ከወንዶች አለም የተሰጠ መግለጫ!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ከወንዶች አለም የተሰጠ መግለጫ!

Postby ዘመጽኩን » Sun Jan 12, 2014 12:11 pm

የሴት ልጅ መብት በመፅሀፍቅዱስ
ሴት ልጅ በ ኦሪት ዘመን


1.“ከደረቅ ሴት ጋር ከምትኖር
ከምድር አውሪዎች ከ አንበሳዎች
ጋር መኖር ይሽላል”።(መጽሐፈ
ሲራክ 25:16)

2. “ከሴት ቸርነት የወንድ ንፉግነት
ይሽላል።ውሽማዋንና ባሏን
የምታቃና ሴት አፍረት ናት “።
(መጽሐፈ ሲራክ 42:14)

3. “ከልብስ ብል ይገኛል፤ኃጢያትም ሁሉ
ከሴቶች ይገኛል” (መጽሐፈ ሲራክ
42:13-14)

4. “ሚስጢርህን እንዳታወጣብህ ለሴት
ልብህን አትስጣት” (መጽሐፈ ሲራክ 9:5) “

5. በቤትህ አጠገብ ለውሀ መፍሰሻ አታበጅላት
ለሴት የልብህን ሚስጢር
አታውጣላት” (መጽሐፈሲራክ25:24)

6.”በእቅፍክ ለምትተኛዋ እንካ ስለ
ምትነግራት ቃል
ተጠንቀቅ”(ሚኪያስ7:5)


7. ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ
በውጪ በቤት ማዕዘን ላይ መቀመጥ
ይሻላል።
ምሳ 21፡9

8. ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ
በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
ምሳ 21፡14

9. በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ
ሴት አንድ ናቸው፤
እርስዋንም መከልከል ነፍስን መከልከልና
ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።
ምሳ 27፡15-16

10. መጽሐፈ ምሳሌ
19:13 ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ኀዘን ነው፥
ጠበኛም ሚስት እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ
ናት።

11. ምድር በሶስት ነገሮች ትናወጣለች
እንዲያውም መሸከም የማትችላተው
አራት ነገሮች ናቸው
ባሪያ ሲነግስ
ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ
የተጠላች ሴት ባል ስታገባ
ሴት ባሪያ በእመቤቷ እግር ስትተካ ምሳሌ
30:21-23

12. “ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥
እርስዋም ለባል የተሰጠች ዋጋዋም
ያልተከፈለ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥
ቅጣት አለባቸው፤ አርነት አልወጣችምና
አይገደሉም።”
ኦሪት ዘሌዋውያን 19:20

13. <<ጥንቱንም ሃጢአት ከሴት ተገኘች : ስለ
እርሱዋም ሁላችንም እንሞታለን}}::
{መጽሐፈ ሲራክ25:23} እውን ይህ
የአምላክ ቃል ነውን መጽሐፍ ቅዱስ
የሚያስተምረው አምላክ ሴቶችን እንዲህ
ይጠላልን? ወይስ ይህ የሠው ቃል ነውn?

14. ስለ ወር አበባ ደም(ሀይድ)በኢስላም

አዒሻ ረ.ዐ እንዲህ አሉ:-
የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ በወር አበባ ላይ
እያለው በታፋዬ ላይ የሚደገፉና ቁርአን
የሚቀሩ ነበር ቡኻሪይ301
ሙስሊም8/297

ስለ ወር አበባ በክርስትና

ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣው የደም
መፍሰስ ቢኖርባት የወር አበባ እርኩሰት
እስከ ሰባት ቀን ይቆያል በዚህ ጊዜ ማንም
ሰው ቢነካት እስከ ማታ ድረስ እርኩስ
ይሆናል የተጠቀመችበትን ማንኛውም
ነገር የነካ ሰው ልብሱን ይጠብ ሰውነቱንም
በውሀ ይታጠብ እስከ ማታ ድረስ ግን
እርኩስ ይሆናል ዘሌላውያን15:19-22

15. በሰርግዋ ምሽት ድንግል ያልሆነችዋን ሴት
ሁሉ ግደል (ዘዳግም 22:20-21)

16. 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3
7 እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ
ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር
በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ
እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን
ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ
አክብሩአቸው።

17. ‹‹ሴት ጊዜውን
እየጠበቀ የሚመጣውን የደም መፍሰስ
ቢሞርባት፤ የወር አበባዋ ርኩሰት እስከ ሰባት
ቀን ይቆያል፤ በዚህ ጊዜ ማንም ሰው
ቢነካት እስከማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡
የተቀመጠችበትን ማንኛውም ነገር የነካ
ሰው ልብሱን ይጠብ ፤ ሰውነቱንም በውሃ
ይጠብ ፤ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ
ይሆናል፡፡››(ኦሪት ዘሌዋውያን 15 19፡22)

18. 1 Timothy 5:9,10 ባልቴት በመዝገብ
ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፥
የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን
ያስፈልጋል፤
10 ልጆችን በማሳደግ እንግዶችንም
በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች
በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት
በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን
መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት
ልትሆን ይገባል።
11 ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን
አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው
ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና፤

19. እኔ ደሞ በጣም ከሚገርመኝ ነገር
በክርስትና አምነት ወንዶች ብቻ ለምን
ለህዝብ ቆጠራ የመረጣሉ
ዘኁልቁ1:1-2
ዘኁልቁ3:15

1፤ እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ
በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥
በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥
ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው
ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው።
የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ድምር፥
በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥
በየስማቸው ቍጥር፥ ወንዱን በየራሱ፥ ውሰዱ።ዘኁልቁ1:1-2

የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች
በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ
ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን
ቍጠራቸውዘኁልቁ3:15

20. ‹‹ወንድማማቾች
በአንድነት ቢቀመጡ አንድም ልጅ
ሳይኖረው ቢሞት የሞተው ሰው ሚስት
ልላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ
ነገር ግን የባልዋን ወንድም ወደ እርሳዋ
ገብቶ እርሰዋን ያግባ ከእርሰዋ ጋር
ይኑር፡፡›››(ኦሪት ዘዳግም 25፡5)

21. 9 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት
ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን
የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥
የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል
አላቸው።

11 እርሱም። ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ
ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤

12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ
ታመነዝራለች አላቸው።

18 ሚስቱንም የሚፈታ ሁሉ ሌላይቱንም
የሚያገባ ያመነዝራል፥ ከባልዋም
የተፈታችውን የሚያገባ ያመነዝራል።

22. በሰርግዋ ምሽት ድንግል ያልሆነችዋን ሴት
ሁሉ ግደል (ዘዳግም 22:20-21)

20፤ ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥
በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፥
21፤ ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ
ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ
የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥
በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ
ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ
ይውገሩአት እንዲሁም ክፉውን ነገር
ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

23. ዘፍጥረት 3፡16
“ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ በምጥ
ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በስቃይም
ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ
ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ
ይሆናል፡፡

24. <<ጥንቱንም ሃጢአት ከሴት ተገኘች : ስለ
እርሱዋም ሁላችንም እንሞታለን}}::
{መጽሐፈ ሲራክ25:23}

25. “ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥
እርስዋም ለባል የተሰጠች ዋጋዋም
ያልተከፈለ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥
ቅጣት አለባቸው፤ አርነት አልወጣችምና
አይገደሉም።”
ኦሪት ዘሌዋውያን 19:20

26. ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ
በሰገነት ማዕዘን መቀመጥ ይሻላል።
ምሳ 25፡27

27. መጽሐፈ ምሳሌ
19:13 ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ኀዘን ነው፥
ጠበኛም ሚስት እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ
ናት።

28. ሴተኛ አዳሪ
ከነልጆቻቸው ማግባት ይፈቀዳል ማለት
ነው???


ሆሴዕ 1
2 እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ
በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆሴዕን፦
ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ
ሸርሙጥና ታደርጋለችና ሂድና ሸርሙጣ
ሴትና የሸርሙጣንን ልጆች ለአንተ ውሰድ
አለው።.

29. ‹‹ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት
ብስጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን
ብመርገማ ሰባት ቀን ትቀመጣለች
የሚነካትም ሁሉ እስከማታ ድረስ እርኩስ
ነዉ፡፡ መርገምም ስትሆን የምትኛበት ነገር
ሁሉ እርኩስ ነዉ የምትቀመጥበት ነገር
ሁሉ እርኩስ ነዉ መኝታዋንም የሚነካ
ልብሱን ያጥባል በውሃም ይታጠባል እስከ
ማታም ድረስ እርኩስ ነዉ የምትቀመጥበት
ነገር ሁሉ የሚነካ ልብሱን ያጥባል
ብውሃም ይታጠባል
እስከማታም እርኩስ ነው››(ኦሪት
ዘሌዋዌያን 15፤19-22)

30. ሴት ልጅ ሰባት
ቀን ከማሃረሰቡ ተገልላ ብቻዋን
ተትቀመጣለች?????
ኦሪት ዘሌዋውያን21:9፤

31. የካህንም ልጅ
ራስዋን በግልሙትና ብታረክስ አባትዋን
ታረክሰዋለች፤ በእሳት ትቃጠል።

5 እነሆ፥
በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት
ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ
እገልጣለሁ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥
ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።
6 ርኵሰትንም በላይሽ እጥላለሁ፥
እንቅሻማለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።
ትንቢተ ሚልክያስ 2
2

32. መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ሴት ልጅ ትዋብ /
ትኳል የሚለው የቱ ጋር ነው ???

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3
1-2 እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥
ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት
የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን
ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ
ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ
ተገዙላቸው።

3 ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን
በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ
በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥
4 ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው
እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ
ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ
የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።

5 እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር
ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ
ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤
6 እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም። ጌታ ብላ
እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም
ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ
መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።

33. ኦሪት ዘኍልቍ
ምዕራፍ 5

14 በባልዋም ላይ የቅንዓት መንፈስ
ቢመጣበት፥ እርስዋም ስትረክስ ስለ ሚስቱ
ቢቀና፤ ወይም እርስዋ ሳትረክስ የቅንዓት
መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤

15 ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥
የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ ገብስ
ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤
የቅንዓት ቍርባን ነውና፥ ኃጢአትንም
የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና
ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም
አይጨምርበት።

16 ካህኑም ያቀርባታል በእግዚአብሔርም
ፊት ያቆማታል፤

17 ካህኑም የተቀደሰ ውኃ በሸክላ ዕቃ
ይወስዳል፤ ካህኑም በማደሪያው ውስጥ
ካለው ትቢያ ወስዶ በውኃ ላይ ይረጨዋል፤

18 ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት
ያቆማታል፥ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፥
በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን
የእህል ቍርባን፥ ለቅንዓት ቍርባን፥
ያኖራል፤ በካህኑም እጅ እርግማንን
የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል።

19 ካህኑም ያምላታል፥ ሴቲቱንም እንዲህ
ይላታል። ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም
አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ እንደ ሆነ፥
እርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ
ንጹሕ ሁኚ፤

20 ነገር ግን ባልሽን ትተሽ ረክሰሽ እንደ ሆነ፥
ከባልሽም ሌላ ከወንድ ጋር ተኝተሽ
እንደሆነ፤

21 ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ
ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን። እግዚአብሔር
ጭንሽን እያሰለሰለ ሆድሽንም እየነፋ፥
እግዚአብሔር ለመርገምና ለመሐላ
በሕዝብሽ መካከል ያድርግሽ፤

22 እርግማንንም የሚያመጣ ይህ ውኃ
ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ሆድሽንም ይንፋው፥
ጭንሽንም ያበስብሰው ይላታል፤ ሴቲቱም።
አሜን አሜን ትላለች።
23 ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ
ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ
ይደመስሰዋል፤

24 እርግማን የሚያመጣውንም መራራ
ውኃ ለሴቲቱ ይጠጣታል፤ የእርግማኑም
ውኃ በገባባት ጊዜ መራራ ይሆናል።

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቍርባን
ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም
ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት
ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም
ያመጣዋል፤

26 ካህኑም ከእህሉ ቍርባን አንድ እፍኝ
ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው
ላይ ያቃጥለዋል፥ ከዚያም በኋላ ለሴቲቱ
ውኃውን ያጠጣታል።

27 ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ
ይሆናል፤ ረክሳና በባልዋ ላይ አመንዝራ
እንደ ሆነች፥ እርግማንን የሚያመጣው
ውኃ ገብቶ መራራ ይሆንባታል፥ ሆድዋም
ይነፋል፥ ጭንዋም ይሰለስላል፤ ሴቲቱም
በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።
28 ያልረከሰች ያለ ነውርም እንደ ሆነች፥
ንጹሕ ትሆናለች፥ ልጆችንም ታረግዛለች።


33. ((ጌታው ሚስት አጋብቶት እንደሆነ ወንዶች
ወይም ሴቶች ልጆች ብትወልድለት
ሚስቱና ልጆችዋ ለጌታው ይሁኑ እርሱም
ብቻውን ይውጣ፡፡ባርያዉም፡-ጌታዬን
ሚስቴን ልጆቼን እወዳለሁና አርነት
አልወጣም ብሉ ቢናገር ጌታው ወደ
ፈራጆች
ይውሰደው ወደ ደጁ ወደ መቃኑ አቅርቡ
ጆሮዉን በወስፌ ይብሳው ለዘላለምም
ባሪያው ይሁን፡፡ሰውም ሴት ልጁን ለባርነት
ቢሸጥ ባሪያዎች እንደሚወጡ እርስዋ
አትውጣ፡፡ጌታውን ደስ ባታሰኘው በዎጆ
ይስደዳት ስለ ናቃት ለሌላ ወገን ሰዎች
ይሽጣት ዘንድ አይገባውም፡፡ለልጁም
ቢድራት ለሴት ልጆች የሚገባውን
ያድርግላት፡፡ከእርስዋ ሌላ ቢያጋባው
መኖዋን ልብስዋን ለምንጣፍዋም
ተገቢውን
አያጉድልባት፡፡ይህንም ሦሥት ነገር
ባያደርግላት ያለ ገንዘብ በከንቱ ትውጣ፡፡))
(ዘፀአት 21፡4-11)

34. ሚስቱን የሚፈታት
ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ ፡፡ እኔ
(እየሱስ)ግን እላችዋለሁ ያለ ዝሞት
ምክንያት ሚስቱን
የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያረጋታል
የተፈታችውን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል))
(ማቴዎስ 5፡31-32

35. ሚስት ባልዋ ቢሞት ወንድሙን ታግባ
አንድ ሴት ባልዋ ቢሞት የሟች ባልዋ
ወንድም እንድታገባ ህጉ ያዛል፡፡
የሚወለደው
የመጀመሪያ ልጅ በማEች ባልዋ ስም
የጠራል፡፡የማEች ወንድም ሴቲቱን
አላገባትም
የማለት መብት አለው፡፡ለሴቲቱ ግን ይህ
አማራጭ አልተሰጠም፡፡
((ወንድማማቾቹ በአንድነት ቢቀመጡ
አንድም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት የሞተው
ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ
ውጭ አትሂድ፡፡ነገር ግን የባልዋ
ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ
ከእርስዋ ጋር ይኑር….ከእርስዋ
የሚወለደው በኩር ልጅ በሞተው
በወንድሙ ስም ይጠራ፡፡…..))
(ዘዳግም25፡5-10)

36. ድንግል ካልሆነች ተወግራ ትሙት
በአባትዋ ቤት እያለች ያላገባች ሴት ድንግል
መሆን አለባት፡፡ድንግልና ሳይኖራት ያገባች
ሴት በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ህጉ
ያዛል፡፡ወንዶች ድንግልናቸውን ይጠብቁ
የሚል ሕግ ግን የለም፡፡
((ማናቸውም ሰው ሚስት
ቢያገባ…ድንግልናዋ ባይገኝ ብላቴናይቱን
ወደ አባትዋ ደጅ ያውጡአት፣
በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር
አድርጋለችና በአባትዋም ቤት የከተማዋ
ሰዎች እስከምትሞት ድረስ በድንጋይ
ይውገሩአት))
(ዘዳግም 22፡13-21)


* ሴት ልጅ በአዲስ ኪዳን ዘመን(በኢየሱስ ዘመን)

1 ፡-ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥
የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ
እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ
እወዳለሁ። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡
3)

2 ፡-1ኛ ቆሮንጦስ 14፡34 ላይ እንዲህ
ይላል«ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ ህግ
ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ
እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና፡፡ ለሴት
በማህበር መካከል መናገር ነውር ነውና
ምንም ሊማሩ ቢዱወዱ በቤታቸው
ባሎቻቸውን ይጠይቁ፡፡»ይላል

3 ፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ
ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ
ልትሰለጥን አልፈቅድም። (1ኛ ወደ
ጢሞቴዎስ 2፡12)

4 ፡-ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ
ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥፡፡
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡10-11)

5 ፡-ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ
ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ
ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል
አንድ ነውና። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
11፡5)

6 ፡-ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ
ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡
22)

7 ፡-ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ
ለባሎቻችሁ ተገዙ። (ወደ ቆላስይስ ሰዎች
3:18)

8 ፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ
ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ
ልትሰለጥን አልፈቅድም። አዳም ቀድሞ
ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች።
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎ11፡12)

9 ፡-የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ
ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም
ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ
ትድናለች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡
14-15)

10 ፡-ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር
ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት
ግን የወንድ ክብር ናት። ሴት ከወንድ ናት
እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና። ሴት ስለ
ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት
አልተፈጠረምና። ስለዚህ ሴት ከመላእክት
የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል።
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡7-10)
ይህ ነው እንግዲ ወንጌል የሚያስተምው
የሴቶች መብት

ታዲያ በዘመነ
አዲስ ኪዳን ነው ሴቶች ነፃ የወጡት?
—————————————————————-
መጀመሪያ የማቲልዳ ጆስሊን አስተያየት
እንቀበል ከዚያ ደግሞ የመጽሐፍ
“ቅዱስ”ን ከዚያ ደግሞ ያንተን አስተያየት
እንጠብቃለን
የአሜሪካ የሴቶች ጸረ ሰቆቃ ማህበር መሪ
የነበረችው ማቲልዳ ጆስሊን በክርስትና ስለ
ሴቶች የመናገር መብት እምነት እንዲህ
ስትል፤- ጽፋለች፡- “ጳውሎስ ሴቶች ዝም
እንዲሉ ባዘዘው መሰረት ሴቶች በአውሮፓና
በክርስቲያኑ አለም የመናገር መብት
አልነበራቸውም፡፡

ለምሳሌ፡- በ1833
እ.ኤ.አ መጀመሪያ በተቋቋመው ሴቶችና
ወንዶችን በአንድነት በሚያስተምረው
አሜሪካ ኦብርሊን ኮሌጅ ሴቶች በአብዛኛው
ክፍል ውስጥ እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም
ነበር ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶች ላይ የጣለወ
የመናገር እገዳ እስከ ተነሳበት ቅርብ ጊዜ
ድረስ ማንኛዋም ሴት ስለ ፖለቲካ ሆነ ስለ
ሌላ ጉዳይ ሀሷባን መግለጽ አይፈቀድላትም
ነበር፡፡ ለምሳሌ በእንጊሊዝ እ.ኤ.አ በ1664
በሄንሊ በተምስ አንዲት ሴት በፓርላማ
የተወሰነውን ግብር ጭማሪን በመተቸት
በቤተ ክርስቲያንና በፓርላማ የተወሰነውን
የግብር ጭማሪን በመተቸቷ በቤተ
ክርስቲያንና በፓርላማ ተወገዘች፡፡ ምላሷ
ወደ ውጭ ተስቦ በገበያ ቀን በመሀል ገበያ
ከዛፍ ጋር ታስራና የተቀጣችበትን ምክኒያት
የሚገልጽ ወረቀት ተለጥፎባት ውላ ነበር፡፡
(Matilda Joslyn Gage, Women,
Church and State, P.308-309 )
ይታያችሁ እንግዱ ይህ ነው እውነተኛ ፍርድ
ክርስቲያን ሰባኪዎች ሌትተቀን የሚነግሩን
በዘመን አዲስ ኪዳን ሴቶች ነፃ እንደወጡ
ነው፡፡ ግና በተጨባጭ ነፃ ወጥተዋልን
ህይወታቸውስ ከዘመነ ብሉይ ተሻሽሏልን?
በቀላሉ የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን
“ምኞት” ውድቅ ያደርጋሉ::
ዘመጽኩን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Sun Jul 10, 2011 3:13 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 2 guests