2009 5:30 pm

የተለመደው መስመር የማሳት እና ጭቅጭቅ ንትርክ ንዝንዝ ከሚወዱት ወገን ቀጥሏል;; ይሁንና እውቀት የማጣት ጉድለት ተወደደም ተጠላም ነበረ አሁንም በግልጽ ይታያል ወደፊትም ችግሩን ለማስወገድ ከመጣር ይልቅ መነዛነዝ መነታረክ በጥላቻ ተሞልቶ መናገር ችግሩን ለመቅረፍ መርዳት ሳይሆን እንደውም ወደ ድቅድቅ ወዳለ ጨለማ ይመራል;;; እስኪ ስለክርክር መጽሀፍ ቅዱስ ምን ይላል;;

የአዲስ ኪዳን ገጽ 172 ገላትያ ምዕራፍ 5:21 የስጋ ስራ የተገለጠ ነው ርኩስት መዳራት ጣኦትን ማምለክ ጥል ክርክር ቅናት ቁጣ አድመኝነት....................................አስቀድሜም እንዳልኩት ይሄንን የሚያደርጉ የእግዚያብሄርን መንግስት አይወርሱም;;


ተብሎ ተጽፏል;;

ከዚህ በመቀጠል እንማማራለን;;

ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚያብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም;;

ለመሆኑ ዳግመኛ መወለድ ምን ማለት ነው;;<<<<, መጽሀፍ ቅዱስ ስለዚህ ምን ይላል;?????
shebellawiye
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Sat Oct 21, 2006 9:32 pm

Postby ብርኃናዊት » Mon May 18, 2009 5:53 pm

ፕሮቴስታንቶች 34 ጥያቄ ተጠይቀው 1.5 ከ 34 እንዴት አመጡ?? :lol:

:lol: :lol:

1.5 / 34????

ቱ ቱ ቱ ቱ!

አበስኩ ገበርኩ!

35ኛ ጥያቄ ይቀጥላል እሺ ሸበላዊ?

እና.... ያው ተጠያቂዎቹ ፓስተሮቻችሁ መሆናቸውን አብረን እንመለከታለን::
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ሀሁሁሁ » Mon May 18, 2009 6:13 pm

አይ ብርሀናዊት

የክርስትና መለኪያ ያንቺን ጥያቄ መመለስ መስሎሽ ከሆነ ምስኪን ነሽ ..

ለተረት ተረትሽ የላም በረት ለምን አላላችሁም ብሎ መወቀስ ድርቅና ይመስለኛል .

እግዚያብሔር ይርዳሽ ከእንኪያ ሰላምታ ወጥተሽ አሜን እንደቃልህ ይሁንልኝ የምትይበት ዘመን ይምጣልሽ ::

1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6
የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።
የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፥ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።
እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥
በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
ሀሁሁሁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 308
Joined: Fri Jan 20, 2006 11:44 pm

Postby ብርኃናዊት » Mon May 18, 2009 6:18 pm

ሀሁሁሁ:

ስለ ክርስትና ሳይሆን ስለመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ነው ሸበላዊ እያወራ ያለው::

በአስተያየቱ መሰረት- መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ቀርቧል::

35ኛ ጥያቄ

እና እስቲ መልሷት? :lol:
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ሱቱኤል » Mon May 18, 2009 7:41 pm

ሽብላዊም ሆነ ሌሎቻችሁም በሙሉ ይህንን ካማለታችሁ በፊት እራስህን ጠይቅ በመጀመሪያ ሰው ስለራሱ አውቆ ስለሌሎች ቢናገር ጥሩ ነበር ነገር ግን እናንተ ስለሰው ሀጢያት ወይም ተጠያቂነት ታወራላችሁ እናንተስ????????????
Peace
ሱቱኤል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Aug 11, 2006 9:01 pm
Location: All over

Postby shebellawiye » Tue May 19, 2009 7:21 am

ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ የእግዚያብሄርን መንግስት አያይም ብሎ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው ይሄንን ለአንድ የአይሁድ አለቃ ኒቆዲሞስ ለሚባል ሰው የመለሰለት;; ኒቆዲሞስም ግራ ገባው;; እውቀት ማነስ ችግር ነበርና ያደረገው ነገር ምንድን ነው??? ጥያቄን ጠየቀ;;

ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል??? ዳግመኛ ከእናቱ ማህጸን ገብቶ መወለድ ይችላልን??????? ኒቆዲሞስ የጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛና ተገቢ ነው;;

ጌታችን ሲመልስለት እንዲህ አለ;;

ሰው ከመንፈስ እና ከውሀ ካልተወለደ በቀር የእግዚያብሄርን መንግስት ሊወርስ አይችልም አለው;; ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው;; ዳግመኛ ልትወለዱ ይገባሀል ስላልኩ አታድንቅ ብሎ መለሰለት;;


ታዲያ ከመንፈስ እና ከዉሀ ካልተወለደ በቀር የእግዚያብሄርን መንግስት ሊወርስ አይችልም ያለው ጌታችን እንዴት ነው???

ቸር ይግጠመን ለሚቀጥለው;;

ቦታው የሚገኘው መጽሀፍ ቅዱስ ላይ የዮሀንስ ወንጌል ምእራፍ 3 ላይ ነው አዲስ ኪዳን ላይ ገጽ 81 ላይ ነው
shebellawiye
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Sat Oct 21, 2006 9:32 pm

የሥላሴዎች ልጆች!

Postby ዘላለማዊ » Tue May 19, 2009 9:49 pm

መቼም ወንጌል ሲነሳ «ከጌታ ኢየሱስ ሌላ» ሊነገርለት፣ ሊተረክለት፣ ሊወደስና ሊመሰገን የሚገባው ማንም የለም። እርግጥ ነው የኦርቶዶክስ ቤተኃይማኖት ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን «ኢየሱስ» የሚለውን የከበረና ቅዱስ ስም ማነሳሳት ጀምረዋል። ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ ጎራ ብዬ ነበር እና እግሬን ለማፍታትና አካባቢዬንም ለመቃኘት በእግሬ ሳዘግም አንድ መዝሙር ጆሬዬ ጥልቅ አለ። በያሬዳዊ ዜማ ውስጥ ኢየሱስ የሚለው ቃል ነበር ወደጆሮዬ መጥቶ የደወለው። ቆም ብዬ ዘማሪዋ የምትለውን ማዳመጥ ያዝኩ፦ ምን ትላለች መሰላችሁ «በአንባ ፈረስ ላይ ሆነህ በጽዮን የታየኽኝ… ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ድረስልኝ»። ሁለት የሚገርሙ ቃላትን ቀለብ አደረግሁ፦ «በጽዮን የታየኽኝ» የሚለውና «ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ» የሚሉት ቃላት። መዝሙር ሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የጎደለው ቢሆንም እነዚህ ሁለት ቃላት በዚህ መዝሙር ውስጥ መገኘታቸው ትልቅ ለውጥ ነበር። ለኦርቶዶክስ ቤተኃይማኖት «ሚካኤልዬ ሺህ በክንፉ፤ ሲህ ባክናፉ፤ ጽዮን እናቴ ማርያም» ከሚል ቅዠት ውጪ ተሰምቶ በማይታወቅበት ሰፈር ይህ መገኘቱ የሚደንቅ ነው።

ይህንን ያነሳሁበት ምክንያት፤ በኦርቶዶክስ ቤተኃይማኖት ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች ያሳረፉት ተጽዕኖ እየጨመረ መሆኑን አስተዋልኩኝ። የዚህ ሲገርመኝ ደግሞ «ማቴቴስ» የሚባል መጽሔት በመጋቢት ወር እትሙ የተዋህዶውን ፓትርያርክ፣ የፕሮቴስታንት ኃይማኖቶች ህብረት ጸሃፊንና የካቶሊኩን የኢትዮጵያ መሪ ፎቶ በውጭ ሽፋኑ ላይ ግጥም አድርጓቸው መጥቷል። ከፎቶው በላይ፦ «ይሳካ ይሆን?» የሚል ጉልህ ጽሁፍ አለ። ምኑ? ብሎ መጠየቅ ተፈጥሮአዊ ነውና… መጽሔቱን የውስጡን ይዘት እንኳን ሳላገላበጥ ዝም ብዬ ገዝቼው ወደቤት ገባሁ። ውስጡ ምን እንዳገኘውሁ ታውቃላችሁ፦ ቃል በቃል ልጥቀስ፦

ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ (በኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ ስኪያጅ) ባቀረቡት ጽሁፍ ላይ ጸረ ህብረት ያሏቸውን አራት ተግባራት አቅርበዋል። እነዚህም፦ የአብያተ ክርስቲያናት መነቃቀፍ፣ የሌላውን አማንያን ማስኮብለል፣ ብልሹ ስነምግባርን መደገፍ እና አለመግባባት ሲፈጠር ኃይልን እንደ መፍትሄ መውሰድ የተሰኙ ናቸው

ከፕሮቴስታንቱ ወገን የሆኑት ፓስተር ዶ/ር ስለሺ ከበደ ደግሞ፦ የክርስቶስ ወንጌል በትክክል ገብቷቸው ለደቀመዝሙርነት ሕይወታቸው እዛው [በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን] መሆን የፈለጉ አማኞች ካሉ ልንፈቅድላቸው ይገባል።… በዚያ [በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን] ያሉትም ለደቀመዝሙርነት ህይወታቸው የወንጌላውያን ቤተክርስቲያን የሚመቻቸው ከሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ባርካ ልትሸኛቸው ይገባል።

በነገራችን ላይ ይህ ስብሰባ የተጠራው በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ «ማቴቴስ» መጽሔት ገልጧል።

እነዚህ ቤተኃይማኖቶች አንዱ «መናፍቃን» ሲል፤ ሌላው ደግሞ «አህዛብ» ብሎ አጸፋውን እየመለሰ ሲወጋገዙና ሲናቆሩ የኖሩ ናቸው። የትምህርት ልዩነታቸውን እንዴት ያቻችሉት ይሆን? አሁንም ቢሆን ገመድ ጉተታው እንደቀጠለ ነው። ግን ይህንን አይነት ህብረት እውን የክርስቶስ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሊፈጽሙት የሚገባቸው ነውን? ሆኖም ሁለቱንም የሚያስማማቸው ነገር አለ፦ «ሁሉም ሶስት አምላኮች ነው የሚያመልኩት፤ ስሙም ሥላሴ ይባላል»። አምላኮቻቸው መስማማት አይችሉም፣ አማኞቻቸውን ያስማሙዋቸው ይሆንን? ቆይተን እንመለከተዋለን።
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
ዘላለማዊ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Mon Aug 16, 2004 12:03 pm
Location: ethiopia

Re: የሥላሴዎች ልጆች!

Postby ብርኃናዊት » Tue May 19, 2009 10:01 pm

ዘላለማዊ wrote: እርግጥ ነው የኦርቶዶክስ ቤተኃይማኖት ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን «ኢየሱስ» የሚለውን የከበረና ቅዱስ ስም ማነሳሳት ጀምረዋል።


:lol: ዘላለማዊ በሕይወት ዘመንህ እንደዛሬ ቀልደህ አታውቅም::

ከምር!
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ex-protestant » Wed May 20, 2009 3:56 am

እህታችን ብርሀናዊት ዘላለማዊ እኮ "እየሱስን" የሚጠራው እንደዚህ ነው
http://www.youtube.com/watch?v=fmdVyg9Noyw

እውነት ግን ጸበል ሲጠመቁ የሚጮሁት ባለዛሮች እና እነዚህ በጣም አይመሳሰሉም ? ምን መመሳሰል ብቻ አንድ ናቸው እንጂ
ex-protestant
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Tue May 19, 2009 12:46 am

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 4 guests