ኦርቶዶክስ ቄስ ወደ ኢስላም ተቀየረ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby አሉ-ኡላ » Thu Nov 29, 2012 12:38 pm

ሰላም ወልድያ

ቃል በገባሁት መሰረት የኢየሱስን መወለድ በተመለከተ አስቀድመው ተነግረው የነበሩትን ትንቢቶች ላሳይህ::

የምጽፈውን በሙሉ በጥሞና እንደምታነብ አምናለሁ:: መቀበል ያለመቀበል ሌላ ነው:: ነግር ግን ትኩረት ሰጥተህ እንደምታነበው እተማመናለሁ::
ቁርአን ኢየሱስን ያለ ወንድ ግንኙነት በተአምር እንደተወለደ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ተአምራትን ማለትም በሽተኞችንና አካለ ስንኩላንን እንደፈወሰ የሞቱትን ወደ ህይወት እንደመለሰ ያምናል::
እንግዲህ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር አምላክ ሰዎችን ከፈጠረ ቡሃላ የሚባዙበትን ህግና ስርአት አውጥቶ በዚያ መሰረት ሰዎች አሁንም ድረስ ይባዛሉ:: አንድ ልጅ ለመወለድ የወንድና የሴት ጾታዊ ግንኙነት የግድ ነው:: በርግጥ ባሁኑ ወቅት ከማህጸን ውጪ የሚደረግ እርግዝና አለ:: ያም ቢሆን ከወንዱ የወጣ ዘርንና ከሴቲቱ የተገኘ እንቁላልን በማገናኘት የሚደረግ ነው:: ይህም ቢሆን የተፈጥሮ ህግን የተከተለ ነው:: ያ ማለት የወንድ ዘርና የሴት እንቁላል መገናኘት የግድ ነው ከዚህ ውጪ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁንም ያልተደረ ነገር ነው::
አምላክ ይህን የተፈጥሮ ህግ ሳይከተል በተአምር እንዲወለድ ያደረገውንን እንዲሁም በጣም አስደናቂ የሆኑ ተአምራትን እንዲያደርግ ሃይልን የሰጠውን ኢየሱስን ያለአንዳች አላማ ይልከዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነትና ስህተትም ነው::
አላው ደግሞ ከረጅም ጊዜ በፊት ያሰበው በመሆኑ ይህንን እንደሚያደርግ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በትንቢት ሊያሳውቅ እንደሚችል ማሰብም ጥበብ ነው:: የተለያዩ ሌሎች ከዚህ ያነሰ ትኩረት የሚሰጣቸውን ነገሮች እንኩዋን በትንቢት አሳውቆአል:: በመሆኑም ኢየሱስንም በተመለከተ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የሚሆኑትን ሁኔታዎች በሙሉ በትንቢት አሳውቆአል::

በርግጥ መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ከመጀመሪያው ጀምሮ ኢየሱስን በተመለከተ ትንቢት ተነግሮ የነበረ ቢሆንም በጣም ግልጽ የሆኑትንና አንተ በቀላሉ ትረዳቸዋለህ የምላቸውን ዋና ዋና የሆኑትን የተወሰኑትን አሳይሃለሁ::

ካለ ወንድ ግንኙነት ድንግል ከሆነች ሴት እንደሚወለድ የሚያመለክተው ትንቢት

ኢሳያስ 7: 14
… ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች …
ከማቴዎስ 1: 22 ጋር አወዳድረው::

አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ማንም ሰው ያለወንድና ሴት ጾታ ግንኙነት የተወለደ ከኢየሱስ በስተቀር ማንም የለም::

የት ቦታ እንደሚወለድ
ሚክያስ 5: 2
አንቺ ቤተ ልሄም ኤፍራታ ሆይ … አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል/
ከማቴዎስ 1፣ 5 እና 6 ጋር አወዳድረው

የምስራች እንደሚሰብክና እንደሚያስተምር በሽተኞችን እንደሚፈውስና ብዙዎችን እንደሚያጽናና

ኢሳያስ 61: 1 – 3
የጌታ ዬግዚአብሄር መንፈስ በኔ ላይ ነው ለድሆች የምስራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሄር ቀብቶኛል
የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ … በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት በሃዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጎናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል::
ከሉቃስ 4: 17 – 19 ጋር አወዳድረው::

መስዋእታዊ ሞት እንደሚሞት ዘሚያመለክተው ትንቢት
ኢሳያስ 53: 4 - 12

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ህማማችንንም ተቀብሎአል ...
ተጨነቀ ተሰቃየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም ...
ነፍሱን ስለ ሃጢአት መስዋዕት ካደረገ ቡሃላ ዘሩን ያያል ...
ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና ከአመጸኞችም ጋር ተቆጥሮአልና
እርሱ የብዙዎችን ሃጢአት ተቸከመ::

ከሃዋሪያት ስራ 8: 32 እና 33 ጋር አወዳድረው

በተጨማሪም መቼ እንደሚሞት የሚገልጸው ትንቢት
ዳንኤል 9: 25 እና 26
ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳለምን መጠገንና መስራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከአለቃው እስከ መሲህ ድረስ ሰባት ሱባኤና ስድሳ ሁለት ሱባኤ ይሆናል:: ...
ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም ቡሃላ መሲህ ይገደላል:: ...

መሲህ የግሪክኛው ትርጉም ክርስቶስ ማለት ሲሆን በአማርኛ የተቀባ ማለት ነው::
ይህም ለአንድ ከፍተኛ ስልጣን ወይም ለንግስና መታጨትን ወይም መሾምን የሚምያለለክት ነው::

1ሳሙኤል ቀዳማዊ 10: 1
ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው:: ሳመውም እንዲህም አለው:-
በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሄር ቀብቶሃል:

1ሳሙኤል ቀዳማዊ 16፣ 1 እና 13
... በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ በልጆቹ መካከል ንጉስ አዘጋጅቻለሁ ...
እግዚአብሄርም ይህ ነውና ተነስተህ ቅባው አለ ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ...እነዚህና ለሎችም በርካታ ትንቢቶችን አስቀድሞ እንዲነገሩ በማድረግና ልክ በወሰነው ሰአት ትንቢቶቹ ሁሉ እንዲፈጸሙ አድርጎአል::

ነገር ግን ሙስሊሞች መጽሃፍ ቅዱስን ተበርዞአል በሚል ምክንያታዊነት በጎደለው ሰበብ እንዳይመለከቱት እንቅፋት ሆኖባቸዋል::
ተበርዞአል ለማለት የሚያስችል ምክንያት እንደማይኖርና እንደሌለም እንዲሁም ተበርዞአል የሚለው አባባል ከእውነታው ውጪ እንደሆነ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ በቀጣዩ ለማሳየት እሞክራለሁ::

እቀጥላለሁ::
አመሰግናለሁ::
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby አሉ-ኡላ » Mon Dec 10, 2012 11:57 am

ሰላም በድጋሚ ወልድያ
እየተከታተልከኝ ነው ብዬ ስለማስብ ለመቀጠል ያሰብኩትን እቀጥላለሁ::

ስለ ኢየሱስ መወለድ የተጻፈውን የትንቢት ቃል በተመለከተ የጻፍኩትን እንዳየኸው እርግጠኛ በመሆን ባልኩት መሰረት መጽሃፍ ቅዱስ ተበርዞአል ሊባል የማይችልበትን ምክንያቶች አቀርባለሁ::

እውነት እንነጋገር ከተባለ ሙስሊሞች ከበላዮቻቸው የሙስሊም ሊቃውንት መጽሃፍ ቅዱስ ተበርዞአል ተብሎ የተነገራቸውን እንዲሁ በጭፍን አምነው ይቀበሉታል እንጂ አንዳቸውም መበረዙን ያረጋገጡበት መንገድ የለም:: ሊቃውንቱም ቢሆኑ ቁርአንን ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር ሲያስተያዩት ተመሳሳይ ታሪኮች ቢኖሩም ባብዛኛው የማይስማማና የሚጋጭ በመሆኑ ብቻ ቁርአንን እንደትክክለኛ በመቁጠር መጽሃፍ ቅዱስን በደፈናው ተበርዞአል ብለው በመወሰን ይመስላል ድምዳሜ ላይ የደረሱት::
ኦሪጅናሉ መጽሃፍ የአምላክ ቃል ሲሆን አሁን ያለው ግን ሰዎች በርዘውታል በመሆኑም የአምላክ ቃል አይደለም ብለው ሁሉም ሙስሊሞች ማለት ይቻላል ይህንን ያምናሉ::

በመሰረቱ ተበርዞአል ብሎ በእርግጠኝነት ለመናገር የሚችለው ሁለቱንም ማለትም ኦሪጅናል የሆነውንና ተበርዞአል የተባለውን መጽሃፍት በሚገባ ያየውና ያነበበው ሰው ነው:: አንድ ሰው ኦሪጅናሉን ሳያይና በሚገባ ሳያነብ ኮፒውን ተበርዞአል ከኦሪጅናሉ ጋር አንድ አይደለም ለማለት የሚያበቃ ምንም ምክንያት የለውም::

ብሉይ ኪዳን የተባለው ኦሪትን መዝሙራትንና ነቢያትን የያዘው መጽሃፍ ሙሉ በሙሉ የአይሁዳውያንን ጉዳይ ብቻ የያዘ መጽሃፍ ባይሆንም በመጀመሪያ በአይሁዳውያን የተጻፈና ለአይሁዳውያን ተሰጥቶ የነበረ መጽሃፍ ነው:: ነገር ግን አይሁዳውያን ታማኝ ባለመሆናቸው ምክንያት አምላክ ሲተዋቸው ጥፋተኛ የሆኑት ሰዎቹ እንጂ ቃሉ ባለመሆኑ ቃሉ ታማኝና እውነተኛ እንደሆነ ይቀጥላል::
አምላክ አይሁዳውያንን ትቶ ከክርስቲያኖች ጋር ግንኙነቱን ሲመሰርት ክርስቲያኖች ከአይሁዳውያን ጋር በአምልኮ ባይተባበሩም ቃሉን ግን ሙሉ በሙሉ ይቀበሉታል ኢየሱስም ቢሆን ሲያስተምር የነበረው ከዚያው አይሁዶች ይዘውት ከነበረው መጽሃፍ በመመሰረት ሲሆን ሃዋሪያቱም ቢሆኑ ያንኑ የኢየሱስን መንገድ ነበር የተከተሉት:: በዚህ ምክንያት ነው ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን ፈጽሞ የማይጋጩት::
ቁርአን የአምላክ ቃል ነው ከተባለ ከሌሎቹ የአምላክ ቃል ከተባሉት መጻህፍት ጋር ማለትም ቁርአን ተውራት (ኦሪት) ዘቡር (መዝሙር) ኢንጂል (ወንጌል) ከሚላቸው መጻህፍት ጋር መስማማት ሲኖርበት የሆነው ግን ተቃራኒው ነው:: ይባስ ብሎም ሙስሊሞች በጠላትነት አይን እንዲመለከቱት መደረጉ ነው::

እንዲያው እስቲ ተበርዞአል ብለን ብናስብ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚነሱትን ጥያቄዎም መመለስ ይኖርብናል::

መጽሃፍ ቅዱስ ሁለት ክፍሎች ያሉት መጽሃፍ ነው:: ብሉይና አዲስ ኪዳን የሚባሉት::
ሁለቱም ባንድ ወቅት ተበረዙ ወይስ በተለያየ ወቅት?
ተበርዞአል ከተባለ ብሉይ ኪዳንን የበረዘው ማን ነው?
የተበረዘው በግለሰብ ነው ወይስ በቡድን?
አይሁዳውያን በጠቅላላው ናቸው የበረዙት? ወይስ የተወሰኑ ሰዎች?

መጽሃፍ ቅዱስ አንድ መጽሃፍ ሳይሆን የበርካታ መጽሃፍቶች ስብስብ ነው:: የተጻፈውም በተለያየው ወቅት ነው:: አይሁዳውያን ኦሪጅናሉ ከተጻፈ ቡሃላ በተለይ ነገስታቱ የየራሳቸው ኮፒ እንዲኖራቸው ህጉ ያዝ ስለነበር ከያንዳንዱ ኦርጂናል በተጨማሪ በርካታ ኮፒዎች ነበሩዋቸው:: ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት በየምኩራቦቻቸው ውስጥ ኮፒዎች ስለነበሩ ኢየሱስም በተለያየ አጋጣሚ በምኩራን ሲገኝ ያነብ የነበረው ከነዚህ ኮፒዎች ውስጥ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም:: በዚያ ላይ ሁሉም በተናጠል በጥቅልል መልክ እንጂ እንዳሁኑ ባንድ ጥራዝ አልተዘጋጁም ነበር::

የአይሁዳውያን ምኩራቦች በመላው እስራኤል እና ከእስራኤል ውጪ በሶርያ በግብጽ በኢጣሊያ እና በለሎችም አገሮች በርካታ ከተሞች ውስጥ የነበሩ በመሆናቸው ምን ያህል በርካታ ኮፒዎች እንደሚኖሩ መገመት ይቻላል::

እንግዲህ ወደ አበራረዙ ሁኔታ እንምጣ:: ኦሪጅናል የተባለው በቀጥታ በሙሴ የተጻፈው ተውራት(ኦሪት) በዳውድ (ዳዊት) እናም ነቢያቶች በቀጥታ የጻፉትን ነው::
እናም የተበረዘው ከነሱ ቡሃላ ወዲያው ነው ወይስ ምን ያህል ቆይቶ?
ወዲያው ከሆነ ለረጂም አመታት አይሁዳውያን በተበረዘውና በተሳሳተው መጻህፍቶቻቸው እየተመሩ ከአምላክ ጋር ግንኙነታቸውን ቀጥለዋል ማለት ነው::
በጣም ብዙ ቆይቶ ከሆነ ደግሞ ከኦሪጅናሉ ቡሃላ በርካታ እውነተኛ ኮፒዎች ከተዘጋጁ ቡሃላ በመሆኑ እነዚህን በርካታ ኮፒዎች ማን አጠፋቸው? እንዴትስ ሊጠፉ ቻሉ?

ወይም በራዡ ግለሰብም ሆነ ቡድን እነዚህን ሁሉ ነው እየተዘዋወረ የበረዛቸው ወይንስ የራሱን አንድ ሌላ መጽሃፍ ጽፎ አቀረበና ሌሎቹን አሳምኖ ሁሉም የኦሪጅናል ትክክለኛ ኮፒዎች የተባሉትን ባንድ ላይ ሆነው አጠፉት??

ቁርአን ኢንጂል ብሎ የሚጠራው ወንጌል አንድ መጽሃፍ ሳይሆን ወንጌሎች አራት መጻህፍት ሲሆኑ ለሎቹ ደግሞ የሃዋሪያት ስራንና መልእክቶቻቸውን የሚያጠቃልል ነው::
የተጻፉትም በተለያዩ ሰዎችና በተለያዩ ጊዜያት ነው::

የወንጌል በራዦች ክርስቲያኖች ራሳቸው ናቸው ወይስ አይሁዳውያን ወይም ደግሞ ሌሎች?
ወንጌል በክርስቲያኖች ተበርዞአል ከተባለስ የተበረዘው ከአይሁዳውያን ጋር በመመካከር ካልሆነ በስተቀር ተበርዞአል ከተባለው ብሉይ ኪዳን ጋር እንዴት ሊመሳሰል ቻለ??
ይህንን ሴራስ አምላክ እያየ እንዴት ዝም ሊል ቻለ??
ለሎችም ለሎችም ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ::

ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱስ በፍጹም እንዳልተበረዘም ሆነ የኦሪጅናሉ ኮፒዎች በሌላ ሃሰተኛ ኮፒ እንዳልተዘጋጁ ሊያሳይ የሚችል በማስረጃ የተደገፈ ሃሳቤን በሚቀጥለው አቀርባለሁ::

አመሰግናለሁ::
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby አሉ-ኡላ » Thu Jan 03, 2013 10:09 pm

ወልድያ አለህ ብዬ ስለማምን ሰላምታዬ ይድረስህ

የጀመርኩትን መጨረስ እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ነው መጻፌን የምቀጥለው::

ቀደም ብዬ ገልጬው እንደነበረ የሙስሊም ሊቃውንት ካለምንም ማስረጃ መጽሃፍ ቅዱስን ተበርዞአል በማለት ለአማኞቻቸው ያስተማሩትን መላው ሙስሊም በጭፍን በመቀበል በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ በጠላትነት እንዲነሱ ምክንያት ሆኖአል::

አዎ መጽሃፍ ቅዱስ ተበርዞአል ለማለት የሚያስችል ምንም አይነት ማስረጃ የለም::

በመጀመሪያ ነገር መጽሃፉን ለመበረዝ የሚያበቃ ምክንያት መኖር አለበት:: ሃይማኖትን ለመለወጥ ከሆነ መጽሃፉን አሁን ባለው ይዘት ሳይሆን ጨርሶውኑ ሌላ አዲስ የህግና መመሪያ መጽሃፍ ማዘጋጀትና አዲስ ሃማኖት መመስረት ይሆን ነበር:: ልክ እንደ ኢስላም ማለት ነው::

ለመበረዝ የሚያነሳሳቸው ምክንያት ምንድነው??
አንድ ሰው ወይም አንድ አካል አንድን እርሱን የሚመለከተውን ታሪክ ለመበረዝ የሚያነሳሳው ስለሱ የተጻፉ ስሙን የሚያጎድፉ መረጃዎችን ለማጥፋትና የታሪኩን ይዘት ሳይለውጥ የራሱን መልካም ስሞች አድሶ በሌሎች ጥሩ ጥሩ ቃላት ለመተካትና ራሱ የሚፈልጋቸውን መረጃዎች ለሌሎች ለማስተላለፍ ሲል ነው::

የመጀመሪያውን የኦሪት መጻህፍትን የጻፈው ሙሴ ነው:: ሙሴ አምላክን በቀናነት የሚያገለግል ነቢይ ቢሆንም እንደማንኛችንም አይነት ሰው ስለሆነና ስህተት ሊሰራ የሚችል በመሆኑ እስራኤላውያንን በሲና በረሃ እየመራ ባለበት ወቅት ስህተት ሰርቶ ነበር:: በዚያ ስህተት የተነሳ አምላክ ተቆጥቶትም ነበር:: በመሆኑም ለህዝቡ የሚያወርሰውን የተስፋይቱን ምድር በሩቅ ሆኖ እንደሚያይ እንጂ እንደማይገባ አምላክ በቅጣት መልክ ነግሮታል::
ሙሴ በታማኝነት ይህንን ስህተቱን ግልጽ በሆነ ሁኔታ ጽፎ አስተላልፎአል::

ሌላው አሮንንና እስራኤላውያንን የሚመለከት ነው:: ሙሴ በተራራው ላይ በቆየበት ወቅት እስራኤላውያን አሮንን የወርቅ ጥጃ እንዲሰራላቸው በመጠየቅ ካሰሩ ቡሃላ ከግብጽ ያወጣቸው ያ የወርቅ ጥጃ እንደሆነ በመቁጠር ሲያመልኩትና ሲሰግዱለት እንደነበርና በዚህም ምክንያት አምላክ ተቆጥቶ በርካታ እስራኤላውያንን በሞት እንደቀጣቸው ቁልጭ ባለ ሁኔታ ተጽፎአል::
በመጀመሪያ የጸሃፊው ታማኝነትን እናያለን:: የራሱንና የሕዝቡን ስህተት እንኩዋን ሳይደብቅ መጻፉን::
ሌላው ደግሞ ከረጅም ጊዜ ቡሃላም አይሁዳውያን የእምነታቸው መስራችና የአምላክ ታላቅ ነቢይ አድርገው የሚያዩት ሙሴ የሰራውን ስህተትና አባቶቻቸው በበረሃ ውስጥ በተደጋጋሚ የሰሩትን ስህተቶች ማውጣትና በሌላ ቃላት መተካት ይኖርባቸው ነበር:: ታድያ በራዡ ወይም በራዦቹ ይህንን በምን ምክንያት ተውት?? መልስ የለም

በተስፋይቱም ምድር ከገቡ ቡሃላም በመንግስትነት ከተመሰረቱና ነገስታቶቻቸው መግዛት ከጀመሩም ቡሃላ በተደጋጋሚ ከባድ የሆኑ አምላክን የሚያስቆጡ ሃጢአቶችን በመስራት አምላክን ያሳዘኑበት ወቅት ነበር::
እንደምሳሌ ያህል ኤርምያስ በነበረበት ወቅት ከጥቂቶች አምላክን በቅንነት ከሚያገለግሉ አይሁዳውያን በቀር መላው እስራኤል ንጉሱን ጨምሮ በክፉ ድርጊታቸው አምላክን ያሳዘኑበት ወቅት ነበር:: በመሆኑም ኤርሚያስ በተደጋጋሚ የህዝቡንም ሆነ የንጉሱን ስህተት በግልጽ ይናገር ነበር:: ኤርሚያስ ብዙ መከራ ቢደርስበትም በታማኝነት ተልእኮውን ተወጥቶታል:: በመሆኑም አምላክን ሳይሰሙ በመቅረታቸው አምላክ ለባቢሎናውያን አሳልፎ በመስጠት አገሪቱ እንድትጠፋና የሚኮሩበት ቤተመቅደስ እንዲቃጠል የተረፈውም ህዝብ በምርኮ ወደ ባቢሎን እንዲጋዝ አድርጎአል::

ያ ድርጊት ለእስራኤላውያን አሳፋሪ ታሪክ ነው:: በራዡ ወይም በራዦቹ አይሁዳዊያን ይህንንና ሌሎቹንም የአይሁዳውያንን ክፉ ድርጊቶች የሚገልጹትን ታሪኮች በምን ምክንያት ሳይበርዙትና በሌላ ጥሩ ቃላት ሳይተኩት ቀሩ?? አሁንም መልስ የለም

በአይሁዳውያን በራዦች ተበርዞ ቢሆን ኖሮ እነዚህን ክፉ ድርጊታቸውን የሚገልጹትን ታሪኮች እንዳሉ አይቆዩንም ነበር::

አይሁዳውያን በብሄር ደረጃ ኢየሱስን በአምላክ ተልኮ እንደመጣ ወይም እንደመሲህ አድርገው አልተቀበሉትም:: ኢየሱስ ግን እርሱ ይመጣል የተባለው መሲህ ራሱ እንደሆነ ትንቢቱን ራሳቸው ይዘውት ከነበረው መጽሃፍ እየጠቀሰ ያሳያቸው ነበር::
ያ ማለት በወቅቱ ብረዛ እንደአልተካሄደበትና ከዛም ቡሃላ ያው ቃል እስካሁንም ስላለ እንዳልተበረዘ ያሳያል::

ሌላው አኪዎሎጆያዊ ግኝቶች ናቸው::
በተለያዩ ቦታዎች በቁፋሮ በተገኙ እጅግ ጥንታዊ በሆኑ የሸክላ ገበታዎች ላይ፣ በጥንታዊ የቤተመንግስት ፍርስራሾች ግድግዳዎች ላይ በጽሁፍ ተቀርጸው የተገኙ መረጃዎች ካሁኑ መጽሃፍ ቅዱስ ጋር ተመሳሳይ መሆናቸው ነው:: በተለይም በጥንቱዋ ፐርሺያ ባሁኑዋ ኢራን የተገኘው የቂሮስ ሲሊንደር ተብሎ በሚታወቀው ላይ ተቀርጸው የተጻፉት ጽሁፎች በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ተጽፎ ካለው ታሪክ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ መሆኑ አንዱ ማስረጃ ነው:: ያ የሲሊንደርና ሌሎቹም የሸክላ ላይ ጽሁፎች በአምላክ አገልጋይ በሆኑት አይሁዶች የተጻፈ ሳይሆን አምላክን በማያገለግሉ እንዲያውም በአምላክ ሕዝብ ጠላቶች የተጻፈ ነው::

በተጨማሪም ሙት ባህር አካባቢ ኩምራን በተባለ ዋሻ ውስጥ ተቀብረው የተገኙት ጥቅልሎች ከክርስቶስ ልደት ሁለት መቶ አመታት ቀደም ብለው እንደተጻፉ የሚገመቱ ናቸው::
በተለይ የኢሳያስ መጽሃፍ ሙሉው ነው የተገኘው በመሆኑም ካሁኑ ጋር ያንዳንድ ቃላትና የስራተ ነጥብ ልዩነት ካልሆነ በቀር ዝርዝሩ ያው ነው::
ሌሎችም ጥንታዊ ጥቅልሎች እንዲሁ ተገኝተዋል ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው::

አዎ እነዚህ ሁኔታዎች ፈጽሞ መጽሃፍ ቅዱስ እንዳለተበረዘ የሚያሳዩ ቢሆንም በሌላ በኩል ግን ጠቅላላውን መጽሃፍ ቅዱስን ለማጥፋት ተደጋጋሚ ሙከራዎች ከመደረጋቸውም በላይ በርካታ ኮፒዎች ባደባባይ እንዲቃጠሉ ተደርገዋል:: ያም ሆኖ ግን እስካሁን በጽናት በመቆየት በመላው አለም ተወዳዳሪ በማይገኝለት ሁኔታ ሊሰራጭ ችሎአል::

መጽሃፍ ቅዱስ ተበርዞአል የሚለው አባባል ግን መጽሃፉን ለማጥፋት ከተደረገው ሙከራ በተጨማሪ ስሙን ለማጉደፍ የተደረገ ሴራ ነው::
ሰዎች ያን ቢሉትም እውነተኛነቱ ግን ይቀጥላል::

በመሃል ይህን ብናነሳም የጀመርነውና እኔም በሱ ላይ ሃሳብ መስጠት የጀመርኩት ሌላ ርዕስ ስላለ ወደሱ እመለሳለሁ::

አመሰግናለሁ
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby ወልድያ » Tue Jan 08, 2013 9:21 am

ሰላም አሉ ኡላ የክረምቱ ቅዝቃዜ እንዴት ይዞሀል ?

ግዜ በጣም የሚወስድ ስራ ስላለብኝ እንደልብ ለመወያየት አልቻልኩም ሆኖም አልፎ አልፎ ምላሾችህን አያለው በጥልቀት ለማብራራት የምታደርገውን ጥረት አደንቃለው

አንድ ነገር አንዱን እያስነሳ ጭብጦቹ እየሰፉብን የሄዱ ይመስለኛል

እንግዲህ ካንተ ጋር በተውያየሁበት ብዙ ከተግባባንባቸው ነጥቦች በተጨማሪ ካንተ እምነት የተረዳህዋቸው የእምነትህ core ነገሮች

. አምላክ መጀመርያ የፈጠረው እየሱስን መሆኑን የተቀሩትን ፍጥረታት ከእየሱስ ጋር በመተጋገዝ መፍጠሩን

.አዳም አትብላ ከተባለው ዛፍ በመብላቱ ሞትን በአዳም ዘር ላይ ማምጣቱን

.አምላክ የገደለ ይገደላል የሚለውን የራሱን ህግ ላለመጣረስ ሞትን ለማስቀረት እየሱስ እንዲገደል ማድረጉን በእየሱስ ሞት ምክንያትም በአዳም የመጣብን ሞት መድህን መሆኑን

.በዚህ መስዋእት ያመነ የዘላለም ህይወት ሲያገኝ ያላመነ ደግሞ የዘላለም ሞት እጣው እንደሚሆን አምላክ ሰውን ፈጽሞ በገሀነም እሳት እንደማይቀጣ ...

.የእየሱስ መወለድና መስዋእት መሆን በቀደምት መጻህፍት ላይ መገለጹ ለመጽሀፍ ቅዱስ እውነተኛ የአምላክ ቃልነትና ለእየሱስ መስዋእትነት ምስክር መሆኑን ..

እነዚህንም ነጥቦች በተለያየ ማስረጃዎች ለመደገፍ ምክረሀል

ለምሳሌ እየሱስ መጀመርያ ለመፈጠሩ " ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩ እኔ አለሁ ...' የሚል ... ሆኖም ይህ የተባለው ለእየሱስ መሆኑን ወይንም እየሱስ ይህን ማለቱን በምን እናውቃለን አምላክ መጽሀፍ መጀመርያ ላይ አምላክ በአጭሩ በመጀመርያ እየሱስን ፈጠረ እንዲሁም እንዴት እንደፈጠረው መግለጽ አይችልምን ? ይህ ቀድሞ የሆነ ክስተት ከሆነ በኢሳያስ ትንቢት ወዘተ የተለያዩ hint ከዛም ከዚም በማጋጠም ሊደረስበት የሚገባ ነገር መሆን ነበረበት ? የመጀመርያ ፍጥረት እየሱስ ነው የማያሻማ አንድ አረፍተ ነገር .. ከሁሉም ቅድምያ የተከሰተ ነገር እንደመሆኑን መጽሀፉ ላይም የመጀመርያ ክስተት ተደርጎ መወሳት ያለበት ድርጊት ነው እንዲሁም ሰማይና ምድርን በውስጥዋ ያለውንም ሲፈጥር የእየሱስ እገዛ እንደነበረበት አንድም ቦታ ላይ አይገልጽም እንድያውም አምላክ በመጽሀፍ ቅዱሱ ሰማይና ምድርን ስፈጥር ከኔ ጋር ማን ነበረ ? ሲል ሀያልነቱን ሲገልጽ ነው የምናየው.. አንተ ሲጀምር እየሱስ ተራ ሰው ባይሆንም አምላክ አይደለም ብለሀል ሆኖም በፍጥረተ አለም ላይ ድርሻ ከነበረው አምላካዊ ባህሪ አይደለምን ?

አዳም ተእዛዝን በመተላለፉ ሞትን አመጣ አዳም ከተፈጠረ በሰባት ሺ አመታት ብቻ ይህች ምድር ከአጽናፍ እስከአጽናፍ አትላንቲክን ተሻግሮ ፓሲፊክና ተሻግሮ የተለያየ ቀለም ጂኦግራፊ ባህል ቅዋንቅዋ ባላቸው ሰዎች ተወረረች ለማለት አስቸጋሪ መሆኑ ባይታበልም እነዚህ ሁሉ ህልቆ መሳፍርት ሰዎች በአዳም ጥፋት ተያዥ የሚሆኑበት ነገር ሎጂካል አይደለም ከፍትሀዊ አምላክም አይጠበቅም ሆኖም ፍትሀዊው አምላክ ልጅ በአባት ስራ አይጠየቅም ይላል እዝቄል 18 ላይ እንወያይ እስቲ በዚህ ጉዳይ ግልጽ መመርያ ይመስለኛልና

አምላክ ህግ አለው የገደለ ይገደላል እርግጥ ነው ግን የሚገደለው የገደለ ነው የገደለ ሰው ዘመዶች አይገደሉም አዳም አልተገደለም የመጀመርያው የተገደለ ሰው አቤል ነው ቃኤል አቤልን ስለገደለ በዚህ የአምላክ ህግ መሰረት መገደል ነበረበት ሆኖም እየሱስ ማንንም አልገደለም ስለዚህ የሚገደልበት አምላካዊ ህግም ሆነ ሰብአዊ ህግ የለም ምክንያቱም በአዳም ሞት ላይም ሆነ በአዳም ሀጥያት ላይ ምንም ተሳትፎ አልነበረውም

እየሱስ አስቀድሞ የተፈጠረ ፍጡር ከነበረ እንደአዳም ምድር ላይ መገኘት (መከሰት ነበረበት እንጂ በድጋሚ መጸነስ በማህጸን መቆየት መወለድ ማደግ... ነበረበትን ?

እየሱስ በሞቱ አዳም በሰው ልጅ ላይ ያመጣውን ሞት ከፈለ ካልን ከእየሱስ መስዋእትነት በፊት የነበሩ ሰዎችና ከዛ በህዋላ የተፈጠሩ ሰዎች ጀነቲክስ ላይም ሆነ ባህሪ ላይ የመጣ ለውጥ አለ ወይ ? ማለትም በእየሱስ ሞት ምክንያት በሰው ልጆች ላይ የታየው ተጨባጭ ገሀዳዊ ለውጥ ምንድነው ? ስለእየሱስ መስዋእት ያልሰሙ ሆኖም በሙሴ ያመኑ በአብርሀም ያመኑ በኖህ ያመኑ ሰዎች እጣ ምንድነው የእየሱስ ሞት እንሱንም ከሞት ነጻ ያደርጋል ባያዩት እና ስለሱ መስዋእት ባይሰሙም ስለዚህም ባያምኑበትም

እየሱስን በሀሰት የከሰሱ እና ገድለዋል የተባሉ ሰዎች አምላክ ፊት ይጠየቁበታል ይቀጡበታል ወይንስ የፈጸሙት ድርጊት አምላክ የሰው ልጅን ከሞት ለማዳን የወሰነው ድርጊት በመሆኑ የሰው ልጅ መድህን ተግባር እንደፈጸሙ ነው የሚቆጠረውና ውሳኔውንም የሚያገኙት በዛው ምልከታ ነው ?

የእየሱስ እራሱ እና መስዋእቱ ታላቅ ክስተቶች ናቸው ትአድያም ትንቢቱ ግልጽ መሆን አልነበረበትም ?

ማርያም ከምትባል ድንግል ሴት በበተልሄም ይወለዳል የተጸውኦ አባቱም ዮሴፍ ይባላል በሀሰት ይከሰሳል ይሰቀላልም በሱም ሞት ምክንያት የሰው ልጆች ይድናሉ ...
እንዲህ ቢገለጽ ስለማን እየተወራ እንደሆነ ግልጽ ነው ከመስዋእትነቱ ግዙፍነት አንጻርም አንደ ብቻ ስይሆን እየተደጋገመ በግልጽ መተንበይ የነበረበት ነገር ነው

ግን ደንግል ትወልዳለች ስሙንም አማኑእል ይሉታል ..የትኛዋ ድንግል የትኛው አማኑእል ? ትንቢቱ ደግሞ እዛ ላይ አልቆመም ይቀጥልና ስለአማኑኤል ያብራራል አማኑኤል ተአምራት ይሰራል የሞተ ያስነሳል ለMጣም ይፈውሳል ..አይልም አማኑኤል ስለሰው ልጅ ይሞታል ይሰቀላል አይልም በግብሩ እንኳን ብንሄድ የተዘረዘሩት የአማኑኤል ግብሮች ከእየሱስ ፍጹም አይገኙም !

መሲህ ይገደላል ስለየትኛው መሲህ ነው እየተወራ ያለው ስለየትኛው መሲህ ነው እየተወራ ያለው እንዴት ተገደለ ለምን ተገደለ ሞትን ድል አድርጎ ስለመነሳቱስ እዛው ላይ ለምን አልተገለጸም ? ኮንተክስኡን ስናየው ስለእየሱስ ያብራራል ? የተቀባ (መሲህ ) እየሱስ ብቻ ነው ነገስታት ይቀቡ አልነበረምን ? ከኢሳያስ ወደሳሙኤል እይህእድን ከማገናኘት ይልቅ ወጥ በሆነ ሁኔታ የተተረከ ስሙን ውልደቱን እድገቱን ሞቱን (ለሰው ልጅ ሀጥያት እንደሚሞት ) ትንሳኤውን ለመግለጽ አንድ ፓራግራፍ ይበቃል ይህ የት ይገኛል ?

እነዚህን ነገሮች አንስተን ገረፍ ገረፍ እንዳደረግን ይሰማናል አሁን አንስቼ ላሰለችህ ሳይሆን ሎጂክን ለግዜው ላልጠቀምበት ብወስን እንኳን ይህ ትምህርት የክርስትና አንኳር ትምርቱ ከሆነ መጽሀፍ ቅዱስ የማያሻማ መረጃ ሊያቀርብባቸው ሲገባ ከዛም ከዚም አንቀጾች ተሰካክተው የተፈለገውን ኢሜጅ እንዲፈጥሩ እንጂ ወሳኝና ወጥ የሆነ ያልተዛባና ከ context ጋር ያልተጋጨ መረጃ የቀረበባቸው ናቸው ብዬ ስላላመንኩ ነው

ግዜዬን ሳገኝ እመለሳለው

.
ወልድያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 497
Joined: Mon May 24, 2010 3:58 pm

Postby አሉ-ኡላ » Sun Jan 13, 2013 9:15 pm

ወልድያ wrote:ሰላም አሉ ኡላ የክረምቱ ቅዝቃዜ እንዴት ይዞሀል ?

ሰላም ሰላም ብያለሁ ወልድያ
የስራ መብዛቱማ እኔምጋ ያው ነው ለመኖር ያው መስራት የግድ ነው
የብርዱን ነገር ግን ተውኝ ክረምት ለኔ ሁሌም አዲስ ነው በረዶውን ብወደውም ቅዝቃዜውን ግን አልወደውም አይስማማኝም
በተረፈ እስካሁን ደህና ነኝ

ወልድያ እነዚህ ከላይ ያነሳሃቸውን ነጥቦች ሁሉ በደንብ የተወያየንባቸው ይመስለኛል እንደገና ወደሁዋላ ተመልሶ ከአንድ መጀመሩ ዋጋ የለውም ሌሎች ምላሽ ያላገኙ የጀመርናቸው ግን አንጠልጥለን የተውናቸው ውይይቶች አሉ

ነገር ግን ላንዳንዶቹ ትንሽ ግልጽ እንዲሆን አንዳንድ ልበል:: ካለኝ የጊዜ እጥረት አንሣር ግን ባጭሩ ሆኖም ግን ግልጽ በሆነ መንገድ ልንገርህ::
እንደገባኝ ስለኢየሱስ ለምን ከመጀመሪያው ግልጽ በሆነ መንገድ ወይም አባባል አልተነገረም ወይም አልተጻፈም የሚል ነው
የመጽሃፍቅዱስ አጻጻፍ ልክ እንደ ፍቅር እስከመቃብር አይነት አጻጻፍ አይደለም የተጻፈው:: ታሪኮች ቁልጭ ባለ መልክ ታሪካቸው ሲጻፍ ትንቢቶች ግን አጻጻፋቸው ለየት ያለ ነው
በነቢያት መጻህፍት ውስጥ ሆነ በኦሪት ኢየሱስ በስም አልተጥቀሰም:: አምላክ አንድ መሲህ እንደሚመጣና ምን ምን ነገሮች እንደሚያከናውን በተለያየ መልኩ አስነግሯል:: በመሰረቱ ከረጂም ጊዜ ቡሃላ የሚፈጸም ትንቢት ሲነገር ትንቢቱን የሚናገረው ሰውም ሆነ በወቅቱ ያሉ ሰዎች ዝርዝር ትርጉሙን አይረዱትም ነበር ያ ለነሱ ምንም ጥቅም አይሰጥም እንደምሳሌ ያህል ነቢዩ ዳንኤል ትንቢቶችን በራእይ ካየ ቡሃላ... ሰማሁም ግን አላስተዋልኩም:: በማለት ከተናገረ ቡሃላ ራእዩን ያሳየውን መልአክ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ሲጠይቀው » የዚያን ጊዜም ጌታየ ሆይ የዚህ ሁሉ ፍጻመ (ትርጉሙ) ምንድነው አልሁ» መልአኩ የመለሰለትን ልብ በል » ቃሉ እስከ ፍጻሜ ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ » ብሎታል ዳንኤል 12: 8, 9 ትርጉሙ ለዳንኤል አስፈላጊ ባለመሆኑ አላብራራለትም ነበር::
እዚሁ ምእራፍ 12 ላይ ከፍ ብሎ በቁጥር 4 ላይ እንዲህ ተብሎ ተነግሮት ነበር »ዳንኤል ሆይ አንተ ግን እስከፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ መጽሃፉንም አትም ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ እውቀትም ይበዛል»
ትንቢቱ ሊፈጸም ሲል ወይም ሲፈጸም ነው ግልጽ የሚሆነው በመሆኑም ስለኢየሱስ በወቅቱ ዝርዝር መግለጫ መስጠት አስፈላጊ አልነበረም:: ኢየሱስ በተወለደበት ወቅት ግን ትንቢቶቹን ተረድተውት እንደነበር ባለፈው ከተወያየንበት መረዳት ትችላለህ ከተወለደና ተልእኮውን ከተወጣ ብሃላ ግን ስለእርሱ ብዩ ነገሮች የበለጠ ግልጽ ሆነዋል
አፈጣጠርን በተመለከተ የተድበሰበሰ ነገር የለውም ...... ሰማይና ምድር ሳፈጠሩ እኔ አለሁ........ የሚል ብቻ አይደለም
ቆላስይስ 1. 15. 17 18 እንዲህ ይላል እርሱ የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው .... ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረትም ሁሉ በፊት በኩር ነው::
በኩር ማለት የመጀመሪያ ማለት ነው የፍጥረቱ ሁሉ በኩር ማለትም የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ ማለት ነው
በተጨማሪ ዕብራውያን 1: 1-3
ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሀር በብዙ አይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም አለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለኛ ተናገረን
አለማትን በሙሉ በልጁ አማካኝነት ፈጥሮአል ማለት ነው ግልጽ ይመስለኛል ቅን ልብ ላለው እነዚህ ለመረዳት አስቸጋሪ አይደሉም

አዎ አምላካዊ ባህሪ አለው:: አምላካዊ ባህሪ ምን ማለት ነው? አምላክ መንፈስ ነው ኢየሱስም መንፈሳዊ አካል ነው ያለው:: በተጨማሪም ኢየሱስ አምላክ ያስተማረውን እና ያዘዘውን ብቻ ስለሚያደርግ እኔን ያየ አብን አየ ማለት ችሎአል ዮሃንስ 14: 9
ይህ ማለት ኢየሱስ ያደርገው የነበረው በሙሉ አብ ሊያደርገው ያለውን በሙሉ በመሆኑ የሚያንጸባርቀው የአባቱን ባህሪ ነበር ማለት ነው እንደዚያ ማለት ግን ሁሉን ቻይ የመሆን አምላክነት ስልጣን አለው ማለት አይደለም

እነዚህን ከዚህ በፊት ከተወያየንበት ጋር አዳምረህ ተመልከተው

ስለአዳም የሃጢአት ሁኔታና ስለየሱስ መስዋእታዊ ሞት ከዚህ በፊት በደንብ ያብራራሁ ይመስለኛል
እንደገና ብትመለከተው ደስ ይለኛል::

አመሰግናለሁ
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby አሉ-ኡላ » Wed Jan 16, 2013 9:28 pm

ወልድያ wrote:ግን ደንግል ትወልዳለች ስሙንም አማኑእል ይሉታል ..የትኛዋ ድንግል የትኛው አማኑእል ? ትንቢቱ ደግሞ እዛ ላይ አልቆመም ይቀጥልና ስለአማኑኤል ያብራራል አማኑኤል ተአምራት ይሰራል የሞተ ያስነሳል ለMጣም ይፈውሳል ..አይልም አማኑኤል ስለሰው ልጅ ይሞታል ይሰቀላል አይልም በግብሩ እንኳን ብንሄድ የተዘረዘሩት የአማኑኤል ግብሮች ከእየሱስ ፍጹም አይገኙም !

.ሰላም ወልድያ
ሳላሰፍራት የቀረች አንድ ሃሳብ እንዳለችህ አሁን ነው ያየሁት
ትንቢትን በተመለከት ከላይ የጠቀስከውን የኢሳያስን ትንቢት እንመልከት::

ድንግል ትጸንሳለች ስሙም አማኑኤል ይባላል የሚለውን ትንቢት አንስተህ የትኛዋ ድንግል የትኛው አማኑኤል ነው?
ምናልባት ያልተረዳኸው አንተ ብቻ ትሆን እንደሆን አላውቅም እንጂ ግልጽ ነው ::
የሰው ዘር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዛሬም ድረስ ድንግል የሆነች ሴት ከወንድ ጋር ያልተገናኘችና የወንድ ዘር በምንም መልኩ ከሴቱዋ እንቁላል ጋር ሳይገናኝ የወለደች ሴት እንዳለች ሰምተህ ታውቃለህ??
በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ ከኢየሱስ እናት ከማርያም በስተቀር እንዲህ ያለውን ተአምራዊ አወላለድ የወለደች ሴት እንዳለች ሰምተህ አታውቅም::
ስለዚህ ያ ትንቢት በሱዋ ላይ እንደተፈጸመ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም አንገትን ካላደነደኑ በስተቀር::
ከመጀመሪያው ማርያም የሚለው ስም ተጠቀሰም አልተጠቀሰ ትንቢቱ ሲፈጸም ግን ማንነቱዋ ቁልጭ ብሎ ይገለጣል::

ስሙም አማኑኤል ይባላል ማለት ምን ማለት ነው?? በመሰረቱ ከመጀመሪያውም የድንግልዋ ሴት የተጸውዖ ስም እንዳልተጠቀሰ ሁሉ የሚወለደውም ልጅ የተጸውዖ ስምም አልተጠቀሰም::
ስም ማለት ምን ማለት ነው?? መጽሃፍ ቅዱስ ስም የሚለውን ቃል በምን መልኩ ነው የሚጠቀምበት?? ይህንን ያልተገነዘብክ ይመስለኛል??

ለምሳሌ ያህል መክብብ 7: 1 እንዲህ ይላል:-
ከመልካም ሽቱ መልካም ስም ... ይሻላል::
መልካም ስም ማለት ምን ማለት ነው?? ከበደ አለማየሁ ታሪኩ አበበ ወዘተ. የትኛው መልካም የትኛው መጥፎ ስም ነው? እነዚህ የተጸውዖ ስሞች ናቸው:: አንድን ሰው ከሌላው የሚለይ የግል መጠሪያ ማለት ነው::
አንድ ሰው መልካም ስም አለው የሚባለው መቼ ነው? የ ሂትለር ስም ሲጠራ ቶሎ ብሎ ባይምሮህ የሚመጣ ያደረገው ስራ ይኖራል:: ሂትለር በብዙዎች ዘንድ መልካም ስም የለውም:: መንግስቱ ሃይለማርያም ሲባልም እንደዚሁ በብዙዎች ዘንድ መልካም ስም የለውም :: አራጅ ጅምላ ጨፍጫፊ .ወዘተ. የሚል ስም ተሰጥቶታል:: ባደረገው ድርጊት የተነሳ ሰዎች የተሰማቸውን የገለጹበት ስም ነው እንጂ የግሉ መጠሪያ ሆኖ አይደለም::
ባንጻሩ መልካም ስም ያተረፉ በርካታ ሰዎችም ይኖራሉ:: መክብብ ላይ ስም የሚለው ቃል የተሰራበት ከዚህ አንጻር ነው:: ሰዎች በሚያደርጉት ወይም በሚሰሩት ስራ የተነሳ የሚሰጣቸው ስም መሆኑ ነው:: በርግጥ የመጽሃፍ ቅዱሱ አባባል ከአምልክ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ነው::

ሌላ አንድ ምሳሌ ልጨምርልህ
እዚያው ኢሳያስ 9: 6 ላይ ያለ አንድ ትንቢት እንዲህ ይላል:-

ሕጻን ተሰጥቶናል ወንድ ልጅም ተወልዶልናል.... ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምልክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል:: ይላል ታድያ ይሄ ሁሉ የልጁ ስም ይመስልሃል?? መቼም ይህ ሁሉ ያንድ ሰው የተጸውዖ ስም ወይም የግል መጠሪያ ስም ነው እንደማትል አምናለሁ:: ይህ ትንቢት የሚያመለክተው የሚወለደው ሰው የሚያደርገውን ድርጊት ወይም የሚያከናውናቸውን ነገሮች ነው::

ወደ አማኑኤልም ስንመጣ ስሙ የተባለውም በሚያከናውነው ድርጊት የተነሳ የሚያተርፈውን ስም ለማመልከት ነው::
ልብ በል ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት ካደረጋቸው ታላላቅ ተአምራት የተነሳ የሆነውን ተመልከት
ሉቃስ 7: 16 እንዲህ ይላል:-
ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸውና ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነስቶአል ደግሞም እግዚአብሄር ሕዝቡን ጎበኘ እያሉ እግዚአብሄርን አመሰገኑ::
አይሁዳውያን አምላክ እንደተዋቸው ተሰምቶአቸው የነበረበት ወቅት ስለነበር ኢየሱስ ባከናወናቸው ተአምራት የተነሳ ሰዎቹ አምላክ እንደጎበኛቸው ማለትም በመካከላቸው እንደሆነ ተሰምቶአቸዋል:: አማኑኤል ማለትም ትርጉሙ እግዚአብሄር ከኛ ጋር ነው ማለት ነው::
አዎ አማኑኤል ይባላል ሲል ኢየሱስ ከሚያደርገው ድርጊት የተነሳ የሚያተርፈውን ስም እንጂ የግል መጠሪያ ስሙን አይደለም::
ስለዚህ ትንቢቱ በመጀመሪያ ድንግል ሴት ሆና የወለደች ማርያም ብቻ ስለሆነ እሶአን ማመልከቱ ግልጽ ሲሆን በድንግልና የወለደችውም ልጅ ኢየሱስ ነው:: ስም ተጠራ አልተጠራ የትንቢቱ ፍጻሜ ከማርያምና ከኢየሱስ ሌላ ለማንም አይሆንም:: ሌላ ማንም ይህን ትንቢት ያሙዋላ የለም::

አመሰግናለሁ
ሰላም ሁን
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby አሉ-ኡላ » Thu Feb 21, 2013 8:42 pm

ሰላም ወልድያ
ዋርካ ለሁሉም ተበላሽቶ የቆየ መሰለኝ መቼም ለኔ ብቻ አይመስለኝም
እንደገና በመስራቱ ደስ ብሎኛል የተጠፋፋን መስሎኝ በጣም አዝኜ ነበር::

የጀመርኩትን ከስራህ ፋታ በምታገኝበት ሰአት ታየዋለህ ስለምል እኔም ባገኘሁት አጋጣሚ የተወሰነች ለመጻፍ እሞክራለሁ::

ከዚያ በፊት ግን ስለክርስቶስ የቤዛዊ መስዋእትነት ሁኔታ ባነሳኸው ጥያቄና በተለይም ልትረዳው ያልቻልክበትን በተመለከተ አንድ ልበል::

ቁርአን አንድ መጽሃፍ ነው የተጻፈውም በ23 አመታት ጊዜ ውስጥ ነው:: ይህ የአንድ የወጣት ሰው እድሜ ነው::
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ የበርካታ መጽሃፎች ስብስብ ሲሆን ጠቅላላው መጻህፍት ተጽፈው ለማለቅ የወሰደበት ጊዜ ወደ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አመታት ያህል ነው:: በዚህ የጊዜ ርዝመት ውስጥ በሙሉ አምላክ ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት እውነተኛው አምላክ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምን አይነት አምላክ መሆኑና ባህሪያቶቹ በሙሉ ግልጽ ብለው ለመታየት የቻሉበት ወቅት ነው::
ሃይሉን ጥበቡንና ችሎታውን በተግባር ያሳየበት
ህጢያተኞችን በደለኞችንና ከትእዛዙ የሚወጡትን በሙሉ የሚቀጣ መሆኑን በተግባር ያሳየበት
ተጸጽተው ይቅርታ የሚለምኑትን ይቅር ባይነቱን ቸርነቱን ሩህሩህነቱን በተግባር ያሳየበት
በተለይም ህዝቦቹን ከያዘበት አያያዝ አንጻር የፍቅር አምላክ መሆኑን የፍትህ አምላክ እንዲሁም ፍርድን የማያዛባና ፍርዱን የሚያስፈጽም አምላክ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ወቅት ነው :: በመሆኑም መጽሃፉ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ግልጽ በሆነ መንገድ ይዞአል::
ከዚህም በተጨማሪ የወደፊቱን ሁኔታ ከረጂም ጊዜ በፊት የሚያውቅ መሆኑንና የተናገረውም ሁሉ የሚፈጸም መሆኑን በተግባርና በጊዜ ሂደቶች ውስጥ አሳይቶአል

ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስረዳት:-
ሃይል ያለው ጥበብ ያለውና ሁሉን አዋቂ አምላክ ለመሆኑ ሃይሉንና ጥበቡን ያሳየባቸውን ጊዘያቶችና ሁኔታዎች ከመጽሃፉ ማግኘኘት ይቻላል
የፍቅር አምላክ ነው መሃሪና ሩህሩህ ነው ለማለት የሚያስችለንን በተግባር የታየባቸውን ጊዘያቶችና ሁኔታዎች በትክክል ለመረዳት በሚያስችል መንገድ መጽሃፉ መረጃዎችን ይዞአል::
በተለይም የፍትህ አምላክ ነው ለማለት የሚያስችለንን ምክንያቶችና ፍትህ በአምላክ ዘንድ ምን ያህል ቦታ እንዳለው የሚያሳይ በተግባር የተገለጹ ድርጊቶችን የሚያሳይ መረጃ ይዞአል
ሌላም ሌላም ...

ስለዚህ የእነዚህን ሁሉ የአምላክን ባህሪያት በተግባር ያላወቀ አንድ ሙስሊም በተለይም አምላክ ስለፍትህ ያለውን አመለካከትና ፍትህ በአምላክ ዘንድ ምን ቦታ እንዳለው ያለተረዳ አንድ ሙስሊም የክርስቶስን የቤዛዊ መስዋእነት አስፈላጊነቱ ጨርሶ ሊገባው አይችልም::

ማንም ቢሆን የቁርአንን ያህል ገጾች ያሉትን አንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ብቻ በማንበብ ስለአምላክ ማንነትም ሆነ ስለባህሪዎቹ ፈጽሞ ምንም ሊረዳ አይችልም:: ሙሉው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ወይም መጻህፍቶች ናቸው ያንን ሁሉ መረጃ የሚሰጡት::

በመሆኑም ላንተም ለመረዳት ቢከብድህ የሚደንቅ አይደለም::

ወደ ሁለተኛው ነጥብ ስመጣ ደግሞ ቀደም ብዬ ጀምሬው ግን እልባት ሳላደርግለት ወደ ቆምኩት ሃሳብ እመጣለሁ::

ቁርአን የአምላክ ቃል ለመሆኑ ማስረጃህ ምንድነው ብዬ የጠየኩህን እኔን መልሰህ ቁርአ የአምላክ ቃል አይደለም የምትልበትን ምክንያት አቅርብ ባልከኝ መሰረት የጀመርኩት ነው::

በአንደኛ ደረጃ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው ብለው ክርስቲያኖች የሚያምኑትን ቁርአን በተዛባ መልኩ ብቻ ሳይሆን የክርስቲያኖችን እምነት ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ መጻፉን አሳይቻለሁ::

ከዚህም በተጨማሪ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እንደ ዋና ዋና አድርጌ የማያቸውን አንዳንድ ነጥቦች ላንሳ::

1: ቁርአን ላይ አላህ የአብርሃም የይስሃቅ የእስማኤል የያእቆብ አምላክ የአይሁዳውያንና ቡሃላም የክርስቲያኖችም
አምላክ እንደሆነ ስሙም አላህ እንደሆነና እነሱም አላህ ብለው ይጠሩት እንደነበር ይገልጻል::
ይህ እውነትነት የሌለው ነው::

2. ቁርአን ላይ በተደጋጋሚ አብርሃም እና ልጁ ኢስማኤል መካ ወስጥ ካባን እንደገነቡ ይናገራል
ይህም ቢሆን ጨርሶ እውነትነት የሌለው ነው::

3. አብርሃም ኢስማኤል ያእቆብ ሌላው ቀርቶ ሙሴም ሁሉም ሙስሊሞች እንደሆኑ ቁርአን ይናገራል
ይህም ፈጽሞ ውሽት ነው::

ሌሎችም ሌሎችም ቢኖሩም ለጊዜው እነዚህን ብናይ ደስ ይለኛል::

ሰሞኑን በነዚህ በያንዳንዱ ነጥብ ላይ እውነትነት የሌለው ነው ያልኩበትን ምክንያት ለማቅረብ እሞክራለሁ::

አመሰግናለሁ
ከአክብሮታዊ ሰላምታ ጋር
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby ወልድያ » Tue Mar 05, 2013 2:48 pm

ሰላም አሉ ኡላ

ለጠናህ እንደምን አለህ
እስቲ አንዳንድ ነገር ልበል;

ቁርአን አንድ መጽሃፍ ነው የተጻፈውም በ23 አመታት ጊዜ ውስጥ ነው:: ይህ የአንድ የወጣት ሰው እድሜ ነው::
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ የበርካታ መጽሃፎች ስብስብ ሲሆን ጠቅላላው መጻህፍት ተጽፈው ለማለቅ የወሰደበት ጊዜ ወደ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አመታት ያህል ነው:: በዚህ የጊዜ ርዝመት ውስጥ በሙሉ አምላክ ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት እውነተኛው አምላክ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምን አይነት አምላክ መሆኑና ባህሪያቶቹ በሙሉ ግልጽ ብለው ለመታየት የቻሉበት ወቅት ነው::

.

አሉ ኡላ የመጽሀፍ ቅዱስ እድሜ አንተ ከጠቀስከውም በላይ እንደሚሆን እገምታለው ሆኖም የመጻህፍቱ ደራስያን እነማን ናቸው ነው ጥያቄው ?

አንድ ምሳሌ እንውሰድ የጳውሎስ ደብዳቤዎችን ማን ጻፋቸው ? መልሱ ቀላል ነው ጳውሎስ !!! የነብዩ ሞሀመድ ባልደረቦችና ከሳቸው ህልፈት በህዋላም የነበሩ መልካም አበው የጻፉት ደብዳቤና የሰጡት ዲስኩር እንዲሁም የተላያዩ ትረካዎች ከቁርአን ጋር እንዲዳበሉ ቢደረግ መጽሀፉ ምን አይነት ቮልዩም እንደሚኖረው ገምተሀል ? በኢስላም ግን ሁሉም በአንድ ጥራዝ እንዲቀላቀል አልተፈቀደም የአምላክ ቃል ለብቻው አንድ ጥራዝ የነብዩ ቃል ለብቻው ሌላ ጥራዝ የታሪክ መጽሀፍ ለብቻው ደብዳቤዎች ለብቻቸው ...በመልክ በመልኩ ስልተቀመጡ ተቀላቅለው ለመለየት በሚያስቸግሩበት መልክ አይደሉም ስለዚህ የመጽሀፉን እድሜ ሳይሆን ማየት የሚኖርብህ በዚህ ዘመን ስንት አይነት የአምላክ ያልሆነ ንግግር በአምላክ ስም እንደተቀየጠ ነው መገመት ያለብህ ቁርአንም ያስፈለገው ለዚህ እንደሆነ ነው የምናምነው

ሃይሉን ጥበቡንና ችሎታውን በተግባር ያሳየበት
ህጢያተኞችን በደለኞችንና ከትእዛዙ የሚወጡትን በሙሉ የሚቀጣ መሆኑን በተግባር ያሳየበት
ተጸጽተው ይቅርታ የሚለምኑትን ይቅር ባይነቱን ቸርነቱን ሩህሩህነቱን በተግባር ያሳየበት
በተለይም ህዝቦቹን ከያዘበት አያያዝ አንጻር የፍቅር አምላክ መሆኑን የፍትህ አምላክ እንዲሁም ፍርድን የማያዛባና ፍርዱን የሚያስፈጽም አምላክ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ወቅት ነው :: በመሆኑም መጽሃፉ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ግልጽ በሆነ መንገድ ይዞአል::
ከዚህም በተጨማሪ የወደፊቱን ሁኔታ ከረጂም ጊዜ በፊት የሚያውቅ መሆኑንና የተናገረውም ሁሉ የሚፈጸም መሆኑን በተግባርና በጊዜ ሂደቶች ውስጥ አሳይቶአል

ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስረዳት:-
ሃይል ያለው ጥበብ ያለውና ሁሉን አዋቂ አምላክ ለመሆኑ ሃይሉንና ጥበቡን ያሳየባቸውን ጊዘያቶችና ሁኔታዎች ከመጽሃፉ ማግኘኘት ይቻላል
የፍቅር አምላክ ነው መሃሪና ሩህሩህ ነው ለማለት የሚያስችለንን በተግባር የታየባቸውን ጊዘያቶችና ሁኔታዎች በትክክል ለመረዳት በሚያስችል መንገድ መጽሃፉ መረጃዎችን ይዞአል::
በተለይም የፍትህ አምላክ ነው ለማለት የሚያስችለንን ምክንያቶችና ፍትህ በአምላክ ዘንድ ምን ያህል ቦታ እንዳለው የሚያሳይ በተግባር የተገለጹ ድርጊቶችን የሚያሳይ መረጃ ይዞአል
ሌላም ሌላም ...

ስለዚህ የእነዚህን ሁሉ የአምላክን ባህሪያት በተግባር ያላወቀ አንድ ሙስሊም በተለይም አምላክ ስለፍትህ ያለውን አመለካከትና ፍትህ በአምላክ ዘንድ ምን ቦታ እንዳለው ያለተረዳ አንድ ሙስሊም የክርስቶስን የቤዛዊ መስዋእነት አስፈላጊነቱ ጨርሶ ሊገባው አይችልም::

ማንም ቢሆን የቁርአንን ያህል ገጾች ያሉትን አንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ብቻ በማንበብ ስለአምላክ ማንነትም ሆነ ስለባህሪዎቹ ፈጽሞ ምንም ሊረዳ አይችልም:: ሙሉው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ወይም መጻህፍቶች ናቸው ያንን ሁሉ መረጃ የሚሰጡት::

በመሆኑም ላንተም ለመረዳት ቢከብድህ የሚደንቅ አይደለም::

እዚህ ላይ ቀላል ጥያቄ አለኝ ፍርድን የማያዛባ አምላክ በአዳም ጥፋት እየሱስን ለምን አሰቀለ ? በአዳም ጥፋት ብቻ በስህተቱ ምንም ድርሻ የሌላቸውን ለሚልዮናት አመታት የተራቡትን ዘር ማንዘሮቹን ለምን ተጠያቂ ያደርጋል ? ይህ ትክክል ፍርድ ነውን? ይህ ለመረዳት ቢከብደኝም እርግጥ አይደንቅም

ወደ ሁለተኛው ነጥብ ስመጣ ደግሞ ቀደም ብዬ ጀምሬው ግን እልባት ሳላደርግለት ወደ ቆምኩት ሃሳብ እመጣለሁ::

ቁርአን የአምላክ ቃል ለመሆኑ ማስረጃህ ምንድነው ብዬ የጠየኩህን እኔን መልሰህ ቁርአ የአምላክ ቃል አይደለም የምትልበትን ምክንያት አቅርብ ባልከኝ መሰረት የጀመርኩት ነው::

በአንደኛ ደረጃ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው ብለው ክርስቲያኖች የሚያምኑትን ቁርአን በተዛባ መልኩ ብቻ ሳይሆን የክርስቲያኖችን እምነት ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ መጻፉን አሳይቻለሁ::

እዚህ ላይ አንተ በስላሴ የሚያምኑትን ሰዎች ክርስያን አይደሉም ብለሀል የሮማን ካቶሊኮች ብቻ በቢልዮን የሚቆጠሩ ናቸው እነዚህ በስላሴ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ አምላክነት ያምናሉ እየሱስ ብቸኛ (ቢጎትን) ልጁ ነው ብለው ያምናሉ ማለትም አምላክ ይወልዳል ብለው ያምናሉ ያንተ አቋም ደግሞ እስካሁን ከሰማሁት ክርስትና ይለያል

ያንተ ለኔ እንደገባኝ

መጀመርያ አምላክ ብቻውን ነበረ ከዛም እየሱስን ፈጠረ የተቀሩትን ፍጥረታት ከእየሱስ ጋር በመተጋገዝ ፈጠራቸው ስለዚህም እየሱስ አምላክ ባይሆንም የፈጣሪነት ድርሻ (ሼር) አለው የሚል ነው ሆኖም ማስረጃ ብለህ ያቀረብከው ከሩቅ ቦታ ለማያያዝ የተሞከረ ነገርን ነው በመጽሀፍ ቅዱስ ምድር ሰማይ ከዋክብትና ጸሀይ እንስሳትና አታክልት ሰው (አዳም)በየትኛው ቀን እንደተፈጠሩ በማያሻማ መልክ ሲገልጽ እየሱስን ያህል በመጀመርያ የተፈጠረ ፍጥረትን እንዴት ከመጀመርያ አወጣው ? ይህንን በየትኛውም የክርትያን ዲኖሚኔሽን አልሰማሁትም አንተም ያንተን ክርስትና አይነት ወይንም ዲኖሚኔሽን በግልጽ ልትነግረኝ አልወደድክም ይህ ግን የአምላክን ሱፕሪም ፓወር የሚጻረር ከአምላክ ጋር ረዳት አማልክት የሚያስደርግ እምነት በመሆኑ በኢስላም ፍጹም ተቀባይነት የለውም በክርስትናም ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም ክርስትያኖች እየሱስን አምላክ ወይንም የአምላክ ልጅ እንጂ አምላክ እንዲረዳው የፈጠረው የመጀመርያ ረዳት አምላክ ነው ብለ የሚያምኑ አልመሰለኝም

ይህ ሌላም ጥያቄ ያስነሳብሀል መጀመርያ ተፈጥሮ የነበረ ነገር እንደገና ወደማህጸን ተመልሶ 9 ወር በማህጸን መቆየት ምን አስፈለገው ?

ሆኖም አንተ ክርስትያኖች የማይሉትን ቁራን ይላሉ ይላል ካልክ አሁንም ማስረጃውን አምጣ ማስረጃ ስታመጣ ግን ስለምን እመሚወራ እንዲገባህ በቅድማያ አንተ ከምትጠቅሰው አንቀጽ ከህዋላው እና ከፊቱ ያለውንም ቀድመህ አንብብ ስለመካ ጣኦታውያን የተናገረውን ስለክርስትያኖች ነው ብለህ እንዳትረዳው

ከዚህም በተጨማሪ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እንደ ዋና ዋና አድርጌ የማያቸውን አንዳንድ ነጥቦች ላንሳ::

1: ቁርአን ላይ አላህ የአብርሃም የይስሃቅ የእስማኤል የያእቆብ አምላክ የአይሁዳውያንና ቡሃላም የክርስቲያኖችም
አምላክ እንደሆነ ስሙም አላህ እንደሆነና እነሱም አላህ ብለው ይጠሩት እንደነበር ይገልጻል::
ይህ እውነትነት የሌለው ነው::

እዚህ ላይ ለጠቅላላ እውቀት አንድ ነገር ላንሳ አዳም ከተፈጠረ ምን ያህል ግዜ ሆነው ? በመጽሀፍ ቅዱስ ስሌት መሰረት 7 ሺ አመታት ተቆጥረዋል ምድር እና ሰማይም በመጽሀፍ ቅዱስ ስሌት መሰረት ከአዳም አፈጣጠር ጋር ስለሚያያዙ ከ7000 አመታት በፊት የተፈጠሩ ናቸው ! ይህ ግን አሁን ካለንበት የሳይንስ ዘመን አንጻር በጣም ትክክል ያልሆነ ቀመር ነው ምድር እና ሰማይ ከተፈጠሩ ብዙ ሚዮን አመታት ተቆጥረዋል አዳምም (የሰው ልጅ ) ምድርን ከረገጠ ሚልዮኖች አመታት ሆነዋል በነዚህ አመታት የሰው ልጆች ከአጽናፍ እስከአጽናፍ ምድርን ሞልተዋል በዋልታዎች ከሚኖሩት ኤስኪሞዎች አንስቶ በአፍሪካ ጫካዎች እርቃናቸውን እስከሚኖሩት ሰዎች በደቡብ አመሪካ ከሚገኙ ሰዎች አንስቶ በምስራቅ እስካሉት ጃፓኖችያለፉትም ያሁኖቹም የመጪዎቹም የሁሉም አምላክ አንድ እና አንድ ብቻ ነው ስለዚህ የክርስትያን እና የአይሁድ የሙስሊም አምላክ አንድ መሆኑ አይግረምህ የቡዲስቶችም የሂንዱዎችም የአምላክ የለሾቹም አምላክ አንድ ነው ሰዎቹ ማንን እያመለኩ ነው ሌላ ነገር ነው እውነተኛ አምላክ ግን አንድ ብቻ ነው ለሎቻማልክት የሉም ማለቴ አይደለም ሰዎች በተሳሳተ ጎዳና ሆነው የሚገዝዋቸው ብዙ አማልክት አሉ ህንድ ብትሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ አማልክት ታገኛለህ እነዚህ ሁሉ ግን ሊካድባቸው የሚገቡ የሀሰት አማልክት ናቸው እውነተኛ የፍጥረተ አለም ፈጣሪ የሁሉም አምላክ ግን አንድ ብቻ ነው

ሁሉም አላህ ብለው ይጠሩት ነበር የሚል ነገር ቁራን ላይ አለ ያልከውን ግን በማስረጃ አሳየኝ እንደዛ የሚል ነገር ፈጽሞ ስለሌለ

በቁራን ላይ እንደዛ ባይልም ለእውቀትህ ያህል ግን ጎግል ትራንስሌተር ውስጥ ግባና GOD የሚለውን ቃል ተመጣጣኝ ትርጉም በሂብሩ እንዲሰጥህ አድረግ ምን እንደመጣልህ ንገረኝና እንወያይበታለን እየሱስ ሙሴም የሚናገሩት ሂብሩ ነበረና የመጽሀፍ ቅዱሱም ኦሪጅናል ቅጂ መሆን የሚገባው በሂብሩ ብቻ ነበረ የአምላክ ስምም ሊሆን የሚችለው እሱ እንጂ የግሪክ ወይንም የእንጊዝኛው ወይንም ለላ ስም አይደለምና

ለሌሎቹ እመለሳለው [/quote]
ወልድያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 497
Joined: Mon May 24, 2010 3:58 pm

Postby ወልድያ » Thu Mar 07, 2013 9:17 am

ሰላም አሉ ኡላ

.
ቁርአን ላይ በተደጋጋሚ አብርሃም እና ልጁ ኢስማኤል መካ ወስጥ ካባን እንደገነቡ ይናገራል
ይህም ቢሆን ጨርሶ እውነትነት የሌለው ነው ::

ይህንን አብራራለው ባልከው መሰረት እስክታብራራው እጠብቃለው

3. አብርሃም ኢስማኤል ያእቆብ ሌላው ቀርቶ ሙሴም ሁሉም ሙስሊሞች እንደሆኑ ቁርአን ይናገራል
ይህም ፈጽሞ ውሽት ነው ::

እዚህ ላይ እርግጥ ነው እንደዛ ይላል

ነገር ግን ሙስሊም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጽንሰ ሀሳቡን መረዳት አለብህ

ክርስትያን ማለት የክርስቶስ ተከታይ ማለት ነው

አይሁድ ማለትም የጎሳ ወይንም ነገድ ስም ነው

ቡዲስት ማለት የቡድሀ ተከታይ ማለት ነው

ሂንዱ ማለትም ጂኦግራፊያዊ ስያሜ ነው

ወደ ኢስላም ስትመጣ ግን እንደዛ አይደለም አረባዊ ወይንም ሞሀመዳዊ ማለት አይደለም

ኢስላም ማለት 'ሲልም" ከሚለው ስረ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም በሙሉ ፈቃደኝነት መታዘዝ መገዛት እጅ መስጠትን ያመለክታል

በዚህ ዩነቨርስ ላይ ያሉ ክስተቶች በሙሉ ከሰው በስተቀር አምላክ ላወጣው ህግ ታዛዦች ናቸው ስለዚህም they are in a state of islam እንላለን ማለትም ለአምላክ ህግ ታዛዦች ናቸው ማለት ነው ሰው ግን አስቦ የመወሰንና የመምረጥ አቅም ተሰጥቶታል ስለዚህም አምላክ በሱ ህግ እንዲተዳደር ጋብዞታል ለዚህ የአምላክ ህግ ተገዢ ለመሆን የፈቀደን ሁሉ እኛ ሙስሊም ማለትም ታዛዥ እንለዋለን

ለምሳሌ እየሱስ ዮሀንስ ም 5 ቁ 30 ላይ እንዲህ ይላል

30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።

እንግዲህ እኛ የአምላኩን እንጂ የራሱን ፈቃድ የማይፈልግን ሁሉ ሙስሊም እንለዋለን ሌሎቹም ሙስሊም የተባሉት በዚህ ሴንስ እንጂ የሞሀመድ (ሰአወ) ተከታይ ነበሩ ማለት አይደለም

መታዘዝ አለመታዘዝ ደግሞ ከአዳም ጀምሮ የነበረ ነገር እንጂ አዲስ ነገር አይደለም

ነብያት ደግሞ በሙሉ ታዛዦች ስለነበሩ ሙስሊም ነበሩ እንላለን

ግልጽ ካልሆነ አብራራዋለውእስቲ ደግሞ ከላይ ላሉት ነገሮች ግዜ ሳገኝ እመለሳለው

ከሰላምታ ጋር
ወልድያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 497
Joined: Mon May 24, 2010 3:58 pm

Postby አሉ-ኡላ » Wed Mar 27, 2013 10:22 pm

ወልድያ wrote:ሰላም አሉ ኡላ

ለጠናህ እንደምን አለህ
እስቲ አንዳንድ ነገር ልበል;

ቁርአን አንድ መጽሃፍ ነው የተጻፈውም በ23 አመታት ጊዜ ውስጥ ነው:: ይህ የአንድ የወጣት ሰው እድሜ ነው::
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ የበርካታ መጽሃፎች ስብስብ ሲሆን ጠቅላላው መጻህፍት ተጽፈው ለማለቅ የወሰደበት ጊዜ ወደ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አመታት ያህል ነው:: በዚህ የጊዜ ርዝመት ውስጥ በሙሉ አምላክ ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት እውነተኛው አምላክ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምን አይነት አምላክ መሆኑና ባህሪያቶቹ በሙሉ ግልጽ ብለው ለመታየት የቻሉበት ወቅት ነው::

.

አሉ ኡላ የመጽሀፍ ቅዱስ እድሜ አንተ ከጠቀስከውም በላይ እንደሚሆን እገምታለው ሆኖም የመጻህፍቱ ደራስያን እነማን ናቸው ነው ጥያቄው ?

አንድ ምሳሌ እንውሰድ የጳውሎስ ደብዳቤዎችን ማን ጻፋቸው ? መልሱ ቀላል ነው ጳውሎስ !!! የነብዩ ሞሀመድ ባልደረቦችና ከሳቸው ህልፈት በህዋላም የነበሩ መልካም አበው የጻፉት ደብዳቤና የሰጡት ዲስኩር እንዲሁም የተላያዩ ትረካዎች ከቁርአን ጋር እንዲዳበሉ ቢደረግ መጽሀፉ ምን አይነት ቮልዩም እንደሚኖረው ገምተሀል ? በኢስላም ግን ሁሉም በአንድ ጥራዝ እንዲቀላቀል አልተፈቀደም የአምላክ ቃል ለብቻው አንድ ጥራዝ የነብዩ ቃል ለብቻው ሌላ ጥራዝ የታሪክ መጽሀፍ ለብቻው ደብዳቤዎች ለብቻቸው ...በመልክ በመልኩ ስልተቀመጡ ተቀላቅለው ለመለየት በሚያስቸግሩበት መልክ አይደሉም ስለዚህ የመጽሀፉን እድሜ ሳይሆን ማየት የሚኖርብህ በዚህ ዘመን ስንት አይነት የአምላክ ያልሆነ ንግግር በአምላክ ስም እንደተቀየጠ ነው መገመት ያለብህ ቁርአንም ያስፈለገው ለዚህ እንደሆነ ነው የምናምነውሰላም ወልድያ

ቀላል የማይባል የጤና ችግር ገጥሞኝ ጠፋሁ
አሁን ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ሁሉም ነገር እየተስተካከለ እንደሆነ ይሰማኛል

እስቲ አጠር አጠር ያለ ሀሳብ ልስጥ

መጽሀፍ ቅዱስ ስለተጻፈበት የአጻጻፍ መንገድ ትንሽ ልበል::

አምላክ መጽሀፉን ያስጻፈው በተለያየ መንገድ ነው::
በቀጥታ አነጋገር መልክ የተናገራቸውን በተናገረው መልክ የተጻፉ አሉ

እኔ እንዲህ ብያለሁ.... እንዲህ በልና ንገራቸው...... በሚሉ የቀጥታ አነጋገሮች የተጻፉ ቢኖሩም በሌላ መልክም የተጻፉ አሉ::

አንድ ምሳሌ ልናገር

የአንድ ካምፓኒ ማናጀር ጽሀፊውን በቀጥታ ራሱ ያረቀቀውንና የጻፈውን በታይፕ ወይም በኮምፒውተር ጽፋ ለሰራተኞች እንዲታደል ያዛታል:: በታዘዘችው መሰረት የተሰጣትን ጽፋ ታቀርብለትና አይቶ ፈርሞበት ለሰራተኞች ይታደላል:: ሰራተኞቹ ሲያነቡት የጸሀፊዋ ሳይሆን የስራ አስኪያጁ ቃል እንደሆነ ያውቁታል::

በሌላ ጊዜ ደግሞ ያው ስራ አስኪያጅ ረቂቅ ሀሳቦችን ያዘጋጅና ጽሀፊዋን በዚህ ረቂቅ አስተዋጾ ላይ ተመስርተሽ በዝርዝር እንድትጽፊ ብሎ ሀሳቡን ይነግራታል:: ይህቺ ጸሀፊ በስራ አስኪያጁ የተነገራትን መሰረተ ሀሳብ ሳትለቅ በራሷ የአጻጻፍ ስልት ትጽፍና ለስራ አስኪያጁ ታቀርብለታለች አንብቦ የሚታረም ካለም አርሞ ይፈርምበትና አሁንም ለሚመለከታቸው ሰራተኞች ይታደላል:: በዚህ ጊዜም ቢሆን ሰራተኞቹ የጸሀፊዋ ሀሳብ ሳይሆን የስራ አስኪያጁ ቃል እንደሆነ አድርገው ይወስዱታል::

አምላክ በራሱ እጅ ጽፎ የሰጠው ቃልን ጨምሮ እንዲህ በል እንዲህ በላቸው ... እንዲህ ብያለሁ እኔ ተናግሬአለሁ.. በሚሉ በቀጥታዊ አነጋገሮች የተናገረባቸውና የተጻፉ ቢኖሩም አንድ ሙሉ መጽሀፍ በዚህ አይነት አጻጻፍ የተጻፈ የለም::

የመጽሀፍ ቅዱስ ጸሀፊዎች ባብዛኛው አምላክ ሀሳቡን በአእምሯቸው (በልባቸው) አስገብቶ በራሳቸው የአጻጻፍ ስልት እንዲጽፉት ቢያደርግም ቃሉ የአምላክ ቃል እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው::ዋነኛ ተፈላጊው የተጻፈበት መንገድ ሳይሆን መልእክቱ ነው::

ለዚህም ነው ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች የሚከተለውን የጻፈላቸው::
1ተሰሎንቄ 2: 13 እንዲህ ይላል:-
ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሄር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሰራ እንደ እግዚአብሄር ቃል እንጂ እንደሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት እኛ ደግሞ እግዚአብሄርን ሳናቁዋርጥ እናመሰግናለን::

ስለዚህ መጽሀፍ ቅዱስ የተጻፈው ለሰዎች በመሆኑ ሀሳቡን በልባቸው በማስገባት በራሳቸው አጻጻፍ እንዲጽፉት አድርጎአል::

አንዳንድ ጊዜ የመጽሀፍ ቅዱስ ጽሀፊዎች በጻፉት መጽሀፍ ላይ ስማቸውን የማይጠቅሱበት ወቅት አለ:: ያ የተለያየ ምክንያት ይኖረዋል:: ነገር ግን የትኛውን መጽሀፍ ማን እንደጻፈው የምናውቅበት መንገድ ቢኖርም በዋነኛነት አጽንኦት ሊሰጠው የሚገባው ቃሉ ነው እንጂ የጽሀፊው ስም ወይም ማንነት አይደለም:: የመጽሀፍ ቅዱስ ጸሀፊዎች በተለያየ የጊዜ ርዝመት የኖሩ ቢሆኑም እንዲህ እርስ በርሱ የሚስማማ መጽሀፍ መጻፋቸው በራሱ ቃሉ ከአንድ ምንጭ ወይም ህሳቡ ከአንድ ምንጭ እንደሆነ ያረጋግጣል:: የራሳቸውን ሀሳብ ቢሆን ኖሮ ያሰፈሩት አንዱም ካንዱ ጋር አይስማማም ነበር::

ሃይሉን ጥበቡንና ችሎታውን በተግባር ያሳየበት
ህጢያተኞችን በደለኞችንና ከትእዛዙ የሚወጡትን በሙሉ የሚቀጣ መሆኑን በተግባር ያሳየበት
ተጸጽተው ይቅርታ የሚለምኑትን ይቅር ባይነቱን ቸርነቱን ሩህሩህነቱን በተግባር ያሳየበት
በተለይም ህዝቦቹን ከያዘበት አያያዝ አንጻር የፍቅር አምላክ መሆኑን የፍትህ አምላክ እንዲሁም ፍርድን የማያዛባና ፍርዱን የሚያስፈጽም አምላክ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ወቅት ነው :: በመሆኑም መጽሃፉ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ግልጽ በሆነ መንገድ ይዞአል::
ከዚህም በተጨማሪ የወደፊቱን ሁኔታ ከረጂም ጊዜ በፊት የሚያውቅ መሆኑንና የተናገረውም ሁሉ የሚፈጸም መሆኑን በተግባርና በጊዜ ሂደቶች ውስጥ አሳይቶአል

ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስረዳት:-
ሃይል ያለው ጥበብ ያለውና ሁሉን አዋቂ አምላክ ለመሆኑ ሃይሉንና ጥበቡን ያሳየባቸውን ጊዘያቶችና ሁኔታዎች ከመጽሃፉ ማግኘኘት ይቻላል
የፍቅር አምላክ ነው መሃሪና ሩህሩህ ነው ለማለት የሚያስችለንን በተግባር የታየባቸውን ጊዘያቶችና ሁኔታዎች በትክክል ለመረዳት በሚያስችል መንገድ መጽሃፉ መረጃዎችን ይዞአል::
በተለይም የፍትህ አምላክ ነው ለማለት የሚያስችለንን ምክንያቶችና ፍትህ በአምላክ ዘንድ ምን ያህል ቦታ እንዳለው የሚያሳይ በተግባር የተገለጹ ድርጊቶችን የሚያሳይ መረጃ ይዞአል
ሌላም ሌላም ...

ስለዚህ የእነዚህን ሁሉ የአምላክን ባህሪያት በተግባር ያላወቀ አንድ ሙስሊም በተለይም አምላክ ስለፍትህ ያለውን አመለካከትና ፍትህ በአምላክ ዘንድ ምን ቦታ እንዳለው ያለተረዳ አንድ ሙስሊም የክርስቶስን የቤዛዊ መስዋእነት አስፈላጊነቱ ጨርሶ ሊገባው አይችልም::

ማንም ቢሆን የቁርአንን ያህል ገጾች ያሉትን አንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ብቻ በማንበብ ስለአምላክ ማንነትም ሆነ ስለባህሪዎቹ ፈጽሞ ምንም ሊረዳ አይችልም:: ሙሉው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ወይም መጻህፍቶች ናቸው ያንን ሁሉ መረጃ የሚሰጡት::

በመሆኑም ላንተም ለመረዳት ቢከብድህ የሚደንቅ አይደለም::እዚህ ላይ ቀላል ጥያቄ አለኝ ፍርድን የማያዛባ አምላክ በአዳም ጥፋት እየሱስን ለምን አሰቀለ ? በአዳም ጥፋት ብቻ በስህተቱ ምንም ድርሻ የሌላቸውን ለሚልዮናት አመታት የተራቡትን ዘር ማንዘሮቹን ለምን ተጠያቂ ያደርጋል ? ይህ ትክክል ፍርድ ነውን? ይህ ለመረዳት ቢከብደኝም እርግጥ አይደንቅምአዎ ይህ ከላይ ያሰፈርከው ትምህርት ላንተ እንደሚከብድህ አምናለሁ..

ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አምላክ አዳምንና ሚስቱን መጀመሪያ ፈጥሮ ገነት እንዲኖሩ እንዳደረጋቸው ቁርአን ይናገራል:: መቼም ታዛዥ እስከሆኑ ድረስ ሁልጊዜም በገነት እንደሚኖሩ ግልጽ ይመስለኛል:: ልጆች ቢወልዱም ልጆቻቸውም አብረው በገነት ይኖራሉ:: ታድያ አዳምና ሚስቱ የተከለከሉትን ፍሬ በልተው ከገነት ሲባረሩ የወለዱዋቸው ልጆች ለምን ገነት እንዲገቡ አልተፈቀደላቸውም?? እነሱ ፍሬውን አልበሉም ለምን ገነት አልገቡም ነበር???

ሌላው ኢብሊስ (ዲያብሎስ) አዳምን እና ሚስቱን እንዳሳታቸው እና ከገነት እንዲወጡ እንዳደረጋቸው ይናገራል:: ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ራሱ ለአምላክ አልታዘዝም ብሎ ያፈነገጠ መልአክ ነው:: ታድያ አምላክ አዛኝና ሩህሩህ ከሆነ አልታዘዝም ብሎ ባመጸና ባፈነገጠ መልአክ ፍሬውን ያልበሉ የአዳም ዘሮች እንዲሰቃዩ ለምን አደረገ??

አንተ ራስህ ቤተሰብ እንዳለህ አምናለሁ ልጆችም ሊኖሩህ ይችላሉ እናም አንድ ባንተ ላይ ያመጸን ሰው ልጆችህን እንዲፈትንና እንዲያሰቃይ ትፈቅድለታለህ??
ልጆችህን የምትወድ ከሆነ ለልጆችህ አዛኝና ሩህሩህ ከሆንክ ለምን ባመጸብህና አልታዘዝም ብሎህ ከቤትህ ባፈነገጠ ሰው ልጆችህ እንዲሰቃዩ እንደምትፈቅድ ንገረኝ::

እናም የአምላክን ፍትሀዊነት ከዚህ ጋር አያይዘህ ቁርአን የሚያስተምረው ምን እንደሆነ እስቲ ንገረኝ:

ወደ ሁለተኛው ነጥብ ስመጣ ደግሞ ቀደም ብዬ ጀምሬው ግን እልባት ሳላደርግለት ወደ ቆምኩት ሃሳብ እመጣለሁ::

ቁርአን የአምላክ ቃል ለመሆኑ ማስረጃህ ምንድነው ብዬ የጠየኩህን እኔን መልሰህ ቁርአ የአምላክ ቃል አይደለም የምትልበትን ምክንያት አቅርብ ባልከኝ መሰረት የጀመርኩት ነው::

በአንደኛ ደረጃ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው ብለው ክርስቲያኖች የሚያምኑትን ቁርአን በተዛባ መልኩ ብቻ ሳይሆን የክርስቲያኖችን እምነት ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ መጻፉን አሳይቻለሁ::

እዚህ ላይ አንተ በስላሴ የሚያምኑትን ሰዎች ክርስያን አይደሉም ብለሀል የሮማን ካቶሊኮች ብቻ በቢልዮን የሚቆጠሩ ናቸው እነዚህ በስላሴ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ አምላክነት ያምናሉ እየሱስ ብቸኛ (ቢጎትን) ልጁ ነው ብለው ያምናሉ ማለትም አምላክ ይወልዳል ብለው ያምናሉ ያንተ አቋም ደግሞ እስካሁን ከሰማሁት ክርስትና ይለያል

ያንተ ለኔ እንደገባኝ

መጀመርያ አምላክ ብቻውን ነበረ ከዛም እየሱስን ፈጠረ የተቀሩትን ፍጥረታት ከእየሱስ ጋር በመተጋገዝ ፈጠራቸው ስለዚህም እየሱስ አምላክ ባይሆንም የፈጣሪነት ድርሻ (ሼር) አለው የሚል ነው ሆኖም ማስረጃ ብለህ ያቀረብከው ከሩቅ ቦታ ለማያያዝ የተሞከረ ነገርን ነው በመጽሀፍ ቅዱስ ምድር ሰማይ ከዋክብትና ጸሀይ እንስሳትና አታክልት ሰው (አዳም)በየትኛው ቀን እንደተፈጠሩ በማያሻማ መልክ ሲገልጽ እየሱስን ያህል በመጀመርያ የተፈጠረ ፍጥረትን እንዴት ከመጀመርያ አወጣው ? ይህንን በየትኛውም የክርትያን ዲኖሚኔሽን አልሰማሁትም አንተም ያንተን ክርስትና አይነት ወይንም ዲኖሚኔሽን በግልጽ ልትነግረኝ አልወደድክም ይህ ግን የአምላክን ሱፕሪም ፓወር የሚጻረር ከአምላክ ጋር ረዳት አማልክት የሚያስደርግ እምነት በመሆኑ በኢስላም ፍጹም ተቀባይነት የለውም በክርስትናም ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም ክርስትያኖች እየሱስን አምላክ ወይንም የአምላክ ልጅ እንጂ አምላክ እንዲረዳው የፈጠረው የመጀመርያ ረዳት አምላክ ነው ብለ የሚያምኑ አልመሰለኝም

ይህ ሌላም ጥያቄ ያስነሳብሀል መጀመርያ ተፈጥሮ የነበረ ነገር እንደገና ወደማህጸን ተመልሶ 9 ወር በማህጸን መቆየት ምን አስፈለገው ?

ከዚህ በፊት የተናገርኩትን ሙሉ በሙሉ የተረዳኸኝ አለመሰለኝም:: ሁሉንም መድገም አሁን ይከብደኛል

በጭሩና ግልጽ በሆነ መንገድ ግን
አምላክ ለሚያደርገው ነገር በሙሉ አጋዥ ረዳት አማካሪ አያስፈልገውም:: ያልተረዳኸው ግን አንድ ነገር አለ?
በጥያቄ መልክ ላቅርበው
አምላክ ራሱ ማድረግ እየቻለ ለምን መልክተኛ ይልካል?
የመላእክቶች ስራስ ምንድነው ለምንድነው ሁሉንም ራሱ የማይሰራው??

አዎ አንድ ጌታ አገልጋዮች ቢኖሩትና ያዘዛቸውን ቢሰሩ ስራው የጌታቸው ነው እንጂ ያገልጋዮቹ እንደማይሆን ግልጽ ነው:: ጌታው የሚያዛቸውን ማድረጋቸው ከሱ ጋር እኩል ጌትነት እንዳላቸው አያሳይም::ለቀሩትም እመለሳለሁ
ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ ጤንነቴ እንዳለተመለሰ እየነገርኩህ ልዘገይ ብችል እንድትታገሰኝ እለምንሀለሁ::

አመሰግናለሁ
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby አሉ-ኡላ » Sat Apr 20, 2013 9:42 pm

ሰላም ወልድያ
በመጥፋቴ ይቅርታ ህመሜ ከበድ ያለ በመሆኑ ከበድ ያለ ህክምና ላይ ነው የቆየሁት አሁን ደህና የሆንኩ ይመስለኛል:: ግን ብዙም ተቀምጦ መፃፍ ገና ስለሆንኩ የምልከው አጫጭር ሊሆን ቢችልም ግን በተቻለኝ ግልጽ በሆነ መንገድ ለማድረግ እሞክራለሁ::እዚህ ላይ ለጠቅላላ እውቀት አንድ ነገር ላንሳ አዳም ከተፈጠረ ምን ያህል ግዜ ሆነው ? በመጽሀፍ ቅዱስ ስሌት መሰረት 7 ሺ አመታት ተቆጥረዋል ምድር እና ሰማይም በመጽሀፍ ቅዱስ ስሌት መሰረት ከአዳም አፈጣጠር ጋር ስለሚያያዙ ከ7000 አመታት በፊት የተፈጠሩ ናቸው ! ይህ ግን አሁን ካለንበት የሳይንስ ዘመን አንጻር በጣም ትክክል ያልሆነ ቀመር ነው ምድር እና ሰማይ ከተፈጠሩ ብዙ ሚዮን አመታት ተቆጥረዋል አዳምም (የሰው ልጅ ) ምድርን ከረገጠ ሚልዮኖች አመታት ሆነዋል

ወልድያ እዚህ ላይ ካነጋገርህ እንደተረዳሁት የኢቮሉሽን አማኝ ትመስለኛለህ::
ትክክለኛው የክርስትና ትምህርትና ኢቮሉሽን ተጻራሪዎች ናቸው:: በመሆኑም ኢቮሉሽን ለኔ ትክክለኛ ሳይንስ ሳይሆን ያልተረጋገጠ ፈጠራ ነው:: ከፈለክ ርእሱን አንስተን መወያየት እንችላለን::

ስለፍጥረት በተናገርከው ላይ ግን በምን ስሌት ወይም በየትኛው የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ተመስርተህ እንደሆነ አለገባኝም ሰው ከተፈጠረ 7000 አመታት ሞልቶታል ያልከው::

ስለ ትክክለኛው የፍጠረት ትምህርት ግን መፅሀፍ ቅዱስ ከትክክለኛው ሳይንስ ጋር አይጋጭም

የመጽሀፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ዘገባ ተመልከት እንዲህ ይላል:-
ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ::

ልብ በል እዚህ ላይ ምንም ቀናት አልተጠቀሱም ስራውን ወይም ፍጥረቱን ሲጀምር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ነው የፈጠረው:: ሰማይና ምድር ማለት ሰማያዊ አካላትን ማለትም በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዋክብቶች የሚገኙበትን ጋላክሲዎችንና ሌሎች ሰማያዊ አካላትን በሙሉና ምድርን ያጠቃልላል እነዚህን ከአእምሯችን በላይ የሆኑትን የከዋክብቶች እና የሰማያዊ አካላትን እንዲሁም ምድርን ስርአትና ህግጋት ባለው መንገድ ፈጥሮ ለመጨረስ ምን ያህል ጊዜ እንደወሰደ የተጠቀሰ ነገር የለም:: ከዩኒቨርስ ግዙፍነት አንጻር በተለይም ይህ ግዙፍ የሆነው ዩኒቨርስ ያለአንዳች ችግር ለዘላለም መኖር እንዲችል ተፈጥሯዊ ህጎችንና ስርአቶችን የያዘ ከመሆኑ አንጻር ስናየው ብዙ ሚሊዮኖች አመታት ፈጅተው ሊሆን ይችላል:: ሳይንሳዊ የእድሜ ስሌቶችም ይህንኑ ያሳያሉ::
ዘላለማዊ ለሆነው አምላክ ደግሞ ሚሊዮን አመታቶች ምንም አይደሉም::

ዘፍጥረት 1: 2 ላይ በመቀጠል ምድርም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ::
ይላል

ከዚያ ቡሀላ ሰውን ከመፍጠሩ በፊት አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች መፍጠር ሲጀምር ቀናት መቆጠር መጀመራቸውን ልብ ልትለው ትችላለህ::

ቁጥር 3-5 ላይ
እግዚአብሔርም ብርሀንም ይሁን አለ ብርሀንም ሆነ ...
እግዚአብሔርም ብርሀኑን ቀን ብሎ ጠራው ጨለማውንም ሌሊት አለው ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አንድ ቀን::

በመሆኑም ቀናት መቆጠር የጀመሩት ከዚህ የፍጥረት ስራ ቡሀላ መሆኑን ማስተዋል ትችላለህ::

ይልቅ ይህ ከላይ ያለው አመለካከትህ ቁርአን ስለፍጥረት ያለውን ዘገባ ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባኸው ያሳያል

ቁርአን ላይ አላህ ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ፈጠረ ይላል::
እንግዲህ ከሳይንስ አንጻር ሲታይ እንዴት ነው ግዙፉ ዩኒቨርስ ምድርንና ህይወትን ጨምሮ በስድስት ቀናት ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉት???

ከሳይንስ አንጻር ነው አንተም የተመለከትከው እናም መልስህ ከሳይንስ አንጻር መሆን እንዳለበት አትዘንጋ::

ስለፍጥረት እያንዳንዱ ነገር እንዴት እንደተገኘ በትክክል የሚናገር መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ነው::በነዚህ አመታት የሰው ልጆች ከአጽናፍ እስከአጽናፍ ምድርን ሞልተዋል በዋልታዎች ከሚኖሩት ኤስኪሞዎች አንስቶ በአፍሪካ ጫካዎች እርቃናቸውን እስከሚኖሩት ሰዎች በደቡብ አመሪካ ከሚገኙ ሰዎች አንስቶ በምስራቅ እስካሉት ጃፓኖችያለፉትም ያሁኖቹም የመጪዎቹም የሁሉም አምላክ አንድ እና አንድ ብቻ ነው ስለዚህ የክርስትያን እና የአይሁድ የሙስሊም አምላክ አንድ መሆኑ አይግረምህ የቡዲስቶችም የሂንዱዎችም የአምላክ የለሾቹም አምላክ አንድ ነው ሰዎቹ ማንን እያመለኩ ነው ሌላ ነገር ነው እውነተኛ አምላክ ግን አንድ ብቻ ነው ለሎቻማልክት የሉም ማለቴ አይደለም ሰዎች በተሳሳተ ጎዳና ሆነው የሚገዝዋቸው ብዙ አማልክት አሉ ህንድ ብትሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ አማልክት ታገኛለህ እነዚህ ሁሉ ግን ሊካድባቸው የሚገቡ የሀሰት አማልክት ናቸው እውነተኛ የፍጥረተ አለም ፈጣሪ የሁሉም አምላክ ግን አንድ ብቻ ነውወልድያ ተሳስተሀል የሁሉም ሰዎች አምላክ አንድ አይደለም:: የሙስሊሞች የቡድሂስቶች የክርስቲያኖች የሂንዱዎች ወዘተ. አምላክ አንድ አይደለም:: ሁሉም የተለያየ አምላክ ነው የሚያመልኩት:: ከስም ጀምሮ የተለያዩባህሪያት ያሉዋቸውን አማልክት ነው ሰዎች የሚያመልኩት::
ሌላው ቀርቶ የሙስሊሞችና የክርስቲያኖች አምላክ በስምም ሆነ በባህሪያቸው ፈጽሞ የተለያዩ ናቸው::
የሂንዱዎችም ጨርሶ ሌላ ነው:: የሌላውም ሌላ ነው::
ነገር ግን የሁሉም ፈጣሪ አንድ ነው::

በእርግጥ ሰዎች የተለያዩ አማልክትን ቢያመልኩም ሁሉም እውነተኛ ናቸው ማለት አይደለም::
እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ ነው::ላሁኑ በዚህ ላብቃ
ካሁን ቡሀላ ብዙ አልቆይም ለቀሪዎቹ ሰሞኑን እመለሰአለሁ
ሰላምና ጤናን እመኝልሀለሁ
አመሰግናለሁ
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby ወልድያ » Mon Apr 22, 2013 6:24 am

ሰላም አሉ ኡላ

ብዙ ከመወያየታችን የተነሳ በአካል የማውቅህ ያህል ስለሚሰማኝ በመታመምህ በጣም አዝኛለው ለክፉ እንደማይሰጥህ በፍጥነትም ወደቀድሞ ጤንነትህ እንደምትመለስም ምኞቴና ተስፋዬም ነው በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነህ ምላሽ መጻፍህን እንደማደንቅና ተገቢውን ክብር ሰጥቼ እንደማነበውና ሀስብህን ስትቅዋጭም በየደረጃው ምላሸን እንደምሰጥ እገልጽልሀለው

በድጋሚ ቶሎ እንድትሽርና ወደቀድሞው ጤናህ እንድትመለስ እመኝልሀለው

በአክብሮት
ወልድያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 497
Joined: Mon May 24, 2010 3:58 pm

Postby አሉ-ኡላ » Thu May 09, 2013 7:21 pm

ወልድያ wrote:ሰላም አሉ ኡላ

ብዙ ከመወያየታችን የተነሳ በአካል የማውቅህ ያህል ስለሚሰማኝ በመታመምህ በጣም አዝኛለው ለክፉ እንደማይሰጥህ በፍጥነትም ወደቀድሞ ጤንነትህ እንደምትመለስም ምኞቴና ተስፋዬም ነው በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነህ ምላሽ መጻፍህን እንደማደንቅና ተገቢውን ክብር ሰጥቼ እንደማነበውና ሀስብህን ስትቅዋጭም በየደረጃው ምላሸን እንደምሰጥ እገልጽልሀለው

በድጋሚ ቶሎ እንድትሽርና ወደቀድሞው ጤናህ እንድትመለስ እመኝልሀለው

በአክብሮትሰላም ወልድያ
ስለ መልካም ምኞትህ በጣም በጣም ከልብ አመሰግናለሁ
እኔም ከብዙ ውይይቶቻችን የተነሳ በጣም ስለተላመድን የእውነቴን ነው የምልህ ልክ በአካል የማውቅህ ያህል ሆኖ ነው የሚሰማኝ
አሁን ደግሞ አነጋገርህ በጥልቅ ልቤን ነው የነካው እጅግ በጣም ነው የማመሰግነው::
ልዩነታችን የሀይማኖት ልዩነት እንጂ እኔና አንተ ፍጹም ወንድማማች እንደሆንን አስባለሁ በትልቅ አከብርሀለሁ::

ወልድያ ተሻለኝ እያልኩኝ እንደገና እያገረሽብኝ ተቸግሬ ነው የጠፋሁት:: የጀመርኩትን ሳልጨርስ የመቅረቴን ያህል የሚያስጨንቀኝ ምንም ነገር እንደሌለ ልነግርህ እወዳለሁ::
ታምሜ እንኩዋን ውይይታችን መቁዋረጡ ያስጨንቀኝ ነበር::

አሁንም ያው የለመለመ ተስፋ ነው ያለኝ እናም ተሽሎኛል ብዬ አስባለሁ በሰላም ውይይታችንን እንደምንቀጥል ሆኖ ነው የሚሰማኝ::

አሁን ወደጀመርነው ሀሳብ ልሂድ

ሰላም አሉ ኡላ

.
Quote:
ቁርአን ላይ በተደጋጋሚ አብርሃም እና ልጁ ኢስማኤል መካ ወስጥ ካባን እንደገነቡ ይናገራል
ይህም ቢሆን ጨርሶ እውነትነት የሌለው ነው ::

ይህንን አብራራለው ባልከው መሰረት እስክታብራራው እጠብቃለው

Quote:
3. አብርሃም ኢስማኤል ያእቆብ ሌላው ቀርቶ ሙሴም ሁሉም ሙስሊሞች እንደሆኑ ቁርአን ይናገራል
ይህም ፈጽሞ ውሽት ነው ::

እዚህ ላይ እርግጥ ነው እንደዛ ይላል

ነገር ግን ሙስሊም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጽንሰ ሀሳቡን መረዳት አለብህ

ክርስትያን ማለት የክርስቶስ ተከታይ ማለት ነው

አይሁድ ማለትም የጎሳ ወይንም ነገድ ስም ነው

ቡዲስት ማለት የቡድሀ ተከታይ ማለት ነው

ሂንዱ ማለትም ጂኦግራፊያዊ ስያሜ ነው

ወደ ኢስላም ስትመጣ ግን እንደዛ አይደለም አረባዊ ወይንም ሞሀመዳዊ ማለት አይደለም

ኢስላም ማለት 'ሲልም " ከሚለው ስረ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም በሙሉ ፈቃደኝነት መታዘዝ መገዛት እጅ መስጠትን ያመለክታል

በዚህ ዩነቨርስ ላይ ያሉ ክስተቶች በሙሉ ከሰው በስተቀር አምላክ ላወጣው ህግ ታዛዦች ናቸው ስለዚህም they are in a state of islam እንላለን ማለትም ለአምላክ ህግ ታዛዦች ናቸው ማለት ነው ሰው ግን አስቦ የመወሰንና የመምረጥ አቅም ተሰጥቶታል ስለዚህም አምላክ በሱ ህግ እንዲተዳደር ጋብዞታል ለዚህ የአምላክ ህግ ተገዢ ለመሆን የፈቀደን ሁሉ እኛ ሙስሊም ማለትም ታዛዥ እንለዋለን

ለምሳሌ እየሱስ ዮሀንስ ም 5 ቁ 30 ላይ እንዲህ ይላል

30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።

እንግዲህ እኛ የአምላኩን እንጂ የራሱን ፈቃድ የማይፈልግን ሁሉ ሙስሊም እንለዋለን ሌሎቹም ሙስሊም የተባሉት በዚህ ሴንስ እንጂ የሞሀመድ (ሰአወ ) ተከታይ ነበሩ ማለት አይደለም

መታዘዝ አለመታዘዝ ደግሞ ከአዳም ጀምሮ የነበረ ነገር እንጂ አዲስ ነገር አይደለም

ነብያት ደግሞ በሙሉ ታዛዦች ስለነበሩ ሙስሊም ነበሩ እንላለን

ግልጽ ካልሆነ አብራራዋለውእስቲ ደግሞ ከላይ ላሉት ነገሮች ግዜ ሳገኝ እመለሳለው

ከሰላምታ ጋርቁርአን አብርሀም መካ ውስጥ እንደነበረና ካባን እንደገነባ ይናገራል::

በመሰረቱ ከታሪክ እንደምንረዳው ካባ ከኢስላም በፊት ማለትም ሙሀመድ ከመነሳቱ በፊት ጀምሮ መካ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የጣኦት አምልኮ ስርአት ያካሂዱበት የነበረ ቦታ ነው::

ወደ ሌላ ዝርዝር ከመሄዳችን በፊት አንድ የሚነሳ ጥያቄ አለ እስቲ ያንን ለመመለስ ሞክርና እንቀትልበት::

መጽሀፍ ቅዱስ ግልጽ በሆነ መንገድ አብርሀም ኡር የተባለች ከተማ ውስጥ ይኖር እንደነበር ይናገራል:: ኡር በዛሬዋ ኢራቅ ውስጥ ትገኝ የነበረች ከተማ እንደነበረች ከታሪክ ሌላ የአርኪዮሎጂ ግኝቶችም ያስረዳሉ:: ከዚያም በምን ሁኔታ ወደ ከነአን ምድር እንደሄደና ከዚያም እንዴት የእስራኤል ብሄር እንደተመሰረተና አሁን ድረስ ያለበት ቦታ ላይ እንዴት መስፈር እንደቻሉ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል::

ወደጥያቄው
በምን መንገድ ወይም ምክንያት ነው የአብርሀም ዘሮች የሆኑት ኢስሀቅና ያእቆብ ከመካ ወጥተው ከነአን ምድር የሰፈሩትና የእስራኤል ብሄር የተወለደው? ለምን እዚያው መካ ውስጥ ሁሉም ነገር አልተከናወነም??? እንደቅዱስ ከተማ የሚታይ ከሆነ ማለት ነው::

እስቲ ይህን መልስልኝና እንነጋገር::

ሌላው ቁርአን አብርሀም ሙሴ ኢየሱስና ሀዋሪያቱ በሙሉ ሙስሊሞች እንደሆኑ መናገሩ ነው::

አንተ እንዳለከው ከሆነ ሙስሊም የሚባሉት የኢስላም ሀይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ሀይማኖቶች ውስጥ ያሉ ለአምላኮቻቸው ተገዢ የሆኑትን ሰዎች በሙሉ ነው::
እኔም ለአምላኬ ተገዢ እንደሆንኩ ስለሚሰማኝ ሙስሊም ነኝ ማለት ነው:: ሌላውም ሌላውም::

ግን ወልድያ ይህ አሳማኝ ምክያት ይሆናል ብዬ አላስብም::
ስሞች ማለትም ሀይማኖታዊ ስሞች ባብዛኛው የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው:: ካቶሊክ ማለት ዩኒቨርሳዊ የሚል አይነት ትርጉም አለው::
ኦርቶዶክስ ደግሞ እውነተኛ መንገድ ወይም እውነተኛ የሚል ትርጉም አለው:: ሌሎችም የሀይማኖት ስሞች ትርጉም አላቸው:: በትርጉሙ መሰረት ከሄድን ኦርቶዶክስ ማለት እውነተኛ በመሆኑ የእውነተኛው ሀይማኖት እርሱ መሆን ይኖርበታል ማለት ነው:: እንደዛ ነው እንደማትለኝ አምናለሁ::

በመሆኑም የኢስላም ሀይማኖት ሲመሰረት የግድ ከሌሎቹ ራሱን የሚለይበት አንድ መጠሪያ ስለሚኖረው ሀይማኖቱ ኢስላም ተባለ:: የፈለገው ትርጉም ሊኖረው ይችላል:: ሀይማኖቱ ግን ኢስላም ተብሏል ከዚያ በፊት እነ አብርሀምም ሆነ ኢየሱስ የኢስላም ሀይማኖት ተከታይ እንደነበሩ የታሪክም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ማስረጃ የለም:: የአይሁዳውያን ሀይማኖት የተለየ ስም አልነበረውም:: ነገር ግን በህዝቡ ስም የአይሁድ ሀይማኖት እየተባለ ዛሬም ድረስ ይጠራል:: ክርስትናም ሲጀምር ራሱን ከሌሎች ለመለየት ሰዎቹ ክርስቲያኖች ተባሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ላይ የተመሰረተ በመሆኑና የሱ ደቀመዛሙርት (ተማሪዎች ወይም ተከታዮች) መሆናቸውን ለማሳየት ይህን ስም መረጡ:: ሀይማኖቱም የክርስትያኖች ሀይማኖት ወይም ክርስትና ወደመባል ደረሰ ማለት ነው::

ሙስሊም የሚለውም ቃል ወይም ስም የኢስላም ሀይማኖት ተከታይ የሆነን ሰው የሚያመለክት እንጂ ሌላ የተለየ አላማ የለውም:: የስሙ ትርጉም እንደሚያመለክተው አይደለም ለማለት ነው:: ሙስሊም የሚባለው ዛሬ አላህን የሚያመልክና ሙሀመድም የሱ መልክተኛ እንደሆነ የሚያምን ሰው ነው:: በተጨማሪም የቁርአን ግዴታዎችን የሚያሙዋላ ማለትም ሶላትን በትክክል የሚሰግድና ዘካን የሚሰጥ አይነት ህጎችን የሚከተል ሰው ነው ሙስሊም የሚባለው::

ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚያሳየው ሙስሊሞች ምን ያህል ብሬይን ዎሽ እንደተደረጉ ነው::

በመሆኑም አብርሀምም ሆነ ኢስሀቅ ያእቆብም ኢየሱስም ሀዋሪያቶችም ጨርሶ ሙስሊሞች አልነበሩም:: ኢስላም ውስጥም አልነበሩም::

የአላህ ስምንም በተመለከተ የምለው አለኝ::

ከትልቅ አክብሮት ጋር

አመሰግናለሁ
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

Postby ዶር ዛክር » Fri May 10, 2013 4:11 am

አቶ አሉ ኡላ.
በ ኢስላም ወንድሜ ወልድያ እስኪመጣ ድረስ ለአሁን እኔ ብመልስልህስ ??????????????

ቁርአን አብርሀም መካ ውስጥ እንደነበረና ካባን እንደገነባ ይናገራል::

ይህ ምንም ጥርጥር የለውም :: አብራሀም በ ዜግነት ኢራቃዊ ብቻ ሳይሆን የአይሆዶች እና የ አረቦች አባት ጭምር ነው :: ስለዚህ አብራሀም የተወለደውም የኖረውም የሞተውም በአረብ ምድር ስለሆነ በሁሉም መንገድ ታሪኩ የሙስሊሞች ብቻ ነው :: አይ አይደለም ብለህ ከተከራከርከኝ ደግሞ እስኪ ሁሉም ነብያት ከኖሩበት ምድር ውስጥ ተዋህዶን የሚከተል ሰው ምሳሌ ስጠኝ ? አለ ? የለም ? ስለዚህ የ አንተ ታሪክ እውነተኛነቱ አጠራጣሪ ነው ብለህ አታስብም አቶ አሉ ኡላ ???
በመሰረቱ ከታሪክ እንደምንረዳው ካባ ከኢስላም በፊት ማለትም ሙሀመድ ከመነሳቱ በፊት ጀምሮ መካ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የጣኦት አምልኮ ስርአት ያካሂዱበት የነበረ ቦታ ነው::

ልክ ብለሀል :: አባታችን አብራሀም ካባን ካስተካከለልን ከብዙ ጊዜያት ቡሀላ ቃስ በቃስ ከጊዜ ብዛት አብራሀም ካስተማረው ትምህርት በተቃራኒው ጣኦታት እና ታቦታት ካእባ ውስጥ ተቀምጠው ይመለኩ ነበሩ :: ከዛም ነብዩ ሞሀመድ እንክዋን በ ካእባ ውስጥ ብቻ 360 ታቦታትን ሰባብረው በምትኩ አልላህ ብቻ እንዲመለክ አድርገዋል :: ልብ በል አሉ ኡላ ታቦት በቤተስኪአን ብቻ አይደለም ያለው :: የመካ ሙሽሪኮችም ታቦታትን በካእባ አስገበተው ያመልኩ ነበር ::

ወደ ሌላ ዝርዝር ከመሄዳችን በፊት አንድ የሚነሳ ጥያቄ አለ እስቲ ያንን ለመመለስ ሞክርና እንቀትልበት::

ካለኝ ጊዜ አንጻር ከብዙ በጥቂቱ የመለስኩልህ ይመስለኛል ::
መጽሀፍ ቅዱስ ግልጽ በሆነ መንገድ አብርሀም ኡር የተባለች ከተማ ውስጥ ይኖር እንደነበር ይናገራል:: ኡር በዛሬዋ ኢራቅ ውስጥ ትገኝ የነበረች ከተማ እንደነበረች ከታሪክ ሌላ የአርኪዮሎጂ ግኝቶችም ያስረዳሉ::

ቂቂቂቂቂቂ
ታድያ እውነተኛውን የ አብራሀምን ማንነት ከፈለግ ኡር መጠህ ለምን አታይም ??? የኡር እና የ አካባቢው ሰዎች አብራሀም ተዋህዶ ነው ብታላቸው በትክክል ይህ ሰው እውነት የራቀችው የዋህ ሰው ነው ይሉሀል ::
ከዚያም በምን ሁኔታ ወደ ከነአን ምድር እንደሄደና ከዚያም እንዴት የእስራኤል ብሄር እንደተመሰረተና አሁን ድረስ ያለበት ቦታ ላይ እንዴት መስፈር እንደቻሉ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል::

አሁንም ቢሆን ኢስራኤል ክርስትናን አትወክልም :: አብራሀም ክርስትናን አስተምሮ ቢሆን ኖሮ በመላው አረብ እና በ ኢስራኤል ምድር ክርስትናን እናይ ነበር ::

በምን መንገድ ወይም ምክንያት ነው የአብርሀም ዘሮች የሆኑት ኢስሀቅና ያእቆብ ከመካ ወጥተው ከነአን ምድር የሰፈሩትና የእስራኤል ብሄር የተወለደው? ለምን እዚያው መካ ውስጥ ሁሉም ነገር አልተከናወነም??? እንደቅዱስ ከተማ የሚታይ ከሆነ ማለት ነው::

እዚህ ጋ ብዙ ያልገቡህ ነገሮች እንዳሉ አስባለሁ :: ግን በአጭሩ ታድያ አብራሀም መካ ላይ የሰራው ታምር ይሄው በየአመቱ ከመላው አለም ከ 200 ሀገራት ያላነሱ ሀጃጆች መካን የሚያጨናንቁዋት አላህ አብራህምን ሰዎች ሀጅ እንዲያደርጉ ጥራ ባለው መሰረት አይደለምን ?? ታድያ የአብራሀም ትልቁ ስራ መካ ላይ የሰራው ስራ አይደለምን ??? እዚህ ላልይ ብዙ ነገሮችም የምላቸው ነበሩኝ ? እስኪ ከነአን አብራህም ምን ሰራ ????እንዴት ከመካ ስራው ጋር ልታወዳድረው ቻልክ ?

ሌላው ቁርአን አብርሀም ሙሴ ኢየሱስና ሀዋሪያቱ በሙሉ ሙስሊሞች እንደሆኑ መናገሩ ነው::

አዎ በትክክል :: መጽሀፍ ቅዱስ ግን ሌላው ቀርቶ እየሱስ እራሱ የሚከተለው እምነትን አይናገርም :: እየሱስንም ሆነ አብራሀምን ክርስትያኖች ናቸው ብለው ስም የለጠፉላቸው ሰዎች ናቸው :: እኛ ግን የነብያት እምነት ኢስላም እንደነበር አላህ ቁልጭ አርጎ ነግሮናል ::

ሰላም !!!!!!!!!!!!![/quote]
WATCH PEACE TV ..................
ዶር ዛክር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Sun Jan 08, 2012 6:28 pm

Postby አሉ-ኡላ » Sun May 19, 2013 8:18 pm

ወልድያ wrote:ሰላም አሉ ኡላ

ለጠናህ እንደምን አለህ
እስቲ አንዳንድ ነገር ልበል;

ወደ ሁለተኛው ነጥብ ስመጣ ደግሞ ቀደም ብዬ ጀምሬው ግን እልባት ሳላደርግለት ወደ ቆምኩት ሃሳብ እመጣለሁ::

ከዚህም በተጨማሪ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እንደ ዋና ዋና አድርጌ የማያቸውን አንዳንድ ነጥቦች ላንሳ::

1: ቁርአን ላይ አላህ የአብርሃም የይስሃቅ የእስማኤል የያእቆብ አምላክ የአይሁዳውያንና ቡሃላም የክርስቲያኖችም
አምላክ እንደሆነ ስሙም አላህ እንደሆነና እነሱም አላህ ብለው ይጠሩት እንደነበር ይገልጻል::
ይህ እውነትነት የሌለው ነው::

እዚህ ላይ ለጠቅላላ እውቀት አንድ ነገር ላንሳ አዳም ከተፈጠረ ምን ያህል ግዜ ሆነው ? በመጽሀፍ ቅዱስ ስሌት መሰረት 7 ሺ አመታት ተቆጥረዋል ምድር እና ሰማይም በመጽሀፍ ቅዱስ ስሌት መሰረት ከአዳም አፈጣጠር ጋር ስለሚያያዙ ከ7000 አመታት በፊት የተፈጠሩ ናቸው ! ይህ ግን አሁን ካለንበት የሳይንስ ዘመን አንጻር በጣም ትክክል ያልሆነ ቀመር ነው ምድር እና ሰማይ ከተፈጠሩ ብዙ ሚዮን አመታት ተቆጥረዋል አዳምም (የሰው ልጅ ) ምድርን ከረገጠ ሚልዮኖች አመታት ሆነዋል በነዚህ አመታት የሰው ልጆች ከአጽናፍ እስከአጽናፍ ምድርን ሞልተዋል በዋልታዎች ከሚኖሩት ኤስኪሞዎች አንስቶ በአፍሪካ ጫካዎች እርቃናቸውን እስከሚኖሩት ሰዎች በደቡብ አመሪካ ከሚገኙ ሰዎች አንስቶ በምስራቅ እስካሉት ጃፓኖችያለፉትም ያሁኖቹም የመጪዎቹም የሁሉም አምላክ አንድ እና አንድ ብቻ ነው ስለዚህ የክርስትያን እና የአይሁድ የሙስሊም አምላክ አንድ መሆኑ አይግረምህ የቡዲስቶችም የሂንዱዎችም የአምላክ የለሾቹም አምላክ አንድ ነው ሰዎቹ ማንን እያመለኩ ነው ሌላ ነገር ነው እውነተኛ አምላክ ግን አንድ ብቻ ነው ለሎቻማልክት የሉም ማለቴ አይደለም ሰዎች በተሳሳተ ጎዳና ሆነው የሚገዝዋቸው ብዙ አማልክት አሉ ህንድ ብትሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ አማልክት ታገኛለህ እነዚህ ሁሉ ግን ሊካድባቸው የሚገቡ የሀሰት አማልክት ናቸው እውነተኛ የፍጥረተ አለም ፈጣሪ የሁሉም አምላክ ግን አንድ ብቻ ነው

ሁሉም አላህ ብለው ይጠሩት ነበር የሚል ነገር ቁራን ላይ አለ ያልከውን ግን በማስረጃ አሳየኝ እንደዛ የሚል ነገር ፈጽሞ ስለሌለ

በቁራን ላይ እንደዛ ባይልም ለእውቀትህ ያህል ግን ጎግል ትራንስሌተር ውስጥ ግባና GOD የሚለውን ቃል ተመጣጣኝ ትርጉም በሂብሩ እንዲሰጥህ አድረግ ምን እንደመጣልህ ንገረኝና እንወያይበታለን እየሱስ ሙሴም የሚናገሩት ሂብሩ ነበረና የመጽሀፍ ቅዱሱም ኦሪጅናል ቅጂ መሆን የሚገባው በሂብሩ ብቻ ነበረ የአምላክ ስምም ሊሆን የሚችለው እሱ እንጂ የግሪክ ወይንም የእንጊዝኛው ወይንም ለላ ስም አይደለምና

ለሌሎቹ እመለሳለው

ሰላም ወልድያ
እያዘገየሁ በመጻፌ ይቅርታህ እንዳልተለየኝ ስለማውቅ በጣም ነው ትእግስትህን የማደንቀው::

የጀመርኩትን በዚህ ጽሁፍ ወደመቁዋጫው ላምጣውና እድሉን ላንተ ልስጥ::

የአምላክን ስም በተመለከተ ከላይ ያልኩትን ማለተም አብርኃም ይስሀቅ... ሌሎችም አላህ ብለው ይጠሩት እንደነበር ለተናገርኩት በማስረጃ አሳየኝ እንደዛ የሚል ነገር ቁርአን ውስጥ የለም ብለሀልና እስቲ በመጀመሪያ ማስረጃዬን ላቅርብልህ::
ወልድያ በእርግጠኝነት የለም ማለትህ አስገርሞኛል ምናልባትም ቁርአንን ስታነብ አላስተዋልከው እንደሆነ እንጃ እንጂ እዚህ ላይ የጠቀስኩዋቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ከአብርሀም በፊት የነበረው ኖህን ጨምሮ ዳውድም (ዳዊትም) ሱሌይማንም (ሰለሞንም).. ሌሎችም ነበሩ አላህ ብለው ይጠሩት እንደነበር ቁርአን የሚያሳየው::

ከኑህ (ኖህ) ልጀምርልህ
ሱራ 23: 23 እንዲህ ይላል:-
ኑህንም ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው ወዲያውም:- ህዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን? አላቸው::

ኖህ ነው ለህዝቦቹ አላህን ተገዙ ብሎ የተናገረው::

ኢብራሂም (አብርሀም)
29: 16-19 እንዲህ ይላል:-
ኢብራሂምንም ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ):- አላህን ተገዙ ፍሩትም...
ከአላህ ሌላ የምትገዙት ጣኦታትን ብቻ ነው ...

ኢብራሂም (አብርሀም) ነው በሱ ዘመን ለነበሩት የጣኦት አምላኪዎች የተናገረው::

21: 62-66
ኢብራሂም ሆይ በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራህ አንተ ነህን? አሉት ... ታድያ ለናንተ ምንም የማይጠቅማችሁንና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን? አላቸው::

በተጨማሪም 21: 51- 57 ተመልከተው

ያእቆብ
የዩሱፍ (የዮሴፍ) አባት የሆነው ያእቆብ ወይም እስራኤል በዩሱፍ (በዮሴፍ) መጥፋት የተሰማውን ሲገልጽ 12: 18 ላይ እንዲህ ይላል:-
በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ (አባታቸው) አይደለም ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ ስለዚህ መልካም ትእግስት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉት ላይ መታገሻው አላህ ብቻ ነው አለ::

ሙሳ (ሙሴ) እንዲህ አለ:-
7: 128
ሙሳ ለሰዎቹ:- ለአላህ ተገዙ ታገሱም ... አላቸው::

ዳውድ (ዳዊት) እና ሱሌይማንም( ሰሎሞንም) የተናገሩትን 27: 15 ላይ መመልከት ትችላለህ

ኢሳም (ኢየሱስም) አላህ ብሎ እንደጠራ በ5: 112 እና 117 ላይ ተመልከተው::

የሚበቃ ይመስለኛል::

ከሁሉም የባሰ ትልቅ ስህተት ግን በሱራ 27: 9 እና በሱራ 28: 30 ላይ ያለው ጥቅስ ነው::

ሙሴ በተራራው ላይ ቁጥቁዋጦ ሲቃጠል አይቶ ቀረብ ሲል ከእሳቱ ውስጥ አላህ እንደተናገረው የሚያሳየው ጥቅስ ነው::እንዲህ ይላል:-

እኔ የአለማት ጌታ አላህ ነኝ

ቁርአን ለሙሴም ራሱን እኔ አላህ ነኝ ብሎ አስተዋውቆታል ማለት ነው::
ይህ ውሸት ነው::
በፍጹም እኔ አላህ ነኝ ብሎ ለሙሴ አልተናገረም

አብርሀም ከነልጆቹ ሙሴና በጠቅላላው አይሁዳውያን ያመልኩት የነበረው አምላክ አላህ ይባል እንደነበር በጥንታውያን የእብራይስጥ ጽሁፎችም ሆነ በዘመናዊዎቹ ውስጥ የተጠቀሰ ነገር ካለመኖሩም በላይ ምንም አይነት ታሪክም ይህንን አያረጋግጥም::

በጥንታዊ የእብራይስጥ ጽሁፎችም ሆነ በዘመናዊዎቹም ላይ እንደሚገኘው ሙሴ ካየው እሳት ውስጥ ራሱን ያስተዋወቀው አምላክ ስሙን የነገረው በእብራይስጡ አጻጻፍ መሰረት YHWH ወይም ሲነብ ያህዌ የሚል ስሙን ነው የነገረው:: አብርሀምም ይህን ስም ያውቀውና ይጠራው እንደነበር የሚያሳይ የመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃ አለ ዘፍጥረት 22: 14 ላይ ልጁን ለመሰዋት ባቀረበበት ምትክ በጉን ከሰዋ ቡሀላ የተናገረውን ልብ በል:- እንዲህ ይላል
አብርሀምም ያንን ቦታ ያህዌ ይርኤ ብሎ ጠራው::

ያህዌ ይርኤ ማለት ያህዌ ያያል ማለት ነው::
አብርሀምም ስሙን ይጠራው የነበረው ያህዌ ብሎ እንጂ አላህ ብሎ እንዳለሆነ መመልከት ይቻላል::
አይሁዳውያን አምላካቸውን ያህዌ ብለው ይጠሩት እንደነበር ከመጽሀፍ ቅዱስ ሌላ የታሪክና እጅግ በርካታ የሆኑ የአርኪዮሎጂ ግኝቶችም ይመሰክራሉ::

አላህ የአረብኛ ቃል ነው:: al ilah ከሚሉ ቃላት የተፈጠረ ስም ነው:: al ilah ማለት the god የሚል ትርጉም ነው ያለው ይላሉ የጥናት ጽሁፎች:: ስሙንም የመካ ጣኦታውያን ለጣኦት አምላካቸው ይጠቀሙበት እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል::

አንዳንድ ምሁራን እና የጥናት ጽሁፎች አላህ የሚለው ቃል Eloah ከሚለው የእብራይስጥ ቃል የመጣ እንደሆነ ይናገራሉ::
ቁዋንቁዋ ተወራራሽነት ባህሪ ስላለውና ቃላቶች ካንዱ ቁዋንቁዋ ወደሌላው በውርስ የሚሸጋገሩ በመሆናቸው ይህ እውነት ሊሆን ይችላል:: በአማርኛችንም ቢሆን ብዙ በአረብኛ ውስጥ ያሉ ቃላቶች አሉበት ለምሳሌ ደም, ሞት,.. የሚሉት ቃላት በአረብኛውም ሆነ በአማርኛው አንድ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው:: ሌሎችንም እንዲሁ መጥቀስ ይቻላል:: ጀሀነም የሚለው የአረብኛ ቃል ከእብራይስጡ ገሀነም የሚለው ቃል የመጣ ነው::

ስለዚህ አላህ የሚለው ቃል ኤሎህ ከሚለው የእብራይስጡ ቃል መጣ ብንልም አሁንም የአምላክን የተጸዎ ስም አያመለክትም:: ኤሎህ ማለት አምላክ ማለት ነው God የሚለውም ቃል ቃል በቃል ትርጉሙ አምላክ ማለት ነው:: ይህ ቃል ለሀሰተኛውም ለእውነተኛውም አምላክ ሊሰራበት ይችላል:: ቃሉ የወል (የጋራ) ስም እንጂ የተጸውኦ (የግል መጠሪያ) ስም አይደለም::
ኢየሱስ በተሰቀለበት ጊዜ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ብሎ እንደጮኸ ይናገራል ትርጉሙም አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ማለት ነው ይላል:: አዎ ኤሎህ ማለት አምላክ ማለት ነው:: ይህ ቃል እውነተኛ ለሆነው አምላክም ለሰይጣንም ለሰዎችም ለሆድም ለገንዘብም ለእንጨትም ለዛፍም ባጠቃላይ ለሀሰጠ
ተኛ አማልክትም ይሰራበታል::
በመሆኑም አላህ የሚለው ስም የአምላክ የተጸውኦ ስም ወይም የግል መጠሪያው ስም ሳይሆን የጥንት አረቦች የሚጠቀሙበት የጣኦት መጠሪያ ነው::

በመሆኑም በእውነተኛ ልብ ለተመለከተው የእውነተኛውን አምላክ ስም በተመለከተ ቁርአን ላይ የተዘገበው በሙሉ ስህተት እንደሆነ ማየት ይቻላል::

የአምላክን ስም ለማጥፋት ብዙ ጥረት ቢደረግም በሚያስደንቅ ሁኔታ አሁንም ድረስ ያለ በመሆኑ በቅርቡ በታተመው የአማርኛ መጽሀፍ ቅዱስም ላይ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በኦሪጅናሉ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ተደርጎአል::
ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ን የእብራይስጥና ኢንግሊሽ ኢንተርሊኒየር ትርጉምን ከጉግል ላይ አውጥተህ መመልከት ትችላለህ::

በነገራችን ላይ የአማርኛው እግዚአብሄር የሚለውም ስም የአምላክ የተጸውኦ ወይም የግሉ መጠሪያ ስም አይደለም ከጊዜ ቡሀላ ሰዎች ያወጡለት ስም ነው:: የእንግሊዝኛውም ቃል God , god የአምላክ የተጸውኦ ስም አይደለም::

ያቀረብኩት በሙሉ አጠር ባለ አቀራረብ በመሆኑ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች ሊኖሩ ቢችሉና ቢነገረኝ እንደገና ማብራራት እችላለሁ::

ስለትእግስትህ በድጋሚ አመሰግናለሁ::
አሉ-ኡላ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Wed Apr 21, 2004 1:46 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests