ጦርነት በመጽሀፈ ቅዱስ !!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ጦርነት በመጽሀፈ ቅዱስ !!!

Postby መርፊው » Mon Jan 06, 2014 10:42 pm

ጦርነት በቅዱስ ቁርአንና በመጽሐፍ ቅዱስ
**«የቃልኪዳኗ» መሬት የሆኑትን ከተሞች የመውረርና የመክበብ መርሆች

** በኦሪት ዘዳግም ምዕ.20 ከቁ.16-18 ላይ «የቃል ኪዳን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ውስጥ በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የሚደረገውን ወረራ አስመልክቶ የሚከናወነው ድርጊት እንደሚከተለው እናነባለን፡-«
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ከሚሰጥህ ከእነዚህ አሕዛብ ከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም።
ነገር ግን ለአማልክቶቻቸው ያደረጉትን ርኵሰት ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እንዳያስተምሩአችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት እንዳትሠሩ፥ አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዘዘህ ኬጢያዊውን አሞራዊውንም ከነዓናዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈጽመህ ታጠፋቸዋለህ።»
ከላይ የጠቀስነው ስድስት የብሄር/የህዝብ አይነቶች በጥቅሱ ውስጥ በተገለጸው መልኩ ዘራቸው ከምድረ-ገጽ እንዲጠፋ ከእግዚአብሔር ተወስኖባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል ከላይ እንደተጠቀሰው ዓይነት ህዝቦች የእርቅ ወይም የግብር ጥሪ አይቀርብላቸውም የሚቀርብላቸው አንድ ነገር ብቻ ነው *ሰይፍ*፡፡ ከሰይፍ ሌላ አማራጭ፤ ከመገደል ሌላ ምርጫ፤ ከውድመት ውጭ ሌላ ነገር በአማርጭነት አይቀርብላቸውም፡፡ የሚጠብቃቸው መጥፋት ብቻ ነው፡፡

** እነዚህን ህዝቦች ለመገደልና ለመውደም ፍርደ ገምድላዊ ውሳኔ እንዲበቁ ያደረጋቸው አንዳችም ወንጀል ፈጽመው አይደለም፡፡ ያደረጉት ነገር ቢኖር ከኦሪታዊያኑ በፊት «የቃል-ኪዳን መሬት» በሚሉት አከባቢ ተረጋግተው በሰላም መኖራቸው ብቻ ነው፡፡
የኦሪት አንቀጾች በማብራራት ተግባር ላይ የተሰማሩ ተንታኞች ይህንን አንቀጽ አስመልክትው ቀጣዩን ገለፃ እንዲህ በማለት ያደርጋሉ..«በተጠቀሰው የአህዛብ ከተማዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች በዘህ መልኩ እንዲወድሙ አምላክ ሊያዝ የቻለው፡- የእስራኤላውያን ደህነት ከጣኦት አምላኪን ለመጠበቅና ለማጽዳት ሲል ነው፡፡ እርግጥ ነው እስራኤላውያን በእነዚህ ክፉ ህዝቦች ላይ እንዲፈጽሙት አምላካቸው ያዘዛቸውን ነገር በተፈገው መልኩ አልተገበሩም፡፡ እንዲያጠፏቸው የታዘዙትን ህዝቦች በታዘዙት መልክ ከምድረ-ገጽ ላይ ቢያጠፏቸው ኑሮ፤ ይህ ሁሉ ስደት፡ መንከራተት፡ መሞትና መበታተን ባልገጠማቸው ነበር ፡፡»

**እንዲህ ያለውን ዘር የማጥፋት የወንጀል ተግባር የተጠቀሱት የመጽሐፍ ተንታኞች አሳፋሪ በሆነ መልኩ ሲደግፋት እናስተውላለን፡፡እንዲሁም የእስራኤላዊያኑ ሰይፍ ዘር የማጥፋቱን ወንጀል ሙሉ በሙሉና ‹‹በተሳካ›› መልኩ ባለመፈፀሙ ምክንያት ማዘናቸውን ገልፀዋል- ተንታኞቹ፡፡

እንግዲህ ቅዱስ ቁርአንና ኦሪት በጦርነት ወቅት የሚከተሉትን ህግና ሥርዓት በማነፃፀር ስልጡን የሆነው አካሄድ የትኛው እንደሆነ ብይኑን መሥጠት ለእናንተ ለውድ አንባቢያን የተተው ህሊናዊ የቤት ስራ ይሆናል፡፡

**ኦሪታዊያኑ ‹‹የቃል ኪዳኗ መሬት›› እያሉ በሚጠሯት ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ‹‹ፈፅመህ ታጠፋቸዋለህ ›› ‹‹ምንም ነፍስ አታድንም›› በሚሉት ትዕዛዛት መሠረት በህይወት የመኖር ዕድሉ ይነፍጋቸዋል፡፡

የክርስትና ሐይማኖት የሚከተሉት አውሮፓዊያን ወራሪዎች በሚሲዮናዊን መንገድ ጠራጊነትና በስመ ክርስትና ለቅኝ ገዥነት በተንቀሳቀሱ ጊዜ በሰሜን አሜሪካና በአውስትራሊያ የፈፀሙትን የዘር ማጥፋት ተግባር ማን ይዘነጋው ይሆን? እነዚህ ክርስቲያን ወራሪዎች በሰሜን አሜሪካ ይኖሩ የነበሩ ‹‹ቀይ ህንዶች›› የሚባሉትን ቀደምት ነዋሪዎች ያለ ርህራሄ አውድመዋቸዋል፡፡ በአንድ እጃቸው ወንጌልን በሌላኛው ደግሞ ሰይፍን አንግበው የመጡት እንግሊዛዊያንም እንዲሁ በአውስትራሊያ ቀደምት ነዋሪ የነበሩትን ‹‹አቦርጅኖች›› ለወሬ ነጋሪ ሊተርፍ በማይችል መልኩ አጥፍተዋቸዋል፡፡

***እነዚህ ወራሪዎች በተጠቀሱት ህዝቦች ላይ ይህ ነው ሊባል የማይችል ፍፅም ከሰባዊነት የወጣ ዘግናኝ ተግባር ፈፅመውባቸዋል፡፡ይህን የጥፋት ተግባር በወቅቱ የነበሩ ታዛቢዎች ‹‹አውሬያዊ ተግባር›› ብለው ሰይመውት ነበር፡፡ ተግባሩ ግን ከአውሬነት በላይ ነው፡፡ለምን ቢሉ አውሬ ለጥቅማ ጥቅም ብሎ በመሰሉ ላይ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ተግባር ሲፈጽም አልታየምና ነው፡፡አውሬ ከመሰሉ ውጭ ያለን እንስሳ ለምግብነት እንኳ ከፈለገው የሚበቃውን ያህል በልቶ ረሀቡ ሲታገስለት መብላቱን ያቆማል፡፡ የጠቀስናቸው ወራሪዎች ግን ግድያ የመግደል ረሃባቸውን አያስታግስላቸውም ፡፡የሰው ደም እንደጅረት ማፍሰስ የሰው ደም የመጠጣት መሰየም በእጅጉ ያንሳቸዋል፡፡

የተወሰኑ ብሔሮችን ከምድር-ገጽ የማስወገድና ዘር የማጥፋት እሳቤ የመነጨው ‹‹ቅዱስ›› እየተባለ ከሚጠራው መፅሐፍ ከ ‹‹ ኦሪት›› ነው፡፡ አይሁዳዊያንና ክርስቲያኖች ይህንኑ እሳቤ በዚሁ መፅሐፍ ተወራርሰውታል፡፡እንዲህ ያለው የጥፋት እሰቤ ግን በእስልምና ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው፡፡

**የዘር ማጥፋት እሳቤ ከቅዱስ ቁርአን አንፃር በጭራሽ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ለማወቅ በቁርአን ውስጥ የተገለፀውን የፈርኦን ታሪክ ማጤን ያስፈልጋል፡፡ፈርኦን የእስራኤል ዘሮችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በሚል እስራኤላዊ ወንዶችን አርዶ በመግደልና ሴቶችን ለባርነት በማስቀረት የሚያከናውነውን የጥፋት ተግባር ቁርአን ጥብቅ በሆነ አገላለጽ አውግዞታል፡፡ እንዲህ ይላል . . .‹‹ ፈርዐውን ምድር ላይ አምባገነን ሆነ፡፡ነዋሪዎችንም ከመካከላቸው ከፊሎቹን (በመጫንና) በማዳከም ወንዶች ልጆቻቸውን በማረድና ሴቶቻቸውን በመተው÷ (ወደ አንጃዎች) ከፋፈለ፡፡እርሱ ከበካዮች ነበርና፡፡›› (አል-ቀሶስ÷ 4)

እንዲህ ዓይነቱን ዘር የማጥፋት እኩይ እሳቤ እንኳንስ በሰው ዘር ላይ በእንስሳትም ላይ እንዲፈፀም የእስልምና አስተምህሮት ፈፅሞ የሚፈቅደው ነገር አይደለም፡፡እስልምና የትኛውም ዓይነት ምክንያት ቢቀርብ ዘር የማጥፋትን እሳቤ የሚያስተናግድበት ቦታ የለውም፡፡ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ውሻ ምንም እንኳ አስከፊ በሽታ የሚያስከትል እንስሳ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ መጥፋት እንደሌለበት ሲገልፅ . . ‹‹ውሾች እንደሌለው ፍጡራን ሁሉ ህያው ፍጥራን ባይሆኑ ኖሮ እንዲጠፋ አዛችሁ ነበር፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡

ውሻ ከሚያስከትለው ጥፋት አኳያ ከያለበት ተለቅሞ መወገድ የሚገባው እንስሳ ቢሆንም÷ ነቢዮ (ሰ.ዐ.ወ) ምልከታቸው እጅግ ጥልቅ ነበርና ይህን አላደረጉትም ፡፡ጉዳዩን በቁርአን መነፅር ተመልከቱት ፡፡ በቁርአን አገላለጽ ተንቀሳቃሽ የሆነ ህያው ፍጡር በሙሉ ‹‹ህዝብ›› በሚል ተጠርቷል ፡፡ማንኛውም ህያው ፍጡር የሚኖረው በህብረት ነው፡፡በመንጋ ፡፡ሁሉም ፍጡር የራሱ የሆነ መግለጫ፣ መለያ ፣ባህሪ፣ የአኗኗር ዘይቤ…..ወዘተ አለው፡፡በዚህ ምክንያት አላህ(ሱ.ወ) ተንቀሳቃሽ ፍጡራን በአጠቃላይ ‹‹ህዝብ›› ብሎ ጠራቸው፡፡ . . ‹‹ከተንቀሳቃሽ ፣ በምድር (የሚሄድ) ፤ በሁለት ክብፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጂ ሌላ አይደለም፡፡›› (አል-አንአም÷38)

**ሰለጠነ የሚባለው ዓለም ዛሬ ዛሬ ትኩረት የቸረውን የተለያዩ ሕያው ፍጡራንን ዝርያ ከጥፋት የመጠበቅ የተቀደሰ ተግባር ÷ኢስላም ከዛሬ እስር አራት ምዕተ-ዓለም በፊት በዚህ መልኩ ቀድሞ አስተዋውቆታል ፡፡በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ የዛሬዎቹ ድርጅቶች ተግባሩን ‹‹የኖህ ተልዕኮ›› እያሉ ያሞካሹታል፡፡

** የህያው ፍጡራንን ዝርያ ከጥፋት የመጠበቅና ተንከባክቦ ሁሉ ከሺህ ዘመናት በፊት ያስተዋወቀው መርህ ነው፡፡ይህን መሰሉን መርህ እንግዲህ ‹‹ኦሪት›› ያስተማራቸው ምዕራባዊያን ቀደም ሲል በተጠቀሰው መልኩ ከፈጸሙት አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር እያነፃፀሩ መታዘብ ነው፡፡በ ‹‹ኦሪታዊው›› አስተምህሮ ተኮትኩተውና ታንፀው ያደጉት ምዕራባዊያን የሰው አገር በቅን ገዥነት ለመያዝ ሲሉ የፈፀሙትን ዘርን ከምድረ ገፅ የማጥፋት ተግባር እኛ ብቻ የምናውቀው ጉዳይ ሳይሆን ታሪክ በማይፋቅ ብዕሩ ያሰፈረው ጉዳይ ነው፡፡

የአይሁድ ፅዮናውያን ጭፍራዎች በፍልስጤም ነዋሪዎችና ህዝቦች ላይ የፈፀሙት የጥፋት ተግባር ታሪክን ለመጠየቅ መዛግብት ሳንበረብርና ሩቅ ሳንሄድ በዓይናችን በብረቱ ያየነው ነገር ነው፡፡ እነዚህ አሸባሪ ፅዮናውያን ‹‹ዲርያሲን›› የተባለውን የፍልስጤም ከተማ ጥሰው ገብተው ከተማውን በመክበብና ነዋሪውን በማገት ፍልስጤማውያንን በግፍ አርደዋል፡፡በሰላም የተቀመጡ ሲቪል ነዋሪዎችን ህፃን ከሽማግሌ ፣ ሴት ከአረጋዊ ሳይለዮ ያለምንም ርህራሄና እዝነት በጅምላ ጨፋጭፈዋቸዋል፡፡

** አይሁዳዊያኑ ከጭካኔያቸው የተነሳ÷ የእርጉዝ ሴቶችን ሆድ በሳንጃ ተርትረዋል፡፡በሰይፍ ስለቶቻቸው ማሕፀን ውስጥ ያለን ፅንስ አርደው ገድላዋል፡፡ ይህን መሰሉን ዘግናኝ ተግባር ሲፈፅሙም እያመነቱና እየዘገነናቸው ሳይሆን እየሳቁና እየተሳለቁ ነበር! ልጆችን በሚሳሳው እናቶቻቸው ዓይንና በሚባባው የአባቶች ሆድ ፊት ገድለዋል፡፡እናትና አባቶችን ክፈውን ከደጉ ባልለዩ አንድ ፍሬ ልጆቻቸው ፊት አንገታቸውን ቀልተዋል፡፡
በዚህ ሰቅጣጭና ጭራቃዊ ተግባራቸው በፍልስጤማዊያን ህዝቦች ልብ ውስጥ ሽብርን ዘርተዋል፡፡በዚህም ምክንያት ፍልስጤማውያኑ እትብታቸው የተቀበረበትን ፣ ተወልደው አድገው አፈር የፈጩበትን ቀዬአቸውን ደም ለተጠሙቱ አሸባሪ አይሁድ ፅዮናውያን ለቀውና ትተው ሸሽተዋል፡፡ አገር ጥለው ተሰደዋል፡፡
እነዚህ በንጹህ ፍልስጤማውያን የግፍ ደም እጃቸው የጨቀየው አክራሪ ጽዮናውያን ከላይ የተገለፀውን ዓይነት ወንጀል ሲፈፅሙ÷ በተግባር እየተረጎሙ የነበረው የእምነታቸውን ምንጭ ከሆነው ‹‹ኦሪት›› የቀሰሙትን ‹‹ከአህዛብ ከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም ›› የሚለውን አስተምህሮ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
ፅዮናዊያን የተገበሩት ‹‹ ፈፅመህ ታጠፋቸዋለህ ››የሚለውን ኦሪታዊ ህጋቸውን ነው፡፡ ‹‹ከአህዛብ ከከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም››፡፡
መውረር የሚፈልጓቸውን ከተማዎች በእጆቻቸው ሲወድቁ ይህን እንዲያደርጉ ነበር የሙሴ ፣ የተከታዮቹና የህዝቡ ‹‹አምላክ እግዚያብሔር›› ያስተላለፈላቸው ትዕዛዝ ፡፡የታዘዙት ትእዛዝ ግልፅና አጭር ነበር፡፡ከተማ ለመውረር ውጊያ ይከፍታሉ፡፡ነዋሪውን ወደ መግደል ይሸጋገራሉ፡፡ በሚወረረው ከተማ ውስጥ የሚኖረው ነዋሪ ከሰይፍ ስለት በስተቀር ሌላ ምንም ተተኪ አማራጭ አይኖረውም፡፡ይኸው ነው!

*^* ይህ መሰሉን ‹‹ኦሪታዊ›› ትዕዛዝ ቀጥሎ ከምናነበው ቁርዓናዊ ትእዛዝ ጋር እንደምን እናነፃፅረው ይሆን ? እንዲህ ይነበባል. . . ‹‹እነዚያን የሚዋጓችሁን በአላህ መንገድ ተዋጉ፡፡ግን ወሰኞችን አትለፍ፡፡ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድም፡፡ካገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው ፡፡እነርሱ እናንተን ካስወጧችሁ ሥፋራ እናንተም አስወጧቸው፡፡ (ለሙእሚኖች) ‹ፊትና› (እምነትን መፈታተን) ከግድያ የከፋ ነው፡፡ከተከበረው መስጂድ ክልል (ሐራም) ውስጥ - እነርሱ ውጊያ እስኪጀምሩ ድረስ አትዋጓቸው ፡፡ውጊያ ከጀመሩ ግን ተዋጓቸው፡፡ይህ ለከሐዲዎች ተገቢ ቅጣት ነው፡፡›› (አል-በቀራህ÷ 190-191)

ከቀጣዩ የቁርዓን መርህ ጋርስ እንዴት ሊወዳደር ይችላል? .‹‹ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡ ››(ሱረቱ አት-ተውባ 9፡5)
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests