ያባይ ግድብ በሚሳይል እንዲመታ ተጠየቀ::

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ያባይ ግድብ በሚሳይል እንዲመታ ተጠየቀ::

Postby ክቡራን » Tue Jun 04, 2013 2:36 am

እሪ በል ያገሬ ልጅ !! ለዝርዝሩ እቺን ያበጥሩ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Tue Jun 04, 2013 2:48 am

እሪ በል ሸዋ አለ ...እስቲ ምክርዬ ይሄ ሰውዬ ምን እያለ ነው..እስኪ ፍታልኝ...በዓላህ!!
http://www.youtube.com/watch?v=HKWgVad9 ... r_embedded
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ምክክር » Tue Jun 04, 2013 8:15 am

ክቡራን wrote:እሪ በል ሸዋ አለ ...እስቲ ምክርዬ ይሄ ሰውዬ ምን እያለ ነው..እስኪ ፍታልኝ...በዓላህ!!
http://www.youtube.com/watch?v=HKWgVad9 ... r_embedded


ተረጋጋ ክቡዬ:: እሪ እያልን እየቀዘን አይሆንም:: ሊንኩን ማምጣትህ አበጀህ:: ትላንት ማታ በአረብያን ቲቪ ላይ ስከታተለው ነበር:: አረብኛ ብታነብ ኖሮ ለአረቢያን የላኩትን ኢሜይል ኮፒውን እዚህ ለጥፈህ የዋርካው ምክክር መኩሪያ መኩራሪያ መሆኑን በተረዳህ::

ወደ ቁምነገሩ እናምራ:-
በግብጽ ፕሬዘዳንት የሚመራ እንዲህ አይነት ግልጽ ውይይት በቀጥታ ለአድማጭ እንዲተላለፍ ማድረጋቸው በራሱ አንድ መልዕክት አለው:: በፍርሃት የተሸፈነ ፉከራ! ሽለላ! እናም ፉከራችንን ስሙልን ነው:: እየተከታተልናችሁ ነን...ዝም አላልንም...መጣንላችሁ ዓይነት ነው... "ውሃችን አንድ ጠብታ መነካት የለባትም": ሲል አንዱ ሌላው "የውሃ ደህንነታችንን እናስጠብቃለን" ይላል:: ይህ ናሽናል ኮንፍረንስ ጥሩ መረጃ ነው ለኢትዮጵያ:: ካስፈለገ እናጠነጥነዋለን ቃል በቃልል::

በጣም የገረሙኝና ያሳቁኝን እናካችሁ.. አንዱ ሃገር ወዳድ "እኔ ጦርነት ወዳለሁ ማለት ከጠላት ጋር:: ጦርነታችን ደግሞ ከእስራኤልና ከአሜሪካ እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር አይደለም" :D ይቺ ማዘናጊያ ናት:: እነ ወ/ሮ ማዘንጊያን ይሸውዱ እንዲያ እያሉ:: ዶሮን ሲያታልሏት ውሃ ሚሞቀው ሻወር ልትወስጂ ነው አሏት ዓይነት ነው::

ያስገረመኝ አንድ ሁለት ተሳታፊዎች ያሉት ነው:: "ኢትዮጵያ ውሥጥ ሰርገን መግባት አለብን:: ኢትዮጵያ ውሥጥ ኤምባሲ ሳይሆን የሚያስፈልገን የተደራጀ የመረጃ ድርጅት ነው:: ልክ እንደ እግር ኳስ በአርትም በውትድርናም በሁሉም መስክ ተጽእኖ ማሳደር መቻል አለብን::" ወይ ጉድ!

ጥሩ የታዘብኩትና የጠበኩት ግን ይህ ነው:: የግድ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጥታ ሰርገን ተልዕኳችንን እናሳካለን ማለት የለብንም:: በተዘዋዋሪ ብዙ መሥራት እንችላለን:: ለምሳሌ ጎረቤት አገሮች እንደ ጀቡቲ: ሶማሊያና ኤርትሪያ ጋር በጋራና በጥቅም በመስራት በእጅ አዙር ኢትዮጵያ ውሥት ጥቅማችንን ማስጠበቅ እንችላለን:: እንደምታውቁት ኢትዮጵያ የብዙ ብሔርሰብ አገር ናት:: ይህ ለኛ ጠቃሚ ነው:: :lol: ሁስኒ ሙባረክ ከእስር ቤት ሆኖ ሙርስን እያመከረ ይሆን? ይቺ እኮ የሱ ጨዋታ ናት! ለሚገባው ዜጋ ይህ ጥሩ መልዕክት አለው:: ዌክ አፕ ኮል ናት ለመላው ኢትዮጵያዊያን....የዋርካ ፒለቲከኞች ንቁ:: አትባሉ:: ይህ ተሳታፊ ድድብናውን ሲያጎላ "አፍሪካ ለእንዲህ ዓይነቱ ሥራ አመቺ ናት" ብሏል:: የቱን አትሉኝም? ጅብን ለመጉዳት አህያውን ተጠግቶ....በሌላ ትርጓሜ ባክ ዋርድ ኤንደ ፕሪሚቲቭ ኮንቲኔንት ለማለት ነው ብሎ የሚረዳም ካለ አልተሳሳተም::

ያለ ውሃ አንኖርም.....ውሃ ሕይወት ነው:: ሕዝባችን ይህን ዝም ብሎ አይመለከትም.. በተደጋጋሚ ይሰማል::

አንዳንዶች በጣም ዲፕሎማቲክ ባሕሪ አሳይተዋል:: ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ:; ያለ ነው:; እኛ ከኢትዮጵያም ሆነ ከሱዳን ሕዝብ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ ነን...እናክብራቸዋለን ዓይነት:: አንዱ ተሳታፊ ጦርነት በጭራሽ የማይታሰብ መሆኑንና ሌላ የተሻለ መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው ተናግሯል::

አንዱ በንዴት እያሳቀ ያለውን አስታወስኩ:- የኢትዮጵያ ጋዜጦች ምን እያሉ እንደሚጽፉ ታውቃላችሁ? ግብጽ ኢትዮጵያን በሚሳይልም ሆን በጀት የመምታት አቅም የላትም" የንዴት ሳቅ...ሞክሮ ቢያሳየን እንዴት በወደደ:: እግር ኳስ ሌላ ጦርነት ሌላ::

ማጠቃለያ ግምገማ ለመሥጠት ያህል:- ይህ ናሽናል ኮንፍረንስ ሪላክሴሽን የታየበት ቢሆንም በጭንቀት የተጨናነቀ ነበር:: ምን እናድርግ የሚለውን ለመመልስ አልቻሉም:: ሚስጥራዊ ውይይታቸው በግልጽ እንዲተላለፍ ማድረጋቸው ጥንካሬ አይመስለኝም:: ኮንፍረንሱ ያየው አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው:: "ናሽናል ኢንተረስት" ከዚያ አኳያ አያይዘው ስለ "ሪጅናል ኢስታቢሊቲ" አንድም ቃል የተነፈሰ የለም:: ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን መብት ያነሳ የለም:: መብቷ የሌሎችን ጥቅም እንደማይነካ የተረዳ የለም ያስረዳም እንዳለ አልሰማሁም:: ግድቡ በግብጽ ላይ የሚያስከትለው ውድቀት አለ ወይስ የለም ብለው ኢንዲቴይል አልተወያዩም:: ያው ጠቅለል አርጌ ሳየው እንደ ማስፈራሪያ ዓይነት ናት:: ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ ስላለት መብት የዓለም ሃያላን መንግሥታት ግሪን ላይ ሰተዋል:: የሚቀረን ሪጅናል ስታብሊቲ እንዲኖር...ግብጾችን የማይጎዳ መሆኑን ማስረዳትና ማሳየት ነው::

እናም ክቡዬ አይዞኝ:: ጋዜጠኞች "ባድ ኒውዝ ኢዝ ጉድ ኒውዝ" እንደሚሉት እንዲህ ዓይነቱ ዜና እንደማያስደስትህን አምናለሁ::

በኢትዮጵያዊነታችን አንድ እንሁን:: አንድ ነን እኛ!
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 290
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ክቡራን » Tue Jun 04, 2013 7:56 pm

በጣም ግሩም አናሊስስ ነው ምክክር:: አላህ ያክብርልኝ መጣሁ ወደ በኌላ ::


ምክክር ወንድሜ እንዳብራራው::

ማጠቃለያ ግምገማ ለመሥጠት ያህል :- ይህ ናሽናል ኮንፍረንስ ሪላክሴሽን የታየበት ቢሆንም በጭንቀት የተጨናነቀ ነበር :: ምን እናድርግ የሚለውን ለመመልስ አልቻሉም :: ሚስጥራዊ ውይይታቸው በግልጽ እንዲተላለፍ ማድረጋቸው ጥንካሬ አይመስለኝም :: ኮንፍረንሱ ያየው አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው :: "ናሽናል ኢንተረስት " ከዚያ አኳያ አያይዘው ስለ "ሪጅናል ኢስታቢሊቲ " አንድም ቃል የተነፈሰ የለም :: ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን መብት ያነሳ የለም :: መብቷ የሌሎችን ጥቅም እንደማይነካ የተረዳ የለም ያስረዳም እንዳለ አልሰማሁም :: ግድቡ በግብጽ ላይ የሚያስከትለው ውድቀት አለ ወይስ የለም ብለው ኢንዲቴይል አልተወያዩም :: ያው ጠቅለል አርጌ ሳየው እንደ ማስፈራሪያ ዓይነት ናት :: ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ ስላለት መብት የዓለም ሃያላን መንግሥታት ግሪን ላይ ሰተዋል :: የሚቀረን ሪጅናል ስታብሊቲ እንዲኖር ...ግብጾችን የማይጎዳ መሆኑን ማስረዳትና ማሳየት ነው ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests