ኢትዮጵያውያንን ከስውዲ ማስወጣት የአላህን ትዛዝ ማፍረስ ነው

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ወርቅነች » Tue Nov 19, 2013 1:55 am

ቅቅቅቅቅ...ክቡ ምነው ሰንዴውን ከንክርዳድ ደባለቅክው....እዚህ ጉዳይ ዲን ምን አገባው :lol: ኡስታዝ መሆን የምትችል አይመሰለኝም በተለይ የዚህን ቤት አርእስትን ባንክሮ ብታነበው :lol: :lol: እኔ እንደሆን ማንንም አላምንም በተለይ አህባሾችና ቄሶችን :lol: :lol: መቼም ታሰረው ተደብድበው ኪሳቸው ተበርብሮ የተዘረፉትን ወገኖቻችን ወያኔ ይተካላቸዋል ብዮ አምናለሁ.....መቼም ሰሞኑን የደረሰህ መገልጽ ከሞትም ሰለመለሰህ ብዙ ማሰተማር እንደምችል በቂ የምሰክር ወረቀት አግኝትህ ዲጎኔ እንኳ በሚገጣጥመው ግጥም አልረሳህም.... በል ከስራ በህዋላ መልካም ጊዜ ይሁንልህ ትላሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:

ክቡራን wrote:ወርቅዬ በችኮላ ነው የምጽፍልሽ....ልወጣ ነው ከኦፊስ..እኔ እኮ ያልኩት እኛን እንደ እውነተኛ ሙስሊም አያዩንም ያልኩት የእኛ ሙስሊሞች ትክክለኛውን ዲና ስለሚከተሉ የቁራኑን ህግ አፕላይ ስለሚያደርጉ ላረቦቹ አልተመቹላቸውም ልልሽ ፈልጌ ነው እውነቱም ይሄ ነው እነሱ እኮ ማጅራት መቺዎችና ዱርዬዎች ናቸው:: ያሰሯቸውን ልጆች ገንዘብ ፈትሽው ወስደውባቸዋል:: አላህ እንደውም ለሌለው ጨምረህ ስጥ እንጂ ያንተ ያልሆነውን አትንካ ይላል...ይሄ ታዲያ እስልምና ነው ትያለሽ...?? እነዚህን አረቦችን አትመኚ ባጠቃላይ ከሳውዲ የሚመጣን ምንም ነገር አትመኚ!!! አንድ ነገር ብቻ መካ ውስጥ ታሪካዊ ቦታ አለ ተብሏል:: ይሀውም አብርሀም ልጁን ለመስዋትነት ያቀረበበት ቦታ ስለሆነ ሊከበር ይገባል:: ያንን ብቻ በልብሽ ያዥው ሌላው ወንጀልና ቴረር ነው:: ያገርሽን እምነት አህባሽን ( ትክክለኛውን እስልምና ያዥ) እስኪ ወርቅዬ እንደው እናንተ ሰፈር ቦታ ፈልጊልኝ...ኡስታዝ መሆን የምችል ይመስለኛል..ችግር የለም ቁራኑም ባማርኛ ስለሆነ የሰባት አመቱን ትምህርት በሰባት ቀን አስተካክለዋለሁ:: ሰላም አምሺልኝ ሰሞኑን በተሰጠኝ መገለጽ ከመጸሀፍ ቅዱስም ከቁራንም እየጠቀስኩ የሰማይን ሚስጥር አስተምርሻለሁ:: በነገራችን ላይ የምንወደው ወንድማችን ዲጎኔ እኮ የግጥም ደራሲ ሆነ ..ካልሰማሽ ብዬ ነው:: :D
ዮሀንስ ዐፍወርቅ ነኝ:: ሞቼ ነበር አላዋጣ ሲለኝ ተመልሼ መጣሁ:: :lol: :D
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ምክክር » Wed Nov 20, 2013 8:47 am

ክቡሻ ፒስ ነው.?

ጥሩ ጋዜጤኛ ለመሆን መከተል ካለብህ አንዱ መርህ:-

-ለየትኛውም ፓርቲ ሆነ ግሩፕ: ሃይማኖት ወይም ጎሳ ታማኝ ወይም ተገዥ ወይም ቱልቱላ አለመሆን ነው:: የአንተ እምቢልታ እንደምወደው የትግርኛ ዘፈን ቢቱ ጥርት ኩልል ያለ ነው::

ሙያዊ ሥራህን ተወጣ:: ኢትዮጵያውን ስደተኞችን ለመርዳት የተከፈተ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ካለ አፈላልግና ለጥፍልን:: አንድ ትልቅ ሥራ ሠራህ ማለት ነው:: ነብዩ ምን አለ...... አላህ እንዲህ አለ እያልክ አትዘላብድ:: ቁምነገርና ፌዝ በጣም ትቀላቅላለህ:: አትንቀልቀል!

አትዛነፍ
ከአርዕስቱ ብንጀምር የዚህ ዓምድ መልእክት የተዛነፈ ነው:: ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሀዲስ ስለ ሀበሻ የተናገሩት መልካም ጉዳይ አለ:: የዚያች አገር ንጉስ ፍትሃዊ መሬቷም (ሕዝቧም) መልካም ነውና ወደዚያች አገር ሂዱ ያሉትን አጭርና ግልጽ መልዕክት መሰነጣጠቅ አያስፈልግም:: አንደኛህን ነብዩ የኢትዮጵያን ስደተኞች አትንኩ ብሏል ማለቱ ይቀላል:: የተዛነፈ ነው ያልኩት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሩት አሁን ሳዑዲያ ከወሰደችው እርምጃ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም:: እንዝርት እያሾርክ ለመፍተል: ጥልፍ ለመጠላለፍ ካልሆነ በቀር:: በተፈጠረው አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የጥያቄ ምልክት ማስቀመጥ: ከሃይማኖትና ጎሳ ጋር ማናኮስ: የአንተ ልዩ ምልክት ብቻ ሳይሆን የወያኔ ፉጨት መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው:: ሁሉንም ሃይማኖትና ጎሳ እኩል ማክበርና ማስተናገድ አለብህ:: ይህ ሃይማኖትን ከተከታዮች ለይተህ መረዳት ከቻልክ ነው እንግዲህ...

ግርግር ትወዳለህ::
ሃገረ-ነክ የሆኑ ጉዳዮችን እንኳ ከሃይማኖትና ከጎሳ ጋር ማወሳሰብህ ዓላማህን ፍንትው አርጎ ያሳያል:: ቦታህን ያቀለዋል እንጂ የሚያስገኝልህ ምንም ክሬዲት የለም:: ከዚህም በፊት ነግሬሃለሁ:: አንተ ዋርካ ላይ ጥሩ ሰርተህ ዝና እና ክብር ማትረፍ ስትችል ክሬዲትህን እያጣህ ነው:: ትጉህና ቅን ጋዜጠኛ ለመሆን የሚጠራጠር እንጂ እንዳንተ የለየለት ጠርጣራ ወይም ጨለምተኛ መሆን የለበትም::

የጋዜጠኛ ክብር ልክ እንደ ድንግል ነው:: ይግባህ....
Don't mortagage your integirity.
It is like Virginity....
...once you lose it you've lose it forever.


CHASE YOUR DREAM....Stop living for others!
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 290
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ክቡራን » Thu Nov 21, 2013 1:18 pm

ምክርዬ ነፍሴ አባቴ ወንድሜ :: ያገሬ ልጅ...ወገኔ የመከርከኝን ምክር ኪስህ ውስጥ ክተተው:: መኅረብም አድርገው ተናፈጥበትም:: አልፈልገውም..አልቀበለውም:: ይሄን የምሰማበት ወይም የሚሰሙህ ኢትዮጵያውያኖች አይኖሩም:: አንተ ዴሊብርተሊ የወገኖቻችን ስቃይና ጨሀት እንዳይሰማ ወሀቢስት አረቦችን ሲሲተማቲክ በሆነ መንገድ እየተከላከልክ ነው:: ወሀቢስት መሆን መብትህ ነው:: ወሀቢስት ነን እያሉ ይሄን የመሰለ ሀጢያት በሰው ልጅ ላይ የሚሰሩትን መከላከል ግን ወንጀል ነው:: እቺን ተጫን::
http://www.ethiograph.net/video/watch.php?vid=0c02a2f81
አንድ እምነት የሚያምኑትን ሰዎች መንፈስ መለወጥ ካልቻለ ያ እምነት ወይም ዶክትሪን ላይ ችግር አለ:: ሀይማኖት ፊሎሶፊ አይደለም..ሀይማኖት የሰዎችን እምነት መለወጥ አስተሳሰባቸውን መግራት ወደ ፍቅርና ሰላም መምራት ይኖርበታል:: አስተውል እስልምናን ( የሰላም እምነትን) እንይደለም እየተቃወምኩ ያለሁት:: እኔ የምቃወመው በስመ እስልምና የመጣውን ዘመን አመጣሹን ወሀቢዝምን ነው:: ሲያስተርር ሲያሰቃይ እንጂ የእላህን ፍቅር ሲያሳይ አላየሁትም:: ምናልባት ይሄ ጉዳይ ክርስቲያን (ካፊር) በሚባሉት ላይ ብቻ ነው እንዳልል ...ሌላውንም የነሱን እምነት ያልተከተለ ሙስሊምን ተመሳሳይ ነገር ሲያደርጉበት አይቻለሁና ነው:: እነሆ እውነትን የሚናገር በመጥፋቱ ከዛሬ ጀምሮ ትክክለኛውን እስልምና ለማስተማር ራሴን አዘጋጅቻለሁ:: stop thinking for others ነው ያልከኝ? እኔ የተማርኩት መጽሀፍ ደሞ ይሄን ይላል live for others!! እውነቱን ፈልገህ አግኝ::
ቢላል እባላለሁ::
እቺን ይጫኑ የተከበሩ አንባቢ:: ተከታታይ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
http://www.youtube.com/watch?v=lG3_Gp_AybU
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ምክክር » Sat Nov 23, 2013 9:19 am

ዋሀቢዝም...የሰሞኑ የወያኔዎች እሮሮ
.....እነሆ ያቃዥህ ጀመር እንቅርትህ ላይ ተቀርቅሮ::

የሚገርመው እንደ ራይቫል ኮምፒት ማድረግ ሲያቅትህ እንደልማድህ የሆነ አይደንቲቲዬ ላይ ታፔላ እየለጠፍክ ኢሪለቨንት ልታረገኝ ትሞክራለህ::

በእንዲህ መሰል ያላሰ-ለሰ ጥረት አባጨጓሬ ሆነህ ቀረህ:: እኔ ደሞ የምለው ክቡሻ ከአባጨጓሬነት ተቀይረህ ቢራቢሮ መሆን ትችላለህ ነው:: ምርጫዉን ላንተ ትቻለሁ::


ሰሞኑን ከአሳዳሪዎችህ የተሰጠህ የቤት ሥራ ሊሆን ይችላል...ግን ወያኔዎቹ አሳዳሪዎችህም ይሄ የሳዑዲያው ግርግር እንዲባባስ የሚፈልጉ አይመስለኝም:: ቀሽም :cry: ....ተቃዋሚዎች ጥሩ ሥራ እየሰሩበት ነው:: አለቆችህ ፊያቶ ስለሌላቸው ለግድቡም የዲፕሎማሲ ጥረቱን እንዳያሰናክል ይቺ ሳዑዲያ የተከሰተችው ድርጊት እንዳትባባስ ..ጸጥ እንድትሉ አንተና ቢጢዎችህ ትዕዛዝ በቅርቡ ይደርሳችኋል:: :o አንዱ ዉሥጥ አዋቂ ነው ሹክ ያለኝ:: ከቨር ሀፕ እንለዋለን!
ዋርካ ፓለቲካ ላይ አንደኛው ባልደረባህ የሚጽፈዉም ይህንኑ ነው:: :oops: ስለማባረር መብት:: ለምን አለፍከው?

ስማኝማ
አሁን በኢትዮጵያውያኖች ላይ ለደረሰው ቅሬታችንን ድምጻችንን የምናሰማው ለዘውድ አገዛዙ ነው:: እኛ መንግሥት የምንለው:: ፓሊስያቸው ላይ ነው ምናነጣጥረው:: የሳዑዲያ መንግሥት ወሀቢስት ሆነ ፔንጤ ቂቂቂቂ አንተ ሚጡ ወያኔ ከአቅምህ በላይ የሆነ ነገር ዉሥጥ ገብተህ አትፈትፍት .....በወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ወሀቢዝምን አጀንዳ አርገህ መርታት አትችልም:: ከቶዉን ለቅዋሜ መነሻ ነጥብ ሊሆን አይችልም:: ቀሽም አስተማሪ ነው ያለህ:: ኦሮሞ: አማራ : ጉራጌ: ኦርቶዶክስ: አህባሽ: ኢስላም ምናምን እያላችሁ በጎሳና በሃይማኖት የቀለማችሁትን ታፔላ ቀናችሁ እስኪደርስ እዛው አገር ቤት ለጣጥፉ! በዋሀቢስት ምትክ ሱና ወይም ሌላ ሴክት በሳዑዲያ ዶሚናንት ቢሆንስ ኖሮ አሁን የደረሰው አይደርስም ብለህ ነው ምታስበው? የምንቃወመው እንዳለ ሆነ እውነታዉንም ጎን ለጎን ማየት አለብን:: የተባረሩት ሕጋዊ የሥራ ፍቃድ የሌላቸው ከመላው ዓለም የመጡ ዜጎች ናቸው:: እንደ ጋዜጠኛ ይህን ሃቅ እንኳ አልፈኸዋል:: ከነዚህ መሀከል ፊሊፒኒዎች...የመኒዎች...ኢንዶኔዥያንስ እንዳሉ አስተውለሃል? ከተባረሩት ሙስሊሞችም እንዲሁ ወሀቢስቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠርጥረሃል? እርምጃው የፓሊሲ እንጂ ከሃይማኖት የመነጨ ፍጥጫ አይደለም:: ክርስትያኖች ይውጡ አልተባለ ነገር ዝምብለህ ጥላቻህን ትቀረሻለህ:: እንበል ወያኔ ኦሮቶዶክስ ብትሆንና አሁን ለተጀመረው የግድብ ሥራ አንድ የግብጽ ጋዜጤኛ የቄሶቹን ጥምጣምና መስቀል ሲያወግዝ ቂቂቂቂ እንደዛ'ኮ ሆንሽ ክቡሻ..... ወያኔ ምንም አይደለችምና ተመችህ ማለት ነው::

ምኑን ከምን ነው ምትቀይጠው ያልኩህ ለዚህ ነው::

ክቡሻ:-
በብረሽ ተረግዞ በሰባት ወር እንደተወለደ ልጅ ቅዥቅዥ...ጥድፍድፍ አትበል:: ችኩል!
ኦልዌይስ ኢን ረሽ
.ክቡ ኦልዌይስ ኢን ረሽ ጎይንግ ኖ ዌር!! የትም አትደርሽም :roll: :roll: :roll: :roll: :roll:
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 290
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests