ፓስተር ክሪስ መጽሀፍ በትርጉም

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ፓስተር ክሪስ መጽሀፍ በትርጉም

Postby ቀዳማይ » Sat Sep 14, 2013 3:20 pm

ሰላምና ጤና ለሁላችን እየተመኘው የፓስተር ክሪስን ትምህርቶች እየተረጎምኩኝ ለማቅረብ ከፍተኛ ፍላጎት ነበረኝ ዛሬ ግን ጨከን ብዬ ይዤላችሁ ቀርቤያለው:: አብረን እንከታተለው መልካም ንባብ::

ለዛሬ የመረጥኩት መፅሀፍ 'በትክክለኛው መንገድ መፀለይ" የሚለውን ነው::

መግቢያ

አንድ ግዜ ስለ ቻርልት ግራንድሰን ፊኒ ቀልቤን የሳበ ጹሑፍ አንብቤ ነበር:: እንዲህም ብሎ ነበር በየግዜው ቤ/ክርስቲያን ቢሄድም ልቡን ግን ለጌታ አሳልፎ አልሰጠም ነበር:: በፀሎት ስነ-ስርአት ግዜም እምብዛም አይናገርም ነበር::

ታዲያ አንድ ቀን የቤ/ክርስቲያኑ አባላት ቻርልት ብዙ ግዜ ስትፀልይ አይተንህ አናውቅም ምክንያቱ ምን ይሆን ብለው ጠየቁት::

እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው"እዚ ቤ/ክርስቲያን ለረጅም ግዜ ብመላለስም እናንተን ስመለከት ሁል ግዜ ትፀልያላችሁ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ድረስ ለፀሎታችሁ መልስ ያገኛችሁ ግን ስለማይመስለኝ ግዜዬን አላቃጥልም ብዬ ነው የማልፀልየው" ብሎ ይመልስላቸዋል::

ይሁን እንጂ እንደገና ጌታን ተቀብሎ በመንፈስ ቅዱስ መፀለይ ሲጀምር እነዛ ሰዎች ለምን ፀሎታቸው እንደማይመለስላቸው ተረዳ:: ትክክለኛ ባልሆነ መልኩ ነበር የሚፀልዩት::

ፊኒ ይሄንን ልብ ያለው ከዛሬ መቶ አመት በፊት ነበር:: ይሁን እንጂ በዚ ባለንበት ዘመን ብዙዎች ክርስቲያኖች እንደዚህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከመንፈሳቸው ጋር ሲሟገቱ ይስተዋላሉ:: ብዙዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ልሳን የሚናገሩ, ወይም መጽሀፍ ቅዱስን እጅግ አድርገው የሚያውቁ ሆነው ሳሉ ፀሎታቸው መልስ ባለማግኘቱ ግን ተስፋ ቆርጠው ሲበሳጩ ይታያሉ:: አንዳንዶቹ ደግሞ እንዴትና ምን ተብሎ እንደሚፀለይ በፍፁም የማያውቁም አሉ::

ብዙ ሰዎች የሀይማኖታቸው ስነ-ስርአት ለማክበር ብቻ ነው የሚፀልዩት:: አንዳንዶቹ ደግሞ እግዚአብሄር እንዲፀልዩ ግዴታ የጣለባቸው ስለሚመስላቸውም የሚፀልዩ ሞልተዋል:: ይሁን እንጂ ለምን እንደሚፀልዩ የማያውቁ ብዙ ሰዎች አሉ:: አንዳንድ ግዜ መልስ እናገኝ ይሆን ብለን በመጠራጠር እንፀልያለን:: ወገኖች የእግዚአብሄር ትልቁ አላማ ግን ለኛ ፀሎት ምላሽ መስጠት ነው::

ስለ ፀሎት በተመለከት የተለያዩ አይነት ጥያቄዎች ከተለያዩ ቦታ ይመጣሉ::

ወንድም እገሌ እህት እገሊት ፀሎታቸው ሲሰማላቸው ለምን የኔ ግን ከደመና በታች ይቀራል?

ለምንስ መፀለይ አስፈለገኝ እግዚአብሄር የምፈልገውን ያውቃል ሳልፀልይ ሊሰጠኝ አይችልም?

አንዳንዱም ደግሞ 'ለመሆኑ ፀሎት ምንድን ነው?" ብሎ የሚጠይቅም አለ::

የእግዚአብሄር ቃል ፀሎትንና መልስን በተመለከተ ግልፅና ቀጥተኛ ነው:: ብዙሀኑ ፀሎቱ ያልተመለሰለት ትክክል ባልሆነ መልኩ ስለሚፀልይ ብቻ ነው:: ከእውቀት ማነስ የተነሳ ቃሉ ፀሎትን በተመለከተ ምን እንደሚል መረዳት ባለመቻላችን ፀሎታችን ሁሉ ከደመና በታች ሊቀር ችሏል::

መንፈስ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ግዜ እንዳስተምር ረድቶኛል:: ይሄንን መፅሀፍ ስናነብ ልባችንን በመክፈት የእግዚአብሄር ቃል እንዲመራን እንዲያሳየን ስህተታችንንም እንዲያርምልን እድል እንስጠው:: እንዴት አድርገንም ትክክለኛ በሆነ መልኩ መፀለይ እንዳለብን እንማራለን::

ምእራፍ አንድ
Last edited by ቀዳማይ on Tue Sep 17, 2013 2:01 am, edited 1 time in total.
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ዲጎኔ » Mon Sep 16, 2013 2:17 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ ቀዳማይ በዚህ መልካም ጅምርህ በርታ::
የቻርለስ ፊኔን የመንፈሳዊ መነቃቃት በሀገር ቤት ከሁለት አስርተአመታት በፊት አቅርቤ ነበር::ለመከረኛዋ ሀገራችንም ሆነ ለመላ አለም የነፍስና የስጋ ፈውስ የሚጠቅም ነውና ግፋበት::ጀማሪና ፈጻሚ ክርስቶስ ይርዳህ!
ዲጎኔ ሞረቴው ከሱባኤው መንደር ተሀድሶ ጽሎት ቤት
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ቀዳማይ » Tue Sep 17, 2013 2:03 am

ዲጎኔ ስለ መልካሙ አስተያየትህ ምስጋናዬን አቀርባለው:: ባልከው መሰረት እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ቶሎ ቶሎ አቀርባለሁኝ:: ዋርካ ግን አንዳንዴ አላስገባ ትላለች ወይስ ከኔ ነው ችግሩ?
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Tue Sep 17, 2013 5:51 am

ምዕራፍ አንድ-

ትክክለኛ የጸሎት መንገድ

ብዙ ሰዎች ጸሎታቸው ለምን እንደማይሰማላቸው በማሰብ ይጨነቃሉ:: ነገሮችም እንደሚፈልጉት ባለመሳካታቸው ሕይወታቸውን ያማራሉ:: ለዚህም ነው ጸሎት ትልቁ ከፈጣሪ ጋር የመግባቢያና የምንፈልገውን የምንጠይቅበት መሳሪያ በመሆኑ በትክክለኛው መንገድ መከናወን የሚገባው::

በመጀመሪያ ለጸሎት ከመነሳታችን በፊት እንዲህ ብለን ማሰብ አለብን:: እግዚአብሄር ጸሎታችንን ሰምቶ መመለስ ይፈልጋል:: ለዚህም ስለሆነ ነው መጸለይ እንዳለብን ያሳሰበን

የሚያሳዝነው ነገር ብዙ ክርስቲያኖች ይሄንን ነገር አያውቁትም ምክንያቱም በቂ ግዜ የእግዚአብሄርን ቃል በማጥናት አያሳልፉም:: በዚህም የተነሳ ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸው ግንኙነት የሻከረ ነው::

እግዚአብሄር መቀበል ከምትችሉት በላይ አብዝቶ የሚሰጥ አምላክ ነው

ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የሞላበት ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም አይቶ በፊቱ ወደቀና። ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። ሉቃስ 5:12

ይሄን ለምጽ ያለበት ሰው ብትመለከቱ የእግዚአብሄርን የመፈወስ ሀይል አልተጠራጠረም:: ኢየሱስ ለምጻሞችን እንዳነጻም ሰምቷል:: የሱ ችግር ግን ኢየሱስ እሱን እንደሚፈውሰው መጠራጠሩ ላይ ነበር::

ዛሬ በአለማችን ይሄንን የመሰሉ ብዙ ሰዎች አሉ:: የእግዚአብሄርን ሀይል ያውቃሉ በፍጹምም አይጠራጠሩም በነሱ ላይ ፍቃዱ ይሁን አይሁን ግን እርግጠኛ አይደሉም:: እንዲህም ይላሉ "እንጃ እግዚአብሄር ሊያድነኝ ፍቃደኛ መሆኑን" ፈጥነው ወደ ዶክተርም ይሮጣሉ:: እንዲያው ለነገሩ ግን ሊያድንህ የእግዚአብሄር ፍቃድ ካልሆነ ወደ ዶክተር በመሄድ መዳን ይቻላል?:: ይሄም ማለት ወደ ዶክተር በመሄድ የእግዚአብሄር ፍቃድ ያልሆነውን በማድረግ ሀጢያት ሰራንስ ማለት አይደለም?::

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:13 ላይ እንዲህ ይላል ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ጥሩ ነገር የምንፈልገው የእግዚአብሄር ፍላጎት በራሳችን ላይ ሲገለጥ ነው:: ማንም አባት ልጆቹ እሱ ባለፈበት መከራ ውስጥ እንዲያልፉ አይፈልግም:: ያም እንዳይደርስባቸው ጥንክሮ ይሰራል::

የሰው ልጅ ቤተሰቡን ከእግዚአብሄር አብልጦ ሊጠብቃቸውና ሊንከባከባቸው አይችልም:: ታላቁ እግዚአብሄር ግን በአለም ላይ ካሉ አባቶች ሁሉ የላቀ አባት ይሆናቸዋል ለልጆቻችን:: የእግዚአብሄርም ስጦታ መቀበል ሁሉ ከምንችለው በላይ ነው:: እሱም እጅግ በስራችን በኑሯችን ባጠቃላይ በሕይወታችን ሁሉ ሊባርከን ፈላጎት አለው::

ለምጻሙ ሰውዬ ኢየሱስ እንደሚያድነው ያምን ነበር:: እሱ ግን እርግጠኛ ያልነበረው ኢየሱስ ሊፈውሰው መፍቀዱን ነበር:: ይሄን አይነት ምክንያት ነው ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ማግኘት ያለባቸውን ታአምራት እንዳያገኙ ያገዳቸው:: የእግዚአብሄርን ፍቃድ አጥብቀው ይጠራጠራሉ:: አንዳንዶቹ እንዲያውም እግዚአብሄር ያሳመማቸው ትሁትና ትጉህ ሊያደርጋቸው እንደሆነ ያስባሉ:: ሌሎቹ ደግሞ አሟቸው እቤት የዋሉት እግዚአብሄር ከሌላ ችግር ሊያወጣቸው አስቦ እንዳሳመማቸው ያምናሉ::

እግዚአብሄር ልጆቹን ለማሰልጠን የሴጣን መሳሪያ አያስፈልገውም:: ለምንስ የሴጣንን መሳሪያ ለጽድቅ ይጠቀማል ሴጣን የነብሰገዳይና የውሸት አባት መሆኑን ከነገረን በሗላ?:: እግዚአብሄር እኛን ትሁት ለማድረግ የሚያሳምመን ከሆነና መድሀኒት ከወሰድንበት እግዚአብሄር እኛን አሳምሞ ትሁት የሚያደርግበትን መንገድ በመዳኒት ስለተቃወምነው የሴጣንን ስራ ሰራን ማለት አይደለም? እግዚአብሄር እንደዚህ አይነት አምላክ አይደለም::

ያለጥርጥር ግን በዚህ ዘመን ሁሉም ክርስቲያን የእግዚአብሄርን የማድረግ ጥበብና ሀይል ያምናል እግዚአብሄርንም እንደ አባታችን ተቀብለነዋል::

ለምጻሙ ሰውዬው ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ ነበር ያለው:: ማንም ሊነካው ፈቃደኛ አልነበረም ኢየሱስ ግን በጁ በመዳሰስ ፈቃደኝነቱን አሳየው:: መጽሀፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወዳለሁ፥ ንጻ አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው። እወዳለው የምትለዋ ቃል ዛሬ በዘመናችን የእግዚአብሄርን ማዳን ለሚጠራጠሩ ሁሉ መልስ ሆና ተገኝታለች:: አዋ እግዚአብሄር ሊያደርግልን ይወዳል ስለዚህ በልበ ሙሉነት እንዲፈውሰን እንጠይቀው::

የጸሎታችንን መልስ መጠበቅ
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Tue Sep 17, 2013 1:50 pm

አንዳንድ ሰዎች በፍጹም አይጸልዩም ቢጸልዩም መልስን አይጠብቁም:: በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት ከሌለን እንደገና አልተወለድንም ማለት ነው:: በእግዚአብህር ልጅነታችን ካመንን ለጸሎታችን መልስ ማግኘት ደግሞ የልጅነት መብታችን ነው:: ይሁን እንጂ ጸሎቱ እግዚአብሄር በሚፈልገውና በቅዱስ መጽሀፉ ላይ በሰፈረው መልኩ መከናወን አለበት::

እግዚአብሄር ሁሌም እንድንጸልይ ይጋብዘናል:: በጸሎታችንም በፍጹም አይሰላችም:: ሁልግዜም ጸሎታችንን ለማዳመጥ ዝግጁ ነው:: በምንጸልይ ግዜ እግዚአብሄር ይሰማናል ምክንያቱም እኛ ልጆቹ ነን የኛ መጸለይም ፍቃዱ ነው:: አንዱን ካንዱ አበላልጦ አያይም በምንጸልይበት ግዜ እኩል ይሰማናል እኩል ይመልስልናል:: እንዲህም ይላል የዮሐንስ ወንጌል 16:14 እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። ይሄ የእግዚአብሄር ቃል ነው:: ከጠየቃችሁ በእውነት ሁሉንም ታገኛላችሁ::

በጸሎት የማይቻል ይቻላል
በጸሎት በብዙ ነገሮች ላይ ድልን መቀናጀት ይቻላል:: እግዚአብሄር በጸሎታችን ምንም ነገር መቀየር እንደምንችል አሳይቶናል:: ቁጣንም ሆነ መከራ እግዚአብሄር ሊያመጣብን ቢሆን እንኳን በጸሎት መመለስ ይቻላል:: ምናልባት ይሄ ነገር ያስደንቃችሁ ይሆናል በእውነት ግን ለእግዚአብሄር የማይቻል ምንም ነገር የለም:: በኛ ላይ ሁኔታዎች ሊከሰቱ የሚችሉት በሚከተሉት መልኩ ነው::

1-ያነገር እንዲደርስብን ስንፈልግ::
2-ወይም እንደሚደርስብን አናውቅም::
3-እንደሚደርስብን እያወቅን ይሄን ለመቀየር ግን ምን ማድረግ እንዳለብን ሳናውቅ ስንቀር::
4-ሁኔታዎች እንደሚደርሱብን አናውቅም ግን ቢደርስብን ምን ማድረግ እንዳለብን አስቀድመን አለማወቃችን ናቸው::

እግዚአብሄር ሕይወታችንን እጅግ ሚስጢራዊ በሆነ መልኩ ነው የሚመራው:: የሆነ ነገር ማድረግ ሲፈልግ ማንም አይቀይረውም ነገሩ እስከሚያልቅም ድረስ ማንም አያውቅም:: ኦሪት ዘዳግም 29:29 ላይ እንዲህ ይላል ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ስለዚህ እግዚአብሄር የማንንም ጣልቃ ገብነት ካልፈለገ ማንም በማያውቀው መልኩ ጉዳዩን ይጨርሰዋል:: ጉዳዩን ግን ከነገረን እኛ ከለመነው ሊቀይረው እንደሚችል ሲያሳየን ነው:: በጸሎት ብቻም ነው ልንቀይረው የምንችለው እሱም በትክክለኛ መልኩ ስንጸልይ ብቻ ነው::

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሄርን ሀሳብ የሚያስቀይሩ ብዙ ሁኔታዎች ተከስተዋል ለምሳሌ ኦሪተ ዘጸአት 32:7-14 ሙሴ በእግዚአብሄርና በሕዝቦቹ መካከል ቆሟል:: የእስራኤል ህዝብ በእግዚአብሄር ላይ ባመጹ ግዜ እግዚአብሄር ሊያጠፋቸውም ወስኖ ነበር:: ሙሴ ግን እንዲህ ነበር ያለው
ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም። አቤቱ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ?
ግብፃውያንስ። በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ።
ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ።
በዚህም ግዜ እግዚአብሄር ለህዝቡ ራራ ቁጣውም ተመለስ ይላል መጽሀፉ::

ሌላ ምሳሌ ደግሞ የምናገኘው በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 20 ላይ ፍጹም ከእግዚአብሄር የተወሰነውን ነገር አንድ ሰው እንዴት እንደቀየረው ያሳየናል:: ንጉስ እዝቅያስ እስከ ሞት በሚያደርስ በሽታ ታሞ ሳለ ነበር ነብዩ ኢሳያስ ወደ እርሱ ገብቶ እንዲህ ነበር ያለው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል አለው።( መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 20:1) ይሄ እንግዲህ እዝቅያስን በተመለከተ የራሱ የእግዚአብሄር ቃልና ፍርድ ነው:: እንግዲህ ራሱ እግዚአብሄር ባለው ነገር ላይ መውጫው የጠበበና ሞት አይቀሬ ይመስለን ይሆናል:: እዛው ምእራፍ ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል (መጽሀፈ ነገሥት ካልዕ 20:2) ፊቱንም ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሄርንም በጸሎትና በእንባ ተማጸነ:: መጽሀፈ ነገሥት ካልዕ 20:4-7
ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ከተማ አደባባይ ሳይደርስ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት።
ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው። የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።
በዕድሜህም ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ ስለ እኔም ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ።
ኢሳይስም፥ የበለስ ጥፍጥፍ አምጡልኝ አለ አምጥተውም በእባጩ ላይ አደረጉለት፥ እርሱም ተፈወሰ።
ያለቀን የሞተን ነገር መለወጥ የሚቻለው በጸሎት ብቻ ነው::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Wed Sep 18, 2013 3:03 am

ምእራፍ ሁለት

የአዲስ ኪዳን ጸሎቶች

ጸሎት በአዲስ ኪዳን ከእግዚአብሄር ጋር የመገናኛ መንገድ ብቻ ሳይሆን ተሰብስበን የምናመልክበትም መንገድ ነው:: አንዳንድ ሰዎች የሚጸልዩት የመጸለይ ግዴታ ስላለባቸው ይመስላቸዋል:: ነገሩ ትክክል ነው:: ሉቃስ 18:1ሳይታክቱ ዘወትር ሊጸልዩ እንደሚገባቸው......" የሚል ቃል አለ:: እዚ ላይ የሚያሳየን መጸለይ የሀይማኖት ግዴታችንም ጭምር መሆኑን ነው:: ይሁን እንጂ የምንጸልየው ግዴታችን ስለሆነም ብቻ አይደለም::

ጌታ እየሱስ መጸለይ እንዳለብንና ግዴታችንም እንደሆነ ቢያሳየንም የምንጸልይበትን ነገር ማወቅና እንዴት አድርገን ማቅረብ እንዳለብንም መረዳት አለብን::

ብዙ የማይጸልዩ ሰዎች ቢኖሩም ብዙ የሚጸልዩም ሰዎች አሉ:: ከነዚህም ብዙሀኑ መልስን አላገኙም ምክንያቱም የጸሎትን ትርጉም ሳያውቁ ስለሚጸልዩ ብቻ ነው::

አንድ ነገር ማወቅ አለብን በምንጸልይ ግዜ መለኮታዊ ከሆነ ሀይል ጋር እየተነጋገርን ነው:: ይሄም ንግግር ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኙነት በጅጉ ያጠነክረዋል:: ጸሎት በእርግጠኝነት ወደ እግዚአብሄር የምናተኩርበት መሳሪያና በመግኘቱም እራሳችንን የምንፈውስበት ታላቅ ስጦታ ነው::

ይቀጥላል..........
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ዲጎኔ » Fri Sep 20, 2013 11:19 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገኔ ቀዳማይ በጣም ተባረክ ልዩህ የትርጉም ጸጋ አለህ::
ተጋራዊ ጸሎት ሲሰራ በህይወቴ አይቻለሁ::በዚህ በሰው ሀገር በልዩ አልሰንት ሰዎችን ሳማክር በጸሎት መንፈስ ስሆን ጌታ እንደተስፋቃሉ የምትናገሩት እናንተ ሳትሆኑ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው ሲፈጸም የዛሬ 7 አመት የምረቃ ጽሁፈ ላይና ዛሬም እያየሁት ነው አዎ ተግባርዊ ልባዊ ጸልት ይቀጥል::
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Sat Sep 21, 2013 1:22 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን:: አንዳንድ ነገር ከተፈቀደልኝ ልበል...ከጥቅሶች ቀነስ አድረገን በቃሉ ለመኖርና ለመለማመድ እንደ ቃሉ ለመራመድ የምናደርገውን ጉዞ ጨመር ብናደርግ ምን ይለናል?? ሌላ ለማለት የፈለኩት አንድን ሰው ልዩ የጸጋ ስጦታ አለህ... ልዩ ተሰጦዖ አለህ እያልን አንካበው...ሰው ነውና ሊታበይ ይችላል:: ድመትን ነብር ትመስያለሽ ካሏት ከዛሬ ጀምሮ ሳምባ አልበላም ጠቦት አምጡልኝ ልትል ትችላለች:: ወንድሜ ዲጎኔ ወንድሜ ቀዳማይን ልዩ ጸጋ አለህ.. ልዩ ተሰጥዖ አለህ የሚለውን ብታቆም መልካም ይመስለኛል:: ለቀዳማይ መንፈሳዊ እንቅፋት ወይም ደንቃራ ትሆንበታለህ:: ሌላው ደሞ በሀሳብ የተለዩንን ክፉኛ አንጥላቸው...ወንድሞቻችን እንደሆኑ በማስብ በቀና እንመልስላቸው:: ስህታቸውን በቀናነት እናሳያቸው:: በመግቢያዬ እንዳልኩት ጥቅሱን ቀነስ ....ተግባራዊ የምድር ኑሯችንን ጠበቅ ብናደርግ በሰማይ ያለው የሁላችንም አባት እግዚአብሄር ደስ እንዲመለው ስነግራቹ በርግጠኝነት ነው:: ደህና እደሩ:: :D

በሀሳብ ከሱ የተለዩትን የሚጠላውና የሚሳደበው እንዲሁም ክፉ እንዲደርስባቸው በጸሎት የሚቃትተው ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገኔ ቀዳማይ በጣም ተባረክ ልዩህ የትርጉም ጸጋ አለህ::
ተጋራዊ ጸሎት ሲሰራ በህይወቴ አይቻለሁ::በዚህ በሰው ሀገር በልዩ አልሰንት ሰዎችን ሳማክር በጸሎት መንፈስ ስሆን ጌታ እንደተስፋቃሉ የምትናገሩት እናንተ ሳትሆኑ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው ሲፈጸም የዛሬ 7 አመት የምረቃ ጽሁፈ ላይና ዛሬም እያየሁት ነው አዎ ተግባርዊ ልባዊ ጸልት ይቀጥል::
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቀዳማይ » Mon Sep 23, 2013 3:29 pm

ሰላም ለሁላችን ዲጎኔ ስለ ቅኑ አስተያየትህ አመሰግናለው:: ከሰሞኑ አንዱ ጓደኛዬ ይሄንን መጽሀፍ ለትርጉም ማቅረብ ከኮፒ ራይት አንጻር ትክክል እንዳልሆነ አሳስቦኝ ነበርና ይሄን ሳሰላስል ነው መጥፋቴ:: የእግዚአብሄርን ቃል ለማያውቁ ማስተማሩ በኔ በኩል ችግሩ አይታየኝም መጽሀፉንም የአገሬ ሰዎች ሊያውቁትና ሊረዱት የሚገባ ስለሆነ ፓስተር ክሪስ ቅር የሚለው አመስለኝም:: አስተያየታችሁን እስቲ አካፍሉኝ::

ክቡራን እኔ ለመታበይ የሚያደርስ እውቀት የሌለኝ ሰው ነኝና አይዞህ አሳብ አይግባህ ይሄ ነገር አይደርስም:: ስጋትህ ግን ይገባኛል በቅን ልቦናም በማቅረብህ ልትመሰገን ይገባሀል:: ለሁላችሁም ግን ሰላሙን እየተመኘው ልለያቹ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ዲጎኔ » Tue Oct 29, 2013 3:30 pm

ቀዳማይ wrote:ሰላም ለሁላችን ዲጎኔ ስለ ቅኑ አስተያየትህ አመሰግናለው:: ከሰሞኑ አንዱ ጓደኛዬ ይሄንን መጽሀፍ ለትርጉም ማቅረብ ከኮፒ ራይት አንጻር ትክክል እንዳልሆነ አሳስቦኝ ነበርና ይሄን ሳሰላስል ነው መጥፋቴ:: የእግዚአብሄርን ቃል ለማያውቁ ማስተማሩ በኔ በኩል ችግሩ አይታየኝም መጽሀፉንም የአገሬ ሰዎች ሊያውቁትና ሊረዱት የሚገባ ስለሆነ ፓስተር ክሪስ ቅር የሚለው አመስለኝም:: አስተያየታችሁን እስቲ አካፍሉኝ::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Tue Oct 29, 2013 4:02 pm

ችግር የለውም ቀዳማይ ወንድማችን:: የኮፒ ራይት ጥያቄን ካነሳን ያንን ጣሰ ማለት የሚቻለው እንደውም ፓስተር ክሪስ ራሱ ነው;; ለመሆኑ ይሄ የፓስተር ክሪስ ፈጠራ ነው እንዴ..?? እግዚአብሄር ቢፈልግ ፓስተር ክሪስን ኮፒ ራይቴን ነጥቀህኛል ብሎ ፍርድ ቤት ሊገትረው ይችል ነበር...እንጂ ፓስተር ክሪስ ሂምሰልፍ ዳዝንት ሀቭ ኮፒ ራይት!! ስራው የእጊዚአብሄር ነው የክሪስ አይደለም:: ይሄን የመከረህ ጔደኛህ አጋንንቶች የተጠጉት ይመስለኛል:: ስለ አጋንቶች አሰራርና ጥበብን በተመለከተ ደግሞ ወንድማችን ዲጎኔ ተሞክሮው አለውና ሊያብራርልን ይችላል ማይክ ፍሪ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቀዳማይ » Fri Nov 01, 2013 10:34 am

ክቡራን ስለ አስተያየትህ እያመሰገንኩህ መፅሀፉን ለመቀጠል ወስኛለው:: እንግዲህ ጥያቄና አስተየየት ይፈቀዳል ሁላችንም አብረን እንከታተለው::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Fri Nov 01, 2013 11:20 am

........ጸሎት እንግዲህ የእግዚአብሄርን ቃል በልባችን እንዲያድርም እገዛ ያደርግልናል:: አንዳንድ ሰዎች "በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተናል ትንቢትም እንናገራለን" ሲሉ ይሰማሉ እውነት ለመናገር ጻድቅና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላን ነን ስላልን ብቻ ነን ማለት አይደለም:: ጳውሎስም ለኤፌሶን ቤ/ክርስቲያን የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።" ብሎ ነበር
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:17 ጥበብና መገለጥ የሚገኘው በፀሎት ብቻ ነው ወገኖች:: የእግዚአብሄር ቃል በልባችን ስር እንዲሰድና እንድናውቀው ዘንድ አበክረን መፀለይ ይገባናል::

በፀሎት ምንም ነገር መቀየር እንችላለን

ጌታ እየሱስ የሉቃስ ወንጌል18:1 ላይ ዘወትር ሳይታክቱ መፀለይ እንዳለባቸው አሳስቧቸው ነበር:: በስራችን ላይ, በሕይወታችን ላይ, በሰውነታችን ላይ ብዙ ነገሮችን በፀሎት መቀየር እንችላለን:: እንዲያውም የሌላ ሰው ሕይወት ሁሉ በፀሎት መቀየር እንችላለን:: ለዚህም ነው እንዴት አድርገን መፀለይ እንዳለብን ማወቅ ያለብን:: በማቴዎስ ወንጌል ላይ ጌታ እንዲህ ብሎ ነበር
ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም። የማቴዎስ ወንጌል 17:20 ጌታ እንደዚህ ሲናገር እንዴት ደስ ይላል በህይወታችን ተስፋና ብርሃን ይፈነጥቃል:: ይታያችሁ እንግዲህ የሰናፍጭ ቅንጣት ማለት እጅግ ያነሰ ነገር ነው:: የዛችን ታክል ትንሽዬ እምነት እንኳን ቢኖራችሁ በፊታችሁ ያለው ተራራ ሁሉ ይወገዳል እያለን ነው:: ባጠቃላይ እምነት ካላችሁና አጥብቃችሁ ከፀለያችሁ "የሚሳናችሁ ነገር የለም" ነው ጌታ እየሱስ ያለን:: የማርቆስ ወንጌል 9:23 ላይ ጌታ እንዲህ ብሎ ነበር ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ትልቁ ጥያቄ እዚ ላይ ነው ታምናላችሁ? በእውነት በእግዚአብሄር ቃል ካመናችሁና በፀሎት ከተጋችሁ የማይቻል ምንም ነገር የለም::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Sun Nov 03, 2013 3:57 am

ምዕራፍ ሶስት[
በጌታ በየሱስ ክርስቶስ ስም መፀለይ
ከመወለዳችን አስቀድሞ በተሰጠን ስም በመፀለይ ወደ እግዚአብሄር እንቅረብ:: እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።የዮሐንስ ወንጌል 14:6 ጌታ እየሱስ እንግዲህ ይሄን ማለቱ ባጠቃላይ ወደ እግዚአብሄር በኔ በኩል ቅረቡና የዘላለም ሕይወትን አግኙ ሲል እየጋበዘን ነው:: ይሄንን የሕይወት ግብዣ ከተቀበልን የእግዚአብሄር መንግስት ህዝቦች እንሆናለን::

አሁን ግብዣውን ተቀብለን ወደ እሱ ከመጣን ዘንድ ሕይወታችን ሁሉ ክርስቶስን ሊመስል ይገባል:: አንዴም ወደ እግዚአብሄር ከመጣን በሱ ቸርነትና አምላክነት ጥላ ስር ዘላለም እንኖራለን:: ለዚህም ነው "በጌታ በኢየሱስ በኩል" የማንፀልየው መፀለይም የሌለብን::

ምናልባት እንደዚህ የሚፀልዩ ሰዎች ይኖሩ ይሆናል ይሄ ግን በፍፁም የተሳሳተና ሊሰራ የማይችል ፀሎት ነው:: አንዳንዶቻችሁ በዚህ መልኩ ፀልየን ሰርቶልናል ልትሉም ትችላላችሁ ቢሰራላችሁም እንኳን ያኔ ገና ህፃንና ያልበሰላችሁ በመሆናችሁ እግዚአብሄር ጥፋታችሁን እንዳላየ አልፎላችሗል:: አሁን ግን በእምነታቹ የመጠንከሪያና የማደጊያ ግዜ ስለሆነ በትክክለኛው መልኩ መፀለይ መማር ይገባችሗል::

በአዲስ ኪዳን የተገለጠልን የእግዚአብሄር ቃል እንደሚያመላክተው ለእግዚአብሄር በጌታ በየሱስ ክርስቶስ ስም መፀለይ እንዳለብን ነው ብዙ ሰዎች ይሄንን ለመረዳት እጅግ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል:: ለዚህም ነው ጸሎታቸው ተሰሚነት የማይኖረውና ከደመና በታች የሚቀረው:: እጅግ ብዙ ፀሎቶቻቸው ሳይመለሱ ከመቅረታቸው የተነሳ በፀሎት ላይ ያላቸው ተስፋም እየተመናመነ ይመጣል::

ለጌታ እየሱስ ወይም በሱ በኩል መፀለይ እስካላቆምን ድረስ ፀሎቶቻችን ሁሉ ተመላሽነት አይኖራቸውም::

በእየሱስ ስም መፀለይና በእየሱስ በኩል መፀለይ እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው:: በእየሱስ በኩል መፀለይ ማለት ጌታ እየሱስ ፀሎታችንን እንዲያስተላልፍልን መንገር ማለት ነው:: ይሄ ደግሞ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው ለኛ ለክርስቲያኖች ጌታ እየሱስ የጌቶች ጌታ እንጂ መልክት አስተላላፊ አይደለም::

ይሁን እንጂ በጌታ በየሱስ ስም ስንፀልይ ግን የሱን ስም እንድንጠቀም የሰጠንን ስልጣን እየተገበርን ነው:: ምንም ነገርም በሱ ስም ጠይቀን ፈፅሞ አንከለከልም::

አዲስ ቀን, አዲስ ሕዝብ, አዲስ ፀሎት

ጌታ እየሱስ በዮሐንስ ወንጌል 16:23 ላይ እንዲህ ብሏልበዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። ይሄ ማለት በኔ በኩልም ሆነ ለኔ መፀለይ የለባችሁም በስሜ እንጂ ማለቱ ነው::

እዚ ጋር ጌታ እየሱስ ክርስቶስ አዲስ አይነት ፀሎት ለአዲስ ሰዎች እንዳለ እየነገረን ነበር:: ለአዲስ ኪዳን ሕዝቦች! እንዲህም አለን በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።

ልብ አላችሁ ጌታ እየሱስ በኔ በኩል ብትፀልዩ ሳይሆን በኔ ስም ብትፀልዩ ነው ያለው:: ስለዚህ በአዲስ ኪዳን በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ስም እንፀልያለን::

በአዲስ ኪዳን እየሱስ ክርስቶስን ምንም ነገር አንጠይቀውም:: ይሁን እንጂ ምን ያህል እንደምንወደው, እንደምናመልከው, እንደምናመሰግነው ልንነግረው ስንችል በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ስምም ለእግዚአብሄር ምስጋና ማቅረብ እንችላለን:: ለእግዚአብሄር በጌታ በየሱስ ክርስቶስ ስም እንፀልያለን እንጂ ለራሱ ለእየሱስ ክርስቶስ አንፀልይም::

ጌታ እየሱስ በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም ማለቱ ከተሰቀለ በሗላ ያለውን ቀን ለማመላከት ብሎ ነው:: ያ ቀን አዲስ ሰው የተፈጠረበት, ጻድቃንም ወደ እግዚአብሄር መንግስት የሚገቡበት, ቀን ነው:: ያ ቀን ዛሬ የምንኖርበት የምሕረት አመት ነው::

የስሙ ሀያልነት
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests