ሴቶች በመጽሀፈ (ቅዱስ)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ሴቶች በመጽሀፈ (ቅዱስ)

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 12:35 am

እውነት በዘመነ አዲስ ኪዳን ነው ሴቶች ነፃ የወጡት? ?

-----------------------------------------
የአሜሪካ የሴቶች ጸረ ሰቆቃ ማህበር መሪ የነበረችው ማቲልዳ ጆስሊን በክርስትና ስለ ሴቶች የመናገር መብት እምነት እንዲህ ስትል፤- ጽፋለች፡- “ጳውሎስ ሴቶች ዝም እንዲሉ ባዘዘው መሰረት ሴቶች በአውሮፓና በክርስቲያኑ አለም የመናገር መብት አልነበራቸውም፡፡ ለምሳሌ፡-
በ1833 እ.ኤ.አ መጀመሪያ በተቋቋመው ሴቶችና ወንዶችን በአንድነት በሚያስተምረው አሜሪካ ኦብርሊን ኮሌጅ ሴቶች በአብዛኛው ክፍል ውስጥ እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም ነበር ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶች ላይ የጣለወ የመናገር እገዳ እስከ ተነሳበት ቅርብ ጊዜ ድረስ ማንኛዋም ሴት ስለ ፖለቲካ ሆነ ስለ ሌላ ጉዳይ ሀሷባን መግለጽ አይፈቀድላትም ነበር፡፡ ለምሳሌ በእንጊሊዝ እ.ኤ.አ በ1664 በሄንሊ በተምስ አንዲት ሴት በፓርላማ የተወሰነውን ግብር ጭማሪን በመተቸት በቤተ ክርስቲያንና በፓርላማ የተወሰነውን የግብር ጭማሪን በመተቸቷ በቤተ ክርስቲያንና በፓርላማ ተወገዘች፡፡ ምላሷ ወደ ውጭ ተስቦ በገበያ ቀን በመሀል ገበያ ከዛፍ ጋር ታስራና የተቀጣችበትን ምክኒያት የሚገልጽ ወረቀት ተለጥፎባት ውላ ነበር፡፡ (Matilda Joslyn Gage, Women, Church and State, P.308-309 ) ይታያችሁ እንግዱ ይህ ነው እውነተኛ ፍርድ
ክርስቲያን ሰባኪዎች ሌትተቀን የሚነግሩን በዘመን አዲስ ኪዳን ሴቶች ነፃ እንደወጡ ነው፡፡ ግና በተጨባጭ ነፃ ወጥተዋልን ህይወታቸውስ ከዘመነ ብሉይ ተሻሽሏልን? በቀላሉ የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን "ምኞት" ውድቅ ያደርጋሉ፡-


1፡-ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3)


2፡-1ኛ ቆሮንጦስ 14፡34 ላይ እንዲህ ይላል«ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ ህግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና፡፡ ለሴት በማህበር መካከል መናገር ነውር ነውና ምንም ሊማሩ ቢዱወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ፡፡»ይላል


3፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡12


4፡-ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥፡፡(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡10-11)


5፡-ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡5)


6፡-ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡22


7፡-ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ። (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:18)

8፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎ11፡12)


9፡-የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡14-15)

10፡-ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት። ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና። ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና። ስለዚህ ሴት ከመላእክት የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡7-10)

ይህ ነው እንግዲ ወንጌል የሚያስተምው የሴቶች መብት
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 3:59 pm

የሴቶች መብት በኢስላምና በክርስትና
ሴት ብቻ ለምን ትሸፈን?
------------------------------
መጽሐፍ ቅዱስ ወንድ መሸፈን የሌለበትን ምክኒያት እንዲህ ሲል ይገልጻል፡-
‹‹ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም›› (1ኛ ቆሮንቶስ 11፡7) የክርስቲያን ምሁራን እንዲህ ሲሉ ማብራሪያ ጽፈዋል›-

‹‹ወንድ ራሱን መከናነብ የማይገባበት ምክኒያቱ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጨረሻና መደምደሚያ ሆኖ በእግዚአብሔር መልክ ስለተፈጠረ በእርሱም ሁሉ ስለ ተገዛ ነው፡፡ (ዘፍ. 1›26፡28) እርሱ የእግዚአብሔር ክብር አክሊልም ነውና የተገዢ ምልክት አሳይቶ ራሱን መከናነብ አይገባውም፡፡ ሴት ግን ስትፈጠር ከወንድ (ዘፍጥ. 2፡21-23) እና ስለ ወንድ ስለ ተፈጠረች(ዘፍጥ. 2፡18)እርስዋ የወንድ ክብር ናትና ከስልጣን በታች መሆንዋን የሚያመለክተው ያራስ መሸፈኛ ሊኖራ ይገባል፡፡››የመጀመሪያይቱ የሐዋሪያ ጳውሎስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች፤ ገጽ 89

በኢስላም አስተምሮ ሴት መሸፈን ያለባት ከወንድ ስለምታንስ አሊያም ከወንድ ስልጣን ስር መሆኗን እንድታሳይ ሳይሆን ለራሷ ክብርና በሴት ልጅ አማላይ ገላ በቀላሉ ወንዱ ስሜቱ ተነሳሰቶ ሁለቱም ለጥፋት እንዳይዳረጉ ለመጠበቅ ነው፡፡ ከወንዱ ስሜት የሌላት(በባልነት) እንደ ልጃገረዷ ያለ ሂጃብን እንድታደርግ አትገደድም፡፡ ይህንንም አላህ(ሱ.ወ) በቁርአን እንዲህ ሲል ይገልጻል፡-
‹‹ከሴቶች እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉ(ከወንድ ስሜት ያጡ) ባልቴቶች በጌጥ የተገለጹ ሳይሆኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ(ባያደርጉ) ኋጠአት የለባቸውም፡፡››(ሱረቱ አል-ኑር፡60)
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 5 guests