ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby ጌታ » Mon Aug 12, 2013 5:48 pm

http://news.yahoo.com/religious-people- ... ml#upCr476

ወንድሜ ዲጎኔ:

ይህንን ጥናት 'ተብዬ' ጉግል አድርጌ ሳይሆን እንዳው ባጋጣሚ ያሁ ፍሮንት ፔጅ ላይ አግኝቼው ላካፍልህ ወደድኩ:: ከ1921 ጀምሮ አደረግን ባሉት 'ጥናት' ኃይማኖተኞች ከኢአማኞች ያነሰ ኢንተሊጀንስ አላቸው ይላል:: ለዚህም ዋቢ አድርጎ የሚጠቅሰው በብዛት ሳይንቲስቶችን ነው:: አብዛኛው ሳይንቲስቶች ተጠራጣሪ ናቸው ይሉናል:: እንዲሁም ኢንተሊጀንት ሰዎች በትዳር የመቆየት አዝማሚያ ያሳያሉ ይላል:: አንተን ሳስብህ አማኝና ትዳር ላይ ብዙ የቆየህ ትመስለኛለህ:: ከራስህና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ይህን ጥናት እንዴት ታየዋለህ?

እነ ፀዋር ዳግማዊስ ምን ትላላችሁ?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby ዲጎኔ » Tue Aug 13, 2013 3:16 am

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው..ላይኛይቱ ጥበብ እውነተኛና ንጽህት ነች-- መጽሀፈ ምሳሌ 1:7 ያእቆብ 3:17
ብዙ ማለት አልፈልግም ስነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል ብቻ ይበቃል::በተረፈ ታላቁ ሳይንቲስት ይስሀቅ ኒውተንና የሬነሳንስና የአውሮፓ የስልጣኔ ተሀድሶ ፋና ወጊዎች ጽኑ ክርስቲያኖች እንደነበሩ ታሪክ ይመሰክራል::እዚህ አሜሪካ ሳይቀር ስደተኛውን ጦቢያን ያኮራው በጸጋው ከፕሬዚዳንት ኦባማ አድናቆት ያገኘውና ሌላዋ ከኮሜዲያን ኮስቢ ሽልማት ያገችው ማእረግ ተሸላሚ ጦቢያ አሜሪካዊት ወጣት ከጽኑ ክርስቲያን ቤተስብ እንደወጡ ስነግርህ ያገኙት ነጥብ 3.99 ነው::በጦቢያ ከመካነየሱስ ህይወት ብርሀን መሰረተ ህይወት ት/ቤቶች ያፈሯቸው የሀገሪቱ ድንቅ ምሁራን አሉን::በአሜሪካ ከክርስቲያን ትምህርት ቤቶች የሚመረቁት 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ መግባት እድል 80ከመቶ የሴኩላሩ 40 ከመቶ ነው::ለዛሬ ይብቃኝ አንብቤና ሰርች አድርጌ እመጣለሁ::
ያ የክርስቲያን ነቃፊ አፍ የሚያዘጋ እናመሰግናለን ምናለ ብቅ ቢልና ቢጨምር!

ጌታ wrote:http://news.yahoo.com/religious-people-are-less-intelligent-than-atheists--study-finds--113350723.html#upCr476
ወንድሜ ዲጎኔ:
ይህንን ጥናት 'ተብዬ' ጉግል አድርጌ ሳይሆን እንዳው ባጋጣሚ ያሁ ፍሮንት ፔጅ ላይ አግኝቼው ላካፍልህ ወደድኩ:: ከ1921 ጀምሮ አደረግን ባሉት 'ጥናት' ኃይማኖተኞች ከኢአማኞች ያነሰ ኢንተሊጀንስ አላቸው ይላል:: ለዚህም ዋቢ አድርጎ የሚጠቅሰው በብዛት ሳይንቲስቶችን ነው:: አብዛኛው ሳይንቲስቶች ተጠራጣሪ ናቸው ይሉናል:: እንዲሁም ኢንተሊጀንት ሰዎች በትዳር የመቆየት አዝማሚያ ያሳያሉ ይላል:: አንተን ሳስብህ አማኝና ትዳር ላይ ብዙ የቆየህ ትመስለኛለህ:: ከራስህና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ይህን ጥናት እንዴት ታየዋለህ?

እነ ፀዋር ዳግማዊስ ምን ትላላችሁ?
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጌታ » Tue Aug 13, 2013 2:23 pm

አመሰግናለሁ ወንድሜ ዲጎኔ:: ፈረንጆች ተመራምረው ትልቅ ሥልጣኔ ላይ የመድረሳቸውን ያህል አንዳንዴ በምርምር ሥም ለነሱ የተመቻቸውን ድምዳሜ እውነት ነው ብለን እንድንቀበል ሲሞክሩ እናስተውላለን:: እነዚሁ ተመራማሪዎች እኔና አንተን በቀለማችን ብቻ ከነሱ እጅግ ያነሰ አይኪው እንዳለን ሊነግሩንም ሞክረዋል:: ታላቁ መሪያችን ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለማሪያም 'ትግላችን' በሚለው መጽሐፉ እንደገለጻቸው 'የተማሩ መሃይሞች" እንበላቸው?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby ኤዶም* » Wed Aug 14, 2013 4:49 am

ጌታ wrote:http://news.yahoo.com/religious-people-are-less-intelligent-than-atheists--study-finds--113350723.html#upCr476

ወንድሜ ዲጎኔ:

ይህንን ጥናት 'ተብዬ' ጉግል አድርጌ ሳይሆን እንዳው ባጋጣሚ ያሁ ፍሮንት ፔጅ ላይ አግኝቼው ላካፍልህ ወደድኩ:: ከ1921 ጀምሮ አደረግን ባሉት 'ጥናት' ኃይማኖተኞች ከኢአማኞች ያነሰ ኢንተሊጀንስ አላቸው ይላል:: ለዚህም ዋቢ አድርጎ የሚጠቅሰው በብዛት ሳይንቲስቶችን ነው:: አብዛኛው ሳይንቲስቶች ተጠራጣሪ ናቸው ይሉናል:: እንዲሁም ኢንተሊጀንት ሰዎች በትዳር የመቆየት አዝማሚያ ያሳያሉ ይላል:: አንተን ሳስብህ አማኝና ትዳር ላይ ብዙ የቆየህ ትመስለኛለህ:: ከራስህና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ይህን ጥናት እንዴት ታየዋለህ?

እነ ፀዋር ዳግማዊስ ምን ትላላችሁ?

ሰላም ጌታ የጥንቱ የጠዋቱ ዘመዴ! ከዋርካ ከጠፋሁ በስንት ጊዜዬ እዚህ ላይ ያነሳሀት ጉዳይ ስባኝ ዘው ብዬ ገባሁ.....ለነገሩ የጠየቅከው በዋነኝነት ወንድማችን ዲጎኔን እንዲሁም ፀዋር ን እና ዳግማዊን ቢሆንም ያንተው የወዳጄ ቤት ነውና ሳልጠራ በመግባቴ ቀላዋጭ አልባልም ብዬ ተስፋ አረጋለሁ

መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል መሰለህ? " እግዚአብሄር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የአለምን ሞኝ ነገር መረጠ" .......ክርስትና ለማያምኑ ሰዎች ሞኝነት ነው......ያላመኑ ሰዎች አማኞችን አላዋቂዎች እና መሀይሞች ቢሏቸው አይገርመኝም........በነገራችን ላይ አለምን በአጭር ጊዜ በትምህርታቸው የሞሏት 12 የጌታ ደቀ መዛሙርት ፕሮፌሰሮች ወይም የህግ ሊቃውንት አልነበሩም.......አብዛኞቹ ተራ አሳ አጥማጆች ነበሩ........ጳውሎስን ከመሳሰሉ እጅግ ጥቂቶች በቀር አንዳቸውም የተመሰከረላቸው የህግ አዋቂዎች አልነበሩም......ጳውሎስም ቢሆን ምንም እንኳን የሚያስመካ እውቀት ቢኖረውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከማክበር በቀር.....ስለራሱ እውቀት አንድም ቀን በትምክህት ሲናገር አልተሰማም

አለም በጥበቧ እግዚአብሄርን ማወቅ ባለመቻሏ ምክንያት የእግዚአብሄር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ የአለምን ጥበብ ሞኝነት በማድረግ ገለጠው..........ወደ ጥናቱ ስንመጣ ይህንን ጥናት ያጠኑ ሰዎች ኢንተለጀንት የሚለውን ቃል እንዴት ይተረጉሙታል የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ግድ ይላል........መቼም ኢንተለጀንስ በዲግሪ ወይም በትምህርት ማዕረግ ብዛት ይለካል ብለው አያምኑም ብዬ አስባለሁ........ አንድ ሰው ኢንተለጀንት ነው ለማለት ዋናው መመዘኛው ምንድነው? .........ኢቲስቶቹ በሎጂክ ያምናሉ......አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ከሆነ ሁለት ሲቀነስ አንድ አንድ ይሆናል አይነት ሎጂክ.......ይህ አካሄድ እዚህ ድረስ ምንም ችግር የለበትም......ችግር የሚሆነው በዚህ ሎጂክ ተሞርኩዘን የእግዚአብሄርን ማንነት ተመራምረን እንደርስበታለን ብለው ሲያስቡ ነው......

የእምነት ሰው ከምንም በላይ በእግዚአብሄር ህልውና ያምናል........ይህ እምነቱ የሎጂክን ወይም የተፈጥሮን ህግ የሚጥስ አይነት ቢሆንም እንኳን ከሁለት ሺ አመት በፊት ከድሀ ቤተሰቦች በከብቶች በረት የተወለደ.....ለራሱ ማስገቢያ ጎጆ እንኳን ያልነበረው ሆም ለስ.....ተፈርዶበት....ተገርፎ....ተደብድቦ....ተስቆበት...ተተፍቶበት... በሚዘገንን ሁኔታ ከወንጀለኞች ጋ በስቅላት የተገደለ........በተውሶ መቃብር የተቀበረ! አንድ ሚስኪን አይሁዳዊ ....ዛሬ በ21 ኛው ክ/ዘመን ላይ ሆነን ....የሞተልኝ ለኔ ሲል ነው ብሎ ማመን......በእርሱ ቁስል ተፈወስኩ......የዘላለም ህይወት የማገኘው በእርሱ በኩል ብቻ ነው ....ዳግመኛ ሊወስደኝ ይመጣል ብሎ ማመን ይህ ለአንድ ኤቲስት በጣም የሚያስቅ ሞኝነት ነው.....ስለዚህ አማኙን መሀይም ማሰብ የማይችል ሰነፍ ደካማ ቢለው አይገርመኝም..........

በበኩሌ ኤቲስቶቹ ተሰብስበው በማእረግ ከሚያንበሻብሹኝ....አምላኬን አምኜ መሀይም ተብዬ ብኖር ይሻለኛል....አንድ ዘማሪ ምን አለ መሰለህ........" ሰይጣን ከሚያቆላምጠኝ......ኢየሱስ ይርገጠኝ " በነገርህ ላይ ኢየሱስ ክፉውን ዲያብሎስን ካልሆነ በቀር ማንንም አይረግጥም.......ሰይጣን ግን ኤቲስቶችን ኢንተለጀንት እያለ ያቆላምጣቸዋል........

ወገኔ !ለአለም ሞኝነት ቢመስላትም ድንቅ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ይሻልሀል........ከሞት ሊያድንህ የሚችል ብቸኛ አዳኝ እርሱ ብቻ ነው......ቢታመኑበት ታማኝ....ቢደገፉበት ድጋፍ......ቢሞረኮዙት ምርኩዝ......ቢመኩበት ትምክህት.....ቢሸሸጉበት...መሸሸግያ ...ቢጠለሉበት...መጠለያ.....ቢኖሩበት መኖርያ...........የሆነውን በዘመናት መካከል የማያረጅ የማይሻር የአለም ጥበብ ሊገልጠው የማይችል.........ሀያላን ነገስታት አዋቂዎች ሲሻሩ ሲወድቁ ሲረሱ ሲሞቱ ሲዋረዱ....እርሱ ግን አምሮና ደምቆ ለዘላለም የሚኖር ...ቅጥቅጥ ሸምበቆን የማይሰብር....የሚጤሰውን ጧፍ የማያጠፋ.....ሚስኪኑን የሚወድ......ይቅር የሚል ምህረቱ ለልጅ ልጅ የሆነ እንዳየ የማይፈርድ.......ቅን ፈራጅ እውነተኛ የሆነውን የዘላለም ሸማህን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅና መከተል ይበጅሀል

ይህን በማድረግህ አለምና ወዳጆቿ .....አላዋቂ መሀይም ---- ሊሉህ ይችሉ ይሆናል........ያሉትን ይበሉ ተዋቸው......ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል........' የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ ...የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ.......ጥበበኛ የት አለ? ጣፊስ የት አለ? የዚች አለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሄር የዚችን አለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?"

በእግዚአብሄር የተቀባ እውነተኛ ኢንተለጀንት ሰው እንዲህ ብሏል......

''የደከሙትን በቃል እደግፍ ዘንድ እግዚአብሄር የተማሩትን አፍ ሰጥቶኛል "

ሰላም!
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ጌታ » Wed Aug 14, 2013 3:53 pm

ኤዶም ወንድሜ ዋርካ ላይ ከጠፋ ሰንበትበት ያለውን ጤናማ የውይይት መንፈስ አመጣኸው - ያውም ኃይማኖት ነክ ጉዳይ ላይ! ያለህ ጠንካራ እምነት እና ስለምታምነውም ነገር ያዳበርከው ግንዛቤ አስቀንቶኛል:: በልጅነቴ መጽሐፍ ቅዱስን ያለማንም ገፋፊነት ከጫፍ እስከጫፍ ሳነብ ከክርስቶስ ቀጥሎ የማረከኝ ጠቢቡ ሰለሞን ነበር:: እግዚአብሔር ሰለሞንን በዓለም ላይ ካሉ ነገሮች ምን ልስጥህ ሲለው ሐብት አላለም - ጥበብን ነበር የጠየቀው:: አዎ ጥበብ ካለ ሁሉም ይመጣል:: የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ደግሞ እግዚአብሔርን መፍራት ነው:: (እዚህ ጋ ዳግማዊ ሲስቅ ይታየኛል)

ስለሰጠኸኝ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እያመሰገንኩ ሌሎች እንዳንተ በቀና መንፈስ የሚሉትን ለመስማትና ለመማር እጠብቃለሁ::

መልካም ጊዜ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby ዲጎኔ » Fri Aug 16, 2013 10:22 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ ወንድሞቸ ገታና ኤዶም
ይህን ድንቅ ምላሻችሁን አይቼ ፈጥኜ ለመመለስ የተለመደው ኢንተርኔት ችግር ቢያጋጥመኝም እነሆ አሁን ችያለሁ::
የሰማዩ እውቀት በምድሩ አየለካም የምድሩን እውቀት ሰጥቶ አለማችንን ለዚህ ያበቃው የሰማዩ ጥበብ ነው::
አክባሪያችሁ
ዲጎኔ ሞረቴው
ኤዶም* wrote:
ጌታ wrote:http://news.yahoo.com/religious-people-are-less-intelligent-than-atheists--study-finds--113350723.html#upCr476
ወንድሜ ዲጎኔ:
ይህንን ጥናት 'ተብዬ' ጉግል አድርጌ ሳይሆን እንዳው ባጋጣሚ ያሁ ፍሮንት ፔጅ ላይ አግኝቼው ላካፍልህ ወደድኩ:: ከ1921 ጀምሮ አደረግን ባሉት 'ጥናት' ኃይማኖተኞች ከኢአማኞች ያነሰ ኢንተሊጀንስ አላቸው ይላል:: ለዚህም ዋቢ አድርጎ የሚጠቅሰው በብዛት ሳይንቲስቶችን ነው:: አብዛኛው ሳይንቲስቶች ተጠራጣሪ ናቸው ይሉናል:: እንዲሁም ኢንተሊጀንት ሰዎች በትዳር የመቆየት አዝማሚያ ያሳያሉ ይላል:: አንተን ሳስብህ አማኝና ትዳር ላይ ብዙ የቆየህ ትመስለኛለህ:: ከራስህና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ይህን ጥናት እንዴት ታየዋለህ?

እነ ፀዋር ዳግማዊስ ምን ትላላችሁ?

ሰላም ጌታ የጥንቱ የጠዋቱ ዘመዴ! ከዋርካ ከጠፋሁ በስንት ጊዜዬ እዚህ ላይ ያነሳሀት ጉዳይ ስባኝ ዘው ብዬ ገባሁ.....ለነገሩ የጠየቅከው በዋነኝነት ወንድማችን ዲጎኔን እንዲሁም ፀዋር ን እና ዳግማዊን ቢሆንም ያንተው የወዳጄ ቤት ነውና ሳልጠራ በመግባቴ ቀላዋጭ አልባልም ብዬ ተስፋ አረጋለሁ

መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል መሰለህ? " እግዚአብሄር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የአለምን ሞኝ ነገር መረጠ" .......ክርስትና ለማያምኑ ሰዎች ሞኝነት ነው......ያላመኑ ሰዎች አማኞችን አላዋቂዎች እና መሀይሞች ቢሏቸው አይገርመኝም........በነገራችን ላይ አለምን በአጭር ጊዜ በትምህርታቸው የሞሏት 12 የጌታ ደቀ መዛሙርት ፕሮፌሰሮች ወይም የህግ ሊቃውንት አልነበሩም.......አብዛኞቹ ተራ አሳ አጥማጆች ነበሩ........ጳውሎስን ከመሳሰሉ እጅግ ጥቂቶች በቀር አንዳቸውም የተመሰከረላቸው የህግ አዋቂዎች አልነበሩም......ጳውሎስም ቢሆን ምንም እንኳን የሚያስመካ እውቀት ቢኖረውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከማክበር በቀር.....ስለራሱ እውቀት አንድም ቀን በትምክህት ሲናገር አልተሰማም

አለም በጥበቧ እግዚአብሄርን ማወቅ ባለመቻሏ ምክንያት የእግዚአብሄር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ የአለምን ጥበብ ሞኝነት በማድረግ ገለጠው..........ወደ ጥናቱ ስንመጣ ይህንን ጥናት ያጠኑ ሰዎች ኢንተለጀንት የሚለውን ቃል እንዴት ይተረጉሙታል የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ግድ ይላል........መቼም ኢንተለጀንስ በዲግሪ ወይም በትምህርት ማዕረግ ብዛት ይለካል ብለው አያምኑም ብዬ አስባለሁ........ አንድ ሰው ኢንተለጀንት ነው ለማለት ዋናው መመዘኛው ምንድነው? .........ኢቲስቶቹ በሎጂክ ያምናሉ......አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ከሆነ ሁለት ሲቀነስ አንድ አንድ ይሆናል አይነት ሎጂክ.......ይህ አካሄድ እዚህ ድረስ ምንም ችግር የለበትም......ችግር የሚሆነው በዚህ ሎጂክ ተሞርኩዘን የእግዚአብሄርን ማንነት ተመራምረን እንደርስበታለን ብለው ሲያስቡ ነው......

የእምነት ሰው ከምንም በላይ በእግዚአብሄር ህልውና ያምናል........ይህ እምነቱ የሎጂክን ወይም የተፈጥሮን ህግ የሚጥስ አይነት ቢሆንም እንኳን ከሁለት ሺ አመት በፊት ከድሀ ቤተሰቦች በከብቶች በረት የተወለደ.....ለራሱ ማስገቢያ ጎጆ እንኳን ያልነበረው ሆም ለስ.....ተፈርዶበት....ተገርፎ....ተደብድቦ....ተስቆበት...ተተፍቶበት... በሚዘገንን ሁኔታ ከወንጀለኞች ጋ በስቅላት የተገደለ........በተውሶ መቃብር የተቀበረ! አንድ ሚስኪን አይሁዳዊ ....ዛሬ በ21 ኛው ክ/ዘመን ላይ ሆነን ....የሞተልኝ ለኔ ሲል ነው ብሎ ማመን......በእርሱ ቁስል ተፈወስኩ......የዘላለም ህይወት የማገኘው በእርሱ በኩል ብቻ ነው ....ዳግመኛ ሊወስደኝ ይመጣል ብሎ ማመን ይህ ለአንድ ኤቲስት በጣም የሚያስቅ ሞኝነት ነው.....ስለዚህ አማኙን መሀይም ማሰብ የማይችል ሰነፍ ደካማ ቢለው አይገርመኝም..........

በበኩሌ ኤቲስቶቹ ተሰብስበው በማእረግ ከሚያንበሻብሹኝ....አምላኬን አምኜ መሀይም ተብዬ ብኖር ይሻለኛል....አንድ ዘማሪ ምን አለ መሰለህ........" ሰይጣን ከሚያቆላምጠኝ......ኢየሱስ ይርገጠኝ " በነገርህ ላይ ኢየሱስ ክፉውን ዲያብሎስን ካልሆነ በቀር ማንንም አይረግጥም.......ሰይጣን ግን ኤቲስቶችን ኢንተለጀንት እያለ ያቆላምጣቸዋል........

ወገኔ !ለአለም ሞኝነት ቢመስላትም ድንቅ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ይሻልሀል........ከሞት ሊያድንህ የሚችል ብቸኛ አዳኝ እርሱ ብቻ ነው......ቢታመኑበት ታማኝ....ቢደገፉበት ድጋፍ......ቢሞረኮዙት ምርኩዝ......ቢመኩበት ትምክህት.....ቢሸሸጉበት...መሸሸግያ ...ቢጠለሉበት...መጠለያ.....ቢኖሩበት መኖርያ...........የሆነውን በዘመናት መካከል የማያረጅ የማይሻር የአለም ጥበብ ሊገልጠው የማይችል.........ሀያላን ነገስታት አዋቂዎች ሲሻሩ ሲወድቁ ሲረሱ ሲሞቱ ሲዋረዱ....እርሱ ግን አምሮና ደምቆ ለዘላለም የሚኖር ...ቅጥቅጥ ሸምበቆን የማይሰብር....የሚጤሰውን ጧፍ የማያጠፋ.....ሚስኪኑን የሚወድ......ይቅር የሚል ምህረቱ ለልጅ ልጅ የሆነ እንዳየ የማይፈርድ.......ቅን ፈራጅ እውነተኛ የሆነውን የዘላለም ሸማህን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅና መከተል ይበጅሀል

ይህን በማድረግህ አለምና ወዳጆቿ .....አላዋቂ መሀይም ---- ሊሉህ ይችሉ ይሆናል........ያሉትን ይበሉ ተዋቸው......ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል........' የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ ...የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ.......ጥበበኛ የት አለ? ጣፊስ የት አለ? የዚች አለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሄር የዚችን አለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?"

በእግዚአብሄር የተቀባ እውነተኛ ኢንተለጀንት ሰው እንዲህ ብሏል......

''የደከሙትን በቃል እደግፍ ዘንድ እግዚአብሄር የተማሩትን አፍ ሰጥቶኛል "

ሰላም!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ኤዶም* » Sat Aug 17, 2013 6:36 am

ሰላም ወገኖቼ

ወገኖች ስለ እውነት ሲያወሩ ከመስማት በቀር ደስ የሚል ነገር ምን አለ ? ይህን ትሬድ ወድጄዋለሁ.....ብቻውን ጥበበኛና አዋቂ ስለ ሆነው ስለ ጌታችንና አምላካችን ያየነውን የቀመስነውን እና የሰማነውን መመስከራችንንን እንቀጥል

ወንድም ጌታ በልጅነትህ ያነበብከው መጽሀፍ ቅዱስን አሁንም እንድታነበው አበረታታሀለሁ.....ተዝቆ የማያልቅ ጥበብና ዘላለማዊ ህይወት ሞልቶበታል......መፅሀፍ ቅዱስ እንደሌላ መፅሀፍ አይደለም.........በማስተዋል መነበብ ይኖርበታል......በልጅነትህ ታሪኩን አንበህ የወደድከው ጠቢቡ ሰለሞን......በመፅሀፈ መክብብ እንዲህ ብሏል.......' የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ' አዎን አንድ ቀን ደስ አይሉም የምንላቸው አይነት ቀናት ይመጣሉ.....ያኔ ምንም ነገር ለማረግ ፈረንጆቹ እንደሚሉት '' ቱ ሌት '' ይሆናል ........በነገራችን ላይ ጥበበኛው ሰለሞን ጥበቡ አላዳነውም.......መጨረሻው አላማረም........እንደ አባቱ እንደ ዳዊት መንገዱን ከአምላኩ ጋር ስላላደረገ .....ሴቶችን አብዝቶ ከመውደዱ የተነሳ ከምንም አንስቶ ያንን ሁሉ ሀይል ጥበብና ዝና ሰጥቶ ጠላቶቹን ሁሉ አስገብሮለት በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ እንዲነግስ ያደረገውን አምላኩን እግዚአብሄርን ከድቶ የአህዛብን አማልክት አምልኮ ነው ያለፈው......

ሰለሞን ከዝናው ከጉልበቱ ከሀብቱና ከጥበቡ ጋር አልፏል..........ከሱ በፊትም ሆነ በሁዋላ የተነሱ ጥበበኞችም እንዲሁ ከነ ጥበባቸው አልፈዋል........ባንድ ወቅት አለምን ያንቀጠቅጡ የነበሩ ሀያላን ተረስተዋል ....ነገስታት ተረስተዋል......በእውቀታቸው ከዳር እስከ ዳር የተጨበጨበላቸው አዋቂ ምሁራን ሳይንቲስቶች አልፈዋል.....ለዘላለም የማያልፍ ...ጥበቡ እጅግ የማይነገር እፁብ ድንቅ የሆነ.....እግዚአብሄር አለምን የፈጠረበት ቃሉ ግን ለዘላለም አያልፍም........እርሱን መደገፍ ማስተዋል ነው

በሰለሞን ጥቅስ ልሰናበት......

"" የሚሰማኝም በእርጋታ ይቀመጣል
ከመከራ ስጋትም ያርፋል ""

ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ!!!!!
ሰላም!
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Re: ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby ፀዋር » Thu Aug 22, 2013 12:15 am

ሠላም ጌታ: ለተሳታፊዎችና ለእድምተኞች :D

እኔ በአጠቃላይ IQ በሚባል መመዘኛ አላምንም:: ብዙ ችግር ያለበት ስለሆነ:: ከዚህ በፊት ጥቁሮች በተፈጥሮ ከነጮች ያነሰ IQ አላቸው የሚል ዘረኛ ጥናት አጋጥሞኝ ነበር:: ሰውዬው እንደ እብድ ታዬ እንጂ የተቀበለው "ሰው" አልነበረም:: ዛሬም እብዶች መሆን አለባቸው እንደዚህ አይነት ጥናት አድርገው አንኢቲካል የሆነ መደመደምያ የሚሰጡ::

ሲጀመር ማን ከማን ጋር ነው የሚወዳደረው? አብዛኛው ኤቲስት የተማረ ነው:: ከተማረ ብኋላ ነው ኤቲስትነቱን የሚያውጀው:: አማኙ ደግሞ የተማረንም ያልተማረንም ያካትታል:: ሳምፕል ሲወሰድ ሁለቱም እኩል የሆነ ቤንችማርክ ከሌላቸው ማወዳደር አትችልም:: ወይም የጥናትህ ውጤት ባያዝድ ይሆናል:: ሌላው አንድን ባዮሎጂስት ከአንድ ትዩሎጂስት ዲያቆን ጋር በምን መልኩ ነው ልታወዳድር የምትችለው? ሳይንሳዊና ኮመን ሰንስ ጥያቄዎችን ብቻ እያቀረብክ ወይስ ሜታፊዚካል ጥያቄዎችን ጨምረህ? ከላይ ኤዶም* እንዳለው አሁን የሚጠቀሙበት የIQ መመዘኛ ስልት ሳይንሳዊ ስልትን የተከተለ ነው:: ሳይንስ ደግሞ ሜታፊዝክስ ጋር አይግባባም:: ስለዚህ ጥያቄው ሁሉንም ያማከለ ካልሆነ ውጤቱ አሁንም ባያዝድ ነው የሚሆነው:: ሌሎች ብዙ ህጸጾችን መጥቀስ ይቻላል: ለአብነት ግን እነዚህ ሁለቱ ይበቃሉ:: በምንም መስፈርት የጌታን ትክክለኛ አይኪው መመዘን አይቻለኝም:: እንደምንም ብመዝን እንኳን ከዲጎኔ አይኪው ወይም ከራሴ አይኪው ጋር ማወዳደር አልችልም:: የወተትን ንጣት ከማሲንቆ ድምጽ ጋር ማወዳደር አይቻልም::

ኤቲስቶች ክርስቶስ እንደ ሶቅራጠስ ሰው ነው ብለው ያምናሉ:: ነብዩ መሐመድ ሰው ነው ብለው ያምናሉ:: በታሪክ የነዚህን ሁለት ግለሰቦች ያህል በዓለም ተጽኖ መፍጠር የቻለ ሰው እንደሌለም ጠንቅቀው ያውቃሉ:: ሶቅራጥሥ አልፈጠረም:: አንስታይን አልፈጠረም:: ለምን? ሰዎች ስንባል ከፍተኛ አይኪው ካለው ይልቅ ዝቅተኛ አይኪው ያለውን መከተል ስለሚቀለን? የነዚህን "ግለሰቦች" አይኪው እንዴት ነው መመዘን የሚቻለው? በጣም ከባድ ነው:: አንዳንዴ የሰዎችን አይኪው መመዘን የሚችለው ሰው ያልሆነ ከሰው በላይ ኢንተለጀንስ ያለው መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ::

የእምነት ልዩነቶች አሉን:: ከኤቲስቶች ጋር የማልስማማበት ነጥብ አለኝ:: ከአማኞች ጋር የማልስማማበት ነጥብ አለኝ:: ማንኛችን ትክክል እንደምንሆን ግዜ ይፈታዋል:: አማኙ ከኔ በታች: የማያምነው ደግሞ ከኔ በላይ አይኪው አለው ብዬ መናገርና መቀበል ግን አልችልም:: የእምነታችን ልዩነት: ነገሮችን የምንረዳበት መንገድ ልዩነት እንጂ የጉብዝና(ስንፍና) ወይም የመረዳት አቅማችን ልዩነት ነው ብዬ አላምንም:: የመረዳታችን ልዩነት ደግሞ በጭንቅላታችን አቅም ብቻ ሳይሆን በብዙ ሁነቶችና ነገሮችን ጭምር የሚገለጽ እንደሆነ ሳይንስ ራሱ አስተምሮናል:: እና ባጭሩ ሳጠቃልለው "ግብዝነት ነው" ብዬ ነው::

ሠላም!
ጌታ wrote:http://news.yahoo.com/religious-people-are-less-intelligent-than-atheists--study-finds--113350723.html#upCr476

ወንድሜ ዲጎኔ:

ይህንን ጥናት 'ተብዬ' ጉግል አድርጌ ሳይሆን እንዳው ባጋጣሚ ያሁ ፍሮንት ፔጅ ላይ አግኝቼው ላካፍልህ ወደድኩ:: ከ1921 ጀምሮ አደረግን ባሉት 'ጥናት' ኃይማኖተኞች ከኢአማኞች ያነሰ ኢንተሊጀንስ አላቸው ይላል:: ለዚህም ዋቢ አድርጎ የሚጠቅሰው በብዛት ሳይንቲስቶችን ነው:: አብዛኛው ሳይንቲስቶች ተጠራጣሪ ናቸው ይሉናል:: እንዲሁም ኢንተሊጀንት ሰዎች በትዳር የመቆየት አዝማሚያ ያሳያሉ ይላል:: አንተን ሳስብህ አማኝና ትዳር ላይ ብዙ የቆየህ ትመስለኛለህ:: ከራስህና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ይህን ጥናት እንዴት ታየዋለህ?

እነ ፀዋር ዳግማዊስ ምን ትላላችሁ?
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby እናመሰግንሃለ » Fri Aug 23, 2013 9:53 pm

ጉዳዩ የኢንቴሊጀንስ (በጠቅላላው: የአእምሮ ምጡቅነት) ልዩነት ሳይሆን: የፍጥነትና የብልጣ ብልጥነት ጉዳይ ነው [ከውስጥ ዓመጸኛነቱ እንዳለ ሆኖ]:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ ሲል ተናግሯል:

"ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ መጋቢ የነበረው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ በእርሱ ዘንድ። ይህ ሰው ያለህን ይበትናል ብለው ከሰሱት። ጠርቶም። ይህ የምሰማብህ ምንድር ነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ አለው። መጋቢውም በልቡ። ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፥ መለመንም አፍራለሁ። ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ አለ። የጌታውንም ባለ ዕዳዎች እያንዳንዳቸውን ጠርቶ የፊተኛውን። ለጌታዬ ምን ያህል ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ማድጋ ዘይት አለ። ደብዳቤህን እንካ ፈጥነህም ተቀምጠህ አምሳ ብለህ ጻፍ አለው። በኋላም ሌላውን። አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ጫን ስንዴ አለ። ደብዳቤህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ አለው። ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው: የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።" (ሉቃ 16: 1-8)

የዚህ ዓለም ልጆች (በእግዚአብሔር የማያምኑ) ከብርሃን ልጆች (በእግዚአብሔር ከሚያምኑ) ይልቅ: ለትውልዳቸው [ይህ ቃል በአትኩሮት ይታይ] ይልቅ ልባሞች ናቸው--- ማለትም: ምንም አመጸኛ ቢሆኑ: ዘመኑ የሚጠይቀውን ነገር አይተው: ራሳቸውን ከጥፋት ለማዳንና ከሰው በላይ ለመሆን: በአስተሳሰባቸውና በርእዮተ ዓለማቸው እጥፍ ግልብጥ ማለት ይችላሉ:: በዚያም ተመስግነውና ተሞግሰው ያልፋሉ:: በአመጻ ገንዘብ ላይም ይሰለጥናሉ:: በእውነተኛው ገንዘብ ላይ (ማለትም በእግዚአብሔር መንግሥት) ግን ቦታ የላቸውም:-

" እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው። እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል? በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል?" (ማቴ 16: 9-12)

ማለትም: እንዴት በዚህ ዓለም ያሉ ሰዎች ለራሳቸው ደኅንነት እንኳ ሲሉ በዓመጻ ገንዘብ ላይ እጥፍ ግልብጥ ሲሉና ጥሩ ስም የሚያስሰጣቸውን ሥራ ሲሠሩ እያያችሁ: እኔ በምነግራችሁ በእውነተኛው ትምህርትና ገንዘብ (ርስት መንግሥተ ሰማያት) ለመሰልጠን እንዴት ተሳናችሁ? እነርሱ በሰብአዊነት በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅትነት በምናምን ስማቸውን ሲያስጠሩና ዓመጻቸውን ደብቀው ቢያንስ ከላይ ከላይ ሲያስመስሉ: እናንተ: አይሁድ: ሃይማንተኞች የተባላችሁ ፈሪሳውያን እንዴት በትክክሉ ምጽዋት አድርጋችሁ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የመፈለግ አዝማሚያ አልታይባችሁ አለ?

ሶ! ጉዳዩ ኢንቴሊጀንስ ሳይሆን: ብልጣ ብልጥነት ነው:: ውስጣዊ ዓላማውም ጊዜያዊ የበላይነት ስለሆነ: ለዚያው ለትውልዳቸው ብቻ ካስኬዳቸውና ከሰራ ይቀበሉታል እንጂ በሁዋላ ደግሞ ጥለውት እጥፍ ይላሉ:: የብርሃን ልጆች ግን መስሎ መታየት ሳይሆን ሆኖ መገኘት ስለሚጠበቅባቸው: ያውም በሰው መለኪያ ሳይሆን: በእግዚአብሔር ሚዛን ስለሆነ: ቀድሞውኑ ነገር: በሰዎች ዘንድ: ወይ ተገፍተው: ወይ ተረስተው: ወይ ከቁምነገር ሳይቆጠሩ: ተቅበዝብዘው: አዝነው: ስሜታቸው ተነክቶ: ተሸናፊዎች መስለው [ሆነውም] በዚህች ምድር ይኖራሉ:: ወደመቃብርም; ከነጅልነታቸውና ከነተገፊነታቸው ይወርዳሉ:: በምድር የሚተዉአት ጅል መሳይ የየዋሕነት ፍሬ ግን የሆነ ቀን አንዱ ያነሳትና ለፍሬ ያበቃታል:: ሌሎችም ይመጣሉ: ይጠቀሙባታል:: ......ጌታ እስኪፈርድ ድረስ: የዚህ ዓለም ልጆች: ለትውልዳቸው: ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ሆነው: ይኖራሉ:: ይህን እውነታ ጌታ ክርስቲያኖች እንዲቀበሉትና እንዲያውቁት: ከዚህ ዓለምም ምንም እንዳይፈልጉና ተጠሪነታቸው ለርሱ ብቻ እንዲሆን ይመክራቸዋል:: እስማኤል በይስኃቅ ላይ እየሳቀና እየኮረኮመው ይኖር ዘንድ ግድ ነው:: አንዴ በደካማ አቅሙ: አንዴ በየዋህ ጅልነቱ እያላገጠበት ማለት ነው::
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ዲጎኔ » Sat Aug 24, 2013 1:08 am

ሰላም ለሁላችን
ውድ እናመሰግንሀለን ዛሬ በስንበቱ ዋዜማ እጅግ መልካም ትንታኔ ያጻፈህ ቅዱስ አምላክ ይባርክህ::እባካህን እንዲህ ብቅ እያልክ ከቃሉ የሚስማማውን አቅርበልን ጆሮ ያለው ይስማ ይላልና ታላቁ መጽሀፍ::
ጸዋርም የሰጠው እንዲሁ የሚደገፍ ነው:: የዋርካው ጌታ አሁን አይን ገላጭ ምላሾች እንዳገኘ ተስፋ አደርጋለሁ::
ዲጎኔ ሞረቴው ወደዚህ ታላቅ የጥበብ ቤት ግቡ ከሚለው አንጋፋ ዘመናዊ ትምህርት ቤት መካነኢየሱስ አምስት ኪሎ

እናመሰግንሃለ� wrote:ጉዳዩ የኢንቴሊጀንስ (በጠቅላላው: የአእምሮ ምጡቅነት) ልዩነት ሳይሆን: የፍጥነትና የብልጣ ብልጥነት ጉዳይ ነው [ከውስጥ ዓመጸኛነቱ እንዳለ ሆኖ]:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ ሲል ተናግሯል:

"ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ መጋቢ የነበረው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ በእርሱ ዘንድ። ይህ ሰው ያለህን ይበትናል ብለው ከሰሱት። ጠርቶም። ይህ የምሰማብህ ምንድር ነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ አለው። መጋቢውም በልቡ። ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፥ መለመንም አፍራለሁ። ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ አለ። የጌታውንም ባለ ዕዳዎች እያንዳንዳቸውን ጠርቶ የፊተኛውን። ለጌታዬ ምን ያህል ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ማድጋ ዘይት አለ። ደብዳቤህን እንካ ፈጥነህም ተቀምጠህ አምሳ ብለህ ጻፍ አለው። በኋላም ሌላውን። አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ጫን ስንዴ አለ። ደብዳቤህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ አለው። ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው: የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።" (ሉቃ 16: 1-8)

የዚህ ዓለም ልጆች (በእግዚአብሔር የማያምኑ) ከብርሃን ልጆች (በእግዚአብሔር ከሚያምኑ) ይልቅ: ለትውልዳቸው [ይህ ቃል በአትኩሮት ይታይ] ይልቅ ልባሞች ናቸው--- ማለትም: ምንም አመጸኛ ቢሆኑ: ዘመኑ የሚጠይቀውን ነገር አይተው: ራሳቸውን ከጥፋት ለማዳንና ከሰው በላይ ለመሆን: በአስተሳሰባቸውና በርእዮተ ዓለማቸው እጥፍ ግልብጥ ማለት ይችላሉ:: በዚያም ተመስግነውና ተሞግሰው ያልፋሉ:: በአመጻ ገንዘብ ላይም ይሰለጥናሉ:: በእውነተኛው ገንዘብ ላይ (ማለትም በእግዚአብሔር መንግሥት) ግን ቦታ የላቸውም:-

" እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው። እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል? በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል?" (ማቴ 16: 9-12)

ማለትም: እንዴት በዚህ ዓለም ያሉ ሰዎች ለራሳቸው ደኅንነት እንኳ ሲሉ በዓመጻ ገንዘብ ላይ እጥፍ ግልብጥ ሲሉና ጥሩ ስም የሚያስሰጣቸውን ሥራ ሲሠሩ እያያችሁ: እኔ በምነግራችሁ በእውነተኛው ትምህርትና ገንዘብ (ርስት መንግሥተ ሰማያት) ለመሰልጠን እንዴት ተሳናችሁ? እነርሱ በሰብአዊነት በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅትነት በምናምን ስማቸውን ሲያስጠሩና ዓመጻቸውን ደብቀው ቢያንስ ከላይ ከላይ ሲያስመስሉ: እናንተ: አይሁድ: ሃይማንተኞች የተባላችሁ ፈሪሳውያን እንዴት በትክክሉ ምጽዋት አድርጋችሁ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የመፈለግ አዝማሚያ አልታይባችሁ አለ?

ሶ! ጉዳዩ ኢንቴሊጀንስ ሳይሆን: ብልጣ ብልጥነት ነው:: ውስጣዊ ዓላማውም ጊዜያዊ የበላይነት ስለሆነ: ለዚያው ለትውልዳቸው ብቻ ካስኬዳቸውና ከሰራ ይቀበሉታል እንጂ በሁዋላ ደግሞ ጥለውት እጥፍ ይላሉ:: የብርሃን ልጆች ግን መስሎ መታየት ሳይሆን ሆኖ መገኘት ስለሚጠበቅባቸው: ያውም በሰው መለኪያ ሳይሆን: በእግዚአብሔር ሚዛን ስለሆነ: ቀድሞውኑ ነገር: በሰዎች ዘንድ: ወይ ተገፍተው: ወይ ተረስተው: ወይ ከቁምነገር ሳይቆጠሩ: ተቅበዝብዘው: አዝነው: ስሜታቸው ተነክቶ: ተሸናፊዎች መስለው [ሆነውም] በዚህች ምድር ይኖራሉ:: ወደመቃብርም; ከነጅልነታቸውና ከነተገፊነታቸው ይወርዳሉ:: በምድር የሚተዉአት ጅል መሳይ የየዋሕነት ፍሬ ግን የሆነ ቀን አንዱ ያነሳትና ለፍሬ ያበቃታል:: ሌሎችም ይመጣሉ: ይጠቀሙባታል:: ......ጌታ እስኪፈርድ ድረስ: የዚህ ዓለም ልጆች: ለትውልዳቸው: ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ሆነው: ይኖራሉ:: ይህን እውነታ ጌታ ክርስቲያኖች እንዲቀበሉትና እንዲያውቁት: ከዚህ ዓለምም ምንም እንዳይፈልጉና ተጠሪነታቸው ለርሱ ብቻ እንዲሆን ይመክራቸዋል:: እስማኤል በይስኃቅ ላይ እየሳቀና እየኮረኮመው ይኖር ዘንድ ግድ ነው:: አንዴ በደካማ አቅሙ: አንዴ በየዋህ ጅልነቱ እያላገጠበት ማለት ነው::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Re: ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sun Aug 25, 2013 7:08 am

ሠላም ታላቅ ሰው ጌታ

አጥኚዎቹ በጥናታቸው የኃይማኖተኞችን እና የኢአማኞችን ኢንተለጀንስ ለማመዛዘን የተጠቀሙበትን ዘዴ ለማየትና ስለሁለቱ ኢንተለጀንስ ለማውራት ጥናቱን ማየት ይጠይቃል:: ስለዚህ ጥናቱን እስካየው ድረስ ለጊዜው ይህን ሀሳብ ላቆየው

ነገር ግን አንድ ግልፅ የሆነ ጉዳይ አለ:: ሀይማኖተኞች እምነትን በተመለከተ የሚመሩት በአእምሮቸው ሳይሆን በ'ቀልባቸው" ነው :D......እከሌ እንደዚህ አለ.......እከሌ የሚባለው መፅሀፍ ላይ እንዲህ ይላል ....ወዘተ እያሉ ማመን ብቻ ነው......ደሞ ለማመን :wink:.... የምታምኑት ፈጣሪ የታለ ስትላቸውም የሆነ ጥቅስ ጎትተው ያመጡልሀል :lol: .......ኢአማኞች ግን አዕምሯቸውን ይጠቀማሉ.......ለማመን በቅድሚያ መኖር አለመኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል ይላሉ.......ስለዚህ በአእምሮና በጨበጣ ከሚንቀሳቅሱ ሰዎች መሀል በአጠቃላይ ብናየው የትኛው የተሻለ ኢንተለጀንስ ሊኖረው እንደሚችል ለመገመት ጥናትም ላያስፈልገው ይችላል :wink:

በተረፈ ዋናውን አጀንዳ ለመሸፋፈን; የሚስማማቸውን የመፅሀፍ ቅዱስ; ቅዱስ ቁራን; ጊታ ምናምን ወይንም ሼክስፒር እንዳለው :D እያሉ ባዶ ጥቅስ መደርደር ሳይሆን አለ የሚሉትን ፈጣሪ ያመላክቱንና ኢንተለጀንሳቸውን እንመስክርላቸው :wink: :lol:

ማሳሰቢያ: "ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን ናቸው" እንዳትሉኝ ብቻ...አደራችሁን :lol: :lol:ጌታ wrote:http://news.yahoo.com/religious-people-are-less-intelligent-than-atheists--study-finds--113350723.html#upCr476

ወንድሜ ዲጎኔ:

ይህንን ጥናት 'ተብዬ' ጉግል አድርጌ ሳይሆን እንዳው ባጋጣሚ ያሁ ፍሮንት ፔጅ ላይ አግኝቼው ላካፍልህ ወደድኩ:: ከ1921 ጀምሮ አደረግን ባሉት 'ጥናት' ኃይማኖተኞች ከኢአማኞች ያነሰ ኢንተሊጀንስ አላቸው ይላል:: ለዚህም ዋቢ አድርጎ የሚጠቅሰው በብዛት ሳይንቲስቶችን ነው:: አብዛኛው ሳይንቲስቶች ተጠራጣሪ ናቸው ይሉናል:: እንዲሁም ኢንተሊጀንት ሰዎች በትዳር የመቆየት አዝማሚያ ያሳያሉ ይላል:: አንተን ሳስብህ አማኝና ትዳር ላይ ብዙ የቆየህ ትመስለኛለህ:: ከራስህና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ይህን ጥናት እንዴት ታየዋለህ?

እነ ፀዋር ዳግማዊስ ምን ትላላችሁ?
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Re: ዲጎኔ ይህንን ጥናት አስተባብል

Postby እናመሰግንሃለ » Sun Aug 25, 2013 3:47 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote: ሀይማኖተኞች እምነትን በተመለከተ የሚመሩት በአእምሮቸው ሳይሆን በ'ቀልባቸው" ነው :D......

ይሄ በአሁን ወቅት በዓለማችን ካሉ የባዮሎጂ ምርምር አእምሮዎች አንዱን የያዘው ሰውዬ: ሮሜ 8:6 ላይ ሐዋርያው የተናገረውን ቁምነገር ለመረዳት ከአምላክ የለም ባይነት ወደአምላክ አለ ባይነት ያሸጋገረውን በጣም ረጅም የምርምር ሕይወት ማሳለፍ ነበረበት:: ሰውየው "ቀልቡን" የማያምን ጠርጣራ ነበረ:: እነሆ አሁን መጽሐፍ ቅዱሱን በሳይንስኛ ከሚተረጉሙ ሰዎች መሃል ሆኗል:-

http://www.youtube.com/watch?v=0quDjlkVvPM

እግዚአብሔር እንድናውቀው የሚፈልገውን እውነታ ሁሉ: "ቀልባችን" ውስጥ አስቀምጦ ነው የፈጠረን:: ለምርምርና ሙከራ የበቁ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው:: ብዙዎቻችን ከጅ ወደአፍ ተጠምደን እንኖራለን:: እግዚአብሔር እውነቱን በቀልባችን ውስጥ አድርጎልን ባይፈጥረን ኖሮ: ለጥቂቶች በሕዝብ ገንዘብ ለሚማሩና ለሚመራመሩ ዕድለኞች ብቻ እውነቱን አስቀምጦ: ለኛ ባዶዋችንን ፈጠረን ማለት ይሆን ነበር:: ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ፍጹም ፍርደ-ገምድል ያደርገዋል:: እግዚአብሔር ማለት ያለምንም ምርምር በተፈጥሮ ቀልብ ብቻ ሊረዱት የሚገባ ኃይል ሊሆን ይገባዋል:: አለዚያ ምኑን እግዚአብሔር ሆነው? በሁሉ ቦታ ያለ ከሆነ በቀልባችንም ውስጥ ሊኖር ይገባዋል::

የሆነ ሆኖ: የአበሻ ጠርጣሮች: ከራሳቸው ከሳይንቲስቶቹ በላይ ኤቴዪስት የሚሆኑበት ምክንያት ይገርመኛል:: ነጮቹ ሳይንቲስቶች: በእግዚአብሔር ባያምኑ እንኳ: አማኞቹ "እግዚአብሔር" የሚሉት ሌላ ጠፈራዊ ወይም ሥነ-ልቦናዊ ወይም የዝግመታዊ ለውጥ ኃይል ነው ይላሉ እንጂ አማኞችን ፈጽሞ ማሰብ እንደማይችልና የሌለ ነገርን ፈጥሮ እንደሚያምን ዝቅተኛ ፍጥረት አድርገው አያዩም:: ለአማኞቹ: እግዚአብሔር የመሰላቸው ሌላ ሳይንሳዊ ኃይል እንደሆነ ብቻ ነው የሚናገሩት:: የኛን አበሾች ኤቴዪስቶች የሚነዳቸው ግን: የራሳቸው አለማመን ወይም ጠፈራዊውን ኃይል በሌላ መንገድ ከመረዳት የመጣ የአእምሮ እውቀታቸው ሳይሆን በአማኞች ላይ ያላቸው መራራ የጥላቻ ስሜት ነው:: ለዚያ ነው: እነርሱ የዝህችን ዓለም አካሄድና ተፈጥሮ እንዴት እንደሚርረዱት ከማስቀመጥና በመገረም ከመመራመር ይልቅ የሃይማኖተኞችን የበታችነት በማሳየት ላይ ዕድሜያቸውን የሚያጠፉት:: ይህ ስሜት በኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ሰዎች ላይ ነው በከፍተኛ ደረጃ የሚስተዋለው:: በሌላ አገር እንዲህ ያለ ከፍተኛ ንቀትና ጥላቻ የለም:: ጉዳዩ የኢትዮጵያውያንን መንፈስ ለመግደል ዲያብሎስ የሚያሰማራው ከባድ ሥነ-ልቦናዊ ጦርነት በፖለቲከኞችና የማኅበራዊ ሳይንስ ካድሬዎች የሚመራ ሰፊ ዘመቻ እንጂ የግለሰቦች አስተሳሰብና የግል ጥርጣሬና ምርምር የፈጠረው ወጣ-ባይነት እንዳልሆነ እናውቃለን:: እንዲህ ያሉ ግለሰቦችን በግሌ አውቃለሁ:: ኢትዮጵያውያን በሳይንስ የሚያምኑ ተጠራጣሪዎች: ይህ ጥርጣሬያቸው ሌላውን እንዲንቁና እንዲጠሉ ሳይሆን: እነርሱ ዐውቀው እንዲያሳውቁና ስኅተት የመሰላቸውን ነገር ለማረም ከመፈለግ የሚመጣ ስለሆነ: አማኝም ቢሆንም ባይሆንም: ጓደኛቸውን አይንቁም:: ፖለቲከኞቹ ግን: በሃይማኖተኞች ላይ የሚበግነው የዲያብሎስ ንዴትና ቁጣ ቀጥተኛ አንጸባራቂዎች ስለሆኑ: ሳይንሱን በቅጡ ለማወቅ ምንም ፍላጎት ሳይኖራቸው: ጫፉን ይዘው: ዋና ታርጌታቸው የሆነውን ሃይማኖተኛ ወንድማቸውን ለማንጓጠጥ ይጠቀሙበታል::

Atheism = Is a chronic type of skepticism. It is too bad for the individual, but good for the religious person (because it makes him clarify why he believes what he believes). Finally, maybe, it is good for the atheist individual himself/herself if he keeps searching for the Truth because God is interested in people who search and seek Him, especially if they are earnst and humble.

BUT, Haterade and contempt towards religious people = Is satanic identity = too bad for the atheist because he does not know what is driving him/her. Haterade makes one blind.

Fellas, I am trying to help you and me understand your critical condition (as well as your likes who populate Ethiopian politics). We r too unlucky to have people like u dominate our ideology in Ethiopia.
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ኤዶም* » Sun Aug 25, 2013 4:27 pm

ሰላም

እናመሰግናለን የልቤን ስለተናገረ ምንም ነገር መድገም አልፈልግም.........ለዳግማዊ ግን ጥያቄ ይኖረኛል .......እንዲህ ከ ፕሮፌሰር ስቴቨን ሀውኪንግስ በላይ ኤቲስት ያደረገህ ነገር ምንድነው?

ያ ሙሉ በሙሉ ፓራላይዝ ሆኖ በ ማሽን እርዳታ የሚናገረውና የሚያስተምረው የዘመናችሁ ምርጥ አስተማሪያችሁ እንክዋን የሚያምንበትንን እና ተመራምሬ ደረስኩበት ያለውን ነገር 24/ 7 ከአእምሮው ጋ በተገጠመለት ማሽን እርዳታ ያወራል እንጂ ሌሎችን ሲዘልፍ አይሰማም......

http://www.youtube.com/watch?v=PmRHQ5qYlhw
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ፀዋር » Mon Aug 26, 2013 12:30 pm

ሠላም ወገኖች

አንዳንዴ ለምን ስለ ሀይማኖት እንደምንክራከር ግራ ይገባኛል:: ማለቴ ዓላማችን ምንድን ነው? እንደኔ እንደኔ መንፈሳዊ ህይወታችንን ሳንረብሽ ምድራዊ ህይወታችንን የተሻለ ለማድረግ ይመስለኛል:: በመንፈስም በስጋም የተረጋጋ ኑሮ እንድንኖር ይመስለኛል:: አንዳንዱ የሰዎችን መንፈስ ለማወክ ሆን ብሎ ይዳክራል:: እንጭጭነት ነው ይሄ:: ሳይንስ ስንት ያልመለሳቸው ጉዳዮች አሉ:: በቀላሉ ሊመልሳቸው የማይችሉ መዓት ርዕሰ ጉዳዮች አሉ:: ኮንሸይስነስ: ሶል: ስፕሪት: ጋድ:... ወዘተ:: እነዚህ ሁሉ መልስ ባላገኙበት ሁኔታ ጫፍ ይዞ በፊዚካል ሳይንስ ብቻ መንጠላጠሉና ሌሎችን ማወኩ ምን የሚባል "አዋቂነት" ነው? ኢቭን ፊዚካል ሳይንስ ራሱ በኢሉዥን የተሞላ መሆኑን ከሳይንቲስቶቹ ራሱ ሁሌም የምንሰማው ጉዳይ ነው:: የምናየውን ነገር ብቻ ነው የምናምነው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግራ ይገባኛል:: የሚታይ ነገር ብቻ የሚታመንበት ምክንያት ምንድን ነው? ለዛውም የምናየው ነገር ግማሽ ውዥንብር እንጂ ምንም እውነታ የሌለው ሆኖ ሳለ::

ብሪያን ኮክስ የተባለው ዝነኛ አስትሮኖሚስት በአንድ ወቅት ሌክቸር ሲያደርግ: የሰውነታችን 99.9999...% የተሞላው "በኢምፒቲ ስፔስ" እንደሆነ ገልጾ ነበር:: የዩኒቨርስን ኢምፒቲ ስፔስ በሙሉ አውጥተን: ጠጣር ነገሮችን ብቻ አንድ ላይ ብንጨፈልቃቸው ሳይዙ ከዶሮ እንቁላል እንደሚያንስ ገልጾ ነበር:: ከዛ ውጪ የሆነው ነገር በሙሉ በባዶ የተሞላ ነው:: ባዶ! አይናችን የሚያየው ግን ሌላ ነው:: አይናችን የሚያየውን ብቻ ማመናችን ያደግንበት ኮንቬንሽናል ዌይ ነው::

የቱ ሪያሊቲ የቱ ኢሊዥን እንደሆነ በማይታወቅበት የሰው ልጅ ህይወት: እኛ የመሰለንን ሌሎች ካልተቀበሉ ዝቅተኛ ኢንተለጀንስ እንዳላቸው መቁጠር ግብዝነት ነው:: ብሎም ድንቁርና ነው::

አንድ ጊዜ የስቴፈን ሀውኪን መጻፍ ሳነብ ያጋጠመኝን አንድ ሀሳብ ላካፍላችሁ:: ፕ/ሩ ስለ ባልክሆል ቲየሪ በሚያወራበት ጊዜ ሁሉም ነገር በብላክ ሆሉ ሲሳብ ቤዚክ እንፎርሜሽኑ የትም እይሄድም ይላል:: ግድግዳ ላይ ቀለም እንደምንቀባው አይነት የእያንዳንዱ ነገር ኢንፎርሜሽን የብላክ ሆሉ ሰርፌስ ላይ ለተወሰነ "ጊዜ" ይለጠፋል:: ቀጥሎ የሚሳበው ነገር ኢንፎርሜሽኑ እላዩ ላይ ይለጠፋል:: እያለ የኢንፎርሜሽን ለየር ይሰራል:: ይህ ትየሪ ትክክል ከሆነ ይላል ፕ/ሩ: ይህ የምናየው አይነት 3D world የዛ ሰርፌስ ፕሮጀክሽን ሊሆን ይችላል:: ልክ በ3D ፕሮጀክተር ሙቪ እንደማየት ቁጠሩት:: ያ ከሆነ ደግሞ ዘ ሆል ዩኒቨርስ ኢሉዥን እንጂ ሪያሊቲ አይደለም ማለት ነው ይላል ሰውዬው:: ባጭሩ የማናየው ነገር በአፈታሪክ ከምንሰማው ሚዝ በተለየ የምናምንበት ምንም ምክንያት የለም:: ሳይንስ ለጊዜው ይህን ያህል ብሎናል::

በእ/ር ማመን ያለማመኑ ጉዳይ የግለሰቡ ውሳኔ ነው:: ማንም ማንንም በትክክል ሊያሳምን አይችልም:: የሌሎችን ስላም ማደፍረስ ግን ይቻላል:: እንደ ዳግማዊ አይነት ሰዎች ሆን ብለው ሰዎችን ለመበጥበጥ የተነሱ ይህን መረዳት ይከብዳቸዋል:: ይህን ያክል ረቂቅ ስለሆነው ጉዳይ ቀርቶ በእጃቸው ያለውን ዜጎችን በሰለጠነ መንገድ ለማስተዳደር ፍላጎቱ የሌላቸው ሰዎች ይህ ማራከስ የሰውን መንፈሳዊ ህይወት የመጥበጥ ተጓዳኝ ስራቸው ቢሆን እንጂ እውነትን ፍለጋ የሚደረግ ጥረት ሊሆን አይችልም::

በተለይ የኛ አገር የእምነት ተቋሞች ማስተካከል ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ:: በመንፈሳዊው ህይወት ተአማኒነት የሌላቸውና ዋጋ ቢስ የሆኑ: በስጋዊ ህይወትም ለጭቆናና ለድንቁርና የዳረጉ ገድሎችና ስንክሳሮች አሉ: መስተካከል የሚገባቸው:: እዛ ላይ እርምት ማድረጉ የአባት ነው:: እምነት የለሽና ስነ ምግባር የለሽ ለማድረግ የሚደረገው ርብርብ ግን ሌላ ምንም ሳይሆን ድንቁርና የወለደው በሽታ ነው:: የማይድን በሽታ ነው:: ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ጋር አጉል ጉንጭ መላፋቱን ወደጎን ትቶ: ገንቢ የሆነ እምነትን የማጥራት ውይይት ቢለመድ ጥሩ ነው እላለሁ::

ሠላም ሁኑ!
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby እናመሰግንሃለ » Mon Aug 26, 2013 8:25 pm

ፀዋር wrote:

በተለይ የኛ አገር የእምነት ተቋሞች ማስተካከል ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ:: በመንፈሳዊው ህይወት ተአማኒነት የሌላቸውና ዋጋ ቢስ የሆኑ: በስጋዊ ህይወትም ለጭቆናና ለድንቁርና የዳረጉ ገድሎችና ስንክሳሮች አሉ: መስተካከል የሚገባቸው:: እዛ ላይ እርምት ማድረጉ የአባት ነው::
ሠላም ሁኑ!

This statement would have been true if the above study was conducted on religious people that read ገድል and ስንክሳር and as a result became less intelligent than atheists. No, it isn't. Participants are not readers of ገድሎችና ስንክሳሮች:: Maybe, their brian would have lightened up a bit more had they bee regular readers of ገድሎችና ስንክሳሮች:: These books are applications (life stories) of a teaching (Gospel). Application is the beginning of higher order thinking skill. Stretchy!!
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 6 guests