ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት በመጽሀፈ ቅዱስ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት በመጽሀፈ ቅዱስ

Postby መርፊው » Thu Jan 23, 2014 9:37 pm

ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በመፅሐፍ ቅዱስ
--------------------------------------------
ኦሪት ዘዳግም 21፡15 ላይ እንዲህ ይላል «ለአንድ ሰው አንዲት የተወደደች አንዲት የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት….»

መጹሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ፡3-4 ላይ እንዲህ ይላል «ዳዊት ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አካናሆምን ወሰደ ሁለቱም ሚስቶች ሆኑለት፡፡»

መፅሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ24፡3 ላይ እንዲህ ይላል «ዩዳሄም ሁለት ሚስቶች አጋባው ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ»

መፅሐፈ ዜና መዋዕል 13፡21 ላይ እንዲህ ይላል«አብያም ፀና አስራ አራት ሚስቶችን አገባ ሃያ ሁለት ወንዶች ልጆችና አስራ ስድስት ሴቶች ልጆች ወለደ »

መፅሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 11፡21 «ሮብዓምም ከሚስቶችና ከእቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሰሎምን ልጅ መዓካን ወደደ አስራ ስምንት ሚስቶችና ስድሳ ስድስት እቁባቶች ነበሩት፡፡»

መፅሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 11፡2-3 «ከነዚህ ጋር ሰለሞን በፍቅር ተጣበቀ፡፡ለእነርሱም ወይዛዝርት የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶ እቁባቶች ነበሩት፡፡»ይላል

1ኛ ዜና መዋዕል 14፡3 ላይ እንዲህ ይላል «ለዳዊትም በእየሩሳሌም ቡዙ ሚስቶች አገባ»
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests