ሀይማኖተኛ ነን ያላችሁ...እስቲ እንያችሁ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ሀይማኖተኛ ነን ያላችሁ...እስቲ እንያችሁ

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Jun 07, 2013 5:36 am

ሠላም ለሁላችሁም

የተከበራችሁ ውድ አማኞች/ሀይማኖተኞች ሆይ :D

የእኔ እምነት/ሀይማኖት ከአንተ እምነት/ሀይማኖት ይበልጣል......የአንተ እምነት/ሀይማኖት የተሳሳተ ነው እያላችሁ መከራችሁን ታያላችሁ......ፈሳችሁን ትረጫላችሁ :D

አንድ ጥያቄ አለኝ.....አንድ ብቻ :!: :lol:.......የየትኛውም እምነት አማኝ.......የየትኛውም ሀይማኖት ተከታይ ብትሆኑም ጥያቄው ለሁላችሁም ነው :wink:

መቼም ስለእምነታችሁ/ሀይማኖታችሁ ይህን ያህል ወገባችሁን ይዛችሁ የምትከራከሩ ከሆነ ቢያንስ የምታመልኩትን አምላክ ታውቃላችሁ ማለት ነው :wink: :lol:

ስለዚህ.......ተጠየቁ...........በፈጠራችሁ ይሁንባችሁ :wink: .....ጥያቄዬን መልሱልኝ :D ...........ፈጣሪ መኖሩን በምን አረጋገጣችሁ :?: :?: :?:

ስለትብብራችሁ አስቀድሜ አመሰግናለሁ :!:

ዳግማዊ ዋለልኝ ነኝ
በባዶ ሜዳ ሽኩቻ የሚያስቀው :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Fri Jun 07, 2013 6:00 am

ዳግማዊ
የማስረጃ አለመኖር...ያለመኖር ማስረጃ አይደለም!! ስለዚህ አንተ ለአማኞች ያቀረብከውን ጥያቄ አማኞችም አንተን ሊጠይቁህ ይችላሉ:- አንተ ፈጣሪ አለመኖሩን በምን አረጋገጥህ?
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Jun 07, 2013 6:03 am

እቴጌይት wrote:ዳግማዊ
የማስረጃ አለመኖር...ያለመኖር ማስረጃ አይደለም!! ስለዚህ አንተ ለአማኞች ያቀረብከውን ጥያቄ አማኞችም አንተን ሊጠይቁህ ይችላሉ:- አንተ ፈጣሪ አለመኖሩን በምን አረጋገጥህ?

ጥራዝ ነጠቋ እቴጌይት......ፈጣሪ ይኑር አይኑር ማስረጃ ስለሌለኝ እንደባለአእምሮ አግኖስቲክ ሆኜ ተቀምጫለሁ :lol: :lol:...የምጠይቀውም ለዚህ ነው :D .......ተመለሰልሽ :?:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Fri Jun 07, 2013 8:38 am

ዳግማዊ
ለአንተ የአንድ ነገር ሕልውና ማረጋገጫ ማስረጃ ተብሎ የሚወሰደው ምንድን ነው?

ለመነሻ ከEmpirical evidence እንጀምር?
ዩንቨርስን ስንመለከት አንድ ነገር በሆነ ነገር ካልተገፋ በራሱ ካለመንቀሳቀስ (ፖቴንሻሊቲ) ወደ መንቀሳቀስ (አክቹዋሊቲ) ሊሄድ አይችልም! ስለዚህ በመንቀሳቀስ ላይ (አክቹዋሊቲ ላይ ያለ) በሙሉ (በሌላ አነጋገር ዩንቨርስ) መጀመሪያ ያንቀሳቀሰው (የመጀመሪያ ገፊ) ነገር ሊኖረው ግድ ይላል::
Empirically አንድ ነገር ከምንም ራሱን ሊፈጥር አይችልም:: የግድ cause ያስፈልገዋል:: ለራሱ ከምንም መፈጠር cause ለመሆን ከመፈጠሩ በፊት መኖር ሊያስፈልገው ነው:: ከዛ በፊት መኖሩን cause ለማድረግ እንደገና ከዛ በፊት....... እያለ የትዬለሌ chain of causes ሊኖር አይችልም:: ስለዚህ የመጀመሪያ cause (ለራሱ cause የሌለው) ሊኖር ግድ ይላል:: ስለዚህ አሁን ኢምፔሪካሊ ከምናየው የዩንቨርስ ባህሪ በመነሳት ሰዎች የመጀመሪያ ፈጣሪ አለ ይላሉ!!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ፀዋር » Fri Jun 07, 2013 12:23 pm

አንተ የዞረብህ ወያኒእ

በመጀመሪያ ደረጃ አግኖስቲክ ማለት ጠያቂ ሳይሆን የእግዚአብሂእር መኖር ወይም አለመኖር አያገባኝም ወይም ማወቅም አልፈልግም የሚል የመሀል ሰፋሪዎች አቁአም መሆኑን ተረዳ:: እንደሰው የተሰጣቸውን ጭንቅላት ተጠቅመውና ልቦናቸውን ከፍተው እውነትን መፈለግ ስለማይችሉ ከሌሎች መልስ የሚጠባበቁ የድኩማን አቋም ነው:: ኤቲስት ነኝ በልና ጥያቄህን አስተካክል:: አግኖስቲክ ነኝ ካልክ ደግሞ እንደመሀል ሰፋሪነትህ ዝም ብለህ ዝም በል:: ቢኖር ባይኖር: ማረጋገጫ ቢሰጥህ ባይሰጥህ ምን ያረግልሀል:: ዞሮ ዞሮ መሀል ሰፋሪ ነህ::ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:
እቴጌይት wrote:ዳግማዊ
የማስረጃ አለመኖር...ያለመኖር ማስረጃ አይደለም!! ስለዚህ አንተ ለአማኞች ያቀረብከውን ጥያቄ አማኞችም አንተን ሊጠይቁህ ይችላሉ:- አንተ ፈጣሪ አለመኖሩን በምን አረጋገጥህ?

ጥራዝ ነጠቋ እቴጌይት......ፈጣሪ ይኑር አይኑር ማስረጃ ስለሌለኝ እንደባለአእምሮ አግኖስቲክ ሆኜ ተቀምጫለሁ :lol: :lol:...የምጠይቀውም ለዚህ ነው :D .......ተመለሰልሽ :?:
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Jun 07, 2013 11:47 pm

እቴጌይት

ስለዩኒቨርስም ሆነ ስለማንኛውም ነገር መነሻም ይሁን መድረሻ ካላወቅሽ እኮ አላውቅም ማለት ወይንም ገና እየተመራመርኩኝ ነው ማለት እንጂ ከመሬት ተነስተሽ ፈጣሪ አለ ብሎ መደምደም ምን የሚሉት ማስረጃ ነው :?: :lol: :lol:

ቀባጣሪው ፀዋር

ስለአግኖስቲኮች የማታውቀውን ከመቀባጠርህ በፊት አለ የምትለውን ፈጣሪህን በመጀመሪያ መኖሩን አረጋግጥ :wink: ......ከቻልክም አሹፈኝ :lol: :lol: :lol:

አግኖስቲክ ማለት ፈጣሪ ይኑር አይኑር ማስረጃ የለም የሚል እንጂ አያገባኝም የሚል አይደለም...ዲየዲየብ :lol: :lol:

እቴጌይት wrote:ዳግማዊ
ለአንተ የአንድ ነገር ሕልውና ማረጋገጫ ማስረጃ ተብሎ የሚወሰደው ምንድን ነው?

ለመነሻ ከEmpirical evidence እንጀምር?
ዩንቨርስን ስንመለከት አንድ ነገር በሆነ ነገር ካልተገፋ በራሱ ካለመንቀሳቀስ (ፖቴንሻሊቲ) ወደ መንቀሳቀስ (አክቹዋሊቲ) ሊሄድ አይችልም! ስለዚህ በመንቀሳቀስ ላይ (አክቹዋሊቲ ላይ ያለ) በሙሉ (በሌላ አነጋገር ዩንቨርስ) መጀመሪያ ያንቀሳቀሰው (የመጀመሪያ ገፊ) ነገር ሊኖረው ግድ ይላል::
Empirically አንድ ነገር ከምንም ራሱን ሊፈጥር አይችልም:: የግድ cause ያስፈልገዋል:: ለራሱ ከምንም መፈጠር cause ለመሆን ከመፈጠሩ በፊት መኖር ሊያስፈልገው ነው:: ከዛ በፊት መኖሩን cause ለማድረግ እንደገና ከዛ በፊት....... እያለ የትዬለሌ chain of causes ሊኖር አይችልም:: ስለዚህ የመጀመሪያ cause (ለራሱ cause የሌለው) ሊኖር ግድ ይላል:: ስለዚህ አሁን ኢምፔሪካሊ ከምናየው የዩንቨርስ ባህሪ በመነሳት ሰዎች የመጀመሪያ ፈጣሪ አለ ይላሉ!!
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ፀዋር » Sat Jun 08, 2013 12:17 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:አግኖስቲክ ማለት ፈጣሪ ይኑር አይኑር ማስረጃ የለም የሚል እንጂ አያገባኝም የሚል አይደለም...ዲየዲየብ :lol: :lol:

:lol: :lol: :lol:
አንተ አሳዳጊ የበደለህ እንጭጭ ሰው : ለስድብ አፍህን በከፈትክ ቁጥር ስለ ራስህ ባዶነት እያወራህ እንደሆነ ሊገባህ አይችልም መቼስ:: ባንተ ቤት አውቀህ ልብህ ውልቅ ብሏል ::

የትኛው ኤቲስት ወይም ቲስት ነው የፈጣሪን መኖር ወይም አለመኖር የሚያሳይ ማስረጃ አለኝ ያለው? አለ ብሎ የሚያምን ያምናል:: የለም ብሎ የሚያምነውም የለም ብሎ ያምናል:: ማረጋገጫ ቢኖረው እምነት ሳይሆን እውቀት ይባል ነበር:: ባለማወቅ በማመን ብቻ የተመሰረተ: ለእምነቱም በምክንያት የተመሰረተ ስለሆነ: ሰዎች በመኖሩ ወይም ባለመኖሩ ያምናሉ:: ያንተ ቢጤ የዞረበት አግኖስቲክ ደግሞ: ለመኖሩ ወይም ላለመኖሩ ማስረጃ (የለም ሳይሆን) ማቅረብ አይቻልም ብሎ ደምድሟል:: አይቻልም ብለህ ከደመደምክ ብኋላ ማስረጃ ፍለጋ መውጣት መዘላበድ ነው:: አንዳንዶቹ ደግሞ ቢኖርም ባይኖርም አስፈላጊነቱ አይታየንም ብለው አክትመዋል:: ስለዚህ መልሱን በእርግጠኝነት ከሚያቁት ጎራ ራስህን መድበህ ሳለ ያንተ መቅበዝበዝ ምን ይሉታል? ሰው ማስረጃ ይኑረው አይኑረው ምን አስጨነቀህ:?: በእርግጠኝነት መናገር የምችለው: እየጠየቅክ ያለኸው ለመማር አይደለም:: አውቃለሁ ለማለት ለመመጻደቅ ብቻ ነው:: ሌሎችንም ሰላም ለመንሳት::

ለመሆኑ ስለራስህ መኖርስ ማስረጃ ማቅረብ ትችላለህ :?: :idea: የሆንክ ጥልማሞት :D
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ዲጎኔ » Sat Jun 08, 2013 6:25 pm

ፀዋር wrote:
:lol: :lol:

:lol: :lol: :lol:
አንተ አሳዳጊ የበደለህ እንጭጭ ሰው : ለስድብ አፍህን በከፈትክ ቁጥር ስለ ራስህ ባዶነት እያወራህ እንደሆነ

የብዙሀን ዋርካዊያን ትዝብትን የሚጋራ አባባል
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sun Jun 09, 2013 6:42 am

ዲየዲየቡ ፀዋር......ምነው ተበሳጨህ :?: :wink:.....ፈጣሪህን ፈልገህ አስፈልገህ አጣኸው አይደል :?: :lol: :lol: :lol:

ፈጣሪ አለ የሚሉም ፈጣሪ ስለመኖሩ አያውቁም......ባልተጨበጠ ተረት ያምናሉ :lol: :lol: :lol: .......ኤቲዪስቶችም ፈጣሪ የለም ብለው ያምናሉ......አሁንም ማረጋገጫ የሌለው ባዶ እምነት :lol: :lol:

በዚህ አይነትማ እነአባባ ገና; ቱዝፌሪ ወዘተ አሉ ብሎ ማመንም ይቻላል...ቀላል ነገር እኮ ነው :wink: :lol: :lol: :lol: :lol:....እንዳንተ አይነቱ ዲየዲየቡም; ዘገምተኛውም ዕብዱም በባዶ ሜዳ ማመን አያቅተውም :lol: :lol: ቅቅቅቅቅቅ

እኛ አዕምሯችንን በትክክል የምንጠቀም አግኖስቲኮች ግን በተረት ተረት አናምንም........ፈጣሪ አለምም የለምም የምትል ከሆነ ለምን እንዳልክ ማስረጃህን ማቅረብ እንጂ ለምን ትጠይቃላችሁ ብሎ ብስጭት ምን አመጣው :?: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ከቻልክ አስረዳ.......ካልቻልክም ያው ተረትህን ይዘህ ጥግህን ይዘህ ራስህን ፎግር እንጂ የማውቀውን ዲየዲየብነትህን ደጋግመህ አታረጋግጥልኝ :wink: :lol: :lol:

ዳግማዊ ዋለልኝ ነኝ
ፀዋርን የአእምሮ ዘገምተኛ አድርጌ የፈጠርኩት :lol:

ፀዋር wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:አግኖስቲክ ማለት ፈጣሪ ይኑር አይኑር ማስረጃ የለም የሚል እንጂ አያገባኝም የሚል አይደለም...ዲየዲየብ :lol: :lol:

:lol: :lol: :lol:
አንተ አሳዳጊ የበደለህ እንጭጭ ሰው : ለስድብ አፍህን በከፈትክ ቁጥር ስለ ራስህ ባዶነት እያወራህ እንደሆነ ሊገባህ አይችልም መቼስ:: ባንተ ቤት አውቀህ ልብህ ውልቅ ብሏል ::

የትኛው ኤቲስት ወይም ቲስት ነው የፈጣሪን መኖር ወይም አለመኖር የሚያሳይ ማስረጃ አለኝ ያለው? አለ ብሎ የሚያምን ያምናል:: የለም ብሎ የሚያምነውም የለም ብሎ ያምናል:: ማረጋገጫ ቢኖረው እምነት ሳይሆን እውቀት ይባል ነበር:: ባለማወቅ በማመን ብቻ የተመሰረተ: ለእምነቱም በምክንያት የተመሰረተ ስለሆነ: ሰዎች በመኖሩ ወይም ባለመኖሩ ያምናሉ:: ያንተ ቢጤ የዞረበት አግኖስቲክ ደግሞ: ለመኖሩ ወይም ላለመኖሩ ማስረጃ (የለም ሳይሆን) ማቅረብ አይቻልም ብሎ ደምድሟል:: አይቻልም ብለህ ከደመደምክ ብኋላ ማስረጃ ፍለጋ መውጣት መዘላበድ ነው:: አንዳንዶቹ ደግሞ ቢኖርም ባይኖርም አስፈላጊነቱ አይታየንም ብለው አክትመዋል:: ስለዚህ መልሱን በእርግጠኝነት ከሚያቁት ጎራ ራስህን መድበህ ሳለ ያንተ መቅበዝበዝ ምን ይሉታል? ሰው ማስረጃ ይኑረው አይኑረው ምን አስጨነቀህ:?: በእርግጠኝነት መናገር የምችለው: እየጠየቅክ ያለኸው ለመማር አይደለም:: አውቃለሁ ለማለት ለመመጻደቅ ብቻ ነው:: ሌሎችንም ሰላም ለመንሳት::

ለመሆኑ ስለራስህ መኖርስ ማስረጃ ማቅረብ ትችላለህ :?: :idea: የሆንክ ጥልማሞት :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Jun 12, 2013 11:31 pm

ሠላም ዋርካውያን

ጥያቄዬን ካቀረብኩኝ በኍላ የዋርካ የሀይማኖት ስድድብም ጋብ ብሏል.......ለሁሉም ጥሩ የቤት ስራ ሰጠሁኝ መሰለኝ :lol: :lol: :lol: :lol:

ለጥያቄዬ መልሱን ካገኛችሁ ብቅ በሉ.....አደራችሁን :D :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ቀዳማይ » Sun Jun 23, 2013 3:18 pm

የራሱን መኖርና ህጉን በነብያቶች አማካኝነት አስተላልፎልናል:: ይሄንን የማያምኑ ሰዎች ብዙ እንደመሆናቸው ሪዝን አምጡ ሲሉ ይስተዋላሉ:: ፍጥረቶች ኢቮሉሽንን ሲቃወሙ ይስተዋላል:: ከፍጥረት የመጀመሪያው የሰው ልጅ አንደኛ ምሳሌ ሆነ ሊጠቀስ ይችላል:: ሰውነታችን እጅግ ጥበበኛ በሆነ መሀንዲስ የተገነባ ነው:: እንዲሁ በአክሲደንት የመጣን ቢሆን ኖሮ ሁለት አይን ሁለት እግር ሁለት ኩላሊት ..........የመሳሰሉት አይኖሩንም ነበር:: ከብሬናችን ጀምሮ እስከ ቆዳችን ድረስ በጥንቃቄ የተሰራን የክቡር ፈጣሪ እጅ ስራዎች ነን::
በእንሰሶችም ወገን እንዲሁ ነው:: ለምሳሌ ውድፒከር ወይም በአማርኛው አጠራር ግንደ ቆርቁር ግንድ በሚቆረቁር ግዜ አይኑን መጨፈን ግድ ይለዋል:: ምክንያቱም አይኑን ከገለጠ የሚጠቀመው ፎርስ በጣም ፓወር ስላለው አይኑን ሊያፈርጠው ይችላል:: ስለዚህም ነው አይነ ስውር ግንደቆርቁር የሌለው:: አይኑን መጨፈኑን ሚስ አድርጎ አያውቅምና:: እኛ የጀነቲክ አክሲደንት አይደለንም የእጅ ስራ ጥበብ ውጤት እንጂ:: ለዚህም ነው ሳይንቲስቶች ሞክረው ሞክረው መልስ ሲያጡ የሆነ ፎርስ አለ ይላሉ:: ያለ ፊልዴ ገብቼ ነው ይሄንን የጻፍኩት ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ጸጥ ስላሉ ብዬ ነው:: እጅግ ሰፊ ነገር ማቅረብ ፈልጋለው ግን ሲጀመር አጀማመሬን አካልወደድከው ግዜ ማባከን ስለሚሆን በዚሁ ላብቃ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Sun Jun 23, 2013 3:28 pm

አንድ የረሳውት ነገር ቢኖር መጽሀፍ ቅዱስን ብታነበው ብዙ ነገር ማወቅና መረዳት ትችላለህ:: ለመሆኑ እግዚአብሄር የለም ያስባለህ ፖይንት ምንይሆን? እስቲ አንተም የለም ያልክበትን አብራራልኝ ለመመለስ እንዲመቸኝ:: ሁሉም ጥያቄና መልስህ ሌላው ከተናገረው ይመስለኛል ኦርጂናል የሆነ ጥያቄህ የፈጣሪን መኖር ቢሆንም አንተም ፈጣሪ የለም ብለህ የደመደምክበትን ምክንያት አቅርብልን::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Jun 26, 2013 11:47 pm

ሠላም ቀዳማይ

ቀዳማይ wrote:የራሱን መኖርና ህጉን በነብያቶች አማካኝነት አስተላልፎልናል:: ይሄንን የማያምኑ ሰዎች ብዙ እንደመሆናቸው ሪዝን አምጡ ሲሉ ይስተዋላሉ:: ፍጥረቶች ኢቮሉሽንን ሲቃወሙ ይስተዋላል:: ከፍጥረት የመጀመሪያው የሰው ልጅ አንደኛ ምሳሌ ሆነ ሊጠቀስ ይችላል:: ሰውነታችን እጅግ ጥበበኛ በሆነ መሀንዲስ የተገነባ ነው:: እንዲሁ በአክሲደንት የመጣን ቢሆን ኖሮ ሁለት አይን ሁለት እግር ሁለት ኩላሊት ..........የመሳሰሉት አይኖሩንም ነበር:: ከብሬናችን ጀምሮ እስከ ቆዳችን ድረስ በጥንቃቄ የተሰራን የክቡር ፈጣሪ እጅ ስራዎች ነን::
በእንሰሶችም ወገን እንዲሁ ነው:: ለምሳሌ ውድፒከር ወይም በአማርኛው አጠራር ግንደ ቆርቁር ግንድ በሚቆረቁር ግዜ አይኑን መጨፈን ግድ ይለዋል:: ምክንያቱም አይኑን ከገለጠ የሚጠቀመው ፎርስ በጣም ፓወር ስላለው አይኑን ሊያፈርጠው ይችላል:: ስለዚህም ነው አይነ ስውር ግንደቆርቁር የሌለው:: አይኑን መጨፈኑን ሚስ አድርጎ አያውቅምና:: እኛ የጀነቲክ አክሲደንት አይደለንም የእጅ ስራ ጥበብ ውጤት እንጂ::

1. የሰው ልጅ 'ሁለት አይን; ሁለት እግር; ሁለት ኩላሊት' ስላለው የፈጣሪ መኖሩ ማረጋገጫነት ነው ያልከው ግልፅ አይደለም :D......እባብ ሁለት እግር ስለሌለው ፈጣሪ የለም ብልህ ትቀበላለህ :?:...ወይስ እባብ በፈጣሪ አልተፈጠረም :?: :roll: :lol:

2. ጥበበኛ መሀንዲስ የፈጠረን ከሆንን ምናለበት ሁለት ሁለት ልብና ጉበት ቢፈጥርልን ኖሮ :lol: :lol: :lol:.....እንደምሰማው ከሆነ ብዙ ሰውን የሚገለው የልብ በሽታ እንጂ የእጅና እግር ህመም አይደለም :wink: :lol: :lol:

3. ግንደቆርቁር ያልከው ምሳሌም በኢቮሊዩሽን ሊመለስ ይችላል.....በረዶ ቦታ የሚኖረው ተኩላ በጣም ፀጉራም እንደሆነው ሁሉ......ሰለዚህ ሁሉም እንስሳ እንደሚኖርበት አካባቢና የአኗኗር ሁኔታ ለመኖር የሚያስችለውን አካላዊ ለውጦች በሂደት ያዳብራል የሚለው ሀሳብ መልስ የሚሰጥህ ይመስለኛል

ለዚህም ነው ሳይንቲስቶች ሞክረው ሞክረው መልስ ሲያጡ የሆነ ፎርስ አለ ይላሉ::

መልስ ሲያጣ "የሆነ ፎርስ አለ" የሚል ሀሳብ ሳይንሳዊ አይደለም......የግል አመለካከትና መላ ምት ማስረጃ አይሆንም :!:

ያለ ፊልዴ ገብቼ ነው ይሄንን የጻፍኩት ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ጸጥ ስላሉ ብዬ ነው:: እጅግ ሰፊ ነገር ማቅረብ ፈልጋለው ግን ሲጀመር አጀማመሬን አካልወደድከው ግዜ ማባከን ስለሚሆን በዚሁ ላብቃ::

ስለዚህ ጉዳይ ማሰብ መጀመርህም ጥሩ ነው.....ግን ራስህን ለማሳመን ሳይሆን ከአስተሳሰብህና እምነትህ በላይ እውነታውን ለመፈለግ ሞክር

It's hard to accept the truth when the lies were exactly what you wanted to hear. የሚለውን አባባል ልብ ይሏል :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Jul 20, 2013 10:00 am

እንዴት ነው ነገሩ :?: :D

ፈጣሪውን/አምላኩን በእርግጠኝነት የሚያውቅና የፈጣሪውን/አምላኩን ማንነት የሚያስረዳ አንድም ዋርካዊ የለም ማለት ነውን :?: :lol:

ያሳዝናል.......ያሳዚናል........ቤታም.....በጣም.....ቤጣም.....ቢጢጣም :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ወንበዴው » Wed Jul 31, 2013 3:38 am

እግዚአብሄር የተፈጠረው በሰው ምናብ ስለሆነ የሚኖረውም እዛው ነው:: ባጭር ንግግር:-ይህ ቂላቂል አማኝ ከሌለ እግዚአብሄርም አይኖርም ማለት ነው::
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests