ለእየሱሳውያን ቤተሰቦች የሚሆን የአላህ አምላክነት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ለእየሱሳውያን ቤተሰቦች የሚሆን የአላህ አምላክነት

Postby መርፊው » Thu Dec 26, 2013 12:33 pm

ሙስሊሞችና መጽሐፍ ‹ቅዱስ›
=================

ለሙሣ በተወረደው ተውራትና ለኢሣ በተወረደው ኢንጅል ማመን የእስልምና እምነት መሠረቶች አካል መሆኑን የሚጠራጠር ሙስሊም የለም፡፡ ይህ ማለት ግን አሁንም በክርስትያኖች እጅ የሚገኘው ብሉይ ኪዳን ለሙሣ የወረደ ተውራት ነው፣ ማለት አይደለም፡፡ ሙሣ ከሞቱ ከብዙ ምእተ አመታት በኋላ ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየውን አፈ ታሪክ መሠረት አድርገው የጻፉት የግለሰቦች ድርሰት እንጅ ለሙሣ የወረደላቸው መልእክት አይደለምና፡፡ ውስጡን በበርካታ ስህተቶችና ችግሮች የተሞላ መሆኑን የክርስትያን ሊቃውንት ራሳቸው በተደጋጋሚ መስክረዋል፡፡ ከካምብሪጅ፣ ከበርሚንግ ሃም፣ ከለንደንና ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ሰባት የክርስትና ሐይማኖት ምሁራን በብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ላይ ለአመታት የዘለቀ ጥልቅ ምርምር ካደረጉ በኋላ The myth of God Incarnate በሚል ርእስ በ1978 ባሳተሙት መጽሐፍ መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል መልእክት አስፍረዋል፡-«የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትን ሰዎች በተለያዩ ተጨባጭ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው እንደጻፏቸው ግንዛቤ እያገኘ መጥቷል፡፡ ከአምላክ የወረዱ ቃላት ናቸው በሚለው ሐሳብ መስማማት የሚቻል አይደለም፡፡»ኢኸቲላፍ ፊ ተራጁሚ ኪታቢል ሙቀደስ፣ በሊዋእ አህመድ አብዱል ወሃብ ገጽ 113

ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ ቅጽ ሁለት ገጽ 501 ላይ የሚከተለውን ጉልህ ምስክርነት እናገኛለን፡-

«በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ የሰፈሩ መልእክቶች ሙሉ በሙሉ እውነት እንዳልሆኑ (ከፊል እውነትነት ብቻ እንዳላቸው)ግልጽ ሆኗል፡፡»

‹ብሉይ ኪዳን ከ1400-400 ከክርስቶስ በፊት በልዩ ልዩ ቦታዎች፣ 40 በሚያህሉ ልዩ ልዩ ጸሐፊዎች እንደተጻፈ ይነገራል፡፡› የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር፣ ገጽ 34

ስለዚህ ብሉይ ኪዳን የአምላክ ቃል ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ ከአላህ ዘንድ ለሙሣ የተሰጣቸውን ተውራትም አይወክልም፡፡ የመጽሐፍ ‹ቅዱስ› መዝገበ ቃላት እንደሚያስረዳው የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች ሙሳ ሳይሆን 40 የተለያዩ ሰዎች ናቸው፡፡ የነዚህ ሰዎች ማንነትም በውል አይታወቅም፡፡ እናም ሙስሊሞች በተውራት እናምናለን ማለት በብሉይ ኪዳን እናምናለን ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

==============================

አዲስ ኪዳንን በተመለከተም እውነታው ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ አዲስ ኪዳን ለኢሣ የተወረደላቸውን ኢንጅል አይወክልም፡፡ እርሳቸው ካረጉ በኋላ እስከ 125 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ከኢሣ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌላቸው ግለሰቦች የተከተቡ የግል ደብዳቤዎችና ድርሳናት ናቸው፡፡ ጸሐፊዎችም እንደ ግል ደብዳቤ ጻፏቸው እንጅ ከጊዜ በኋላ የተቀደሱ ይሆናሉ የሚል ግምት አይነበራቸውም፡፡ ከወንጌል ጸሐፊዎች መካከል አንዳቸውም ‹ይህ ጽሑፌ የአምላክ ቃል ስለሆነ ተቀበሉት› አላሉም፡፡ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው እንዲህ በማለት ነበር፡-

«የከበርክ ቲዎፍሎስ ሆይ፣ ከመጀመሪያ በአይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፣ በኛ ዘንድ ስለተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለሞከሩ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፡፡»

ከሉቃስ አባባል እንደምንረዳው፡-

በርሱ ዘመን በርካታ ሰዎች የየራሳቸውን ወንጌል ይጽፉ ነበር፡፡ በክርስትና የመጀመሪያ ክፍለ ዘመን ወንጌሎች እንደ አሸን የፈሉበት ሁኔታ ነበር፡፡

ሉቃስ ጽሑፉን የጻፈው ‹የጌታ ቃል› ብሎ ሳይሆን ለባልንጀራው የግል ደብዳቤ ነው፡፡

የጻፈውም ‹መልካም ሆኖ ታየኝ› በማለት በግል ተነሳሽነት ሲሆን ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው ጀምሮ በመከታተል በግል ጥረቱ እንጅ በመንፈስ ተሞልቶ አይደለም፡፡

ሉቃስ ደብዳቤው ከዘመናት በኋላ ወንጌል ይሆናል ብሎ ፈጽሞ አላሰበም፡፡ ለጓደኛው እርግጡን ያውቅ ዘንድ ሲል ነው የጻፈለት፡፡

ሉቃስ የእየሱስ ተማሪ እንዳልነበር ይታወቃል፡፡

ማቲዮስ ወንጌሉን የጀመረው ስለ እየሱስ ትውልድ በመተረክ ሲሆን ‹ይህ ጽሑፍ ከአምላክ በእይ ተገለጸልኝ› የሚል መልእክት አላሰፈረም፡-

«የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ፣ የእየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ፡፡ አብርሃም ኢስሐቅን ወለደ፤ ኢስሐቅም ያእቁብን ወለደ . . . » (ማቲዮስ ም 1 ቁ 1-8)

የጸሐፊው ማንነት አይታወቅም፡-

‹ወንጌሉን የጻፈው ማቲዮስ ነው ያሉት የቀደሙ የቤተክርስትያን አባቶች ናቸው እንጅ የጸሐፊው ስም አልተጻፈበትም፡፡ መች እንደተጻፈ ደግሞ አልታወቀም፡፡›የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር፣ ገጽ 41

ማርቆስ ወንጌሉን ‹ተገለጸልኝ› በማለት አልጀመረም፡፡ ባይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የግል ጽሑፉን ወንጌል ብሎ ሲጠራው እናነባለን፡፡ ማርቆስ የእየሱስ ተማሪ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የጸሐፊው ማንነትም አይታወቅም፡-

‹ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር ስለዚህኛው ወንጌል ጸሐፊ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ መጽሐፉ በየትኛውም ስፍራ ስሙን አይጠቅስም፡፡›ሜሪል ሲ. ቴኒ፣ የአዲስ ኪዳን ቅኝት፣ ገጽ 236

ዩሐንስ ወንጌሉን የጻፈው ለተለየ አላማ መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ እርሱም እየሱስ የአምላክ ልጅ መሆኑን ለማሳመን ነው፡፡ በዩሐንስና በሌሎች ጸሐፊዎች ድርሳናት መካከል የእሳትና የጭድ አይነት ልዩነት ስለመኖሩ ምእራባዊ የሐይማኖት ሊቃውነት የሰጡትን ምስክርነት ከዚህ ቀደም ማስፈራችን ይታወሳል፡፡ ዮሐንስ የጽሑፉን ዓላማ እንዲህ በማለት ይጠቅሳል፡-

«እየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል፡፡» (ዮሐንስ ም 20 ቁ 31)

ዮሐንስ የእየሱስ ተማሪ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ማንነቱም በውል አይታወቅም፡፡

ጳውሎስ በሕይወቱ ለአንድ ጊዜ እንኳ ከእየሱስ ጋር አልተገናኘም፡፡ ክርስትያኖችን በጠላትነት ሲያሳድድ ከቆየ በኋላ በድንገት ‹እየሱስ ተገለጠልኝ› አለና የክርስትና ሰባኪ መሆኑን አወጀ፡፡ መጀመሪያ ላይ የእየሱስ ተማሪዎች ተጠራጥረውት ነበር፡፡ ባርናባስ በተባለ ደግ ሰው ማግባባት ነው የተቀበሉት፡፡ (የሐዋሪያት ስራ ም 9 ቁ 1-28ይመልከቱ፡፡)

የጳውሎስን ደብዳቤዎች በቅርበት ስናጠና የግል ጉዳዮቹን የጻፈባቸው ሆኖ እናገኛቸዋለን፡፡ በሰላምታ ይጀምራሉ፡፡ እገሌን እገሌን ሰላም በልልኝ፣ ሳምልኝ፣ በሚል ሰላምታም ይጠናቀቃሉ፡፡ ለምሳሌ፡-

«በከንክርኦስ ባለች ቤተክርስትያን አገልጋይ የምትሆን እህታችንን ፌበንን አደራ ብያችኋለሁ፤ ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሏት፤ እርሷ ለብዙዎች ለኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፤ከናንተም በምትፈልገው በማንናቸውም ነገር እርዷት፡፡ በክርስቶስ እየሱስ አብረውኝ ለሚሰሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱም ስለነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፤ የአህዛብ አብያተ ክርስትያናት ሁሉ የሚያመሰግኗቸው ናቸው እንጅ እኔ ብቻ አይደለሁም፤ በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስትያን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከእስያ ለክርስቶስ በኩራት ለሆነው ለምወደው ለአጤንጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ፡፡ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ፡፡ በሐርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ፣ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ አብረውኝም ለታሰሩ ዘመዶቼ ለእንዲራኒቆን እና ለዩሊያን ሰላምታ አቅርቡልኝ፡፡ በጌታ ለምወደው ለጵላጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ. . .» (ወደ ሮሜ ሰዎች ም 16 ቁ 1-21)

የግል ጉዳዮቹን ሲጽፍ እናየዋለን፡፡ ለምሳሌ ፡-

«ለጵርስቅላና ለአቂላ፣ ለሔኔሲፎሩም ቤተሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ፡፡ ኤርስጦስ በቆረንጦስ ቀረ፣ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውኹት፡፡ ከክረምት በፊት እንድትመጣ ትጋ፡፡ ኢውግሎስና ጱዴስ ሊኖስም ቅላውዲያውም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሐል፡፡» (ወደ ጢሞትዮስ ም 4 ቁ 19-21)

እነዚህ የግል ሐሳቦችና ደብዳቤዎች ናቸው ከጊዜ በኋላ ‹ወንጌል› ተሰኝተው ‹ቅዱስ› የተደረጉት፡፡

ስለዚህ ለኢሣ ከወረደው ኢንጅል ጋር ዝምድና የላቸውም፡፡ ቁርአን በኢንጅል እመኑ ሲል ማርቆስ፣ ማቲዮስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ እና ጳውሎስ የተባሉ ግለሰቦች ከእየሱስ ከብዙ አስርት አመታት በኋላ ለግል ጉዳዮቻቸው በጻፏቸው እና በአሁኑ ሰአት ኦሪጅናል ይዘታቸው በጠፋው የግል ደብዳቤዎች እመኑ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

♣ ♣ ♣

ታዲያ ሕልውና በሌላቸው መጽሐፍት እንድናምን ቁርአን ለምን ያዘናል? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በእርግጥ ቁርአን እመኑ ያለን ለሙሣ እና ለኢሣ ብቻ ሳይሆን ለኢብራሂም በተሰጠው ‹ሱሑፍ›ና ለዳውድ በተሰጠው ‹ዘቡር› ጨምሮ ለሁሉም ነብያት በተወረዱት መጽሐፍት ነው፡፡ የሙሣ እና የኢሣ መጽሐፍት በተለየ ሁኔታ የሚታዩበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በቀደምት መጽሐፍት ማመን የሚከተሉት ዋናዋና ጠቀሜታዎች አሉት፡፡

1) በአምላክ ሐይማኖት አንድነት ማመን ማለት ነው፡፡ አምላክ ለሰው ልጆች የተለያዩ ሐይማኖቶችን አልመረጠም፡፡ የወደደላቸው አንድ ሐይማኖት ብቻ ነው፡፡ እርሱም እስልምና ነው፡-

«አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች በመካከላቸው ላለው ምቀኝነት ዕውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡ በአላህም አንቀጾች የሚክድ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ (19)» (አል ኢምራን 19)

«ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ (85):»(አል ኢምራን 85)

٣

«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡::» (አልማኢዳህ 3)

2) የአምላክ መልእክተኞችን አንድ አይነት አላማና የጋራ ተልእኮ ያረጋግጣል፡፡

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ፡፡ በአላህና በመላእክቱም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን፣ የካደ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ (136)

(አል በቀራህ 136)

3) ለነቢዩ ሙሐመድ ከሰማይ መልእክት መውረዱ እንግዳ ነገር እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ ምክንያቱም ለሙሣ፣ ለኢሣና ለሌሎችም ነብያት በተመሳሳይ ሁኔታ መልእክት ወርዶላቸዋልና፡፡
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby ዲጎኔ » Fri Dec 27, 2013 11:58 am

ሰላም ለሁላችን/አሰላማሊኩም
ውድ የሀገር ልጆች መርፌውና ጎነጠ እንዲህ በጨዋነት ስትወያይዩ እንዴት ያስደስታል:: በስድብ ምክንያት የራቅሁ ጠቅላላ እውቀት አምድ እንድጎበኝ ምክንያት ሆናችሁኛል::
በርቱ የሁሉ ፈጣሪ አንዱ አምላክ ወደመልካሙ መንገድ ያድርሳችሁ::
ዲጎኔ ሞረቴ በጨዋነት ለጦቢያ አብረው ከተቀመጡ የሀይማኖት አባቶች ሀጂ መሀመድ ሳኒ ቄስ ፍራንሲስ አቡነ ተክለሀይማኖትና አቡነ ጳውሎስ ጸአድዋ ክበብ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests