ልብ ያለው ልብ ይበል !!!!!!!!!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ልብ ያለው ልብ ይበል !!!!!!!!!!!

Postby መርፊው » Thu Sep 26, 2013 9:11 pm

ልብ ያለው ልብ ይበል!
አስደንጋጩ የእንግሊዝ ጳጳሳት ጥናት
እንግሊዝ በሚገኘው ዴይሊ ኒውስ በተባለ ጋዜጣ ላይ ‹‹አስደንጋጭ የእንግሊዝ ጳጳሳት ጥናት›› በሚል የመግለጫ ፅሁፍ ላይ ከግማሽ በላይ የእንግሊዝ ጳጳሳት በስምምነት ላይ በደረሱት መሰረት ‹‹ክርስቲያኖች ኢየሱስ ጌታ ነው ብለው የማመን ግዴታ የለባቸውም›› የሚለው ዘገባ መላውን እንግሊዝና ሌሎችንም የአለም ክርስቲያኖች አስደንግጦ ነበር፡፤ በዘገባው መሰረት ከ 39 የእንግሊዝ ጳጳሳት ውስጥ 31 ጳጳሳት የኢየሱስን መለኮታዊ የክርስትና ሀይማት መርሆችን በማውገዝ ሁለቱንም ፅንሰ ሃሳቦች ሙሉ ለሙሉ ዋጋ ቢስ አድርጋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ለብዙ ዓመታት በክርስቲያኖች ዘንድ ሲታመንባቸው የቆ ሁለት ፅንሰ ሃሳቦች በተሳሳተ መልኩ ከኢየሱስ ብዙ ጊዜያት በኋላ ሰዎች የከተቷቸው እንደሆኑ ተገልፃል፡፡

ጳጳስ ጄንኪንስ የክርስተረናን መሰረታዊ አስተምሮ አወገዘ
አዲሱ ለደርባን የተሸሙትና የኢንግሊዝ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የጳጳሳት ደረጃ አራተኛ ላይ የሚገኙት ቄስ ፕሮፌሰር ዴቪድ ጄንኪንስ በለንደን ውስጥ ‹‹ክሬዶ(CREDO)›› ከተባለው ሳምንታዊ የቲቪ ፕሮግራም ላይ በተደረገላቸው ቃለ መጠየቅ ላይ ጠንካራ መሰረት በሌለው የክርስትና ሀይማኖት በተገነባበት መርህ ላይ ከፍተኛ ሂስ ሰንዝረዋል፡፡
በክርስትና ሃይማኖት ውስጥ ከምንም በላይ መሰረታዊ የሆነውን የኢየሱስ መለኮታዊነት (አምላክነት) እና ሞቶ መነሳቱን ጉዳይ ስህተት መሆኑን የኢየሱስን ተልእኮ በመጥቀስ ፕሮፌሰሩ እንዲህ ይገልጹታል፡- ‹‹…..በፍጹም እውነት ያልሆነ ነገር ሲሆን ሆኖም የቀደምት ክርስቲያኖች የኢየሱስ መሲህ(የተቀባ) መሆን ላይ ያላቸውን ጠንካራ እምነት ለመግለጽ ሲሉ በኢየሱስ ታሪክ ውስጥ የጨመሩት ስህተት ነው፡፡›› ይህ ትክክለኛን የአምላክን አምላክነት እና የኢየሱስን መልዕክተኝነት ቀደምት ሀዋሪያት፤ የቀደምት ክርስቲያኖች፤ ጥንታዊና የዘመኑ የክርስቲያን ምሁራን፤ ፀሀፍት እንዲሁም ተራ ክርስቲያኖች ይቀበሉታል፡፡ ኢየሱስ ራሱም በማቴዎስ ወንጌል ላይ እንዲህ ይላል፡-
‹‹……..ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና….›› ማቴ.ወ 4፡10
በዮሐንስ ወንጌል ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል፡-
‹‹እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላክውንም ኢየሱስ ክርስቶስ ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ህይወት ናት፡፡›› የዮሐንስ ወንጌል 17፡3
በሌላ የዮሐንስ ወንጌል አንቀጽ ላይም እንዲህ ይላል፡-
‹‹እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና አምላካችሁ ዐርጋለሁ››(የዮሐንስ ወንጌል 20፡17)
እንዚህ አንቀጽች ግልጽ አይደሉምን? ኢየሱስ(ዐ.ሰ) እን አምላክ የሚታየው ከየት በመጣ መረጃ ነው?
እዚህ ጋር የቢሊየን ዶላር ጥያቄ እናንሳ ‹‹እውን ስላሴ መለኮታዊ ራዕይ ነውን?
Source:- Is the trinity doctrine divinely inspired? Page 13
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests

cron