ምላሽ አልባው የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ምላሽ አልባው የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭት

Postby መርፊው » Fri Dec 06, 2013 7:01 pm

ምላሽ አልባ የመፅሀፍቅዱስ የእርስ በርስ ግጭቶች
ክፍል አንድበመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ በጣም በርካታ ቅራኔዎች መኖራቸውን ክርስትያን ያልሆኑት ብቻ ሳይሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮችም ሳይቀሩ እየተቀበሉ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት፤ በአንድአንድ የምእራቡ አለም ሚሽነሪዎች እንዲሁም በሚያስተዳድሯቸው ድህረገፆቻቸው ላይ የምንመለከተው ግን ከዚሁ በተቃራኒ ጠርዝ ላይ የሰፈሩ መልእክቶችን ነው፡፡‹‹አይደለም 50000፣ አይደለም 101… አንድም ግጭት ሆነ ቅራኔ በመፅሀፋችን ውስጥ አይገኝም›› የሚሉ ሰበካዎችን በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ፡፡በሀገራችንም የሚገኙ አንዳንድ ሰበኪያን የውጮቹን አባባል አንዲትም ፊደል ሳይቀንሱ ኮፒፔስት በማድረግ የነርሱን ሽለላ በመድገም ላይ ይገኛሉ፡፡ እውን እነርሱ እንደሚሉት አንድም ግጭት የለውም? በአላህ ፍቃድ በሚመጡት ሳምንታት እጅግ በርካታ ግጭቶችን ከመልስመልስ ጋር እናቀርባለን(ግጭቶቹን ማቅረብ ብቻሳይሆን፤ መልስ ብለው የሚያቀርቡት መከራከርያ ሀሳቦቻቸውንም ለአንባብያን በማስነበብ የማያዳግም የመልስመልስ ይሰጣቸዋል፤ ኢንሻአላህ!)


1.ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ የት ነበር?


በኢየሱስ ስቅላት ዙሪያ ከሚነሱ በርካታ ውዝግቦች መካከል አንዱን መዘን በማውጣት ነው ለዛሬ አሀዱ ብለን የምንጀምረው፡፡ ‹‹ኢየሱስ ስንት ሰዓት ላይ ተሰቀለ?›› ‹‹እንዲሁም ለስንት ሰዓታት ያህል መሰቀሉ ላይ ቆየ?›› የሚሉት ጥያቄዎች ዛሬም በክርስትናው አለም ውስጥ አቧራ በማጬስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ ንትርክ መንስኤዎች ተብለው ከሰፈሩት መካከል በመፅሀፉ ውስጥ የሚገኙ ጥቅስች አንዱ ከሌላው ጋር አለመጣጣማቸው እንደ ዋነኛ ምክንያትመጥቀስ ይቻላል፡፡ በተለይ በሶስቱ ወንጌላት(አግኖሰቲክ) እና በዮሀንስ ወንጌል መካከል ያሉት ቅራኔዎች እጅግ በጣም የተለጠጡ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ አራቱ ወንጌላት ስለ ጊዜው ምንይላሉ? እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡


የሉቃስ ወንጌል እና የማቴዎስ ወንጌል በምድር ላይ ከ6 ሰዓትእስከ 9 ሰዓት ድረስ ጨለማ ስለመሆኑ ከመዘገባቸው በቀር(ማቴ 27፡45፤ ሉቃ 23፡44)የጊዜውን ሁኔታ በጥልቀት አልፃፉም፡፡ ባይሆን ከማርቆስ ወንጌል ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ያቀረቡት ይመስላል፡፡ መቼም የንፅፅር ሀይማኖት ውይይቶች በ‹ይመስላል› አይሆንምና እስኪ መፅሀፉን ገልጠን እንመልከተው (ነገር በመረጃ ያምራል አይደል ሚባለው)፡፡ ማርቆስ 15፡25 እንደሚነግረን፤ ኢየሱስ መስቀሉ ላይ ሲወጣ ከጧቱ ሶስት ሰዓት እንደነበረ ነው፡፡ 33 ቁጥርም ላይ ሲደርስ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ምድርን ጨለማ እንደዋጣትይገልፃል፡፡ ይህም የማርቆስ ወንጌል ከሉቃስና ከማቴዎስ አቀራረብ ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ መሆኑን የሚያመላክትነው፤ የቅድሙን ግምታችንም ወደእውነታነት ይቀይርልናል መለት ነው፡፡ በመሆኑም ሶስቱም ወንጌላት ኢየሱስ ቢያንስ ለ6 ሰዓታት ያህል በመስቀሉ ላይ እንደቆየ፤ የተሰቀለውም ከጧቱ 3 ሰዓት እንደነበረ ይስማማሉማለት ነው፡፡
ዮሀንስ ስለ ስቅለቱ ሲተርክልን ኢየሱስ እኩለ ቀን(6 ሰዓት) ላይ ገና በፍርድ ሂደት ውስጥ እንደነበረ ነው(ዮሀ 19፡14)፡፡ ይህም ከሶስቱ ወንጌሎች አንፃር ሲታይ ለየትያለ ነው፡፡የፍርዱም ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ጎልጎታ ከሄደ በኋላ በዚያው ተሰቀለ፤ ሰባትም፣ ስምንትም ሰዓት ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ታድያ የቱን እንቀበል? ይህ ጥያቄ ነው ታድያ አሁንም በእንጥልጥል ምላሽ አጥቶ ለንትርክ ምንጭ የሆነው፡፡ ኦሬንታሊስቶች ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ያልቆፈሩት ጉድጓድ የለም፡፡ብቸኛ ማምለጫ መንገድ አድርገው የቆጠሩተም የዮሀንስን የግዜ አቆጣጠር መቀየር ነው፡፡ ‹‹3ቱ የእስራኤላውያንን የግዜአቆጣጠር የተጠቀሙ ሲሆን ዮሀንስ ደግሞ የሮማውያንን የጊዜ ቀመር ነው የተጠቀመው›› ሊሉን ይወዳሉ፤ በዚህም መሰረተአልባ መልስ ሲመፃደቁ ይስተዋላል (ለአብነትያክል(1))፡፡የሚገርመው ነገር ለዚህ መላምታቸው አንድም መረጃ ማቅረብ አይችሉም፤ በባዶ ሜ ዳ ከመጮህ በቀር፡፡


እስራኤላውያን ሰዓታትንየሚቆጥሩት የፀሃይን መግባት መሰረት አድርገው ሲሆን ሮማውያን ደግሞ እኩለ ሌሊትን በመመርኮዝ ነው፡፡ የእስራኤላውያን አቆጣጠር ከሞላ ጎደል ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚመሳሰል ሲሆን የሮማውያን ደግሞ ከአሁኑ የምእራባውያን አቆጣጠር ጋር የሚዛመድ ነው፡፡ታድያ ዮሀንስ የሮማውያንን አቆጣጠርተጠቅሟል ካልን ኢየሱስ በፍርድሸንጎ ውስጥ የነበረው ገና ከሌሊቱ 12 ሰዓትላይ እንደማለትነው፡፡ በእነርሱ ምልከታ መሰረት ጴጥሮስ ኢየሱስን የካደው ከሌሊቱ 12 ሰዓትበፊትነበር፤ ዶሮዋም የጮኸችው ከሌሊቱ 12 ሰዓትበፊትነበር.. ጲላጦስ ኢየሱስን በበርባንለመተካትየሞከረው ከሌሊቱ 12 ሰዓት በፊት..ዶሮዋ ከጮኸች በኋላ ነበር… ኢየሱስምየተገረፈው ከአስራ ሁለት ሰዓት በፊትነበር… ብቻ ምን አለፋን… ሌሊቱ ቀን ሆኖ ነበር ማለት ነው… ይህ ሁሉ ክስተቶች የተፈፀሙት ከሌሊቱ 12 ሰዓት በፊት ነበር..በሰውኛ ካየነው የመሆን እድሉ አስቸጋሪ ቢሆንም ፤ አይደለም ብሎ ግን በእርግጠኝነት ለመናገር ተጨማሪ ማጠናከርያ መረጃዎችን መፈለጉ አይቀሬ ነው፡፡

በመሆኑም ዮሀንስ የአይሁዶችን እንጂ የሮማውያንን አቆጣጠር ላለመጠቀሙ ፍንትው አድርገው ከሚያሳዩን ጥቅሶች መካከል ሁለቱን በምሳሌነት እናቅርብ፡፡


‹‹ ኢየሱስ መንገድ በመሄድ ደክሞ በጉድጓድ አጠገብ እንዲህም ተቀመጠ፤ ግዜውም ስድስት ሰዓትያህልነበር፡፡ ከሰማርያ አንዲት ሴት ውሃ ልትቀዳ መጣች..››(ዮሀ 4፡6-7)


ስድስት ሰዓት ተብሎ የተፃፈው በሮማውያን አቆጣጠር ነውየምንል ከሆነ፤ ከሌሊቱ(ጧቱ) 12 ሰዓትነበርማለትነው፡፡ታድያኢየሱስ ከመንገድደክሞ እረፍት የወሰደው ሌሊቱን ሲጓዝ ቆይቶ ነው? ይሄ በየትኛውም በኢየሱስ ህይወት ውስጥያልተስተዋለ ክስተትነው፡፡ ምናልባትአይሁዶችንፈርቶ ሲሸሽ ነው እንዳንልገናዮሀንስወንጌል መግቢያ ላይነውይህክስተት የተፈፀመው፡፡ ሴቶችስ በሌሊትለብቻቸው ውሀ ለመቅዳት ከቤታቸው ይወጣሉን? በፍፁም፡፡ ጥቅሱ የሚያሳየን ከሌሊቱ 12 ሰዓትመሆኑንሳይሆንእኩለቀን 6 ሰዓትእንደነበረነው፡፡ እረፍትየሚወሰደውምበዚሁወቅትነው፡፡ሆኖም ‹‹ቢሆንስ?ምን ችግር አለው›› በማለት 100 ፐርሰንት አልተዋጠልንም የሚሉ አይጠፉምና እስኪ በውድም ይሁን በግድ እንዲጋቱት አንድ እናክልላቸው፡፡


‹‹በዚያም ቀን በእርሱ(ኢየሱስ) ዘንድ ዋሉ፤ አስር ሰዓትያህል ነበር›› (ዮሀ 1፡40)
ለአንባብያን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ፤ ኦሬንታሊሰቶቹ በሚነግሩን ሁኔታ ይህን ጥቅስ ወደ እኛ ከቀየርነው ይህንን ይመስላል፡፡
‹‹በዚያም ቀን በእርሱ (ኢየሱስ) ዘንድ ዋሉ፤ አራት ሰዓት ያህልም ነበር››
የመጀመርያው ክፍል ዋሉ እያለን እንዴት ከጧቱ 4 ሰዓት ሊሆን ይችላል?ጉድበል! ማታ ነው ደግሞ እንዳንል አመሹ አላለን! ዋሉ ነው የሚለው! ከቀኑ አስር ሰዓት እንጂ 4 ሰዓት አልነበረም! የተጠቀመው የአይሁዳውያንን እንዳልነበር ያረጋግጥልናል፡፡ አራት ነጥብ! ምንም መፈናፈኛ የለም! ይህም ድምዳሜ በዮሀ 19፤14 መሰረት ኢየሱስ ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ መስቀል ላይ እንዳልነበረ መረዳት እንችላለን ማለት ነው፡፡ ታድያ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ኢየሱስ የት ነበር? መስቀል ላይ ወይስ የፍርድ ሸንጎ ውስጥ? መልሱን ለነፃ አእምሮ እተወዋለሁ!
በማር 15፡25 እና በ ዮሀ 19፡14 መካከል አንስታይንም ቢመጣ የማይፈታው ግጭቶችን እንመለከታለን፡፡ መቼም ግጭትን የሚያስተናግድን መፅሀፍ 100 ፐርሰንት የአምላክ ቃል ነው ለማለትአንደፍርም፤ ሊሆንምአይችልም፡፡ ታድያ ለምን መቶ በመቶ ግጭት አልባ የሆነን መፅሀፍ በጋራ አንፈልግም፡፡
በሚቀጥለው ክፍል እስከምንገናኝ ወቢላሂተውፊቅ! ሻሎም! ሰላም!
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby ጌታ » Fri Dec 06, 2013 9:25 pm

የራሳቸው ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳያዩ የሰው ጉድፍ ይታያቸዋል::

ቭላዲሚር ኢሊች ሌኒን
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ጌታ » Fri Dec 06, 2013 9:31 pm

የሌላው እምነት ስህተት መሆን በራሱ ያንተን ትክክል አያደርገውም:: ሌላው መሳሳቱን ከምትነግረኝ ይልቅ አንተ እንዴት ትክክል እንደሆንክ ብትነግረኝ ይሻላል::

የዋርካው ጌታ
ዲሴምበር 2014
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby መርፊው » Fri Dec 06, 2013 11:01 pm

እኛም እያልን ያለነው የሄኑ ነበር::ለዚህም ያደረሱንም የራሳቸውን ጉድፍ ትተው የሰውን ሲያቦኩና ስያጨማልቁ እኛም መርፊሆቹ የመልስ ምት ሰጠናቸው እንጅ ድሮም ምን አግብቶን ብሰው እምነት እያልን በአጭሩ እንገልጣለን
በነገራችን ላይ ስለ ሚዛናዊ አስተያየትህ ሳናደንቅህ አናልፍም
መርፊው ዘ_ነገደ የሁዳ
ከዴር ሱለጣን :idea:ጌታ wrote:የሌላው እምነት ስህተት መሆን በራሱ ያንተን ትክክል አያደርገውም:: ሌላው መሳሳቱን ከምትነግረኝ ይልቅ አንተ እንዴት ትክክል እንደሆንክ ብትነግረኝ ይሻላል::

የዋርካው ጌታ
ዲሴምበር 2014
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sat Dec 07, 2013 4:39 pm

^*^*^ ስለ መሰቀሉና ሞቶ ስለመነሳቱ የተፃፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እውነት ከሆኑ ለምን እርስ በርስ ይጋጫሉ?^*^*^

****ምንም እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሰቀሉ፤ ከደሙ ከኃጢያት ሊያነፃ እንደመጣ በአንደበቱ በግልጽ ያብራራበት አንድም ጥቅስ ባይኖርም እንዲሁም በቦታው ኖሮ የተመለከተ ማንም የአይን እማኝ የፃፈው ጥቅስ ባይኖርም በሰሚ ሰሚ የሆነውን የስቅለት እና የትንሳኤ ሁኔታ የፃፉ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው በተለይም ኢየሱስን በአካል አይቶት እንኳን አይቶት የማያውቀው ጳውሎስ ዘግቦታል፡፡ ጳውሎስ ኢየሱስን ክርስቶስን አይቶት አያውቅም የሰማውን ነው የጻፈው አብዛኛዎቹ ደቀመዛሙርቶቹም ይህንኑ ነው ያደረጉት ለምሳሌ ሀዋርያው ሉቃስ የሰማሁትን እንዳየሁ አድርጌ እጽፋለሁ ብሏል ይህ ታዲያ ትክክለኛ ሀይማኖታዊ አካሄድ ነውን?

***በመሆኑ ይህ ዘገባ የአይን እማኝ ባለመኖሩና መረጃ አልባ በመሆኑ፤ በሰሚ ሰሚ የተፃፈ በመሆኑ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ስቅለት የተነገሩ ትቅሶች እርስ በርስ ይጋጫሉ፤ እስቲ ለአብነት ያህል እነዚህን ጥቅሶች እንመልከት፡-

≠ የማርቆስ ወንጌል 15፡25 ‹‹ኢየሱስ ሲስሉት ጊዚው ‹‹ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት›› ነበር፡፡››

≠ ዮሐንስ ወንጌል 15፡25 ‹‹የፋሲካ ዝግጅት ነበር ጊዜውም ወደ ‹‹ስድስት ሰዓት›› ነበር በዚያን ጊዜ ጰላጦስ አይሁዳውያኑን ‹‹እነሁ ንጉሳቸው›› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ‹‹ወዲ ውሰደው ወዲያ ወስደህ ስቀለው›› እሉ ጮሁ፡፡

^^ ኢየሱስ ስንት ሰዓት ነው የተሰቀለው 3 ሰዓት ዌም 6 ሰዓት?

≠ ማቴዎስ ወንጌል 27፡17 ‹‹ከገዚው ግቢ ሲወጡ ‹‹ሰምኦን›› የተባለው የቀሬና አገር ሰው አገኙና የኢየሱስን መስቀል ‹‹እንዲሸከም አደረጉት››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 19፡17 ‹‹ከዚህ በኃላ ‹‹ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ›› የራስ ቅል ወደ ሚባል ስፍራ ወጣ››

^^ መስቀሉን ማን ተሸከመ ኢየሱስ ወይም ስምኦን?

≠ ማቴዎስ ወንጌል 28፡1 ‹‹ሰንበት ካለፈ በኃላ ‹‹መቅደላዊት ማርያም ፤ ሌላይቱ ማርያም ›› መቃብሩን ለማየት ሄዱ››

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡1-2 ‹‹ሰንበት ቀን ካለፈ በኃላ ‹‹መቅደላዊት ማርያም፤ የያዕቆብ እናት ማርያም፤ ስሎሜም›› ሆነው የኢየሱስን አስክሬን ለመቀባት ሽቶ ገዙ፡፡ እሁድ ጠዋት ልክ ፀሐይ ስትወጣ ወደ መቃብሩ ሄዱ፡፡››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 20፡1 ‹‹እሁድ ጠዋት በማለዳ እና ጎህ ሳይቀድ ‹‹መቅደላዊት ማርያም›› ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች፡፡››

^^ ወደ ኢየሱስ መቃብር የሄዱት እነማን ናቸው?

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡5 ‹‹ወደ መቃብሩም በገቡ ጊዜ ነጭ ‹‹ልብስ የለበሰ ጎልማሳ›› በስተቀኝ በኩል ተቀምጦ በማየታቸው ደነገጡ››

≠ የዮሐንስ ወንጌል 20፡12 ‹‹የኢየሱስም አስክሬን በነበረበት ስፍራ ‹‹ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላዕክት›› ንዱ በራስጌ አንዱ በግርጌ ተቀምጠው አየች››

^^ መቃብር ውስጥ የነበረው ማነው?‹‹ነጭ ልብስ ጎልማሳ ወይም ሁለት መላዕክት?

≠ የማርቆስ ወንጌል 16፡8 ‹‹ሴቶቹም በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ከመቃብር ወጥተው ሸሹ እጅግ ፈርተው ስለነበረ ‹‹ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም››

≠ የሉቃስ ወንጌል 24፡8-9 ‹‹ሴቶቹ የኢየሱስን ቃል አስታወሱ ከመቃብር ተመልሰው ‹‹ይህንን ሁላ ለአስራ አንዱና ለቀሩትም ነገሩዋቸው፡፡››

^^ ሴቶቹ ተናግረዋል ወይስ አልተናገሩም?

****ከጥቅሶቹ በግልጽ እንደምንረዳው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልም ሆነ ከሞት መነሳት ተፅፈዋል የተባሉት መረጃዎች እርስ በርሳቸው እንደሚቃረኑ ነው፡፡ እውን ስቅለቱ እውነት ቢሆን ለምን ጠንካራ መረጃ ጠፋለት? በመሰረቱ የተጋጩ ሀሳቦችን አምኖ መቀበል ልክ ነውን?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby ጌታ » Mon Dec 09, 2013 7:28 pm

መርፊው wrote: በነገራችን ላይ ስለ ሚዛናዊ አስተያየትህ ሳናደንቅህ አናልፍም
መርፊው ዘ_ነገደ የሁዳ
ከዴር ሱለጣን :idea:


ይመችህ ወንድማችን:: ጥበብ እንደንጉሱ ሰለሞን ትገለጥልህ! ሱሌማን እንዳለው

የጥበብ ሁለ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው
መፅሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ አንድ ቁጥር 7
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby መርፊው » Tue Dec 17, 2013 9:22 pm

በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› ውስጥ በነብያት ዙሪያ የተሰነዘሩ አስጸያፊ ሐሰቶች*^*^*

*** በኦሪት ዘፍጥረት 19:31-35 ) ውስጥ ሉጥን በተመለከተ አስጸያፊ መልእክቶች ሰፍረዋል፡፡ ሉጥ አስካሪ መጠጥ ጠጥተው መስከራቸው፣ ከዚያም ከሴት ልጃቸው ጋር መዘሞታቸው፣ እርሷም ማርገዟና ዝሪያቸው በርሷ በኩል መቀጠሉ ተጠቅሷል፡፡ እስኪ አስቡት! አላህ የሶዶምን ከተማ የገለበጠውና ሕዝቡን ያጠፋው የሶዶም ሕዝብ የኒህን ንጹህ ነብይ ቃል ባለመስማቱ፣ በርሳቸው እና በትምርታቸው በመሳለቁ ነበር፡፡ ወደ ንጽህና ያደረጉትን ጥሪ ባለመቀበሉ በጅምላ ቀጣው፡፡ የኢብራሂም የወንድም ልጅ የሆኑትን የሉጥን ንጽህና ለመመስከር ከጠፉ ከተሞች ቅሪቶች ውጭ ሌላ ምስክር ባይኖር እንኳ በቂ ምስክር አይደለምን? እንዲህ ዓይነት አስጸያፊ መልእክቶችን የያዘን መጽሐፍ መለኮታዊ ብለን ልንቀበለው እንችላለን?

*** ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 38 ላይ የየእቁብ ልጅ የሁዛ -ምን አልባትም ነብይ ሊሆን ይችላል- ከልጁ ሚስት ጋር ዝሙት መፈጸሙ ተጠቅሷል፡፡ የበኑ ኢስራኤል ነብያት ዝርያ ለምሳሌ (ዳውድና ሱለይማን) የተገኙት ከዚህ የዝሙት የዘር ግንድ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
ይህ ዘገባ ሐሰት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው ቅጥፈት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንደሚሉት፡- ‹‹ከአደም አንስቶ የርሳቸው የዘር ግንድ በጋብቻ ላይ ብቻ የተመሰረተ እና የተገኘ ነው፡፡›› (ደላኢሉ ኑቡዋ በይሐቂ 1/173-175)

በሌላ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነብያት የአንድ አባት ልጆች ናቸው፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም)

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አያት ቅድመ አያት ውስጥ አንድም የዝሙት ልጅ ከሌለ ይህ ባህሪ በሌሎች ነብያትም ላይ የሚሰራ ነው፡፡ እርሳቸው የኢብራሂም የልጅ ልጅ አይደሉምን? የሁዛም እንደዚሁ የኢብራሂም የልጅ ልጅ ነው፡፡ በነብያት ቤት ውስጥ ዝሙት ሊከሰት አይችልም፡፡

*** በመጽሐፈ ነገስት ምእራፍ 11፣ውስጥ ሱለይማን በእድሚያቸው መጨረሻ ላይ እንደካዱና ጣኦት ማምለክ እንደጀመሩ ይገልጻል፡፡ በዚህም ሆነ በመጭው ዓለም ታላቅ ደረጃ ለግሶ አላህ የመረጠው ነብይ ክህደት ይፍጽማል ተብሎ እንዴት ይታሰባል? ሱለይማን አላህን በጽኑ አምላኪና አመስጋኝ ነብይ እንደሆኑ በቁርአን ተጠቅሷል፡፡ ለነብይ ተገቢው ባህሪ ይህ አመስጋኝነት ነው፡፡

ቁርአን ዒሳን፡- ‹‹አላህ ወደ መርየም ያኖረው መንፈሱና ቃሉ›› ሲል ይገልጻቸዋል፡፡ (አል ኒሣእ 171)

ኢብራሂም የአላህ ምርጥ ወዳጅ፣(አልኒሣእ 125)

ሙሳ አላህ ያናገራቸው፣ ( አልኒሣእ 114) መሆናቸውንም ተናግሯል፡፡

የዳውድን ቤተሰብም፡- ‹‹የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ፣ አመስጋኞች ስትሆኑ ስሩ›› ሲል አናግሯቸዋል፡፡ (ሰበእ 13) አላህ ነብያቱን የሚገልጽባቸው ባህሪያት እነዚህ ናቸው፡፡

*** ብሉይ ኪዳን ስለ ነቢዩላህ ዳውድ ሲተርክ አርያ የተባለውን ሰው ሚስት እንደተመኙና ሆነ ብለው እርሱን በማስገደል ሚስቱን እንደቀሙት ይተርካል፡፡ ሳሙኤል 2ኛ 11፡2-4)

ይህ እኩይ ባህሪ ለነቢይ ቀርቶ ለተራ ሰው፣ በእውን ቀርቶ በሕልም እንኳ የሚያስጸይፍ ነው፡፡ አላህ ዳውድን በተመለከተ ‹‹ምን ያምር አገልጋይ፡፡ እርሱ ወደ አምላኩ ተመላሽ ነው፡፡›› ብሏል፡፡ (ሱረቱ ሷድ 30)

*^*^* የነብያትን ስም እንዲህ የሚያጠፋና የሚያረክስ መጽሐፍ እንዴት ከአላህ የተገኘ ሊሆን ይችላል? ይህ ታሪክ ይከሰታል ብሎ ማሰብ የነብይነትን ደረጃ አለማወቅ ነው፡፡ ነቢ ዳውድ አላህን አዘውትረው የሚያመልኩና አልቃሽ ነብይ ነበሩ፡፡ ከርሳቸው ጋር የተቀመጡ ሁሉ የርሳቸው ለቅሶ ተጋብቶበት ያለቅሳል፡፡ ወደ አላህ በንስሐ መመለስን ያበዛሉ፡፡ ፊታቸውን ከአምላካቸው ለቅጽበት እንኳ አላዞሩም፡፡
የሕይወታቸው ዋነኛ መርህ ዑቡዲያ ነበር፡፡ አላህን ዘወትር ማምለክ፡፡(ሷድ 17)

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የነቢይ ዳውድን ኢባዳ ሲያወድሱ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ከአላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ሶላት የዳውድ ሶላት ነው፡፡ ከላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ጾም የዳውድ ጾም ነው፡፡ የሌሊቱን ግማሽ ይተኙና ሲሶውን ይቆማሉ፡፡ 1/6ኛውንም ይተኛሉ፡፡ 1 ቀን ይጾማሉ፣ አንድ ቀን ያፈጥራሉ፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም)

ነቢይ ዳውድ ንጉስ ነበሩ፡፡ የመንግስት ሃብት በአጠቃላይ በእርሳቸው እጅ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን ያን ሃብትና ንብረት ለግላቸው ለመጠቀም፣ ሌላው ቀርቶ በርሱ አንዲት ቁራሽ ምግብ እንኳን ለመግዛት ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚቀልቡት የእጅ ሙያቸውን ተጠቅመው በሚያገኙት የግል ገቢ ነበር፡፡ አንዲት ቁራሽ እንኳ ያለ አግባብ ለመውሰድ ባልፈቀዱት፣ የሕይወት መርሃቸው እና ልዩ ባህሪያቸው አላህን ማገልገል በሆኑት በዚህ ነብይ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ያንን አጸያፊ ቅጥፈት ይደርትባቸዋል፡፡ እጅግ ብጹእ እና ንጹህ ከመሆናቸው አኳያ ይህ ቅጥፈት በተግባር ቀርቶ በሐሳብ እንኳ ለቅጽበት ሊታወሳቸው ፈጽሞ የሚችል አይደለም፡፡

**** በብሉይ ኪዳን (ዘፍጥረት 32፡22-28) ውስጥ አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ሌላም አስገራሚ ነገር እናገኛለን፡፡ እርሱም እስራኤል (ያእቁብ) ከአምላክ ጋር ታግለው ማሸነፋቸው ነው፡፡ እናም የምእራቡ አለም ቁሳዊ ፍልስፍና ወሰንን ሁሉ ጥሶ አምላክን የሰው ቅርጽ በማስያዝ ከነብዩ ጋር እንዲታገል አድርጎታል፡፡ ሐምዛ ከመስለማቸው በፊት ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የተናገሩት ተከታዩ ቃል ለነዚህ ወገኖች ጥሩ ምላሽ ይዟል፡-

‹‹የወንድሜ ልጅ ሙሐመድ ወይ፣ ሌሊት በበረሃ በምዘዋወር ጊዜ አላህ በግንብ ውስጥ ተወስኖ ከመቀመጥ በላይ መሆኑን እረዳለሁ፡፡››
ስለዚህም ክርስትያኖችና አይሁዶች የአምላክ ቃል ነው ብለው የሚያስቡት መጽሐፍ በዘመነ መሐይምነት ወደነበሩት ሐምዛ የሕሊና ደረጃ እንኳ ከፍ ሊል አልቻለም፡፡ ታዲያ በእንዲህ አይነት ብክለቶች የተሞላውን ይህን መጽሐፍ የአምላክ ቃል ነው ብሎ እንዴት ማሰብ ይቻላል?

ይህ መጽሐፍ ስለ ነቢያት የሚናገረው ሊታመን ይችላልን? በፍጹም አይታመንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አላህንና ነቢያቱን አስመልክቶ በቅጥፈትና በጥመት የተሞላ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን የጥመት ምንጮች ናቸው፡፡

*^* ቁርአን በነብያት ዙሪያ ለተደረቱ ቅጥፈቶች ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ምክንያቱም ነብያትን ሙሉ በሙሉ እንድንከተል ያዘናልና፡፡ በቁርአን ትምህርት መሠረት ነብያት ስብእናቸው የተሟላ፣ የቅን ጎዳና መሪዎች፣ በሁሉም ጉዳዮች ሊከተሏቸው እና ሊታዘዟቸው የሚገቡ ታላላቅ መምህራን ናቸው፡፡ ሁሉም ነብያት የአላህን ውዴታ የሚያየንጸባርቁልን መስታወቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ መስታወቶች ላይ አንዲት እንኳ የአቧራ ቅንጣት አይገኝም፡፡ የተከበረው ቁርአን ይህንን እውነታ እጅግ ውብና ግልጽ በሆነ መልኩ አስቀምጦታል፡፡
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ የአንዳንድ ነብያትን ድርጊቶች በስህተት በመረዳት ነብያት ሐጢአት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ የሚያስቡ ወገኖችን እናገኛለን፡፡ የስህተታቸው ምንጭ መልእክቶችን በወጉ አለረዳት ሲሆን ጥቂት ቢያስተነትኑ የአስተሳሰባቸውን ግድፈት መረዳትና እንደብዙሐን ዓሊሞች ለነብያት ተገቢውን ክብር መስጠት በቻሉ ነበር፡፡

ምንጭ፡- ዘላለማዊ ብርሃን
በሙሐመድ ፈትሁላህ ጉለን
ትርጉም፡ በኡስታዝ ሐሰን ታጁ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 3 guests

cron