እውን ቁረአን ይጋጨል ?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

እውን ቁረአን ይጋጨል ?

Postby መርፊው » Sun Dec 08, 2013 10:32 am

ጥያቄ ቁርአን ይጋጫል ወይ?

ቁርአን የአላህ ቃል አይደለም ፣ ቁርአን እርስ በእርሱ ይጋጫል፣ ቁርአን ታሪክን አሳስቷል፣ ቁርአን ሳይንስን ተቃርኗል፣ ቁርአን መለኮታዊ አይደለም፣ ቁርአን ምንጩ ከኛ ነው.. ወዘተረፈኘ ሲሉ ሚሽነሪዎች አንድም በፌስቡክ ሁለትም በፅሁፍ ሶስትም በንግግር ደግመው ደጋግመው እንደፓሮት ቀንና ማታ ይነግሩሃል .. ቁርአን እርስ በርሱ ይጋጫል ….ተወውና ወደ ኛ ና ሲሉ ረፍት ይነሱሃል አንግዲህ እንዲህ ኡማውን በሆነ ባልሆነ ረፍት በመንሳት ጭንቅላትህም ላይ አግባብ ያልሆነን folder ከፍተው ሲያበቁ ያንተኑ አእምሮ ማወክ ከጀመሩም ሰነባብተዋል የ ምን መሰነባበት ብቻ መእተ አመታትንም አስቆጥረዋል፡፡ ይህ ሁሉ እስኪሰለችህ ሚነግሩህ ግን ወደው እንዳይመስለህ እውቀት የለህም ሲሉ አንተኑኑ ስለገመቱህም ስለተመኑም በመሆኑ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የነሱ ስውር ዳባ አያሳስብህ አእምሮህም ውስጥም ቦታ አትስጠው ቀላል እና ተራ አድርገህ እየው ይህን እያልኩህ ያለሁት ለምን ይመስልሀል? እንዲህ የምልህ ቢያስቡም ቢያሰላስሉም ፣ ቢወጡም ቢወርዱም፣ ቢዘሉም ቢፈርጡም . …. ለሚያነሱት ጥያቄ ሁሉ መልስ እንዳለው እንድትገነዘብልኝ ስለምፈልግ ነው(ማ አንዘለላሁ ዳአን ኢላ አንዘለለሁ ሺፋእ) ፡፡ የሆነ ሆኖ ምክሬን እዚህ ጋር ያዝ ላድርግልህና ቁርአን ተጋጭቷል ሲሉ ወደ ሚጠይቋቸው constant ጥያቄዎች እና ወደ ማያዳግመው መልሳቸው ልለፍ መሰለኝ……..
ጥያቄ 1. አማላጅ ማነው? አላህ ብቻ (32፡4፣2፡48፣2፡122-3) ሌሎችም አሉ (2፡255)
ይህ ከላይ የተመለከትከውም ያነበብከውም ጥያቄ እንደ ፓሮት ከሚደገሙ ጥያቄዎች ውስጥ መሆኑ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ግጭት አለው ወይስ የለውም ከማለትህ እና ከማጠቃለልህ በፊት ግን መቅደም ያለበት ነገር መኖሩ ልንገርህ ፡፡ እሱም ምን መሰለህ ሐቢቢ….. ሙሉ አንቀፁን እስከ ሙሉ ድምቀቱ እና ውበቱ ማንበብ ሲደመር ማስተንተን ካልቻልክም መጠየቅ፡፡ ይህንን ካላረክ ግን ከተሳሳተ መነሻ ተነስተህ ፍፃሜህም የተሳሳተ መድረሻ ላይ ስለመሆኑ ለማወቅ እንግዲህ ነብይ አሊያም ረሱል መሆን አያስፈልግም እልሀለው….. ለዛሬ ይህን ካልኩህ ጥያቄ ወደ ቀረበባቸው የተአምራዊው ቁርአን አንቀፆች ልለፍ
አማላጅ አላህ ብቻ ነው ይላል ተብሎ በክስ መዝገብ ቁጥር አንድ ላይ ክስ ከቀረባቸው የቁርአን አንቀፆች ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ የቀረበው የ አልሰጀዳህ ምእራፍ ሲሆን ፡፡ እንዲህም አንብብልኝ
““…ከርሱ ሌላ ረዳትም አማላጅም ማንም የላችሁም አትገሰፁምን?”(32፡4)
ይህን አንቀፅ ያጠናክልኛልሲ ሉ ሚሽነሪዎች በክስ መዝገቡ ላይ ካቀረቧቸው አንቀፆች ውስጥ በትኩሱ ሲቀርብ
﴿وَلاَ يُقْبَلُ مِنْهَا شَفَـعَةٌ﴾
(ከሷ የሆነ ምልጃ ተቀባይነት በሌለው ጊዜ)(2፡48) ይሀው መልእክትን አራሱ ቃል በቃል አል በቅራህ 2፡122-3 ተደግሟል ሚሽነሪዎች ከፍተው ስላላዩት ቢን እንጂ በቁርአን ውስጥ መሰል አንቀፆች በቃኝ እስክትል መጠቀሱን(1) ለማወቅ ቁርአንን ያፈዘ እንዲሁም ያነበበ ከኔ የተጨመረ ምስክር ከመሆን ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖረውም ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያሉ ክስ ቁጥር ሁለት ላይ ይደረሱና አሁንም ይጠይቃሉ…….
በክስ መዝገብ ቁጥር 2 ላይ ክስ የቀረበበት የቁርአን አንቀፅ ደግሞ እንዲህ አንብብልኝ፡፡
“አላህ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም ሕያው
ራሱን ቻይ ነው ማንገላጀትም እንቅልፍም
አትይዘውም በሰማያት ውስጥና በምድር
ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው ያ እርሱ
ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጂ የሚያማልድ
ማነው? (2:255)”
ይህ አንቀፅ እንዲሁም የተለያዩ ሀዲሶች ደግሞ ነብያት አማላጅ እንደሚሆኑ ስለሚገልፁ ሀቁ የቱነው አላህ ብቻ ወይስ ሌሎች?
ሚሽነሪዎች ቁርአናችሁ ይጋጫል እያሉን ነው ፡፡ ቁርአን በበኩሉ ግጭት ሚባል ብትፈልግ ብኝ ድካምን እንጂ ሌላን አታተርፍም ሲል በግልፅ ይነግረናል(2)፡፡ እውነቱ የቱ ይሆን? እውነቱን ለማወቅ ብቻ ንባብህን ቀጥል
ቁርአን ይጋጫል ለሚሉ
ቁርአን ይጋጫል ከሚሉ ጠያቂዎች አንዱ ከሆንክ የጥያቄው መልስ የሆነውን ዋና መድሃኒት ከመውሰድህ በፊት መድሃኒቱ ከሰውነትህ ጋር ይዋሃድ ያስችለው ዘንድ ግልጋሎት ይሰጥ ዘንድ መወሰድ ያለባቸው ተጨማሪ መድሀኒቶችን መውሰድ የግድ ሊልህ ነው ወይም (must) ሊሆንብህ ነው ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ምን ይሆኑ ንገረን እስኪ? ካልክ አይቀር ግን ወደ መልሱ ልለፍ
ብዙን ጊዜ እናንተ ሚሽነሪዎች ምትስቱት ነጥብ ቢኖር የቁርአን ትንታኔ ነው፡፡ ቁርአንን እንደ መፅሀፍ ቅዱስ በዘፈቀደ አሊያም ከልብወለድ ለመተንተን አደገኛ ሙከራ ታደርጋላችሁ በዚህም ምክንያት ከተሳሳተ መነሻ የተሳሳተ መድረሻ ሆናችሁ እርፍ ትላላችሁ ፡፡ በዘፈቀደ የተደረገ የቁርአን ትንታኔ ተቀባይነት የለወም ይሉናል ታላቁ ሙጀዲድ የኡማው አንበሳ ሼይሀል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ምን ነበር ያሉት ኢማማችን?
“ቁርአንን ለመተንተን ትክክለኛ ከሆኑ መንገዶች የመጀመሪያው ቁርአንን በቁርአን መተንተን ሲሆን ቀጥሎም ቁርአንን በሀዲስ ፣ ቁርአንን በሰሀቦች ነግግር እና ቁርአንን በሰለፎች ንግግር መተንንተን ነው፡፡ ቁርአንን በዘፈቀደ ከልብወለድ መተንንተን ግን ክልክል ነው”(3)
እያልኩህ ያለሁት ይህን ነው ፡፡ ቁርአን መተንተን የሚቻለው አንድም ከቁርአን ሁለትም ከሀዲስ ሶስትም ከሰሃቦች እንደሆነ እኔ ብቻ ሳልሆን ምልህ አላህ በቁርአኑ(4) ብሎሃል ነብዩም በሃዲሳቸው ነግረውሃል(5) የኡማው አሊሞችም ብለዋል በዚህ መንገድ ካልተነተንከው የ አንቀፁን አሰባበ ኑዙል ካላወቅከው ይጋጭብሃል ለ አንተ ብቻ ሳሆን ለ መሰልህ ሁሉ ካንተው ጎን ይደመራሉ፡፡
ስለሆነም አንቀፁ አስባበ ኑዙል እና ትንታኔው ምንድነው ብለህ ካሁን በኋላ አንድ እርምጃ መራመድ ከሌሎች ትንሽ ለየት ማለት እንዳለብህ በመንገር እኔም ወደ መልሱ በር ዘው ብዬ ልለፍ?
መልስ አንድ፡- ለክስ መዝገብ ቁጥር አንድ እና ሁለት
““…ከርሱ ሌላ ረዳትም አማላጅም(መቃረቢያ) ማንም የላችሁም አትገሰፁምን?”(32፡4) ይህ አንቀፅ አበክሮ ሚነግርህ ከአላህ ሌላ ረዳትም ሆነ አማላጅ የላቸውም ሲል ነው ፡፡ በዚህን ጊዜ መጠየቅ ያለብህ መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነሱም አንቀፁ ለማን ነው የወረደው? እንዲሁም ምን ለማለት ተፈለጎ ነው? የሚሉት ሲሆኑ ይህን ጥያቄ እኔን ከጠየቅከኝ አይቀር በሚከተለው መልኩ እመልስልሀለው
1. አንቀፁ የመኪይ አንቀፅ ሲሆን የወረደውም ለጣኦታውያን ነው፡፡ ጣኦታውያኑ አላህን ብቻ ተገዙ ለምን ጣኦታት ትገዛላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ወደ አላህ እንዲያቃርቡን ነው እርዳታንም እንዲያጎናፅ ፉን ነው ሲሉ መልስ ይሰጡ ነበር ይህን ጉዳይ አስመልክቶ አላህ በብዙ ቦታዎች ላይ ነግሮናል
( እነዚህ(ጣኦታት) ወደ አላህ አማላጆች ናቸው ይላሉ…)(10፡18) ይህን ፅንሰ ሀሳብ በመረጃ ማጠናከር ከተፈለገ የሲራ መፅሃፎችን መመልከት ተገቢ ይሆናል በመካ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣኦት አምልኮ እንዲጀመር የአንበሳውን ድርሻ የያዘው አምር ኢብን ሉሀይ (6) ጣኦታትን ከሶሪያ እንዲያመጣ በበዋነኝነት የሚጠቀሰው ምክንያት ስለ ጣኦታት የጠየቀው ጥያቄ ነበር፡፡ እነዚህን ጣኦታት ለምን ትገዛላቹህ ብሎ በጠየቀ ጊዜ የሰጡት ዋነኛ ምላሽ በችግር ጊዜ ይረዱናል የሚል ሲሆን(7) በነብዩም ጊዜ ጣኦታውያኑ ለምን ከ አላህ ውጪ ጣኦታትን ትገዛላችሁ ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት ምላሽ ከ አሚራቸው ያገኙትን ቃል በቃል እና ተመሳሳይ መሆኑ ነው ፡፡ ይህም መልስ እንዲረዱን እንዲሁም ወደ አላህ እንዲያቃርቡን(እንዲያማልዱን) ብለው ነበር በዚህም ጊዜ አላህ ይህንን የነሱን ምላሽ በመቃወም ከ አላህ ውጪ ረዳትም መቃረቢያም የላችሁም የሚልለው አንቀፅ ወረደ፡፡ ስለ ሆነም በአላህ ካልሆነ በቀር ወደሱ የሚደረግ መቃረቢያ የለም ብሎ ነው ሚነግርህ የቁርአኑ አንቀፅ ፡፡ ነብያትስ ካልክ? አንቢያዎች ሆኖ ረሱሎች ከ አላህ የሆኑ መቃረቢያ ናቸው፡፡ አሁን ሳይሆን የውመል ቂያማ ምክንያቱም ከ አላህ ፍቃድ አግኝተዋል ይህ ሚሆነው ግን ለምእመናን ብቻ ና ብቻ ነው፡፡ በጥያቄ የቀረበውን የ አል ሰጀዳህ ምእራፍ አል ሀፊዝ ኢስማኢል ኢብኑ ከሲር በተነተነበት ሂደቱ የሚከተለውን ብሏል

“ማንም ወደ አላህ አያቃርብም ከአላህ ፍቃድ ያለው ሲቀር”(8) በመሆኑም ከ አልበቅራህ 2፡255 ጋር ብትዘልም ብትፈርጥም አይጋጭም ማለት ነው፡፡ ምክንያትም በ አላህ ፍቃድ የተደረገ መማለድ ከአላህ የሆነ መማለድ ነው፡፡
2. አንቀፁ ሚጀምረው ከርሱ ሌላ ረዳት የለም ሲል ነው፡፡ ይህን አንቀፅ ብቻ ይዘህ ከ ሱራ አንፋል ስምንተኛው ምእራፍ ጋር ይጋጫል ምክንያቱም ምእመናንን ጦርነት(9) ላይ መላእካን ረድተዋቸዋል ብትል ” የሰው መሳቂያ እና መሳለቂያ መሆንን ቢሆን እንጂ ሌላን አታተርፍም፡፡ ምክንያቱም መላእካን ምእመናንን እንዲረዱ ፍቃድ የሰጣቸው አላህ ነው፡፡ መላእካንም ከአላህ የሆኑ ረጂዎች ናቸው፡፡ አላህ በመላኢካን አማካኝነት ምእመናን ረድቷል ስለለሆነም እርዳታ ከአላህ ብቻ ሆናል ማለት ነው፡፡ ሌላም ምሳሌ ካስፈለገህ ታመህ ወደህክምና ብትሄድና ዶክተሩ መዳኒት ሰጥቶህ ብትፈወስ ማነ የፈወሰህ ብትባል መድሃኒቱ ወይም ዶክተሩ አሊያም ደግሞ ፈጣሪ ልትል ትችል ይሆናል፡፡ ከሶስቱ አንዱን አልክ ማለት ግን ተሳሳትክ ወይም ተጋጨህ ማለት አይደለም በፈጣሪ ፍቃድ ባይሆን መፈወስ ባልቻልክ ነበር፡፡ ፈጣሪ ፈወሰኝ ብትል አልተሳሳትክም ለምን የመፈወስ ስልጣን ያለው ፈጣሪ ብቻና ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ደ/ሩን እና መድሀኒቱን ግን ሰበብ አረገልህ፡፡እናም በፈለገው መልኩ ፈወሰህ፡፡ በተመሳሳይ ሎጂክ ከሱ ውጪ አማላጅ ወይም መቃረቢያ የለም ሲልህ የምልጃው ባለቤት አላህ ሲሆን ይህን ግን እሱ በፈቀደው መልኩ አድርጎታል ፡፡ ለሩሱሎች የውሙል ቂያማ ፈቅዶላቸዋል ይሀውም ለምእመናን ብቻ(10) ሲሆን እዚህ ጋር የአማላጅነት ስልጣን ያለው እና ባለቤቱ አላህ ሲሆን ልክ ምእመናንን በጦርነቱ ላይ መመላኢካ እንደረዳቸው ሁሉ ምእመናንንም በ ረሱሎች አማካኝነት ወደሱ አቃርቧቸዋል ወይም አማልዷቸዋል ፡፡ ከአላህ ውጪ አማላጅ የለም ሲልህ እሱ ከፈቀደው መንገድ ውጪ ምልጃ የለም ስለዚህም ጣኦታት አያማልዱም ለማለት መሆኑን ይሰመርት፡፡ አሁንም ከ አልበቅራ አንቀፅ ጋር በምንም መልኩ አንቀፁ አይጋጭም ማለት ነው፡፡
3. አረበኛ ለሚረዳ ሰው ጉዳዩ ግልፅ ነው ፡፡ በቋንቋው መሰረት ﴿مَا لَكُمْ مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلاَ شَفِيعٍ﴾ ሲል ከሱ ከፈቀደለት ውጪ የሆነ ረዳትም አማላጀም ረዳትም የለም ማለቱ ነው ፡፡ ተፍሲር ኢብኑ ከሲርን ተመልከት፡፡ (ቁርአን በአረበኛ ቋንቋ መሰረት ትርጋሜ እንሚሰጠው ኡማው ተስማምቶበታል)(11)
4. አንዳንድ ሚሽነሪዎች ጭራሽ ምልጃ ሚባለው ነገር የውል ቂያማ አይሰራም ማለት ነው ይሉናል፡፡ ይህም የሆነበት ተጨባች ምክንያት ቁርአን 2፡48 እንዲሁም 2፡121-123 ላይ የማንም ምልጃ ተቀባይነት እንደማያገኝ ይገልፃል፡፡ ይህን ጥያቄ አስመልኩቶ ሼይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ የሚተለውን ብሏል፡
“አንቀፁ እንደሚነግረን የማንም ምልጃከ አላህ ጋር ላጋሩ ሰዎች በሚሉ አይሰራም ….. ”(12) ኢብኑ ተይሚያህ ምልጃ በተነተኑበት ሂደታቸው “ በአላህ ካጋራህ የነብያት ምልጃ ከእሳት አይታደግህም ”( 13) ኢብኑ ከሲርም ኢብን ጀሪር በተፍሲራቸው ከሀዲያንን መሆኑን ጠቅሰዋል(14) በመሆኑም በአላህ ያጋራ ማንኛውም አካል አማላጅ የለውም ካለውም ምልጃው ተቀባይነት ያጣል ማለት ነው ፡፡ ይህንንም የሚያጠናክሩተመሳሳይ የቁርአን አንቀፆች እጅግ የበዙ ናቸው(15) በመሆኑም ከአንቀፁ ጋር ግጭት ሊኖረው ወፍ የለም…..
5. አንዳንድ የቢድአ አራማጆችም በዚህ ምድር ላይ ሳለን በሞተ አካል ምልጃ ይፈቀዳል ለዚህም መረጃ የሚሆነው የ አደም ሀዲስ ሲሆን “ አደም እንዳትበለ የተባለውን ፍሬ በበላ ጊዜ ፡፡ አላህ ለምን በላህ ሲለው አላህ ሆይ በሙሀመድ ይሁንብህ ይቅር በለኝ ብሎ ስለለመነው አላህ ማረው የሚል ሀዲስ አለ ”(16) በመሆኑም አላህ ይቅር አለው ይሉናል ፡፡ በእርግጥ ሀዲስ አለ ግን ሀዲሱ ግን ቅጥፈት ነው ፡፡ የሀዲስ ሊቃውንት እንደሚሉን ከሆነ ሀዲሱ የሚሽከረከረው አብዱረህማን ኢብን ዘይድ ኢብን አስለም በሚባል ሰው ላይ ሲሆን ሰውየው እጅግ ደካማ ነው(ዘገባው ውድቅ ነው) የሀዲስ ሊቃውን ጭንቅላት አል ሃፊዝ አዝ ዘሀቢ ሀዲሱን በተቹበት ሂደታቸው “የሀዲሱ ኢስናድ ላይ አብደላህ ኢብን ሙስሊም አል ፊር የሚባል ሰው መኖሩን ጠቅሰው ሲያበቁ ይህ ሰው እውቅ ውሸታም መሆኑን አያይዘው ነግረውናል ኢብኑ ሂባንም በበኩላቸው ይህ ሰው ሀዲስ በመቅጠፍና ከኢማሙ ማሊክ ሰማሁ ብሎ በመዋሸት እንደሚታወቅ ከ አዛህቢ የተደመሩ ምስክር ሆነዋል፡፡ ስለሆነም ሀዲሱ ውድቅ ና ቅጥፈት ነው ለመረጃም አይበቃም፡፡ ኦኬ!
6. በመሆኑም በቁርአን የተፈቀደ እና የተከለከለ የምልጃ አይነት አለ የተፈቀደው በአላህ በኩል(አላህ በፈቀደው) ሲሆን የተከለከለው ከአላህ ውጪ የሆነው ነው ምን ነበር ያልከው ኢብኑ ተይምያህ “ ቁርአን የተቃወመው ምልጃ ከከሃዲያን በአላህ ካጋሩ በኩል የሚመጣወን ብቻ ነው”(17)
በመጨረሻም ሳልነግርህ የማላልፈው ቁርአን ሳይሆን የተጋጨው ጭንቅላትህ መሆኑ ነው ፡፡ እናም ቁርአን ውስጥ ግጭት እፈልጋለው ካልክ ድካም እንጀ ምንም አታተርፍም የምልህ ካሁን በኋላ ላለው እንድታስብበት ነው፡፡


መርፊው ዘ- ነገደ የሁዳ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Wed Dec 11, 2013 8:23 pm

እውን ቁርአን ይጋጫል ወይ ክፍል-2


ሚሽነሪዎች ቁርአን ውስጥ ግጭት፣ ፍጅት አለ ሲሉ ሙስሊሞች ደግሞ “ወፍ!!”…. ግጭት ቀርቶ “ግ” እንኳ የለም!! ኢንጅሩ!!! የሚል አፀፋዊ ምላሽ ይሰጣሉ ፡፡ በመሆኑም እናንተ ሚሽነሪዎች ልታዩት የቻላችሁት እኛ ሙስሊሞች ግን እንኳ በ አይናችን ቀርቶ አለም ላይ ረቀቀ … በተባለው አጉሊ መነፅር ማየት የተሳነን ግጭት የቱ ይሆን ? ስንል መጠየቅ እንግዲህ የሙስሊምነታችን መለያ ነው፡፡
እናም እንጠቃለን !!! Which verses of the Quran contradict each other? እንላለን ፡፡ ቢሆንም ግን እንዳልኩህ ሚሽነሪዎች ቁርአን ውስጥ ግጭት አለ ሲሉ ስትሰማ ሁልጊዜም ቢሆን ሲባል የሰሙት መሆኑን አስምረበት……
በክስ መዝገብ ቁጥር 2 ካሰፈሯቸው የታላቁ ቁርአን አንቀፆች ውስጥ የሚከተሉት እንደወረዱ ይቀርባሉ፡፡
“ጥያቄ 2. መጀመሪያ የተፈጠረው መሬት ወይስ ሰማያት አል በቀራህ 2፡29 መሬት ሲል አን ናዚያት 79፡27-30 ሰማያት ”
ይህ ከላይ ያነበብከው ሚሽነሪዎች ደግመው ደጋግመው በዌብ ሳይታቸው የነገሩንን ነው እንደወረደ ወደ አማርኛ ብቻ ተተርጉሞ አንተው ያነበብከው ፡፡ ቢሆንም ግን መጠየቅህ አግባብ ነው፡፡ ይህን አንቀፅ እውን ይጋጫል ወይ? በማለትህም ብትወደስ እንጂ አትወቀስም፡፡
ወደ ርእሴ ስመልስህ ለሚሽነሪዎች እራሱን ብርት ጥርት አርጎ ያሳየ ከኛ ደግሞ ስውር እውር ሲል ህልም እልም ያለውን ግጭትን እንግዲህ ባትሪም ይዘን እንፈልገዋለን እንጂ አንላቀቅም ግን ከዛ በፊት እቺን ግጥም…….
ታላቁ ተአምር የአለም መመሪያ
የሰውን ዘር ሁሉ ዘላለም ሚመራ
ሰላም ለፈለገ ሰላምን የሚሰጥ
አውቀት ለፈለገ በ እውቀት የሚያጠምቅ
በውስጡ ተአምር ዘላለም ያዘለ
ግጭት ሚባል ነገር በውስጡ የሌለ
አእምሮን ሚጋብዝ ለጥልቅ ምርምር
ንገሩኝ እንግዲህ ይህን ተአምር?(1)

1. በጥያቄ ላይ ያሉ አንቀፆች እንደወረዱ?

“هُوَ الَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى الاٌّرْضِ جَمِيعاً ثُمَّ اسْتَوَى إِلَى السَّمَآءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَـوَاتٍ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
“እርሱ ያ በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ለ እናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው” (2፡29)
ሲሆን ሁለተኛው በክስ መዝገብ ቁጥር 2. ሁለተኛው መስመር ላይ የሰፈረው ደግሞ የ ሚከተለውን ይመስላል
“ أَءَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقاً أَمِ السَّمَآءُ بَنَـهَا - رَفَعَ سَمْكَهَا فَسَوَّاهَا - وَأَغْطَشَ لَيْلَهَا وَأَخْرَجَ ضُحَـهَا - وَالاٌّرْضَ بَعْدَ ذَلِكَ دَحَـهَا ”
“ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይስ ሰማይ? (አላህ ገነባት፡፡ ከፍታዋን አጓነ ፣ አስተካከላትም፣ ሌሊቷንም አጨለመ ቀኗንም ገለፀ፡፡ ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡”(79፡27-30)

ተመልከት እንዚህን ሁለት አንቀፆች ናቸው እንግዲህ ተጋጭተዋል ሲሉ የሚድያ ፍጆታ ያረጓቸው፡፡ የመጀመሪያው አንቀፅ መሬት ቀድማ ተፈጥራለች ሲለን ሁለተኛው አንቀፅ በበኩሉ ሰማይ ቀድማ ተፈጥራለች ይለናል ሲሉ አንድ ሚሉን ……
ይህን መሰል ጥያቄዎች አሁንም ቢሆን በ እንጭጩ ካልተቀጩ ኡማውን እረፍት ስለመንሳታቸው አንጠረጠርም ወይም በትግረኛው አይንጠራጠርን!!! በመሆኑም ዳግም በማያንሰራሩበት መልኩ አፈራርሰናቸው … የሚሽነሪዎችንም ክስ ከሚሽነሪዎች አእምሮ ሽረን እፎይ ማለት ይኖርብናል….. በመሆኑም ወደ ጥያቄዎቹ እና መልሶቻችን እንደ ንፋስ ሽው ብለን እንለፍ ….
ለክስ መዝገብ 2 የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ

1. እንግዲህ ቁርአን ውስጥ ግጭት የለም ስልህ በደመነፍስ አለመሆኑ በመረጃ መሆኑ ዛሬ ሚሽነሪ ከሆንክ አይቀር ያለ መንፈስ ቅዱስ ኢንሻአላህ ይገለፅልሀል (መረጃው በቂ ነው) እልሃለው ፡፡ ካንተ ሚጠበቀው ብቻ ማስተዋል ፣ ማስተንተን ፣ብቻ እን ብቻ ነው…..
ከላይ የጠቀስከው የ አል በቅራ አንቀፅ እንዲህ አንብብልኝ ፡-
“እርሱ ያ በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ለ እናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው” (2፡29) ነው፡፡ እዚህ ላይ የ ሳትከውን ነጥብን አስተውል፡፡ አንቀፁ ምድር ከሰማይ ቀድማ ተፈጥራለች አይልም ፡፡ በጭራሽ አይልም፡፡ ካልሆነ ደግመህ አንብበው፡፡
ሰማይ ቀድማ ተፈጥራለች ካለለ አንቀፁ ምን ይሆን ሚለው? ካልክ እና ከጠየክ አይቀር …. አንቀፁ ሚልህ ሰማይ ሰባት ተደረጋለች ነው ይህም ማለት ሰማይ ከተፈጠረች በኋላ ያካሄደችውን ዝግመተ ለውጥ ነው ሚነግርህ ፡፡ በሚገባህ ቋንቋ ስነግርህ ሰማይ 7 ከመደረጓ ቀድማ ተፈጥራለች - ይህንንም አንቀፁ ቀድሞ ነግሮሃል ተመልከት አንቀፁ “ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ” ይልሃል ፡፡ ይህ አንቀፅ ሰማይ 7 ከመደረጓ በፊት ቀድማ ተፈጥራ እንደነበር ይነግርሃል፡፡ ምክንያቱም ወደ ሰማይ አሰበ ይላልና ፡፡ ሰማይ ሳትፈጠር እንዴት ወደ ሰማይ ይታሰባል እንዴትስ 7 ትደረጋለች? ስለሆነም በውድም በግድም እንድትቀበል ምነግርህ ነገር ቢኖር በዚህ መልኩ በወፍራሙ ይቀርባል እንደሚከተለውም አጣጥምልኝ
- ሰማይ ና ምድርን በቢግ ባንግ ተገኙ(21፡30)(2)
- ሰማይን ከፍታዋን አጓነ ፣ አስተካከላትም፣ ሌሊቷንም አጨለመ ቀኗንም ገለፀ አን ናዚያት 79-27-30( ግና ሰባት አላደረጋትም)
- ምድርን ዘረጋት(79፡30)
- በምድር ላይ ያሉ ሁሉን ለኛ ፈጠረ(2፡29)
- ወደ ሰማይ አሰበ ፣
- አንድ ወጥ የነበረችውን ሰማይ 7 ሰማያት አደረጋት
ኢማም አቁርጡቢያ ረሂመሁላህ በበኩሉ ሰማይ ከተስተካከለች በኋላ ምድር እነደተዘረጋች ከላይ የጠቀስኩልህን አወራረድ ተፍሲሩ ላይ ጠቅሶታል(3)፡፡አል ሀፊዝ ኢስማኢል ኢብኑ ከሲርም ተፍሲሩ ላይ ተመሳሳይ መልእክት በመጥቀስ ከኢማም ቁርጡቢይ የተደመረ መረጃ ለመሆን ችሏል(4) ይህ ጥያቄህን አፈር የሚያበላ የመጀመሪያ መረጃ ሲሆን ከሳይንስ ጋር ምንም አይነት ግጭት እንደሌለው ም ጨምሬ ሳልነግርህ አላልፍም(5)፡፡ ልብ ካለህ ልብ በል አንቀፁ አይጋጭም ኦኬ!!!!
2. ሰማእ የሚለው አረበኛ ቃል በቋንቋ ከበላይህ ያለውን ቦታ ሁሉ ያመላክታል፡፡( ከዚህ አለም ውጪ ያሉት ሰባቱ ሰማያት እንደተጠበቁ ሆኖ) ይህን ለማወቅ ቁርአንን መመልከት እራሱ በቂ ነው፡፡(ወነዘልና ሚነ ሰማኢ ማእ) ሲልህ ከሰማይ ውሀ አወረድን ማለቱ ሲሆን ፡፡ ይህ እዚህ ጋር የጠቀሰው ሰማይ ዝናብ የሚወርድበትን የዚን ምድር አትሞስፌር ነው፡፡ ይህ ዝናብ የሚወርድበት የመጀመሪያው የ አትሞስፌር ክፍል ሰማእ ከተባለ ምድር ላይ ያሉት አትሞስፌሮች ሰማ ቢባሉ አይገርምም ይህን አስመልክቶ ታዋቂው ሙስሊሙ የሳይንስ ሊቅ ሀሩን ያህያ የምለው አለኝ ይለናል፡፡ እስኪ አንድ ይበሉን ሀሩን ያህያ?
“The layer of air around Earth is called the "atmosphere". The atmosphere is made up of seven layers……In the Qur'an, Allah mentions that He arranged the heaven into seven heavens…..The word "heaven" used in many verses in the Qur'an also means "sky". It is also thought to refer to the different depths of space as well as the Earth's sky. If this second meaning of the word is considered, it is stated in the verse that Earth's sky, that is, the atmosphere is made up of 7 layers. Of course, there can be other meanings of the verse, but it is very interesting that when we study the sky, we find that it is composed of seven layers”(6) በኔው አማርኛ በአጭሩ ስተረጉምልህ “ በምድር ላይ ያለው የከባቢ አየር ሽፋን አትሞስፌር ይባላል፡፡ ይህ አትሞስፌር የተገነባው ከ ሰባት ክፍሎች ነው፡፡…. ቁርአን ሰማያት ሰባት ስለመደረጋቸው ይናገራል …. ይህ ሰማይ የሚለው ቃል በቁርአን በዙ ቦታዎች ላይ የተጠቀሰ ሲሆን “የምድራችን ሰማይ” ተብሎም ይተሮጎማል….. በዚህ ሁለተኛ ትርጉም መሰረት (የመሬት ሰማይ) .. የመሬት ሰማይ ሰባት ክፍሎች አሉት . በዚህም መሰረት ሰማይን ስናጠና ሰባት ክፍሎች እንዳላቸው በሚገርም ሁኔታ እንረዳለን”
ሐሩን ያህያ እነዚህ የምድራችን ክፍል ላይ ሚከኙትን 7 ሰማእ እንዲህ ሲል ጨምሮ ይነግርሀል “ ትሮፖስፌር፣ ስትራቶስፌር፣ ሜዞስፌር፣ቴርሞስፌር፣ ኤግዞስፌር፣ አዮኖስፌር፣ ማግኔቶስፌር”(7)
እኔም እንደምልህ ቁርአን የመጀመሪያውን ዝናብ ሚወርድበትን ክፍል ሰማ ብሎ ከጠራ ሌሎችም 6 ክፍሎች ተመሳሳይ ትርጉም ማግኘታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ስለሆነም አል በቅራህ ላይ የተጠቀሰው ሰባት ሰማያት አደረጋቸው ሲል የነገረህ የቁርአኑ አንቀፅ በሁለተኛ ትርጉሙ መሰረት እየነገረህ ያለው የምድር ከባቢ አየር ላይ ሚገኙትን ሰማያት እንጂ ሱራ ናዚያት ላይ የጠቀሰውን ሰማያት አለመሆኑ ይታወቅልን ኦኬ!!!
አሁንም አንቀፁ አይጋጭም !!! ይበቃል ወይስ መረጃ ይጨመር? ….. በደንብ ግልፅ ይሆንልህ ዘንድ ልጨምር
3. በአል በቅራህ አንቀፅ ላይ የተጠቀሰው አረበኛ ቃል ثُمَّ (ሱመ) የሚል ሲሆን ከ አንድ በላይ ትርጉም አለው፡፡ “ከዛም ” ተብሎ ይተሮጎማል ከፈለክ “እንዲሁም” ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ምናልባት ግር ያለህ አማርኛውን ትርጉም ወይም ኢንግሊዘኛውን አንብበህ ይሆናል፡፡ ቀጥተኛውን ትርጉም ሚነጉሩን ተርጓሚዎች ሳይሆኑ የቁርአን ተንታኞች ናቸው ፡፡ ምን ነበር ያልከው አል ሀፊዝ ኢስማኤል ኢብን ከሲር?
“በ አልበቅራህ 2፡29 ላይ የተጠቀሰው ሱመ አረበኛ ቃል ሚያመላክተው “ ከዛም” የሚለውን አይደለም ይህ ደግሞ ከኢብን አባስ እና ከ አሊ ኢብን አቢ ጣሊብ የተላለፈ ነው፡፡”(8) ቁርጡቢይ በበኩሉም በተፍሲሩ ላይ ተመሳሳይ ትርጉምን አክሎ ነግሮናል፡፡(9) አንቀፁም በሚከተለው መልኩ ይነበባል ማለት ነው፡፡
“እርሱ ያ በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ለ እናንተ የፈጠረ ነው፡፡ እንዲሁም ወደ ሰማይ አሰበ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው” (2፡29)
ስለሆነም ይህ የቁርአን አንቀፅ ምድር ቀድማ ስለመፈጠሯ አይገልፅም ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ከ ናዚያት አንቀፅ ጋር አይጋጭም እልሀለሁ…..
በመሆኑም የናንተ ጥያቄን ከ አንዴም አሰራ አንዴ ስመለከተው “በቅሎ አባትህ ማነው ሲባል እናቴ ፈረስ ነች አለ” አይነት ሆነብኝ ለዘም ነው ገና ከጅምሩ ለሙስሊሞች እራሱን የደበቀ ለናንተ እራሱን የገለፀው አንቀፅ የቱ ነው ስል የብልህነት ጥያቄን የጠየኩህ……. ክፍል ሶስት እስክንገናኝ እንግዲህ ሀቢቢ… አሰላሙ አለይኩም ስል ልሰናበትህ..

መርፊው ዘ-ነገደ የሁዳ.
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 5 guests