ጳውሎው ማን እንደሆነ ያውቃሉን ?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ጳውሎው ማን እንደሆነ ያውቃሉን ?

Postby ዘመጽኩን » Sun Jan 12, 2014 11:40 am

?


ጳውሎስ ማን እንደሆነ ያውቃሉ?ጳውሎስ አብዛኛዎቻችን እናውቀዋለን የክርስትና እምነት ተከታዮች ጳውሎስን (ሃዋሪያው ጳውሎስ) በማለት ይጠሩታል እንዲሁም በርካታ የጳውሎስ ጹሁፎችን እንደ ማስረጃ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ እንዲያውም በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጠ 14 መጽሀፍት በመጻፍ ሪከርዱን የያዘው እሱ ነው፡፡

ጳውሎስ እየሱስ ካረገ ከብዙ አመታት በኋላ የመጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከእየሱስ የበለጠ ተቀባይነትነ አግኝቷል፡፡ ለዚህም ነው በርካታ ሰባኪያን የኢየሱስን ቃል ውድቅ በማድረግ ጳውሎስ ከራሱ የሚናገረውን እንደ ማስረጃ የሚጠቀሙበት ከዚህ በመቀጠል ስለ ጳውሎስ ማንነት በጥቂቱ ለመቃኝት እንሞከራለን፡፡

በማቴዎስ ወንጌል 10፡1-4 ባለው ውስጥ የሃዋሪያቶችን ማለትም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች ስም ዝርዝር ተጽፏል፡፡ በዝርዘሩ ውስጥ ግን ጳውሎስ አልተካተተም፡፡ ይህ የሚያሳየን ኢየሱስ ከመረጣቸው ሃዋሪያት ዉስጥ ጳውሎስ የሚባል እንደሌለ እና እንደማይታወቅ ነው ስለዚ የጳውሎስ ሃዋሪያነት ከየት የመጣ ነው?

አንድ ሰው ራሱን በራሱ ሀዋሪያ ማድረግ ይችላልን?

በዚ ላይ ሁላችንም የምንስማማበት አይችልም በሚለው ነው፡፡ ታደያ ጳውሎስ ሀዋርያ ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ ማን ሃዋርያ አደረገው?

ሃዋርያነት በድምጽ ብልጫ መምረጥ ይቻላል?

እየሱስ አንድ የተናገረው ቃል አለ ለሚያስተውሉ ሰዎች በዩሃንስ ወንጌል 5፤31 እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክርነቴ እውነት አይደለም፤፤ እየሱስ ስለ ራሱ ቢመሰክር ምስክርነቱ እውነት አለመሆኑን በግልጽ ተናገሯል፡፡ ታድያ ጳውሎስ ጌታ ተገልጠልኝ ሀዋርያ ነኝ ብሎ ስለ ራሱ ሲመሰክር እንዴት ተቀባይነትን ሊያገኝ ቻለ?

እየሱስ በራሱ ላይ ቢመሰክር እውነት ካልሆነ ጳውሎስ በራሱ ላይ የመሰከረው እንዴት እውነት ሊሆን ቻለ?

ከእየሱስ የበለጠ ጳውሎስ እውነተኛ ነው ማለት ነው? በጥንቃቄ ያስተውሉት፡፡ በተጨማሪም የጳውሎስ ጹሁፎች ከመጽሃፍ ቅዱስ አንቀጾች ጋር የሚቃረን እና የሚፋለስ ነው ጥቂቱን ማይት ይቻላል፡፡

ለምሳሌ ዘፍጥረት 17፡10 እግዚአብሄር ከአብረሃም ጋር የተገባለት ቃል ኪዳን ይህ ነው ከናንተው ወንድ ሁሉ ይገረዝ‹‹ እግዚአብሄር ወንድ ሁሉ እንዲገረዝ ስላዘዘ አብረሃምን እንደታዘዘ አደረገ የሉቃስ ወንጌል 2፡21 እየሱስ መገረዙን ያሳያ ጳውሎስ ግን የእግዚአብሄርንና የኢየሱስ መንገድ ስለማይመቸው ግርዛትን ተቃወመው ገላቲያን 5፡2 እነሆ እኔ ጳውሎስ አላቹሃለው ብትገረዙ ክርሰቶስ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡

እንግዲ ጳውሎስ ግርዛቱን ከተቃወም እንዴት ነው የሚመለከቱት?

የኢሱስን ቃል ውድቅ አድርጎ አትገረዙ ማለቱ መጽሀፍ ቅዱስን የተጋጨ ሃሳቦችን እንዲይዝ አድርጎታል፡፡

ኢየሱስ ተገረዙ ብሏል ጳውሎስ እንዳትገረዙ ይላል የትኛው ነው ትክክል?

ጳውሎስ መጽኃፍ ቅዱስን መቃወሙን በዚ አላቆመም ስለ አስካሪ መጠጥ መጥፎነት ቁርአን እና መጽሃፍ ቅዱስ ይናገራሉ፡፡ ጥቂቱን ማየት ቢስፈልግ ትንቢተ ሆስዕ 4፡11 ግልሙትና የወይን ጠጅ ስካርንም አዕምሮን ያጠፋል፡፤ እንዲሁም በተጨማሪ መጠጥ መጥፎ መሆኑን እና መጽሀፍ ቅዱስም የከለከለው መሆኑን የሚጠቁሙ አንቀጾች ኦሪት ዘሌውያን 10፡9 ትንቢተ ኢሳያስ 5፤11 ሉቃስ ወንጌል 21፤34 እንዚህ በሙሉ መጠጥ ክልክል መሆናቸውን ነው የሚናገሩት፡፡ አንዲሁም ቁርአን ሱራ አል ማኢዳሕ 5፤90 እናንተ የመናቹህ ሆይ የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣኦታትም አዝላምም ከሰይጣን ስራ የሆኑ እርኩስ ብቻ ናቸው (እርኩስን) እራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ አስካሪ መጠጥ እርኩስና የስየጣን ስራ መሆኑን ቁርሃን አረጋግጦልናል እንዲሁም በመጽሃፍ ቅዱስ ጳውሎስ ምን ይላል?

1ኛ ጢሞቲዎስ5፤23ስለሆድህና ሰለበሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ አንጂ ወደፊት ውሃ ብቻ አትጠጣ ፡፡መጽሃፍ ቅዱስ ክልከል ያደረገውን መጠጥ ጳውሎስ መፍቀዱ ለምን ይሆን? መጽሃፍ ቅዱስን የመሻር መብት አለውን?

ለነገሩ ጳውሎስ የፈለገውን ቢናገር የሚናገረው ቃል ከራሱ መሆኑን ገልጽዋል፡፤ ነገር ግን የሚገርመው የጳውሎስን ቃል እንደ መረጃ የሚያቀርቡ ሰዎች ናቸው፡፡ ጳውሎስ እንዲ ይላል 2ኛ ቆሮንቶስ 11፤17 እንደዚ ታምኜ ሰመከ የምናገረው በሞኝነት እነጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም፡፡ ጳውሎስ በሞኝነቱ እነጂ ጌታ እንዳዘዘው የማይናገር ከሆነ ከጳውሎስ ምን ይጠብቃሉ ከሞኝ ቁም ነገር ይጠበቃልን?

በተጨማሪም 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡12 ሌሎችንም እኔ እላለሁ ጌታም አይደለም፡፤ በማለት የሚናገረው ጌታ ያላለውን መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፤ ታድያ እርሶ የጳውሎስ ቃል ውይስ የጌታን ቃል ነው የሚመርጡት? አላሀወ (ሱ.ወ) በቁራን ዉስጥ ለእንደዚ አይነቶቸች ሰው የሚሰጠው ማስጠንቀቂእንዲህ ነው አል በቀራ 2፡79 ለነዚየም መጽሀፍን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት ይህ ከአላህ ዘንድ ነው ለሚሉ ወየውላቸው ለነርሱም እጆቻቸው ከጻፉት ወየውላቸው ለነርሱ ከዚያ ከሚፈሩት (ሃጢያት) ወየውላቸው፡፡ ሌላው እየሱስ እንዲ ይላል

በማቴዎስ ወንጌል 23፡15 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን አንድ ሰው ልታሳምኑ በባህርና በደረቅ ስለምትዞሩ በሆነም ጊዜ ከናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት ወየውላቹ፡፡ እየሱስ ፈሪሳውያን እና ጻፎች ሰውን እጥፍ የገሃነም እንደሚያደርጉ ተናገሯል፡፡ ጳውሎስ ታድያ ማን ነው?

የሀዋርያት ስራ 23፡6 ጳውሎስ ግን እኩሌቶቹ ሰደቃውያን እኩሌቶቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን አይቶ ወንድሞች ሆይ እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊም ልጅ ነኝ አለ፡፡ እየሱስ ፈሪሳውያን ሰው እጥፍ የገሃነም እንደሚያደርጉት ተናገሯል፡፡ ጳውሎስ ደግሞ ፈሪሳዊ ነኝ ብሎናል፡፤ ታድያ ሰውን እጥፍ የገሀነም እያደረገ አይደለምን?? መንቃት ያስፈልጋል ማንንም መቀበል የለብንም፡፤ እንደ ጳውሎስ ሰውን ወደ ገደል የሚገፋ ሊሆኑ ይችላሉና፡፡

እንዲሁም ገላቲያ 2፡7 ጴጥሮስ ለተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደተሰጠው እንዲሁ ለኔ ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደተሰጠኝ አዩ፡፤ ለተገረዙት ሀዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሰራለት ለኔ ደግሞ ለአህዛብ ሀዋርያ እንድሆን ሰርቷልና፡፡

ጳውሎስ ላልተገረዙ የሆነ ወንጌል አደራ ተበሏል ለተገረዙት ደግሞ ጴጥሮስ፡፡ ስለዚ እርሶ አልተገረዙም እንዴ??

የጳውሎሰን ወንጌል የሚከተሉት ጳውሎስ እኮ እንደተናገረው ላልተገረዙት ነው እንጂ ለተገረዙት አልተላከም፡፡ ታድ እርሶ ከየትኛው ኖት??

ጳውሎስን የሚከተሉ ከሆነ አለመገረዞን ያረጋግጡ፡፡ ጳውሎስ ተላከ የሚለው ላልተገረዙት ነውና፡

ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ ጌታ እንደተገለጠለት ተናግሯል የተናገረውን ቃል ከማመናችን በፊት ሰለተናገረው ጉዳይ ማጤን ተገቢ ይመስለናል ፡፡

ከጳውሎስ ጋር ወደ ደማስቆ የሄዱት ስዎቸስ ምን አጋጠማቸው ? የሐዋርያት ስራ 22፡9 ከኔ ጋር የነበሩት ብርሃኑን አይተውት ፈሩ የሚናገረኝን የእረሱን ድምጽ ግን አልሰሙም እዚህ ላይ በግልፅ እንደሚያሳየን ከጳውሎስ ጋር የነበሩት ሰዎች ብርሃኑን እያዩ ድምጹን ግን አንዳልስሙ ነው ይህን የሚቃወም ወይም ከዚህ አባባል ጋር የሚጋጭ አንቀጽ በንጠቅስ የሐዋሪያት ስራ 9፡7ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምጹን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደዲዳዎች ቆሙ፡፡ በዚህኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ የምንረዳው ከጳውሎስ ጋር ያሉት ድምጽ እንደሰሙና ማንንም እንዳላዩ ነው ታዲያ ይህ አባባል በመጀመሪያ ካነበብነው የሐዋርያ ስራ 22፡9 ጋር በቀጥታ ይጋጫል፡፡ አንድ በአንድ ማየት ካስፈለገ፡

የሐዋርያት ስራ 22፡9 ከኔ ጋር የነበሩትም ብርሀኑን አይተው ፈሩ፡፡

የሐዋርያት ስራ 9፡7 ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቆሙ

የሐዋርያት ስራ 22፡9 የሚናገረኝን የርሱን ድምጽ ግን አልሰሙም

የሐዋርያት ስራ 9፡7 ከርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምጹን እየሰሙ

እንግዲህ አዚህ ላይ ግልጽ የሆነ ግጭት እያየን ነው፡፡ አንደኛው ብርሀን አዩ ሲል በሌላ ቦታ ደግሞ አላዩም እያለ ነው፡፡ እንዲሁም ድምጽ አልሰሙም ሲል ሰምተዋል እያለ ነው፡፤

ታደያ ጳውሎስ ጌታ እንደተገልጸለት ለማረጋገጥ የትኛውን አንቀጽ ይዘን የትኛውን እንጣል ሁሉም ይጋጫል እንዴት ታድያ እውነት ብለን የጳውሎስን ውሸት እንቀበል?

ምክንያቱም አንድ በመንፈስ የሚመራ ስው ሁለት የሚጋጩ ሃሳቦችን አይጽፍም፡፡ በተጨማሪም በዚሁ አንቀጽ ማለትም የሀዋርያት ስራ 22፡7 በምድር ላይ ወድቄ ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለኝን ድምጽ ሰማሁ፡፡

እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየው በምድር ላይ የወደቀው ጳውሎስ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይህን አንቀጽ የሚቃወም ጹሁፍ እናገኛለን፡፡ የሀዋርያት ስራ 26፡14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ግዜ በዚህኛው ገለጻ ደግሞ ሁሉም መውደቃቸውን ነው የሚናገረው፡፡ እርሶስ ምን ይላሉ? ጳውሎስ ብቻ ነው የወደቀው ወይንስ ሁሉም?

የሀዋርያት ስራ 22፡7 በምድር ላይ ወድቄ፡፡

የሀወርያ ስራ 26፡14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ግዜ
እውነት አንዱ እንጂ ሁለቱም ሊሆን አይችልም፡፡

ትክክል ነው ብለው ካሉ የትኛው እንደሆነ በትክክል ማወቅና ሌላኛውን ውድቅ ማድረግ ይኖርቦታል፡፡ አይ ሁሉም ትክክል ነው የሚሉ ከሆነ ግን በመጽሀፍ ቅዱስ እንዲ የሚል እናገኛለን፡ መጽሐፈ ምሳሌ 14፡15 የዋህ ቃሉን ሁሉ ያምናል ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል፡፡
ስለዚህ የዋህ ሆነው የተጻፈውንና የተባለውን ከሚያምኑ በልህ ሆነው አካሄዶዎትን ቢመለከቱ ይሻላል ፡፡

ስለዚህ ጳውሎስ ጌታ ተገለጸልኝ የሚለው ልብ ወለድ አንጂ እውነት አለመሆኑን በአንቀጾቹ መጋጨት ምክንያት አረጋግጠናል ፡፡

ሌላው ደግሞ ጳውሎስ ከእየሱስ ጋር ተሰቅያለሁ እያለ ሰዎችን እያደናገረ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ከመጻሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል

ገላትያ 2፡19እኔ ለእግዛብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና ከክርሰቶስ ጋር ተሰቅያለሁ. . .
ማንም ክርሰቲያን ጳውሎስ በእየሱስ ዘመን እንዳልነበር ያውቃል ታዲያ የጳውሎስን ከእየሱስ ጋር የመሰቀሉን ነገር እንዴት ያዩታል ?

አስደናቂ የትንግርት ድረሰት ነው፡፡ ለነገሩ ጳውሎስ የሰይጣን እገዛ እየተደረገለት የሚጓዝ ሰው ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል ፡፡

ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 2ኛ 12፡7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የስጋዬ መውጊያ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ ይኽውም እንዳልታበይ ነው ታዲያ በሰይጣን የሚታገዝ እንዴት ሃዋሪያ ነው ብለን ወገባችንን ይዘን እንሟገታልን በሰይጣን የሚታገስ ሰው እንዴት እንደጽድቅ ሰው ልናየው እንችላለን ፡፡ጳውሎስን የሚክተሉ ከሆነ ሰይጣንንም እንደሚከተሉ ሊያምኑ ይገባል ምክንያቱም ጳውሎስ በሰይጣን ነውና የሚመራው ፡፡

እንዲሁም 1ኛጢሞቲዎስ 1፡20 . . .ከእነዚያም እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው ጳውሎስ ሁለት ሰዎችን እንዳይሳዳቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፎ መሰጠቱን ተናግሯል

እንግዲህ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደማይገኝ ሁሉ ከሰይጣንም ጥሩ ነገር እንደማይገኝ ሁላችንም እናውቃለን ፡፡

ታዲያ ጳውሎስ ለምን ይሆን ሁልቱን ሰዎችን እንዲማሩ ለሰይጣን መስጠቱ ?

ጳውሎስ ሰዎችን ወደ ሰይጣን የሚልክ ከሆነ እርሱ እራሱ ማን እንደሆነ ለማወቅ አያዳግትም ፍረዱን ለእናንተ ትተናል፡፡

ታዲያ እረስዎም አሁን እውነቱን የተረዱት ይመስለናል ፡፡ሰይጣንን የሚከትሉ ሁሉ መጨረሻቸው አያምርም ፡፡ሰይጣንንም የተከተለ የእሳት ነው፡፡ ጳውሎስንም የሚከተል እነዲሁ ነው ፡፡ስለዚህ እረሶውም ምረጫዎን ያስተካክሉ ገነትን የሚሹ ከሆነ ሐቅን ከልብ ይፈልጉ ሐቅ እንዲሁ በዋዛ አይገኝምና ፡፡በጫዋታና በቀልድ ጊዜዎትን ባያጠፉ መልካም ይመስለናል ፡፡አምላክ የሰጠንን አህምሮ እንጠቀምበት ፡፡እራሰዎንም በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ይፈትሹ፡፡ሞት ቀጠሮ ሰጥቶ አይመጣምና ዛሬም ነገም ሊሆን ይችላል፡፡ቃሉ??
ዘመጽኩን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Sun Jul 10, 2011 3:13 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests