የስላሴ ጽንሰ ሐሳብ ከየት መጣ ????

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የስላሴ ጽንሰ ሐሳብ ከየት መጣ ????

Postby መርፊው » Fri Jan 03, 2014 7:39 pm

*^* የሶስትዮሽ (የስላሴ)ጽንሰ ሃሳብ ከየት መጣ? *^*

** የሶስትዮሽ ጽንሰ ሃሳብ (Concept of Trinity )በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› በየትኛውም ምዕራፍ የማይገኝ ሲሆን ከየት መጣ ለሚለው የእምነቱ ተከታዮች እራሳቸው በቂ መረጃ ያለው መልስ የላቸውም(አለን የምትሉ ከሆነ ደግሞ ይህው በሩ ክፍት ነው…..) በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› አንድም ቦታ ነብያቶች ሆኑ አምላክ የተባለው እየሱስ ክርስቶስ(ሰላም በሱ ላይ ይሁንና) እንዲሁም ሃዋሪያቶች ማናቸውም ስለ ሶስትዮሽ ያስተማሩት አንድም ትምህርት የለም በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› በየትኛውም ጥቅስ የሦስትዮሽ ጽንሰ ሃሳብ አልተጻፈም ይልቁንም የፈጣሪ አንድነት ነው በሰፊው የተነገረው የሶስትዮሽ ጽንሰ ሃሳብ በአንዳንድ ጸሐፊዎች ከየት እንደመጣ ሲገለጽ በመጀመሪያ የተመሰረተው አቴናሲዮስ /Athanasius/ በሚባል የአሌክሳንድሪያ ጳጳስ በ325 ዓ.ል ሲሆን እራሱም ቢሆን ስለ ስላሴ ሲያስረዳ ‹‹ጽንሰ ሃሳቡን በጻፍኩት ቁጥር ሃሳቡን ለማስረዳት ያለኝ አቅም በጣም አናሳ ይሆናል›› ብሎ ጽንሰ ሀሳቡ ለማመን የሚቸግር መሆኑን አምኗል፡፡ በዚያን ግዜም ቢሆን አብና ወልድን ብቻ በመግለጽ ነበር፡፡ ይህንንም ወልድን ከአብ ጋር እኩል የማድረግ ፅንሰ ሀሳብ 300 ጳጳሳት በተሰበሰቡበት የኒቄያ ጉባኤ ላ በድምጽ ብልጫ ተወሰነ ይህ ሀሳብ በአንድ ጳጳስ እስከሚጸድቅበት ጊዜ ቤተክርስቲያንኖችም ሆኑ የሀይማኖቱ ተከታዮች በአንድ እግዚአብሔር ብቻ ነበር የሚያምኑት ፡፡ ይህም ማለት ሃይማት የሚያህል ነገር አብና ወልድ አንድ ናቸው በሚል በአንድ ጳጳስ የቀረበ ሃሳብ የክርስትና እምነት እስከ 325 ዓ.ል ድረስ በአንድ አብ የሚያምነው እምነት በ300 ጳጳሳት ውሳኔ በመነሳት የፈጣሪ ቃል ሳይሆን የእምነቱ አካል ተደረገ፡፡ በመቀጠልም በ381 ዓ.ል ከ56 ዓመታት በኋላ መንፈስ ቅዱስመረ አንደ የአምልኮ አካል እንደሆነና ሶስቱ እንደ አንድ እንደሆኑ በቆስጠንጢያንው ጉባኤ ፀደቀ ፡፡ እንግዲህ የሶስትዮሽ ጽንሰ ሀሳብና አምልኮ የመጣው በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው፡፡ ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በሚለው መጽሃፋቸው ይህን እውነታ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠዋል፡-
‹‹የኒቅያው [nicea} ጉባኤ በ325 ዓ.ም ታሪካዊውን አስተምሮ-ሥላሴን አፀደቀ፡፡በዚህም መሰረት ክርስቶስ ከአብ ጋር የባህሪ እኩልነት ያለው መሆኑ ግንዛቤ አገኘ፡፡›› ሲሉ ጽፈዋል (ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ ፤1993 አዲስ አበባ ገጽ-13

ቀጠሉና

“በአርዮስ ትምህርት የተነሳ የተፈጠረው ውዝግብ ለመፍታት በ325 ዓ.ም ኒቂያ በተባለው ስፍራ አንድ ጉባኤ ተካሄደ፡፡በጉባኤው ላይ 300 ጳጳሳት ተገኝተው ነበር፡፡ጉባኤው አርዮስንም ሆነ አርዮሳዊነትን የሚቀበሉትን ሁሉ አውግዟል፡፡ በንጉሱ ካስፀደቀ በኋላም የሚከተለውን መግለጫ አወጣ፡- “ሁሉም በሚችል፤ የማይታየውንና የሚታኘውን በፈጠረ፤ በአንድ አምላ በእግዚአብሔር እናምናለን ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በአንዱ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ፤ ከአብ ብቻውን በተገኘው ከአብ መገኛው (“ኡሲያስ”/ousias) አንድ በሆነው፤ ከአምላክ በተገኘው አምላክ፤ በብርሃ በተገኘው ብርሃ፤ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘው እውነተኛ አምላክ፤ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፤ ከአብ ጋር በማንነት (homoousion) አንድ በሆነው፤ ሁሉ በእርሱ በሆነ፤ በሰማይም ሆነ በምድር ባለው፤ ለእኛ ለሰው ልጆች ደህነት ወርዶ ስጋ በሆነ፤ ሰውም በሆነ፤ መከራን በተቀበለበት በሶስተኛውም ቀን በተነሳ፤ ወደ ሰማይ ባረገ፤ በሙታንና በህያዋን ላይ ሊፈርድ በሚመጣው እናምናለን፡፡( ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ ፤1993 አዲስ አበባ ገጽ-33-34

** መቼም እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ ያስነሳል- በኒቂያ ጉባኤ መሰረት “ክርስቶስ ከአብ ጋር የባህሪ እኩልነት ያለው መሆኑ” ግንዛቤ ሳያገኝ በፊት ቤተ ክርስቲያን የስላሴን እምነት ሳይሆን የአንድን አምላክ ኃያልነትና ብቸኝነት ስታስተምር ተሳስታ ነበርን? ከኒቂያ ጉባኤ በፊት የነበሩ አማኞችና ሐዋሪያትና የእየሱስ ባህሪያት ከአብ ጋር መስተካከል ሳይረዱትና ግንዛቤውን ሳያገኙ ቆየረተው በኒቂያ ጉባኤ ተገኝተው በድምጽ ብልጫ የወሰኑት 300 ጳጳሳት ግንዛቤውን አገኙን? እምነት የሚጸድቀው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በጉባኤ ነው ወይስ በአምላክ ትዕዛዝ? ይህስ ትክክለኛ አካሄድ ነውን?

** ከላይ እንደተገለጸው ይህ የኒቅያ ጉባኤ እራሱ “በእግዚአብሔር አብ እናምናለን እንጂ አንድ እግዚአብሔር በሚሆኑት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እንደማይል እናስተውልን?
“በኒቅያ ጉባኤ የሃይማኖት መግለጫ ውስጥ ከስላሴ አካላት የአንዱ መንፈስ ቅዱስ አስተምሮ በግልጥ አልተቀመጠም፡፡ መግለጫው ያረጋገጠው “በመንፍ ቅዱስ እናምናለን” የሚለው ብቻ ነበር ፡፡ “የቆስጠንጢያው ጉባኤ በ381 ዓ.ም “ጌታ በሆነና ሕይወት በሚሰጥ፤ ከአብ በሚወጣና ከአብና ከወልድ እኩል አምልኮን በሚቀበል፤ በነብያትም በተነገረ መንፈስ ቅዱስ እናምናለን” የሚለውን መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግለጫው መንፈስ ቅዱስ በህልውና ከወልድና ከአብ ያነሰ ሳይሆን እኩል መሆኑን በፅኑ አረጋግጧል፡፡” ይላል (ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ ፤1993 አዲስ አበባ ገጽ-34፡፡
ታዲያ መንፈስ ቅዱስም እንደ ወልድ ከአብ የሚወጣ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም የፈጣሪ ልጅ ነውን? ካልሆነ ለምን?
መጽሐፍ‹‹ቅዱስ›› እንዲህ ይላል ፡- ኢሳያስ 46፡9 ላይ “እኔ አምላክ ነኝና ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስብ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፡፡” ይላል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን አሃዳዊን እምነት ወይስ ከኒቂያ ጉባኤ በኃላ የመጣውን የስላሴ አስተምሮ እንቀበል? “ ጥቅሱ ግን የጥንቱን ነገር አስብ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፡፡” ነው የሚለው፡፡

^*^ በጣም የሚገርመው በመጽሐፍ‹‹ቅዱስ›› አንድም ቦታ ያልተገለጸው ሦስትዮሽ በተከበረው ቁርአን በበርካታ ቦታዎች ተጠቅሷል፡- ሁለቱን እንመልከት

‹‹እነዚያ አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው(ከሶስት አማልክት አንዱ ነው) ያሉ በእርግጥ ካዱ አምላክም አንድ አምላክ እንጂ ሌላ የለም ከሚሉት ነገር ባይከለከሉ እነዚያ የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡›› (ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፡73)

‹‹ እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « (አማልክት) ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡
(ሱረቱ አል-ኒሳዕ 4፡171)

** ስላሴ የተባለውን ጽንሰ ሀሳብ ለመረዳት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ጥርጣሬ ሃሳብ በምንም ዓይነት እርስ በእርሱ የማይጣጣምና የሚጋጭ ከመሆኑም በላይ ማንም ሊረዳው የማይችል ሀሳብ ነው፡፡ይህንንም ሃይማnoት ምንድነው? (What is Religion?) በሚል በሊዩ ቶልስቶይ /Leo Tosloy/ በተጻፈው ጽሁፍ ላይ *‹‹አንድ ሰው በአፉ አምላክ አንድም ሶስትም መሆኑን አምናልሁ ሊል ይችላል ነገር ግን ይህንን ማም ሊያምን አይችልም ምክኒያቱም ቃሉ በራሱ ምንም ስሜት አይሰጥም›› * ሲል ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪ በኤች. ኤ. ዋሽንግተን /H.A Washington/ /Jefferson’s Works/ በሚለው መጽሐፍ ገጽ 269-70 ላይ እንዲህ ይላል፡-

*^*‹‹የሦስትዮሽ እምነት ሶስት አንድ አንድ ሶስት የሚለው ሀሳብ ለሰው ልጅ አዕምሮ ከባድና የማይገባ በደፈናው ወደ መረዳት የሚመራ ሀሳብ ነው፡፡ ማንም ኖርማል ሰው የማይረዳው ምንም ዓይነት መልስ የማያገኝለት ሀሳብ ነው፡፡ ለነገሩ እንዴት መልስ ይገኛል መረጃ ለሌለውና ጠንካራ ሀሳብ ያልያዘ ነገር እንዴት መረዳት ይቻላል? ይህ የሶስትዮሽ ጽንሰ ሀሳብ ገብቶኛል የሚል ሰው ቢኖር እንኳ እራሱን እያታለለለ መሆን አለበት›› *^* ሲል ተጠቅሷል፡፡ ሌሎችም በርካታ አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን ሁለቱ ለናሙና ያህል በቂ ይሆናል በማለት ነው፡፡የዚህና መሰል አስተያየቶች የተዘነዘሩት ሙስሊም ካልሆነ አካለት መሆኑ ደግሞ ግርምት የስጭራል

በሌላ በኩል የፈጣሪ አንድነት በርካታ ሃይማቶች የሚጋሩት ሃሳብ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ በራሱ የፈጣሪ አንድነት በርካታ ቦታዎች ላይ ተጠቅሶ ይገኛል ፡፡ የተለያ ሃይማቶች በተለይም የአይሁድና የክርስትና ሃይማት መመሪያዎች ይበልጥ የአንድ አምላን አስተምሮ እንደሚያስተምሩ አላህ(ሱ.ወ)በተከበረው ቁርአን ላይ እንዲህ በማለት ይገልጻል፡- ‹‹ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ ››(ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡64)

*^* ኢየሱስ አምላክ ወይስ መልዕክተኛ?*^*
ይቀጥላል………………
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests