የሀሰት ምንጭ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የሀሰት ምንጭ

Postby ዶር ዛክር » Sat Apr 13, 2013 7:55 pm

አቶ ዘመድኩን እንዳማረብዎ ዋርካን ለቀው ቢዎጡ የተሻለ ይመስላል :: ይህን ባያደርጉ ግን ወየልዎ !!!!!!!!!!!!
WATCH PEACE TV ..................
ዶር ዛክር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Sun Jan 08, 2012 6:28 pm

Postby መርፊው » Wed Apr 17, 2013 8:31 pm

ማሳሰቢያ፡- በመጀመሪያ ደረጃ - የዚህ ፅሁፍ ዋና አላማ አንዱን ደግፎ ሌላውን ደግሞ ነቅፎ አንዱን "ለማስደሰት" እንዲሁም ሌላውን "ለማስኮረፍ" አይደለም፡፡ በተለይ የክርስትናን እምነት ትከተል ከሆነ በየደረጃው እየወረድክ በምታነበው ምሁራዊ ትንተና ልትናደድ ወይም ውስጥህ ብግን ሊል አይገባም፡፡ ትግስት ምታጣ እንዲሁም ያዙኝ ልቀቁኝ ምትል ከሆነ ይህን ፅሁፍ ባታነበው ይመረጣል፡፡ ይህ ፅሁፍ ሀይሞኖቶችን በንፅፅር ለሚያጠና እንዲሁም በዩነቨርስቲይ እና በኮሌጆች የሀይማኖት ጥናት መስክ ውስጥ ላለ ተማሪ ያለውን ተጨባጭ ነባራዊ እውነታ ያስተውል ዘንድ ግብአት ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ ነው፡፡ ማንኛውም ሙስሊም ይህን ፅሁፍ ተገን አድርጎ የሌላው እምነት ላይ ትርፍ ቃል(አላስፈላጊ) ከመናገር ይቆጠብ ዘንድ፡፡

የሐዲስ ሳይንስ እና የአዲስ ኪዳን ጉድ

ካስታወስክ በክፍል አንድ ፅሁፋችን የ ነ ካዝን ፈሊጥ አፈር አብልተናል፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ በየደረጃው እየወረድን ይህን ኢስናድ አልባ ፅሁፍ እንተነትነዋለን
ሐዲስ እና አይነቱ
- በኢስላም አንድ ሀዲስ የመጣበትን ኢስናድ ተከትሎ ሙተዋቲር( በብዙ ሰንሰለት የመጣ) አሀድ ( በአንድ ሰንሰለት የመጣ) ተብሎ ይከፈላል፡፡ ይህ የአሀድን ሐዲስ ኢስናድ ተመልክተው ሲያበቁ ሙሀዲሶች ሀዲሱን ምናልባት ገሪብ( እንግዳ) ወይም አዚዝ( ጠንካራ ) የሚል ካባን ያለብሱታል፡፡ (1)
- የአስተላላፊዎችን ተማኝነት ተከትሎ አንድ ሀዲስ ሰሂህ(ትክለኛ) ሀሰን(ጥሩ) ደኢፍ እና መውዱእ (እጅግ ደካማ ወይም የተፈበረከ) ተብሎ ይከፈላል(2)
አሁን ላይ እነዚህ ሁለቱ የሀዲስ ደረጃዎች ተከትለን ለክርስትያኑ መለኮታዊ ሆኖ የታየ ለኛ ግን እንኳን በአይናችን አለ በተባለው አጉሊ መነፅር መለኮታዊ ሆኖ ያልታየውን ፅሁፍ እንፈትሸዋለን
አዲስ ኪዳን እና ፅሁፉ
በክፍል አንድ እንዳየነው የአዲስ ኪዳን የወንጌል ፀሀፊዎች አይታወቁም(የኦርጅናሉ ፅሁፍ) ማትዮስ ማርቆስ ወይም ዮሐንስ ይሆናሉ ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገሩት ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ተከታዮች ናቸው እነዚህ ተከታዮች ደግሞ በመጀመሪያዎቹ ክርስትያኖች በአይሁድ ክርስትያኖች መናፍቃን የሚል የ እምባሻ ስም አግኝተዋል ሆን ብለው ሀይማኖቱን ለመቀየር የተነሱ ተደርገው ተወስደዋል እንዴት ተአማኒነት ይኖራቸዋል? ፡፡ የአዲስ ኪዳን ፀሀፊዎችን በተመለከተ እውቁ የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ በርት ኢህራማን እውነቱን እንዲህ ብሎ ቢገልፀው አይገርምም
"First of all none of thes gospel make any such claim about itself" (3) ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች በእየሱስ ደቀ መዝሙር ነው ሲሉ የመደቧቸው ማትዮስ እና ዮሐንስ ወንጌሎች አራሱ በውስጣዊ ትችት መሰረት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ናቸው፡፡ ይህን ስልህ እንድትደናበር ወይም እንድትደናገጥ አይደለም አእምሮህን እንድታሰራ እንጂ!!! ጠያቂ ሚጠይቀው ቀጣይ ጥያቄ እንዴት ሚለውን ሲሆን አንድ በአንድ እንመለከተዋለን
1. ማትዮስ ፃፈው የተባለው ወንጌል ማትዮስ ለመፃፉ ምን ማስረጃ አለ? ሲጀመር ማትዮስ ነው የፃፈው ያሉት ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ተከታዮች ከፅሁፉ ከምተ አመታት ቡሀላ ነው ፡፡ አንድም የአይን ምስክር የለም ሁለተኛ ደግሞ ይህን የሚያስረግጥ ኢስናድ የለም( የዘገባ ቅብብሎሽ) መስመር የለም?
2. ማትዮስ ፃፈው በተባለው ወንጌል ውስጥ እንዲህ ሚል ፅሁፍ እናገኛለን "እየሱስ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ ማትዮስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ ማስከፈያ ኬላ ተቀምጦ አየ ተከተለኝ አለው እሱም ተነስቶ ተከተለው"(4) ፡፡ ተመልከት! ፀሀፊው ማትዮስ ቢሆን ኖሮ " እየሱስ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ እኔን በቀረጥ ማስከፈያ ኬላ ተቀምጬ አየኝ ተከተለኝም አለኝ እኔም ተነስቼ ተከተልኩት" ብሎ ይነግረን ነበር፡፡ ባይሰበር!!! እዚህ ጋር የወንጌሉ ፀሀፊ ሌላ ሰው መሆኑ አእምሮውን ለሚያሰራ ሰው ሁሉ ግልፅ ነው የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቃውንትም ይህንኑ ነው ያፀደቁት (5) ፡፡ ይህ ፀሀፊ ራሱ ማንነቱ ታሪኩ ታማኝነቱ አይታወቅም ማንነቱ ከማይታወቅ ሰው የመጣውን ፅሁፍን ነው እንግዲህ እስካሁንም ድረስ መለኮታዊ የሚል ጭንብል ያጠለቁለት!!! ሐሰትም ሲፅፍ ማስተዋልን አስተውለናል የሆነ ሆኖ ይህን ጉዳይ ከክርስትና ዶክትራይን አንፃር እንመለስበታለን ………
3. ሌላው በእየሱስ ደቀ መዝሙር ተብሎ የሚል ማረጋገጫ የሌለው ድምዳሜ የተወሰደበት የዮሐንስ ወንጌል ነው፡፡ ይህ ወንጌል እውን በ ዮሐንስ ተፃፈ ለሚለው ምሁራን አልተፃፈም ብለው ምላሽ ሰተዋል ፡፡ በበኩሌ ይህን ወንጌል በዮሀንስ ለመፃፉ ከመፅሀፍ ቅዱስ ራሱ ጥያቄ ለማንሳት እገደዳለሁ ይህ ጥያቄ ዮሐንስ የዘብዴዎስ ልጅ ማርቆስ ፃፈው በተባለው ወንጌል ውስጥ ባልተረጋገጠው ታሪክ ውስጥ አሳ አጥማጅ እንደነበረ ተጠቅሷል ይህ ሰው ደግሞ ማንበብ እና መፃፍ እንደማይችል (ἀγράμματοί- አግራማቶኢ) ወይም ያልተማረ እንደነበረ ከ ሐዋርያት ስራ 4፡13 እንረዳለን በጣም አስገራሚ የሆነው ነገር ይህ ወንጌል የግሪክን ቋንቋ ትምህርት በላቀ ሰው እንደተፃፈ ምሁራን ይስማማሉ….(5) ጥያቄው ሲጀመር የእየሱስ ቋንቋ አረማይክ ነው ግሪክ አይደለም፡፡ እየሱስ ከሄደ በኋለ ዮሐንስ የግሪክን ቋንቋ በመጠቀ መልኩ ተምሮ ፃፈው እንዳየባል አንድም ታሪካዊ ማስረጃ የለም እናም ምሁራን ይህ ሁሉን በጊዜው ከነበረው ታሪካዊ ሁኔታ አንፃር አመሳክረው ሲያበቁ ጥንታዊ የተባሉት ወንጌሎች በ እየሱስ ደቀ መዝሙር እንዳልተፃፉ አስረግጠው ፅፈዋል፡፡
በመሆኑም ይህ ወንጌሎችን የፃፈው ፀሀፊ ማንነት እስካሁን አልታወቀም፡፡

-------------በጊዜው እነዚህ ፅሁፎችስ መለኮታዊ ናቸው ተብለዋል ወይ---------------
እነዚህ ፀሀፊያቸው የማይታወቁ ጥንታዊ ፅሁፎች ከእየሱስ ቡሀላ ለሁለት መቶ አመታት መለኮታዊ ተደርገው እንዳልተወሰዱ ምሁራን በአንድ ድምፅ ይስማማሉ፡፡ ለዋቢነት The Interpreter's Dictionary Of The Bible መጥቀስ ይቻላል
The original copies of the NT books have, of course, long since disappeared. This fact should not cause surprise. In the first place, they were written on papyrus, a very fragile and perishable material. In the second place, and probably of even more importance, the original copies of the NT books were not looked upon as scripture by those of the early Christian communities (6)
እዚህ ጋር ወሳኝ ጥያቄ ይነሳል እነዚህ መለኮታዊ ፅሁፎች ከነበሩ ለምን በወቅቱ በነበሩ ክርስትያኖች መለኮታዊ ተብለው አልተወሰዱም፡፡ ለምን ተአማኒነትን አላገኙም? ወይስ አንድ መፅሀፍ ወይም ፅሁፍ መለኮታዊ ሚሰኘው ፐሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች በ ጉባኤ ሲያፀድቁት ብቻ ነው? ያውም በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ፡፡ ደስ አለህም ጎረበጠህም እነዚህ ፀሀፊያቸው የማይታወቁ ፅሁፎችህ እስከ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ መለኮታዊ አልነበሩም ከዛ በኋላ ነው መለኮታዊ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ፡፡
በኢስላም አንድ ዘገባ ሙተዋቲር ከተባለ በተለያዩ ሰዎች የዘገባ ቅብብሎሽ ግና በ አንድ አቋም መምጣት አለበት ፡፡ ይህ ለመፅሀፍ ቅዱስ አይሰራም፡፡ ኢስናድ አልባ ሙተዋቲር ልንለው እንኳ አንችልም በወቅቱ እያንዳንዱ የክርስትና አንጃ የራሱን ትክክል ስለሚያረግ የትኛው ታማኝ እንደሆነ የሚያሳይ የነጥብ መረጃ የለም፡፡ ሁሉም ልክ እንደ ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትያን ሁሉ ፅሁፌ ከ እየሱስ ደቀ መዝሙር ነው ይላል ግና ኢስነድ ሚባለው ወይም ማረጋገጫ ሚሆን ነገር ወፍ ኢንጅሩ!!! ከዛ በዘለለ ስለ እየሱስ የተፃፉት ጥንታዊ ፅሁፎች ሁሉ ስምምነት የላቸውም፡፡ እነዚህ በምልህ ጥንታዊ ፅሁፎች ላይ አብዛኛው ውድቅ ተደርገዋል ምክንያቱም የእየሱስን አስተምሮ ስለሚንዱ አልፎ ተርፎ ተቀባይነት በተሰጣቸው ወይም ባገኙ ወንጌሎች ውስጥ እራሱ ግጭት ሞልቶ ተርፏል፡፡ አንዱ ከአንዱ ሲጋጭ ታየዋለህ፡፡ ይህ ደግሞ ክርስትና እምነት መሰረት ይንዳል ይህን በምሳሌ መመልት ይቻላል

1.-------መፅሀፍ ቅዱስ በመንፈስ ተፃፈ ነው የመጀመሪያው የክርስትና ዶክትራይን-------

የክርስት እምነት መሰረታዊ ዶክትራይን አንዱ እና ዋነኛው የፅሁፉ መለኮታዊነት ነው፡፡ ይህንም በተመለከተ ጴጥሮስ ፃፈው በተባለው ግና ጴጥሮስ ባልፃፈው 2ኛ ጴጥሮስ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን በኋላ እንዳታግሮሞርም እውቁና በአንደኝነት ሚጠቀሰው የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ ብሩስ መተዝገር ስለ 2ተኛ ጴጥሮስ በዚህ መልኩ የፃፈውን አንብብ
" Although the author of this letter calls himself "Simon Peter, a servant and apostle of Jesus Christ" (1:1), and makes reference to his being present at the transfiguration of Jesus Christ (1:18), several features of its style and contents have led nearly all modern scholars to regard it as the work of an unknown author of the early second century who wrote in Peter's name."(7)
ከና ከጅምሩ ጴጥሮስ ነው የፃፈው ሲል በመዋሸት በጴጥሮስ ስም የፃፈው ይህ የማይታወቅ ፀሀፊ ስለ መፅሀፍት መለኮታዊነት እንዲህ ሲል ይነገረናል፡፡
"ከሁሉ በፊት ይህን ልታውቁ ይገባቹሀል መፅሀፍ ያለው የትንቢት ቃል ሁሉ ማንም ሰው በገዛ ራሱ መንገድ ሚተረጉመው አይደለም ምክንያቱም ትምቢት ከእግዚአብሄር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፍቃድ አይደለም"(2ጴጥ 2፡20-21)
ሲጀመር ይህ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ወይም በ እግዚአብሄር መንፈስ ተመርቶ ወንጌሉን ሊፅፍ ከቻለ ለምን ጴጥሮስ ነው ወንጌሉን የፃፈው ብሎ መዋሸት አስፈለገው? ሹፍ!! የዚህ ፅሁፍ ምንጩ ውሸታም በመሆኑ ሲደመር በመረጋገጡ በሀዲስ መመዘኛ ውድቅ ከመሆን የዘለለ ቦታ የለውም፡፡ ይህ ነው እንግዲህ መለኮታዊ ሲባል ሚያዜሙለት አንዱ መፅሀፍ!!!!
አልፎ ተርፎ ጳውሎስ ፃፈው በተባለው ግን ጳውሎስ እንደፃፈው ማረጋገጫ በሌለው 2ጢሞጥዮስ 3፡16 እንዲህ የሚል ፅሁፍ ብናነብ አይገርምም
"ቅዱሳን መፅሀፍት ሁሉ የእግዚአብሄር መፅሀፍ ያለባቸው ናቸው…"(2ጢሞ፡3፡16) በመሆኑም የመጀመሪያው እና መሰረታዊው የክርስትያን ዶክትራይን መሰረቱን ያፀናው እዚህ ላይ ነው፡፡ የመፅሀፉ መለኮታዊነት፡፡ አንድ ህፃንን ልጅን ስለ ፈጣሪ ምንነት ብትጠይቀው ፈጣሪ እውነተኛ እንደሆነ ነው ሚነግርህ … እነዚህ በጭብጨባ መለኮታዊነታቸው የፀደቁ ፅሁፎች ግን ብዙውን ጊዜ እውተኛ አለመሆናቸውን እናስተውላለን ለምሳሌ 1 ጢሞጥዮስ 3፡16 መመልከት እንችላለን፡፡
ኪንጅ ጀምስ የመፅሀፍ ቅዱስ ቅጂ ትክክለኛ ነው ሲል የተጠቀመበት ጥንታዊ ቅጂ ወይም ማኑስክሪፕት Textus Receptus 1 ጢሞ 3፡16 ላይ እንዲህ ፈጣሪ በስጋ ተገለጠ ይላል ወይም በግሪኩ theos ephanerothe en sarki ይለናል፡፡ ይህ ንባብ የያዙ ማንስክሪፕቶች አሉ እንደ Prof. Raymond Brown states አብዛኛዎቹ በ 12 እና በ 13 ክ/ዘመን የተፃፉ ናቸው (8)፡፡ ፕሮፌሰር በርት ኢህራማን በበኩሉ በማኑስክሪፕቶች ላይ ይህ ለውጥ የተደረገው በሶስተኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ነግሮናል(9) በተመሳሳይ እድሜ በሶስተኛው እና በአራተኛው የነበሩ ማኑስክሪፕቶች በዚህ አንቀፅ ላይ hos ephanerothe en sarki የሚል አንቀፅ አስነብበዋል፡፡ ቲኦስ በሚለው ግሪከኛ ቃል ትርጉሙን ከወሰድነው ፈጣሪ በስጋ ተገለጠ የሚል ትርጉም ይይዝና የክርስትያኖችን የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ያፀድቃል፡፡ ግና ሆስ በሚለው ካነበብነው እሱ የሚል ትርጉም ይዞ ሲያበቃ ሙሉ በሙሉ ትርጉሙ ይለወጣል የስላሴን ፅንሰ ሀሳብም ፍሬ ያሳጣል፡፡ የሆነ ሆኖ ቲኦስ የሚለው ትርጉም ሆን ተብሎ የተጨመረ መሆኑን ምሁራን ይስማማሉ ለክፍለ ዘመናትም ሲታመንበት የነበረ የንባብ ስልት መሆኑ ነው እንግዲህ… ስንት ትውልድ በዚህ የሀሰት ትምህርት ተታሏል ማለት ነው፡፡ (10) ይህ ሆኖ ሳለ በጥንታዊ ፅሁፎች ላይ ያለው የንባብ ልዩነት የክርስትናን ዶክትራይን ላይ ለውጥ አላመጡም የሚሉ ተምረው ያልተማሩ ሚሽነሪዎችን አይቼ በጣም አዝኛለው፡፡
ሌላው የንባቡ ልዩነቶቹ የሐሳብ መቃረን ማምጣታቸው ግልፅ ነው፡፡ ለምሳሌ እየሱስ ተቆጣ እና እየሱስ ተደሰተ ማለት ፍፁም ተቃራኒ ሀሳቦች ናቸው፡፡ ከፈጣሪ የታሪክ መዛባት ይመጣል የሚለኝ ቀላጅ አይኖርም ፡፡ ምክንያቱም እንደ ክርስትና እምነት ፈጣሪ እውነተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የትኛውም አይነተት ንባብ የሚያመጣው በማኑስክሪፕቶች ላይ የሚታየው የትርጉም ለውጥ የመፅሀፍ ቅዱስ ተአማኒነትን ዜሮ ያደርገዋል ወይም አንዱ እውነተኛ ሌላውን ሀሰተኛ ያስብለዋል ይህ ነው እንግዲህ እንደክርስትያኖች መለኮታዊ ሲባል ቀን ማታ ሚሰበከው ፡፡
2----------------ተመሳሳይ ታሪክ ላይ የታየ ተቃርኖ-------------------------------

በመንፈስ ቅዱስ የተፃፈ ፅሁፍ እንግዲህ ተቃርኖ ሊኖረው አይገባም፡፡ይህን በመንፈስ ሽፋን የተገረን ወንጌል ውስጥ ተመሳሳይ ታሪክ ግን ነጭ ተቃርኖን መመልከት ከጀመርን ውለን አድረናል፡፡ ለምሳሌ ማትዮስ 19፡17 እና ማርቆስ 10፡18
ማት 19፡17 “ከዛም አንድ ሰው ወደ እየሱስ ቀርቦ መምህር ሆይ የዘላለምን ህይወት እንዳገኝ ምን መልካም( ἀγαθόν) ነገር ልስራ ሲል ጠየቀው፡፡ እየሱስም ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ መልካም የሆነ አንዱ ብቻ ነው"
ማር 10፡18 ፡፡" አንድ ሰው ወደ እርሱ እየሮጠ መጣ በፊቱም ተንበርክኮ ቸር(መልካም ἀγαθόν) መምህር ሆይ የዘላለምን ህይወትን ለመውረስ ምንማድረግ ይገባኛል አለው እየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት ለምን ቸር( ἀγαθόν) ትለኛለህ ከአንዱ እግዚአብሄር በቀር ቸር የለም …."
ምናልባት በተለያዩ ጊዜያት ይህን ታሪክ አንብበህ ከሆነ ተመሳሳይ መስሎህ እንዲሁ በዝምታ አልፈሀው ይሆናል ደግመህ ታሪኩን አንብበው ማትዮስ ላይ ሰውየው ስለ መልካም ስራ ሲጠይቀው እየሱስ መልሱ ለምን ስለመልካም ስራ ትጠይቀኛለህ መልካም አንዱ ብቻ ነው ሲል የመለሰለት፡፡ ማርቆስ ላይ ግን ሰውየው ስለመልካም ስራ ሳይሆን የጠየቀው እየሱስ ራሱን ነው መልካም ያለው፡፡ እየሱስም ምላሹ ለምን መልካም ትለኛለህ የሚል ነው፡፡ እንጂ ለምን ስለ መልካም ስራ ትጠይቀኛለህ የሚል አልነበረም፡፡ በሀዲስ ሳይንስ ከመዘነው አንዱ ፀሀፊ የማስታወስ ችሎታው እጅግ ደካማ ነው ታሪክን በማዛባት ይታወቃል ማለት ነው በመሆኑም ዘገባው ውድቅ ነው፡፡ እናም ሐቢቢ እነዚህ ወንጌልን የፃፉ ፀሀፊዎች በመንፈስ ተገፍተው ነው ማለት ሚቻለው ቸርች እንጂ ምሁራን ጋር አደለም፡፡ ኦኬ!!!! እዚህ ላይ ሁለት ነገር ማንሳት ይቻላል አንድም የሙተዋቲር ዘገባዎች መፋለስ ሁለትም የታሪክ መዛባት…….. ካዛ በዘለለ በመንፈስ ነው ተገፍተው የፃፉት የሚለውን የክርስትና አስተምህሮ ከስር መሰረቱ መናድ
3. ------------------ የእየሱስ ሽወዳ----------------------------------
ወንድማችን እና እውቁ የመፅሀፍ ቅዱስ አጥኚ ኢብኑ አሚን በዚሁ ገፅ ላይ እየሱስ ቃሉን ያጠፈበት ወይም ደንቆሮ ብለህ አትሳደብ ብሎ ራሱ የተሳደበበትን ፅሁፍን ካስታወስክ አስነብቦህ ነበር(http://www.facebook.com/photo.php?fbid= ... =1&theater)፡፡ እኔ ደግሞ የእዩስን ሽወዳ አሁን ላይ አስነብበሀለው፡፡
ዮሐንስ 7፡8-10 እንዲህ ይነበባል “እናንተ ወደ በአሉ ሂዱ ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ስላልደረሰ ወደ በአሉ አልሄድም፡፡ ይህን ብሏቸው በገሊላ ቆየ፡፡ ይሁን እንጂ ወንድሞቹ ወደ በአሉ ከሄዱ በኋላ እርሱም በግልፅ ሳይሆን በስውር ወደ በአሉ ሄደ፡፡"
ተመልከት እየሱስ ደቀመዛሙርቱን ጊዜዬ ስላልደረሰ ወደ በአሉ አልሄድም ብሎ ሸውዷቸው ሲያበቃ ተደብቆ ወደ በአሉ መሄዱ በጣም ይገርማል፡፡ አትወሽ የሚለውን የአስርቱ ትእዛዛትን የዘነጋው ይመስላል……
ሳይነሳ ማይታለፈው ወሳኝ ነጥብ በአንቀፁ ላይ ጊዜዬ ስላልደረሰ የምትለዋ ቃል በአንዳንድ ጥንታዊ ፅሁፎች ላይ ስትኖር በሌሎች ላይ የለችም ፡፡ ምሁራን በነዚህ ቅጂዎች ላይ ሆን ብለው እንደተጨመረች ነግረውን ሲያበቁ እየሱስን እየሱስን ባይሳካላቸውም ከችግር ለማውጣት ቃሏን እንደጨመሯት ጨምረው ነግረውናል፡፡ (11) በ ሁለተኛው ክፍለመን የተፃፉት p66 እና p75 ጥንታዊ መዛግብት ላይ ጊዜዬ ስላልደረሰ የምትለዋን ቃል እናገኛለን “Western” በመባልሚታወቁት ፅሁፎች ላይ ግን ልክ እንደነ א D K 1241 lat syእና c bo. እንዲሁም በቤዛንታይን እና ሲናይቲከስ ጥንታዊ መዛግብት ላይ ይህን ፅሁፍ አናገኝም ፡፡
እውቁ የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ ብሩስ መተዝገር የምለው አለኝ ይለናል ፡፡ ምን ነበር ያልከው?
“The reading οὔπω was introduced at an early date (it is attested by P,) in order to alleviate the inconsistency between ver. 8 and ver. 10.” (12)
የካቶሊኩ ፀሀፊ Stephen K. Ray እንዲህ ቢል አይገርምም
“In fact, some of the Greek New Testament manuscripts appear to have been tampered with to “cover” for Jesus’ apparent dishonesty, by adding the word “yet”, as in, “I do not go up to the destival yet”.”(13)
እንዲሁም Eugene Boring, Fred Craddock እንዲህ ሲሉ ፅፈዋል
“7:8 (yet): Some manuscripts reflect scribal efforts to keep Jesus from contradicting himself or changing his mind, by inserting “yet” (see v. 10 and NRSV note) but the original text read simply “not.”(14)
የሆነ ሆኖ ምሁራን እየነገሩህ ያሉት ጌዜዬ ስላልደረሰ የምትለዋ ቃል ጭማሪ መሆኑዋን ነው፡፡ ለምን? እየሱስን ከውሸት ለማዳን ቢሆንም ግን እውቁ የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ Kannaday እንዳለው ሙከራው አልተሳካም(15) ለምን ጊዜዬ ስላደረሰ ብሎ ሸውዷቸው ተከትሎዋቸው በድብቅ በመሄዱ……..
የሆነ ሆኖ ኦርጂናሉ ቃል እንዲህ ይነበባል “እናንተ ወደ በአሉ ሂዱ እኔ ወደ በአሉ አልሄድም፡፡ ይህን ብሏቸው በገሊላ ቆየ፡፡ ይሁን እንጂ ወንድሞቹ ወደ በአሉ ከሄዱ በኋላ እርሱም በግልፅ ሳይሆን በስውር ወደ በአሉ ሄደ፡፡"
እንደ ወንጌሉ እየሱስ መሄዱ እንዳይታወቅበት በስውር መሄዱ በውሸት ያስከስሰዋል፡፡ ተመልከት የክርስትና ጥንታዊ የተባሉ ፅሁፎች ላይ ብረዛ እና ክለሳ ሲያስተናገዱ ነበር ማለት ነው፡፡ እናም እየሱስን በውሸት የሚፈርጅ ይህ ፀሀፊው የማይታወቅ ወንጌል እንዴት በመንፈስ ቅዱስ ሊፃፍ እንደቻለ መንፈስ ስለሌለብኝ መሰለኝ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ወደፊትም አይችልም፡፡

4. ----------------የትንቢት ማዛባት--------------------------------

ማርቆስ ወንጌል 1፡2 እንዲህ ቢል አይገርምም “በነብዩ ኢሳያስ እንዲህ ብሎ ተፅፏል መንገድህን ሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ" ይህን ቃል በቃል ማንም በበኢሳያስ መፅሀፍ ውስጥ ሊሳየኝ አይችልም፡፡ ይህ አንቀፅ ቃል በቃል ሚገኘው ኦሪት ዘ ፃእት 23፡20 ላይ አንዳንዱ ኪንግ ጀምስ የመፅሀፍ ቅዱስ ቅጂን ጠቅሶ ሲያበቃ አንቀፁ የሚለን "በነብያት እንዲህ ብሎ ተፅፏል…." ሙሴ ነብይ ስለሆነ አንቀፁ ችግር የለውም ሲሉ ከችግር ለመውጣት የሚያደርጉትን ተራ ሙከራ አይተናል ይህ ግን አያስኬድም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ኪንግ ጀምስ የተጠቀማቸው ጥንታዊ መዝገቦች A, E, F, G, H, P, W, S, family 13, minuscules, Syriac ….. የተሰኙትን መዛግብትን ሲሆን እነዚህ ፅሁፎች በአራተኛው ክ/ዘመን የተፃፉ ናቸው ፡፡ ይህ በነብያት የተሰኘው ንባብ ምንጩ አራተኛው ክ/ዘመን ነው፡፡ ግና ኢሳያስ የሚለውን ፁሁፍ የያዙ መዛግብት ፡ Aleph, B, L, D, Q, family 1, 33, 205, 565, 700, 892, 1071, 1241, 1243, 2427, Itala MSS (a, aur, b, c, d, f , ff2, l, q, Vulgate, Syriac Peshitta, Syriac Palestinian, Coptic ወዘተረፈ ሲሆኑ …. እነዚህ ከመጀመሪያዎቹ ጥንታዊ ይሰኛሉ ተመልከት ይህን ጉድ አስመልክቶ Prof. Samuel Tobias Lachs’ A Rabbinic Commentary on the New Testament: በተሰኘ ፅሁፉ እንዲህ ቢለን አይገርምም
“Mark, v. 1 in Isaiah the prophet As the text stands it is incorrect, since verses are taken from Mal. 3.1 and Isa. 40.3. “The mistake may have arisen because the Malachi quotation was added later or possibly St. Mark took the texts, already combined, from a testimony-book i.e. a collection of passages from the Old Testament put together by the early Church as throwing light on the life and work of Christ.” The variant reading “the prophets” if not original was substituted to solve the problem.” (16) ይህ ደግሞ አሉ የሚባሉ ምሁራን አቋም እንደሆነም ጨምሮ ነግሮናል(17)
Wilson, R.M በፃፈው Peake’s Commentary on the Bible ላይ እንዲህ ይለናል፡፡
“2-8 The Ministry of John-The first quotation is from Mal. (3:1; cf. Exod. 23:20), hence some MSS emend to read ‘in the prophets’; whether Mk was in error or 2 is a later insertion (it is missing here from Mt. and Lk.), ‘in Isaiah the prophet’ is probably original.”(18)
The Oxford New Testament scholar Prof. C.M. Tuckett ጉዳዩን አስመልክቶ the Oxford Bible Commentary እንዲህ ማለቱ ተጠቅሷል
“They first bring on to the stage not Jesus himself but the figure of John the Baptist, and in turn john is introduced by a (mixed) OT citation. (v. 2 is a mixture of Ex. 23:20 and Mal 3:1; v.3 is from Isa 40:3. The reference to Isaiah in the introductory words in v.2 is probably a mistake.)(19)
ይህን በመደገፍ The New Interpreter’s Study Bible ፡
“Verse b might be a conflation of Mal 3:1 and Exod 23:20, though the fit is not exact. Whatever its origin, it is not from the prophet Isaiah, which raises the question of the level of scriptural knowledge held by the author of Mark or the level the author believed the audience would have. Both Matthew and Luke remove the verse from the Isaiah quotation…”(20)
ኪንግ ጀምስ ቅጂ የተጠቀማቸው ጥንታዊ ፅሁፎች ላይ የተደረገው ለውጥን ተመልክቶ ሲያበቃ የሜተዲስቱ የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ Adam Clarke እንዲህ ቢለንስ
“As it is written in the prophets. Rather, “As it is written by Isaiah the prophet.” I think this reading should be adopted, instead of that in the common text. It is the reading of several MSS. and versions of great repute, and in several of the Fathers. As this prophecy is found in Isaiah and Malachi, early scribes probably changed the reading to the prophets, that it might comprehend both.” (21)

መች እዚህ ጋር አብቅቶ Ralph Earle, Professor of New Testament at Nazarene Seminary, Harvey J.S. Blaney, Professor of Religion and Chairman of the Graduate Division of Theological Studies at Eastern Nazarene College and Charles W. Carter, Professor of Philosophy and Religion at Taylor University in their The Wesleyan Bible Commentary say: “Isaiah the prophet is the correct reading here rather than “the prophets”(KJV). It is easy to understand why some copyists would change to the latter, since the first part of the quotation (v. 2) is from Malachi 3:1. Only in verse 3 does Mark quote from Isaiah (40.3). It would appear that he had mainly in mind the words from Isaiah and then inserted the ones from Malachi as “an afterthought”. Matthew (3:3) and Luke (3:4) have only the quotation from Isaiah.”(22)
እናስ በጥንታዊ መዛግብት ውስጥ የምናያቸው የንባብ ልዩነቶች የመፃፍህን መለኮታዊነት እና የክርስትናን እምነት እንዴት አደጋ ውስጥ እንደሚከቱ የተመለከት ይመስለኛል…… ሌላው አዲስ ኪዳን ከሁሉም ጥንታዊ መዛግብት ጋር ተመሳክረዋል የሚለውን የዌብ ሚሽነሪዎች ብሂል ስህተት እንደሆነ ምሁራዊ በሆነ መልኩ ማሳየቴ ይታወሳል ይህን (http://www.facebook.com/photo.php?fbid= ... =1&theater) ይመልከቱ ከአብዛኘው ጋር ማመሳከር መለት መለኮታዊ ፅሁፍህን ሀሰት መሆኑን ይበልጥ ማረጋገጥ ማለት ነው ምክንያቱም 80-90 ፐርሰንት ሚሆኑት መዛግብት ሀሰትን ይዘዋል በሚል ሽፋን የአዲስ ኪዳን ማመሳከሪያ እንዳይሆኑ ተደርገዋል፡፡
5.----------የስላሴ አስተምሮ እና ጥንታዊ ፅሁፎች------------------------------

የ1611 ኪንግ ጀምስ ቅጂ አንደኛ ዮሐንስ መልእክት 5፡7 አንዲህ የሚል ቃል በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ቢጨምር አይገርምም፡፡
"በሰማይ ሶስት አሉ አብ ቃል መንፈስ ቅዱስ ሶስቱም አንድ ናቸው"
ይህ ቃል ከአራተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ባሉት የመፅሀፍ ቅዱስ መዛግብት ውስጥ እንዳለ ምሁራን ነግረውናል፡፡ ግን ከዛ በፊት በተገኙት መዛግብት ላይ የለም፡፡ በእነዚህ በ አራተኛው ክፍለ ዘመን መዛግብት ላይ የሚገኘው ንባብ ከላይ ያለው ሲሆን ከዛ በፊት ባሉት መዛግብት ግን ይህን ንባብ አታገኘውም፡፡ እናስ? ይህ አንቀፅ ሆን ተብሎ Math የማይፈታውን ስላሴ ለማፅደቅ የተጨመረ ነው፡፡
ይህን ጉዳይ ተበልክቶ ሲያበቃ The Interpreter‟s Dictionary of the Bible, እንዲህ ይለናል
"1 John 5:7 in the KJV reads: There are three that bear record in heaven, the Father, the Word, and the Holy Ghost: and these three are one‘ but this is an interpolation of which there is no trace before the late fourth century."(23)
Peake's Commentary on the Bible የምለው አለኝ ይለናል
The famous interpolation after ‗three witnesses‘is not printed even in RSVn, and rightly. It cites the heavenly testimony of the Father, the logos, and the Holy Spirit, but is never used in the early Trinitarian controversies. No respectable Greek MS contains it. Appearing first in a late 4th-cent. Latin text, it entered the Vulgate and finally the NT of Erasmus.(24)
ተመልከት እንግዲህ እኩል ስልጣን ያላቸውን ሶስት አማልክትን ታስተምሩ ዘንድ ሽፋን ለማግኘት እናንተው ክርስትያኖች የጨመራቹሀት አንቀፅ መሆኗ ነው፡፡ ምንም ቢጎረብጣችሁም ግን በኋላ ላይ የጨመራችሁት በመሆኑ ጥንታዊ ፅሁፉን ሚተቹ ምሁራን ከመፅሀፋችሁ ውስጥ አሽቀንጥረው ጥለውታል እናም እስካሁን ድረስ የስላሴን ፅንሰ ሀሳብ ሊያራምድ የሚችል አንድም የአዲስ ኪዳን አንቀፅ የለም…………….

6. ----------ሙተዋቲር ፅሁፎች እና አዲስ ኪዳን--------------

ይህ በብዙ መስመር በማይታወቅ ሰዎች የመጣው አዲሰ ኪዳን ወደ አምስት ሺ ጥንታዊ መዛግብትም ቢኖሩትም አንድም ያሁኑ አዲስ ኪዳን ከ አምስት ሺውም ጋር አልተመሳከረም ፡፡ ሁለትም አምስት ሺውም ኢስናድ አልባ ነው፡፡ ሶስትም እነዚህ አምስትሺ መዛግብት አብዛኛዎቹ ፀሀፊያቸው አይታወቅም አራትም በመዛግብቱ ላይ ሁነኛ ለውጥ ተደርጎባቸዋል፡፡ አምስትም አምስትሺውም በአንድ አ/ነገር አይስማሙም፡፡ ስድስትም የ አምስት ሺው ኦርጅናል የለም ኮፒውም የለም የኮፒውም ኮፒ የለም ከዛ በኋለ የመጡ ፅሁፎች ላይ የተሰተዋለው ልዩነት በመንፈስ የሚለውን የክርስትና መሰረትን መሰረቱ እንደተመታ ቤት ያፈራርሰዋል ……..
በመሆኑም ይህ በብዙ ማኑስክሪፕቶች ላይ የተስተዋለው ልዩነት እንዲሁም 80-90 ፐርሰንት ማኑስክሪፕቱ በውሸታም በቀጣፊነት መፈረጅ እንዲሁም በሁሉም ላይ ያለው ልዩነት መፅሀፍ ቅዱስ ሙተዋቲር ዘገባው የተለያየ እንዲሆን ያረገዋል አልፎ ተርፎ ሁሉም አሀድ ዘገባ ከመሆናቸው የተነሳ ገሪብ(እንግዳ) ከመሆን በሻገር ዘገባዎቹ መውዱእ እንዲባሉ ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ምን ነበር ያልከው George Arthur Buttrick
"It is safe to say that there is not one sentence in the NT in which the MS tradition is wholly uniform"(25)

7. -------------ኦርጅናል ፅሁፉ መቼም አይመለስም----------------------------
ለምን ለሚለው ጥያቄ የምሁራኑ የመጀመሪያ ምላሽ ፅሁፉ ስለሌለ ይሉናል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ቢመለስ እንኳ ከግጭት እና ከመጭበርበር አልተረፈም ከላይ እንዳየነው ትንቢትን ማዛባት ተቃርኖ ያለውን ታሪክ መዘገብ ወዘተ ---- በሶስተኛ ደረጃ የኦርጅናሉ ፀሀፊ ማን እንደሆነ አይታወቅመም ----- በአራተኛ ደረጃ ይህ ፅሁፍ መለኮታዊ ተብሎ በጥንታውያን ክርስትያኖች አልተወሰደም ምክንያቱም እነሱ ትክክለኛ ሚሉት እና ለነሹ መለኮታዊ የነበረ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላ በ ኦርቶዶክስ መሪዎች መለኮታዊነቱን ያጣ ሌላ መፅሀፍ ነበራቸው እነዚህ መፅሀፍት ደግሞ ያለምንም ምክንያት በጭብጨባ ውድቅ ተደረጉ ምክንያቱም የፕሮቶ ኦርቶዶክስን እምነት ከስር መሰረቱ ስለሚንዱ----- ይህን ርእስ በሰፊው ወደፊት እመጣበታለው የሆነ ሆኖ ኦርጅናሉን ትክክለኛ ፅሁፍ እስከ ትንሳኤ ድረስ መመለስ እንደማይቻል የግሪኩን አዲስ ኪዳን አርቃቂ እና አዘጋጅ ኮሚቴ ውስጥ አንዱ የሆነው ዴቪድ ፓርከር እንዲህ ቢል አይገርምም
"The text is changing. Every time that I make an edition of the Greek New Testament, or anybody does, we change the wording. We are maybe trying to get back to the oldest possible form but, paradoxically, we are creating a new one. Every translation is different, every reading is different, and although there’s been a tradition in parts of Protestant Christianity to say there is a definitive single form of the text, the fact is you can never find it. There is never ever a final form of the text"(26)
ግን ለምን ?
የዚህን ጥያቄ መልሱን እንዲሁም በየወንጌሉ የተስተዋለውን ልዩነት ዝርዝር … ሆን ተብሎ ለውጥ መደረጉን እና የጥንታዊ ክርስትያኖች ዋና አቋም ወዘተረፈ በሚቀጥለው ርእስ በክፍል ሶስት እያልኩ ለዛሬው እዚህ ጋር ልሰናበትህ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Fri May 24, 2013 5:50 pm

ስለ መሰቀሉና ሞቶ ስለመነሳቱ የተፃፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እውነት ከሆኑ ለምን እርስ በርስ ይጋጫሉ?^*^*^

****ምንም እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሰቀሉ፤ ከደሙ ከኃጢያት ሊያነፃ እንደመጣ በአንደበቱ በግልጽ ያብራራበት አንድም ጥቅስ ባይኖርም እንዲሁም በቦታው ኖሮ የተመለከተ ማንም የአይን እማኝ የፃፈው ጥቅስ ባይኖርም በሰሚ ሰሚ የሆነውን የስቅለት እና የትንሳኤ ሁኔታ የፃፉ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው በተለይም ኢየሱስን በአካል አይቶት እንኳን አይቶት የማያውቀው ጳውሎስ ዘግቦታል፡፡ ጳውሎስ ኢየሱስን ክርስቶስን አይቶት አያውቅም የሰማውን ነው የጻፈው አብዛኛዎቹ ደቀመዛሙርቶቹም ይህንኑ ነው ያደረጉት ለምሳሌ ሀዋርያው ሉቃስ የሰማሁትን እንዳየሁ አድርጌ እጽፋለሁ ብሏል ይህ ታዲያ ትክክለኛ ሀይማኖታዊ አካሄድ ነውን?

***በመሆኑ ይህ ዘገባ የአይን እማኝ ባለመኖሩና መረጃ አልባ በመሆኑ፤ በሰሚ ሰሚ የተፃፈ በመሆኑ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ስቅለት የተነገሩ ትቅሶች እርስ በርስ ይጋጫሉ፤ እስቲ ለአብነት ያህል እነዚህን ጥቅሶች እንመልከት፡-

≠ የማርቆስ ወንጌል 15፡25 ‹‹ኢየሱስ ሲስሉት ጊዚው ‹‹ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት›› ነበር፡፡››

≠ ዮሐንስ ወንጌል 15፡25 ‹‹የፋሲካ ዝግጅት ነበር ጊዜውም ወደ ‹‹ስድስት ሰዓት›› ነበር በዚያን ጊዜ ጰላጦስ አይሁዳውያኑን ‹‹እነሁ ንጉሳቸው›› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ‹‹ወዲ ውሰደው ወዲያ ወስደህ ስቀለው›› እሉ ጮሁ፡፡

^^ ኢየሱስ ስንት ሰዓት ነው የተሰቀለው 3 ሰዓት ዌም 6 ሰዓት?

≠ ማቴዎስ ወንጌል 27፡17 ‹‹ከገዚው ግቢ ሲወጡ ‹‹ሰምኦን›› የተባለው የቀሬና አገር ሰው አገኙና የኢየሱስን መስቀል ‹‹እንዲሸከም አደረጉት››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 19፡17 ‹‹ከዚህ በኃላ ‹‹ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ›› የራስ ቅል ወደ ሚባል ስፍራ ወጣ››

^^ መስቀሉን ማን ተሸከመ ኢየሱስ ወይም ስምኦን?

≠ ማቴዎስ ወንጌል 28፡1 ‹‹ሰንበት ካለፈ በኃላ ‹‹መቅደላዊት ማርያም ፤ ሌላይቱ ማርያም ›› መቃብሩን ለማየት ሄዱ››

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡1-2 ‹‹ሰንበት ቀን ካለፈ በኃላ ‹‹መቅደላዊት ማርያም፤ የያዕቆብ እናት ማርያም፤ ስሎሜም›› ሆነው የኢየሱስን አስክሬን ለመቀባት ሽቶ ገዙ፡፡ እሁድ ጠዋት ልክ ፀሐይ ስትወጣ ወደ መቃብሩ ሄዱ፡፡››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 20፡1 ‹‹እሁድ ጠዋት በማለዳ እና ጎህ ሳይቀድ ‹‹መቅደላዊት ማርያም›› ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች፡፡››

^^ ወደ ኢየሱስ መቃብር የሄዱት እነማን ናቸው?

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡5 ‹‹ወደ መቃብሩም በገቡ ጊዜ ነጭ ‹‹ልብስ የለበሰ ጎልማሳ›› በስተቀኝ በኩል ተቀምጦ በማየታቸው ደነገጡ››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 20፡12 ‹‹የኢየሱስም አስክሬን በነበረበት ስፍራ ‹‹ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላዕክት›› ንዱ በራስጌ አንዱ በግርጌ ተቀምጠው አየች››

^^ መቃብር ውስጥ የነበረው ማነው?‹‹ነጭ ልብስ ጎልማሳ ወይም ሁለት መላዕክት?

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡8 ‹‹ሴቶቹም በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ከመቃብር ወጥተው ሸሹ እጅግ ፈርተው ስለነበረ ‹‹ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም››

≠ የሉቃስ ወንጌል 24፡8-9 ‹‹ሴቶቹ የኢየሱስን ቃል አስታወሱ ከመቃብር ተመልሰው ‹‹ይህንን ሁላ ለአስራ አንዱና ለቀሩትም ነገሩዋቸው፡፡››

^^ ሴቶቹ ተናግረዋል ወይስ አልተናገሩም?

****ከጥቅሶቹ በግልጽ እንደምንረዳው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልም ሆነ ከሞት መነሳት ተፅፈዋል የተባሉት መረጃዎች እርስ በርሳቸው እንደሚቃረኑ ነው፡፡ እውን ስቅለቱ እውነት ቢሆን ለምን ጠንካራ መረጃ ጠፋለት? በመሰረቱ የተጋጩ ሀሳቦችን አምኖ መቀበል ልክ ነውን?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby gorgora » Fri May 24, 2013 11:59 pm

ቁራኑም ያው ነው !! ቁራን ለነቢዩ ሙሀመድ ከአላህ የተላከ ደብዳቤ ነው :: ላኪ አላህ......መለዕክተኛ ገብርኤል......ተቀባይ ነቢዩ ሙሀመድ.......ጸሀፊው/ዎቹ ሙስሊሞች:: simply ridiculous !!
gorgora
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 148
Joined: Tue Aug 10, 2004 2:37 pm
Location: Europe


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron