የቁርአን አዲስ ትርጉም በአማርኛ በድምጽና በጹሁፍ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የቁርአን አዲስ ትርጉም በአማርኛ በድምጽና በጹሁፍ

Postby ሰይፈዲን » Sat Jan 11, 2014 8:41 pm

ሰሰላም ሐቅን ለተከተለ ሁሉ ይሁን :
ከስር በሚገኝው ሊንክ ስር የአላህ ፈቃዱ ከሆነ የተወሰኑ የቁርአን ትርጉሞችን በዩቲዩብ ተፈጥሮን እየቃኙ የአረብኛውንና የአማርኛውን ጹሁፍ እያነበቡ እና እያደመጡ ሙሉ ትኩረቶትን ሰጥተው እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል :: ከጊዜዎ ጋር ለማጣጣም አጫጭር ምእራፎችን በሚፈጁት ደቂቃዎች ያውቁዋቸዋል መልካም ምሪት ለሚያደምጥ ሁሉ እንመኛለን ::

http://www.youtube.com/channel/UC5crnTbEoQkV7eGLt2aYZAQ


..
ሰይፈዲን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Mon Dec 29, 2003 9:35 pm

Postby ሰይፈዲን » Sun Jan 12, 2014 9:03 pm

1ኛ - ጁዝ
1ኛ፤ ሱራህ አል-ፋቲሐ
በመካ የወረደች - 7 አያዎች አሏት

1. በአላህ ሥም ፍፁም አዛኝ ፍፁም ርኀሩሁ በሆነው ።

2. ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ (ይገባው፤)

3. ፍፁም አዛኝ ፍፁም ርኀሩሁ ለሆነው።

4. የፍርዱ (የቂያማ) ቀን ባለቤት (ብቸኛ ፈራጅ ለሆነው አላህ ምስጋና ይገባው)

5. (አላህ ሆይ) አንተን ብቻ እንገዛለን፤ በአንተም ብቻ እንታገዛለን፡፡

6. (አላህ ሆይ የጀነትን) ቀጥተኛውን፤ መንገድ፤ ምራን፡፡

7. የነዚያን በጎ የዋልክላቸውን፤ (እንደ አይሁድ) ያልተቆጣህባቸውንና፤ (እንደ ነሳራ) ያልተሳሳቱትን፤ (የነብያትንና የፃድቃንን) መንገድ ምራን፡፡


ክፍል 30፡፡
114ኛ ሱረቱ አል -ናስ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 6 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ (1)
1. (አንተ ነብይ ሆይ ) በሰዎች ጌታ (አላህ ) እጠበቃለሁ በል።
مَلِكِ النَّاسِ (2)
2. የሰው ልጆች (ሁለ መናቸውን ) ገዢ (በሆነው አላህ እጠበቃለሁ በል )
إِلَهِ النَّاسِ (3)
3. የሰው ልጆች (በጠቅላላ ) አምላክ (በሆነው አላህ እጠበቃለሁ በል )
مِنْ شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ (4)
4. (በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ) ብቅ እልም በሚሉ ጎትጓች (ሰይጣኖች ) ክፋት (በአላህ እጠበቃለሁ በል )።
الَّذِي يُوَسْوِسُ فِي صُدُورِ النَّاسِ (5)
5. እነዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ በሚጎተጉቱት። (ሰይጣኖች ክፋት በአላህ እጠበቃለሁ በል )።
مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ (6)
6. (የሰይጣን ባሕርይ ከተላበሱ ) ከጋኔኖችና ከሰዎች (ክፋት በአላህ እጠበቃለሁ በል። )


ክፍል 30፡፡
112ኛ ሱረቱ አል -ኢኸላስ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 4 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ (1)
1. (አንተ ነብይ ሆይ ስለ አላህ ባሕርይ ስትጠየቅ ) አላህ (ብቸኛ ተመላኪ ) አንድ (አምላክ ) ነው በል።
اللَّهُ الصَّمَدُ (2)
2. አላህ (የፍጡራን ሁሉ ) መጠጊያ ነው።
لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ (3)
3. (አላህ ማንንም ) ፈፅሞ አልወለደም፤ ፈፅሞም አልተወለደም፡፡
وَلَمْ يَكُنْ لَهُ كُفُوًا أَحَدٌ (4)
4. (አላህን በተመላኪነቱ፤በባሕሪውና በፈጣሪነቱ ) የሚመሳሰለው አንድም (ፍጡር ) ፈፅሞ የለም።

ክፍል 30
113ኛ ሱረቱ አል -ፈለቅ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 5 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ (1)

1. (አንተ ነብይ ሆይ፤ ንጋትን በሚቀደው ) በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ (በአላህ ) እጠበቃለሁ በል።
مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ (2)

2. (አላህ ) ከፈጠራቸው ክፋት ሁሉ (እጠበቃለሁ በል )
وَمِنْ شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ (3)

3. ሌሊቱም (ድቅድቅ ያለ ) ጨለማ ሲሆን ከሚኖረው ክፋት (በአላህ እጠበቃለሁ በል )
وَمِنْ شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ (4)


4. በቋጠሮዎችም ላይ ተፊዎች (በሆኑ ድግምታም ሴቶች ) ክፋት (በአላህ እጠበቃለሁ በል )
وَمِنْ شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ (5)
5. ምቀኛም በተመቀኘ ጊዜ ከሚኖረው ክፋት (በአላህ እጠበቃለሁ በል )

ክፍል 30፡፡
111ኛ ሱረቱ አል -ለሀብ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 5 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።
تَبَّتْ يَدَا أَبِي لَهَبٍ وَتَبَّ (1)
1. የአቡ ለሃብ እጆቹ ጠፉ፤ (በእርግጥ እራሱም ) ጠፋ።
مَا أَغْنَى عَنْهُ مَالُهُ وَمَا كَسَبَ (2)
2. ገንዘቡም ሆነ ያፈራው ንብረት (ከመጥፋት ) አላዳነውም።
سَيَصْلَى نَارًا ذَاتَ لَهَبٍ (3)
3. ተቀጣጣዩ (የጀሃነም ) እሳት ውስጥም ይገባል።
وَامْرَأَتُهُ حَمَّالَةَ الْحَطَبِ (4)
4. እንጨት ተሸካሚዋ (የአቡ ለሃብ ) ሚስትም (ጀሃነም ) ትገባለች።
فِي جِيدِهَا حَبْلٌ مِنْ مَسَدٍ (5)
5. አንገቷም ላይ ከቃንጫ የሆነ ገመድ አለባት።
ሰይፈዲን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Mon Dec 29, 2003 9:35 pm

Postby ሰይፈዲን » Sun Jan 12, 2014 9:46 pm

ክፍል 30፡፡
105ኛ ሱረቱ አል -ፊል፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 5 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ ﴿١﴾
1. (አንተ ነብይ ሆይ እነዚያ ካእባን ለማፍረስ የዘመቱት ) በዝሆን ባለቤቶች ((በሃበሻው አብረሃ እና ግብራበሮቹ )) ላይ ጌታህ እንዴት እንዳደረገ አታውቅምን ?
أَلَمْ يَجْعَلْ كَيْدَهُمْ فِي تَضْلِيلٍ ﴿٢﴾
2. (ጌታህ የአጥፊዎችን ) የተንኮል ሴራ እንዲከሽፍ አላደረገምን ?።
وَأَرْسَلَ عَلَيْهِمْ طَيْرًا أَبَابِيلَ ﴿٣﴾
3. በነሱም (በአጥፊዎቹ ) ላይ፤የወፎች መንጋ ላከባቸው።
تَرْمِيهِم بِحِجَارَةٍ مِّن سِجِّيلٍ ﴿٤﴾
4. (ወፎቹም ) ከተቃጠለ ጭቃ የሆነ ድንጋይ (ጠጠር ) ይወረውሩባቸዋል።
فَجَعَلَهُمْ كَعَصْفٍ مَّأْكُولٍ ﴿٥﴾
5. (ከብቶች ) አኝከው እንደተፉት ቅጠል አደረጋቸው። ((አስመሰላቸው ))

ክፍል 30፡፡
106ኛ ሱረቱ ቁረይሽ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 4 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

لِإِيلَافِ قُرَيْشٍ (1)

1. ለቁረይሽ (ጎሳ ብዙ ነገር ) ተመቻቸላቸው።
إِيلَافِهِمْ رِحْلَةَ الشِّتَاءِ وَالصَّيْفِ (2)


2. የተመቻቸላቸውም በክረምትና በበጋ (ለንግድ ያለሥጋት ) መጓዛቸው ነው።
فَلْيَعْبُدُوا رَبَّ هَذَا الْبَيْتِ (3)
3. ስለዚህ የዚህን ቤት (የካዕባን ) ጌታ (አላህን ) ይገዙ (ያመስግኑትም )።
الَّذِي أَطْعَمَهُمْ مِنْ جُوعٍ وَآَمَنَهُمْ مِنْ خَوْفٍ (4)
4. ያ በረሃብ (እንዳይጎዱ ) የመገባቸውንና (ከጠላትም ) ፍራቻ የጠበቃቸውን (አላህ ይገዙ )

ክፍል 30
107ኛ ሱረቱ አል -ማዑን፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 7 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።
أَرَأَيْتَ الَّذِي يُكَذِّبُ بِالدِّينِ ﴿١﴾
1. (አንተ ነብይ ሆይ በመጪው ዓለም የፅድቅና ኩነኔ ) ምንዳ እንዳለ የሚያስተባብለውን (ከሃዲ ) አየህን ?
فَذَلِكَ الَّذِي يَدُعُّ الْيَتِيمَ ﴿٢﴾
2. (በመጪው ዓለም ምንዳ ስለሚያስተባብልም ነው ከሃዲው ) ወላጅ አልባ ሕፃንን የሚነፍገው።
وَلَا يَحُضُّ عَلَى طَعَامِ الْمِسْكِينِ ﴿٣﴾
3. ድኻንም በመመገብ ላይ ሌሎችን አያነሳሳም።
فَوَيْلٌ لِّلْمُصَلِّينَ ﴿٤﴾
4. (ለዝንጉ ) ሰጋጆች ወየውላቸው ?
الَّذِينَ هُمْ عَن صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ ﴿٥﴾
5. እነዚያ በሰላታቸው ላይ ተዘናጊዎች ለሆኑት (በገሃነም እሳት ወየውላቸው )
الَّذِينَ هُمْ يُرَاؤُونَ ﴿٦﴾
6. ለነዚያ ለይዩልኝ ባዮች (ወየውላቸው )
وَيَمْنَعُونَ الْمَاعُونَ ﴿٧﴾
7. ዕቃንም ማዋስ ለሚከለክሉ (ወየውላቸው )

ክፍል 30፡፡
108ኛ ሱረቱ አል -ከውሠር፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 3 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ (1)
1. (አንተ ነብይ ሆይ ) እኛ ከውሰር (የተባለችውን የጀነት ወንዝ እና መልካም ነገሮችን ) ሰጠንህ።
فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ (2)
2. ለጌታህም (ለአላህ ) ስገድ (በስሙም ) ሰዋ (እረድ )።
إِنَّ شَانِئَكَ هُوَ الْأَبْتَرُ (3)
3. በእርግጥ (አንተ ሳትሆን ) የሚጠላህ እራሱ ነው ዘር አልባ ((የሚረሳ )) የሚሆነው።

ክፍል 30፡፡
109ኛ ሱረቱ አል -ካፊሩን፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 6 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።
قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ (1)
1. (አንተ ነብይ ሆይ ) እናንት ከሃዲያን ሆይ በላቸው።
لَا أَعْبُدُ مَا تَعْبُدُونَ (2)
2. (እኔ ) ያ የምታመልኩትን (ጣዖት ) አምላኪ አይደለሁም።
وَلَا أَنْتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ (3)
3. እናንተም ያ እኔ የማመልከውን (ፈጣሪ አላህን ) አምላኪ አይደላችሁም።
وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَا عَبَدْتُمْ (4)
4. እኔም እናንት የምታመልኩትን (ጣዖት ) አምላኪ አልሆንም።
وَلَا أَنْتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ (5)
5.እናንተም (ከጥመታችሁ ስለማትመለሱ ) ያ እኔ የማመልከውን (ፈጣሪ አላህን ) አምላኪ አትሆኑም።
لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ (6)
6. ለናንተም (ለከሃዲያን፤ ወደ ጥመት የሚመራችሁ ) ሃይማኖት አላችሁ። ለእኔም (የምድንበት ኢስላም ) ሃይማኖት አለኝ።
ክፍል 30፡፡
110ኛ ሱረቱ አል -ነስር፤
በመዲና የወረደች ናት፤ አያትዋ 3 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

إِذَا جَاءَ نَصْرُ اللَّهِ وَالْفَتْحُ (1)
1. (አንተ ነብይ ሆይ በቁረይሽ ከሃዲያን ላይ ) የአላህ ድልና፤ የመካ መከፈት በሚፈፀምበት ጊዜ።
وَرَأَيْتَ النَّاسَ يَدْخُلُونَ فِي دِينِ اللَّهِ أَفْوَاجًا (2)
2. ብዙ ሰዎች ወደ አላህ ሃይማኖት (ኢስላም ) በቡድን በቡድን ሆነው ሲገቡም አይተሃል።
فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا (3)
3. ስለዚህ (ጌታህን አላህ ) በማመስገን አወድሰው፤ምሕረትም ለምነው፤በእርግጥ (አላህ ) ፀፀትን ተቀባይ (መሐሪ ) ነውና።
ሰይፈዲን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Mon Dec 29, 2003 9:35 pm

Postby ሰይፈዲን » Sun Jan 12, 2014 10:04 pm

Posted: Sun Jan 12, 2014 8:52 pm Post subject: Reply with quote Edit/Delete this post Delete this post


ክፍል 30፡፡
96ኛ ሱረቱ አል -ዐለቅ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 19 ናቸው፡፡

بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ ﴿١﴾
1. (አንተ ነብይ ሆይ ) ያ (ፍጥረታትን ሁሉ ) በፈጠረው ጌታህ ሥም (ቁርአንን ) አንብብ።
خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ ﴿٢﴾
2. (አላህ ) የሰውን ልጅ (በመሃፀን ተንጠልጣይ በሆነው ) ከረጋ ደም ((ሽል )) ፈጠረው።
اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ ﴿٣﴾
3. (አንተ ነብይ ሆይ ቁርአንን ) አንብብ፤ ጌታህም ፍፁም ለጋሽ ነው።
الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ ﴿٤﴾
4. ያ (ጌታህ አላህ ሰውን ) በብእር (መፅሃፍን ) አስተማረው።
عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ ﴿٥﴾
5. (አላህ ) ፍፁም እማያውቅ የነበረውን የሰውን ልጅ (ዕውቀት ) አስተማረው።
كَلَّا إِنَّ الْإِنسَانَ لَيَطْغَى ﴿٦﴾
6. (ክህደት ተገቢ ) አይደለም። በእርግጥ የሰው ልጅ (የአላህን ትእዛዝ ) ይጥሳል።
أَن رَّآهُ اسْتَغْنَى ﴿٧﴾
7. (የሰው ልጅ እራሱን ባለፀጋ አድርጎ ) በማየቱ በራሱ ይብቃቃል፤ (በፈጣሪው አይመካም )።
إِنَّ إِلَى رَبِّكَ الرُّجْعَى ﴿٨﴾
8. (አንተ ነብይ ሆይ ) በእርግጥ (የተጣመመ ሁሉ እንደየሥራው ሊመነዳ ) ወደ ጌታህ ተመላሽ ነው።
أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَى ﴿٩﴾
9. (አድማጭ ሆይ ስግደት ) የሚከለክለውን (የአቡጀህልን ሥራ ) አየህን ?
عَبْدًا إِذَا صَلَّى ﴿١٠﴾
10. (ለአላህ ) ተገዢ (ነብዩ መሐመድ ) በሰገደ ጊዜ (የከልካዩን ሥራ አየህን ?)
أَرَأَيْتَ إِن كَانَ عَلَى الْهُدَى ﴿١١﴾
11. (አድማጭ ሆይ ) አየህን ? (ሰጋጁ ) በእርግጥ በትክክለኛው ምሪት ላይ እያለ (ስግደት መከልከል አለበትን ?)
أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَى ﴿١٢﴾
12. ወይንም (ለሌሎች የአላህን ) ፍራቻ መንገድ በማዘዙ (ስግደት መከልከል አለበትን ?)
أَرَأَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّى ﴿١٣﴾
13. (አድማጭ ሆይ ) አየህን ? (ስግደት ከልካዩ ) በእርግጥ (ሐቅን ) በማስተባበሉና (ከአላህ ትእዛዝ ) በማፈንገጡ። (አላህን አይፈራምን ?)
أَلَمْ يَعْلَمْ بِأَنَّ اللَّهَ يَرَى ﴿١٤﴾
14. (ስግደት ከልካዩ መጥፎ በመሥራቱ ) አላህ በእርግጥ እንደሚያየው አያውቅምን ?
كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ ﴿١٥﴾
15. (ጉዳዩ ስግደት ከልካዩ እንደሚገምተው ) አይደለም፤ (ከተንኮሉ ) ባይታቀብ አናቱን (ቆንጥረን ) በመያዝ (ጀሃነም እንከተዋለን )።
نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ ﴿١٦﴾
16. (የስግደት ከልካዩ አናት ) ዋሾ፤ ስህተተኛ የሆነች አናት ናት።
فَلْيَدْعُ نَادِيَه ﴿١٧﴾
17. (ስግደት ከልካዩ ተንኮሉን እቀጥልበታለሁ ካለ ለእርዳታ ) ግብራበሮቹን ይጥራ።
سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ ﴿١٨﴾
18. (እኛም ቅጣት ፈፃሚ መላእክቶችን፤ የጀሃነም ) ዘበኞቻችንን እንጠራለን።
كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِبْ * ﴿١٩﴾ ۩
19. (አንተ ነብይ ሆይ አቡጀህል እንደሚገምተው ሊያጠቃህ ) አይችልም፤ (ሰላትህን ተው የሚለውን ጥሪ ) አትቀበለው፤ (ለአላህም ) ስገድ (ትእዛዙንም በማክበር ጌታህን ) ተቃረበው።

ክፍል 30፡፡
97ኛ ሱረቱ አል -ቀድር፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ (አንቀጾችዋ ) 5 ናቸው፡፡

بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።


إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ ﴿١﴾
1. እኛ (ቁርአኑን ) በተከበረችዋ ሌሊት አወረድነው።
وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ ﴿٢﴾
2. (አንተ ነብይ ሆይ ) የተከበረችዋ ሌሊት ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ ?
لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ ﴿٣﴾
3. በተከበረችዋ ሌሊት (መልካም ሥራ ) ከሺህ ወር (መልካም ሥራ ) የተሻለ ነው።
تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ ﴿٤﴾
4. (በተከበረችዋ ሌሊት ) ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጅብሪል ) በጌታቸው ፈቃድ (የቀጣዩን አመት የአላህ ) ውሳኔዎችን ሁሉ ይዘው (ተከታትለው ) ይወርዳሉ፤
سَلَامٌ هِيَ حَتَّى مَطْلَعِ الْفَجْرِ ﴿٥﴾
5. (ሌሊቷም ) ፈጅር እስኪደርስ ድረስ ሰላም (ይሰፍንባታል )።


ክፍል 30፡፡
98ኛ ሱረቱ አል -በይናህ፤
በመዲና የወረደች ናት፤ አያትዋ 8 ናቸው፡፡

بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّى تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ ﴿١﴾
1. እነዚያ ከመፅሃፉ ባለቤቶች (ከየሁድ፤ ነሳራ ) እና (በአላህ አምልኮ ) የሚያጋሩ (ሙሽሪኮች ) ግልፅ የሆነ ማስረጃ እስኪመጣላቸው ድረስ (ከቀድሞው ከተሳሳተው እምነታቸው ) የሚላቀቁ አይደሉም።
رَسُولٌ مِّنَ اللَّهِ يَتْلُو صُحُفًا مُّطَهَّرَةً ﴿٢﴾
2. (ግልፅ ማስረጃውም ) ከአላህ የተላከ (ከስይጣን ጣልቃ ገብነት ) የፀዳ ፁሁፍን (ቁርአንን ) የሚያነበንብ መልእክተኛ ነው።
فِيهَا كُتُبٌ قَيِّمَةٌ ﴿٣﴾
3. (በቁርአኑ ) ውስጥም ቀጥተኛ የሆኑ (ሐቅን አመላካች ) ፁሁፎች አሉበት።
وَمَا تَفَرَّقَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ إِلَّا مِن بَعْدِ مَا جَاءتْهُمُ الْبَيِّنَةُ ﴿٤﴾
4. እነዚያ የመፅሐፉ ባለቤቶች (የሁድና ነሳራ ) ግልፅ ማስረጃ (ቁርአን ) እስኪመጣላቸው ድረስ (እርስ በርስ ) አልተለያዩም ነበር። (ቁርአን ሲመጣ ግን የተወሰኑት በመስለም የተወሰኑት በቅናት በመክዳት ተለያዩ )
وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاء وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ وَذَلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ ﴿٥﴾
5. (አይሁዶችም ሆኑ ነሳራዎች፤በኦሪትም ሆነ በወንጌል ) ሃይማኖትን ፍፁም ለአላህ አድርገው ወደ (እስልምና ) አዘንብለው ሰላትን በመስገድና ዘካን በመስጠት አላህን እንዲገዙ እንጂ በሌላ (ጉዳይ ) አልታዘዙም። ይህም (እንዲከተሉት የታዘዙበት ሃይማኖት እስልምና ) ትክክለኛ ሃይማኖት ነው።
إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أُوْلَئِكَ هُمْ شَرُّ الْبَرِيَّةِ ﴿٦﴾
6. እነዚያ ከመፅሐፉ ባለቤቶች (ከየሁድና ነሳራ ) (በእስልምና ) የካዱትና፤ (በአላህ አምልኮ ) አጋሪዎችም፤በእርግጥ በጀሃነም እሳት ውስጥ ናቸው። (በእሳቷም ) ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ እነዚህ (በዘመናቸው ) መጥፎ (የሰው ) ፍጥረት ናቸው።
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُوْلَئِكَ هُمْ خَيْرُ الْبَرِيَّةِ ﴿٧﴾
7. እነዚያ በእርግጥ (በኢስላም ) አምነው፤ መልካም (ተግባራትን ) የሰሩ፤ እነዚያ (በዘመናቸው ) ምርጥ (የሰው ) ፍጡር ናቸው።
جَزَاؤُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ذَلِكَ لِمَنْ خَشِيَ رَبَّهُ ﴿٨﴾
8. (አማኞችም ) ከጌታቸው ዘንድ (የሚያገኙት ) ምንዳ፤ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈስባቸው ዘላቂ የሆኑ ገነቶች ሲሆኑ፤ (በገነቶቹም ) ውስጥ ሁሌ ዘውታሪዎች ናቸው። (በአማኞቹም መልካም ሥራ ) አላህ እረካባቸው። (አማኞችም በገነት በተሰጣቸው ምንዳ በአላህ ) እረኩ። ይህም (ምንዳ የሚቸረው ) ጌታውን ለሚፈራ ብቻ ነው።

ክፍል 30፡፡
99ኛ ሱረቱ አል -ዘልዘላህ፤
በመዲና የወረደች ናት፤ አያትዋ 8፤ ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا ﴿١﴾
1. (ቂያማ ሲደርስ ) ምድር ሃይለኛውን መንቀጥቀጥ በተንቀተቀጠች ጊዜ።
وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا ﴿٢﴾
2. ምድርም (በውስጧ ያሉትን ክምችትና ሙታንን ) ባወጣች ጊዜ።
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا ﴿٣﴾
3. የሰው ልጅም (ምድር ) ምን ሆነች ? ባለ ጊዜ።
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا ﴿٤﴾
4. በዚያ (በቂያማ ) ቀን (ምድር በላዪዋ ላይ ጥሩም ይሁን መጥፎ የተከሰተውን ተግባር ) ወሬዎቿን ትናገራለች፤ ((ትመሰክራለች ))
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَى لَهَا ﴿٥﴾
5. (የምድርም መናገር ) ጌታህ ስላዘዛት ነው።
يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتًا لِّيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ ﴿٦﴾
6. በዚያ (በቂያማ ) ቀን ሰዎች (ከቀብር ተነስተው ከተሰበሰቡ በኋላ መጥፎም ይሁን ጥሩ ) የስራቸውን (ውጤት ) ለማየት በየግል (ወደ ጀነት ወይንም ጀሃነም ) ይሰማራሉ።
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ ﴿٧﴾
7. የቁጫጭ ክብደት የሚያህል መልካም የሰራ (ሙስሊም ብቻ በመጪው አለም የመልካም ሥራውን ውጤት ምንዳ ) ያየዋል።
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ ﴿٨﴾
8. የቁጫጭ ክብደት የሚያህል መጥፎ የሰራ (ምህረት ያላገኘ ሙስሊምና ባጠቃላይ ከሃዲ በመጪው አለም የመጥፎ ሥራውን ውጤት ቅጣት ) ያየዋል።

ክፍል 30፡፡
100ኛ ሱረቱ አል -ዓዲያት
በመካ የወረደችናት አያትዋ፤ 11 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحًا ﴿١﴾
1. (እኔ አላህ ወደ ጦር ሜዳ ) እያለከለኩ ጋላቢ በሆኑ (ፈረሶች ) እምላለሁ።
فَالْمُورِيَاتِ قَدْحًا ﴿٢﴾
2. (በግልቢያ ወቅት በሸኾናቸው ) የእሳት ብልጭታን ጫሪዎች በሆኑ (ፈረሶች እምላለሁ )
فَالْمُغِيرَاتِ صُبْحًا ﴿٣﴾
3. (ወደ ጠላት ) በማለዳ (ድንገት ) በሚያጠቁ (ፈረሶች እምላለሁ )
فَأَثَرْنَ بِهِ نَقْعًا ﴿٤﴾
4. (በጠላት ክልል ) አቧራን በማስነሳት በሚያስጨንቁ (ፈረሶችም እምላለሁ )
فَوَسَطْنَ بِهِ جَمْعًا ﴿٥﴾
5. (ተዋጊ ጋላቢዎችን ይዘው ) (በጠላት ) ስብስብ መሀል በሚያስገቡ (ፈረሶች እምላለሁ )
إِنَّ الْإِنسَانَ لِرَبِّهِ لَكَنُودٌ ﴿٦﴾
6. በእርግጥ የሰው ልጅ ጌታው (በሰጠው ፀጋ የማያመሰግን ) ከሃዲ ነው።
وَإِنَّهُ عَلَى ذَلِكَ لَشَهِيدٌ ﴿٧﴾
7. (የሰው ልጅ የራሱ ባሕሪ ክህደቱን ) በራሱ ላይ መስካሪ ነው።
وَإِنَّهُ لِحُبِّ الْخَيْرِ لَشَدِيدٌ ﴿٨﴾
8. (የሰው ልጅ ) ለገንዘብ ያለው ውዴታ በጣም ሃይለኛ ነው።
أَفَلَا يَعْلَمُ إِذَا بُعْثِرَ مَا فِي الْقُبُورِ ﴿٩﴾
9. (የሰው ልጅ አላህ ለሒሳብና ለምንዳ ሙታንን ) ከቀብር በሚያወጣበት ጊዜ (የሚጠብቀውን ሁኔታ ) አያውቅምን ?
وَحُصِّلَ مَا فِي الصُّدُورِ ﴿١٠﴾
10. (ሙታን ሲቀሰቀሱ በሰው ልጆች ) ልቦች ውስጥ የነበሩ (የእምነትና የሥራ አይነት ) ይገለፃሉም።
إِنَّ رَبَّهُم بِهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّخَبِيرٌ ﴿١١﴾
11. በእርግጥ በዚያ (በቂያማ ) ቀን ሰዎች (በሰሩት ሥራ ) ላይ ጌታቸው ውስጠ አዋቂ ነው።

ክፍል 30፡፡
101ኛ ሱረቱ አል -ቃሪዓህ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 11 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

الْقَارِعَةُ ﴿١﴾
1. (ያቺ ድንገት ልብን ) አንኳኪዋ ፤ (ቂያማ )
مَا الْقَارِعَةُ ﴿٢﴾
2. ምንድናት (ያቺ ልብን ) አንኳኪዋ (ቂያማ )?
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْقَارِعَةُ ﴿٣﴾
3. (የሰው ልጅ ሆይ ያቺ ) አንኳኪዋ (ቂያማ ) ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ። ?
يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوثِ ﴿٤﴾
4. (አንኳኪዋ ቂያማ ማለት ) ሰዎች (እርስ በርስ ) እንደሚተረማመሱ (እንጭጭ ) ቢራቢሮዎች የሚሆኑበት ቀን ነው።
وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ الْمَنفُوشِ ﴿٥﴾
5. (በቂያማ ቀን ) ተራሮች እንደተነደፈ ሱፍ (ቡን ) ይላሉ።
فَأَمَّا مَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ ﴿٦﴾
6. (በቂያማ ቀን መልካም ሥራዎቹ ) ሚዛኖቹን ያከበዱለት ሰው።
فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ ﴿٧﴾
7. ኑሮው በተወዳጇ (ገነት ) ውስጥ ይሆናል።
وَأَمَّا مَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ ﴿٨﴾
8. (በቂያማ ቀን የመልካም ሥራዎቹ ) ሚዛኖች የቀለሉበት ሰው (ግን )።
فَأُمُّهُ هَاوِيَةٌ ﴿٩﴾
9. መኖርያው ((የምታቅፈው )) ገሃነም ናት።
وَمَا أَدْرَاكَ مَا هِيَهْ ﴿١٠﴾
10. (አንተ ሰው ሆይ ሃውያ ) ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ ?
نَارٌ حَامِيَةٌ ﴿١١﴾
11. (ሃውያ ) የጋለች (የገሃነም ) እሳት ነች።

ክፍል 30፡፡
102ኛ ሱረቱ አል -ተካሡር፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 8 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ ﴿١﴾
1. (ሁሉንም ሐብት ) ማካበት፤ (አላህን ከመገዛት ) አዘናጋችሁ።
حَتَّى زُرْتُمُ الْمَقَابِرَ ﴿٢﴾
2. (መዘናጋታችሁም ሞታችሁ ) ቀብሮችን እስክትጎበኙ ድረስ ነው።
كَلَّا سَوْفَ تَعْلَمُونَ ﴿٣﴾
3. (መዘናጋት ) አይገባም፤ (መዘናጋታችሁ ጎጂ መሆኑን ) ወደ ፊት ታውቁታላችሁ።
ثُمَّ كَلَّا سَوْفَ تَعْلَمُونَ ﴿٤﴾
4. በእርግጥ (መዘናጋት ) አይገባም፤ (መዘናጋታችሁ ጎጂ መሆኑን ) ወደ ፊት ታውቁታላችሁ።
كَلَّا لَوْ تَعْلَمُونَ عِلْمَ الْيَقِينِ ﴿٥﴾
5. (መዘናጋት ) አይገባችሁም፤ (በቀብርና በቂያማ ቀን የሚገጥማችሁን ፈተና ) እርግጠኛውን እውቀት ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልተዘናጋችሁ ነበር )።
لَتَرَوُنَّ الْجَحِيمَ ﴿٦﴾
6. (ሁላችሁም ) ጀሃነምን ታዩታላችሁ፤
ثُمَّ لَتَرَوُنَّهَا عَيْنَ الْيَقِينِ ﴿٧﴾
7. በእርግጥ ጀሃነምን (ጥርጥር የሌለውን ) ትክክለኛውን ማየት ታያላችሁ። (ከጀሃነም ቅጣት ሙስሊሙ ሲተርፍ ከሃዲው ግን ይገባታል )።
ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ ﴿٨﴾
8. በዚያ (በቂያማም ) ቀን በተሰጣችሁም ፀጋ (አላህን ስለማመስገናችሁ ወይንም ስለመካዳችሁ ) ትጠየቃላችሁ።

ክፍል 30፡፡
103ኛ ሱረቱ አል -ዐስር፤
በመካ የወረደች ነት፤ አያትዋ 3 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

وَالْعَصْرِ ﴿١﴾
1. (እኔ አላህ ) በዘመን እምላለሁ።
إِنَّ الْإِنسَانَ لَفِي خُسْرٍ ﴿٢﴾
2. የሰው ልጅ በእርግጥ በኪሳራ ውስጥ ነው።
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ ﴿٣﴾
3. እነዚያ (በአላህ ) ያመኑ፤ መልካሞችንም የሰሩ፤ በሃቁ (በአላህ ትእዛዝ ላይ ) አደራ የተባባሉትና በትግስትም (እንዲፀኑ ) አደራ የተባባሉት ሲቀሩ፤ (ሌሎች ሰዎች ኪሳራ ውስጥ ናቸው )

ክፍል 30፡፡
104ኛ ሱረቱ አል -ሁመዛህ፤
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ 9 ናቸው፡፡
بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ሥም ፍፁም ርኅሩህ ፍፁም አዛኝ በሆነው ።

وَيْلٌ لِّكُلِّ هُمَزَةٍ لُّمَزَةٍ ﴿١﴾
1. (ሙስሊሞችን ) ለሚያንቋሽሽ ሃሜተኛ ሁሉ (በጀሃነም ሸለቆ ቅጣት ) ወየውለት።
الَّذِي جَمَعَ مَالًا وَعَدَّدَهُ ﴿٢﴾
2. ያ ገንዘብን የሚሰበስብና የሚሰስት።
يَحْسَبُ أَنَّ مَالَهُ أَخْلَدَهُ ﴿٣﴾
3. በእርግጥ (የሰሰተው ) ገንዘቡ (በምድር አለም ላይ ) የሚያዘወትረው ይመስለዋል።
كَلَّا لَيُنبَذَنَّ فِي الْحُطَمَةِ ﴿٤﴾
4. (ከሃዲው በምድር ዘውታሪ ሆኖ የሚቀር እንደሚመስለውም ) አይደለም፤ አጨማታሪዋ (ገሃነም ) ውስጥ ይወረወራል።
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْحُطَمَةُ ﴿٥﴾
5. አጨማታሪዋ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ ?
نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ ﴿٦﴾
6. (አጨማታሪዋ ማለት ) ተቀጣጣይዋ አላህ (የሚያዛት የጀሃነም ) እሳት ነች።
الَّتِي تَطَّلِعُ عَلَى الْأَفْئِدَةِ ﴿٧﴾
7. ያቺ (የጀሃነም እሳት ከጎጂነቷ ብዛት የሰዎች ) ልቦች ውስጥ ዘልቃ ትገባለች።
إِنَّهَا عَلَيْهِم مُّؤْصَدَةٌ ﴿٨﴾
8. (እሳቷ በገሃነም ሰዎች ) ላይ የተዘጋች ናት።
فِي عَمَدٍ مُّمَدَّدَةٍ ﴿٩﴾
9. (ጀሃነም የተዘጋችውም ) በረዛዘሙ ቋሚዎች ነው።
ሰይፈዲን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Mon Dec 29, 2003 9:35 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 4 guests