ዲጎኔ የምጠይቅህ አንድ ነገር ስላለኝ ይህን ቤት ክፈት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ዲጎኔ የምጠይቅህ አንድ ነገር ስላለኝ ይህን ቤት ክፈት

Postby እናመሰግንሃለ » Sat Jan 12, 2013 9:01 pm

ዲጎን; ብቅ ስላልክ እግዜር ይስጥልኝ;;

እንዲህ የሚባል ትንቢት አለ:-

የሰሎሞን ቤተመቅደስ እንደገና በኢየሩሳሌም ይሠራል;; ብዙ ነገሮች በአለም ዙርያ ይፈጸማሉ;; ከሚፈጸሙት መሃል አንዱ ከኢትዮጵያ የሙሴ ጽላት ወደነበረችበት እንደምትመለስና በቃል ኪዳን ታቦትነቷ ከእሥራኤል ሕዝብ ጋር እንድትቀጥል እንደምትደረግ ነው ነው:: የትንቢቱ ጥቅስም ይሄ ነው:-

ሶፎ 3: 9-10


9 በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሐን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።

10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።


ክርስቶስም ዳግመኛ መጥቶ 1,000 ዓመት በሶሎሞን ቤተመቅደስ ይነግሳል:: ያመኑትም ከርሱ ጋር ይነግሳሉ::ይህንን ትንቢት ምን ያህል ታምንበታለህ?

?
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ዲጎኔ » Mon Jun 24, 2013 2:35 am

ሰላም ለሁላችን ለወገን እናመሰግንሀለን ጭምር
ስለመጨረሻው ዘመን ብዙ ትንቢቶች ቢኖሩም የትንቢቱ ፍጻሜ ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ የሆነው ነው በዝማሬ እናክብረው::የሺው አመት መንግስት/Millenium የሚለው በሰነመለኮት ሰዎች premilenium/post millenium and millenium ተብሎ ተከፍሏልና የትንቢቱን ጀማሪና ፈጻሚ ክርስቶስን ብቻ እንሰማ እናንግስ እናክበር እንመን::ብቻውን ያለደባል የሚያድን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ!
https://www.facebook.com/photo.php?v=57 ... =2&theater
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ሀሁሁሁ » Wed Jun 26, 2013 10:37 pm

ሰላም

ከጥያቄህ እንዳየሁት የአዲስ ኪዳን ውበት የመስቀሉ ሚስጥርን የተረዳህ አልመሰለኝም:: በኦሪት ጊዜ የነበረው ቤተመቅደሱም ሆነ ታቦቱ ሊመጣ ላለው የክርስቶስ ስራ ጥላ እንጂ አካል አልነበረም:: አካሉ ከመጣ ሚስጥሩ ከተገለጠ መጋረጃው ከተቀደደ በሁዋላ ገና ታቦቱ ይመጣል ቤተመቅደሱ ይሰራል ማለት የክርስቶስን ስራ የመስቀሉን ውበት መካድ ይሆናል::
ሀሁሁሁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 308
Joined: Fri Jan 20, 2006 11:44 pm

Re:

Postby ዲጎኔ ሞረቴ » Mon Aug 27, 2018 2:17 am

ሰላም ለወገኖች ሁሉ
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም ለዘላለም ያው ነው -ወደእብራዊያን 13፡8
ቃሉ ፈዋሽ ነውና ቃሉን በዋርካ ፎረሞች ላይ ሁሉ ዘራለሁ ክፉ አሳቹን መንፈስ በኢይሱስ ክርስቶስ ስም መታለሁ!
https://www.facebook.com/photo.php?v=57 ... =2&theater[/quote]
ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ለወገን እናመሰግንሀለን ጭምር
ስለመጨረሻው ዘመን ብዙ ትንቢቶች ቢኖሩም የትንቢቱ ፍጻሜ ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ የሆነው ነው በዝማሬ እናክብረው::የሺው አመት መንግስት/Millenium የሚለው በሰነመለኮት ሰዎች premilenium/post millenium and millenium ተብሎ ተከፍሏልና የትንቢቱን ጀማሪና ፈጻሚ ክርስቶስን ብቻ እንሰማ እናንግስ እናክበር እንመን::ብቻውን ያለደባል የሚያድን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ!
https://www.facebook.com/photo.php?v=57 ... =2&theater
ዲጎኔ ሞረቴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Thu Oct 06, 2016 3:59 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 4 guests