የአምላክ ቃል እርስ በእርሱ ይጋጫልን?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የአምላክ ቃል እርስ በእርሱ ይጋጫልን?

Postby መርፊው » Sun Jan 26, 2014 12:44 pm

የአምላክ ቃል እርስ በእርሱ ይጋጫልን?

5ኛ፡-) አካዚያስ በእስራኤል ሲነግስ እድሜው ስንት ነበር?

መንገሥ በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሀያ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች።(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 8፡26)

አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች።(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 22፡2)ይህ 81 አሃዱ ላይ ይገኛል

ጥ- በ22ዓመት ወይስ በ42 ዓመት ነገሰ?

6ኛ) ዩአኪንም ሲነግስ እድሜው ስንት ነበር?
ዮአኪን መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአሥራ ስምንት ዓመት ጕልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ እናቱም ኔስታ ትባል ነበር እርስዋም የኢየሩሳሌም ሰው የኤልናታን ልጅ ነበረች።(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 24፡8)

ዮአኪንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ስምንት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና አሥር ቀን ነገሠ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 36፡9)

ጥ- 18 ዓመት ወይስ 8 ዓመት?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests