አወዛጋቢው እየሱስ !

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

አወዛጋቢው እየሱስ !

Postby መርፊው » Sun Dec 01, 2013 12:24 am

አወዛጋቢው እየሱስ :idea: :idea:

"በገነነው ስብእና" ማንነት ላይ በሚነሱ እልህ አስጨራሽ ክርክሮች በስተጀርባ ያለ ታሪክ
ክፍል አንድ
--------
ክርስቶስ ማን ነው? Who Is Christ?

መልስልኝ እንጂ ! ማነህ ልጥይቅህ
ነብይ ወይስ አምላክ ምንድነህ ልወቅህ
ሰዎች አምላክ አሉክ ሰዎች ነብይ አሉክ
ከፊሉ ወደዱክ ከፊሉ ሰደቡክ
አንተ ኑ እስኪያውቁ ዳግመኛ እስክተመጣ
እሳት ያነዳሉ ይመጣል ጦስ ጣጣ !!!!

ወሳኝ ጥያቄ!!! በዘመናት ስንቱ ሲጠይቅ ጠይቆም ሲያጠያይቅ የደከመለት መሰረታዊ ጥያቄ !!! "ክርስቶስ" ማን ይሆን???

አዎ! እየሱስ ማ ነው?

ሂድ ! ቫቲካን እና የሮማን ካቶሊክ አባቶችን ጠይቅ ወይም ደግሞ ግብፅ ፣ ግሪክ ፣ ራሻ፣ ወይም እዚሁ ሐገርህ የሚገኙ የ ኦርቶዶክስ ሊቃውንትን ጠይቅ ! ወይም አዲሱ ሐይማኖታዊ ተሐድሶ እናራምዳለን ባዮችን የጆሆቫ ምስክሮች ፣ ፋንዳሜታሊስት ክርስቲያኒዝም ፣ፔቲዝም፣ኢቫንጄሊካሊዝም፣ ጴንጤቆስጤኒዝም ወይም ቅዱሳዊ እንቅስቃሴ በሚል ስያሜ ብቅ ብቅ ያሉት የ "ክርስትና" አማኞችን ጠይቅ ! እየሱስ ማ ነው ንገሩኝ በላቸው ? ደግመህ ደጋግመህ ጠይቃቸው!!! ፡፡ ጠይቀህም ስታበቃ እያንዳንዱ ስለነገሩህ እየሱስ ማንነት እና ምንነት ለየብቻው በወረቀት ላይ ፃፈውና አንበው፡፡ እመነኝ! የተለያዩ እየሱሶችን ማንነት ከተለያዩ አእምሮዎች ከፈለቁ አንፃራዊ ምክከታ እና የተቃረነ አመለካከት ጋር "ፏ" ብለው ታያለህ ፡፡
ምሁራን እንዲህ ቢሉም አይገርምም
"Christianity in a modern world richly divers phenomenon" (3)
" በአዲሱ አለም ያለው ክርስትና በ እጅጉ ተለያይቶ ይገኛል"
"As there are reported to be approximately 41,000 Christian denominations"(4)
"ጥናቶች እንደሚያመላክቱት 41.000 የሚሆኑ የክርስትና ቅርንጫፎች አሉ"

በእርግጥ ለአንዱ እየሱስ እጅግ የተለያየ ማንነት ያላበሰው ዘመናዊው አለም ላይ ያለ የተለያየ አመለካከት እና ሳይነሳዊ ፍልፍና ሲሆን እየሱስ ላይ ላለው አመለካከት እና እምነት መሰረት የሆነው ግን አንድ ወጥ መፅሀፍ እና ፅሁፍ ነው " የሚል ፎርሙላን ያነገበ አጥበቆ ተከራካሪ ይኖር ይሆናል፡፡ ግን ይህስ እውነት ነው? ሌላው ጥያቄ?
የሰው ልጅ ጠያቂ እና ነገሮችን ፈታሽ በመሆኑ ብቻ ጥያቄን በጥያቄ ላይ በማከታተል ይጠይቃል፡፡ ጠይቆም ይፈትሻል እንዲሁም ይመረምራል ፡፡ በቃ! ያልተመለሰ ጥያቄ ይዞ ሲኖር እረፍት አይኖረውም፡፡ ማን? ይህ ድንቅ ፍጡር !!!የሰው ልጅ!!! ፡፡
በ እየሱስ ማንነት ላይ "ዘንድሮ እንጂ ድሮ" ጥያቄም ተነስቶ አያውቅም ፡፡ የሚሉ " ምእመናንም" ቀላል አይደሉም፡፡ ባለመሆናቸውም ብዙሐኑ አማኝ ጥንት ስለነበረው ክርስትና ጠይቆ አያውቅም፡፡ ስላልጠየቀም የያዘው አመለካከት ለሱ እውነት ነው፡፡ ግን ነው?
ይህ እና መሰል ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ጊዜውን ወደኋላ እንድንመልስ እና የታሪክ የኋላ ገፆችን እየገለጥን እንድናይ ምክንያት ሚሆነን፡፡ በዚም መልኩ ብቻ ና ብቻ ነው በ ገነነው " እየሱስ" ዙሪያ ያለውን ትክለኛ አመለካከት " ምን ነበር? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ሚያስችለን " ስለዚህ እንጠይቅ ?

ትናንት እና ዛሬ

እንዳልኩህ "ትናንት(ጥንት)" የነበረው ክርስትና "አንድ ወጥ" አድርገው ሚያስበቡ ምእመናን ቀላል አይደሉም፡፡ በ እጅጉ ብዙ ናቸው ፡፡ "ዘንድሮ እንጂ ድሮ ልዩነት የለም" የሚል ብሂልን አንግበው ሲያበቁ እንደ ገደል ማሚቱ እየተቀባበሉ ሚያስተጋቡ ሚሽነሪዎች እና አማኞችም ቸርች ይቁጠራቸው እንጂ ቆጥረህ አትዘልቃቸውም፡፡
የታሪክ ምሁራን ይህን ጉዳይ ጊዜ ሰጥተው ጥልቀት ባለው ሁኔታ ቃኝተውታል፡፡ ዛሬ ያለው ክርስትና ትናንት ከነበረው ክርስትና አንፃር ሲታይ በእጅጉ እንደሚለይም ፅፈዋል፡፡ አንድ ደረጃ ወደላይ ከፍ ሲሉ ትናንት የነበው ክርስትና ዛሬ ካለው ክርስትና ጋር ሲታይ "ሆድ እና ጀርባ" ነው ሲሉ በአገርህ ብሂል አሞካሸተውታል፡፡
በ እርግጥ ትናንት በነበሩ የክስትና አማኞች እና ዛሬ ባሉ የክርስትና አማኞች መካከል ያለው" እየሱሳዊ አመለካከት" እንደ የ ጊዜው የተለያየ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የትናቱ ከዛሬ ሚለየው የትንቱን አመለካከት "አይኖች አላዩትም " የዛሬውን ግን "አይኖች አይተውታል"!!! ይህ ነው ልዩነቱ!!!! ይህን ስል እያጋነንኩ መስሎህ እንዳትሸወድ ፡፡
በቃ! ትናንት " እየሱስ አምላክ አደለም ሰው ነው " የሚሉ ክርስትያኖች እንደነበሩ ሁሉ በተገላቢጮሹ "አምላክ ነው ግን ሰው አደለም" የሚሉም ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ "እየሱስ ሰው እና አምላክ ተደባልቀው የሰጡት ባዮሎጂካል ውጤት ነው" የሚሉም ክርስትያኖች እንደነበሩ ሁሉ "የእየሱስ ማንነት ተደባልቆ የተፈጠረ ኬሚካላዊ ውህድ ሳይሆን ያ ማንነት አምላክም ሰውም የተሰኘ ሁለት ባህሪ ያንፀባረቀ ነው" ብለው ሚያምኑም ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ በተገላቢጦሹ ደግሞ "እየሱስ ካሉት 365 አማልክት አንዱ ነው " የሚሉ ክርስትያኖች እንደነበሩ ሁሉ "እየሱስ ሰውን ከጨካኙ የሙሴን አምላክ ለመታደግ የመጣ 2ተኛ አምላክ ነው፡፡" የሚሉም ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ "እየሱስ ተወልዷል ሞቷል " የሚሉ ክርስትያኖች እንደነበሩ ሁሉ "አልተወለደምም አልሞተምም የሚሉ ክርስትያኖች ነበሩ፡፡ "ብሉይ ኪዳን(Old Testament) ከክፉ መፅሀፍ ሲሆን የወረደውም ከክፉ አምላክ ነው" የሚሉ ክርስትያኖች እንደነበሩ ሁሉ "አምላክ ይህን አለም አልፈጠረም፡፡ እዚህ አለም ውስጥ በሚደረጉ ተግባራትም ውስጥ ጣልቃ አይገባም" የሚሉም ክርስትያኖች ነበሩ፡፡"(5) የለየለት አስተምህሮ እና ውዝግብ የተስተዋለበት ጊዜ ነበር ትናንት፡፡ በትናንቱ ክርስትና !!!
ይህን የትናንቱ ክርስትና ዛሬ ላይ ሆነህ በለበስከው የዛሬው ክርስትና መነፅር ስታየው "ክርስትና አይደሉም " ትል ይሆናል፡፡ አዲስ ኪዳንን መሰረት አርገህ ስታበቃም አዲስ ኪዳን እየሱስ ካሉት ብዙ አማላክት አንዱ እንዳልሆነ ይናገራል እንዲሁም የሙሴ አምላክ ጠላት እንዳልሆነ ያውጃል ወይም ከላይ በዝርዝር ያነሰኋቸው ነጥቦች በሙሉ ቃወማል ስትል ሰይፍ ትመዝ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል?
ሰይፍ እንድትመዝ ሰበብ የሆነው ዋና ምክንያት የሚሆነው… አንተ የ ዛሬ ክርስትያን በመሆነህ እንጂ ሌላ "ሂሳባዊ ስሌት የለውም "፡፡ ልክ እነዚሁ ትናንት የነበሩ ክርስትያኖችም "ሞትን ድል አድርገው" ቢነሱና በትናንቱ ክርስትና መነፅር የዛሬውን አለም ቢያዩ ከዛም አንተንም ያለውን አማኝንም በሙሉ " ክርስትያን አይደለህም "ቢሉ የሚገርም አይሆንም፡፡ ምክንያቱም "በትናነቶቹ ምእመናን" ወይም "በነሱ" እና በዛሬው ምእመን "ባንተ" መካከል ያለው እየሱሳዊ መራሽ ጉዞ" የፈለቀበት ምንጭ "ለየቅል" በመሆኑ ! አንተ" አዲስ ኪዳን" መሰረት አርገህ ለ እየሱስ ትርጉም ትሰጣለህ፡፡ እነሱ ደግሞ ልክ እንዳንተ አዲስ ኪዳን አይነት ሌላ "አዲስ ኪዳን " ስላለቸው ባላቸው ፅሁፎች ተመርኩዘው " የማርያምን ልጅ እየሱስ" ሌላ ያደርጉና ፡፡ እናም ባንተ እና በነሱ መሃል እጅግ ከፍተኛ እኛ ማስታረቅ የማንችለው የለየለት ልዩነት አለ፡፡ ምናልባት እየሱስ ዳግም ሲመጣ ያስታርቀው ይሆናል!!!!
የሆነ ሆኖ ትናንት እና ዛሬ አንድ አልነበሩም፡፡…. ይቀጥላል ክፍል ሁለት
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests