ለእየሱስ አምላክነት የተሰጡ ውሀ የማይቋጥሩ ምክንያ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ለእየሱስ አምላክነት የተሰጡ ውሀ የማይቋጥሩ ምክንያ

Postby መርፊው » Tue Dec 31, 2013 1:06 am

ለእየሱስ አምላክነት የሚሰጡ ውኃ ማይቋጥሩ ምክንያቶች ?
^^^^----^----
1.የአለአባት መወለዱ ?
በድንግልና መወለድ በንጽጽር ሲታይ የሚያስደንቅ አይደለም ከዚህይ የበለጠ አባታችን ነብዩላህ አደም(አዳም)(ዐ.ሰ) የአለአባት የለእናት በዚ መስፈርት አምላክ ቢኮን መሆን ነበረባቸው ግን አይሆንም፡፡

2.የሰራቸው ድንቅ ተዓምራት
የሰራቸው ተአምራት አምላክ አያደርጉትም፡:: why ?

}--> አንድ ፡-በሌሎች ተሰርተዋል እነሱ አምላክ ሳልተባሉ ለምሳሌ 1 **የሞተን መቀስቀስ ኤልሳም ይህን አድርጓል

<<ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 13፡21

2**በውሀ መራመድ ማንም ያውቀዋል እነ ሙሴም ተራምደዋል ዘጽአት 14፡22 ተመልከት

3**አጋንነት ማውጣት ማንም ያወጣል
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
በጥቅሉ ተአምር መስራት የአምላክነት መገለጫ አይደለም ሀሳዊያን እንኳን ይሰራሉና
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
‹‹ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። ማቴውስ 24፡24 እነደውም

‹‹በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ። ማቴውስ 7፡22

--> አዎ ነብያት ለህዝባቸው ጉዳይ ቀዳሚ መስካሪ ናቸው(ኒሳእ 4፡41 እና ነኽል 16፡89 ተመልከት) በዚያ ጊዜ እየሱስን ጨምር ነብያት መስካሪ ፈራጁ አንዱ ህያው ጌታችን አላህ ነው፡፡

}--> ሁለት፡- በራሱ ችሎታ አይደለም የሰራቸወ
ምሳሌ ሀ. ***********************
<<እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። የሐን 5፡30
ምንም ማድረግ እንደማችል ከመግለጹም ባሻገር የተላከ መልክተኛ መሆኑን በግልጽ ይገልጻል

ምሳሌ ለ.አጋንንት ሲያወጣ በራሱ ነበርን ? በፍጹም

‹‹እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ..› ሉቃስ 11፡20
ምሳሌ ሐ
አልአዛር ከሞት ሲያስነሳ በራሱ ነበርን ? በፍጹም ምስጋና የሚገባው የእየሱስ ጌታ ነው፡፡
‹‹ድንጋዩንም አነሡት። ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ።››

** ቁርዓንም በአላህ ፍቃድ ሙታንን ህያው…ሌሎችንም አንዳደረገ በማኢዳ 5፡110 ይነግረናል፡፡ ዱአ ያደርጋል በአላህ ፍቃድ ይሳካል::

‹‹ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር። ሉቃስ ወንጌል 5፡16
… በጣም ጥቂት ማሰያ ነው፡፡

^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
3. ሌላው በተደጋጋሚ ያነበብኩት አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ በሎዋል (ዩሐን 8፡58) የሚል ነው
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
በርግጥ እንደ ሙስሊም ይህ አባባል 100 ትክክል ነው ግን ኢሳ(እየሱስ)(A.S) ብቻ ሳይሆን ሁላችነም ሰዎች ስንባል ከአብራም ብቻ አይደልም ከዚያም በፊት በጌታች እውቅት ስር ነፍሳችን ምንነቷ ትታወቃለችና አባባሉ ትክክል ነው (ከአዕራፍ7፡172) አንጻር፡፡

ባይብልን ቃኛት ካደረግን ሰማይ ምድር ከመታሰቡ በፊት ነበርኩ የሚሉ ነብያትን እናገኛለን ለምን እነሱስ አምላክ አልሆኑም ? ለምሳሌ

***እነ ሰለሞን ምን ሊባሉ ነው፡፡****
‹‹ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥ የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ።ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድሁ፥ምድሪቱንና ሜዳውን ገና ሳይፈጥር የመጀመሪያውን የዓለም አፈር።ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ፥ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፥ የቀላይን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥ ….›መጽሐፈ ምሳሌ 8፡23-28 … አላለቀም ከፍተው ያንብቡ

** እነ ኤርሚያስ በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ ሳይኖር ይታወቃል አንዴ ? ***
‹‹የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። ትንቢተ ኤርሚያስ 1፡4-5
**እነ እዮብስ***
‹‹ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር። እዮብ 38፡4 ጀምሩ *****የት አንደነበረ መናገር የሚችል አለን ?የራሱን መናገር ሳይችል ግን ስለ እየሱስ መናገር ምን የሉታል?
አንቀጹ ይሄድና 21 ቀጥር ላይ እዮብ 38፡21 ላይ መልሱን ይሰጣል
‹‹በዚያን ጊዜ ተወልደህ ነበርና፥ የዕድሜህም ቍጥር ብዙ ነውና፤ በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም።››እዮብ 38፡21

**ካህኑ መልከ ጼዴቅ ወዘተ…
**********
ታዲያ በመቆየት መስፈርት አምላክ የሚባል ከሆነ እኛም አምላክ መባል ሊኖርብን ነው ባይብል ላይ
የተጠቀሱ ሌሎቸ ነብያትም መሆን ነበረባቸው ግን እንደዚሁ አይደለም፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
4. (((በዘላለማዊነት :->ሁሉን ኣዋቂነት :->ሁሉን ቻይነት )) በዚህ መስፈርት መሰረት ዕውነታውን አንፈታትሽ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
1. ዘልዓለማዊነት ፡- አምላክ ዘልአለማዊ ህያው ነው አዎ ፡፡ እየሱስ ግን ‹”ሞቶዋል”›ትላላችሁ አየደል ?

2. ሁሉን ኣዋቂነት፡- አምላክ ሁሉን ያውቃል እየሱስ ግን አንደማያውቅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ነገሮናል ከሁኔታዎች አኛም ተረድተናል ምሳሌ ‹ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። › ማር 13፡32

3. ሁሉን ቻይነት ፡- አምላክ ከሙሉ ክብሩ ጋር ሀሉን ቻይ ነው ፍቃድ አያሻውም ፡- እየሱስስ ግና ‹እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።› ዩሐንስ ወንጌል 5፡30

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
5. ሰዎች ጌታ ብለውታል፤ሰግደውለታል… ስለዚያ አምላክ ነው የሚልም ካለ ትንሽ ጥያቄ ላንሳ
~~~~~~~~~~~~~~~~~`------
1ኛ. ጌታ የሚለው አገላለጽ እንደ ባይብል ለክብር የሚውል እዚህ እዚያ የምናገኘው ነው ታዲያ ሌሎች ጌታ የተባሉ እንደ አብርሃም፤ ሙሴ..(ኦሪት ዘፍጥረት 24፡18፤ኦሪት ዘኍልቍ 11፡28) ለምን አምላክ አልተባሉም ለክብር ካልሆነ?ወይስ አንሱም አምላክ ናቸው ?

2ኛ. ሰዎች እኔን አስመልክቶ ቢናገሩ ወይም ቢሰሩ ትክክል ነው? ከእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ቢያንስ የኔ ምስክርነት ያስፈልጋል እስኪ እየሱስ ለማን መሰገድ አንዳለበት … ይንገረን ባይብሉ
- › ‹ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው። ›ሉቃስ 4፡8 ይህን በቃል በተግባርም ተዘዥነቱ ለጌታ በፊቱ እየተደፈ እራሱ ሰግዶ ሳለ አንዴት ለረሱ ይሰገዳል ? ወይስ አሱም ለራሱ ነው የሰገደው ? ምሳሌ ማቴ 26፡39 ተመልከት

3ኛ.እሱ ራሱ አምላክ አንዳለው በግልጽ አስቀምጦዋል ታዲያ አምላክ አምላክ ይኖረው ይሆን ?

‹ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።›› ዩሐ 20፡17 አምላካችን
‹‹እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የዮሐንስ ወንጌል 17፡3

4ኛ. ጌታ የሚሉትን ሁሉ ልብ በሉ <<ሁሉ ነ› አመጸኛነታቸው ሲገልጽ ለዚያውም ተራ አማኞች አንዳይመስሉዋቸው አሁን እንደሚታየው እልል..እልል የሚያስብሉት ተዐምር ሰራን፤አጋንን አወጣን ያሉትን ነው አንብቡት:-
{{{{ 21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ? ይሉኛል።
23 የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።}}}} ማቴ 7፡21-23
------ ወዘተ
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
6. ዮሃ10:30 ‹‹አንድ ነን›› ብሎዋል አዎ እኔም አንድ አይደሉሙ አልወጠኝም ይህ አንድነት ግን የዓላማ ብቻ ነው ተመልከት
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
አምላክ በላጭ ነው ይልሃል ባይብል

‹‹..የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር..›› ዩሐ 14፡28

እየሱስም ደግሞ የዚህ አምላክ የተላከ ተላኪ መልክተኛ መሆኑን ዩሐ 7፡16 ፤ዩሐ 7፡16፤ ዩሐ 16፡5፤ሉቃስ 10፡16፤ዩሐ 7፡29 .. .. ..ከ10 ያላነሱ ቦታዎች መልክተኛ(ረሱል) መሆኑን ፈንትው አርገው ይገልጻል፡፡ ስለ መልክተኛ ጥቁር ዕውነታው ደግሞ
‹..መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።›› ዩሐ 13፡16

በሌላ በኩል ተላኪ ያለከውን ከማስፈጸም ውጭ ሌላ ተልዕኮ ስለሌለው እየሱስም ሆነ እንዲሁም ሀዋሪያት እንዲሁም አምላክ በአላማ አንድ እንደሆነ ሲገልጽ ደግሞ

‹‹…አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።›› ዩሐ 17፡20 ይልሃል አንድ ነን ሲባል ከዚሁ አንጻር ነው፡፡ አይሆን በአካልም፤በዐውቀትም .. አንድ ነው ዘራፍ ካልከኝ በአላህ ፍቃድ አንድነት ወይስ ልዩነት የሚለውን አጭር ጽሑፍ አስነብብ ሃለው ለማንበብ ፈላጎት ብቻ አሳይ ወገኔ ፡፡

በመጨረሻም ኢሳ(እየሱስ) ለወገኖቹ ምን አላቸው
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ኢምራን 51 «አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» (አላቸው)፡፡ተጨማሪ መርየም 36 አንዳለው

ባይብል ላይም
---> <…እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት። (ዮሐንስ 20.17)

--> ‹..ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም› ማቴ 7፡21

--> ‹…የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።ማቴዎስ 15፡8-9

--->ልጠቅልለው፡፡
እየሱስ አንድም ቦታ እኔን አምልኩ፤ አምላክ ነኝ… . አይነት ቃሎች አልወጡትም የወንድሜ ቃል አሚን አገላለጽ ልዋስ “ወፍ የለም ኢንጂሩ” …ተቀራኒውን ከአምላክ የሚለየውን በርካታ ነጥቦች ደግሞ እየሱስ ደጋግሞ ጠቅሶዋል፡፡

ሰላም ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ይሁን መንገድ የሳተውን አላህ ይምራው አሚን፡፡
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests