ለምን እየሱስ አምላክ አይደለም ?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ለምን እየሱስ አምላክ አይደለም ?

Postby መርፊው » Mon Sep 09, 2013 11:54 am

መግቢያ

ይህ ለምእተ አመታት ራስ ምታት የሆነው የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ምንነት በጥልቀት መረዳት ያስችልህ ዘንድ ታሪካዊው ክርስትናን ማወቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ምንነቱ እስከ ምንጩ ስላልታወቀ ነገር ብነግርህ ትደናገር ወይም ትደናበር ይሆናል፡፡ ይህን ስልህ ለምን መሰለህ አንድ ነገር ከተድበሰበሰና በአግባቡ ካልተገለፀ ለመጋፈጥ ይከብዳል፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት ግን አስቀድሜ ታሪካዊውን ክርስትና መሰረታዊ አስተምሮቱ እና እድገቱን ማሳወቅ የነፍስ ወከፍ ግዴታዬ ነው፡፡ እናም ይህን ጉዳይ ቅድሚያ ብቸረው ሊገርምህ አሊያም ሊደንቅህ አይገባም……………

ሲጀመር ለብዙሀኑ የተሰወረ ለጥቂቱ ግን የታየ አንድ ነገር አለ፡፡ ብዙሀኑ እራሱን የክርስትና እምነት ተከታይ አሊያም ደግሞ አማኝ አድርጎ የሚቆጥረው ማህበረሰብን ስትመለከት ወይም ስታጠና አብዛኛው አማኝ እምነቱን መመርመር እንደወንጀል ይቆጥርና "ክርስትና ማለት ሞኝነት" ነው የሚል ድምዳሜ ውስጥ ይደርስና በጭፍኑ ሲያምን ታዋለህ፡፡ እምነቱን መመርመር ፈጣሪን እንደመዳፈር እንዲሁም እምነቱ ላይ ጥርጣሬን እንደመጫር አድርጎ ስለሚቆጥር ይህ ማህበረሰብ በእምነቱ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችን ለመቀበል አሻፈረኝ ሲል ይታያል፡፡

ብዙሀኑ መፅሀፍ ቅዱስን ታሪካዊ አመጣጡን ምሁራዊ በሆነ መልኩ ስለማያጠናው ይመስላል አብዛኛውን ጊዜ ስለ እየሱስ እና አስተምሮቱ ማወቅ እጅግ ቀላል አድርጎ ይወስደዋል፡፡ አራቱ ወንጌሎች እያሉ እንዴት አስተምሮቱን ማወቅ አይቻልም? ሲሉም ሲሞግቱም ይሰማል፡፡
እውቁ የመፅሀፍ ቅዱስ ጠበብት በርት ኢህርማን ይህን የተሳሳተ የብዙሀኑን ሀሳብ ጠቅሶ ሲያበቃ እንዲህ የሚል ማስተባበያን አክሎ ፅፏል፡፡
“The problem is in part that the Gospels are full of discrepancies and was written decades after Jesus’ ministry and death by authors who had not themselves witnessed any of the events of Jesus’ life”(30)

መፅሀፍ ቅዱስ መሰረታዊ አስተምሮ ላይ ታሪካዊነት በማጓደሉ ፣በመከለስ እና በመበረዝ ሂደት ውስጥ በማለፉ እንዲሁም በተያያዥ ምክንያቶች ሰበብ አንድ ወጥ ዶክትሪን(ቀኖና) ሊኖረው አልቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ የክርስትና አንጃዎች ጥንትም ሲፈለፈሉ ነበር አሁንም በመፈልፈል ላይ ናቸው፡፡ አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ዛሬ ላይ እነዚህ አንጃዎች 41000 ለመድረስ ችለዋል(31)፡፡ አስተውለህ ከሆነ ዛሬ ላይ ብዙሀኑ የሚያስበው ከ 1800 አመት በፊት የነበረው ክርስትና እና ያሁኑ ክርስትና መካከል ልዩነት የሌለ አድርጎ ነው፡፡ እናም የሚያምንበት ክርስትና እየሱስ ያመጣው እንዲሁም ያስተማረው ደቀመዛሙርቱም ተቀብለው ያስተላለፉት አድርጎ ሲያበቃ ያለ ምንም ማመንታት ሀቅ ላይ ነን ሲል ትሰማዋለህ ፡፡

የሆነው ሆኖ ይህ አስተሳሰብ ታሪካዊነት ያልተላበሰ እና ከታሪክ አኳያ ድጋፍ ያልተቸረው መሆኑን ለማወቅ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በኋለ የተስተዋለውን የክርስትና ታሪክ ላይ ጥናት ማድረግ በቂ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ስለስላሴ ከመናገሬ በፊት ስለ ታሪካዊ ይዘቱ ትኩረት የሰጠሁት……………

2.1 ክርስትና በጥንት (Christianity in Antiquity)
እነሆ! በጥንት የነበረውን ክርስትና እምነት ታሪክ ለማጥናት የተነሳ አንድ የክርስትና አማኝ በሚያሳልፈው የጥናት ህይወቱ የሚያስተውለው የለየለት የአስተሳሰብ እና የእምነት ልዩነት አስደንጋጭ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ይህን ስልህ ለምን መሰለህ? በሁለተኛ ክ/ዘመን የነበረው ክርስትና እና አንተ አሁን የምትከተለው ክርስትና ፍፁም ተቃራኒ እና የማይገኛኝ ነው፡፡እመነኝ በጥንት አንድ አምላክ ብቻ የሚያመልኩ ክርስትያኖች እናዳሉ በ 2 እንዲሁም 365 አምላክ የሚያምኑ ክርስትያኖች ነበሩ፡፡መች ይህ ብቻ ብሉይ ኪዳንን እንዲሁም የሙሴ አምላክን የሚያጣጥሉ እንዲሁም የሚሳደብ ክርስትያኖችን ነበሩ፡፡ አምላክ ይህን አለም አልፈጠረም እንዲሁም ከዚህ አለም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም የሚሉም ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ እየሱስ የሰው አካል እንዲሁም ነፍስ አልነበረውም አልሞተም እንዲሁም አልተወለደም የሚሉም ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ አልፎ ተርፎ እየሱስ ምድር ላይ ሳለ አግብቷል ከማርያም መቅደላዊት ጋር የነበረውን የፍቅር ታሪክ የፃፉ ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ ይህ ምናልባት ሊገርምህ እና ይህን እምነት የሚያራምድ ማንኛውም ሰው ክርስትያን አይደለም ልትል ትችላለህ፡፡ (32) እነሱም አንተ የምታምነውን ቢሰሙ ኖሮ አንተ ለነሱ ምትለውን መልሰው ላንተው ባሉህ ነበር… ምናልባት አዲስ ኪዳን በዋቢነት አቅርበህ ስታበቃ አዲስ ኪዳን እኮ! እየሱስ የሰው አካል የለውም፣ አልተወለደም አልሞተም፣ የሙሴ አምላክን አይሰድብም፣ አንጃ ግራንጃ …. ትል ይሆናል፡፡ ይህም መከራከሪያ ላንተ አያስኬድም ምክንያቱም ልክ አንተ አዲስ ኪዳን በ እየሱስ ደቀ መዝሙር ተፃፈ ብለህ እንደምታምነው ሁሉ እነሱም የራሳቸው በእየሱስ ደቀ መዝሙር ተፃፉ ሲሉ የሚያምኑበት ወንጌል ነበራቸው፡፡ እናም የማነው ትክክል? የሚለው አንተ ላይ የሚደቀን አይኑን ያፈጠጠ እና ራስ ምታት ፈጣሪ ጥያቄ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ዋናው ጥያቄ እና የተነሳሁበት ርእስ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በመሆኑ ይህ ፅንሰ ሐሳብ መች ተቀባይነትን አገኘ የሚለው ጥያቄ መመለስ የግድ ይላል፡፡ እናም ለዚህ ፅንሰ ሐሳብ መንደርደሪያ የሚሆኑትን ቀደምት ክርስትያኖች እና ታሪካቸውን በመቀጠል እንመልከት፡፡

2.1.1 የአይሁድ ክርስትያኖች ክርስትና ፡- የመጀመሪያው ጥንታዊ ክርስትና ይህ ሲሆን ይህ እምነት በዮርዳኖስ ሐይቅ በስተምስራቅ በፍሊስጢም ውስጥ በሚኖሩ አይሁዶች ሲታመንበት የነበረ የክርስትና አይነት ነው ፡፡ ይህን ክርስትና የሚከተሉ ክርስትያኖች እምነታቸውን የገነቡት አንድ እና ብቸኛ በሆነው አምላክ ላይ ሲሆን እየሱስንም የሚገልፁት ፃድቅ ሰው፣ የአይሁድን ህግጋት ጠባቂ ነብይ አድርገው ነው፡፡ እነዚህ የክርስትና አንጃዎች እየሱስ በፈጣሪ ፍቃድ ሙታን እንዳስነሳ ፣ ለምፃም እንደፈወሰ እንዲሁም ሌሎች ተአምራቶችን እንደሰራ ያምናሉ፡፡ አምነውም ሲያበቁ ግን እየሱስን ፈጣሪ ወይም አምላክ ሲሉ መለኮታዊ ስልጣንን በጭብጨባ አሊያም በስብሰባ አልሰጡትም ወይም አልሾሙትም፡፡እመነኝ እነዚህ ክርስትያኖች እምነታቸውን ያፀኑት እየሱስ ፍፁም ሰው ነው ሲሉ እንጂ መለኮታዊ ነው ሲሉ አይደለም ፡፡ እናም እነዚህ ክርስትያኖች ምናልባት የትንሳኤ ቀን አግኝተህ ስለ ስላሴ ብትነግራቸው ወይም አምላክ አንድም ሶስትም ነው ብትላቸው፡፡ፈጣሪን ተሳዳቢ ከሀዲ እንደሆንክ ነው ሚነግሩህ፡፡ እነዚህ ክርስትያኖች የእምነት መሰረት ያደረጉት የቶራህ አንቀፅ ኦሪት ዘዳግም 6፡4 ላይ የሚገኘው ሲሆን " ስማ እስራኤል ሆይ ጌታችን አምላካችን አንድ ጌታ ነው፡፡" ሲል ሙሴ ህዝቦቹን ያስተማረው ነው፡፡ እናም በ እምነታቸው መሰረት እየሱስ የመጣው ይህን የሙሴ ህግ ለማስቀጠል እንጂ ለማደፍረስ እንዳልሆነው ያምናሉ፡፡ ለነዚህ ክርስትያኖች ስላሴ ምትለውን ፅንሰ ሐሳብ ጭራሽ ሰምተውት አያውቁም ቢሰሙትም አይቀበሉትም ንፍቅና እና ክህደት አድርገው ነው ሚቆጥሩት ይህንንም ፅንሰ ሐሳብ የሚያራምድ ማንኛውንም ግለሰብ ከሃዲ እንደሆነ ነው የሚያውጁት፡፡ የሆነ ሆኖ እዚህ ጋር የሚነሳ ወሳኝ ጥያቄ አለ እነዚህ የአይሁድ ክርስትያኖች ይህ እምነትን የያዙት ምን መሰረት ቢኖራቸው ነው? እውነት እውነት እልሀለው እምነቱን የያዙት በደመነስ አይደለም ግና እየሱስ አስተምሮታል ሲሉ በማመኛቸው ቢሆን እንጂ ፡፡ እነዚህ ክርስትያኖች የሚያምኑበት የራሳቸው ወንጌል ያላቸው ሲሆን እየሱስ አምላክ ነው የሚለውን ማንኛውም ግለሰብ በክህደት የሚፈርጁ የክርስትያን አንጃ ናቸው፡፡ በነዚህ ክርስያኖች መሰረት ጳውሎስ ከሀዲ እና የእየሱስን አስተምሮ ለመበረዝ የተነሳ ግለሰብ ተደርጎ ተፈርጇል፡፡ ልምን ተባለ ካልክ ሚሰጡህ ምላሽ ጳውሎስ ከሙሴ ህግ ጋር ፀበኛ በመሆኑ እና የሙሴ ህግ ተሸሯል ብሎ በማስተማሩ ሲሉ እውነቱን በእንቅጩ ይነግሩሀል፡፡ እነዚህ ክርስትያኖች ዛሬ ምታምንበትን አዲስ ኪዳን ፅሁፎች መለኮታዊ ነው ሲሉ አይቀበሉትም፡፡ ግና እነሱ መለኮታዊ ሲሉ የሚቀበሉት የራሳቸው መፅሀፍ እና ወንጌሎች አላቸው፡፡(33) ያም ሆነ ይህ በነዚህ የሁለተኛ ክ/ዘመን ክርስትያኖች እምነት መሰረት ስላሴ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ አንድም ሶስትም የሚለው ፅንሰ ሐሳብ ቢኖርም እንኳ እንደ ክህደት እንጂ እንደ እውነት አይወሰድም……………

2.1.2 ማሪኪዮናይት ክርስትና ፡- ይህ ክርስትና እና የዚህ ክርስትያኒቲ አራማጆች የነበሩት ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ እስከ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ሲሆን፤ የሚገኙትም በሚድትሪያንያን አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ አብዛኛው የዚህ እምነት አቀንቃኞች በ ኤዥያ ማይኖር ወይም ደግሞ በአሁኗ ቱርክ ውስጥ ነበር የሚገኙት፡፡ የነዚህ እምነት ስያሜ ማሪኪዮናይት የሚባል ሲሆን ስያሜውን ያገኙት ከተቃዋሚዎቻቸው ክርስትያን አንጃዎች መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ የክርስትና እምነት መስራች ማርኪዮን የተባለ የሁለተኛ ክፍለ ዘመን ወንጌላዊ ስለሆነ ነው፡፡ይህ ሰው የጳውሎስን መልእክት እና አስተምህሮት መለኮታዊ ፅሁፍ እንደሆነ ተቀበለ ተቀብሎም ሲያበቃ እጅና እግሩን አጣጥፎ ቁጭ አላለም፡፡ ይህን መለኮታዊ ሲል ያመነበትን ፅሁፍ መሰረቱ አድርጎ ነበር ስብከቱን የቀጠለው፡፡ እናም በዚህ የክርስትና አንጃ መሰረት እየሱስ ባስተማረው አስተምሮ እና ሙሴ ባስተማረው አስተምህሮ መካከል ልዩነት እንዳለ ወይም አንድነት እንደሌለ ያምናል፡፡ ይህ አንጃ እንደሚነግረን ከሆነ የሙሴ እና የአይሁዶች አምላክ ርህራሄ የሌለው ነው፡፡ አይን ለአይን ጥርስ ለጥርስ ይላልና ፡፡ ክርስቶስ አምላክ ግና ርህራሄ አለው ይለናል፡፡ በዚህም መሰረት ሁለት ልዩነት ያላቸው አምላኮች እንዳሉ ማርኪዮን ነገረን፡፡ማርኪዮን እየሱስ ለምን እንደመጣ በገለፀበት ሂደቱ - እየሱስ የመጣው የሰውን ልጅ ከሙሴ አምላክ ለመታደግ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ ተመልከት እነዚህ ክርስትያኖች የሙሴ አምላክ ይህን አለም እንደፈጠረ ቢያምኑም ኢስራኤላውያንን እንደመረጣቸውም ቢቀበሉም ግና ጨርሰው እየሱስ የመጣው እነዚህን ህዝቦች ከጨካኙ እና ርህራሄ አልባ ከሆነው ከ ሙሴ አምላክ ለመታደግ ነው ይሉናል፡፡በመሆኑም እየሱስ በእርግጥ የተወለደ እንዲሁም ትክክለኛ ስጋ እና አጥንት ያለው እንዳልሆነ ማመን የነዚህ አንጃዎች አቂዳ ዋና ነው፡፡ ይህን አባባላቸውን ያየ አንባቢ ጥያቄን ይጠይቃል፡፡እሱም እየሱስ እውን ስጋ እና አጥንት ከሌለው እንዴት ይርበዋል አሊያም ደግሞ ይጠማዋል ይላል እነዚህ ክርስትያኖች ለዚህ ጥያቄ መልስ አለን ይላሉ እሱም እየሱስ እውን ርቦት አሊያም ደግሞ ጠምቶት ሳይሆን ለመመሳሰል ያደረገው ድርጊት ነው ሲሉ ምላሹን በአራት ነጥብ ይደመድማሉ፡፡ በመሆኑም በእውነቱ እየሱስ አልተወለደም ፣ አልራበውም፣ አልጠማውም፣ አልሞተም ሲሉ እነዚህ ክርስትያኖች ያምናሉ ፡፡ በነዚህ ክርስትያኖች እምነት መሰረት እየሱስ ፍፁም አምላክ ነው፡፡ ሰው አይደለም፡፡ ይህ የሁለተኛዎቹ የክርስትና እምነት አስተምህሮ መሆኑ ነው፡፡(34) በነዚህ የክርስትና አንጃ አስተምህሮ መሰረት ሁለት አምላክ አለ አንድም እየሱስ ሁለትም የሙሴ አምላክ ግና እነዚህ አማልክት ጠበኞች ናቸው፡፡ አስተምሮታቸውም የተለያየ ነው፡፡ ዘለልክም ፈረጥክም በነዚህ አንጃዎች አስተምሮ መሰረት ስላሴ የሚለው ነገር የለም ኢንጅሩ!!!


2.1.3. ጊኖስቲክ(gnostic) ክርስትና እና ተከታዮቻቸው፡- በሁለተኛው ክፍለ ዘመን አስተምሮቶቻቸውን በማስፋፋት ቢዚ ከነበሩ የክርስትና አንጃዎች ሶስተኛዎቹ እነዚህ ጊኖስቲክ በመባል የሚታወቁት የክርስትና አንጃዎች ናቸው ፡፡ እራሳቸውን ጊኖሲስ (35) በሚል ስያሜ ስለሚጠሩ ነው ጊኖሲስቲክ የተባሉት፡፡ የእነዚህ የክርስትና አንጃዎች መገኛቸው በሜድትሪያኒያን አካባቢ ወይም ደግሞ በ ግብፅ፣ሲርያ፣ኤዝያ ማይኖር (ያሁኗ ቱርክ) ፣ሮም እንዲሁም ጋኡል እና መሰል ከተሞች እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል፡፡እነሆ በእነዚህ የክርስትና አንጃዎች ውስጥ ሌሎች አንጃዎች ሲኖሩ በውስጣቸው ያለውን የእምነት እና የ አመለካከት ልዩነት በእጅጉ የበዛና የገዘፈም ነበር፡፡ ጊንዮስቲኮች ከማርኪዮናይቶች ጋር ሚስማሙበት አቋም እንዳላቸው ሁሉ ከ አይሁድ ክርስትያነኖች ጋርም ሚስማሙበት አቋም አላቸው፡፡ እንዳልኩህ የማርኪዮናይት ፅንሰ ሐሳብ አራማጆች እየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ እንደሆነ ያምናሉ ፡፡ ጊኖስቲኮችም ይህን ሀሳብ እና እየሱስ ክርስቶስ ይህን አለም ከፈጠረው የተለየ ሌላ አምላክ እንደነበር ከሚያትተው ከ ማርኪዮናይት ፅንሰ ሐሳብ ጋር በመስማማት አዎ ልክ ናቹህ ሲሉ ያምናሉ ፡፡ ይህን ስልህ ከማርዮናይት ጋር ፍፁም ተመሳሳይ አንድ ናቸው እያልኩህ መስሎህ እንዳትስት፡፡ ከማርኪዮናይት ክርስትያኖች ጋር የሚያስማማቸው እምነት እንዳለ ሁሉ የሚለያያቸውም እንዳለ መሳት የለብህም፡፡ ከጣዩ አእምሮ የሚያነሳው ወሳኝ ጥያቄ እነዚህን የክርስትያን አንጃዎች ከ ማርኪዮናይትስ የሚያለያያቸው ምን ይሆን ?
የሚለያቸው ምን መሰለህ!!! እነዚህ የክርስትና አንጃዎች ኢየሱስ ፍፁም ሰው ነው ሲሉ ጨምረው ማመናቸው ነው፡፡ እንዴት ካልካቸው “ክርስቶስ የሚባለው በውስጡ ያለው ፍፁም አምላክ ሲሆን እየሱስ ሚባለው ግን ክርስቶስን ተሸክሞ የያዘው ስጋዊ አካል ነው ” ይሉሀል፡፡ ወደ ዋናው እና መሰረታዊው ነጥብ ስመልስህ እነዚህ የክርስትና አንጃዎች ስላሴን አያውቁም ከስላሴ በቁጥር በላጭ አማልክት አሏቸው አንዳንዱ 2 ሌላው 12 አማልክት ሲኖሩት አንዳንዱ ደግሞ 365 አማልእክት አለው፡፡(36)

ማጠቃለያ
እንዳልኩህ የመጀመሪያዎቹ የክርስትና አንጃ የአይሁድ ክርስትያኖች አቂዳቸው የተገነባው በ አንድ አምላክ ላይ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ሲቀጥል ማርኪዮናይቶች ደግሞ በ ሁለት አምላክ ላይ ብቻ ነበር እምነታቸውን የገነቡት፡፡ ብሶም ሲገኝ ኖስቲሶች የፈለጉትን ያህል አማልክት ነበሯቸው ቢሆንም ግን እነዚህ ከላይ ባየሀቸው ክርስትያኖች ዘንድ ስላሴ የሚለው ፅንሰ ሐሳብ አይገኝም! ወፍ!!!!!!

2.2 ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትና
እነሆ ይህ የክርስትና አንጃ በ ሌሎች የክርስትና እምነቶች ላይ የበላይነቱን ያገኘ አንጃ ነው ሲሉ ምሁራን ይገልጹታል፡፡ ይህም ሲባል ሌሎቹ የክርስትና አይነቶች ከጊዜ መለወጥ ጋር ተያይዞ እነሱም ህልውናቸው እየተለወጠ ሄደ ፡፡ ቀስ በቀስ እየተመናመኑ መጡ በዚህም ወቅት ይህ አንጃ እየሰፋ እና እየተስፋፋ በመምጣት ለዛሬው ክርስትና መሰረት ለመሆን ችሏል፡፡ (37)

የሆነ ሆኖ ይህ የክርስትና አንጃ በኋላ ላይ የመጣ የክርስትና አንጃ ቢሆንም ብዙሃኑን ገጎኑ ማሰለፍ በመቻሉ እራሱን ሀቅ ላይ እና ትክክለኛ ጎዳና ላይ እንዳ በ መቁጠር (orthodoxy) አስተምህሮቱን የሚቃወመውን ደግሞ በ ንፍቅና (hetrodoxsy, heresy) ሊፈርጅ ችሏል፡፡ እናም ከዚህ ጊዜ በኋላ ያለው ሂደት በ ዚህ አንጃ እና በሌሎች አንጃዎች መሀል በ እምነት እና በ ንፍቅና አቧራ ሲጨስበት እንደነበረ የታሪክ ምሁራን ፅፈዋል፡፡ የሆነ ሆኖ ቀጣዩ ጥያቄ የዚህ አንጃ አስተምሮ ምን ይሆን ? የቆመለት አላማስ ምንድነው? የሚለው ነው፡፡ እናም መሰረታዊ አስተምሮቱ ምን ይሆን ወደ ሚለው ጉዳይ ልግባ!

ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትና እየሱስ አምላክ ብቻ ነው ሰው አይደለም የሚለውን የ ማርኪዮናይትስ ወይም ዶሰቲስት (Docetists) ሐሳብን ይነቅፋል ፡፡ ይህንም ፅንሰ ሐሳብ ይዞ ሚያራግበውን ሁሉ በ ንፍቅና ይፈርጃል ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እየሱስ ፍ ፁም ሰው ነው አምላክ አይደለም የሚለውን የ አይሁድ ክርስትያኖች ወይም ኢቦናይትስ እና የ ቲኦዶታያንስ ፅንሰ ሐሳብ ያወግዛል አልፎ ተርፎ እየሱስ አምላክ እና ሰው ሁለት አካል ነው የሚለውን የ ጊኖስቲክ ወይም ኖስቲዝም እምነት እና አመለካከትን ጨምሮ ውድቅ ያደርጋል ፡፡ ይህን ስልህ መሰረታዊ እምነቱ እና አመለካከቱ ምን እንደሆነ እኔን መጠየቅህ አይቀርም ፡፡ እኮ ምን?
በመጀመሪያ ደረጃ መሳት የሌለብህ ቁምነገር ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትና ስልህ ከ አሁኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋር እንዳትደባልቅብኝ እና የተሳሳተ ፍፃሜ ላይ እንዳትደር እነግርሀለው፡፡ እኔ ሁለተኛው እና ሶስተኛው ክ/ዘመን ላይ ነው ያለሁት….. ስቀጥልም ይህ አንጃ በዋነኝነት ሚያምነው እየሱስ አንድ ወጥ አካል ነው ጊኖስቲኮች እንደ ሚሉት ሁለት አደለም ፡፡ ይህ አንድ ወጥ አከል ፍፁም ሰውም ነው ፍፁም አምላክም ነው፡፡ ይህ ነው የዚህ አንጃ መሰረታዊ አስተምሮ እና እምነት ፡፡ ይህ አንጃ በወቅቱ እየሱስም አምላክ ነው ይበል እንጂ በስላሴ አይምንም አንድም ሶስትም የሚለው ኢ - ሒሳባዊን ፎርሙላን ገና አልመሰረተም ነበር፡፡

እንዳልኩህ ጊኖስቲኮች እየሱስ የተባለው ስጋው ሲሆን ክርስቶስ የተባለው ደግሞ ውስጡ ያለው አምላካዊ አካል ነው ሲሉ እየሱስ ከ ሁለት አካል የተገነባ ግን ፍፁም ሰው እና አምላክ ለመሆኑ ማብራሪያ አለን ሲሉ ማብራሪያቸውን አቀረቡ ፡፡ እስቀ ቀብራቸውም ድረስ ተፋለሙለት ፡፡ ግና ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትና ይህን 2 አካላት ያሉት አንድ እየሱስ የሚለውን ብሂል ተቃወመ ፡፡ ተቃውሞም ሲያበቃ ይህን ፅንሰ ሐሳብ የሚያራመንደውን ሁሉ በንፍቅና ፈረጀ ፡፡ የኔ አስተሳሰብ ብቻ ነው ትክክል ሲል እየሱስ አንድ ወጥ መሆኑን ጨምሮም ይህ አንድ ወጥ የሆነው አካል ፍፁም ሰውም ፍፁም አምላክ ነው የሚል9* አዋጅን አወጀ ፡፡ በ ወቅቱ ይህ በ ዚህ አንጃ የታወጀው አቂዳ ማህበረሰቡ ውስጥ የገባ ፈንጅ ነበር ቢባል ማጋነን አይደለም እንዴት አንድ ወጥ አካል ፍፁም ሰው እንዲሁም ፍፁም አምላክ የሚለው ማህበረሰቡን ያወዛገበ እስካሁንም እያወዛገበ ያለ አጀንዳ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ ውዝግብ በወቅቱ እንደ ሰደድ እሳት እየሰፋ እና እየተስፋፋ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የጊዜው ትውስታ ነበር ፡፡

የሆነ ሆኖ በወቅቱ የተነሳው ውዝግብ ወደ ቀጣዩ ርእስ ያመራናል፡፡
ፕሮቶ ኦርቶዶክሲዝም እና የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ከላይ እንዳልኩህ በወቅቱ እራሱን ኦርቶዶክስ በሚል ስያሜ በመጥራት ላይ የነበረው ይህ አንጃ ምንም የእየሱስ አምላክነት ቢያፀድቅም ሌሎችንም ተቀናቃኝ አንጃዎችን በንፍቅና ቢፈርጅም ግን እየሱስ አምላክ ለመሆኑ ሲደመር ከ እግዚአብሄር ጋር እኩል ነው ሲል ለሚያስተጋባለት አቂዳ የሚያቀርበው መረጃ ረፍት ነስቶት ነበር፡፡ እናም በወቅቱ አጀንዳው ሲብስ ቀሰውስቱን ፣ ምእመናን ምእመናት ወይም በአጭሩ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሲወዛገቡበት ና አቧራ ሲያጨሱበት እንደነበር ምሁራን ይነግሩሃል፡፡ በሁለተኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እና በ ሰስተኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ ብቅ ያለው ይህ አንጃ ገና ከጅምሩ የተያዘና የተጨበጠ አቂዳ አልነበረውም ግና ቀስ በቀስ አስተምሮቱ እና መሰረታዊ እምነቱ እያደገ እስከ ኒቅያ ጉባኤ ድረስ በውዝግብ እና የ ፅንን ሐሳቦች ፍጅት ውስጥ ነበር ቢባል እውነት እንጂ ሀሰት አይሆንም ፡፡ ይህም ሆነ ያ ወደ ኒቅያዊው ሀረካት ከመግባታችን በፊት ይህ ኋላ ላይ የመጣው እና እርሱን ኦርቶዶክስ ሲል የሰየመው የክርስትና አንጃ እምነቱ ፈር ይይዝለት ዘንድ ጉዞውን አንድ ብሎ ወደ ጀመረበት ዘመናት እንመለስ ዘንድ ምሁራዊው ዲስፕሊን ያስገድደናል፡፡ እናም የዚህ አንጃ ዋና አስተምሮና አመለካከቱ ምን ይሆን ? የሚለው ጥያቄ ቀዳሚ ይሆናል፡፡ እንቀጥል

በወቅቱ የዚህ አንጃ አቀንቃኝነት ከሚታወቁ ምሁራን አንዱ ኢግናተስ ነው፡፡ ይህ ሰው እየሱስ አምላክ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ተቀብሎ ያስተጋባ ስለነበር ይህንኑ ፅንሰ ሐሳብ ፅፎ ሲያበቃ ትራለስ እንዲሁም ስመይርና ለሚገኙ ክርስትያኖች መልክት ለመላክ ችሏል፡፡ በወቅቱ እነዚህ መልክቱ የተላከላቸው የክርስትና አንጃዎች እየሰሱስ ፍፁም ሰው ነው እንዲሁም አምላክ ነው በሚለው የ ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ፅንሰ ሐሳብ አይስማሙም መስማማት ብቻ ሳይይሆን ይህን ፅንሰ ሐሳብ መስማት አይፈለጉም፡፡ ይህን ስልህ ግር እንዳይልህ ምክንያቱም የነዚህ የክርስትና እምነት መሰረታዊ አቂዳ እየሱስ ፍፁም አምላክ ነው እንጂ ሰው አደለም የሚል አስተሳሰብ በመሆኑ የሆነ ሆኖ እነዚህ የክርስትና አንጃዎች ዶሰቲስት(docetists) በሚባል ስያሜ ይጠራሉ(38) ኢግናተስ ይህን ሐሳቡን ወደ ተላያዩ ዶሰቲስቶች በላካቸው ፅሁፎቹ አራምዶታል፡፡(39)ይህ የ ኢግናተስ አቋም የፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትና አጀማመር ላይ ፍንጭ ሰጪ ሆኖ ይቀርባል፡፡ ሌላው በ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከተነሱ የፕሮቶ ኦርቶዶክስ ፅንሰ ሐሳብ አራማጆች አንዱ ቲኦዶተስ (Theodotus) በሚባል ሰው ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ምንም የ ፕሮቶ ኦርቶዶክስ እምነት አቀንቃኝ ቢሆንም ግና ትንሽ ለየት ያለ ፅንሰ ሐሳብ አለው ፡፡ ይህም ሲባል እየሱስ ከ ዮሴፍ እና ከማርያም ግንኙነት እንደተወለደ ያምናል፡:፡ አልፎ ተርፎ ቲኦዶተስ እንደሚነግረን ከሆነ እየሱስ መልካም እና ጥሩ ሰው የነበረ ሲሆን በ ጥምቀት ወቅት ግን የ አለማት አዳኝ ተደርጎ እንደተመረጠ እና የ አለማት አዳኝ እንደሆነ ገልፆልናል፡፡

የዚህ ፅንሰ ሐሳብ ተከታዮች ምንም እየሱስ ሰው ነው የሚል እምነት ቢኖራቸውም ግን ተራ ሰው አይደም አምላክ ነው ወደ ሚለው ድምዳሜ ይደርሳሉ እናም ኢግናተስ ካመጣው ፅንሰ ሐሳብ ጋር ይስማማሉ ፡፡ (40)እንዳልኩህ በወቅቱ በዚህ አንጃ ላይ ራስምታት ሲሆን ረፍት የነሳቸው መሰረታዊ እና ወሳኝ ጥያቄ ነበረ፡፡ ጥያው ምን ይሆን ? ምን መሰለህ ሐቢቢ ”እየሱስ እግዚአብሄር ከሆነ እግዚአብሄርም እግዚአብሄር ከሆነ ስንት እግዚአብሄር ? ወይም በ ኢንተርናሸናሉ ቋንቋ”But if Christ is God, and God is God—how can there be only one God?” ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ለማንኛውም በዛን ወቅት ይህ ጥያቄ ለ እያንዳንዱ ፕሮቶ ኦርቶዶክስ አማኝ ራስ ምታት ነበር ፡፡ በወቅቱ በሮም ይህን ጥያቄ ለመፍታት ብዙ አጨቃጫቂ ፅንሰ ሐሳቦች ብቅ ማለት ጀመሩ ይህን ተያይዞ በሮም የሀይማኖት መሪዎች መካከል ሊዩነት ሊከሰት ቻለ፡፡ በዋቢነት ሚጠቀሰው የ ሂፖላይተስ እና የተከታዮቹ አቋም ሲሆን ይህን ወሳኝ ጥያቄ እንዲህ ሲሉ ለመፍታት ሞከሩ ” እየሱስ ራሱ በሰማይ ያለው አብ ነው ይህ ፈጣሪ ነው አለምን ለማዳን ወደዚህ ምድር የመጣው ” ይህ የሂፖላይተስ እና የተከታዮቹ አቋም ቢሆንም ግን በወቅቶ የነበሩት ቀሳውስት ሳይቃወሙት አለለፉም፡፡ እንዴተስ ያልፉታል!!! የሆነ ሆኖ ይህ ፅንሰ ሐሳብ መፈታት ስላልቻለለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከረረ መጣ አንዳንዱ ”እየሱስ አብ ካልሆነ አብም እየሱስ ካልሆነ ሁለቱም አምላክ ከሆኑ እንዴት አንድ አምላክ ነው ምናመልከው ይባላል” ሲል ይጠይቃል ሌላው ”እየሱስም አብም አንድ ወጥ አካል ናቸው እንዳንል መፅሀፍ የቃወመናል ” ሲል ሚለው ሚያስበው እስኪጠፋው ድረስ እራሱን ያስጨንቃል፡፡ ቢሆንም ግን መልስ ሚባል ነገር ኢንጅሩ!! ወፍ የለም፡፡

የሖነ ሆኖ ጊዜ እንዲህ እንዲህ እያለ በ3ተኛው ክ/ዘመን የ አሌክሳንደሪያው ምሁር እና አርቆ አሳቢ ኦሪገን ብቅ አለ፡፡ ይህ ሰው የ አዲስ ኪዳን እና ብለዩይ ኪዳን ተንታኝ ፅሁፎችን በመፃፍ ይታወቃል፡፡ በመስኩ እጅግ ብዙ ፅሁፎችን እንደፃፈ የታሪክ ቢነግረንም ግና የሱ መፅሀፎች ጠፍተዋል አሊያም ደግሞ ሆን ተብሎ እንዲወድሙ ተደርገዋል፡፡ ኦሪገን ልክ እንደ ቀድሞ ቀሳውስት እንዲሁም የ ሐይማኖት አባቶች እየሱስ እንዴት አማላክ እንደሆነ እና ከ አብ ጋር እንዴት አንድ እንደሆነ ለማብራራት የራሱን ፅንሰ ሐሳብ እና አስተምሮ ይዞ ብቅ ቢልም በወቅቱ የነበሩት የሐይማኖት አባቶች ሊሰሙት አልፈለጉም ”መስሚያ የለንም” ነበር ያሉት ፡፡ ምክንያቱም እነሱ ወደ ፈለጉት አቅጣጫ ባለማምራቱ ይህ የኦሪገን ፅንሰ ሐሳብ ተቀባይነት ያጣ ዘንድ የተደረገው ብርቱ ጥረት እና ልፋት ፍሬ በማፍራቱ ወዲያውኑ የሱ ፅንሰ ሐሳብ ውድቅ ተደረገ፡፡(41)

የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ጅምር እና እድገት
በወቅቱ ተርቱሊያን እና ሂፖላይተስ በመባል የሚታወቁት የሐይማኖት አባቶች ስለ እየሱስ ምንነት ለማብራራት ይሞክሩ እንጂ እየሱስ በሰውነቱ እና በፈጣሪ ነቱ ስላለው መሰረታዊ ባህሪ ለመተንተን አልደፈሩም፡፡ ቢሆንም ግን በወቅቱ የ ነበራቸው እና ያንፀባርቁት የነበረው አቋም ተቃራኒ ቡድኖችን የፈጣሪን ምንነት በ ሶስት አይነት መልኩ ይረዱት ዘንድ አስገድዷቸው ነበር፡፡ ይህም ሲባል ፈጣሪ በህልውናው አንድ ሲሆን ግን በሶስት መልኩ ተገልጧል የሚለው አስተሳሰብ በአረዳድ ደረጃ ይይዙት ዘንድ ምክንያት ሆኗቸው ነበር፡፡ በወቅቱ ሂፖላይተስ እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል ” ፈጣሪ በሐይሉ አንድ ነው ፣ ሀይሉን በመጠቀምም አንድ ነው ግና በመገለፅ ሶስት ነው”(42) ቱርቱሊያንም ፈጣሪ አንድ ወጥ ሲሆን በሶስት እንደተገጠ አትቷል፡፡ የሆነ ሆኖ ስላሴ የ ሚለውን ቃል ለመጀመሪያ የተጠቀመው ቱርቱሊያን እንደሆነ የታሪክ ዘገባዎች ያትታሉ፡፡(43)
ኒቅያያዊው ሐረካትን በ ጨረፍታ

ይህ በእየሱስ ምንነት እና ማንነት ላይ ረፍት ነሺ የሆነው የቃላት ጦርነት እና የ አስተሳሰብ ልዩነት እየተጧጧፈ ያለምንም ገላጋይ ፐሮቶ ኦርቶዶክሱን አለም ያተራምሰው ገባ ፡፡ በወቅቱ በነበሩት የሐይማኖት አባቶች መካከል ያለው ልዩነት እየበረከተ ሄደ ፡፡ ይህ ሁኔታ እስከ 4 ተኛው ክፍለ ዘመን ድርስ ቀጥሏል፡፡በ 4ተኛው ክ/ዘመንም የስላሴን ምንነት ይዘው የተነሱ የፕሮቶ ኦርቶዶክስ አቀንቃኞች ነበሩ ቢሆንም ግን አብ እየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ አምላክ ናቸው ወይስ አምላክ አንድ ነው የሚው አጀንዳ እጅግ ሲያጨቃጭቃቸው ነበር ፡፡ በወቅቱ ያሁኑ የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ ተቀባይነትን አላገኘም ነበር አንድም ሶስትም የሚለው ኢ-ሂሳባዊ ስሌትም አልተጠነሰሰም ነበር ፡፡ ግን የሶስቱ ማለትም የ አብ የ ወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ምንነት ላይ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ነበር፡፡ ይህም ንትርክ ነው በ4-5 ክ/ዘመን በተደረጉ ጉባኤዎች አማካኝነት ለ ስላሴው ፅንሰ ሐሳብ መፅደቅ ምክንያት የሆነው ይህንንም ፅንሰ ሐሳብ የተቃወመም በ ክህደት ወይም ንፍቅና ይፈረጅ ዘንድ ሰበብ የሆነው፡፡ ………..

ከኒቅያው በፊት የነበሩ ውዝግቦችን መጥቀስ ካስፈለገ በ ወቅቱ በ አሌክሳንደሪያ የነበረው እውቁ የ ሐይማኖት ምሁር አሪዮስ እና በ አሌክሳንደሪያው ጳጳስ አሌክሳንደር መካከል የነበረውን ውዝግብ ማየት ይቻላል ምናልባት አንድ ክርስትያን አርዮስ ብሎ ሲሳደብ ሰምተሀው ከሆነ ለምን እንዲህ ብሎ እንደተሳደበ ብትጠይቀው የሓይማኖት አባቶቹን ጠይቆ ሲያበቃ “ የእየሱስ አምላክነት ላይ እንዲሁም የስላሴ ምንነት ላይ ክህድት የፈፀመ መናፍቅ እንደነበረና እሱም በዚህ ምክንያት አርዮስ ብሎ ለመሳደብ እንደበቃ ሳይጨምር ሳይቀንስ ይነግርሐል፡፡ ይህም ሆነ ያ ይህ ስለ እየሱስ ምንነት እና ማንነት የነበረው ውዝግብ እስከ ኒቅያው ጉባኤ ድረስ ቀጥሏል… እኛም እንቀጥል …..

ነገሩ እንዲህ ነው በ312 ቆንስጣንጢን የተባለ ሰው ወደ ንግስናው መንበር ይመጣል፡፡በ ወቅቱ ይህ በ እየሱስ ማንነት ላይ የነበረው ንትርክ ጣሪያ የነካበት ወቅት ስለነበር የዚህን ንጉስ ትኩረት ለመሳብ ችሏል፡፡ በ 324 አ.ል ንጉስ ቆንጣንንጢን የምስራቁን ንጉስ ሊሲኒዮስ ድል አደረገ፡፡ ድል አርጎም ሲያበቃ በምስራቁ አለም የነበረውን የክርስትናን ጉዳይ ያጤነዋል፡፡ እናም በወቅቱ አብያተ ክርስትያናት በዚህ የእየሱስ ማንነት ላይ ከባድ ንትርክ ውስጥ ነበሩ(44)፡፡ ይህ ጉዳይ ትኩረት በመቸር ቆንጣንጢን ሲያወጣ ሲያወርድ ቆየ ፣ ጊዜም ወስዶ አሰበ እናም እንደ ድንገት አንድ ሐሳብ ብልጭ አለበት፡፡ ፊቱም በደስታ ፈንድሻ የተረጨበት መሰለ ፣ ይህም ሀሳብ ምን መሰለ እነዚህ ሚነታረኩ ቀሳውስትን መሰብሰብ ከዛም አንድ ወጥ የአምነት መሰረት ማቆም ፡፡ ይህ ለቆንስጣንጢን ትልቅ ፖለቲካዊ ድል ነበር፡፡ ለምን? ካልክ አንድም ቆንስጣንጢን በ መስራቅ በነበሩ አብያተ ክርስትያናት ተቀባይነት ያገኛል ማህበረሰቡንም በሰላም ይገዛል፡፡ በወቅቱ ቆንሳጣንጢን ክርስትያን ነበር ወይስ አልነበረም የሚለው አጀንዳ አከራራሪ ቢሆንም ቆንስጣንጢን ክርስትያን አልነበረም የሚለው ዘገባ ሚዛን ይደፋል፡፡ ምክንያቱም “ቆንስጣንቲን የተጠመቀው ከ መሞቱ ከጥቂት ጊዜያት በፊት ነውና” (45) (ዊኪፓይዲያ)

ያልተጠመቀ ክርስትያን አይደለም በሚለው መርህ ከተስማማን ቆንስጣንጢን በ ወቅቱ ጉባኤ ሲያካሂድ ክርስትያን እንዳልነበረ ሁሉንም የሚያስማማ ሐሳብ ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ ንጉስ ቆንስጣንጢን አምኖበትም ይሁን ለፖለቲካ ይህ ንትርክ ማብቂያ ይኖረው ዘንድ በ325 አ.ል ስብሰባ ጠራ ይህም ስብሰባ የ ኒቅያ ጉባኤ በሚል የ እምባሻ ስም ይታወቃል፡፡

ይህ ጉባኤ በ 325 በኒቅያ የተካሄደ ሲሆን 318 ጳጳሳትን አቅፏል ከነዚህ እነዚህ ጳጳሳት ከ አንዱ በስተቀር ሁሉም ምስራቃውያን እንደሆኑ የታሪክ ዘገባዎች ያትታሉ ይህን በተመለከተ እውቁ የታሪክ ምሁር ፊሊፕ ስቻፍ እንዲህ ሲል ፅፏል
“The original Nicene Creed dates from the first oecumenical Council, which was held at Nicæa,
A.D. 325, for the settlement of the Arian controversy, and consisted of 318 bishops, all of them“
From the East (except Hosius of Spain).”(46)

ይህ ምሁር በ እንቅጩ እንደነገረህ በጉባኤው ከተሳተፉ ቀሳውስት መሃል ምስራቃዊ ያልሆነው የስፔኑ ሆሲዮስ ብቻና እና ብቻ ነው፡፡
በዚህም ስብሰባ ተካፋይ የሆኑት ቀሳውስት የክርስትናን እምነት መሰረት ነው ሲሉ አንድ የጋራ መገለጫ አወጡ ይህም እንደወረደ በ ኢንተርናሽናሉ ቋንቋ በዚህ መልኩ ይነበባል፡፡
NICENE CREED
We believe in one God, the Father, almighty, maker of all things visible and invisible; And in one Lord Jesus Christ, the Son of God, begotten from the Father, only-begotten, that is, from the substance of the father, God from God,
Light from light, true God from true God, of one substance (h o m o o u s i o s) with the Father, through whom all things came into being, things in heaven
and things on earth, who because of us humans and because of our salvation came down and became incarnate, becoming human, suffered and rose on the third day, ascended to the heavens, will come to judge the living and the dead
And in the Holy Spirit. (47)

በፌደራሉ ቋንቋ እንደወረደ ሲተረጎም
“በ አንዱ አምላክ አመንን፣ አባት ሁሉን ቻይ ፣ የሚታየውን እና የማይታየውን የፈጠረ እንዲሁም በ አንዱ ጌታ እየሱስ ፣ የአምላክ ልጅ፣ ከአባቱ የተወለደ( begotten) ብቸኛ የተወለደ ፣ ከአባቱ ውቅረ ነገር የተወለደ፣ ከ አምላክነቱ አምላክ፣ ከብርሀኑ ብርሀን፣ ከእምነተኛ አምላክነቱ እውነተኛ አምላክ ፣ አንድ ውቅረ ነገር( (ὁμοούσιον)( h o m o o u s i o s ወይም substance) ከ አባቱ ጋር ፣ ሁሉም በሰማይ እና በምድር ያለ በሱ በኩል ነው የመጣው፣ በኛ ሰዎች ምክንያት እና ለኛ ሰዎች ደህንነት ሰው ሆኖ መምጣት ያስፈለገው ፣(እንዲሁም) ተሰቃየ በ ሶስተኛውም ቀን ተነሳ (ከዛም) ወደ ሰማይ አረገ፣ በህያው እና በሙታንም ሊፈርድ ይመለሳል ፡፡ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ (አመንን)፡፡”
በዚህ መልኩ ለመጀመሪያ በቀሳውስት አማካኝነት እየሱስ አምላክ ነው የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ በ አብላጫ ድምፅ አፀደቁት የ እምነትም መሰረት አደረጉት ከዚህ በኋላ እየሱስ ሰው ነው አምላክ አደለም የሚሉ ቡድኖች እንዲሁም እየሱስ ሰውን ለመምሰል ነው የመጣው በስጋ አልመጣም የሚሉ ሁሉ “መናፍቅ ” የሚል የዳቦ ስም እየተሰጣቸው ጭንቅል ጭንቅላታቸው ተቀወሩ ልክ እንደ ነ አርዮስ አይነቶቹም ተወገዙ፡፡ ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት መሰረት ኖረው ፡፡ ከዚህ ውጪ ያሉ ክርሰትናዎች የመጀመሪያዎቹን ጨምሮ የሚያምኑበት ፅሁፍ እና መፅሀፍት እንዲወድሙ ተደረጉ ወደ 300 ከሚሆኑ ወንጌሎች ውስጥ አራቱ ወንጌሎች ብቻ ፅደቁ(48)(እየሱስ የ ኢስላም ነብይ)ኒቅያዊው ሐረካት ይልሐል ይህ ነው፡፡

በዚህ በኒቅያው ጉባኤ እግዚአብሄር እና እየሱስ ሲሆኑ አምላክ የተደረጉት መንፈስ ቅዱስ አምላክ አልተደረገም ነበር፡፡ አዎ አምላክ ነው የሚለው ቃል የጋራ መግለጫ ውስጥ አልነበረም ነበር፡፡ እናስ ? እናማ አሁንም የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት ለማፅደቅ ሌላ ጉባ ኤ ሊያስፈልግ ነው ፡፡

የ ኮንስታንቲኖፕሉ ሁለተኛ ጉባኤ - የ መንፈስ ቅዱስ አምላክነት
እናም እዚም እዚያም የተበታተኑት ጳጳሳት በ 4ክ/ዘመን መጨረሻ ንጉስ ቲኦድዮስ የመጀመሪያው አማካኝነት ዳግም ተሰባሰቡና በ 381 አ.ል በ ኮንስታንቲ ኖጵል ስብሰባ ተቀመጡ፡፡ ስብሰባውም የተፈለገው የኒቂያዊውን መግለጫ ለማሻሻል ነበር ሚጨመረውን ለመጨመር የመንፈስ ቅዱስም አምላክነት የ እምነት መሰረት የሆነው በዚህ ጉባኤ ነበር ፡፡ ከዛ በፊት በኒቅያው መንፈስ ቅዱስ አምላክ አልነበረም ይህን ተመልክቶ ሲያበቃ M. A. C. Cave እንዲህ ሲል ፅፏል ፡፡

“In fact, it was the outcome of the Council of Constantinople in 381 C.E. which agreed to place the Holy Spirit in the same stature as God and Jesus Christ.”(49)
በኔው አማርኛ ሲተረጎም
“በእርግጠኝነት የ መንፈስ ቅዱስ (አምላክነት) የ ኦንስታንቲኖፕሉ ጉባኤ (381) ውጤት ነው፡፡መንፈስ ቅዱስ ልክ ከ አምላክ እና እየሱስ እኩል እንደሆነ የተስማሙበት …”
ይህን ስልህ እንዴት ? ማለትህ አይቀርም እንዴት እንደሆነ እና የ ኮንሰታንት ኖፕሉ ቃል ከ ኒቅያው በ ምን እንደሚለይ ቀጥለህ ተመልከት ግና ከ ኒቅያው ጋር ተመሳሳይ እንዳይመስልህ ተረጋጋና አንብበው፡፡


CONSTANTINOPOLITAN CREED
“We believe in one God, the Father, almighty, maker of heaven and earth, of all things visible and invisible;
And in one Lord Jesus Christ, the only-begotten Son of God, begotten from the Father before all ages, light from light, true God from true God, begotten
not made, of one substance (h o m o o u s i o s) with the Father, through whom all things came into existence, who because of us humans and because of our salvation came down from heaven and was incarnate from the Holy Spirit and the Virgin Mary and became human and was crucified for us under Pontius Pilate
And suffered and was buried and rose again on the third day according to the Scriptures and ascended to heaven and sits on the right hand of the Father and Will come again with glory to judge the living and the dead, of whose kingdom there will be no end; And in the Holy Spirit, the Lord and life giver, who proceeds from the Father, who with the Father and the Son is together worshipped and together glorifled, who spoke through the prophets; in one holy Catholic and apostolic church. We confess one baptism for the remission of sins;
We look forward to the resurrection of the dead and the life of the world to come. Amen.”(50)

የኮንታንቲኖፕሎ የእምነት መሰረት በፌደራሉ ቋንቋ በዚኅ መልኩ ይተረጎማል

“በ አንዱ አምላክ አመንን፣ አባት፣ ሁሉን ቻይ ፣የሰማያት እና የምድር ፈጣሪ የሚታየውን እና የማይታየውን የፈጠረ እንዲሁም በ አንዱ ጌታ እየሱስ ፣ ብቸኛው የአምላክ ልጅ፣ ከጊዜያት በፊት ከአባቱ የተወለደ( begotten) ፣ ከብርሀኑ ብርሀን፣ ከእምነተኛ አምላክነቱ እውነተኛ አምላክ ፣ የተወለደ ግን ያልተሰራ አንድ ውቅረ ነገር( (ὁμοούσιον)( h o m o o u s i o s ወይም substance) ከ አባቱ ጋር ፣ ሁሉም በሰማይ እና በምድር ያለ በሱ በኩል ነው የመጣው፣ በኛ ሰዎች ምክንያት እና ለኛ ሰዎች ደህንነት ሰው ሆኖ መምጣት ያስፈለገው ፣(እንዲሁም) በ ድንግል ማርያም እና መመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተወለደ ሰው ሆነም ከጲላጦስም (ጊዜ) ለኛ ሲል ተሰቀለ ፣ ተሰቃየ እናም ተቀበረ መፅሀፍ እንደሚለውም በ ሶስተኛው ቀን ተነሳ ወደ ሰማይም አረገ ከአብም በቀኝ በኩል ተቀመጠ ፣ በሙታን እንሁም በ ህያዋን ላይ ሊፈርድ ዳግም ከ ክብር እና ከፍርድ ጋር ይመጣል እናም ንግስናው መጨረሻ አይኖረውም፡፡ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ፣ ጌታ ነው ህይወት ሰጪ ነው፣ ከ አብ ይመነጫል ፣ከ አብ እና ከወልድ ጋር አብሮ ይመለካል ፣ በነብያት ውስጥ ሆኖ ሚናገረው እሱ ነው፡፡ እንዲሁም በአንዱዋ ካቶሊክ እና የሐዋሪያት አብያተ ክርስትያን. እና ሐጥያትን በሚሰርይ አንድ ጥምቀት ፣ የሙታን ትንሳኤን እንዲሁም የሚመጣውን አለም እናያለን አሜን”
ተመልከት በ ኒቅያው ጉባኤ አምላክ ያልነበረው መንፈስ ቅዱስ በዚህ ጉባኤ የ አምላክነት ስልጣን አገኘ ከ አብ ከወልድ እና ከ መንፈስ ቅዱስ ጋር እሱም ይመለክ ዘንድ ታወጀ! የዛን ጊዜ አዋጅ ነው አሁንም ድረስ ላለው ክርስትና መሰረት የሆነው፡፡
እናም ለማለት የፈለኩት ወልድ ሲደመር መንፈስ ቅዱስ አምላክ የሆኑት በቀሳውስት ውሳኔ ሆነ ያውም በ 4 ተኛው ክ/ዘመን ይህን የተቃወመ ማንም ሰው ክርስትያንነቱን ማጣቱ ነው ፡፡ ቀጣዩ ጥያቄ አንድም ሶስትም የሚለው ፎርሙላስ መች ብቅ አለ የሚል ጥያቄ ሲሆን ይህም ጥያቄ ወደ አትናሳያኑ አቂዳ ይመራናል…………….

የ አትናስያኑ አቂዳ (The Athanasian creed)

ይህ አቂዳ በላቲኑ Quicumque vult በመባል ይታወቃል (51) የዛሬው ክርስትና የስላሴ አስተምህሮ መሰረት ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ ካስታወስክ በ ምእራፍ አንድ ላይ ስለዚህ አቂዳ የእምነት ቃል ካቶሊክ ኢንሳይክሎፓይዲያን ጠቅሼ አስነብቤህ ነበር፡፡ ለማሰታወስ ይጠቅምህ ዘንድ ዊልያም ዊልሰን ስቴቨን የስላሴ አስተምህሮትን በተነተነበት መፅሀፉ ይህን አስመልክቶ የፃፈውን እንደወረደ አንብብልኝ
"The doctrine of the Trinity states that the Father is God, the Son is God, the Holy Spirit is God and together, not exclusively, they from one God.”(52) እንዲህም ተብሎ ይተሮጎማል “የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ የሚያትተው አብ አምላክ ነው ወልድ አምላክ ነው መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው፡፡ ለየብቻ ሳይሆን በጥምር አንድ አምላክን ይመሰርታሉ” ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያም ተመሳሳይ ሐተታን አትቷል፡፡ ሌላው እንዳትስት ምፈልገው ይህ አቂዳ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ጨምሮ አትቷል፡፡ ይህን ማየት ካስፈለገ የአትናትያስ አቂዳ ነው ከተባለው ፅሁፍ የተወሰነውን መስመር ልምዘዝ
“……For each person -- the Father, the Son, and the Holy Spirit -- is distinct, but the deity of Father, Son, and Holy Spirit is one, equal in glory and coeternal in majesty.”(53)

ወይም “እያንዳንዳቻው አካላት - አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ - የተለያዩ ናቸው - ግን የአብ የወልድ አና የመንፈስ ቅዱስ አምላክነት አንድ ነው….”
ይህ ነው እንግዲህ የ አትናሲያኑ አቂዳ ለማስታወስ ያክል ይህን ካልኩህ ሚቀጥለው ቀጣይ የዚህ አቂዳ መሰራች ማን ነው ፡፡ መችስ ተጀመረ የሚል ይሆናል? አንዳንድ ቀላጅ ክርስትያኖች ምህረት ጨምሮ ይህ አስተሳሰብ ከብሉይ ኪዳን ጊዜ ጀምሮ እንደነበር ሲማጎቱ ሰምተን “ለቸርች ነው ” ብለን ሰምተን እንዳልሰማን አልፈነዋል፡፡ አንዳንድ አክራሪ ክርስትያኖቸ ደግሞ የዚህ አቂዳ መስራች የ አሌክሳንደሪያው ጳጳስ አትንቲዮስ (293-373 AD) ሲሉ አንድምጠናል፡፡ እነዚህ ምሁራዊ አግባብ በሆነ መልኩ ያልተቃኙት የክርስትና ተከታዮች ይህን ይበሉ እንጂ የ ዚህ አቂዳ ወይም አስተምሮ መስራች የ አሌክሳንደሪያው ጳጳስ አትናቲዮስ እንዳልሆነ በምሁራን መሃል ስምምነት አለ፡፡ በሙስሊም ምሁራን አላልኩም፡፡ በክርስትያን ምሁራን ነው ያልኩት የሆነ ሆኖ ይህን ስልህ ግር ይልህ ይሆናል http://christianity.about.com/ የተሰኘው ድህረ ገፅ ይህን ጉዳይ በተመለከተ እንዲህ ሲል ፅፏል
“The Athanasian Creed, one of the lesser known Christian faith statements, is often attributed to Athanasius (293-373 AD), bishop of Alexandria. However, most church scholars believe the statement was written much later, because it was not mentioned at all in early church councils and first appeared in churches in Gaul, North Africa, and Spain.”(54)

“የ አትናሲያኑ አቂዳ በክርስትና የእምነት ቃል ውስጥ በትንሹ ከሚታወቁት ውስጥ አንዱ ነው ፣ አትናቲዮስም አንደፃፈውም ይነገራል ፡፡ ግን አብዛኛው የ ቤተክርስትያን ሊቃውንት እንደ ሚያምኑት ከ አትናቲዮስ ከ ብዙ ጊዜ በኋላ ነው የተፃፈው ፣ ምክንያቱም በጥንታውያን የ ቤ/ክርስትያን ጉባኤዎች ውስጥ በ አንዱም አልተጠቀሰም ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ ብቅ ያለው ጋሉ፣ሰሜን አፍሪካ እና ስፔን ውስጥ በ ሚገኙ ቤ/ክስትያኖች ነው”
http://www.livinghopelc.net/ የተሰኘው ድህረ ገፅም ይህ የ እምነት መሰረት (አቂዳ) የተፃፈበትን ጊዜ በተመለከተ የምለው አለኝ ይላል፡፡
“The Creed was most likely written sometime after 450 and well before 670. Beyond that knowledge, the actual author or authors and the time of writing are unknown.”(55)
“ይህ የ እምነት መሰረት ከ 450 በኋላ እና ከ 670 በፊት ባሉት ጊዜያት እንደተፃፈ ይገመታል፡፡ ከዚህ በዘለለ የፃፈው ሰው ማንነት እና መች እንደፃፋ አይታወቅም”
ይህ የ አትናሲያን አስተምሮ እንስከ አስራ አንደኛው ከፍለዘመን ድረስ አይታወቅም ይለናል እውቁ የታሪክ ምሁር ፊሊፕ ስቻፍ ፡፡ ምን ነበር ያልከው?
“….while the Greeks did not know it till the eleventh century…” (56)
“( አትናሲያኑን አቂዳ) ግሪኮች እስከ አስረ አንደኛው ክ/ዘመን ድረስ አያውቁትም ነበር”
ቀጣዩ ጥያቄ ለምን ይህ አቂዳ የ አትናቲዮስ ሳይሆን የሱ ነው ተባለ? ማንስ አለው ? የሚለው ሲሆን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሊሆን የሚችለውን የ ፐሂሊፕ ስቻፍ ንግግርን እንምዘዝ
“Since the ninth century it has been ascribed to Athanasius, bishop of Alexandria……” (57)
“ከዘጠነኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ነው ይህ ፅሁፍ የ አትናቲዮስ ነው የተባለው”

ማንስ አለው ብለህ ብትጠይቀኝ የፕሮቶ ኦርቶዶክስ ወይም እራሳቸውን ካቶሊክ ሲሉ ሚጠሩት አቀንቃኞች እልሀለው፡፡ ለምን ከተባለ ለምን መሰለህ አብ ወልድ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ አምላክ ናቸው ከተባለ ሰው ሁሉ ሶስት አምላክ የሚለው ነገር ይገነዘባል፡፡ ይህን ሁኔታ ቀድመው የተገነዘቡት የዚህ አንጃ አቀንቃኞች አዲስ የ እምነትን ቃልን መሰረቱ ይህም የእምነት ቃል ክርስትና የ አንድ አምላክ እምነት መሆኑን ለማሳየት የተፈበረከ ቃል ነው፡፡ ይህም ከላይ ያየሀው የ አትናሲያን ቃል፡፡ እናም ይህ በ አምስተኛው ክፍለ ዘመን የተፈበረከው አስተምህሮ አንድም በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ሰለ ተፈለገ የ አትናቲዮስ አቂዳ የሚል የ እንባሻ ስም ሰጡት ፣ አትናቲዮስ ሳይፅፈው እሱ ነው የፃፈው ሲሉ ቀጠፉ እናም አሰራጩት ፡፡ እስከ ዛሬም ድረስ የ አትናቲዮስ ፅሁፍ ነው ተብሎ ይነገርሀል…. እውነት እውነት እልሀለው ይህ ፅሁፍ በ አንዱም የ አትናቲዮስ ፅሁፍ ውስጥ አልተዘገበም ይህን እውነታ አጥንቶ ሲያበቃ ፐጂሊፕ ስቻፍ እንዲህ ሲል ቢፅፍ አይገርምም

“The Symbol is no where found in the genuine writings of Athanasius…….” (58)

“ይህ የእምነት መሰረት በ የትኛውም የ አትናቲዮስ ትክክለኛ ፅሁፎች ውስጥ አልተገኘም”

ይህ የ አትናስያን አቂዳ ነው ለዛሬው የክርስትና እምነት መሰረት የሆነው፡፡ እናም ሚሽነሪው ተቀብሎ ሊያስተጋባው የቻለው፡፡ ከላይ በምእራፍ አንድ እንዳየሀው ይህ አስተምሮ በ ምንም መልኩ አንድ አምላክ ነው ምናመልከው ብለው ከሚነግሩን ፅንሰ ሐሳብ ጋር አይሄድም ….

ማጠቃለያ

ይህ ከላይ የተመለከትከው የክርስትና እምነት የመጀመሪያ ይዘቱ እና እድገቱን እስከ ስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ድረስ በ አጭሩ ነው ፡፡ የሆነ ሆኖ የክርስትና እምነትን በ ምንተነትንበት ሌላ ፅሁፋችን በሰፊው እንመለከተዋለን ፡፡ ቢሆንም ግን ይህ ፅሁፍ የተፃፈበት ዋና አላማ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ጅምር እና እና እድገት አስመልክቶ የሚነሳውን መሰረታዊ ጥያቄ ማለትም መች እና የት የሚለውን ለመመለስ ነው፡፡በተያያዥነት አንዳንድ ሚሽነሪዎች ምህረታብን ጨምሮ ይህ ፅንሰ ሐሳብ ከ ብሉይ ኪዳን ጀምሮ እንደነበረ ለማሳየት የመኮሩትን አግባብ አለመሆኑን ለማሳየት ነው …. ኢንሻ አላህ በ ምእራፍ ሶስት ላይ ከብሉይ ኪዳን እንዲሁም ከ አዲስ ኪዳን የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ያመላክታሉ ተብለው የቀረቡትን አንቀፆች ምሁራዊ በሆነ መልኩ እንመለከታቸዋለን እስከዛው ግን በትእግስት ጠብቁን እንላለን፡፡

Reference sources
30. Bart D. Ehrman: Jesus interrupted, (Revealing the Hidden Contradictions in the Bible and Why We Don’t Know about them).
31. http://en.wikipedia.org/wiki/List_of_Ch ... ominations
32. It was found in The Gospel of Philips.
33. Bart D. Ehrman, New Testament: Ahistorical Introduction to early Christian Writings pp. 3-4
34. ibid pp. 4-5
35. ጊኖሲስ ማለት የግሪክ ቃል ሲሆን እውቀት ማለት ነው፡፡
36. Bart D. Ehrman, New Testament: Ahistorical Introduction to early Christian Writings pp. 5-6
37. Bart D. Ehrman: Lost Christianity: The battles for scripture and the faith we never knew. Pp. 136
38. Docetism - the doctrine that Christ’s body was not human (being either a phantasm or of real but celestial substance) and that therefore his sufferings were only apparent
39. Bart D. Ehrman Lost Christianity: The battles for scripture and the faith we never knew. Pp. 152
40. ibid pp.153
41. ibid pp.155
42. ibid. 156
43. ibid
44. Bart D. Ehrman, Christianity in late antiquity pp.251
45. http://en.wikipedia.org/wiki/Constantine_the_Great
46. Schaff Philip, The creed of Christendom vol.1 pp.40 6 Ed.
47. Bart D. Ehrman, Christianity in late antiquity pp.252
48. Jesus the prophet of Islam.
49. M.A.C. Cave, Is trinity doctrine divinely inspired?
50. Bart D. Ehrman, Christianity in late antiquity. Pp 257
51. http://en.wikisource.org/wiki/Special:S ... sian_Creed
52. William Wilson Stevens: Doctrine of the Christian Religion pp. 113-122
53. http://www.livinghopelc.net/Athanasian_Creed.htm
54. http://christianity.about.com/lr/the_at ... 1029948/1/
55. http://www.livinghopelc.net/Athanasian_Creed.htm
56. Schaff Philip, The creed of Christendom vol.1 pp.50
57. ibid
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Sep 09, 2013 11:52 pm

ስለ መሰቀሉና ሞቶ ስለመነሳቱ የተፃፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እውነት ከሆኑ ለምን እርስ በርስ ይጋጫሉ?^*^*^

****ምንም እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሰቀሉ፤ ከደሙ ከኃጢያት ሊያነፃ እንደመጣ በአንደበቱ በግልጽ ያብራራበት አንድም ጥቅስ ባይኖርም እንዲሁም በቦታው ኖሮ የተመለከተ ማንም የአይን እማኝ የፃፈው ጥቅስ ባይኖርም በሰሚ ሰሚ የሆነውን የስቅለት እና የትንሳኤ ሁኔታ የፃፉ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው በተለይም ኢየሱስን በአካል አይቶት እንኳን አይቶት የማያውቀው ጳውሎስ ዘግቦታል፡፡ ጳውሎስ ኢየሱስን ክርስቶስን አይቶት አያውቅም የሰማውን ነው የጻፈው አብዛኛዎቹ ደቀመዛሙርቶቹም ይህንኑ ነው ያደረጉት ለምሳሌ ሀዋርያው ሉቃስ የሰማሁትን እንዳየሁ አድርጌ እጽፋለሁ ብሏል ይህ ታዲያ ትክክለኛ ሀይማኖታዊ አካሄድ ነውን?

***በመሆኑ ይህ ዘገባ የአይን እማኝ ባለመኖሩና መረጃ አልባ በመሆኑ፤ በሰሚ ሰሚ የተፃፈ በመሆኑ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ስቅለት የተነገሩ ትቅሶች እርስ በርስ ይጋጫሉ፤ እስቲ ለአብነት ያህል እነዚህን ጥቅሶች እንመልከት፡-

≠ የማርቆስ ወንጌል 15፡25 ‹‹ኢየሱስ ሲስሉት ጊዚው ‹‹ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት›› ነበር፡፡››

≠ ዮሐንስ ወንጌል 15፡25 ‹‹የፋሲካ ዝግጅት ነበር ጊዜውም ወደ ‹‹ስድስት ሰዓት›› ነበር በዚያን ጊዜ ጰላጦስ አይሁዳውያኑን ‹‹እነሁ ንጉሳቸው›› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ‹‹ወዲ ውሰደው ወዲያ ወስደህ ስቀለው›› እሉ ጮሁ፡፡

^^ ኢየሱስ ስንት ሰዓት ነው የተሰቀለው 3 ሰዓት ዌም 6 ሰዓት?

≠ ማቴዎስ ወንጌል 27፡17 ‹‹ከገዚው ግቢ ሲወጡ ‹‹ሰምኦን›› የተባለው የቀሬና አገር ሰው አገኙና የኢየሱስን መስቀል ‹‹እንዲሸከም አደረጉት››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 19፡17 ‹‹ከዚህ በኃላ ‹‹ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ›› የራስ ቅል ወደ ሚባል ስፍራ ወጣ››

^^ መስቀሉን ማን ተሸከመ ኢየሱስ ወይም ስምኦን?

≠ ማቴዎስ ወንጌል 28፡1 ‹‹ሰንበት ካለፈ በኃላ ‹‹መቅደላዊት ማርያም ፤ ሌላይቱ ማርያም ›› መቃብሩን ለማየት ሄዱ››

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡1-2 ‹‹ሰንበት ቀን ካለፈ በኃላ ‹‹መቅደላዊት ማርያም፤ የያዕቆብ እናት ማርያም፤ ስሎሜም›› ሆነው የኢየሱስን አስክሬን ለመቀባት ሽቶ ገዙ፡፡ እሁድ ጠዋት ልክ ፀሐይ ስትወጣ ወደ መቃብሩ ሄዱ፡፡››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 20፡1 ‹‹እሁድ ጠዋት በማለዳ እና ጎህ ሳይቀድ ‹‹መቅደላዊት ማርያም›› ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች፡፡››

^^ ወደ ኢየሱስ መቃብር የሄዱት እነማን ናቸው?

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡5 ‹‹ወደ መቃብሩም በገቡ ጊዜ ነጭ ‹‹ልብስ የለበሰ ጎልማሳ›› በስተቀኝ በኩል ተቀምጦ በማየታቸው ደነገጡ››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 20፡12 ‹‹የኢየሱስም አስክሬን በነበረበት ስፍራ ‹‹ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላዕክት›› ንዱ በራስጌ አንዱ በግርጌ ተቀምጠው አየች››

^^ መቃብር ውስጥ የነበረው ማነው?‹‹ነጭ ልብስ ጎልማሳ ወይም ሁለት መላዕክት?

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡8 ‹‹ሴቶቹም በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ከመቃብር ወጥተው ሸሹ እጅግ ፈርተው ስለነበረ ‹‹ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም››

≠ የሉቃስ ወንጌል 24፡8-9 ‹‹ሴቶቹ የኢየሱስን ቃል አስታወሱ ከመቃብር ተመልሰው ‹‹ይህንን ሁላ ለአስራ አንዱና ለቀሩትም ነገሩዋቸው፡፡››

^^ ሴቶቹ ተናግረዋል ወይስ አልተናገሩም?

****ከጥቅሶቹ በግልጽ እንደምንረዳው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልም ሆነ ከሞት መነሳት ተፅፈዋል የተባሉት መረጃዎች እርስ በርሳቸው እንደሚቃረኑ ነው፡፡ እውን ስቅለቱ እውነት ቢሆን ለምን ጠንካራ መረጃ ጠፋለት? በመሰረቱ የተጋጩ ሀሳቦችን አምኖ መቀበል ልክ ነውን?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests