እውን ኢሎሂም የሚለው ቃል የስላሴን መኖርን ያጥድቃልን?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

እውን ኢሎሂም የሚለው ቃል የስላሴን መኖርን ያጥድቃልን?

Postby መርፊው » Wed Sep 25, 2013 10:13 pm

ይህ ፔጅ አላማው ሀይማኖታዊ ውይይቶችን ማዳበር እንደመሆኑ ማንኛውም አንባቢ ወይም ተወያይ ምሁራዊው ዲስፕሊን በ ሚፈቅደው መልኩ ቢወያይ እንዲሁም በ ክፍለ ዘመኑ የቀረውን ስድብ እና ተራ ነገሮችን ላይ ባየተኩር መልካም ነው፡፡ ……

የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ እና የ ሂብሩ ቃል ኢሎሂም

የትም ሒድ የት አንድ ሚሽነሪን የስላሴ ፅንሰ ሐሳብን ህልውና ከብሉይ ኪዳን ውስጥ እንዲያሳይህ አንድ ካልከው የሚሰጥህ ተቀዳሚ ያልሆነ ቀዳሚ የሖነ ምላሹ እግዚአብሄር የምንለው አምላክ ኢሎሂም ተብሎ በብሉይ ኪዳን ተጠርቷል የሚል መሆኑን አትጠርጥር አክሎም ኢሎሂም ነጠላ ቃልን ገላጭ ሳይሆን ብዙ ቁጥርን ገላች መሆኑን ሹክ ይልሐል ከዛም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስላሴ ሚባለው ፅንሰ ሐሳብ እንዳለ ለማሳየት ድቤ ሲደልቅ ታየዋለህ….. እናስ? እናማ ይህ ሁሉ ሲሆን ደግመን ደጋግመን አየን አይተን ሰናበቃም የእርምት እርምጃ መውሰድ አለብን ስንል ለራሳችን ነገርነው…. ምናልባት ሚሽነሪው ይህን ሚለው እና ተከታዩ ተቀብሎ ሚያስተጋባው ከመረጃ እጦት ሳይሆን አይቀርም በመሆኑም መረጃ ማስተካከሉ እና እውነትን አንጠሮ ማሳየቱ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም በመሆኑ ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ተገደድን ነው ሚባለው? አንተ ብቻ ንባብህን ቀጥል እንጂ እውነቱ እስከ ሙሉ ውበቱ እና ድምቀቱ ለማየት ልትገደድ ነው
ወደ ገደለው ጉዳ ይ ስመልስህ እና አንድ ስል የምጠይቅህ ጥያቄ ኢሎሂም የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ያራምዳል ምትለኝ ከሆነ ይህን የነገረህ ማነው ? መረጃውስ ምንድነው? የሚለው ነው…. "ምህረት አብ ስላለ" ወይም "የሖነ ፓስተር" ስላለ የሚል መረጃ ታመጣ ይሆናል፡፡አመጣህ ማለት ግን ልክ ነህ ማለት አደለም ልትሆንም ላትሆንም ትችላለህ … እኔ ደግሞ እንደምልህ እመኘኝ እነዚህ ሰዎች መረጃ አደሉም …ሊሆኑም አይችሉም …መረጃ የመሆን የሞራልም የእውቀትም ብቃት የላቸውም … የሖነ ሆኖ የነሱን ነገር ለነሱ ልተውና ወደ ዋናው ጉዳይ ልመልስህ
1. ኢሉሂም (אלהים) ብዙ ቁጥርን ወይስ ነጠላን
እንደምታውቀው ብሉይ ኪዳንህ ውስጥ ፈጣሪ የተገለጠበት አንዱ የሂብሩ ቃል ኢሎሂም(אֱלֹהִים) የሚል መሆኑ ነው፡፡ ይህም ቃል የሚያልቀው "-ִים" በሚል የሒብሩ ሆሄ ሲሆን አንድም የወንድን ፆታ የያዘ በዙ ቁጥርን አመላካች መሆኑን አያጠያይቅም ፡፡ ከዚህ ተነስተን ምናልባት ልክ ፓስተሩ እንደሚለው ኢሎሂም የሚለው ቃል ብዙ ቁጥርን ያመላክታል ፡፡ ወደ ሚለው ማጠቃለያ ልናመራ እንችላለን፡፡ አማልክትም ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ወደ ሚለው በርም ዘው ብለን እንገባ ይሆናል ፡፡ በርግጥ በ ቃል ደረጃ ብቻውን ከመጣ በዚህ መልኩ መተርጎሙ አጨቃጫቂ አይሆኑም… ግና ዋናው ከ አውድ ወይም ኮንቴክስት ጋር ሲመጣ በ ሂብሩ የቋንቋ ህግ መሰረት ለብቻው ብዙ ቁጥርን ሊያመላክት የሚችል ቃል አንዳንዴ ወደ ነጠላ ቁጥር የመቀየሩን እውነታ ነው፡፡ይህ ማንም የሂብሩ ቋንቋ ተናጋሪ የሚገነዘበው እውነታ ነው….
ሹፍ!!! በ እብራይስጥ ቋንቋ ብዙ ቁጥርን ያመላክታሉ የሚባሉ ቃላት በ ሶስት አይነት አግባብ ይቃኛሉ
1. ብዙ ቁጥር አመላካችን ተከታይ መድረሻ ጋር አብረው ሲመጡ
2. ብዙ አመላካች ከሆነ ግስ ጋር ተያይዘው ሲመጡ እና
3. ብዙ ቁጥርን ከሚያመላክት ቅፅል ጋር አብረው ሲመጡ ናቸው
ይህ ሶስቱ መስፈረትን አሟልቶ የመጣ አንድ አረፍተ ነገር በሂብሩ ቋንቋ መሰረት ብዙ ቁጥርን አመላከተ ይባለል …. ግር እናዳይልህ ምሳሌ ልስጥህ በ ኢንግሊዘኛው The big dog guarded.( ትልቁ ውሻ ጠበቀ) ካልክ ነጠላ ቁጥርን ማመላከቱ ግድ ነው፡፡ ምክንያቱም የተጠቀምከው ስም dog የሚለውን እንጂ dogs የሚለውን አይደለም ይህም ማለት በ ኢንግሊዘኛ ቋንቋ መሰረት የ አንድ ነገር ብዙነትን ሚወስነው ስሙ ነው፡፡ ማለት ነው፡፡ ይህ ካሴት ግን ሲገለበጥ ለ ሂብሩ ቋንቋ ፈለክም አልፈለክም ወደድክም ጠላህም ወፍ! አይሰራም ፡፡ በሂብሩ አንድ ቃል ስም ብዙ ቁጥርን አመላከተና በየትኛውም ስሌት ያ ስም የተጠቀሰበት አ/ነገር ብዙ ቁጥርን ያመላክታል ወደሚል ማጠቃለያ አይወስድም
ተመልከት The big dog guarded. የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል ወደ ብዙ ቁጥር መቀየር ስትፈልክ dog የሚለው ስም ላይ "ኤስ" የሚለውን የ እንግሊዘኛ ሆሄ በመጨመር The big dogs guarded ወደ ሚል ብትቀይረው ትክክል ነህ …. በሂብሩ ከሆነ ግን ይህ አይሰራም … The big dog guarded. የሚለው ቃል ነጠላ ሚሆነው በ ሂብሩ big እና dog የሚሉት ቃላት ነጠላ ቀጥር አመላካች በሆነ መልኩ ሲገለፁ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ምሳሌ ከፈለክ
Singular( ነጠላ): The big (ነጠላ) dog (እሱ) guarded. שָׁמַר הַכֶּלֶב הַגָּדוֹל ከሆነ ይህ አ/ነገር ነጠላ ነው ይባላል

Plural(ብዙ): The big (ብዙ) dogs (እነሱ) guarded. שָׁמְרוּ הַכְּלָבִים הַגְּדוֹלִים ከሆነ ይህ አ/ነገር ብዙ ቁጥርን አመለከተ ይባላል፡፡
ግር እንዳይልህ በአጭሩ ሳስቀምጥልህ በ ሒብሩ ቋንቋ ህግ የ አንድ አረፍተ ነገር ነጠላነት እና ብዙነት ሚወሰነው እንደመጣበት አውድ እንጂ በተናጥል ከስሙ በሚገኘው መረጃ አይደለም፡፡ ይህንን ካላመንክ የሒብሩ ቋንቋን ህግጋት የተማረን ህፃን መጠየቅ ላንተ በቂህ ነው ሳይጨምር ሳይቀንስ እውነቱን ይነግርሐል …… አንተ ብቻ ጠይቅ?
በመሆኑም ኢሎሂም( אֱלֹהִים) የሚለው የሒብሩ ቃል ብዙ ቁጥርን አመላካች ነው ወይስ አይደለም ከማለትህ በፊት የመጣበትን አ/ነገር ምንነት መመልከት ግድ ሊልህ ነው… ይህን ካላረክ እመነኝ እንዳትሆን እንዳትሆን ሆነህ ትጠፋለህ(ትሸወዳለህ)…….
ምሁራን ኢሎሂም የሚለው ቃል በ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በቁጥር 2000 በላይ መጠቀሱን ይነግሩናል፡፡ ነግረውንም ሲያበቁ ግን ዝም አላሉም ይህ ኢሎሂም የሚለው ቃል ወይ ነጠላ ቁጥር አመላካች ቃል ይከተለዋል ካልሆነም ይቀድመዋል ይሉናል…. ኢሎሂም የሚለውን ስም ነጠላ ቁጥር አረፍተ ነገር ከቀደመው ወይም ከተከተለው ደግሞ የስሙ ብዙ ቁጥር አመላካችነት አፈር ይበላል ማለት ነው፡፡ ብዙ ቁጥር አመለካችነቱ አፈር በላ ማለት ሚቀረው ነጠላ ቁጥርን አመላካችነት ይሆናል……… እናስ? እናማ ያ አ/ነገር ነጠላ ቁጥር አመላካች ብቻ ይሆናል …. ብዙ ቁጥር ያ መላክታል ኢሎሂም የሚለው ቃል ከማለት እና አቧራ ከማጨስ በፊትም መቅደም ያለበት ይህ እና ይህ ነው …… በዚህ ከተስማማክ ንባብህን ቀጥል
እንደምታውቀው መፅሀፍ ቅዱስህ ውስጥ ፈጣሪ የሚለው አማርኛ ቃል ኢሎሂም በሚለው ሂብሩ ቃል ነው አብዛኛውን ጊዜ የተተረጎመው ተርጉዋሚዎች ኢሎሂም ምትለውን የብዙ ቁጥር አመልካች ስምን ፈጣሪ በሚል ነጠላ ቃል ተርጉመውታል ይህም ተርጓሚዎች የተከተሉት አተረጓጎም ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም…. ሚሽነሪዎች በሂብሩ ኢሎሂም የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር አመልካች ነው ሲሉ ና ድቤ ሲደበድቡ ጠፍቷቸው ነው ተርጓሚዎች በ ነጠላ ቁጥር የተረጎሙት? ለምን ተርጓሚዎች ኢሎሂም የሚለውን የተባእት ፆታ ብዙ ቁጥር አመላካች ስምን ወስደው ሲያበቁ " ፈጣሪዎች " ሲሉ አልተረጎሙትም? ጠፍቷቸው ብዙ ቁጥር ማመልከቱን? ወይስ ምን ? ጥያቄ በጥያቄ ላይ መነሳቱ ላይቀር ነው፡፡ ይህም ጥያቄ ጥያቄ ወልዶ ሲያበቃ ? ለምን ኢሎሂም የተሰኘው ብዙ ቁጥር አመላካች ቃል በነጥላ ቁጥር አመላካች ቅፅል እና ግስ ጋር ተሳስሮ ሲመጣ ነጠላ ቁጥርን ያመላክታል ? እንድንል ያስገድደናል
ይህም ጥያቄ በ እብራይስት ወዳለው ልዩ የ ቋንቋ እና የሰዋሰው ህግ ይመራናል ይህም "ክብርን አመላካች ብዙ ቁጥር አጠቃቀም " በመባል የሚታወቀው የቋንቋ ምልከታ ….. በዚ ህግ መሰረት ደግሞ ኢሎሂም የሚለው የሚለው የፈጣሪ ስም ነጠላ ቁጥር ተከተለው ክብርን ያመላክታል ….. ግር እንዳይልህ ልድገምልህ ኢሎሂም የሚለው የሂብሩ ቃል ነጠላ ቁጥር ከ ቀደመው ወይም ከተከተለው ክብርን እንዲሁም ዝናን ያመላክታል
የሆነ ሆኖ ይህ ገለፃ በ ኢንተርናሽናሉ ቋንቋ "majestic plural" በመባል ይታወቃል ይህንም በተመለከተ በመስኩ ወሳኝ የተባለለትን ጥናት ያካሄደው የ ሂብሩ ምሁር Nehemia Gordon እንዲህ ቢል አይገርምም፡፡
"The meaning of the plural suffix in the majestic plural is not that there is more than one of the noun, but that the noun is "great, absolute, or majestic"
"ብዙ ቁጥርን ሚያመላክተው ተከታይ መድረሻ ሆሄ በክብር አገላለፅ ውስጥ ከ አንድ ቁጥር በላይ ስምን ለማመልከት አደለም ግን የዛን ነጠላ ቁጥር ስም ክብር ለመግለፅ ነው፡፡"
ኤራድማነስ የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትም( Eerdmans Bible Dictionary) ይህን እውነታ እንደወረደ በዚህ መልኩ ይገልፀዋል
" As a name or designation of the God of Israel, the term is understood as a plural of majesty or an intensive plural, indicating the fullness of the supreme (or only) God ... the canonical intent is clearly monotheistic, even where the accompanying verbs or adjectives are grammatically plural"(1)
"የ ኢስራኤል አምላክ ስም የተገለፀው ክብርን አመላካች በሆነው ብዙ ቁጥር ቃል ነው ይህም የሚያሳየው የ አምላክን ታላክነት እና ክብርን ነው የ ቀኖነው ፍላጎት አንድ አምላክ ፅንሰ ሐሳብ ለማፅደቅ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ተከታዮቹ ቅፅል ወይም ስም እንኳ ብዙ ቁጥርን ሚያመላክቱ ቢሆኑም፡፡"
ብሉይ ኪዳንን በ ተመለከተ የተፃፈው የ ስነ መለኮት መፅሀፍም እንዲህ ቢለንስ
" This word [elohim], which is generally viewed as the plural of eloah [Strong's #433], is found far more frequently in Scripture than either el or eloah for the true God. The plural ending is usually described as a plural of majesty and not intended as a true plural when used of God. This is seen in the fact that the noun elohim is consistently used with singular verb forms and with adjectives and pronouns in the singular."(2)
" በተለምዶ ኢሎሂም የሚለው ቃል ኢሎህ የሚለው ነጠላ ስም ብዙነትን አመላካች ነው ፡፡ በሐይማኖታዊ ፅሆፎችም ኤል ወይም ደግሞ ኢሎህ በሚል ሁኔታ ይገኛል፡፡ የ ብዙነት መግለጫ መጨረሻ (ኤም) የክብርን እንጂ የፈጣሪን ብዙነት አይገልጽም፡፡ ይህም እውነታ ነት የሚታየው ኢሎሂም የሚለውን ቃል ተገትለው በሚመጡ ነጠላ ቁጥር አመላካች ስም ግስ እና ተውላጠ ስሞችላይ ነው"
ይህን እውነታ ቃል በቃል ሜርከር መዝገበ ቃላት(3) ፣የካቶሊክ ኢንሳይክሎፓይዲያ (4) እንዲሁም ሀርፐር ኮሊንስ ኢንሳይክሎፓይዲያ(5) ጠቅሰውታል …….
እውነት እንነጋገር ከተባለ እውነቱ ይህ ነው፡፡ የትም ሂድ የት በ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ኢሎሂም የሚለው ቃል ሁሌም የሚያሳየው ክብርን እንጂ የፈጣሪን ከ አንድ ባለ መሆን አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ምሳሌወችን መመልከት ሚቻል ይሆናል …… ምሳሌዎችን አንድ በ አንድ እንመለስባቸዋለን በክፍል 2…. ኢንሻላህ ይቀጥላል

Reference books

1. Eerdmans Bible Dictionary, edited by Allen C. Myers, William B. Eerdmans Publishers, p. 331
2. Edited by R. Laird Harris, Gleason L. Archer Jr., Bruce K. Waltke. Theological Wordbook of the Old Testament, Volume 1(1980). Chicago: Moody Press. p. 44
3. Watson E. Mills. Mercer Dictionary of the Bible(1991). Macon, Georgia: Mercer University Press. p. 336)
4. New Catholic Encyclopedia, 2nd Ed. Volume 5(2003). Thomson Gale. p. 173
5. Paul J. Achtemeier. HarperCollins’ Bible Dictionary(1996). HarperCollins. p. 737
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Wed Sep 25, 2013 11:10 pm

በክፍል አንድ ጥናታዊ ፅሁፋችን ላይ ኢሎሂም የሚለው ቃል ምንም ብቻውን ሲሆን ብዙ ቁጥርን ቢያመላክትም ተያይዞ የመጣው አውድ ግን ነጠላ ቁጥር ከሆነ በየትኛውም የሒብሩ ቋንቋ ስሌት ብዙ ቁጥርን ሊያመላክት እንደማይችል አይተናል፡፡ በዛሬው ፅሁፍ ላይ የክፍል አንድ ላይ በጥልቀት የተመለከትነውን መሰረታዊ የቋንቋ ህግን አስመልክቶ ከ ብሉይ ኪዳን ምሳሌ አቅርበን ስናበቃ ሌሎች የስላሴ ፅንሰ ሐሳብን ያራምዳሉ ሲሉ ሚሽነሪዎች ከአንዴም አስራአንዴ የሚያቀርቧቸውን መረጃ መሳይ ግና መረጃ ያልሆኑን የብሉይ ኪዳን አናቅጽትን እንመረምራለን ግና ይህን ስታነብ ግር እንዳይልህ ቀድመህ ክፍል አንድን አንብብ እልሃለው፡፡

----- ኢሎሂም ከነጠላ ቁጥር ጋር ተያይዞ መምጣቱን ሚያሳዩ ምሳሌዎች-----

ሹፍ! የፍጥረትን ጅምር የሚጠቅሰው የ ብሉይ ኪዳን መፅሀፍ ዘፍጥረት እንዲህ ብሎ አንድ ሲል የወጀመሪያ እርምጃውን ይወስዳል

ምሳሌ ቁጥር .1

" בראשית ברא אלהים את השמים ואת הארץ
"ቤሬሺት ባራ ኢ ሎሂም ኢት ሃ ሸማኢም ቫ ኤት ሀ ኤሬትስ"
"በመጀመሪያ ኢሎሂም ሰማያት እና ምድርን ፈጠረ"
በ አንቀፁ ላይ በ ግልፅ የሰፈረው እንዲሁም ኢሎሂም ከ ሚለው የሂብሩ ቃል ጋር ተያይዞ የመጣው የሂብሩ ቃል ባራ(ፈጠረ) የሚለው መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ አልፎ ተርፎ ይህ በራ የሚለው ቃል ብዙ ቁጥርን አመላካች ሳይሆን ነጠላ ቁጥርን አመላካች ቃል ነው፡፡ እንዳልኩህ አንድ ብዙ ቁጥር አመላካች የ ሂብሩ ቃል ከነጠላ ቁጥር አመላካች ቃል ጋር ተያይዞ ሲመጣ ያን አንቀጽ ነጠላ ያደርከዋል በ ዚህም ስሌት ነው እንግዲህ ይህ አንቐፅ ነጠላ ነው ምልህ …….. ለ ሚሽነሪዎች ሚመቸው በራ የሚለው ነጠላ የ ሂብሩ ቃል (בראו) ወይም ባሩ በሚለው የብዙ ቁጥር አመላካች ቃል ቢጠቀስ ነበር፡፡ ነበር ባይሰበር ልበለህ እና ወደ ሁለተኛው ምሳሌ ልለፍ

ምሳሌ ቁጥር .2

"ግብፃውያንን በጭካኔ ለ ሚገዛቸው ንጉስ አሳልፌ እሰጣቸዋለው የሰራዊት ጌታ የሆንኩት እኔ እግዚአብሄር ይህንን ተናግሪያለሁ" (ኢሳያስ 19፡4)
በዚህም አንቀፅ የተጠቀሰው( בְּעָלִ) የሚለው የሂብሩ ቃል ቀጥታ ትርጉሙ ጌታ ነው፡፡ ለዚህም የመጀመሪያ ምክንያት ሚሆነው ይህ ቃል ነጠላ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ቃል (בְּעָלִים) ወደሚለው ብዙ ቁጥር አመላካች ቃል ብንለውጠው ቀጥታ ትርጉሙ ጌታዎች የሚለው አይደለም፡፡ እንዴትስ ይሆናል …. ግና ትርጉሙ በፌደራሉ ቋንቋ እንደተተረጎመው "የሰራዊት ጌታ" ወይም በ ኢንተርናሽናሉ ቋንቋ "great master, lord" የሚል ይሆናል….. ይህ የሚሆነው እንዳልኩህ ተያይዞ የመጣው ነጠላ ቁጥርን አመላካች ከሆነው ቅፅል ጋር ነው፡፡ በመሆኑም አንቀፁ ክብርን እንጂ ብዛትን አይመላክትም

ምሳሌ ቁጥር .3

"በሬው የተዋጊነት ልምድ ያለው ቢሆንና ባለቤቱም ቀደም ሲል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በበረት ሳይዘው ቀርቶ ቢሆን ግን በሬው ሰው በሚወጋበት ጊዜ በዲንጋይ ተወግሮ ይገደል፡፡"(21፡29 ዘፃእት)
ተመልከት በ አንቀፁ ላይ ባለቤት በሚል የተገለጸው የአማርኛ ቃል ወደ ሂብሩ ሲቀየር (בְּעָלִים) የሚል ይሆናል፡፡ ይህ የሂብሩ ቃል በዙ ቁጥርን አመላካች በሚል ስሌት ባለቤቶች በሚል አልተተረጎመም … ባለቤት ተብሎ ነው የተተረጎመው ይህም ሲባል በባለቤትነት ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው("absolute owner, complete master".) መሆኑን አመላካች ነው፡፡ ከላይ በተነጋገርነው መልኩ ነጠላ ቃል አመላካች ከሆነ ቅፅል እና ግስ ጋር ተያያዞ ስለ መጣ (בְּעָלִים) የሚለው ቃል ሙሉ በንብረቱ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለውን ግለሰብ ያመለክታል፡፡

1. ኢሎሂም የሚለው ቃል ሁሌም ለአንዱ አምላክ የተሰጠ የክብር መገለጫ ነውን?

በዚህ ከተግባባን !!! እሺ ኢሎሂም የሚለው የሂብሩ ቃል ሁሌም ክብርን እና ይህን አንድ አምላክ ብቻ ያመላክታል ወይ? ብለህ ትጠይቅ ይሆናል….. እኔም አያመላክትም እልሀለው….. ነጠላ ቁጥርን እንደሚያመላክተው ሁሉ ብዙ ቁጥርንም ሚያመላክትበት አገባብ አለው(it depend on the context) …. በዚህ ረገድ በምሳሌነት ተጠቃሽ ሚሆነው አንቀፅ 1ኛ ነገስት ነው፡፡ እንደወረደ በዚህ መልኩ አንብበው
" ይህን የሚያደርገው ሰለሞን እኔን ትቶ ባእዳን የሆኑትን አስታሮት ተብላ ምትጠራውን የሲኖዳ አምላክ(אלהים) ፣ከሞሽ ተብሎ ሚጠራውን የ ሞአብ አምላክና(אלהים) ፣ ሚልኮም ተብሎ ሚጠራውን የ አሞንን አምላክ(אלהים)ስላመለከ ነው……"(1 ነገስት 11፡33)
ሹፍ! በአንቀፁ ላይ እነዚህ የ ጣኦታውያን አማልክት ኢሎሂም ተብለው ተጠርተዋል … ከዚህም መረዳት የሚቻለው ኢሎሂም የሚለው የ አንዱ አምላክ ብቻ የክብር መገለጫ አለመሆኑን ነው፡፡ ስላልሆነም ጣ ኦታት በዚ ቃል ተጠርተዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት የምሰጥህ ድምዳሜ የኢሎሂም ቃል ቀጥተኛ ትርጉም ጣኦታትን ይሁን አንዱን አምላክ ወይም ክብርን ይሁን ብዛትን ሚወሰነው በ መጣበት አውድ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡

2. ስላሴን ያመላክተሉ በሚል በሚሽነሪዎች የሚቀርቡ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀጾች

ሚሽነሪው ቀንም ማታም ፣ ዛሬም ነገም ፣ ስለ ስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ሲሰብክ እና ሲያስተጋባ መረጃ አለኝ በማለት ነው፡፡ እንደምታውቀው አለኝ የሚለህ መረጃ አብዛኛው ከ አዲስ ኪዳን ሲሆን ጥቂቱ ደግሞ ከብሉይ ኪዳን ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን እኛ የተነሳነው እና እየተነጋገርንበት ያለው ጉዳይ ብሉይ ኪዳንን ላይ የሚያውጠነጥን እንደመሆኑ ስላሴን የመላክታሉ በሚል ብሂል አስሬ ወደሚያቀርቧቸው መረጃዎች እንለፍ ነው፡፡

2.1 ሰውን በ አምሳላችን እንፍጠር ዘፍጥረት 1፡26…….

የ ስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ተሟጋቾች እና አራማጆች ሁሉም ማለት ይቻላል ይህን አንቐፅ የ አስተምህሯቸው የብሉይ ኪዳን ሰንደቃላማ አድርገውታል፡፡ ህፃኑንም ጠይቅ ወጣቱን ጎልማሳውንም ጠይቅ ኣዛውንቱን የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ከ ብሉይ ኪዳን አንድ በለኝ ካልከው በዘፈጥረት ላይ ያለውን ይህን አንቀፅ ጀባ ይልሐል፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በእውቀት ማነስ ወነኛ እና ተጠቃሽ ምክንያት ይህ አንቀፅ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ያራምዳል ስሊ ይወተውትሐል፡፡ይህም በመሆኑ ነው እንግዲህ ዛሬ ላይ ቆሜ ስለ ዚህ ርእስ አንድ ሁለት ለማለት የጠገደድኩት
ወደ አንኳሩ ነጥብ ስመልስህ እና አንድ ስልህ እውን ዘፍጥረት ላይ ያለው አንቀፅ የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ያራምዳል?
ያራምዳል ወይም አያራምድም ከማለትህ እና ብይን ከመስጠትህ በፊት አንቀፁን እንደ ወረደ በዚህ መልኩ አንብበው
"ከዚህ በኋላ እግዚአብሄር ሰውን በመልካችን እና በ አምሳያችን እንፍጠር ፣ሰዎችም በባህር ውስጥ ሚኖሩ አሳዎችን ፣ በሰማይ የሚበሩ ወፎችን ፣በእንስሳት እና በምድር ላይ በደረታቸው ተስበው የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችም እንዲሁም በምድር ሁሉ ላይ ስልጣን ይኑራቸው አለ፡፡"(ዘፍ፡1፡26)
ተመልከት በዚህ አንቀፅ ላይ ፈጣሪ እራሱን በመጀመሪ አካል ብዙ ቁጥር አመላካች ጠቅሷል ይህም "በመልካችን"፣ "በአምሳያችን"፣"እንፍጠር" እነዚህ አባባሎች በመጀመሪያ አካል ብዙ ቁጥር አመላካች ወይም(first person plural) መምጣታቸው አያጠያይቅም፡፡ ይህን ተያይዞ የሚነሳው ቀጣዩ ጥያቄ ይህ ፈጣሪ ስንት በመሆኑ ነው ይህን ያለው የሚል ይሆናል? አዎ ስንት?
ከላይ አስረግጠን እንደተነጋገርነው ኢሎሂም የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር አመላካች ቃል ተያይዞ በመምጣቱ ነጠላነትን ያሳያል ግን ክብርንም ያሳያል ብለናል ፡፡ ይሄስ ዘፍጥረት 1፡26 ስ? የሚለው ጥያቄ አይኑን ያፈጠጠ ጥርሱን ያገጠጠ ሆኗል………ስለሆነም መመለሱ ግድ ይለዋል፡፡
ይህም እንደቀድሞው ሁሉ ተመሳሳይ የ ሂብሩ ግራመር ህግን ይከተላል…. ሲጀመር አንቀፁ ፈጣሪ(እሱ) አለ (וַיֹּאמֶר אֱלֹהִים) የሚለው የሂብሩ ቃል ሶስተኛ አካል ነጠላ ቁጥር(3rd person singular ) መሆኑ ነው፡፡ ይህም በግልጽ የሚያሳየው ተናገሪው አካል አንድ እና ብቸኛ የሆነ አካል መሆኑን ነው፡፡ ይህ አንቀፅ ብዙ ቁጥርን ወይም ከ አንድ በላይ አካላትን ያመላክተል ለማለት ከተፈለገ በአንቀፁ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የ ሂብሩ ቃል (וַיֹּאמְרוּ אֱלֹהִים) ይህ መሆን ነበረበት ወይም ኢሎሂም(እነሱ) አሉ፡፡ ግን በዚህ መልኩ አንቀፁ ባለመምጣቱ አንቀፁ አንዱ ፈጣሪን ብቻ የመላክታል ማለት ነው፡፡
ተናጋሪው አንድ አካል መሆኑን ያመላክታል ካለን ቀጣዩ የሚነሳው ጥያቄ ለምን ይህ ብቸኛው አካል "በአምሳላችን" (בְּצַלְמֵנוּ כִּדְמוּתֵנוּ) እንዲሁም "እንፍጠር" (נַעֲשֶׂה) የሚለውን የመጀመሪያ አካል ብዙ ቁጥር አመላካችን ወይም ቃል ተጠቀመ? የሚል ይሆናል ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት አንቀፁን ተከትሎ ሚመጣውን የብሉይኪዳን ከብሉይኪዳንም የዘፍጥረትን አ/ነገር በዚህ መልኩ ለማንበብ ልንገደድ ነው፡፡ እናም በ ወፍራሙ በዚህ መልኩ አንብብልኝ አቦ!
"וַיִּבְרָא אֱלֹהִים אֶת הָאָדָם בְּצַלְמוֹ בְּצֶלֶם אֱלֹהִים בָּרָא אֹתוֹ"
"በዚህ አይነት እግዚአብሄር ሰውን በራሱ መልክና በራሱ አምሳያ ፈጠረው"(ዘፍ 1፡27)
በርግጠኝነት አንቀፁ ነጠላ ቁጥርን ወይም የፈጣሪን ብቸኝነት ማመላከቱ አያጠያይቅም ፈጣሪ ከ አንድ በላይ ቢሆን ኖሮ ይህ አንቀፅ በዚህ መልኩ በቀረበ ነበር፡፡
" וַיִּבְרְאוּ אֱלֹהִים אֶת הָאָדָם בְּצַלְמָם בְּצֶלֶם אֱלֹהִים בָּרְאוּ אֹתוֹ."
"በዚህ አይነት እግዚአብሄር(እነሱ) ሰውን በራሳቸው አምሳል እና መልክ ፈጠሩ"
ነበር ባይሰበር ብዬ ልለፈው እና በዘፍጥረት 1፡26 በሶስተኛ አካል ነጠላ ቁጥር የተገለፀው ፈጣሪ "ተናጋሪ " ብቻውን መሆኑን አስረግጦ ሲያበቃ ንግግሩ ግን በመጀመሪያ አካል ብዙ ቁጥር ተገልፆ ነበር ይህም ከላይ እንዳየሐው በአምሳሌ ሳይሆን ያለው በ አምሳላችን እንፍጠር ነበር ያለው ፡፡ይህ አንቀፅ በ አርት ነጥብ ተደምድሞ ሚቀጥለው አንቀፅ ወይም ዘፍ 1፡27 ይህ በብዙ ቁጥር 360 ዲግሪ በ መዞር በነጠላ ቁጥር ተቀይሯል፡፡ እሱም በብረቱ አይንህ እንዳየሐው አንቀፁ ሚለው "በዚህ አይነት እግዚአብሄር ሰውን በራሱ መልክና በራሱ አምሳያ ፈጠረው" ነውና፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን በመጀመሪያ አካል በብዙ ቁጥር የተነገረው ንግግር ለምን ተነገረ ለሚለው ጥያቄ መልሱ በቋንቋ የፈጣሪን ክብር እና ልቅና ለማሳየት ነው፡፡ ቢሆንም ግን በሂብሩ ቋንቋ ህግጋት መሰረት ፈጣሪም ቢሆን ክብሩን በ መጀመሪያ አካል ብዙ ቁጥር በሚያመላክት ገለፃ ለመግለፅ የሚችለው ከሱ በታች ሌሎች ፍጡራን ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡ የመስኩ ጠበብቶችም እንደሚስማሙት ፈጣሪ ክብሩን ለማሳየት ይህን ቃል ሲጠቀም ከሱ በታች ሰው የተባለው ህልውና ራሱ ባይኖርም መላኢካዎች እንደነበሩ ይስማማሉ… ይህም የመላእካን መኖር እና የፈጣሪ ይህን ቃል መናገር… የፈጣሪ ክብር የተገለፀበት የብዙ ቁጥር አገላለፅ በቋንቋ ደረጃ ያለውን አግባብነት እና ትክክለኛነት ያሳያል፡፡
ንግግሩ ቀጥታ ሚመለከትው ከሱ በታች ያሉን መላክቶችን መሆኑን ነው፡፡ይህን በተመለከተ የብሉይ ኪዳን ጠበብቶች በ አንድ ድምፅ ይስማማሉ ብንል ማጋነን አይሆነም፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ሚሆን የብሉይ ኪዳን አንቀፅ አለ ይሀውም ኢሳያስ ነው፡፡
"ንጉስ አዝያን በሞተበት አመት እግዚአብሄርን አየሁት፣ እርሱ ከፍ ባለ ዙፋን እና ልእልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጎናፀፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር ፡፡ ሱራፌልም ተብለው የሚጠሩ እሳታዊ መላኢካኖችም በዙሪያው ነበሩ ፡፡ እያንዳንዱ መላኢካ ስድስት ክንፍ አለው፡፡ በሁለቱ ክንፎች ፊቱን ይሸፍናል፡፡ሁለቱ ክንፎች እግሩን ይሸፍናል በሁለቱ ክንፎች ይበር ነበር፡፡ አንዱ መልአክ ከሌላው በመቀባበል ቅዱስ፣ቅዱስ ፣ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ቅዱስ ነው ክብሩም በአለማት በሙሉ የሞላ ነውይሉ ነበር(3) ……..(8)ከእዚህ በኋላ እግዚአብሄር "ማንን እልካለሁ ለኛ መልእክተኛ ሚሆንልንስ ማ ነው? ሲል ሰማሁት፡፡ እኔም "እነሆ እኔን ላከኝ እሄዳለው " አልሁ ( ኢሳያስ 6፡1-3፣8)
ስምንተኛው አንቀጽ ላይ ፈጣሪ ለኛ መልእክተኛ የሚሆንልን ሲል የገለፀው አገላለፅ ከላይ ያየነውን ግልፅ ያደርጋል ፈጣሪ ከመላኢካዎች ስብስብ ጋር ነው ክብሩም እየተወደሰ ነበር እሱም የክብርን አገላለጽ በመጠቀም ክብሩን ለመግለፅ ችሏል፡፡
ይህ የመጀመሪያው እይታ ሲሆን ሁለተኛ እይታ እና በ አይሁዶች ዘንድ ተቀባይነት ያለው እይታ አለ፡፡ እሱም ፈጣሪ ሰውን በአምሳላችን እንፍጠር ያለው አንድን ነገር ሲሰራ መላአኮችን በማማካር በመሆኑ ነው የሚለው እይታ ነው፡፡ ይህን የ እምነት ክፍል አይሁዶች ሰማያዊው ጉባኤ ይሉታል እናም ይህ የ እምነት ክፍል ለተነሳንለት ትንታኔ ወሳኝ በመሆኑ ወደዚህ ክፍል ያስገባናል

ሰማያዊው ጉባኤ

በታሪክ እኛ የሚለውን ገለፃ በ ሁለት መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል ተስተውሏል፡፡ አንድም የሆነ አመራር ወይም ገዢ ውሳኔ ሲሰጥ አንድ ሰው ገዢውን ወክሎ ሲናገር "እኛ" በሚለው አገላለፅ ጥበብ ይዞ ሲሄድ ይሰተዋላል፡፡ ሁለትም አንድ ንጉስ የራሱን ንግስና እና ልቅና ብቻ ለመግለጽ ሲፈልግ ይህን አገላለፅ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡ የሖነ ሆኖ ሁለቱም ታሪካዊ ማስረጃ አላቸው በተለይ በተለይ በ ሴሜቲክ ቋንቋ ተናጋሪዎች
ወደ ቁም ነገሩ ስመልስህ ፈጣሪ አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት የሚያማክራቸው እነዚህ "ሰማያዊ ጉባኤ " ተብለው በአይሁድ አምነት ተከታዮች ዘንድ የሚታወቀው ጉባኤ ምን ድ ነው? ሀይማኖታዊ ፅሁፎችስ ላይስ ምንስ መሰረት አለው ? የሚልም ጥያቄ ማንሳቴ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ እናም ይህን እይታ በጥልቀት ወደ ሚዳስሰው የአይሁዶች አመለካከት እንለፍ ነው ሚባለው?
እነሆም መጀመሪያ መነሳት ያለበት ጥያቄ ፈጣሪ አንድ ነገር ከመስራቱ በፊት ሚያማክራቸው አካላት አሉ የሚል ነው? ይህ ጥያቄ መለኮታዊ ተብሎ ከሚታመንበት የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ መልስ ይፈልጋል፡፡የሖነ ሆኖ ምላሹን እንደወረደ ብሉይ ኪዳን ላይ በዚህ መልኩ ይነበባል፡፡
"ልኡል እግዚአብሄር ሚስጥሩን ለ ጉባኤው( סוֹד) ለአገለጋዮቹ ነብያት አስቀድሞ ሳይገልጥ ምንም ነገር አይደርግም"(አሞፅ 3፡7) ፈለክም አልፈለክም እውነታው ይህ ነው፡፡
የሒብሩ ቃል ( סוֹד) ማለት በቋንቋ ደረጃ ብቻ ካየነው እንኳ የሰዎች ፣ የነገሮች ስብስብ ተብሎ ይተረጎማል ዘፍጥረት ላይም ይህን የሚደግፍ ቃል በደማቁ ታገኛለህ
"እነርሱ በቁጣቸው ብዙ ወንዶችን ስለ ገደሉ፣ ከንቱ ምኞታቸውን ለማርካት ብዙ ኮርማዎችን ስለሰባበሩ ፣ በነርሱ ጉባኤ፣ ምክር ( סוֹד) አልገባም" (ዘፍጥረት 49፡6) አልፎ ተርፎ ( סוֹד) ይህ ቃል የሚያማክራቸው ጉባኤ ተብሎ ተተርጉሟል በዚህም ረገድ የምሳሌ መፅሐፍ ተጠቃሽ ነው፡፡
"ካለ አማካሪ(וֹד ) እቅዶች አይሳኩም ፡፡ በብዙ አማካሪዎች ግን ስኬታማ ትሆናለህ" (ምሳሌ 15፡22)
በኤርሚያስ መፅ ሀፍ ላይም (18፡18-23) ( סוֹד) የሚለው ቃል አማካሪ ተብሎ ወይም በ ኢንተርናሽናሉ ቋንቋ council of YHWH ተብሎ ተተርጉሟል፡፡
ያም ሆነ ይህ ዋናው ቁምነገር ምናልባት ቃላት እንደ አውዳቸው የተለያየ ትርጉም እንደ መጡበት አውድ ቢሰጣቸውም ፈጣሪ ግን አማካሪዎች እንዳሉት ይህ ሐይማኖታዊ ፅሁፍ ይገልፃል ፡፡ እናም ሚነሳው ቀጣይ ጥያቄ ፈጣሪ አማካሪዎች ካሉት…. እነዚህ ሰማያዊ አማካሪዎች እነማናቸው? የሚል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህን ተያይዞ ፈጣሪ በመለአክት ታጅቦ እንዳለ የሚገልፅ የሚገልፅ የብሉይ ኪዳን መሰረት አለ
አንደኛ ነገስት ላይ በዚህ መልኩ የሰፈረውን አንቀፅ አንብብ
"እግዚአብሄርም ሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ፣ መላእኩ ሁሉ በቀኝ እና በግራው ተቀምጠው አየሁ"( 1 ነገስት 22፡19)
ምሳሌም ላይ ከፈለክ በዚህ መልኩ ሰፍሯል
"መልአክቱም ሁሉ አመስግኑት፣ በሰማ ያላችሁ ሰራዊት ሁሉ አመስግኑት"(መዝሙር 148፡2)
ሌላው የሰማይ ጉባኤ(መሰባሰቢያ) እንዳለ መረጃ ሚሆነው በ እዮብ መፅሀፍ የተጠቀሰው ታሪክ ነው፡፡
"ከእለታት አንድ ቀን የሰማይ መላእክት(የፈጣሪ ልጆች) በ እግዚአብሄር ፊት በቀረቡ ጊዜ ሰይጣንም አብሮ ቀረበ"(እዮብ 1፡6፣2፡1)
ይህ አንቀፅ ሚያሳየው በእግዚአብሄር ፊት መላኢካን እንደሚሰባሰቡ እንደሆነ ሲደመር ሰማያዊው ጉባኤ
ህልውና እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን የ አይሁድ ምሁራን አስረግጠው ይገልፃሉ፡፡ ከዛ በዘለለ ይህ ሰማያዊ ጉባኤ በ ግልፅ መዝሙር መፅ ሀፍ ላይ ተጠቅሷል
"አንተ በቅዱሳን ጉባኤ(סוֹד קְדֹשִׁים) መካከል የተባረክ ነህ"( መዝሙር 89፡7)
እስካሁን እንደተመለከትከው ፈጣሪ አንድን ነገር ለማረግ ሲወስን አማካሪውን እንደሚያማክር ነው፡፡ የመላክትም ይሁን የነብያትን … ከዚህ ተነስተው የአይሁድ ምሁራን ሰውን በ አምሳላችን እንፍጠር ሲል ሰማያዊ ጉባኤን እያማከረ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡
በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ሚሆኑት የ አይሁድ ፅሁፍ ምሁር ረባይ ሳሙኤል ሚአር ናቸው፡፡ በተንታኝ መፅሀፋቸው እንዲህ ሲሉ ፅፈዋል፡፡
“1.26 Yayyo’mer GOD SAID, to His angels, “LET US MAKE MAN” : So one also finds [God consulting his angels] in the story of Micaiah, the son of Imlah, in Kings(1,22.19-22) and in Isaiah(6., “Whom shall I send? Who will go for us?” and in Job(e.g. 1.6-12).”(6)
"1፡26 ላይ ፈጣሪ ለመላእክቱ እንዲህ ብሏል "ሰውን በአምሳላችን እንፍጠር" በተመሳሳይ መልኩ ፈጣሪ መላእክቱን ሲያማክር በ አንደኛ ነገስት 22፡19-22 እንዲሁም ኢሳያስ 6፡8 ላይ እናገኛለነን፡፡"ማንን እልካለሁ ለኛ መልእክተኛ ሚሆንልንስ ማ ነው?"
የአይሁድ አዋልድ መፅሀፍት ውስጥም እንዲህ የሚል ተፅፏል
“Targum Yonasan paraphrases: “And God said to the ministering angels who had been created on the second day of Creation of the world,’Let us make Man.’
When Moses wrote the Torah and came to this verse (let us make), which is in the plural and implies that there is more than one Creator, he said: “Sovereign of the Universe! Why do you thus furnish a pretext for heretics to maintain that there is a plurality of divinities?” “Write!” God replied. “Whoever wishes to err will err … Instead, let them learn from their Creator Who created all, yet when He came to create Man He took counsel with the ministering angels”(Midrash).”(7)
በኔው አማርኛ ሲተረጎም
"ዮናሳን ታረጉም ላይ እንደተገለፀው " ፈጣሪ ለመላእክቱ አለም በተፈጠረች በሁለተኛ ቀን ላይ እንዲህ አለ "ሰውን በ አምሳላችን እንፍጠር " ሙሴ ይህን በሚፅፍበት ወቅት ቃሉ ብዙ ቁጥርን አመላካች ሆኖ አገኘው እናም የፍጥረት የበላይ የሆንክው ሆይ! ለምን ይህን ቃል ተጠቀምክ ከሃዲያን እኮ ብዙ አማልክታቸውን ለመግለፅ ይጠቀሙበታል፡፡ ፈጣሪም መለስ ሰጠ "ፃፍ!" መሳሳት የፈለገ ይሳሳታል… ሁሉንም ነገር ከፈጠረ ፈጣሪያቸው ቢማሩ ይሻላቸዋል፡፡ ሰውን ሊፈጠር በፈለገ ጊዜ መላእክቱን በማማከሩ ነው ይህን ያለው "

እናም የብሉይ ኪዳን ባለቤቶች ክርስትያኑ እስኪያገኘው ድረስ ለምእተ አመታት በብቸኝነት ሲመሩበት የነበሩት አይሁዶች መሰረታዊ እምነት እዚህ ላይ የተገነባ ነው፡፡ በምንም ተ አምር ዘ ፍጥረት 1፡26 መሰል አንቀጾች የ ፈጣሪን ብዙነት አይሳዩም፡፡ ጭራሽ ህልውናው ከ 3ኛው ክፍለ ዘመን ቡኋላ የመጣውን የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ሊያፀድቅ ቀርቶ ……
በዚህ መልኩ የተነገሩ አነጋገሮች በብሉይ ኪዳን ውስጥ በተለያዩ መልኩ ሰፍረው እናገኛቸዋለን … ምሳሌ መጨመር ካስፈለገ ዘፍጥረት 3፡22 ላይ እንዲህ የሚል ቃል በ ወፍራሙ እናገኛለን " ከዚህ በኋላ እግዚአብሄር አምላክ እነሆ አዳም ደጉን ክፉውን ሊለይ የሚያስችል እውቀት በማግኘቱ ረገድ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" ይህም በቋንቋ ህጉ መሰረት አንዱ ፈጣሪ ለራሱ ሳይሆን ከሌላ አካል አጋር ጋር የሚያደርገውን ንግግር የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱ ከአንዱ ፈጣሪ ጋር የነበሩት መላኢካን መሆናቸውን ተያይዞ መላእካንን እንደሚያመላክት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ዘፍጥረት 11፡7 ላይ ያለውም አንቀፅ በተመሳሳይ መልኩ ይታያል፡፡ ያም ሆነ ይህ ቤትኘውም ስሌት እነዚህ አገላለፆች በ4ኛው ክ/ዘመን የእምነት ክፍል የሆነውን የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ለ ምእተ አመታት እንዳላመላከቱ እና ሊያመላክቱ እንደማያመላክቱ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ሌላው በ ዘፃእት ምእራፍ 32 የተጠቀሰ አንቀጽ ሲኖር ሐሩን ሰራው የተባለው አንዱ ጣኦት በብዙ ቁጥር የተጠቀሰበትን ሁኔታ እናስተውላለን ይህ አንቀፅ ብዙ ቁጥርን ያመላክታል ከተባለ መልሱ አይመላክትም? ክብርንስ ያመላክታል ከተባለ መልሱ አያመላክትም የሚል ይሆናል ? ምን ያመላክታል ከተባለ ነጠላ ቁጥር ን ብቻ እላለው እንዴት በብዙ ቁጥር መልኩ ተጠቅሶ ነጠላ ቁጥርን ያመላክታል የሚል ጠያቄ መነሳቱ አይቀርም ይህም በ ሂብሩ " የመሳሳብ ህግ" ወደሚባለው የቋንቋ ሰዋሰው ይመራናል ኢንሻአላህ ይቀጥላል …….

ማስተዋል ሚሻ ጥያቄዎች

1. በትንቢተ ዳንኤል የሰፈረው በዚህ መልኩ ይነበባል
" דנה חלמא ופשרה נאמר קדם־מלכא"
"ህልሙ ይህ ነው፡፡ በንጉሱ ፊት እኛ ትርጉሙን እንናገራለን…."(2፡36 ) ጥያቄው ንጉስ ናቡከደነስር ፊት የቆመው ዳንኤል ህልሙን እኛ ሲል በብዙ ቁትር አመላካች የገለፀው አንድም ሶስትም ስለሆነ ነው? ወይስ ብዙ ስለነበረ? ምላሹን ተመራመሩበት………
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest