ይሄ ነገር ስሙ ምን ይባላል?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ይሄ ነገር ስሙ ምን ይባላል?

Postby Qeqeba » Sat Aug 17, 2013 5:50 am

ወገኖቼ: አንድ ነገር ከብዙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በተደጋጋሚ ይገጥመኛል;; ይሄውም ግራ እያጋባኝ ነው:: ነገሩ እንደሚከተለው ነው--->
እኔ አንድ መልካም ነገርን በጣም ፈልጌ ሀሳብ አቀርባለሁ:: "እንዲ ብናደርግ: ብዬ ማለት ነው:: ያኛውም ሰው: በጉጉቴና ሀይሌ ተመስጦ ይስማማና እንጀምራለን:: እኔ: እኔ በምችለው (እርሱ በማይችለው) አስተዋጾኦ ላደርግ: እርሱ ደግሞ እርሱ በሚችለው እኔ ግን በማልችለው በኩል አስተዋጾ ሊያደርግ እንስማማና እንጀምራለን;; ወድያው የተወሰነ ስራው ከተገፋ በሁዋላ; ያ ሰው ተስፋ ይቆርጣል:: ብዙ ላበረታታው እሞክራለሁ;; የተወሰነ ደረጃ መስዋእትነትም እከፍላለሁ: ግን ያ ሰው ምንም የሚበረታታ አይሆንም:: ተስፋ አስቆራጭነትና ፈዛዝነትን ያሳያል:: ባዝንም: ወደፊት ይሳካልንና እንቀጥል ይሆናል የሚል ተስፋ ይሰማኝና ነገሩ እንዲሁ ሳይጨበጥና ውል ሳይዝ ይቀራል:: ከዛ ሰው ጋር ግን ግንኙነቴ በሌላ ማህበራዊ አቅጣጫ ምንም ቅያሜ ሳይኖር ይቀጥላል::
በጣም የሚገርመኝ ቀጥሎ ያለው ነገር ነው:: ያ ተስፋ ቆርጦ ተስፋ ያስቆረጠኝ ሰው: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ያንን ነገር በድብቅ ሄዶበት ከግብ አድርሶት እየተንጎማለለ ኮራ ደራ ብሎ ብቅ ይልብኛል:: ብቅ ሲልብኝም: እኔ ተስፋ ቆርጬ መተዌ ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ እንዲሰማኝ በሚያደርግ ሁኔታ እርሱን እግዚአብሔር ረድቶት ከዚያ እንደደረሰና ሙያ በልብ እንደሆነ: እኔም ደግሞ ልበረታ እንደሚገባኝ: በቃል ባይሆንም በተዘዋዋሪ በሌሎች መልክ ሊነግረኝና ሊመክረኝ ሊመጻደቅብኝም ይሞክራል: በቀጥታ ለኔ በመናገር ባይሆንም በሌላ መልክ::

እንዲ ያለ ነገር ሦስት ጊዜ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን ገጠመኝ:: ምን ትላላችሁ? ይህ አድራጎትስ ምንድነው ስሙ? የኔ ጥፋት የቱ ጋር ነው? የነርሱስ ርካታ ምኑ ላይ ነው? እንዲህ ያለ አካሄድስ ምን ያህል የተለመደ ነው? ምክርና አስተያየታቹን እንዲሁም ልምዳችሁን ለግሱኝ::
Qeqeba
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Wed Feb 13, 2008 3:54 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests