መጽሀፈ ""ቅዱስ"" ስለ ታላቁ ነብያት ዙርያ የተሰነዘሩ አስጥ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

መጽሀፈ ""ቅዱስ"" ስለ ታላቁ ነብያት ዙርያ የተሰነዘሩ አስጥ

Postby መርፊው » Tue Dec 31, 2013 1:26 am

በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› ውስጥ በነብያት ዙሪያ የተሰነዘሩ አስጸያፊ ሐሰቶች*^*^*

*** በኦሪት ዘፍጥረት 19:31-35 ) ውስጥ ሉጥን በተመለከተ አስጸያፊ መልእክቶች ሰፍረዋል፡፡ ሉጥ አስካሪ መጠጥ ጠጥተው መስከራቸው፣ ከዚያም ከሴት ልጃቸው ጋር መዘሞታቸው፣ እርሷም ማርገዟና ዝሪያቸው በርሷ በኩል መቀጠሉ ተጠቅሷል፡፡ እስኪ አስቡት! አላህ የሶዶምን ከተማ የገለበጠውና ሕዝቡን ያጠፋው የሶዶም ሕዝብ የኒህን ንጹህ ነብይ ቃል ባለመስማቱ፣ በርሳቸው እና በትምርታቸው በመሳለቁ ነበር፡፡ ወደ ንጽህና ያደረጉትን ጥሪ ባለመቀበሉ በጅምላ ቀጣው፡፡ የኢብራሂም የወንድም ልጅ የሆኑትን የሉጥን ንጽህና ለመመስከር ከጠፉ ከተሞች ቅሪቶች ውጭ ሌላ ምስክር ባይኖር እንኳ በቂ ምስክር አይደለምን? እንዲህ ዓይነት አስጸያፊ መልእክቶችን የያዘን መጽሐፍ መለኮታዊ ብለን ልንቀበለው እንችላለን?

*** ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 38 ላይ የየእቁብ ልጅ የሁዛ -ምን አልባትም ነብይ ሊሆን ይችላል- ከልጁ ሚስት ጋር ዝሙት መፈጸሙ ተጠቅሷል፡፡ የበኑ ኢስራኤል ነብያት ዝርያ ለምሳሌ (ዳውድና ሱለይማን) የተገኙት ከዚህ የዝሙት የዘር ግንድ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
ይህ ዘገባ ሐሰት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው ቅጥፈት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንደሚሉት፡- ‹‹ከአደም አንስቶ የርሳቸው የዘር ግንድ በጋብቻ ላይ ብቻ የተመሰረተ እና የተገኘ ነው፡፡›› (ደላኢሉ ኑቡዋ በይሐቂ 1/173-175)

በሌላ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነብያት የአንድ አባት ልጆች ናቸው፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም)

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አያት ቅድመ አያት ውስጥ አንድም የዝሙት ልጅ ከሌለ ይህ ባህሪ በሌሎች ነብያትም ላይ የሚሰራ ነው፡፡ እርሳቸው የኢብራሂም የልጅ ልጅ አይደሉምን? የሁዛም እንደዚሁ የኢብራሂም የልጅ ልጅ ነው፡፡ በነብያት ቤት ውስጥ ዝሙት ሊከሰት አይችልም፡፡

*** በመጽሐፈ ነገስት ምእራፍ 11፣ውስጥ ሱለይማን በእድሚያቸው መጨረሻ ላይ እንደካዱና ጣኦት ማምለክ እንደጀመሩ ይገልጻል፡፡ በዚህም ሆነ በመጭው ዓለም ታላቅ ደረጃ ለግሶ አላህ የመረጠው ነብይ ክህደት ይፍጽማል ተብሎ እንዴት ይታሰባል? ሱለይማን አላህን በጽኑ አምላኪና አመስጋኝ ነብይ እንደሆኑ በቁርአን ተጠቅሷል፡፡ ለነብይ ተገቢው ባህሪ ይህ አመስጋኝነት ነው፡፡

ቁርአን ዒሳን፡- ‹‹አላህ ወደ መርየም ያኖረው መንፈሱና ቃሉ›› ሲል ይገልጻቸዋል፡፡ (አል ኒሣእ 171)

ኢብራሂም የአላህ ምርጥ ወዳጅ፣(አልኒሣእ 125)

ሙሳ አላህ ያናገራቸው፣ ( አልኒሣእ 114) መሆናቸውንም ተናግሯል፡፡

የዳውድን ቤተሰብም፡- ‹‹የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ፣ አመስጋኞች ስትሆኑ ስሩ›› ሲል አናግሯቸዋል፡፡ (ሰበእ 13) አላህ ነብያቱን የሚገልጽባቸው ባህሪያት እነዚህ ናቸው፡፡

*** ብሉይ ኪዳን ስለ ነቢዩላህ ዳውድ ሲተርክ አርያ የተባለውን ሰው ሚስት እንደተመኙና ሆነ ብለው እርሱን በማስገደል ሚስቱን እንደቀሙት ይተርካል፡፡ ሳሙኤል 2ኛ 11፡2-4)

ይህ እኩይ ባህሪ ለነቢይ ቀርቶ ለተራ ሰው፣ በእውን ቀርቶ በሕልም እንኳ የሚያስጸይፍ ነው፡፡ አላህ ዳውድን በተመለከተ ‹‹ምን ያምር አገልጋይ፡፡ እርሱ ወደ አምላኩ ተመላሽ ነው፡፡›› ብሏል፡፡ (ሱረቱ ሷድ 30)

*^*^* የነብያትን ስም እንዲህ የሚያጠፋና የሚያረክስ መጽሐፍ እንዴት ከአላህ የተገኘ ሊሆን ይችላል? ይህ ታሪክ ይከሰታል ብሎ ማሰብ የነብይነትን ደረጃ አለማወቅ ነው፡፡ ነቢ ዳውድ አላህን አዘውትረው የሚያመልኩና አልቃሽ ነብይ ነበሩ፡፡ ከርሳቸው ጋር የተቀመጡ ሁሉ የርሳቸው ለቅሶ ተጋብቶበት ያለቅሳል፡፡ ወደ አላህ በንስሐ መመለስን ያበዛሉ፡፡ ፊታቸውን ከአምላካቸው ለቅጽበት እንኳ አላዞሩም፡፡
የሕይወታቸው ዋነኛ መርህ ዑቡዲያ ነበር፡፡ አላህን ዘወትር ማምለክ፡፡(ሷድ 17)

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የነቢይ ዳውድን ኢባዳ ሲያወድሱ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ከአላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ሶላት የዳውድ ሶላት ነው፡፡ ከላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ጾም የዳውድ ጾም ነው፡፡ የሌሊቱን ግማሽ ይተኙና ሲሶውን ይቆማሉ፡፡ 1/6ኛውንም ይተኛሉ፡፡ 1 ቀን ይጾማሉ፣ አንድ ቀን ያፈጥራሉ፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም)

ነቢይ ዳውድ ንጉስ ነበሩ፡፡ የመንግስት ሃብት በአጠቃላይ በእርሳቸው እጅ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን ያን ሃብትና ንብረት ለግላቸው ለመጠቀም፣ ሌላው ቀርቶ በርሱ አንዲት ቁራሽ ምግብ እንኳን ለመግዛት ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚቀልቡት የእጅ ሙያቸውን ተጠቅመው በሚያገኙት የግል ገቢ ነበር፡፡ አንዲት ቁራሽ እንኳ ያለ አግባብ ለመውሰድ ባልፈቀዱት፣ የሕይወት መርሃቸው እና ልዩ ባህሪያቸው አላህን ማገልገል በሆኑት በዚህ ነብይ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ያንን አጸያፊ ቅጥፈት ይደርትባቸዋል፡፡ እጅግ ብጹእ እና ንጹህ ከመሆናቸው አኳያ ይህ ቅጥፈት በተግባር ቀርቶ በሐሳብ እንኳ ለቅጽበት ሊታወሳቸው ፈጽሞ የሚችል አይደለም፡፡

**** በብሉይ ኪዳን (ዘፍጥረት 32፡22-28) ውስጥ አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ሌላም አስገራሚ ነገር እናገኛለን፡፡ እርሱም እስራኤል (ያእቁብ) ከአምላክ ጋር ታግለው ማሸነፋቸው ነው፡፡ እናም የምእራቡ አለም ቁሳዊ ፍልስፍና ወሰንን ሁሉ ጥሶ አምላክን የሰው ቅርጽ በማስያዝ ከነብዩ ጋር እንዲታገል አድርጎታል፡፡ ሐምዛ ከመስለማቸው በፊት ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የተናገሩት ተከታዩ ቃል ለነዚህ ወገኖች ጥሩ ምላሽ ይዟል፡-

‹‹የወንድሜ ልጅ ሙሐመድ ወይ፣ ሌሊት በበረሃ በምዘዋወር ጊዜ አላህ በግንብ ውስጥ ተወስኖ ከመቀመጥ በላይ መሆኑን እረዳለሁ፡፡››
ስለዚህም ክርስትያኖችና አይሁዶች የአምላክ ቃል ነው ብለው የሚያስቡት መጽሐፍ በዘመነ መሐይምነት ወደነበሩት ሐምዛ የሕሊና ደረጃ እንኳ ከፍ ሊል አልቻለም፡፡ ታዲያ በእንዲህ አይነት ብክለቶች የተሞላውን ይህን መጽሐፍ የአምላክ ቃል ነው ብሎ እንዴት ማሰብ ይቻላል?

ይህ መጽሐፍ ስለ ነቢያት የሚናገረው ሊታመን ይችላልን? በፍጹም አይታመንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አላህንና ነቢያቱን አስመልክቶ በቅጥፈትና በጥመት የተሞላ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን የጥመት ምንጮች ናቸው፡፡

*^* ቁርአን በነብያት ዙሪያ ለተደረቱ ቅጥፈቶች ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ምክንያቱም ነብያትን ሙሉ በሙሉ እንድንከተል ያዘናልና፡፡ በቁርአን ትምህርት መሠረት ነብያት ስብእናቸው የተሟላ፣ የቅን ጎዳና መሪዎች፣ በሁሉም ጉዳዮች ሊከተሏቸው እና ሊታዘዟቸው የሚገቡ ታላላቅ መምህራን ናቸው፡፡ ሁሉም ነብያት የአላህን ውዴታ የሚያየንጸባርቁልን መስታወቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ መስታወቶች ላይ አንዲት እንኳ የአቧራ ቅንጣት አይገኝም፡፡ የተከበረው ቁርአን ይህንን እውነታ እጅግ ውብና ግልጽ በሆነ መልኩ አስቀምጦታል፡፡
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ የአንዳንድ ነብያትን ድርጊቶች በስህተት በመረዳት ነብያት ሐጢአት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ የሚያስቡ ወገኖችን እናገኛለን፡፡ የስህተታቸው ምንጭ መልእክቶችን በወጉ አለረዳት ሲሆን ጥቂት ቢያስተነትኑ የአስተሳሰባቸውን ግድፈት መረዳትና እንደብዙሐን ዓሊሞች ለነብያት ተገቢውን ክብር መስጠት በቻሉ ነበር፡፡
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 6 guests