ሰይፍና የእምነት ነጻነት !!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ሰይፍና የእምነት ነጻነት !!

Postby መርፊው » Tue Dec 31, 2013 3:47 pm

------------- ሰይፍና የእምነት ነፃነት ---------------
====================================
ቁርአን እርስ በርሱ ይጋጫል ይህም ስለጦርነት እና ስለ ሐይማኖት ነፃነት የሚያወጉ አናቅጽ ናቸው፡፡ቁርአን በአንድ ወገን እንዲህ ይላል፡-
‹‹በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ቀጥተኛው ጎዳና ከጠማማው ፍኞት በሚገባ ተገልፆል፡፡››(አልበቀራህ 256)
በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ካህድያንን ተዋጉ፤ ግደሉ፤አሳዷቸው ፡፡ፋታ አትስጧቸው›› የሚሉ አንቀፆችን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ተከታዩን የቁርአን አንቀጽ እንመልከት፡-
‹‹ተጋደሏቸው፡፡ አላህ በእጆቻችሁ ይቀጣቸዋል፤ ያዋርዳቸዋል ፤እናንተንም -በነርሱ ላይ (ድልን ትቀዳጁ ዘንድ ) ይረዳችኋል፤የአማኞችን ሕዝቦች ልቦችም ያድናል፡፡›› (አል ተውባህ 14)
በሐይማኖት ማስገደድ የለም እያለ ካህዲያን ተጋድሎ ማለቱ ግጭት አይደለምን? ሰይፍ መምዘዝ ማስገደድ አይደለምን? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡
ይህች ክስ ፤-ኢስላም በሰይፍ ነው የተስፋፋው›› ከሚለው ተረት ጋር ጥብቅ ትስስር ያላት በመሆኗ ጥቂት ዘና ብለን፤ሰፋ አድርግ ማየት ያሻናል ጽሄፌን በእውቁ ታሪክ ተመራማሪው ልጀምር “Islam was spread by the sword is given by the noted historian De Lacy O’Leary in the book “Islam at the cross road” (Page 8): “History makes it clear however, that the legend of fanatical Muslims sweeping through the world and forcing Islam at the point of the sword upon conquered races is one of the most fantastically absurd myth that historians have ever repeated” ዲ ሌሲ ኦ ሊሪ የተባለው እዉቅ የታሪክ ተመራማሪ ኢስላም በመንታ መንገድ ላይ በሚለው መጸሐፍ ገጽ 8 ላይ እንዲሆን ብሎ ነበር፡፡ "አክራሪ ሙስሊሞች በዓለም ላይ በመዟዟር በኃይል በወረሯቸው ህዝቦች ላይ እስልምናን በሰይፋቸው አስገድደው ጫኑባቸዉ" የሚለው ሀሰተኛ ውንጀላ ምዕራባውያን እስከዛሬ ከተረካቸዉ ታሪኮች ሁሉ በሚገርም ሁኔታ የተወለጋገደና መሰረት የለሽ አፈ-ታሪክ መሆኑን ታሪክ ራሱ ግልጽ አድርጐልናል፡፡

የነቢዩ ሙሐመድን ሰ.ዐ.ወ የነብይነት ሕይወት መካዊና መዲናዊ ተብሎ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል ፡፡መካዊው ዘመን 13 ዓመታትን የፈጀ ሲሆን መዲናዊው ዘመን 10ዓመታትን ፈጅቶቷ፡፡
በመካ ዘመን ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘው የተነሱት ሐሳብ እንጅ ሰይፍ አልነበረም፡፡እምነታቸውን በነብያዊ ስርአት ማቀረብ ጀመሩ፡፡ ጥቂት ሰዎች ተቀበሏቸው፡፡ ብዙሐኑ ግን ተቃወማቸው፡፡‹ከባህል ወጥተሃል፤ አዲስ ነገር አምጥተሃል›› ሲሉም ነቀፏቸው፡፡ ነገሩ ግን በነቀፌታ ብቻ አልቆመም፡፡ወደ ስነ ልቦናዊ ጦርነት፤ ብሎም ወደ አካላዊ ጥቃት ተሸጋገረ፡፡ በዚያ ዘመን ሙስሊሞች ላይ ስም ከማጥፋት፤ እምነታቸውን ከማጥላላትና የነብያቸውን ስብእና ከማጠልሸት ጀምሮ እስከ ማሳደድ፤ ማሰቃየትና ግድያ የደረሰ ሁለንተናዊ ጥቃት ተከፈተ፡፡ ሙስሊሞች መከራ ሲበዛባቸው፤ ችግር ሲጠናባቸው ሐገር ጥለው በመጀመሪያ ወደ ሐበሻ፤ በኋላም ወደ መዲና ተሰደዱ፡፡
መካዊው ዘመን በእንዲህ አይነት ሁኔታ አለፈ፡፡ በዚህ ዘመን ሰይፍ የተመዘዘው በሙስሊሞች ላይ ነበር፡፡ የእምነት ነጻነት ያጡት፤ የተሰደዱት፤ የተገደሉት፤ የተሰቃዩት ሙስሊሞች ነበሩ፡፡ በዚህ ዘመን የእስልምና መርህና አቋም የእምነት ነጻነት የሚያጸድቅ፤ መቻቻል የሚያንጸባርቅ ነበር፡፡ የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጥያቄም ‹‹ሁላችንም የየራሳችን እምነት በነጻነት እናራምድ፤ የማሰብ ነጻነት ይከበር፡፡›› የሚል ፍታሃዊ ጥያቄ ነበር
‹‹ለናንተም ሐይማታችሁ አላችሁ፡፡ ለኔም ሐይማኖቴ አለኝ›› (ሱረቱ አል-ካፊሩን ምዕ.109 ቁ.1)
በዚህ ዘመን የሰለሙ ግለሰቦች ወደውና ፈቅደው፤ መከራን፤ስቃይንና ሞትን ለመሸከም ተዘጋጅተው ወደ አዲሱ እምነት የገቡ መሆናቸው እርግጥ ነው፡፡ በዚያ ዘመን የሰይፍ ራት የሚያደርገው፤ መከራ የሚያዘንበው፤ ባሰቃቂ ሁኔታ መሞትን የሚያመጣው አለመስለም ሳይሆን መስለም ነበር፡፡ ታሪኩ እንደ ረፋድ ጸሐይ ግልጽ፤ እውነታው ጉልህ ነው፡፡

መዲናውያንም እስልምናን የተቀበሉት ሁኔታም ይህንን የሰይፍ ክስ አስቂኝ ተረት ያደርገዋል፡፡
ነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሱ.ወ ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና መዲና እንደገቡ ሙስሊም ካልሆኑ ወገኖች በተለይም ከአየሁዶች ጋር አብሮ በሰላም የመኖር ስምምነት ተፈራረሙ እንጂ ‹‹ካሰለማችሁ አጠፋችኋለሁ›› በማት ሰይፍ አልመዘዙባቸውም፡፡ በኋላ ላይ ከአይሁዶች ጋር የተፈጠሩ ግጭቶች ሁሉ ምክኒያታቸው አይሁዶች ለዚህ የሰላም ውል ተገዥ ባለመሆናቸው የተከሰቱ እንጂ በሀይል የማስለም አላማ ያነገቡ አይደሉም፡፡
አቅመ ቢስ ኦሪንታሊስቶችና ክርስትያን ሚሽነሪዎች ‹‹ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አቅመ ደካማ እያሉ የሐይማኖት ነጻነት ይሰብኩ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን አቅም ሲያገኙ ግን ማስገደድ ጀመሩ›› የሚል መረጃ አልባ ክስ ሲዘነዝሩ ሰምተህ ሊሆን ይችላል፡፡ ግና ይህም ክሳቸው እንደ አለት ከጠጠረ ጉልህ እውነታ ጋር በመጋጨት ይንኮታኮታል፡፡ ምክኒያቱም ነብዩ(ሰ›ዐ.ወ) ተከታዩን አዋጅ ያወጁት መዲና ውስጥ የሃይል ባለቤት ከሆኑ፤ መንግስት ከመሰረቱ በኋላ ነውና፡-ይህችን እውነታ ኢብን ከሲር የቁርአን ማብራሪያ ቅጽ1 ገጽ 678 (በአረብኛ በተጻፈው) ላይ በግልጽ ተቀምጣል
“በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቀጥተኛው ጎዳና ከጠማማው ፍኖት በሚገባ ተገልጿል፡፡›(ሱረቱ አል-በቀራህ ምዕ.2 ቁ.256)
እስልምና በያዘው እውነት ይተማመናል፡፡ ሰዎችን ለማሳመን ተፈጥሯዊ ጥንካሬው በቂ ነው፡፡ ሐይል አያስፈልገውም ፡፡ ደግሞስ በሃይል ያመነ እምነቱ ትክክል ሊሆን ይችላልን? እስልምና በዚህ ረገድ ያለው አቋም ግልጽና የማያሻማ ፤ ከጊዜና ከቦታ ጋር የማይቀያየር ቋሚ መርህ ነው፡፡ ይኸውም፡-‹‹በሃይማት ማስገደድ የለም ፡፡›› ፤‹‹የፈለገ ይመን፡፡የፈለገ ይካድ፡፡›› የሚል ነው፡፡
ሙስሊሞች መዲና ውስጥ በሰላም የሚኖሩበት ቦታ ማግየታቸው ለመካውያን አልተዋጠላቸው፡፡ ስደተኛችን ለማስመለስ ወደ ሐባሻ ልዑክ ልከው ሳይሳካቸው ቀረ፡፡ መዲናውያንንም ‹‹መሐመድን ከአገር አስወጡ፤ ካልሆነ ግን ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቃችኋል፡፡›› በማለት አስፈራሩ፡፡ የንግድ ማእቀብም ጣሉባቸው፡፡ የተቀደሰውንም የካእባ መስጊድ እንዳይጎበኙም አገዳቸው፡፡በጦርነትም ዛቱባቸው፡፡መዲና ድረስ ሰርገው በመግባትም ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወታቸው ውስጥ ከ13 ያላነሱ የግድያ ሙከራዎች ተደርጎባቸዋል፡፡ መዲና ፍርሃት ነገሰ ፡፡ ወጥቶ መግባት አሳሳቢ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ሊያጠቃ የመጣ ጠላት የመከላከል ፍቃድ ተሰጠ፡፡ ተከታዩ የቁርአን አንቀጽ ተላለፈ፡-
“እነዚያ (በከሓዲያን)ጦርነት የታወጀባቸው፤ ግፍ ተፈጽሞባቸዋልና፤ እንዲዋጉ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አላህም እነርሱን ለመርዳት (ከማንም በላይ) ቻይ ነው፡፡(እርሱም)ያ “ጌታችን አላህ ነው፡፡” በማለታቸው ብቻ ከየቀያቸው የተባረሩ ናቸው፡፡አላህ(የ) አንድን ሕዝብ (ተንኮል) በሌላ ሕዝብ ባይመክት ኖሮ ገዳማት፤ ቤተክርስቲያኖች፤ ምኩራቦች እና የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶች በፈራረሱ ነበር፡፡” (ሱረቱ አል-ሐጅ ምዕ.22 ቁ.39-40) ምኩራቦች ማለት የአይሁድ ቤተ ጸሎት ማለት ነው)
የፈቃዱ አላማ በዚህ በተከበረው የቁርአን አንቀጽ እንደተመለከተው ያልሰለሙትን በሃይል ማስለም ሳይሆን የሙስሊሞችን እና የሁሉንም ሃይማኖቶች የእምነት ተቋማት የእምነት ነጻነት ማስከበር እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
ከዚህ ፍቃድ በኋላ ሙስሊሞች ፋታ የማይሰጡ ተከታታይ ጦርነቶችን አስተናገዱ፡፡ ከውጭ መካውያን፤ የአረብ ዘላኖችና ሮሞች፤ ከውስጥ ደግሞ አይሁዶችና ሙናፊቆች ሊያጠፏቸው ተረባረቡ፡፡ ይሁንና ይህን ሁሉ ተቋቁመው በአሸናፊነት በመወጣት የመኖር መብታቸውን አረጋገጡ፡፡
ሙስሊሞች ተገደው በገቡባቸው በነዚህ ጦርነቶች ውስጥ የሙታን አሐዝ 756 ብቻ መሆኑ ሰብአዊ ኪሳራ እንዳይደርስ ምን ያህል ይጠነቀቁ እንደነበር ረጋግጣል፡፡ ዝርዝሩን እነሆ፡-
የጦርነቱ ስም የሙስሊም ሰማእታት ቁጥር የሌሎች ሙታን ቁጥር
በበድር -------------------- 14 ------------------ 70
ኡሁድ------------------- 70 ---------------- 22
አህዛብ ------------------ 6 ----------------------- 3
በኒ ሙስጠሊቃ --------- 0 -------------------------3
ኸይበር-------------------19 ----------------------- 0
ቢእር መዑናህ -----------69 --------------------- 0
ሙእታህ -----------------14 --------------------- 14
ሁነይን------------------- 4 ------------------------71
ጧኢፍ ------------------- 13------------------------ 0
ሌሎች -------------------- 118 ------------------ 250
ድምር --------------------- 317 ------------------- 439
አጠቃላይ ድምር 756


ይህ አሃዝ የእስልምናን ሰይፍ ተረት ይበልጥ ያጋልጣል፡፡ ጦርነት አልተካሄደም ማለት ይቻላል፡፡ ወይም ደግሞ ሰብአዊ ኪሳራ አለም አይታው በማታውቅ ሁኔታ ኢምንት ነበር፡፡የኢስላም የመቻቻል ፖሊስ ልእልናና የሙስሊሞችን አብሮ የመኖር ድንቅ ባህል በጉልህ ማየትና ማወቅ የፈለገ በረዥሙ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሌሎች ሃይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በተጻራሪዎቻቸው ላይ የፈጸሙት ግፍ ማንበብ ይኖርበታል ፡፡ ለናሙና ያህል እነሆ፡-
በመነሻዋ አከባቢ ከፍተኛ መሳደድና እንግልት በደረሰባት ጊዜ ወደ ሰላምና ፍቅር ትጣራ የነበረችው ክርስትና ከስልጣን ኮርቻ ላይ እንደወጣችና መንግስት እንዳቋቋመች ብዙም ሳትቆይ ነው ተቃዋሚዎቿን ማሳደድና መጨፍጨፍ የጀመረችው፡፡ ሊገልጹት የሚዘገንን እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋም ፈጽማለች፡፡
ፕሮፌሰር ሙሐመድ አብዶህ ‹‹ኢስላምና ክርስትና›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ የሚከተለውን አውሰተዋል፡-
“የስፔን ቤተክርስቲያን የኢብን ሩሽድ ፍልስፍናና አስተሳሰብ በተለይም በአይሁድ ማህበረሰብ ዘንድ በመስፋፋቱ በጣም ተቆጣች፡፡ እና በአይሁድና በሙስሊሞች ላይ የመከራ መዓት አወረደች፡፡ ክርስትና ያልተቀበለ አይሁድ ሁሉ ከሐገር እንዲወጣ ፈረደች፡፡ ቤት ንብረቱን መሸጥ እንደሚችል እና ወርቅ እና ብር ግን ይዞ መውጣት እንደማይቻል፤ በሸቀጥ መልክ ብቻ ይዞ መውጣት እንደሚፈቀድለት ደነገገች፡፡ አይሁዶች በዚህ መልኩ ቤት ንብረታቸውን ትተው ነፍስ አውጪኝ ብለው ፈረጠጡ፡፡ ለዘር አልተረፉም፡፡ ድህነት ረሃብና ችግር፤ እንዲሁም የጉዞ እንግልት ጨረሳቸው፡፡
በ1025 ‹‹የአምላክ ጠላት›› የምትላቸው ሙስሊሞች ክርስትናን ካልተቀበሉ አገር ለቀው እንዲወጡ ቤተክርስቲያን ፈረደች፡፡ የሚሄዱትም አቅጣጫ ወደ ኢስላም ሐገር የሚያደርስ መሆን እንደሌለበትና ይህንን ውሳኔ የተላለፈ በሞት እንደሚቀጣ በየነች ፡፡(ኢስላምና ክርስትና በኢማም ሙሐመድ አብዶህ ገጽ 36-34)
የቤተክርስቲያን ዱላ የተሰነዘረው ወደ ጣኦታውያንና ከርሷ የተለየ እምነት ወዳላቸው ወገኖች ብቻ አልነበረም፡፡ ቤተክርስቲያናን መንግስት ከሚያራምዱት የክርስትና አስተሳሰብ የተለዩ የክርስቲያን አንጃዎች የዚህ ግፍ ቀማሽ ሆነዋል፡፡

የክርስታን ታሪክ ያነበበ በግብጻዊው የሃይማኖት ሊቅ በአርዮስና በተከታዮቹ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አሳምሮ ያውቃል፡፡በወቅቱ የኒቂያ ጉባኤ 325 (እ.ኤ.አ) የእየሱስን አምላክነት መቃወማቸው ከጉባኤው አባላት ዘንድ ተቃውሞ አስነሳ፡፡ እርሱና ተከታዮቹ ብዙሐን ቢሆኑም ከጉባኤው እንዲባረሩ ተደረጉ፡፡ አርዮስ እንዲወገዝና መጽሐፎቹ እንዲቃጠሉ፤ ደጋፊዎቹ ከየትኛውም የስራ መስክ እንዲወገዱና ከሐገር እንዲወጡ፤ የአርዮስ መጽሐፍ ይዞ የተገኘ ወይም አስተሳሰቡን የደገፈ ሁሉ እንዲገደል ጉባኤው ወሰነ፡፡ የእየሱስን አምላክነት በመቃወም ወደ አንድ አምላክ ጥሪ የነበሩ ክርስቲያን አንጃዎች በደረሰባቸው መሳደድና እና ጭፍጨፋ ምክኒያት ከክርስቲያኑ ማሕበረሰብ ሙሉ በሙሉ ጠፉ፡፡ አስተሳሰባቸውም ሙሉ በሙሉ ከሰመ፡፡

በአውሮፓ የፕሮቴስታንት እምነት በሉተር እና በሌሎች ይፋ በሆነ ጊዜ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ያላትን ሐይል ሁሉ ተጠቅማ ይህንን እምነት በብርቱ ተቃወመች፡፡ የሰው ልጅ አይቶት የማያውቀውን እጅግ አሰቃቂ የጭፍጨፋና የማሳደደድ ክስተት ተፈጸመ፡፡ የፓሪስ ጭፍጨፋ (ኦገስት 24 ቀን 1572) በዋነኝነት ይጠቀሳል፡፡ ይሀውም ካቶሊኮች ፕሮቴስታንቶችን ልዩነቶቻችንን እናቀራርብ በማለት እንግድነት በፓሪስ ጠሯቸው፡፡(ይህ ታሪክ ታውቀዋለህ የሚል ግምት አለኝ)አስተናጋጆቹ ሌሊት ላይ እንግዶቻቸው በተኙበት በሽፍጥ አረዷቸው፡፡ ሲነጋ የፓሪስ አውራ ጎዳናዎች በሺዎች በሚቆጠሩ ፕሮቴስታንቶች ደም ተሞልቶ ነበር፡፡ ቻርለስ ዘጠነኛ ለፈጸመው ለዚህ ‹‹ታላቅ ጀብዱ›› ከካቶሊክ ጳጳስ ከንጉሳንና ከታላላቅ ሰዎች የምስጋና መዓት ተላከለት፡፡
የሚገርመው ፕሮቴስታንቶችም ጉልበት ባገኙ ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ ካቶሊኮችን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ጨፍጭፈዋቸዋል፡፡(ክርስትና በዶክተር አህመድ ሸለቢ)

ሉተር ለተከታዮቹ፡- ‹ካናንተ መካከል የቻለ ይግደል፤ ይነቅ ፤ ይረድ፡፡ እነዚህ አመጸኛ ገበሬዎች (ካቶሊኮችን) የምትችሉትን ያህል በሚስጥርም በይፋም ግደሉ፡፡ እነቁ፤ እረዱ፡፡›› የሚል ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ (አይዲዮሎጂያ አልኢንቂላብ ገጽ71)
በአውሮፓ የተከሰተው የሃይማኖት ጦርነት በየትኛውም ዓለም ያልታዩ እጅግ ዘግናኝ ክስተቶች ያቆረ መሆኑ የሚገርም አይደለም፡፡ ‹‹ፊያርክ›› እንዳወሳው ይህ የሃይማኖት ጦርነት አብዛኛው የጀርመን ህዝብ በረሃብና በግድያ እንዲያልቅ አድርጓል፡፡ አብዛያዎቹ ያደጉ ከተሞች በዚህ ጦርነት ጦስ ተቃጥለው ወደ አመድነት ተለውጠዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተቀናቃኝ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ጦርነት ከመክፈት ተቆጥባ አታውቅም ፡፡ አቅሙ ካላት ተቀናቃኞቻን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ትሞክራለች፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ተገንጥለው የወጡ አንጃዎች ይሀው ባህሪ ታይቶባቸዋል፡፡ ከነርሱ ውጭ ያለውን ለማጥፋት ጦር ሰብቀዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን መንታ ጦርነቶችን ታካሄድ ነበር፡፡ አንደኛው ወደ ውጭ ሲሆን፤ በጣኦታውያን ላይ የተከፈተ ነው፡፡ ሁለተኛው ውስጣዊ ሲሆን በቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ አፈንግጠዋል ተብለው በሚታመኑ ክርስቲያኖች ላይ የታወጀ ነው፡፡ በመጀመሪያዎቹ ላይ ከምድረ ገጽ የማጥፋት የመስቀል ጦርነት አዘመተች ፡፡ ለሁለተኛዎቹ ደግሞ ‹‹ፍርድ ቤት›› በማቋቋም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ ያፈነገጡ ክርስቲያኖች በእሳት ተቃጥለው እንዲገደሉ አደረገች፡፡ጥፋቱን ያመነ ፤የተጸጸተና የተመለሰ ደግሞ እድሜ ይፍታህ እስር ይበየንበታል፡፡ የከሃዲ ንብረት እስከ ልጅ ልጁ ይቀማል ፡፡ ማእቀብም ይጣልባቸዋል፡፡ አባታቸውን ወይም ሌላ ከሃዲ እስካላጋለጡ ድረስም ለየትኛውም ሐላፊነተ ብቁ አይሆንም ፡፡ ቅጣቱ በየትኛውም መልኩ ለከሃዲ እገዛ የሰጠን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡(ተረት ተረት ይመስላል አይደል ግን አለማችን ያስተናገደችው ታሪክ ጽፎ ያስቀመጠው እውነታ ነው)
“የነዚህ ፍርድ ቤቶች ጭካኔ እጅግ ከመበርታቱና ከመስፋቱ የተነሳ የዚያን ዘመን ሰዎች፡- ‹‹አንድ ሰው ክርስቲያን ሆኖ በአልጋ ላይ ሰላማዊ ሞት መሞቱ ሐሰት ነው፡፡›› ይሉ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቶች ከተቋቋሚበት ከ1481 ጀምሮ እስከ 1808 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በ340 ሺህ ሰዎች ላይ ቅጣት በይነዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 200ሺህ ያህሉ በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል፡፡ (አይዲዮሎጂያ አል-ኢንቂላብ ገጽ71))
ይህ ድርጊት ለክርስትና እምነት አዲስ አይደለም፡፡ ክርስትና በመጀመሪያ ዘመኑም የተስፋፋው በሰይፍ ነው፡፡ ብሪፎልት እንደገለጸው ክርስትና በስልጣን ጊዜው በአውሮፓ የገደላቸው ሰዎች ብዛት ከሰባት ሚሊዮን እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን(ከ7,,000,000-15,000,000) ይደርሳል ፡፡( አልኢስላም ወነስራኒያህ በፕሮፌሰር ሙሐመድ አብዶ)
በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የእንጊሊዝ ካቶሊካዊት ንግስት የነበረችው ሜሪ ይህንን ሐሳብ እንዲህ ስትል ገልጻለች፡- “የከሃዲያን ነፍስ በገሃነም ውስጥ ዝንተ ዓለም ስትቃጠል የምትኖር እንደመሆኗ በምድር ላይም እነርሱን በማቃጠል መለኮታዊውን የብቀላ ስልት ከመከተል የበለጠ ህጋዊ ስልት የለም፡፡”((አይዲዮሎጂያ አልኢንቂላብ ገጽ714)
ሰለጠነ በሚባለው ዘመናዊው አለም ውስጥ በክርስቲያን አውሮፓ የተፈጸሙ ግፎችና የተደረጉ ኢ-ሰብአዊ ጦርነቶች እጅግ ይዘገንናሉ ፡፡ በሁለተኛ የአለም ጦርነት ብቻ ከ50 ሚሊዮን ያላነሱ ሰዎች በግፍ ተገድለዋል፡፡ በአንደኛ የአለም ጦርነትም እንደዚሁ ሚሊየኖች ረግፈዋል፡፡ እስታሊን በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን 3 ሚሊዮን ያህል ዜጎችን ጨፍጭፏል፡፡ ባሳለፍነው ክፍለ ዘመን በክርስቲያን አውሮፓ የግፍ ጦርነቶች ያለቁ ሰዎች ቁጥር 165 ሚሊዮን ደርሷል፡፡
ወደ ሃገራችን ታሪክ ስንመጣ እውነታው ኢስላም በሰይፍ ተረት ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ ሙስሊሞች ሰይፍ ተመዘዘባቸው እንጂ ሰይፍ አልመዘዙም ፡፡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በሌሎች የክርስትና አንጃዎችና በሙስሊሞች ላይ የፈጸመችው አይነት ግፍ የሃገራችን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፈጽማለች ፡፡ ከይኩኖ አምላክ (1270) እስከ ሐይለ ስላሴ (1974) ድረስ የነበሩ የክርስቲያን ነገስታት በቤተ ክርስቲያን ሙሉ ድጋፍ ሙስሊሞችን ለማጥመቅ የፈጸሟቸውን ወንጀሎች ታሪክ አይረሳቸውም፡፡ ኢስላም በሃገራችን ይህን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ መስፋፋት የቻለው ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህም ኢስላም በሰይፍ የሚለው ተረት ታሪካዊ መነሻ የሌለው ተራ ክስ ከመሆኑን አያልፍም፡፡ ተረቱን የሚያስፋፉት ኦሬንታሊስቶችና የክርሰትያን ሚሽነሪዎች በእስልምና ላይ ጣታቸውን ለመቀሰር የሚያስችል የሞራልም የመረጃም ጉልበት የላቸውም፡፡

ከላይ ከተሰጣው ማብራሪያ እንደምንረዳው የኢስላም መሰረታዊ መርህ እና መመሪያ፡- ‹‹በሐይማኖት ማስገደድ የለም›› የሚለው ሲሆን፤ የሰውን ልጅ ያሻውን ሃይማኖት ሐይማኖት የመምረጥ ነጻነት የሚጋፉ ወገኖች ግን በዝምታ መመልከት አልመረጠም ‹‹ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጥ›› የሚለው ሰበካ ሁሌም ሊሰራ አይችልም፡፡ ቁንጥጫ እንጂ የማይመልሰው ጋጠወጥ በየዘመኑ ምን ገዜም አይጠፋም፡፡ እናም አደብ የሚገዙበትንና የሰዎችን የእምነትና የማሰብ ነጻነት ብልሃት ዘይዷል፡፡ ‹‹ተጋደለዋቸው›› የሚል ትእዛዝ የተላለፈው እነዚህ ጸረ ነጻነቶች በተመለከተ ሲሆን ዓላማው እንዲሰልሙ ማስገደድ ሳይሆንየእምነት ነጻነት መጋፋታቸውን እንዲያቆሙ ጫና ማድረግ ነው፡፡ያኔ ካቆሙ ያሻቸውን ሐይማኖት የመከተል መበረታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹በሐይማኖት ማስገደድ የለም›› በሚለው መርህና ውጊያ አናቅጽ መካከል ግጭት የሚባል ነገር የለም ፡፡ በስተመጨረሻ ነገራቶች ግልጽ ይሆኑ ዘንድ የተወሰኑ ምሳሌዎችን ማንሳት ይጠቅመናል፡-
1) ስፔይንን ለ800 ዓመታት ሲያስተዳድር ህዝቡ ሀይማኖቱን እንዲቀይር በፍፁም አስገድደውት አያውቁም፡፡በኃላ ላይ ግን ክርስቲያን የመስቀል ጦረኖች በሰይፍ ካባረሯቸው በኃላ አንድም ሙስሊም በግልጽ የሰላት ጥሪ /አዛን/ ለማድረግ አልደፈረም፡፡ ሌላም ምሳሌ መጨመር ይቻላል፡- ሙስሊሞች ለ1400 ዓመታት አረቢያን በበላይነት ይዘው ቆይተዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት እንግሊዞችና ፈረንሳዮች አረቢያን ለመግዛት ቢችሉም ከሞላ ጐደል ለ1400 ዓመታት በአረቦች ቁጥጥር ስር ያለ ቦታ ነበር፡፡ ሙስሊሞች ይህንን ያህል ጊዜ የአረቢያን ምድር ቢቆጣጠሩም ግን በአሁኑ ሰዓት 14 ሚሊዮን ከዘር ማንዘራቸዉ ክርስቲያኖች የነበሩ አረቦች ይገኛሉ፡፡ እውነት እንደሚወራው ሙስሊሞች ሀይማኖታቸውን ለማስፋፋት ሰይፍና ኃይል ተጠቅመው ቢሆን ኖሮ ዛሬ በአረብ ምድር አንድም ክርስቲያን ባልተገኘ ነበር፡፡ ደግሞ ሌለም ብናክል ሙስሊሞች ህንድን ለ1000 ዓመታት ያህል አስተዳድረዋል፡፡ ነገር ግን 20 በመቶው የህንድ ህዝብ ብቻ ነው ሙስሊም የሆነው፡፡ በርግጥ ሙስሊሞች በኃይልና በሰይፍ ሀይማኖቱን በማስፋፋት የሚያምኑ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ዛሬ በህንድ ምድር የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ባልተገኘ ነበር፡፡ ሰለዚህ ህንዳውያን እስልምና በሰይፍ እንዳልተስፋፋ ለመግለጽ የሚችሉ ቋሚ ምስክሮች ናቸው፡፡
Finally An article in Reader’s Digest ‘Almanac’, year book 1986, gave the statistics of
the increase of percentage of the major religions of the world in half a century
from 1934 to 1984. This article also appeared in ‘The Plain Truth’ magazine. At
the top was Islam, which increased by 235%, and Christianity had increased
only by 47%. May one ask, which war took place in this century which converted
millions of people to Islam?"
ሪደርስ ዳይጀስት አልማናክ ይር ቡክ" በ1986 የወጣው "የዓለማችን ዋና ዋና ሀይማኖቶች እድገት" በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ ይዞ ነበር፡፡ ይኸው ጽሑፍ ኘሌን ትሩዝ በሚል መጽሐፍ ውስጥም ወጥቶ ነበር፡፡ እንደ መጽሐፍ ከሆነ በተጠቀሱት 50 ዓመታት ውስጥ ከዓለማችን ዋና ዋና ሀይማኖቶች ውስጥ በመቶኛ ከፍተኛውን ጭማሪ ያስመዘገበው እስልምና ነው፡፡ በተጠቀሰው ዓመት ክርስትና 47 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ እስልምና ደግም 235 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ ነበር፡፡ ግልጽ በሆነ አማርኛ ሁለት እጥፍ ተኩል ገደማ መጨመር ማለት ነው፡፡ እስቲ ራስዎን ይጠይቁ፡፡ ከ1934 ጀምሮ የትኛው የሙስሊም ስራዊት ነው፡፡ ይህንን ያህል ሰው ወደእስልምና ያስገባው ?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests