የቁረአን አጠባበቅ ከመጽሀፈ ቅዱስ አንጻር

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የቁረአን አጠባበቅ ከመጽሀፈ ቅዱስ አንጻር

Postby መርፊው » Mon Jan 13, 2014 11:12 pm

የቁርአን አጠባበቅ ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር ክፍል አንድ(Part -1)
ይህ ፅሁፍ በእጅጉ በመርዘሙ ከፋፍለን ለማቅረብ ተገደናልትችት፣ ትችት ፣ አሁንም ትችት ፣ ሁልጊዜም ትችት ፣ ግን ምን ትለዋለህ መረጃ አልባ ትችት፣ ባዶ ሜዳ ላይ ጨሀት እሪ……… የሚሽነሪዎች ዋና መለያ .

1. ትችት ከሀገር ውስጥም ከባህር ማዶም

ትችቱ እንደወረደ ፡
የኛው የሐገር ውስጡ ሀመር ስለ ቁርአን እንዲህ ሲል ፅፏል
- #(ኢስላሞች ቁርአንን ) የመፅሀፎች ሁሉ እናት ይሉታል ፡፡ ይዘቱን መመርመር ድፍረት እና ሐጥያት ነው;(1)
ስለ መፅሀፍ ቅዱስ ደግሞ የሐገር ውስጡ ፀሀፊ መጋቤ ጥበብ ሰለሞን የምለው አለኝ ይለናል ይቀጥሉ ስኪ
- # መጽሀፍ ቅዱስ ተቀባይነት እንዲኖረው ስሙ ብቻ ሳይሆን መልእክቱ መለኮታዊ በመሆኑ ነው(2)134
ስለ ቁርአን ሐመር በበኩሉ
- #እንደ ሰሂሪ ቡካሪ(ሰሂህ አል ቡኻሪ እላለው ብለው ነው ከኢንተርኔት እስከ ቡጉሩ ተርጉመውት ነው) ፣ሙሀመድ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አመታት በቃላቸው (ቁርአንን) አጥንተው የነበሩ ብዙዎቹ የቅርብ ሰዎች በየማማ ጦርነት ላይ በሞቱ ጊዜ ብዙ የቁርአን አንቀፆች ላይገኙ ጠፍተዋል;(3)
ስለ መፅሀፍ ቅዱስ ጆሆቫ ዊትነሶች ከባህር ማዶ
- #የመፅሀፍ ቅዱስ ይዘት በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠ ነው;(4) ሲሉ ነግረውናል ፡፡
በመሆኑም ይህ ለተደማመሩት የክርስትና አንጃዎች የታየ ለኛ ደግሞ ያልታየ እንቢ ያለው የመፅፍ ቅዱስ መጠበቅ ሲደመር የቁርአን አለመበቅ ምክንያቱ ምን ይሆን ? አዎ ምን ይሆን ምክንያቱ?..... እንድንል አስገድዶናል፡፡
የሐገር ውስጡ ሐመር ምንጩን ኬት እንደሆነ ባይነግረንም ቁርአንን መመርመር በኛ በሙስሊሞች ዘንድ አደጋ እንደ ሆነ ነግሮናል፡፡ ሐመር ይህን ቃል በድፍረት ሊናገር የቻለው አንድም ስለ ቁርአን ያለው እውቀት ልል ያልተያያዘ እዚም እዚያም የተበታተነ በመሆኑ ሁለትም ይህንኑ አባባሉን እንዳለ ሳይጨምር ሳይቀንስ ከ ዌብ ሳይት ላይ ተርጉሞ ብቻ ኮፒ ፔስት በማድረጉ መሆኑን ለማወቅ እንግዲህ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡ ይህን የሀመርን ፅሁፍ አንጥንቶ ሲያበቃ #ነጭ ውሸት ; ሲል አጣጥሎታል የሀገራችን የኢስላም ሙጅተሂድ ኡሰታዝ ሀሰን ታጁ(5)፡፡ እኔም ነጭ ውሸት ሚለው ላይ እርቃኑን የቀረ ውሸት የሚል ቅጥያ ጨምሬበታለሁ ፡፡ አንተ ብቻ ፅሁፉን ማንበብህን ቀጥል እንጂ እንዴት እረርቃኑን እንደቀረ በብረቱ አይንህ የምታየው ይሆናል፡፡ ሳልነግርህ ማላልፈው ነገር ቢኖር ሙስሊሙ ቁርአንን እንዲመረምር ትእዛዝን የተቀበለው ከዩኒቨርስቲዎች ወይም ከኮሌጆች አለመሆኑን ነው፡፡ ግና ትእዛዙን የተቀበለው ከሰማየ ሰማያት ነው፡፡ ማለትም ከአላህ ነው የታዘዘው ይህን አስመልክቶ ረህማን ብርሀኑ ሳስቶ በማይደበዝዘው ቃሉ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡፡

﴿أَفَلاَ يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْءَانَ أَمْ عَلَى قُلُوبٍ أَقْفَالُهَآ
#ቁርአንን አያስተነትኑም እንዴ ከአላህ ሌላ ቢሆን ኑሮ ብዙ ልዩነቶችን ባገኙበት ነበር፡፡;(4፡82)
እነሆ ቁርአንን ማስተንተን መመርመር መለኮታዊ ትእዛዝ ነው ማለት ነው፡፡ ሐመር ቁርአንን ቢያነበው ኖሮ እንዲህ ብሎ መፃፍ ሳይሆን ለመፃፍም ባላሰበ ነበር፡፡ ምን ታደርገዋለህ ከእውቀት እጥረት ነው እኮ፡፡ ነበር ባይሰባበር!!!!!!

2. የታላቁ ቁርአን ታሪክ እና የመፅሀፍ ቅዱስን በንፅፅር፡

የቁርአን ምንጭ ኬት ይጀምራል?
ይህን ጥያቄ ሚሽነሪዎች ጠይቀው ቢሆን ኖሮ ምናልባት የሚያገኙት ምላሽ በቁርአን ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ በመጠኑም ቢሆን ይቀንሰው ነበር ፡፡ ግና አልጠየቁም ባለመጠየቃቸው ብዥታው አይናቸው ላይ እንዳለ ነው፡፡ ስለሆነም ነው እንግዲህ ይህ አይናቸው ላይ ያንዣበበውን ብዥታ ለመግፈፍ ሲባል እኔ ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ የተገደድኩት አዎ! የቁርአን ምንጭ ኬት ይጀምራል?
ሹፍ !! ታላቁ ቁርአን በታላቁ ነብይ ሙሀመድ የተቀራና የተነበበ መጽሀፍ ነው ፡፡ በነብዩ የተቀራና የተነበበ መሆኑም ላይ በህያዉም አለም በሙታኑም አለም ልዩነት ያላስተናገደ ሀቅ ነው ሲሉ የታሪክ ምሁራን ነግረውናል፡፡ ይህም ሁሉም ሳያንገራግር ሚቀበለው እና እንደ ረፋድ ፀሀይ ግልፅ ብሎ ታይቶ ያለፈ እውነታ ነውም ብለውናል፡፡ አልፎ ተርፎ ታላቁ ነብይ አንድም ቀን ቁርአን የኔ ቃል ነው ብለው የተናገሩበት አንድም የታሪክ አጋጣሚን ፕላኔታችን ምድር እንዳልሰማች ታውቋል ፡፡ ፕላኔታችን የሰማችው ነገር ቢኖር ነብዩ ቁርአን ምንጩ ከአላህ መሆኑን መናገራቸው እና ማስተማራቸውን ብቻና ብቻ ነው ፡፡
በዚህም እውነት አስገዳጅነት የተለያዩ ምሁራን አስተያየታቸውን አክለዋል ፡፡ ከነዚህም ውስት አንዱ Dr. Muhammed M.Abu Laylah ይባለል፡፡ ምን ነበር ያልከው?
#Prophet Muhammad distinguished clearly and sharply between his words and the words of God. At no time did he ascribe the quran to him self.;(6)
ነብዩ ቁርአን የራሳቸው ቃል እንዳልሆነ ግና ከአላህ ወደሳቸው የወረደ የአላህ ቃል እንደሆነ በእውነት ነግረውናል ፡፡ ይህ ንግግራቸው ተከትሎ የሳቸው ቃል ለብቻ የአላህ ቃል ለብቻ ሊፃፍ ቻለ፡፡ ይህም በቁርአን አጠባበቅ ላይ አራሱን የቻለ አስተዋፆ አበርክቶ አለፈ……..
ወደ ቁርአን አወራረድ ስመልስህ ይህ የምልህ ቁርአን አወራረዱ ላይ ሁለት ደረጃዎችን ኣሳለፈ፡፡ አንደኛውና የመጀመሪያው ኢብኑ አባስ እንዳለው ከ አላህ ወደ በይተል ኢዛህ(የታችኛው ሰማይ)(7) ሲሆን ይህም አወራረዱ ሙሉ በሙሉ በጠቅላላው ( 8) ሁለተኛውና የመጨረሻው ደግሞ ከበይተል ኢዛ ወደ ነብዩ ሰአወ ሲሆን ይህንም 23 አመት የፈጀ ሀቅ መሆኑን ታሪክ በነጭ ገፁ ላይ በደማቁ ፃፈ(9) ፡፡

የመፅሀፍ ቅዱስ ምንጭ
ወደ አንተው ˝መለኮታዊ˝ ተብዬ መፅሀፍ ስመልስህ ይህ መለኮታዊ ነው ስትል ምታንቆለጳጵሰው ፅሁፍ ምንጩ እየሱስ አይደለም ፡፡ ፓስተሮች ባይነግሩህም ያንተውም እየሱስ ይህን ፅሁፍ አይቶትም ሰምቶትም አያውቅም ፡፡ ተመልከት እንግዲህ ይህን ቃል የምልህ እኔ አይደለሁም ፡፡ እኔ ካልሆንኩ የገዛ ያንተው ምሁራንህ መሆናቸውን መጠራጠር የለብህም፡፡ (10) ይህ አባባል ለ አዲስ ኪዳን ብቻ ሚሰራ መስሎህ ደግሞ እንዳትስት ለብሉይ ኪዳን ፅሁፎችህም እንደሚሰራ አስምርበት፡፡ ……
በአይሁዶች ዘንድ ትክክለኛ ሲባል የሚታመንበት ይህ የብሉይ ኪዳን ፅሁፍ ሶስት ክፍሎችን እንደያዘ የመስኩ ጠበብቶች ይስማማሉ ፡፡ እነዚህ ፅሁፎች የመጀመሪያው Pentateuch (ቶራህ) ሲባል ሁለተኛው እና ሶስተኛው Prophets(Nevi'im) እና writings(Ketuvim) ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህም በ አይሁዶች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው 24 መፅሀፎች ጥርቅም Massoretic Text የሚባል ስያሜ አላቸው ፡፡(11)
የሆነሆኖ እነዚህ የብሉይ ኪዳን ፅሁፎች በነብያት ተፃፉ ሲባል ከሀይማኖት አባቶች ˝ለምእናን ̋ ይነገራቸው እንጂ አንድም እነዚህ ነብያት ለመፃፋቸው የምስክርነት ቃል አልሰጡም ሁለትም ጥናታዊ ምርሮች በነዚህ ነብያት ያለመፃፋቸውን ነው የተናዘዙት፡፡
ስለ ብሉይ ኪዳን ፀሀፊዎች
የመጀመሪያ አምስቱ የብሉይ ኪዳን ፅሁፎፎች የተፃፉት በሙሴ ነው ተብሎ ሲሰበክ ከሀይኖት አባቶች ንደበት ሰምተህ ሊሆን ይችላል፡፡ ግና ይህን ስትሰማ ̋አሜን̋ ብለህ ከመቀበልህ በፊት ሁሉንም ፈትሸ መልካሙን መያዝ እንዳለብህ ደግሞ ከቶ መዘንጋት የለብህም ፡፡ ምናልባት የሐይማኖት አባቶች ̋ ከአያት ቅድመ አያት ˝ በሚል ፈሊጥ ይጓዘሀ ይሆናል አንተ ግን መጓዝ ሚኖርብህ ከተረጋገጡ ጥናቶች አንፃሪ እንጂ ከ ሲሉ ሰማው መሆንኑን ይቅርብህ እያልኩህ……
ወደ ተነሳሁበት ርእስ ልመልስህ የብሉይ ኪዳን ፀሀፊዎች እነማን ናቸው? ለዚህ ጥያቄ ሁለት ምርጫዎች አሉህ
ሀ. ሙሴ እና ነብያት ለ. መልሱ አልተሰጠም
ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ ግዴታ ምሁራዊ ጥናቶችን ማየት ለኖርብን ነው፡፡ …….
በመፅሀፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት ካደረጉ የመፅሀፍ ቅዱስ ጠበብቶች ውስጥ አንዱ C.H. Dodd የተባለው ምሁር ነው ይህ ሰው The Bible Today የሚል መፅሀፍ የፃፈ ሲሆን በዚህ መፅሀፉ ውስጥ ስለ አምስቱ የመጀመሪያ ፅሁፎች አንዲሁም ነቢያት ስለሚባሉት ፅሁፎች በተነተነበት ሂደቱ የመጀመሪያዎቹ አምስት የብሉይ ኪዳን ፅሁፎች ተሰብስበው ተፅፈው የመጨረሻ ቅርፃቸውን ያገኙት በ 4ተኛው ቢሲ ነው(12) ሲል ነግሮናል ፡፡ ተመልከት እዚሁ መፅሀፉ ለይ ዶድ ሙሴ የነበረበት ጊዜ ሲነግረን 1300 ቢሲ እንደሆነ ፅፏል (13) እናስ ? እናማ በሙሴ እና እሱ ፃፋቸው በተባሉት እነዚህ አምስቱ መፅሀፎች መካከል ያለውን ርቀት ሰማይና ምድር በለው እንጂ ሌላ ምን ትለዋለህ ? እንቀጥል …
ይህን የብሉይ ኪዳን አፃፃፍ አስመልክቶ Willyam G. Dever Professor of near eastern archeology and anthropology at the University of Arizona ይህን መሰል ግን ከዚህ የሚጠነክር ሀሳብ ይዞ ቀርቧል፡፡ ይህ ምሁር እንዳለው የብሉይ ኪዳን ፅሁፎች በአራተኛው እና በአምስተኛው ቢሲ ሲከለሱ እና ሲደለዙ እንደነበረ አክሎ ነግሮናል፡፡ ሌሎቹም ምሁራን ልክ እንደነ Tom Thompson እና የሱ ተማሪዎች ጉዳዩን በተመለተ ትንታኔን ሲሰጡ እነዚህ ፅሁፎች በአራተኛው እና አምስተኛው ቢሲ(Persian period) እንዲሁም በሁለተኛው እና ሶስተኛውን ቢሲ(Hellenistic Period) እንደተከለሱ እና እንደተደለዙ ባቻ ሳይሆን እንደተእንደተፃፉ ጭምር አንድ ብሎናል ምን ነበር ያሉት ?
̋And number of other scholars both American and European who believe that the Hebrew Bible was not only edited in the Persian/Hellenistic period but was written then.˝(14)
ተመልከት ይህ ምሁር እየነገረህ ያለው ̋ኢንተርናሽናል ምሁራን እየነገሩን ያሉት የብሉይ ኪዳን ፅሁፍ ሙሉ በሙሉ የተፃፈው በሙሴ እና ነብያት አለመሆኑን ነው˝ ሲል ነው ፡፡ በ4ተኛው እና በ5ተኛው ቢሲ ነው እነሙሴ የፃፉት ሰትል እንደማትቀለድ እርግጠኛም ነኝ ፡፡ እናም እስካሁን የነገርኩህ መረጃዎች ተንተርሰህ ከላይ ላቀረብኩልህ ጥያቄ (የብሉይ ኪዳን ፀሀፊዎች እነማን ናቸው?) መልስ ሚሆነው ሀ.( ሙሴ እና ነብያት ) የተሰኘው ሳይሆን መልሱ ለ. መልሱ የለም የሚለው ነው፡፡ መልሱ ከሌለ እንግዲህ መልሱን ምሁራን ምን ይላሉ ሳትል አትቀርም መልሱን ወደ በኋላ እመለስበታለው ስል እዚህ ጋር ያዝ ላርግህ፡፡

ቁርአን እንዴት ተጠበቀ? መፅሀፍ ቅዱስስ?

ይህ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ከላይ ቁርአን ምንጩ አላህ እንደሆነ እና የጠነበበውም በነብዩ እንደሆነ ነግሬሃለው ቀጥዬም የብሉይ ኪዳን ፅሁፎች ምንጫቸው ሙሴ እና ነብያት አለመሆናቸውን አሳውቄሃለው፡፡ አሁን ደግሞ ይህ በነብዩ ሲነበብ የነበረው ቁርአን በምን መልኩ እንደተጠበቀ መረጃን ተመስርቼ ወደ ማሳየቱ ተግባር ልግባ ነው ሚባለው ልለፍ?
1. በመጀመሪያ ቁርአን የመጠበቁ ሀላፊነት የወሰደው የኔና ያንተ አይነቱ የሰው ልጅ አይደለም ፡፡ ግና ሐላፊነቱን የወሰደው ዩኒቨርሱን ያስገኘው ተታላቁ ጌታነው፡፡ ይህን የወሰደውን ሀላፊነት እንዲህሲል ነግሮሃል
˝እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡̋(15፡9)
አላህ ቁርአኑን ለመጠበቅ ሀላፊነትን ወስዷልብለን ካልን ቀጣዩ ጥያቄ እንዴት?እኮ እንዴት ?የሚለው ይሆናል፡፡
2. እንዳልኩህ አላህ ቁርአንን እንደሚጠብቀው ቃልገብቷል ይህንም ቃሉ እስከዛሬ ድረስ ፀንቷል እስከትንሳኤ ድረስም ይፀናል ፡፡ የሆነ ሆኖ አላህ ቁርአንን የጠበቀበት የመጀመሪያው መንገድ ወደ ሆነው ሳመጣህ የመጀመሪያው ቁርአን በቃል እንዲያዝ እና እንዲሸመደድ ገር በማድረጉ ነው፡፡ በዚህም ዘርፍ የተካኑ እልፍ አእላፋት ጭንቅላቶች በፐላኔታችን ከበቂ በላይ አሉን አህጉራት ይቁጠሩት እንጂ ቆጥረህ አትዘልቃቸውም፡፡

የታሪክ ምሁራን እንደሚሉን ጥልቀት ያለው የታሪክ ጥናትን ለማከናወን ሁለት አይነት ምንጮች ያስፈልጋሉ የመጀመሪያው በታሪክ ምሁራን ዘንድ (primery source) ወይም የመጀመሪያው ምንጭ ተብሎ ሚታወቀው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ (secondary source) ሁለተኛ ደረጃ ተብለው የሚታወቁት ናቸው ፡፡ እኔም በመጀመሪያ ደረጃ እንዳትስትበት ምፈልገው ወሳኝ ነጥብ በጊዜው የታላቁ ቁርአን የመጀመሪያ ምንጭ (primery source) የሆኑት በጊዜው የተፃፉ ፅሁፎች ሳይሆኑ በቃል የተጠኑት እና በሰው ልጆች አእምሮ ሊያብረሪ ውስጥ የሰፈሩት ቁርአኖች ናቸው ፡፡ ይህም እውነታ በዛንጊዜ ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ ያገለግላል፡፡ ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት አንድም በጊዜው ልዩ የማስታወስ ችሎታ የነበረው ትውልድ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የቁርአን ገርነት እና ቀላልነት ነው፡፡ በጊዜው ታሪክን በቃል ሸምድዶ የማስተላለፉ ሂደትን አስመልክቶ Michael Zwettler እንዲህ ሲል ፅፏል፡፡
˝'In the ancient times, when writing was scarcely used, memory and oral transmission was exercised ̋(15)
በጊዜው የነበሩ አረቦች ያላቸውን የማስታወስ ችሎታና ታሪክ በቃል የማስተላለፍ ብቃታቸውን የሀገራችን የኢስላም ሙጅተሂድ ሀሰን ታጁ እንዲህ ሲል ፅፎልናል፡፡
˝የቁርአን መልእክት መጀመሪያ የወረደላቸው አረቦች እጅግ የሚየስደምም የማስታወስ ችሎታ ነበራቸው ፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የግጥም ትውፊቶቻቸው ከትውልድ ትውልድ ይተላለፉ የነበሩት በቃለ፤ ነበር፡፡̋(16)

ይህን መሰል የማስታወስ ችሎታ ባለው ማህበረሰብ ውስጥ ለመሸምድድ ገር የሆነው ቁርአን ደግሞ ሲወርድ አእምሮ ምን ያህል ሊይዘው እንደሚችል ሳይታለም የተፈተ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ ቁርአን ለመሸምደድ ገር መሆኑን አላህም እንዲህ ሲል ነግሮናል
˝ቁርአንን ለማስታወስ እና ለመረዳት ገር አደረግነው ተገሳጭ አለን̋( 54፡17) ይህም ምክንያት ሆነው እና ቁርአንን ሸምድደው ሲያበቁ ቃል በቃል እየተቀባበሉ ቁርአኑ እስከዛሬ ድረስ ድርሰውታል እመነኝ ይህ የሆነው አንዲት ቃል ሳትጨመር አንዲት ቃል ሳትቀነስ መሆኑ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የኡማው የለውጥ መሀንዲስ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አንዲህ ሲል ፅፏል
˝ ህዝባችን የሐይማኖት መፅሀፋቸውን በቃላቸው እንዳልያዙት አይሁድ እና ክርስትያን አይደለም ፡፡ በምድር ላይ የሚገኙ የቁርአን ፅሁፎች ሁሉ ቢጠፉ እንኳ ቁርአን በህዝበ ሙስሊሙ ልቦና ውስጥ ተጠብቆ ይቆል፡፡˝(17)
እናም ይህ የቃል በቃል መተላለፍ እና የአእምሮ ተሰጥኦ - ቁርአን ይጠበቅ ዘንድ የራሱን አስተዋፃ አበርክቷል ፡፡ በዚህም መስክ ቁርአንን በቃል በመሸምድድ በተምሳሌትነት መቅረብ የሚችሉት ታላቁ ነብይ (ሰ.አወ) ናቸው ፡፡ በሀዲስ እንደደረሰን ከሆነ ታላቁ ነብይ በመጨረሻው ረመዳን ሙሉ ቁርአንን ሁለት ጌዜ ከ ጂብሪል ሆነው በቃል እንዳነበቡት ተዘግቧል(18) ነብዩ ቁርአንን ብቻቸውን ሸምድደው ዝም ብለው እጅና እግራቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም ያንኑ የማስታወስ ብቃት የነበረውን ትውልድ ወደ ማስደሸምደድ ነበር ያለፉት በዚህም ምክንያት ነብዩ በህይወት እያሉ ብዙ ቁርአንን በቃላቸው ሙሉ በሙሉ የሚያውቁ ትውልዶች ለመፈጠር በቁ አል ሀፊዝ አሱዩጢ ይህን እውነታ ሲያብራሩ እንዲህ ሲሉ ፅፈዋል
'Some of the companions who memorized the Quran were: 'Abu Bakr, Umar, Uthman, Ali, Ibn Masud, Abu Huraira, Abdullah bin Abbas, Abdullah bin Amr bin al-As, Aisha, Hafsa, and Umm Salama'. (19)
በዚህም መልኩ ቁርአን በነብዩ የህይወት ዘመን በቃል ሊጠበቅ ቻለ ከነብዩስ በኋላ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት ግን አንድ ጥያቄ ለማንሳት ልገደድ ነው መፅሀፍ ቅዱስ ነብያት እና በ እየሱስ ጊዜ በቃል ባይጠበቅ በፅሁፍ ተጠብቋል ወይ?
መፅሀፍ ቅዱስስ?
የብሉይ ኪዳን ፅሁፎች የእንኳ በነብያት ጊዜ ሊፃፉ ቀርቶ የታሰቡም አንዳልነበሩ ሳልነግርህ አላልፍም ከላይ እንዳየነውም እነዚህ ፅሁፎች በሙሴም ሆነ በነብያት አልተፃፉም ፡፡ ወደ አዲስ ኪዳንም ስንመጣ እና ስንጠይቅ እውን እነዚህ ወንጌሎች በእየሱስ ተፅፈዋል ስንል አልተፃፉም የሚል ቁርጥ ያለ መልስ ነው ፡፡ ካንተው ምሁራን የሚሰጠን ምላሽ ፡፡ ኦኬ! በእየሱስ ካልተፃፉ በእየሱስ ጌዜ ተፃፉ ብለን አሁንም ስንጠይቅ! ኖ አልተፃፉም የሚል ይሆናል አሁንም የምናገኘው ምላሽ (20) ስለሆነም የብሉይ ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን ምንጮች እነማን ናቸው ? ብለን ለመጠየቅ አንተም እኔም ልንገደድ ነው ፡፡ መልሱን እንግዲህ እንዳትሰላች በዚህ ፅሁፍ ክፍል ሁለት ከጥቂት ቀናት ቡሃላ ምላሽ ታገኛለህ እያልኩህ እዚህ ጋር ልሰናበትህ ያንተው ቃልአሚን፡፡
Reference sources
1. ሐመር ተዋህዶ የሐመር መፅሄት ልዩ መፅሀፍ ገፅ 24
2. አንድ አምላክ ብቻ! 2003 አ.ል ገፅ 134
3. ሐመር ተዋህዶ ሚያዝያ 1999 ልዩ እትም ገፅ 26
4. መፅሀፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው ገፅ 19
5. የሐመር ተዋህዶን ቅጥፈት በ እስልምና እውነት ገፅ 63
6. The Quran and the Bible Comparative study pp 55
7. አልሀኪም አል ሙስተድረክ ጥራዝ 2 ገፅ 665-6 ሀዲስ ቁጠር 4216
8. አል ኢትቃን ፊ ኡሉሙል ቁርአን ጥራዝ 1 ገፅ 122
9. የሐመር ተዋህዶን ቅጥፈት በ እስልምና እውነት ገፅ 16
10. The Orthodox Corruption of Scripture, Bart Ehrman,
11. Dictionary of Bible pp. 972
12. C.H.Dodd The bible today pp. 59-60
13. Ibid
14. H.Shanks, “New Orleans Gumbo:plenty of spice at Annual meeting”,Biblical Archaology Review March/ April 1997 Vol. 23 no.2 pp.58
15. Michael Zwettler, The Oral Tradition of Classical Arabic Poetry, p.14. Ohio State Press: 1978
16. የሐመር ተዋህዶን ቅጥፈት በ እስልምና እውነት ገፅ 17
17. መጅሙእ አል ፈታዋ ኢብኑ ተይሚያህ ቅፅ 17 ገፅ436
18. Transmitted by Abu Hurayrah, collected in Sahih Al-Bukhari, 6.520, translated by Dr. Muhammad Muhsin Khan
19. Jalalu-Din Suyuti, 'Al-Itqan fi-ulum al-Quran, Vol. I p.124
20. The Five Gospels pp. 20
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests