የሴቶች መብት በእስልምና በክርስትና !!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የሴቶች መብት በእስልምና በክርስትና !!!!

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 12:52 am

የሴቶች መብትና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {Part-1}ምስጋና ለአላህ ይገባው ሰውን ከአንዲት ነፍስ ፈጥሮ ጥንድ ላደረገው! እንዲሁም ዝግ ልቦችን በወህይ(በአላህ ራዕይ) ለከፈቱ፤ የታወሩ አይኖችን በእውቀት ላበሩ ደንቆሮ ጆሮዎችን ጥበብ እንዲሰሙ ላደረጉት ነብዩ ሙሐመድ ፤ የአላህ እዝነትና ሰላም ይስፈንባቸው፡፡
ይህ ርዕስ በተከታታይ የሚቀርብ ሲሆን የጹሁፉ ዋናው አላማም ኢስላም ለሴት ልጅ ያጎናጸፋትና ክብርና መብት በሰፊው የሚዳሰስበት እንዲሁም የሴትን ልጅ መብት አስመልክቶ ኢስላም ላይ የሚነሱ ውንጀላዎች በቂ መልስ የሚሰጥበት ርዕስ ነው፡፡ ውሸት ሲደጋገም ‹‹እውነት ይሆናል›› ሳይሆን ‹‹እውነት ይመስላል›› እንዲሉ ኢስላም ሴትን ልጅ ይጨቁናል የሚለውም አስተሳሰብ አሁንም ቢሆን የራሳቸውን እምነት በጥልቀት ባለማወቅ እና ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ከመላካቸው በፊት እንዲሁም ከተላኩም በኋላ ከኢስላም ውጭ ያሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሴት ልጅ የነበራቸውን አመለካከት በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ የሴቶች መብትና እና እኩልነት በሚል ርዕስ የሚቀርበው ተከታታይ ትምህርት ‹‹እውን ኢስላም ሴቶችን ነጻ አውጥቷል ወይስ ሴቶችን ጨቁኗል?›› በዚሁ ርዕስ በሰፊው የሚዳሰስ ይሆናል ኢንሻአላህ!!!

ወደዋናው ርዕሳችን ከመጋባታችን በፊት ለመግቢያ ያህል ከነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መላክ በፊት የነበሩት የተለያዩ እምነት አራማጆች እነ አንጋፋ ስልጣኔዎች ለሴት ልጅ የነበራቸውን አመለካከት በአጭሩ እንመልከት፡-

የሴቶች መብትና እኩልነት ከታሪክ ማህደር

ሴቶች በአይሁዶች ዘንድ
አይሁድ ወንዶች ሴት ሆነው ባለመፈጠራቸው ዘውትር ጠዋት ለፈጣሪ የምስጋና ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ ኢትዮጲያዊቷ ሙሉ ደቦጭ ‹‹ጣዝሙት›› በተሰኘው መጽሐፋቸው እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡- ‹‹ አይሁዳዊ ታሪክ ምሁር የነበረው ጆስፈም ሴት በሁሉም መንገድ ከወንድ እንደምታንስ ለማስረዳት ተሞክሯል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአይሁድ ባህል በሴቶች ላይ ምን አይነት አመለካከት እንደነበረው ዊልያም በርክሌይ በታልሙድ ውስጥ እንደሚከተለው ገልጾታል፡- ‹‹በአይሁዶች የጠዋት ጸሎት ….እያንዳንዱ አይሁዳዊ ወንድ እግዚአብሔር አሕዛብ ፤ ባሪያ ወይም ሴት አድርጎ ስላልፈጠረው አምላክን ያመሰግናል፡፡….በአይሁዶች ህግ ሴት ዕቃ እንጂ ሰው አይደለችም፡፡ ምንም አይነት ህጋዊ መብት የላትም፡፡ ባሏ የፈለጋትን ሊያደርጉ ይችላል፡፡›› (ሙሉ ደቦጭ፤ ጣዝሙት ፤ የሴቶች አገልግሎት ቤተሰባዊ ክርስቲያናዊ ማህበራዊ፤ ገጽ 3)
ኢንሳይክሎፒድያ ባብሊካ ሲያብራራ፡- ‹‹ አንድ ሰው ሚስት አጨ ማለት ገንዘብ በመክፈል ልጅቷን የራሱ አደረገ ማለት ነው፡፡፤ ጋብቻው ህጋዊ ይሆን ዘንድ የልጅቷ ፈቃደኝነት አስፈላጊ የለውም ፡፡ አስፈላጊ ስለመሆኑ በሕጉ ውስጥ የትም ላይ አልተመለከተም፡፡›› (Allen, E.A., History of Civilization, Vol. 3, p. 2942)
ኢንሳይክሎፒድያ ጁዲካ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሚስት የባሏ ንብረት ተደርጋ ትወሰድ ነበር፡፡ ሚስት ዝሙት ብትፈጽም ባል ብቻ በርሷ ላይ ያለው ግኑኝነት የማድረግ መብቱን እንደጣሰች ተደርጋ ትቆጠር ነበር፡፡ ሚስት ግና በባሏ ላይ እንዲህ ያለ መብት አልነበራትም፡፡››(Rosmary Ruther ‘’ Christianity’’ in Arvind Shaurme, ed women world Religions, P. 209 )
ሙሉ ደባጭ ‹‹ጣዝሙት›› መጽሐፋቸው የኦሪት ተከታይ የሆኑት አይሁዳውያን ስቴን ልጅ ስለ ማስተማር ስላላቸው አመለካከት እንዲህ ጽፈዋል፡- ‹‹እንዲሁም ደግሞ ሴትን የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር ተገቢ እንዳልሆነ ይነገር ነበር፤ ታልሙድ እንደሚለው ‹‹የእግዚአብሔርን ቃል ለሴት ከማስተማር ማቃጠል ይሻል ነበር››(ሙሉ ደቦጭ፤ ጣዝሙት ፤ የሴቶች አገልግሎት ቤተሰባዊ ክርስቲያናዊ ማህበራዊ፤ ገጽ 8)

ሴቶች በሂንዱ ዘንድ

የሂንዱ ማኑ ኮድ እንደሚለው ሴቶች ሁሌም በአሳዳሪዎቻቸው ስራ በጥገኝነት ያለነፃነት መኖር አለባቸው፡፡ እንዲህ ይላል ፡- ‹‹በልጅነቷ በአባቷ ሥር መገዛት አለባት ፡፡ ሴት መቼም ቢሆን ከመገዛት ነፃ መሆን የለባትም፡፡››(The Hindu code of Manu (C. 100CE))
ኢሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ የህንድ ሴትን ማዕረግ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
‹‹ዋናው የህንድ መመሪያ ሴት በወንድ መታዘዝ ነው፡፡“ማኑ” እንደሚለው ሴቶች ሌት ተቀን በመከታዎቻቸው ስር በጥገኝነት ይኖራሉ፡፡የውርስ ህግ አያውቃቸውም ፤የውርስ ንብረት ሴቶችን ሳያጠቃልል በወንዶች ብቻ ይከፋፈላል፡፡›› (The Encyclopedia Britannica 11thed. 1911, Vol. 28, P.782.
‹‹በሂንዱ ጽሁፎች ውስጥ የጥሩ ሚስት መግለጫ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡-‹‹አዕምሮዋ፣ ንግግሯና ሰውነቷ በወንዱ የተገዛች የሆነችና በዚህም ዓለም በሚቀጥለውም ዓለም ከፍተኛ ዝና ትጎናፀፋለች፣ ከባሏ ጋርም አንድ ቤት ይኖራሉ፡፡›› (In Mace, David and Vera, Marrige East& west, Dolpin Books, Double day and Co., Inc…,N.Y…1960)
የአቴናዊያን ሴቶች ከህንዳዊያን ወይም ከሮማዊያን የተሸሉ አይደሉም፡-
‹‹የአቴናዊያን ሴቶች ሁሌ ዝቅተኛ ፣ለአንዳንድ ወንዶች ማለትም ለአባቶቻቸው ለወንድሞቻቸውና ለሌሎችም ለሁሉ ዘመዶቻቸው ተገዢ ነበሩ፡፡››(Allen, E.A., History of Civilization, Vol. 3, p. 444.)
ትዳር በተመለከተ የርሷ መስማማት በአጠቃላይ አስፈላጊ አልነበረም፡፡
‹‹የቤትሰቧ ፍላጎቶች ግዴታ የሚሆንባትና የሚያመጡላት ባል የርሷ ጌታ ሲሆን ለርሷም እንግዳ ቢሆንም መቀበል አለባት፡፡››(Allen, E.A., History of Civilization, Vol. 3, p. 443)

‹‹በግሪክ አፈ ታሪክ መሰረት ልክ የአይሁዶች አፈታሪክ የድክመትና ኃጢአት ጀማሪ ሔዋን እንደነበረች እንደሚያትት ሁሉ ‹‹ፓንዶራ›› በመባል የምትባል የምትጠራ ምናባዊ ሲትም የሰው ልጅ ችግሮችና መጥፎ እድሎች ምንጭ ተደርጋ ትወሰድ ነበር ፡፡ ግሪካውያን ሴት ሴትን በህብረተሰብ ውስጥ በማናቸውም መንገድ ከወንዱ በታች አድርገው ከመውሰዳቸውም በላይ እንደጎዶሎ ፍጡር ይቆጥራት ነበር፡፡ በግሪካውያን ዘንድ መናቸውም ዓይነት ክብርና የኩራት ማዕረግ የወንዱ ጾታ ብቻ ነበር፡፡(አቡልአዕላ አልመውዱዲ፤ አል-ሒጃብ፤ ገጽ 12)

በታሪክ የአዋቂዎች የሮማዊያን ሚስት እንዲህ ተገልፃለች፡፡ ‹‹ምንም የማታውቅ፣ ዝቅተኛ፣ታዳጊ ልጅ፣ በራሷ ፍላጎት ምንም መስራት ወይም ማቀድ የማትችልና ባሏ ሁሌ የርሷ ኃላፊና ጠባቂ ሲሆን በባሏ ስርም የምትኖር ናት፡፡››(Allen, E.A., History of Civilization, Vol. 3, p. 550)
በሮማዊያን የስልጣኔ ጊዜ የነበረው የሴቶች ህጋዊ ማዕረግ በኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በሮማዊያን ህግ በታሪካዊ ግዜያቶችም ወቅት ሴት በሙሉ ጥገኛ ነበረች፡፡ስታገባ እርሷና ንብረቷ ወደ ባሏ ይዛወራል….. ሚስት ባል የሚገዛት ንብረት ነበረች፡፡ማለትም ባርያ ለጥቅምብቻ እንደሚገዛ ትገዛ ነበር፡፡ሴት አንድም የመንግስት ወይም የህዝብ ቢሮ ውስጥ መስራት አትችልም….. ምስክር፣ ዋስ፣ አስተማሪ ወይም የሙዝየም (ቤተ መዘክር) ኃላፊ መሆን አትችልም፡፡የሰው ልጅ ማሳደግ ወይም እርሷ በራሷ በጉዲፈቻ ማደግ ወይም ኑዛዜ ማድረግ ወይም ውል መዋዋል አትችልም፡፡››(The Encyclopedia Britannica 11thed. 1911, op.cit Vol. 28, P.782.)
አንዲት ሮማዊት ሚስት በአንድ የታረክ ምሑር እንደሚከተለው ተገልጻለች፡- ‹‹ሕፃን፤ ለሙሉ ሰውነት ያልበቃች ፤ በሞግዚት ስር የምትተዳደር ፤ በራሷ ግላዊ ፍላጎት ምንም ለማድረግ የማትችል ግለሰብ፤ ሁሌም በባሏ ሞግዚትነትና በጥበቃው ስር የምትተዳደር ፍጡር….›› (Allen, E.A., History of Civilization, Vol. 3, p. 550)
የሮማውያን ስልጣኔ ጫፍ ደርሷል በሚባልበትዘመን እንኳ አንድ ሮማዊ ወንድ ሚስቱን የመግደል ሙሉ መብት የሰጠው ነበር፡፡(ዶ/ር ዛኪር ናይክ፤ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ስለ እስልምና የሚጠይቋቸው የተለመዱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፤ ገጽ 14)

የእስካንዲኔቪያን ሴቶች ስልመለከት፡-

‹‹ቢያገቡም ባያገቡም ያለማቋረጥ በኃላፊያቸው ስር ይኖራሉ፡፡ እስከ አስራ ሰባተኛ ክፍለ ዘመንመጨረሻ ማለትም የክርስትና ህግ መንግስት መጨረሻ ይሰራበት የነበረው ህግ አንድ ሴት ያለ ኃላፊዋ ፈቃድ ብታገባ ኃላፊዋ ከፈለገ በህይወት እስካለች ድረስ ንብረቷን ማስተዳደር ይችላል፡፡››(The Encyclopedia Britannica 11thed. 1911, op.cit Vol. 28, P.783.)
የእንግሊዛዊያን ህግ ስንለመለት፡-

‹‹….በጋብቻ ወቅት ሚስት የነበራትን ማንኛውንም ንብረት የባሏ ይሆናል፡፡በጋራ በሚመሩት ኑሯቸው ወቅት መሬትን ማከራየትና የእርስዋ ንብረት ትርፍ ላይ ኃላፊ ባል ነበር፡፡ጊዜያቶችንም አልፈው የእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ያለ ሚስት ፈቃድ ንብረት ወደ ባል እንዲዛወር መመሪያ አረቀቀ፡፡ሆኖም ባል ንብረትን እንዲቆጣር ፣ምርትን ፣ትርፍ ገንዘብን እንዲቀበል መብቱ እንደተጠበቀለት ነበር፡፡የሚስትን ንብረት በተመለከተ የባል ተፅእኖ ፍፁም ነበር፡፡እንዳስፈለገው ቢያወጣ መብት ነበረው፡፡››(The Encyclopedia Americana International(Edition) Vol. 29, P.108.)

በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ነበር ሁኔታው መቀየር የጀመረው፡፡
‹‹በተደጋጋሚ የወጡት ህጎች ፡-የመጀመሪያ የ1870 ያሉት ሴቶች ንብረት ህግ፣ የ1882ና በማሻሻል የወጡ ህጎች እንደ ሴተላጤዎች (ያላገቡ ሴቶች) ፣ባል የሞተባቸው ፣ፈት ሴቶች ሁሉ ያላገቡ ሴቶችም ውል እንዲያደርጉ የሚል መብት ተቀዳጁ፡፡››(The Encyclopedia Britannica 1968, Vol. 23, P.624.)

እስከ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የጥንታዎ ህግ አዋቂ የነበረው ስር ሄንሪ ማይን እንዲህ ሲል ፅፌዋል ፡- ‹‹የክርስቲያን ድርጅቶችን ማንኛውም ሃሳብ የማይጠብቅ ህብረተሰብ ካለ ያገቡ ሴቶች የግል መብት ያረጋገጠላቸውን የመካከለኛውን የሮማዊያን ህግ የሚመስልነው፡፡›› (Quoted in Maca, Marriage East and west, Op. cit, P.81)
ጆን እስቲዎርት ‹‹ዘ ሳብጀክሽን ኦፍ ውሜን›› በሚለው ፅሁፍ፡-
‹‹ስልጣኔና ክርስትና የሴት ፍትሃዊ መብቷን የመለሱ ተደርገው ነበር ተደጋግሞ የተነገረን፡፡ ግን ሴት ትክክለኛ የባል አገልጋይ. . . . ህጋዊ ግዴታዋ እስካሁን ድረስ በተለምዶ ባሪያዎች ከሚባሉት አትለይም፡፡››(Quoted in Maca, Marriage East and west, Op. cit, P.81)

የቁርአን ትእዛዞች የሴትን ማዕረግ ወይም ደረጃ በተመለከተ ያሰፈሩትን ከማየታችን በፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዞች በጥቂቱ ብንመለከት ጉዳዩን በበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ይህም ለማያዳላ ግምገማ ጥሩ መሰረት ይሰጣል፡፡

የቀድሞ የአሜሪካ የሴቶች ጸረ ሰቆቃ ማህበር መሪ የነበረችው ማቲልዳ ጆስሊን በክርስትና ስለ ሴቶች የመናገር መብት እምነት እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- ‹‹ጳውሎስ ሴቶች ዝም እንዲሉ ባዘዘው መሰረት ሴቶች በአውሮፓና በክርስቲያኑ አለም መናር መብት አልነበራቸውም ፡፡ ለምሳሌ በ1833 እ.ኤ.አ መጀመሪያ በተቋቋመው ሴቶችና ወንዶችን በአንድነት በሚያስተምረው በአሜሪካ ኦበርሊን ኮሌጅ ሴቶች በአብዛኛው ክፍል ውስጥ እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶች ላይ የጣለው የመናገር እገዳ እስከተነሳበት ቅርብ ጊዜ ድረስ ማንኛዋም ሴት ስለፖለቲካ ሆነ ሌላ ጉዳይ ሀሳቧን መግለጽ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ እ.ኤ.አ. በ1664 በሄንሊ በተምስ አንዲት ሴት በፓርላማ የተወሰነውን የግብር ጭማሪን በመተቸቷ በቤተ ክርስቲያንና በፓርላማ ተወገዘች፡፡ ምላሷ ወደ ውጭ ተስቦ በገበያ ቀን በመሀል ገበያ ከዛፍ ጋር ታስራ የተቀጣችበት ምክኒያት የሚገልጽ ወረቀት ተለጥፎባት ውላ ነበር፡፡›› (Matilda Joslyn Gage, Women, church and State, P. 308-309)

በሙሴ ህግ ስለሚስት የሰፈረውን ኢሳይክሎፒዲያ ባይብሊካ ሲገልጽ፡- ‹‹አንድ ሰው ሚስት ሲያጭ ማለት በቀላሉ እርሷን በገንዘብ ክፍያ ማግኘት ማለት ነው፡፡››(Encyclopedia Biblica, 1902, Vol.3 P.2942)
ከህግ አንፃር ሲመለከቱት ለትራርዋ ህጋዊነት የሴቷ መስማማት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ‹‹ የሴቷ መስማማመት ያለአስፈላጊ ነው፤ የርሷ የጋብቻ ፈቃደኛ መሆን አለመሆን በህግ ላይ አልተገለፀም፡፡›› (Ibid., P.2942)
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ሙስሊሙ በሚያምንበት በቀደምት ከተረጋገጡት( ሐይማኖቶች) እምነቶችና የመጀመሪያው ጽሁፋች ጋር አሁን ካሉት ሐይማኖታዊ ድርጅቶች አሰራር ጋር በእርግጥ የማይጣጣም ነው፡፡
የፍቺን መብት በተመለከተ ኢሳይክሎፒዲያ ባይብሊካ ይህን እናነባለን፡-‹‹ሴቷ የወንዱ ንበረት እንደመሆኗ መጠን እርሱ እርሷን እንደፈለገ የመፍታት መብት አለው፡፡ለመፍታት ሙሉ መብት ያለው ባል ብቻ ነበር፡፡ ‹‹ከሙሴ ህግ ፍቺ የወንድ ብቻ ልዩ መብት ነበር….፡፡›› (Ibid., P.2947)
የቤተክርስቲያን አቋም እስከ ቅርብ ክፍለ ዘመን ድረስ በሙሴ ህግና በጊዜው የበላይነት በነበራቸው ባህሎችና የሐሳብ አመለካከት ተፅእኖ ነበረባት፡፡
ዴቪድ ቬራሚክ “ሜሬጅ ኢስት ኤንደ ዊስት” በሚለው መጽሐፋቸው የሚከተለውን ጽፈዋል፡-
‹‹የወረስነው የክርስትና እምነታችን ፍርዶችን ከማጓደል ነፃ ነው ብሎ የሚገምት የለም፡፡በቀድሞ የቤተክርስቲያን አባዎች አነስታይ ፆታን በዝቅተኝነት የገለፁ ጽሁፎችን ተመሳሳይ ማግኘት አዳጋች ይሆናል፡፡የታወቀው የታሪክ ምሁር ሌኪ እንደተናገረው (አባዎች ከፃፍዋቸው በጣም ያልተለመዱ በጣም እንግዳ ችግሮች ሁሉ ሴት የሃጢያት ሁሉ እናት እንደሆነች ትቆጠር ነበር፡፡ሴት በመሆኗ ልታፍርበት ይገባታል፡፡በዚህ አለም ላይ ባመጣችው እርግማን ያለ ንስሐ በቅጣት ያለማቋረጥ መኖር አለበት ፡፡በልብሷ ማፈር አለባት፤ ምክንያቱም የእርሷመውደቅ መታሰቢያ ነው፡፡በተለይ በውበቷ ማፈር አለባት፤ ምክንያቱም ዋናው የሰይጣን መሳሪያ ነውና)፡፡ሌላው በሴት ላይ የተደረገው በጣም ፀናፊ ንግግር የቴርተሊያው ነው ፡- “እናንተ ሴቶች ታውቃላችሁ እያንዳአንዳችሁ ሴት መሆናችሁን? እግዚያብሔር በዚህ ፆታ ላይ የፈረደው ፍርድ ጥፋቱ አሁንም በዚህ ፆጻና ኑሮውስጥ ያለ ነው፡፡እናንተ የሰይጣን በሮች ናችሁ፡፡የተከለከለውን የዛፍ ፍሬ በመብላት ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጣሪን የከዳችሁ እናንተ ናችሁ፡፡አዳምን በማሳመን ጉብዝና በሌለው ሰይጣን እንዲጠቃ ያደረጋችሁ እናንተ ናችሁ፡፡የእግዚያብሄርን ምስል ሰው በቀላሉ ያጠፍችሁ፡፡
በእናንተ ሰበብ የእግዚያብሔር ልጅ እንዲሞት ተደረገ፡፡”ቤተክርስቲያን ሴቶችን በዚህ ሁኔታ በዝቅተኝነት ብቻ ሳይሆን የምትመለከተው ከዚህ በፊት ሴት የነበራትን ህጋዊ መብቷንም ጭምር ነበር የከለከለቻት፡፡›› ( Mace, Marriage East& west Op. cit, PP. 80-81)

ሴቶች በኢስላም

ኢስላም በመጣበት ዘመን ከፊል የሰው ልጆች የሴትን ልጅ ሰብአዊ ፍጡርነት በእርግጠኝነት አይቀበሉም ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ ቢያንስ ይጠረጥሩታል፡፡ አንዳንዶች ሰብዓዊ ፍጡርነቷን ቢቀበሉም ወንዶችን ለማገለገል እንደተፈጠረች አድርገው ይቆጥሯታል፡፡

ኢስላም ምስጋና ይግባውና ሴትን ከእንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ነፃ አወጣ፡፡ ሰብአዊ ፍጥረቷን አፀና፡፡ ኃላፊነቷን የመሸከም ፤ የተጠያቂነት እና በስራዋም ጀነትን የመጎናጸፍ ብቃት እንዳላት አረጋገጠ፡፡አለም የድንቁርአን ጥቁር መጋረጃ ባካበበት ዘመን መካከል ለሰው ልጅ የሚያገለግል አዲስ የሚደነቅና ሁለንተናዊ የፈጣሪ መመሪያ በሰፊው በአረብያ አስተጋባ

የተከበረች ሰብአዊ ፍጡር እንደሆነች አወጀ፡፡ ልክ ከወንዱ ጋር እኩል የሰብአዊ መብቶች ተጋሪ አደረጋ፡፡ ሁለቱም የአንድ ግንድ ቅርንጫፎች ናቸውና፡፡ ወንድማማቾች ናቸውና ፡፡ የአንድ አባላት የአንድ እናት ልጆች ፡፡ የሃዋና የአደም ክፋዮች ፡፡ በአፈጣጠር እኩል ናቸው ፡፡ በኃላፊነት ተጠያቂነት እኩል ናቸው፡፡ በምንዳና ፍጻሚ እኩል ናቸው፡፡ አንጸባራቂው ቁርአን ይህንን በማስመልከት እንዲህ ይላል፡-

۞ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا [٤:١]
‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም ተጣማሪዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከሁለቱም በርካታ ወንዶችንና ሴቶች ያበዛውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ያን በርሱ (የጋራ መብቶቻችሁን)የምትጠያየቁበትን አላህን ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡ ›› (ሱረቱ አል-ኒሳእ ምዕ.4 ቁ.1)
አንድ ምሁር ይህን የቁርዐን ጥቅስ አስመልክቶ እንዳሰፈረው፡- ‹‹ እንደሚታመነው ሴት ስብአዊ ፍጡርነት በሁሉም አቅታጫ እንዲህ በሚያስደንቅ አጭር አገላለጽ ጥልቀትና አዲስነት ባለው ጥበብ የተሞላበት የፈጣሪ ህግ ማሳመኛ በማኛውም ፅሁፍ በአሮጌውም በአዲሱም የለም፡፡››(El-khouly, Al Bahly, ‘min usus kadiyat Almar’ah’ (Al-wa’ay-Islam, ministry ok wakf, Kuwait, Vol.3, No.27, June 9,1965) p.17)
በመሆኑም የሰው ልጆች በአጠቃላይ -ሴቶችንም ወንዶችንም አምላካቸው የፈጠራቸው ከአንዲት ነፍስ ነው፡፡ ይህችም ነፍስ ምሉዕነትን ትጎናፀፍ ዘንድ ተጣማሪዋን አደረገላት፡፡ ይህንንም በሌላ አንቀጽ እንዲህ ገልጾታል፡-

وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا
‹‹ እርሱያ ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ፤ ከርሷም ተጣማሪዋን ይረካበት ዘንድ የፈጠረ (አምላክ)ነው››(ሱረቱ አል-አዕራፍ ምዕ.7 ቁ189)
ከዚህች አንድ ቤተሰብ አስገኘ፡፡ ሁሉም የአንድ አምላክ ፍጡሮች ናቸው፡፡ የአንድ አባትና የአንዲት እናት ልጆች ናቸው፡፡ እናም በወንድማማችነት ተሳስረዋል፡፡ ይህም በመሆኑ አንቀጻ የሰው ልጆች አመምላካቸውን እንዲፈሩ ዝምድና ትስስራቸውን እንዲጠብቁ አዘዘችሰ፡-

وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ
‹‹ያን በርሱ (የጋራ መብቶቻችሁን)የምትጠያየቁበትን አላህን ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡ ›› (ሱረቱ አል-ኒሳእ ምዕ.4 ቁ.1)
በሌሎች አናቅጽ መልዕክት መሠረት ወንድ የሴት ወንድም ነው፡፡ ሴትም የወንድ እህት ናት፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ›አ›ወ) ሲናገሩ፡- ‹‹ ሴቶች የወንዶች እህቶች ናቸው፡፡››(አህመድ፤ አቡዳውድ፤ ቲርሚዚና ዳርማይ ዓኢሻን ዋቢ በማድረግ ዘግበውታል)
በመለኮታዊ ትእዛዙ ፤ በአምልኮዎቸና በሃይማኖታዊ አጀንዳዎች ሴት ልጅ ክወንድ እኩል መሆኑን ቁርአን ሲያስተምር፡-

إِنَّ الْمُسْلِمِينَ وَالْمُسْلِمَاتِ وَالْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَالْقَانِتِينَ وَالْقَانِتَاتِ وَالصَّادِقِينَ وَالصَّادِقَاتِ وَالصَّابِرِينَ وَالصَّابِرَاتِ وَالْخَاشِعِينَ وَالْخَاشِعَاتِ وَالْمُتَصَدِّقِينَ وَالْمُتَصَدِّقَاتِ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا [٣٣:٣٥]
‹‹ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡››(ሱረቱ አል-አህዝብ ምዕ.33 ቁ.35)

በሃይማኖታዊና ማህበራዊ ሃላፊነቶች ቁርአን ሁለቱንም ጾታዎች እኩል ያደርጋለን ፡፡

وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ [٩:٧١]
ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡(ሱረቱ አል-ተውባ ምዕ.9 ቁ.71)
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 1:01 am

የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {Part-2}…….መንሳዊ ህይወትን በተመለከተ ሴቶችም በአላህ ዘንድ ከወንዶች ጋር እኩል ደረጃ እንደሚታዩ በተከበረው ቁርአን ውስጥ በማያሻማ ሁኔታ ተገልጿል አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-

كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ [٧٤:٣٨]

‹‹ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ተያዥ ናት›››(ሱረቱ አል-ሙደሲር 74፡38)

فَاسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّي لَا أُضِيعُ عَمَلَ عَامِلٍ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ ۖ بَعْضُكُم مِّن بَعْضٍ

‹‹ጌታቸውም ‹‹እኔ ከናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሰሪን ስራ አላጠፋም፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው በማለት ልመናቸውን ተቀበለ፡፡››(ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡195)

مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ [١٦:٩٧]

‹‹ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡›› (አል-ነህል 16፡97)

وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا [٤:١٢٤]

‹‹ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡››(ሱረቱ አል-ኒሳእ 4፡124)

يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ [٤٩:١٣]

‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡››(ሱረቱ አል-ሁጁራት 40፡13)

ከላይ ያየናቸው የቁርአን አንቀጾች እንደሚያመለክቱት ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንዱ በመንፈሳዊ ህይወት አላህ(ሱ.ወ) ዘንድ እኩል ናት ፡፡

አዳምን ያሳሳተችው ሄዋን ወይስ ዳቢሎስ ?

በክርስትና ሃይማኖት የመጀመሪያዋ እንስት-ሄዋን አዳምን ያሳተች፤ ሞትን በሰው ዘር ያመጣች ተደርጋ ትቆጠራለች፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን እውነታ እንዲህ ይገልጻል፡- ‹‹የበለስ ፍሬን ከበላች በኋላ መጥታ የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ፍጥረቱን አዳምን አሳተችው የፈጣሪዋን ትእዛዝ ስለተዳፈረች በሱም በልጆቹም ላይ ሞትን አመጣች፡፡(መጽሐፈ መቃቢያ ሣልስ 3፡6)

በሌላ ምዕራፍ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ የተሳሳተችው ሄዋን እንጂ አዳም እንዳልሆነ ይገልጻል፡- ‹‹የተታለለም አዳም አይደለም ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፡፡ ››(1ኛ ጢሞቲዎስ 2፡14 )
የክርስትና ሃይማኖት ምሁር ሄዋን ፈጸመች የተባለውን ስህተት በተመለከተ እንዲህ በማለት ጽፈዋል፡- ‹‹እግዚአብሔር በሴቲቱ ሄዋን ላይም ፍርድና አዝዞአል (ኦሪት ዘፍጥረት ቁ.16)፡፡ ሁለት ፍርዶችን አዘዘባት ምንም እንኳ ልጅ የመውለድ አስደሳች ልምድ ቢኖራትም ልጅ የመውለድ ሂደት ከፍተኛ የህመም ስቃይ ያስከትልባታል፡፡ ዛሬ ልጅ በሚወልዱበት ጊዜ ሴቶች ሁሉ ይህን ፍርድ ይቀበላሉ፡፡ ሁለተኛ በባልና ሚስት መካከል የነበረው የእኩልነት ግንኙነት ይቀራል፡፡ ከውድቀት በፊት ለባል ተሰጠ፡፡ኃጢአት በመስራ ሂደት ሔዋን ቀዳሚውን ሚና ስለተጫወተች እርሷና ከእርሷ በኋላ የሚመጡ ሴቶች በወንዶች በሚገዙበት ግንኙነት ለመኖር ተገደዱ፡፡›› (ቲሞ ፌሎስ፤ የኦሪት ዘፍጥረት፤ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፤ ገጽ 92)

‹‹ኦሪት ዘፍጥረት 3፡16 «ለሴቲቱም አለ፡-በፀነስሽ ጊዜ ጭንቀትሽ እጅግ አበዛለሁ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽ ለባልሽ ይሆናል፡፡ እርስም ገዢሽ ይሆናል፡፡»

መምህር ኪዳነማርያም ጌታሁን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-
‹‹ትዕዛዙን የጣሰችው ሔዋን ናት እንጂ አዳም አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ አይዋሽም፡፡ ወንድ ሴት የበላይና የበታች መሆናቸው አያሳፍርም፤ አያጣላም፤ የተፈጥሮ ሕግ አይለወጥም፤ ተፈጥሮና ፖለቲካ ውሕደት የላቸውም፤ ፖለቲካ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ተፈጥሮ ግን አምላካዊ ግኝት ነው፡፡ የተፈጥሮ ሕግ አዳምና ሔዋንን የበላይና የበታች ቢያደርጋቸውም በዘር ሩካቤ አንድ አድርጓቸዋል፡፡ አጣምሯቸዋል፡፡››(መምህር ኪዳነ ማርያም ጌታሁን፤ ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ ገጽ 29)

እንደ ኢስላም አስተምሮ በአደም የመጀመሪያ ስህተት ሴት አትወቀስም፡፡ መለኮታዊ ትእዛዝ የተላለፈላቸው ለሁለቱም እንደሆነ፡፡(ለአዳምና ለሄዋን) ፡፤ ሁለቱም ትእዛዙን ባለመፈጸም ስህተተኛ እንደነበሩ፡፡ ሁለቱም ይቅርታ እንደጠየቁና አላህም (ሱ.ወ) ይቅር እንዳላቸው አላህ (ሱ.ወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

وَقُلْنَا يَا آدَمُ اسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ وَكُلَا مِنْهَا رَغَدًا حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ الشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ الظَّالِمِينَ [٢:٣٥]

‹‹አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ ገነት ውስጥ ተቀመጥ ፡፡ ከርሷ (ከመልካም ፍሬዎቿም) በፈለጋችሁበት ስፍራና ጊዜ ያሻችሁትን ተመገቡ፡፡ ይህችን ዛፍ ግን አትቅረቡ፤ ከበዳዮች ትሆናላችሁና፡፡››(ሱረቱ አል-በቀራህ 2፡35)

ይሁንና በዚህ ታሪክ ውስጥ - በቁርአን ትረካ መሰረት -ኃጢአት ማሰራቱን ‹‹ተግባር›› የፈጸመው ሰይጣን(ዳቢሎስ) እንጂ ሄዋን አይደለችም ይህንን አስመልክቶ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል፡-

فَوَسْوَسَ لَهُمَا الشَّيْطَانُ لِيُبْدِيَ لَهُمَا مَا وُورِيَ عَنْهُمَا مِن سَوْآتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَاكُمَا رَبُّكُمَا عَنْ هَٰذِهِ الشَّجَرَةِ إِلَّا أَن تَكُونَا مَلَكَيْنِ أَوْ تَكُونَا مِنَ الْخَالِدِينَ [٧:٢٠]

‹‹ሰይጣንም ከሀፍረተገላቸው የተሸሸገውን ለነርሱ ሊገልጽላቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡ ጌታችሁም መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳሆኑ እንጂ ከዚች ዛፍ አልከለከላችሁም አላቸው፡፡…በማታለለም አዋረዳቸው፡፡››(ሱረቱ አል-አዕራፍ ምዕ.7 ቁ.20-21)

ሄዋን ፍሬዋን ብቻዋን አልበላችም፡፡ ጀማሪም አልነበረችም ፡፡ ስህተቱም የሁለቱም ነበር፡፡ ፀፀቱን ንሰሐቸው እንዲሁ የሁለቱም ነበር፡፡
ይህን አስመልክቶ አላህ(ሱ.ወ) አንጸባራቂ በሆነው ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ [٧:٢٣]
‹‹ጌታችን ሆይ! ራሳችንን በድለናል፡፡ ካልማርከንና ካላዘንክልን ከከሣሪዎች እንሆናለን፤ በማለት (ጌታቸውን) ተማፀኑ፡፡››(ሱረቱ አል-አዕራፍ 7፡23)

እንደ ቁርአን አስተምሮ አዳምና ሄዋን(ሁለቱም) መሳሳታቸውንና ፈተናውን መውደቃቸውን በዚህም ምክኒያት ተወቃሽ መሆናቸውን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የቁርአን አንቀጽ አዳም ይበልጥ ተወቃሽ ሆነው ቀርቧል፡-

فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ الشَّيْطَانُ قَالَ يَا آدَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ الْخُلْدِ وَمُلْكٍ لَّا يَبْلَىٰ [٢٠:١٢٠]

‹‹ግን ሰይጣን ጎተጎተው፡፡ አደም ሆይ! ዝንትዓለም መኖርና የማይወገድ ሥልጣን ማግኘት የምታስችልህን ዛፍ ለማላክትህን? አለው፡፡›› (ሱረቱ አል-ጧሃ 20፡120)

فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْآتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ الْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰ آدَمُ رَبَّهُ فَغَوَىٰ [٢٠:١٢١]

‹‹ከርሷ(ከዛፊቱ) በሉ፡፡ ለነርሱ ኃፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነት ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፤ አደም(በዚህ አኳኋን) የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፡፡ ስህተት ላይ ወደቀም፡፡››(ሱረቱ አል-ጧሃ 21፡120)

ምንም ይሁን ምን የሄዋን ኃጢአት በርሷ ብቻ ተወስኖ የሚቀር እንጂ ወደ እንስት ልጆቿ እንደ ‹‹በሽታ›› የሚተላለፍ አይደለም አንዷን ነፍስ ኃጢአት ሌላዋ አትሸከምምና፡፡ ማንም ሰው የራውን እራሱ ነው ይህንን አስመልክቶ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

تِلْكَ أُمَّةٌ قَدْ خَلَتْ ۖ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَلَكُم مَّا كَسَبْتُمْ ۖ وَلَا تُسْأَلُونَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ [٢:١٣٤]

‹‹ይህች ያለፈች ህዝብ ናት፡፡ ለርሷም የሥራዋ አላት፡፡ ለናንተም የስራችሁ አላችሁ፡፡ እነርሱ ይሰሩት በነበረው እናንተ አትጠየቁም፡፡››(ሱረቱ አል-በቀራህ 2፡134)

{Part-3 ይቀጥላል }
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby ጎነጠ » Mon Jan 13, 2014 11:00 am

ቡካሪ የሚከተለውን ሐዲት መዝግቧል፡ ‹ኦ ሴቶች! ምፅዋትን ስጡ እንደምመለከተው ከሆነ በሲዖል እሳት ውስጥ ከሚኖሩት ነዋሪዎች ብዙዎቹ እናንተ ሴቶች ናችሁ› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 1, section 'A menstruating woman should not fast', Hadith No. 301፡፡ እንዲሁም ሙስሊም የመዘገበው፡ ‹በገነት ውስጥ ካሉት ነዋሪዎች መካከል ሴቶች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው› Sahih Muslim, English translation, Kitab Al-Riqaq, chapter MCXL Hadith No. 6600፡፡በጣም ጠቃሚው ሁኔታ እናንተ የምታሟሉት
የሴትን የግብረ ስጋ አካል ለመደሰት መብት የሚሰጣችሁ አንድ ጉዳይ ነው› Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, Hadith No. 81. See also Mishkat al-Masabih, Book II, under section dower, Hadith No. 53፡፡

ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፣ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ ..... እነዚያን ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው
በመኝታዎችም ተለዩዋቸው (ሳካ ሳደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና› ቁርአን 4.34 The Qur'an, 4:34.
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 3:24 pm

ሴቶች በማን ተበደሉ?
---------------------
በወር አባባ ጊዜ

የወር አበባን በተመለከተ መፅሐፍ ቅዱስ ይህንያስተምራል፡- ‹‹ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣውን የደም መፍሰስ ቢሞርባት፤ የወር አበባዋ ርኩሰት እስከ ሰባት ቀን ይቆያል፤ በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ቢነካት እስከማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ የተቀመጠችበትን ማንኛውም ነገር የነካ ሰው ልብሱን ይጠብ ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይጠብ ፤ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡››(ኦሪት ዘሌዋውያን 15 19፡22)

የክርስቲያን ምሁራን በዚህ ጥቅስ ላይ በመንተራሰስ ጽፈዋል ከ20 በላይ የክርስትና መጽሐፍ የፃፉት መምህር ኪዳነ ማርያም ስለ ወር አበባስለሚናገረው ስለዚህ ጥቅስ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ይህ መመሪያ ለክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ለመንፈሳዊ ሕይወታው ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ኑሯቸውም እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ በመሆኑ ቤተክርስቲያናችን ትመራበታለች፤ ታስተምረዋለች፤ ይህ መመሪያ ሕግና ስርአት የሌላቸው አህዛብም ቢመሩበት ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው፡፡››(መምህር ኪዳነ ማርያም ጌታሁን፤ ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ፤ ገጽ 297)
______________________________________________
ኢስላም ተፈጥሯዊ በሆነው በወር አበባ ላይ ያለው አስተምሮ ደሙን የነካውን ስፍራ ብቻ እንጂ የሴቷ ኁለመኗ ንጹህ አለ መሆኑን አይቀበልም፡፡ አላህም በቁርአን ሴቶች በወርአበባ ላይ ሳሉ ወሲባዊ ግኑኝነት ማድረግና እንዲህ ይከለክላ፡-
‹‹(ሙሐመድ ሆይ!) ስለወር አበባ ይጠይቁሃል፡፡(በዚህ ወቅት ከሚስት ጋር ግኑኝነት መፈጸም) ጎጂ ነው፡፡ በወር አበባ ወቅት ሴቶችን ራቁ(የግብረ ስጋ ግኑኝነት ከማድረግ፡፡) እስኪጸዱ(የወር አበባ እስኪቋረጥ) ድረስ አትቅረቧቸው(ለመገናኘት)፡፡››(ሱረቱ አል-በቀራህ 2፡222)

የሴቷ ሁለናና የነካችው ነገር እርኩስ ነው የሚለው አስተሳሰብ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ውድቅ አድርገዋል፡፡ ከዓኢሻ(ረ.ዐ) እንደተነገረው በውር አበባ ላይ ሆና ሳለ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሏት፡- ‹‹መስጊድ ውስጥ መስገጃ አድርጊልኝ››ሰሉኝ፡፡‹‹ በወር አበባዬ ላይ ነኝ አልኳቸው ፡፡‹‹የወር አበባሽ በእጅሽ ላይ አይደለምና አድርጊልኝ›› አሉኝ፡፡ መስገጃውን አነጠፍኩላቸው ሰገዱበት፡፡››(በሰሂህ ሙስሊምና በመዕጀሙል አውሰጥ የተዘገበ)

ሚስት በወር አበባ ላይ ስትሆን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሰሀቦች (የእምነት ባደረቦች) ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሲጠይቋቸው ከግኑኝነት በቀር ሁሉን ነገር ማድረግ እንደሚችሉ እንዲህ በማለት መልሰዋል፡- ‹‹ከግኑኝነት በቀር ሁሉን ነገር አድርጉ››(ሙስሊም ዘግበውታል]
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 3:52 pm

የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {Part-3}


የዛሬ ርዕሳችን የሚሆነው ኢስላምና ክርስትና ሴት ልጅ ሴት በመሆኗ ያላቸውን አመለካከት ይሆናል ከዛ በፊት ግን በድጋሚ ማስታወስ የምንፈልገው ነገር አለ እሱም በዚህ ርዕስ ውስጥ የሴትን ልጅ መብት አስመልክቶ ኢስላም ላይ ለሚነሱ ውንጀላዎች በየተያዘላቸው ርዕስ ስር ጊዜያቸውን ጠብቀው በአላህ(ሱ.ወ) ፍቃድ መልሶችን ፖስት እንደምናደርግ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ አሁን ለዛሬ ወደያዝነው ርዕስ እንግባ፡-

ሴት ልጅ በሴትነቷ፡-

መጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› ገና ከጅምሩ ሴት ልጅ ስትወልድ እናቲቱ ወንድ ልጅ ከሚወለድበት ጊዜ እጥፍ እርኩስ እንደምትሆን ይገልጻል፡- ‹‹እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፡- ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ ‹‹ሰባት ቀን›› ያህል የረከሰች ናት፤….ሴት ልጅም ብትወልድ እንደመረገሟ ‹‹ወራት ሁለት ሳምንት›› የረከሰች ናት፤ ከደሟም እስክትነፃ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ጥቀመጥ››(ኦሪት ዘሌዋውያን 12፡1-5)

ከዚህ ጥቅስ በግልጽ እንደምንረዳው ሴት ልጅ ስትወለድ የእናት እርክሰት እጥፍ እንደሆነ ነው፡፡ ለምን ይሆን ምክኒያቱ? የኛ ጥያቄ ነው የክርስቲያን ምሁራን ፈጣሪ ሴት ስትወልድ ለምን የእናቲቱ እጥፍ እንደምትረክስ እንዳደረገ እንደማያውቁ ጽፈዋል፡፡(ቲም ፌሎስ፤ የኦሪት ዘሌዋውያንና የእብራውያን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፤ ገጽ 67)
መምህር ኪዳነማርያም ጌታሁን በበኩላቸው ይህንን ጥቅስ አስመልክቶ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-
‹‹በዚህ ጥቅስ መሰረት ከወንድ ልጅ ቀን ለምን የሴቲቱ እጥፍ ሆነ? ለሚለው ጥያቄ መልስ አይገኝለትም ፡፡ ምክኒያቱም ለሴት ልጅ ይህን ያህል ቀን ለወንድ ልጅ ይህን ያህል ቀን በማለት ቀኖችን እየወሰነ ለሙሴ የነገረው እግዚአብሔር ነው፡፡›› (መምህር ኪዳነማርያም ጌታሁን፤ ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ፤ ገጽ 31)

የክርስቲያኑ መመሪያ የሆነው መጽሐፍ‹‹ቅዱስ›› ስለ ሴት ልጅ እንዲህ ሲል ያስተምራል፡-‹‹ሴት ልጅ ለአባቷ የተሰወረ ቁርጥማት ናት እሷንም ማሰብ እንቅልፍ ያሳጣዋል››(መጽሐፈ ሲራክ 42፡9)

በሌላ ቦታ ላይ ደግሞ እንዲህ ይለናል፡-‹‹ከሴት ቸርነት የወንድ ንፉግነት ይሻላል፡፡ ውሽማዋንና ባሏን የምታቃና ሴት አፍረት ናት፡፡››(መጽሐፍ ሲራክ 42፡14)

«ከልብስ ብል ይገኛል፤ኃጢአትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል፡፡»(መጽሐፈ ሲራክ 25፡24)

የክርስቲያኑ ጸሐፊ መምህር ኪዳነ ማርያም እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡- ‹‹ጥቅሶቹ ለሴቶች መብት የሚጠቅሙ ሳይሆን ነውራቸውን የሚያጋልጡ ናቸው›› በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል(መምህር ኪዳነማርያም ጌታሁን፤ ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ፤ ገጽ 31)

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለሆነው ለአላህ(ሱ.ወ) ይገባውና ኢስላም የሴት ልጅን መብት ከመጠበቅ ባሻገር ለወደፊት የህይወቷ ዘመን ፍትህ እንዳይጓደልባትና በዝቅተኛነት እንዳይመለከቷት ከማድረጉም በላይ በርህራሄና በፍትህ እንድትኖር ቁርአናዊ አንቀጾች እንዲሁም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው ለሴት ልጅ አውንታዊ አመላካከት እንዲኖረው አስተምረዋል፤ መክረዋል ፤ ይህንንም ያደረገ ታላቅ ሽልማት እንዳለውም አበስራዋል፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከተናገሩት ከብዙ ጥቂቱን እንመልከት፡-

‹‹ሦስት ሴት ልጆች ወይም ሦስት እህቶች አሊያም ሁለት ሴት ልጆች ወይም ሁለት እህቶች ያለው መልካም ከዋለላቸው ፤ በነርሱ ላይም ከታገሰ (በጽናት ካገለገላቸው) እና በነርሱም ላይ አላህን ከፈራ ጀነት (ገነት) በእርግጥ ይገባል፡፡››(አቡዳውድ፤ ቲርሚዚ እና ኢብን ሂባን የዘገቡት)

‹‹ማንኛውም ሴት ልጅ ያለው ሰው በህይወት እያለች ያልቀበራት ፤ ያላወረዳት፤ በርሷም ላይ ወንድ ልጁን አብልጦ ያልተመለከተ አላህ ገነትን ይመነዳዋል፡፡››(የኢብን ሐምበል የሀዲስ መፅሐፍ ቁ.1957)
‹‹ለአቅመ አዳም ብቁ እስከ ሆኑ ድረስ ሁለት ሴት ልጆችን አንከባክቦ ያሳደገ እኔና እርሱ በፍርድ ቀን አንድ ላይ እንመጣለን በማለት/ሁለት ጣቶቻቸውን በማገናኘት/ አረጋግጠዋል፡፡››

በተመሳሳይ ሁኔታም ሁለት እህቶቹን የሚል የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር(በኢብኑ ሐምበል የሀዲስ መጽሀፍ ቁ.2104) ይገኛል፡፡
እንዲሁም የአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ሴት ልጆቻችን ተንከባክቦና

በመልካም ሥነ-ምግባር አንጾ ለሚያሳድግ ሰው ጀነትን ቃል ገብተውለታል፡፡ ጀነት ውስጥ ከርሳቸው ጎን እንደሚሆንም አበስረውታል፡፡

ቲርሚዚ ባሰፈሩት ሌላ ዘገባ ደግሞ፡-
‹‹ሁለት እንስቶችን የተንከባከበ፤ እኔና እርሱ ወደ ጀነት እንደዚህ ሆነን እንገባለን በማለት በአውራና በሌባ ጣቶቻቸው አመላከቱ፡፡››
ኢብን ዐባስ እንዳተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ሁለት ሴት ልጆች ኑረውት ለነርሱ የሚያደርገውን እንክብካቤ ያሳመረ፤ አንድም ሙስሊም የለም፤ ጀነት ያስገቡት ቢሆን እንጅ፡፡›› (ቡኻሪ፤ ኢብን አቢ ሸይባህ፤ አህመድና ኢብን ማጃህ)

ሌሎች የሀዲስ ዘገባዎች ደግሞ ለየትኛዋም ሴት ልጅ ቁጥሯ አንድም ይሁን ከዚያም በላይ መልካም የዋለ ሁሉ ይህን መለኮታዊ ሽልማት እንደሚያገኝ አስፍረዋል፡፡
አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ) ባስተላለፉት ዘገባ መልዕክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹በስሩ የሚያስተዳድራቸው ሦስት ሴት ልጆች ኑረውት ክፉ ደጋቸውን ተጋርቶ ያሳደጋቸው፤ አላህ በነርሱ ሰበብና እዝነት ጀነት ያስገባዋል›› በማለት ተናገሩ፡፡‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሁለት ቢሆኑስ? አላቸው አንድ ሰሃባ(የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባ)፡፡ ‹‹ሁለትም ቢሆኑም›› አሉ፡፡ አንድ ሌላ ሰውም፡- ‹‹አንድ ብትሆንስ?›› አላቸው፡፡ ‹‹አንዲትም ብትሆን›› ሲሉ መለሱ፡፡››

እዚህ ጋር ቆም ብለን አንድ ነገር ማስተዋል ግድ ይለናል፡- እንደሚታወቀው ዐረቦች ነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ጠፍቶና ተረስቶ የነበረው የፈጣሪ ሃይማኖትን ኢስላምን ለማዳረስ ከመላካቸዉ በፊት ሴት ልጅ ስትወለድላቸው ይሸማቀቁ ነበር፡፡ ከዚያም ይባስ ብሎ ሴት ልጅ ስትወለድላቸው ከነህይወቷ እስከመቅበር ይደርሱ ነበር፡፡በቀድሞው አረቢያ ምድር ኑሮ ለሴቶች ምን እንደሚመስል በለንደኑ የቤክ ኮሌጅ መምህርት የሆነችው ኘሮፌሰር ከረን አርምስትሮንግ እንዲህ ትገልፃለች፡- "የግድ ልናስታውስ የሚገባነ ሴት ልጅን ከነህይወት መቅበር ልማድ በነበረበት በምንም መልኩ መብት ባልነበራቸውና የበታች ፍጥረት እንደባሪያ ተደርገው በቀድሞው አረቢያ ሴቶች በሚታዩበት ጊዜ ሙሐመድ ለሴቶች የዋለው ውለታ ልዩ ነበር፡፡ በተለይ ህዝቡን ያስገረመው የድርሻቸውን መውረስና ምስክር መሆን ይችላሉ ማለቱ ነበር፡፡” (Karan Armstrong Mohammed, a biography of the prophet, p. 191)

በቀድሞ አረብያ የሴት ከነህይወቷ መቀበር እውነቷ አላህ(ሱ.ወ) አንጸባራቂ በሆነ ቃሉ ድርጊቱን በማውገዝ እንዲህ ይላል፡-

وَإِذَا الْمَوْءُودَةُ سُئِلَتْ [٨١:٨]بِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ [٨١:٩]

‹‹ከነሕይወቷ የተቀበረች ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ በምን ወንጀሏ እንደተገደለች፤››(ሱረቱ አል-ተክዊር 81፡7-8)

በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ) አባቶች ሴት ልጆች በተወለዱላቸው ጊዜ ይሰማቸው የነበረውን ስሜት እንዲህ ገልጾታል፡-

وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِالْأُنثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ [١٦:٥٨]يَتَوَارَىٰ مِنَ الْقَوْمِ مِن سُوءِ مَا بُشِّرَ بِهِ ۚ أَيُمْسِكُهُ عَلَىٰ هُونٍ أَمْ يَدُسُّهُ فِي التُّرَابِ ۗ أَلَا سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ [١٦:٥٩]

‹‹በነርሱ መካከል አንዱ በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ ፊቱ በሐዘን ይጠቁራል፡፡ ቅስሙ ይሰበራል፡፡ በተነገረው ‹‹መርዶ›› ሰበብ ራሱን ከሰዎች ይደብቃል፡፡ የሚደርስበትን ውርደት ችሎና ተሸክሞ ይያዛት ወይስ አፈር ውስጥ ይቅበራት? አዋጅ ፍርዳቸው እጅግ ከፋ!››(ሱረቱ አል-ነህል 16፡58-59)

በነዚያ ልጆቻቸውን በሚገድሉ ጨካኝና አረመኔ ወላጆች ላይ ቁርአን ጠንካራ ውግዘት ሰንዝሯል ፡-

قَدْ خَسِرَ الَّذِينَ قَتَلُوا أَوْلَادَهُمْ سَفَهًا بِغَيْرِ عِلْمٍ وَحَرَّمُوا مَا رَزَقَهُمُ اللَّهُ افْتِرَاءً عَلَى اللَّهِ ۚ قَدْ ضَلُّوا وَمَا كَانُوا مُهْتَدِينَ [٦:١٤٠]

‹‹እነዚያ በቂልነትና በአላዋቂነት ልጆቻቸውን የገደሉና አላህም የሰጣቸውን (ሲሳይ) በአላህ ላይ በመቅጠፍ እርም ያደረጉ በእርግጥ ከሰሩ፡፡ በእርግጥ ተሳሳቱ፡፡ ››(ሱረቱ አል-አንአም 6፡140)

وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُمْ خَشْيَةَ إِمْلَاقٍ ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُهُمْ وَإِيَّاكُمْ ۚ إِنَّ قَتْلَهُمْ كَانَ خِطْئًا كَبِيرًا [١٧:٣١]

‹‹ድህነት በመስጋት ልጆቻችሁን አትግደሉ፡፡ እኛ እናበላቸዋለን፡፡ እናተንም እንዲሁም:: እነርሱን መግደል በእውነቱ ታላቅ ኃጢአት ነው፡፡››(ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፡31)

አንዳንድ ቀደምት ሕጎችና ልምዶች አባት ልጁን ሰፈልግ እንዲሸጥ መብት ይሰጡት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ ምሳሌ የሐሙራቢ ሕግ አንድ ኣባት የሌላን ሰው ሴት ልጅ ከገደለ ለባለ ደሞቹ የራሱን ሴት ልጅ ይገድላት ወይም በሃብትነት ይጠቀምባት ዘንድ የመስጠት ደንብ ደንግገውለታል፡፡

ኢስላም ሲመጣ ሴት ልጅ እንደወንዱ ሁሉ የአላህ ስጦታ መሆኗን አወጀ፡፡ አላህ ለሚሻው የሚሰጣት ለሚሻው የሚነፍጋት ፀጋ መሆኗን ገለፀ፡፡

ይህንንም አስመልክቶ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል፡-

لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ [٤٢:٤٩]

‹‹ የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡ ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም መካን ያደርጋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ(ያሻውን መፈፀም)የሚችልም (አምላክ) ነውና፡፡ ››(ሱረቱ አል-ሹራ 49-50)

በሚገርም ሁኔታ አንዳንድ እንስቶች ከወንዱ ይበልጥ ክብርና ዝና ያላቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ቁርአን በትረካዎቹ አስተምሯል፡፡ የመርየም- የኢምራን ልጅ ታሪክ እንደምሳሌ ይጠቀሳል፡፡ አላህ መረጣት፡፡ ንጽሕትና በፅዕት አደረጋት፡፡ ከዓለማት እንስቶችም አበለጣት፡፡ እናቷ እርሷን አርግዛ እያለ ፅንሷ ወንድ ቢሆን ትመኝ ነበር ፡፡ የቤተ-አምልኮ አገልጋይ እንዲሆን፤ ከደጋግ ሰዎች እንዲሆን ታልም ነበር፡፡ ይህንንም አስመልክቶ አላህ(ሱ.ወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُفَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّي وَضَعْتُهَا أُنثَىٰ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ ۖ وَإِنِّي سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِفَتَقَبَّلَهَا رَبُّهَا بِقَبُولٍ حَسَنٍ وَأَنبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنًا وَكَفَّلَهَا زَكَرِيَّا ۖ كُلَّمَا دَخَلَ عَلَيْهَا زَكَرِيَّا الْمِحْرَابَ وَجَدَ عِندَهَا رِزْقًا ۖ قَالَ يَا مَرْيَمُ أَنَّىٰ لَكِ هَٰذَا ۖ قَالَتْ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ ۖ إِنَّ اللَّهَ يَرْزُقُ مَن يَشَاءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ [٣:٣٧]

‹‹የዒምራን ሚስት እንዲህ ባለች ጊዜ(የሆነውን አስታውስ)፡-‹‹ጌታዬ ሆይ! ከሆዴ ውስጥ የተሸከምኩት (ፅንስ) (ተግባሩ አንተን ብቻ ማገልገል) ይሆን ዘንድ ተሳልኩ፡፡ ይህንን ተቀበለኝ፡፡ አንተ ሰሚም ዐዋቂም ነህ፡፡›› በወለደቻት ጊዜ፡- ‹‹ጌታዬ ሆይ! የወለድኳት ሴት ልጅ ናት›› አለች፡፡(ይህን ተናገረች አልተናገረች ለውጥ የለውም፡፡) የወለደችው ምን እንደሆነ አላህ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ‹‹ሴት ልጅ እንደወንድ ልጅ አይደለችም፡፤ መርየም ብዬ ሰይሜያታለሁ፡፡ እርሷንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ›› (ስትል አከለች)፡፡ አላህ በመልካም አቀባበል ተቀበላት፡፡ መልካም አስተዳደግም አሳደጋት፡፡››( ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡35-37)

{Part-4 to be continue ……..In Sha Allah}
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 8:25 pm

የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {Part-4}


………………አንዳንዶች የሴትና የወንድን እኩልነት ለላመቀበል ‹‹ሴት›› የሚለው ስያሜ በራሱ የድክመት ምልክት አድርገው ይወስዱታል፡፡ ድክመትና ፍርሃት ያለበትን ሰው ይህን የድክመት ምልክት ለመግለጽ ወንድ ቢሆን እንኳ ‹‹ሴት›› በማለት ሲገልጹ ይስታዋላል፡፡ መጽሐፍ ‹‹ቅዱስን›› ስንመለከት ይህኑኑ የሚደግፍ ይመስላል፡፡ በሚገባ ይደግፋል እንጂ! ይህንን ስል ከኪሴ አምጥቼ እንዳይመስላችሁ እራሱ መጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› በተለያዩ ምዕራፎች የተለያዩ ወገኖችን ድክመትና ፍርሃት በሴት መስሏቸዋል ለአብነት እነሆ፡-
‹‹በዚያ ቀን ግብጻውያን ‹‹እንደ ሴት ይሆናሉ›› የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ነሳው ክንዱ የተነሳ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፡፡››(ትንቢተ ኢሳያስ 19፡16)
በሌላ ቦታ ላይም እንዲህ የሚል እናነባለን፡-
‹‹ሰይፍ በፈረሰኞቹና በሰረገሎች ላይ በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ላይ መጣ ! ‹‹እነርሱም እንደሴቶች ይሆና›› ሰይፍ በሀብት በንብረት ላይ መጣ! ለለዝርፊያም ይሆናሉ፡፡››(ትንቢተ ኤርሚያስ 500፡37)
‹‹እነሆ ጭፍሮችሽ ‹‹ሁሉም ሴቶች›› ናቸው! የምድርህ በሮች ለጠላቶችህ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቶአቸዋል፡፡››(ትንቢተ ናሆም 3፡13)
‹‹የባቢሎን ጦረኞች መዋጋ ትተዋል፤ በምሽጋቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኋይሎቻቸው ተሟጧል፤ ‹‹እንደ ሴት ሆነዋል››፡፡›› ( ትንቢተ ኤርሚያስ 51፡30)
የክርስታን ጸሐፊው መምህር ኪዳነ ማርያም ‹‹ሴት የሚለው የድክመት ምልክት ነውን?›› ለሚለው ንዑስ ክፍል እንዲህ ሲሉ የጻፉት ይገኝበታል፡- ‹‹አዎ የድክመት ምልክት ነው፡፡ ወንድና ሴት በተፈጥሮ እኩል ይሁኑ እንጂ በኃይልና በጉልበት እኩል አይደሉም ወንድ ከሴት ይበልጣል፡፡››(መምህር ኪዳነማርያም ጌታሁን ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ ፤ ገጽ 67)

‹‹ኢስላም ለአንዱ ፆታ ‹‹ወንድ›› ለሌላኛው ‹‹ሴት›› በሚለው መጠራታቸው መበላለጥን አያመለክቱም በማለት ያስተምራል፡፡ በሴት ጾታ መጠራት የበታችነትን አያመለክትም፡፡ የበታችነትን የሚያመለክት ቢሆን ኖሮ አላህ(ሱ.ወ) በቁርአን ጨረቃን በወንድ ጾታ ፀሐይን በሴት ጾታ ባልጠራ ነበር ምክኒያቱም ከጨረቃ ፀሐይ ትበልጣለችና፡፡ እንደዚሁም አላህ ሰማይን ፤ ዓለምን ፤ ነፍስ ምድርን እና ገነትን(ጀነትን)በሴት ጾታ ጠርቷቸዋልና፡፡ (የሴቶች መብትና እኩልነት ገጽ 38)

በኢስላም አስተምሮ ‹‹ሴት›› የሚለው ስያሜ የድክመት ምልክት መሆኑን እንደማያመለክት በተጨማሪ በኢስላ ታሪክ ውስጥ ጀግና ከሆኑ እንስቶች መሀከል የአንዷን ታሪክ አብረን እንመልከት፡-
በአህዛብ (በኸንደቅ)ዘመቻ ወቅት የተከሰተውን ክስተት ኢብን ኢስሀቅ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-
‹‹ሶፍያ ቢን አብዱል ሙጠሊብ ከጦር ሰፈር ውስጥ ከሐሳን ቢን ሳቢት፤ እንዲሁም ከሴቶችና ከሕጻናት ጋር ነበረች፡፡ በእለቱ የሆመውን እንዲህ ስትል አውግታለች፡- አንድ የአይሁድ ሰላይ በአጠገባችን አለፈ፡፡ ጦር ሰፈሩን እየተዘዋወሩ ይመለከት ጀመር፡፡ በኑ ቁረይዛዎች ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር የነበራቸውን ውል አፍርሰው ጠላትነታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከነርሱ የሚከላከልልን አንድም ሰው አልነበረም ፡፡ የአላህ መልእክተኛና ሙስሊሞች ከጠላት ጋር የተፋጠጡ በመሆናቸውም አንዳች አደጋ ቢገጥመንም እገዳ ሊያደርጉልን አይችሉም፡፡ እናም፡- ‹‹ሐሳን ሆይ! ይህ አይሁድ እንደምታየው በጦር ሰፈራችን አጠገብ እየተዘዋወረ ነው፡፡ ከኋላችን ላሉት አይሁዶች ያለንበትን ሁኔታ እንዳያጋልጥ እሰጋለሁ ፡፡ የአላህ መልዕክተኛና ባልደረቦቻቸው በቁረይሾች በመጠመዳቸው እገዛ ሊያደርጉልን ስለማይችልሁ አንተ ሂድና ግደለው ፡፡ አልኩት ፡፡ ‹‹ይህንን ማድረግ እንደማልችል ታውቂያለሽ›› አለኝ፡፡ መቀነቴን አጠበኩና ከነበርኩበት የቶር ሰፈር ምሽግ በመውረድ በእንጨት መጥቼ ገደልኩት፡፡››( አብን ሂሻም 2/228)

ሶፍያ የፈጸመችው ይህ ጀብድ የሙስሊሞችን እንስቶች እና ሕጻናት ከጠላት ጥቃት በመጠበቁ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫወተ፡፡ የጦር ሰፈሩ ምንም አይነት የጥበቃ ሐይል ያልነበረው ቢሆንም ይህቺ ጀግና እንስት የፈጸመቸው ተግባር አይሁዶች ሴቶቹና ህጻናቶች ጠንካራ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሆነ እንዲያስቡ አስገደዳቸው፡፡
ትኩት ሊሰጣው የሚገባው ነገር እኩልነት ማለት አንድነት ማለት አይደለም፡-

የሴቶች መብትና እኩልነት በሚለው መጽሐፍ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ለዚህ ንዑስ ክፍል እንዲህ ሲል ጽፏል፡- ‹‹በሴትና በወንድ መካከል ያለው ብቸኛ ልዩነት የተፈጥረሮ ልዩነት ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው የሆነ ልዩ ተፈጥሮ አላቸው፡፡ ሁለቱም በየፊናቸው ለህብረተሰቡ የሚያበረክቱትና በተለይ የሚመለከታቸው አስተዋጽኦ አለ፡፡ አንዳንዶቸ እኩልነት(ተመሳሳይነት አድረገው ለማቅረብ ሲሞክሩ ይስተዋላ ፡፡ ወንድና ሴት ተፈጥሯዊ መመሳሰል እንዳላቸው ሁሉ በርካታ ልዩነቶችም አላቸው፡፡ ሴት የወር አበባ እርግዝና ፤ ወሊድና ለነዚህ የሚያስፈልጉ አካ ይዛ ስትፈጠር ወንድ ግን እነዚህ ካላት የሉትም፡፡ በተመሳሳይነትና በእኩልነት መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ እኩልነት ተፈላጊ ትክክለኛና ተገቢ ሲሆን ሰተመሳሳይነት ግን የመብት መለኪያ አይደለም፡፡ ሰዎች እኩል ሆነው ተፈጠሩ እንጂ ፍጹም ተመሳሳይ (Identical) ሆነው አልተፈጠሩም፡፡ ይህን ለልዩነት በአእምሮ በመያዝ ሴት በደረጃዋ ከወንድ ታንሳለች ብሎ መገመት ቦታ የለውም ፡፡ መብቶቿ በትክክል ከወንዱ መብቶች ጋር ተመሳሳይ ስላልሆነ ከወንዱ ያነሰ ግምት ይሰጣታል ብሎ መገመት ፣መሰረት የለውም፡፡ ደረጃዋ ከወንዱ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ቢሆኑ ኖሮ ተቃራኒ ሳይሆኑ ልክ የወንዱ ትክክለኛ ግልባጭ በሆነች ነበር ፡፡ ኢስላም ፍጹም ተመሳሳይ ሳይሆኑ እኩል መብቶች ለሴት የመስጠቱ እውነታ ተገቢውን ትኩረት የሚሰጣትና የሚያከብራትና ነጻ ስብእናዋን የሚያውቅላት መሆኑን ያሳያል፡፡ እኩልነት ተመሳሳይ ቢሆን ኖሮ ወንድም ‹‹ወንድ›› እንደዚሁም ሴትም ‹‹ሴት›› የሚል የተለያየ መጠሪያ ባልተሰጣቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ወንድ ወንድ ነው፡፡ ሴትም ሴት ነች፡፡ የመርየም እናት ሀና ወንድ ልጅ መውለድ ፈልጋ መርየምን(ማርያምን) ስትወልድ እንዲህ እንዳለች በቁርአን ሰፍሪ ይገኛል፡-

‹‹ወንድም እንደ ሴት አይደለም››(ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡36)
ስለሴትና ወንድ ልዩነት ሙሉ ደቦጭ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፡-
‹‹ምንም እንኳ ወንዶችና ሴቶች በእኩል ደረጃ አስፈላጊዎችና ለእግዚአብሔር ውድ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ አድርጎ አልፈጠራቸውም፡፡ እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶችን ለተለያዩ ግባራትና ዓላማዎች ፈጥሯቸዋል፡፡ እነዚህን ሚናዎች ለመለወጥ ወይም ለማባዛት ብንፈልግ በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ጣልቃ እንገባለን…..ለእግዚአብሔር የእሴትና የአስፈላጊነትና እኩልነት ጋር አንድ አይደለም፡፡ ወንዶችና ሴቶች አንድ ዓይነት ሚናዎች እንዲይዙና በሁሉም የሕይወት ገጽታዎች አንድ ዓይነት ተግባር እንዲያከናውኑ የሚጠይቁ አንዳንድ ምዕራባውያን እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶችን የፈጠረበት ሁኔታ አለመገንዘባቸው እንደሚያንፀባርቁ ግልጽ ነው ፡፡ እስከ ዛሬ ልጅ ወልዶ ያጠባ ወንድ ኖሮ አያውቅም ፡፡ እግዚአብሔር ያንን ድርሻ የሰጣው ለሴቶች ነው ፡፡ የትኛዋም ሴት በሰውነቷ ውስጥ ያለውን እንቁላል ለማዳበር የሚያስችል ወንዴ ዘር/ስፐርም/ አመንጭታ አታውቅም ፡፡ እግዚአብሔር ንን ድርሻ የሰጠው ለወንዶች ነው፡፡ እነዚህ አካላዊ ተግባራ ለስሜታዊና ማህበራዊ የሕይወት አካላት ተዛምዶ ያላቸው ናቸው፡፡››(ሙሉ ደቦ ዝሙት፤ ገጽ 11)

{Part-5 to be continu …
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby ጎነጠ » Mon Jan 13, 2014 8:34 pm

በመኝታዎችም ተለዩዋቸው (ሳካ ሳደርሱ ) [url]፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን ) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና› ቁርአን 4.34 The Qur'an, 4:34.[/url]
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 10:46 pm

የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {Part-5}


……..በጥናት የተራጋገጡ የወንድ እና የሴት መጠነ ሰፊ ልዩነቶች፡-
ሴቶችና ወንዶች ካሏቸው መጠነ ሰፊ ልዩነቶች ውስጥ ሜዲካል መጽሔት በሚያዚያ ወር በ1999 ዓ.ል ባወጣው እትሙ ያሰፈረውን በጥቂቱ እንመልከት፡-

• የወንዶችና የሴቶች አካላዊ ልዩነት ፡- ወንድ ልጅ በሴት ልጅ ላይ በአማካይ 20 በመቶ እርከን አካላዊ ብልጫ አለው(በክብደት)፡፡ ይህ የሆነው ወንዶች በጡንቻ ክምችትና ውፋሬ ላቅ ያለ ተፈጥሮ ስላላቸው ነው፡፡ ሴቶች ግን በዛ ያለ ቅባት ክምችት አላቸው፡፡

• ሴቶች እረጅም የሆነ እድሜ ይኖራሉ፡፡

• ሴት ሰላማዊ ወንድ ወንጀል ወዳድ ነው፡፡

• ሴቶች በቶሎ ያለቅሳሉ፡፡ በቶሎ ይስቃሉ፡፡

• በሂሳብ አቀማመር ወንዶች ይሻላሉ፡፡

• ሴቶች ዙሪያ ጥምጥም ወንዶች ግን በቀጥታ ያስባሉ፡፡

• በገንዘብ አያያዝ ሴቶች የተሸሉ ናቸው፡፡

• ስሜትን ለመቆጣጠር የሚያገለግለው የአንጎል ክፍል ወንዶች ላይ ያንሳል፡፡

• ግራ እና ቀኝ ያሉት አንጎል ክፍሎች ሴቶች ላይ የተሸለ ትስስር አላቸው፡፡
• የወንዶች አንጎል በመጠኑ ከሴቶች ይበልጣል፡፡

• የሴቶች አንጎል ቀድሞ እድገቱን ይጨርሳል፡፡

• ወንዶች የተሸለ እንቅፋቶችን የመጋፈጥ አዝማሚያ የሚጠይቁ ተደጋጋሚ ውድቀቶች ሲያጋጥሙ ሴቶች በፍጥነት ተስፋ የመቁረጥ አዝማሚያ ሲኖራቸው ወንዶች ግን ያለ ሽንፈት መጋፈጥ ይመርጣሉ፡፡

• ወንዶች ከሴቷ ጋር በሚፈጽሙት ተራክቦ ወቅት በአንድ የዘር ፍሰት ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ የስፐርም ሰራዊቶችን ለፅንሰት ሲለቅ ሴቷ ግን ለዚህ ስኬታማነት አንድ እንቁላል ብቻ ነው የሚታዘጋጀው፡፡ ይሁንና ከ60 ሚሊዮን ስፐርሞች ውስጥ ከአንዲቷ የሴት እንቁላል ጋር የሚዋሃደው እንዱ ብቻ ሲሆን ሌሎቹ ስፐርሞች በማህጸን ውስጥ ይሞታሉ፡፡

• የወንድ ዘር ከሴቷ ዘር ይልቅ ረጅም እድሜ ይኖረዋል፡፡

• ሴት ለፅንስ የሚያበቃትን አንዲት እንቁላል በወር አባባ አጋማሽ ላይ ብቻ ስታመርት ወንዱ ግን በየቀኑ የስፐርም ዘር ያመርታል፡፡

• ሴት ልጅ የዘር እንቁላል ታወድማለች፡፡አንዲት ሴት በእናቷ ማህጸን ውስጥ እያች ከ3-4 ሚሊዮን የሚሆኑ እንቁላሎች የሚኖሯት ይሁን እንጂ ስትወልድ ግን አንድ ሚሊዮን የሚሆኑት ብቻ አብረዋት ይወለዳሉ፡፡ ሌሎች ግን ይወድማሉ፡፡ ከ16-45 ዓመት አድሜ ዘመኗ በወር አንዴ እንቁላል እያፈለቀች ትቆይና የተቀሩት እንቁላሎቿ በመጨረሻ (በ50ዎች እድሜ) ወደ ዜሮ ይወርዳሉ፡፡ በዚህ ወቅት ሴቷ ታርጣለች፡፡ ወንድ ልጅ እንዲህ አይነት የዘር ማሽቆልቆል አይታይበትም፡፡

• ሴቶች በደንብ ያርጣሉ፡፤ ወንዶች በመጠኑ ያርጣሉ፡፡

• ሴቶች ልጆቻቸውን ማይቶኮንድሪያ ያወርሳሉ፡፤ ወንዶች ግን አያወርሱም ፡፡

• ሴቶች ፍቅርን ያስቀድማሉ፡፡ ወንዶች ወሲብን ያስቀድማሉ፡፡

• ሴቶች ትከሻ ሰፊ ወንድን ንዶች ደግሞ ዳሌ ሰፊ ሴትን ለፍቅር ይመርጣሉ፡፡(ዶ/ር አቡሽ አያሌው፤ ሜዲካል መጽሔት፤ ሚያዚያ 1999፤ ገጽ 18)

እነዚህ ከሴትና ከወንድ መጠነ ሰፊ ልዩነቶች ውስጥ በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ እንዴት ታዲያ ወንድና ሴትን አንድ አድርገን ልንመለከታቸው ይቻለናል?

‹‹እኩልነት ማለት አንድ አይነት ማለት አይደለም›› የሴት እና የወንድ እኩልነት በመንፈሳዊ ህይወታቸው (እዚሁ ፔጅ ላይ የሴቶች መብትና እኩልነት part-2 የሚለው ላይ በሰፊው ተዳሷል እዛ ላይ ይመልከቱ)

{Part-6 to be continue
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Thu Jan 23, 2014 9:47 pm

የሴቶች መብት በኢስላምና በክርስትና
ሴት ብቻ ለምን ትሸፈን?
------------------------------
መጽሐፍ ቅዱስ ወንድ መሸፈን የሌለበትን ምክኒያት እንዲህ ሲል ይገልጻል፡-
‹‹ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም›› (1ኛ ቆሮንቶስ 11፡7) የክርስቲያን ምሁራን እንዲህ ሲሉ ማብራሪያ ጽፈዋል›-

‹‹ወንድ ራሱን መከናነብ የማይገባበት ምክኒያቱ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጨረሻና መደምደሚያ ሆኖ በእግዚአብሔር መልክ ስለተፈጠረ በእርሱም ሁሉ ስለ ተገዛ ነው፡፡ (ዘፍ. 1›26፡28) እርሱ የእግዚአብሔር ክብር አክሊልም ነውና የተገዢ ምልክት አሳይቶ ራሱን መከናነብ አይገባውም፡፡ ሴት ግን ስትፈጠር ከወንድ (ዘፍጥ. 2፡21-23) እና ስለ ወንድ ስለ ተፈጠረች(ዘፍጥ. 2፡18)እርስዋ የወንድ ክብር ናትና ከስልጣን በታች መሆንዋን የሚያመለክተው ያራስ መሸፈኛ ሊኖራ ይገባል፡፡››የመጀመሪያይቱ የሐዋሪያ ጳውሎስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች፤ ገጽ 89

በኢስላም አስተምሮ ሴት መሸፈን ያለባት ከወንድ ስለምታንስ አሊያም ከወንድ ስልጣን ስር መሆኗን እንድታሳይ ሳይሆን ለራሷ ክብርና በሴት ልጅ አማላይ ገላ በቀላሉ ወንዱ ስሜቱ ተነሳሰቶ ሁለቱም ለጥፋት እንዳይዳረጉ ለመጠበቅ ነው፡፡ ከወንዱ ስሜት የሌላት(በባልነት) እንደ ልጃገረዷ ያለ ሂጃብን እንድታደርግ አትገደድም፡፡ ይህንንም አላህ(ሱ.ወ) በቁርአን እንዲህ ሲል ይገልጻል፡-
‹‹ከሴቶች እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉ(ከወንድ ስሜት ያጡ) ባልቴቶች በጌጥ የተገለጹ ሳይሆኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ(ባያደርጉ) ኋጠአት የለባቸውም፡፡››(ሱረቱ አል-ኑር፡60)
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sat Jan 25, 2014 11:29 pm

የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና

*^* የፍቺ መብት *^*

ከሴቶች መሰረታዊ መብቶች ውስጥ ፍቺ ይገኝበታል፡፡ ለዘላቂ ህይወት ሴት ከአንድ ወንድ ጋር በጋብቻ ስትጣመር እና ጋብቻው ሊሰምር ካልቻለ የመጨረሻው አማራጭ መፍታት እና ከሚሆናት ሌላ ወን...


See More

የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {Part-7}
By Bint Islam

የትዳር አጋር የመምረጥ መብት፡-

መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል ሁለት ወንድማቾች ቢኖሩና አንደኛው ልጅ ሳይኖረው ቢሞት ስለ ሚስቲቱ የማግባት ፍላጎት ምንም ሳይገልጽ የሟች ወንድም ያግባት ሲል እንዲህ ያዛል ፡-‹‹ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ አንድም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት የሞተው ሰው ሚስት ልላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ ነገር ግን የባልዋን ወንድም ወደ እርሳዋ ገብቶ እርሰዋን ያግባ ከእርሰዋ ጋር ይኑር፡፡›››(ኦሪት ዘዳግም 25፡5)

እንግዲህ ያገሬ ገበሬ የዋርሳ እያለ የሚተገብረው ከብሉይ ኪዳን የተማረውን እንጂ ከቁርአን የተወሰደውን ትእዛዝ እንዳልሆነ ልብ ይበሉ!!

በሌላ ምዕራፍ ላይ ያልታጨች ልጃገረድ ብትደፈር አስገድዶ ደፋሪው ያገባት ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ አዟል፡፡ ሴቷ ፈለገች አልፈለገች ‹‹የፈጣሪዋ›› ትእዛዝ ነውና አስገድዶ ደፋሪው ያገባት ዘንድ በዚህ መልኩ ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡-
‹‹ማንኛውም ሰው ድንግልና ያለትን ያልታጨች ልጃገረድ ቢያገኝ ወስዶም ቢደርስባት ቢያገኙትም ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ስቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፣ አስነውሯታልና ሚስትም ትሁነው በዕድሜ ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም፡፡››(ኦሪት ዘዳግም 22፡28-29)

እንግዲህ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ መሰረት አምሳ የብር ስቅል የመክፈል አቅም ያለው ሰው የሚፈልጋትን ሴት ሄዶ………………..፡፡ የሴቶች መብት ተሟጋች ነን ባዮች ይህንን ቅዱስ በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ይህንን አንቀጽ አይተውት ይሆን? ጥያቄያችን ነው

መቼም ይህ እና መሰል የኦሪት ሕጎች በወንጌል ተሽሯል ብለህ/ሽ
ያልሆነ እሳቤ እንዳትይዝ/ዢ ኢየሱስ ህግን ሊሽር እንዳልመጣ እንዲህ ሲል በግልጽ ተናግሯል፡- “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።” (ማቴዎስ 5፡17)


እንደ ኢስላም አስተምሮ አባት ሴት ልጅን እርሷ ለማትፈልገውና ላልወደደችው ባል መዳር አይችልም ፡፡ በርሷ ጋብቻ ጉዳይ ሊያማክራት ግድ ይላል፡፡ ፈቃደኝነቷን ማረጋገጥ አለበት ፡፡ ከአሁን ቀደም የጋብቻን ህይወት የምታውቅ ከሆነች አዲሱን ጋብቻ በግልጽ ቋንቋ ማጽደቋ መረጋገጥ አለበት፡፡ ልጃገረድ ከሆነች ደግሞ ሐፍተት ስለሚይዛት ስምምነቷን በዝምታ መግለጽ ይኖርባታል፡፡ ዝምታዋ ከስምምነት ይቆጠራል ፡፡ አይሆንም ካለች ግን የማትፈልገውን እንድታገባ አባተ ሊያስገድዳት ሥልጣን የለውም፡፡

ቡኻሪና ሙሰሊም አቡ ሁረይራን በመጥቀስ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፡- ‹‹ሴት ልጅ ያለፈቃዷ ልትዳር አይገባም፡፡ ልጃገረድም ፈቃዷ መጠየቅ አለበት››አሉ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ልጃገረድ) መፍቀዷ በምን ይታወቃል?›› አሏቸው፡፡ ‹‹በዝምታዋ›› ሲሉ መለሱ፡፡(ቡኻሪና ሙስሊም)

ቡኻሪና ሙስሊም ባሰፈሩት ሌላ ዘገባ እንደተመለከተው ዓኢሻ ነብዩን፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሴት ልጅ ለጋብቻ ፍቃዷ ሊጠየቅ ይገባልን? በማለት ጠየቀች፡፡ ‹‹አዎ›› አሏት፡፡ ልጃገረድ እኮ ፈቃድ ስትጠየቅ ሐፍረት ተስምቷት ዝም ልትል ትችላለች›› አለቻቸው፡፡ ‹‹ዝምታዋ የፈቃዷ መግለጫ ነው›› አሏት፡፡

የኢስላም ሊቃውንቶች ከዚህ ሐዲስ በመነሳት፡- ለልጃገረድ ዝምታዋ ፈቃዷ መሆኑን መንገር ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

ኸንሳእ ቢንት ኀዳም አል-አንሷሪያ የተባለች ሴት እንዳስተላለፈችው አባቷ ለማትፈልገው ሰው ዳራት ፡፡ አግብታ የፈታች ነበረች፡፡ ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣችና ስሞታ አሰማች፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋቻውን ውድቅ አደረጉ፡፡(ሁሉም የሐዲስ አውታች ዘግበውታል ሙስሊም ሲቀሩ)
ኢብን አባስ እንዳተላለፉት አንዲት ልጃገረድ ከነብዩ ዘንድ ቀረበች ፡፡ አባቷ ያለፍቃዷ ሊድራት መሆኑን ነገረቻቸው፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የፍላጎቷን ትመርጥ ዘንድ ዕድል ሰጧት፡፡››(አህመድ፤ አቡዳውድ፤ ኢብን ማጃህና ዳረል ቁጥን)

ልጅገረድ ለመዳር የርሷ ፍቃድ እና ስምምነት ማግኘት የግድ በመሆኑ ረገድ አባት ከሌሎች የተለየ መብት እንደሌለው እነኝህ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ሙስሊም እና ሌሎች የሀዲስ ጠበብት ባሰፈሩት ዘገባ ዘንዲህ ተብሏል፡-
‹‹ልጃገረድ አባቷ ፍቃድ ሊጠይቃት ይገባል፡፡››

ዓኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው፤ አንዲት ሴት ከርሷ ዘንድ መጣችና አባቷ ለወንድሙ ልጅ ሊድራት መሆኑን ገለጸች፡፡ ዓኢሻም ‹‹ነብዩ እስኪመጡ ድረስ ተቀመጭ›› አለቻት፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሲመጡ የሆነውን ነገረቻቸው፡፡ ነብዩም ወደ አባቷ መልዕክት ልከው አስጠሩት፡፡ የመወሰን ስልጣኗን ለርሷ ሰጡ፡፡ ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የአባቴን ተግባር አጽድቄያለሁ፡፡ እንስት በጋብቻ ጉዳይ የፈቀደችውን የማግባት መብት እንዳላት ለማወቅ ብዬ ነው ክስ ያቀረብኩት›› አለች፡፡(ነሳኢ ዘግበውታል)

የሀዲሱ ግልጽ መልእክት የሚያሳየው እንስት-ልጅገረድም ትሁን ፈት- ፈቃዷ መጠየቁ የጋብቻ መስፈርት እንደሆነ ነው፡፡ አባቷ ወይም ሌላ ወኪሏ ያለፈቃዷ ጋብቻ እንዲፈጸም ካደረጓት የጋብቻው ውል ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከላይ ያየነው የኸንሳእ ቢንት ኸዳሚ ታሪክ ይህን ያመለክታል፡፡ ልጃገረድን በተመለከተ ‹‹ምርጫው የሷ ነው ፡፡ ከፈለገች ጋብቻውን ትቀበላለች፡፡ ካልፈለገች ጋብቻውን ውድቅ የማድረግ መብት አላት፡፡ ፍቃደኛ ካልሆነች ጋብቻው ውድቅ ይደረጋል፡፡ አንድኛው የሀዲስ ዘገባ እንደሚያመለክተው››(ነይሉል አውጧር 6፤254-256)

ሌላው ከኢስላም ድንቅ አቋሞች አንዱ በሴት ልጅ የጋብቻ ጉዳይ እናቷን ማማከር ግድ መሆኑን ማስተማሩ ነው፡፡ ጋብቻን በሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ የጋራ ስምምነት ይፈጸም ዘንድ ይህንን ደንግጓል፡፡ ኢብነ ኡመር(ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ሴቶችን በእንስት ልጆቻቸው የጋብቻ ጉዳይ አማክሯቸው፡፡›(አህመድና አቡዳውድ)

ኢማም ሱለይማን አልኸጣቢ ‹‹ሙዓሊመ ሱነን›› በተባለ መጽሐፋቸው ይሀን ሐደስ ሲያብራሩ ያሰፈሩት ቃል- ጥበብና ትምህርት ያዘለ በመሆኑ ሊጠቀስ የሚገባ ነው፡፡ እንዲህ ብለዋል፡-
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests