Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby የተወደደው » Wed Dec 07, 2016 10:12 pm

faith and science፤

ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

የሳይንስ ምርምርና ግኝቶት ሁሉ (god of the gaps) የሚባለውን information ሁሉ ወደ ብርሃን በማውጣት የሰው ልጆች ፈጣሪያችን ነበር የሚሉትን
ሁሉ ትክክለኛ ፈጣሪ እለምሆናቸውን እረጋግጦል ለምሳሌ በጥንትዋዊዋ ግሪክ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ የመብረቅ እምላክ ነው መብረቁን የጣለው ይሉ ነበር ነገር ግን በሳይንስ ምርምህ ና ኧውቀት የተነሳ ይህ theory ውድቅ ሆናል፤ ይህንን ሃሳብ በዚህ ላይ እነሳሁኝ ኧንጂ በየሃገሩ ባህል መሰረት እምላክ የሚመስሉና የሚመለኩ ብዙ ነገሮች እሉ ይሁን ኧንጂ የሳይንስ ምርምር በበዛ ቁጥር ሳይንስ ኧነዚህን የመስሉ እምላክ ናቸው የሚሉዋቸውን information ሁሉ ውድቅ እድርጎታል. ስለዚህ የሁሉም ነገር መገኛ የሆነውን ፈጣሪን የበለጠ ኧንድናውቀው ሳይንስ ይረዳናል ወይንስ ያርቀናል?
የተወደደው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Dec 05, 2016 3:31 pm

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ወንበዴው » Thu Dec 08, 2016 11:14 pm

የተወደደው ወንድማችን---ሰላም ላንተ ይሁን፡፡ እንደዚህ የሚመራመር ሰው በጠፋ በስንት ዘመኑ ከየት ተገኘህ ጃል? እንግዲህ ጥያቄህን ለመመለስ ያክል- ሳይንስ ባወቅን ቁጥር ' ፈጣሪ' ከሚባለው ነገር እየራቅን መሄዳችን የማይቀር ነው፡፡ ልክ አባቶቻችን ልጅ ሲታመምባቸው - ጠንቋይ ቤት ይሄዱ እንደነበረውና - ዘመናዊ ህክምና ሲመጣ ግን እንደተቀየሱት ማለት ነው፡፡ ሀይማኖት እና ጥንቆላ ደግሞ- ስማቸው ተለያየ እንጂ አንድ ናቸው፡፡ አለማወቅ - ፈሪ ያደርግሃል፡፡ ስትፈራ ደግሞ- ፈሪሃ -እግዚያብሄር እንዲያድርብህና ሃይማኖተኛ እንድትሆን ያደርግሃል፡፡
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby የተወደደው » Fri Dec 09, 2016 1:20 am

በኔ ግምት ብቻ ሳይሆን በእውነትም ቢሆን ሳይንስ ወደ ፈጠርን እምላክ ያቀርብናል ለምሳሌ origin of life or DNA genetic code ወደ አዚህ እንድንደርስ የሳይንስ ምርምርና አውቀት ቢያደሰንም ይህ ይሁን አንጂ ስለ DNA የሚያጠኑ ሰዎች ሲናገሩ የዳርዊን ፍልስፍና ሳይሆን ነገር ግን ኧግዚእብሄር የሰውን ልጆች ዲዛይን እድርጎ ኧንደፈጠራቸው ነው ዕያመኑ የመጡት የበለጠ በስፋት መነጋገር ዕንችላለን'
የተወደደው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Dec 05, 2016 3:31 pm

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ወንበዴው » Sat Dec 10, 2016 7:05 pm

የተወደደው wrote:በኔ ግምት ብቻ ሳይሆን በእውነትም ቢሆን ሳይንስ ወደ ፈጠርን እምላክ ያቀርብናል ለምሳሌ origin of life or DNA genetic code ወደ አዚህ እንድንደርስ የሳይንስ ምርምርና አውቀት ቢያደሰንም ይህ ይሁን አንጂ ስለ DNA የሚያጠኑ ሰዎች ሲናገሩ የዳርዊን ፍልስፍና ሳይሆን ነገር ግን ኧግዚእብሄር የሰውን ልጆች ዲዛይን እድርጎ ኧንደፈጠራቸው ነው ዕያመኑ የመጡት የበለጠ በስፋት መነጋገር ዕንችላለን'የፈጠረን አምላክ የሚባል ነገር የለም፡፡ ከባድ ቁጩ ነው፡፡ ፈጣሪ ማለት -ቄሱም- ፓስተሩም- ሰባኪውም ለእንጀራቸው ሲሉ የፈጠሩት ነገር ነው፡፡ ስለ DNA የተመራመሩ ሰዎች እግዚአብሄር ነው ዲዛይን ያደረገን ሲሉ ግን ሰምቼ አላውቅም፡፡ግን ደግሞ ዲዛይን ማድረጉ ካልቀረ - ምነው ከበሽታ ፍጹም ነጻ የሆነ ሰውን ለምን አልፈጠረም? ለምሳሌ ለምን አንዳንዱን ሰው ስክዋር በሽታ አስይዞ ይፈጥረዋል?
እስኪ ለማንኛውም ይቺን ቪድዮ እንያት--ለጠቅላላ እውቀት

https://www.youtube.com/watch?v=8r-e2NDSTuE
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ደቂቀ ያሬድ » Wed Dec 21, 2016 5:03 am

ሰኳር በሺታ የኢንዳስትርያል ሪቮሉሽን ውጤት እንጅ ከጥንት የነበረ አይደለም፡፡ ስለ እምነትና ሳይንስ ይህን መጽሐፍ እንብብ፡፡

https://www.amazon.com/WOMAN-FOLLY-scie ... B01G4PK60I
ደቂቀ ያሬድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 219
Joined: Sun Nov 27, 2005 10:33 am

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ቆቁ » Wed Dec 21, 2016 6:14 pm

ወንበዴው wrote:የተወደደው ወንድማችን---ሰላም ላንተ ይሁን፡፡ እንደዚህ የሚመራመር ሰው በጠፋ በስንት ዘመኑ ከየት ተገኘህ ጃል? እንግዲህ ጥያቄህን ለመመለስ ያክል- ሳይንስ ባወቅን ቁጥር ' ፈጣሪ' ከሚባለው ነገር እየራቅን መሄዳችን የማይቀር ነው፡፡ ልክ አባቶቻችን ልጅ ሲታመምባቸው - ጠንቋይ ቤት ይሄዱ እንደነበረውና - ዘመናዊ ህክምና ሲመጣ ግን እንደተቀየሱት ማለት ነው፡፡ ሀይማኖት እና ጥንቆላ ደግሞ- ስማቸው ተለያየ እንጂ አንድ ናቸው፡፡ አለማወቅ - ፈሪ ያደርግሃል፡፡ ስትፈራ ደግሞ- ፈሪሃ -እግዚያብሄር እንዲያድርብህና ሃይማኖተኛ እንድትሆን ያደርግሃል፡፡

መልካም ይመስላል ይህ ውይይት
ቢትወደድ ወንድሜ አለማወቅ ብቻ አይደለም ፈሪ የሚያደርገን
እውቀታችን በጨመረ ቁጥር ፍርሃታችን እየጨመረ ነው የሚሄደው
ለመሆኑ የሰው ልጅ ለምን ይሆን የሚፈራው ?
ለመሆኑ የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ መኖር ከጀመረ ጀመሮ ምን ያወቀው ነገር አለ?
ለምሳሌ ግራቪቲሽናል ፎርስ ?
ለሰው ልጅ ምን ጠቀመ የግራቪቲሽናል ፎርስን ማወቅ ?
ይህንን የግራቪቲሽናል ፎርስ የሰው ልጅ አወቀ አላወቀ ምን የሚጠቅመው ነገር አለ?

መሬት ትዞራለች መሬት አትዞርም የሚለው የጋሊሊዮ ስራ
ለሰው ልጅ ምን ጠቀመ ?
መሬት ብትዞር ባትዞር የሰው ልጅ ምን አገባው ?
እንደውም መሬት ኦርቢቱዋን ትስታለች የሚለው አስተሳሰብ ተሰራጭቶ የሰው ልጆች ቅዘን በቅዘን የሆኑበት ወቅት ነበር
በእስትሮይድ መሬት ትመታለች የሚለው ደግሞ ሌላው ቅዘን በቅዘን ማድረጊያ ቲዎሪ ነው

በሕክምናው አንጻር ለምሳሌ በሽታን ለመከላከል የተለያዩ መድሐኒቶችን የሰው ልጅ ፈጥሮእል
ይህ ነገር የሰውን ልጅ ከስጋቱ ከፍርሃቱ ይቀንስለት ይሆን ?
የሰው ልጅ ከጥንቱ ከጠዋቱ መድሐኒት ፍለጋ ላይ አልነበረም ?
ለምሳሌ ለኮሶ ትል የኮሶ መድሐኒት በሐገራችን ?
ወረርሽን እና ተስቦ በሽታ ሊወገድ ችሎእል
የኤይድስ በሽታ እና የካንሰር በሽታ ?

ወንድሞቼ ፡ መኪና መንዳት ፡ አይሮፕላን ማብረር ወይም የሆነ መሳሪያ ፈጥሮ በቴክኒክ መደሰት ወይም ወደ ጁፒተር መስፈንጠር ሁላ የእውቀትን አድማስ ያሰፋው ይመስለናል እንጂ ከስጋታችን ከፍርሃታችን አንድም ነገር የቀነሰው የለም፡፡

ለምን እንፈራለን ?
እኛ በምድር ላይ ካለን ሞት የለም
ሞት ወደ እኛ ከመጣ ደግሞ እኛ የለንም ያለው ፈላስፋው ወንድሜ ማን ነበር ?
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4005
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ወንበዴው » Thu Dec 22, 2016 8:58 pm

ደቂቀ ያሬድ wrote:ሰኳር በሺታ የኢንዳስትርያል ሪቮሉሽን ውጤት እንጅ ከጥንት የነበረ አይደለም፡፡ ስለ እምነትና ሳይንስ ይህን መጽሐፍ እንብብ፡፡

https://www.amazon.com/WOMAN-FOLLY-scie ... B01G4PK60I


ብራዘር ደቂቀ--ስኳር በሽታ ድሮ--የሰው ልጅ ሲፈጥር ዠምሮ የነበረ ነው፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ካንሰርን ጨምሮ ሁሉም በሽታዎች ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ናቸው፡፡ ጨዋታው ያለው ግን - ተመራምሮ የበሽታውን ዓይነት ማወቁ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ - ሳይንስ ደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን መለካት የቻለው ባለፉት 50 ዓመታት ስለሆነ- ቅድም-አያቶቻችን በሽታው እንዳላቸው ሳያውቁ ይሞቱ እንደነበር ለማወቅ እንደ ወንድም ቆቁ ፈላስፋ መሆን አያስፈልግም፡፡ ይህ ነው እንግዲህ አፍጦ የሚታየው ጥሬ ሃቅ፡፡"ሳይንስ መቆም አለበት" ብሎ አንድ የዞረበት ወንድማችን የጻፈውን አርቲ ቡርቲ ግን ለማንበብ ትእግስቱ የለኝም፤ሳይንስን ለማቆም ይቅርና ላንዲት ሰከንድ እንኳን ለመግታት አይቻልምና፡፡

ፈላስፋው ቆቁ- ሰላም ላንተ ይሁን፡፡ ብለህ ብለህ ደግሞ ቴክኖሎጂ ምን ጠቀመን፣ ቢቀርብን ይሻላል ማለት ጀመርክ? ሌላው ይቅርና እንዲህ በኢንተርነት ስንዳረቅ የምንውለው በቴክኖሎጂ ምኽኝያት አይደለምን? ግን የሚገርምህ ነገር -ልክ እንዳንተ የዛሬ ሁለት መቶ አመት አካበቢ "የሰው ልጅ በሰለጠነ ቁጥር - ነጭናጫ እየሆነ ስለሚመጣ ስልጣኔ መገታት አለበት፡፡ እድገት ደስታን ስለሚቀንስብን ይቅርብን፡" - የሚሉ ሰዎች ከሩሲያ ተነስተው ብዙ ተከታዮች ለማፍራት ችለው ነበር፡፡
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ቆቁ » Fri Dec 23, 2016 4:45 pm

ቢትወደድ ወንድሜ ፡ ሰላም ለአንተ ይሁን
ቴክኖሎጂ ምን ጠቀመ ?
ስማ ሂሳብ ስትማር እስከ ስንት ድረስ መቁጠር ተምረህ ነበር እስከ ሚሊዮን እስከ ቢልዮን ...
ያ የተማርከው ቁጥር ለምን ጠቀመ ?
ለአንተ ለኔ ቢጤው ምንም ነገር ፡፡ለሚሊየነሩ ግን ቢልዮን ትሪሊዮን እያሉ በቴክኖሎጂ ውጤጥ ለተከማቸ ገንዘብ መቁጠሪያ!
ያገርህ ሰው ጨርቅ ሲሸጥ በክንዱ እየመተረ ነበር ፡የሚደምረው ባቄላ እየቆጠረ ወይም ጣቱን እየቆጠረ ነበር ፡የሚደመረው የሚያባዛው ከ1000 አይበልጥምና
ቴክኖሎጂ የሰውን ልጅ ላብና ጉልበት ያቃልላል ተብሎ ነበር የተፈለሰፈው፡፡ ነገር ግን የሆኑ ግለሰቦች ሐብት ማዳበሪያ መሆኑን አልገባህም ? አልታየህም?
ኮምፒተር ሲፈጠር የሰው ልጅ ስራው ይቃለላል ተብሎ ነበር፡፡ እስቲ ልብ አድርገው ኮምፑተር ከተፈጠረ ጀምሮ ጭንቅራቱ እየዞረ ኑሮ የሚያስጠላው ስንቱ ነው ?
እንደውም የስራው ብዛቱ ፡ሞኒተር ፊት ቁጭ ብለህ ቁጥር ስትቀምር ዓይንህ መጥፋቱ አይታይህም ?
በኢንተርኔት መዳረቁ ምን ያመጣል?
እንደውም ፍርሃትና ቅዘን የሚያስለቅቅ ሆኖእል፡፡ ለግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ፡ ለእንድ ሐገርም አደገኛ እየሆነ መጥቶእል
ሰለሉኝ በሉኝ እያለ የሚሰጋው ፍጡር ስንት ይመስልሃል? ገንዘቤን በሉት ወይስ ተረፈ የሚሉትስ ? የመንግስት ካዝናም በፍርሃት እየቀዘነ ነው ፡ወንጀለኛው ብዛቱ አልታየህም?
ይህን ሁላ ለፈጣሪ ጥሎ ኢንተርኔት ላይ መካከም ፡ የፈለገው ይሁን ብሎ ኢንተርኔጥ ላይ መፋጠት ካልሆነ በስተቀር ፍርሃትና ቅዘን እኮ በሁላችንም ላይ አለ፡፡
አይመስልህም ?
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4005
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby የተወደደው » Mon Dec 26, 2016 10:48 pm

ሰላም ለእናንተ ይሁን ለዋርካ ታዳሚዎች ሁሉ መልካም የክርስቶስ ልደት እና አዲሱ አመት የደስታ የእውቀት የመበለፀግ እና እንዲሁም የጤና፣ የሰላም፣ ዘመን ይሁንላቹህ በማለት የጀመርነውን ሀሳብ ለግዜው በመተው እናንተ ያነሳችሁትን ኢንፎርሜሽን እንወያይ ።
ለምሳሌ "ወንበዴ " በሚለው ሀሳብ በመስማማት ቆቁ የሚለውን ኢንፎርሜሽን አልጋራም ። መልሱንም ወንበዴው መልሶታል ያም "በሽታ" ሁሉ ከጥንት ጀምሮ የነበረ እና በ time ውስጥ እስካለን ድረስ አብሮን የሚኖር ነው "በሽታ " ከኛ የሚለየው ከtime ውጭ ስንሆን ወይንም ይህንኑ አለም ለቀን ወደ ኢተርንቲ ስንገባ ብቻ ነው ። ምክንያቱም በኦርጋናችን ውስጥ ሊኖር የሚችለው በሽታ በስጋች ወይንም በመሬታው አካላችን ብቻ እስካለን ድረስ ነው ሰጋችን ከዋናው መኖሪያቸን "ከነፍስ " ሲለይ በሽታዎች ሁሉ ስጋ ጋር አብረው ኢዚያው ያከትማሉ ። ይህ ይሁን እንጂ በቴክኖሎጂ ውጤት እና በዘመናቶች የህክምና ምርምር እና የመድኃኒት ግኝቶች እንዲሁም ሪሰርች በማድረግ የበሽታው መነሻ መታወቅ ብቻ ሳይሆን መድሃኒቱንም በማግኘት ከድሮ ሰዎች ይልቅ አሁን በዚህ ዘመን ያሉ ሰዎች በሕክምና እርዳታና እና ድጋፍ ጊዜያዊና ዘላቂ መኖርን ጀምረዋል ። ለምሳሌ ወንድሜ እንዳነሳው ሀሳብ በዚህ በያዝነው "ድንኮን" በስጋ ሰውነታችን ውስጥ ሊያጠቁን ከሚችሉ ነገሮች የልብ ህክምና ፣የስኮር፣ የደም ግፊት ፣ የሴል ፣ የቲሹ ያው ከላይ እንዳልኩት የኦርጋን እንዲሁም "በነፍሳችን" ውስጥ ከሚገኘው
ክፍል ውስጥ ባሉ ኤለመንቶች " እነርሱም አይምሮ፣ የስሜት ፣ እና ፍቃድ ፣ በሳይኮሎጂ እና በሳይካስትሪት ህክምና ዘላቂ ባይሆንም ጊዜያዊ ፈውስን ወይም ዕርዳታን አግኝተዋል "ለግዜው " ያልኩበት ምክንያት ድንኮናዊ የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ማስቀመጫ ወይንም የሰው ኦርጋን የሚታይ እና የሚዳስስ እና በቀላሉ በአይን ስለሚታይ ህክምና ለማድረግ አስቸጋሪ እና አዳጋች አይደለም ። ነገር ግን
በኣካላችን ውስጥ እና ውጭ ላይ እንደምንታመም ሁሉ በነፍሳችን ውስጥ ያሉ ኤለመንቶችም ይታመማሉ በነገራችን ላይ ሰው በስሜቱ፣ በአይምሮ፣ እና ትክክለኛ ውሳኔ ላለማድረግ ሲሬስ በሆነ በሽታ እንደሚታመሙ እናውቅ ይሆን? ሳይኮሎጂ እና ሳይካስትሪት ዕርዳታ የሚያስፈልገው ለዚህ አይነት የነፍስ በሽተኛ ነው ። ለምሳሌ የአዕምሮ መታወክ "ዲፕሬሽን " እራሱን ማጥፋት የስሜት መቃወስ እንዲሁም ትክክለኛ ውሳኔ "ፈቃድ " ለማድረግ አለመቻል አይነቶች ናቸው ። ከላይ እንደገለፅኩትም እነዚህን ነገሮች በቀላሉ በአይናችን ልክ በውስጣችን እንዳለው ኦርጋን ችግራቸውን ማየት እና መረዳት ስለማንችል ለችግሩ ሙሉ በሙሉ በሕክምና ዕርዳታ መድሃኒቶች በመቃም እና መርፌ በመጠርቆስ መፍትሔ አናገኝም ። መፍትሔ ከወዲያኛው ቢኖረውም?
የተወደደው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Dec 05, 2016 3:31 pm

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ቆቁ » Wed Dec 28, 2016 7:09 pm

ወዳጀ የተወደደው
መድሐኒት የተፈጠረው መቼ ነው ?
የሰው ልጅ መድሐኒት እስከ ተፈጠረበት ድረስ ለመኖር በቅቶእል
አንዳንድ በሽታዎች ቢያስቸግሩትም ለመቁዋቁዋም አላዳገተውም ነበር፡፡
ዋናው የበሽታ ምንጭ በምድር ላይ ለመኖር የሚያመቸንን ቦታ በመመረጥ ላይ ይሆናል ፡፡
የሰው ልጅ በብሮንዝ ዘመንን መሳሪያ ገዝቶ ለመኖር ድንበር ባይሰራ ኖሮ ተስማሚ የሆነ ቦታ ለማግኘት አያስቸግርም ነበር ያለ መድሐኒት ማለት ነው፡፡
ከዛም በኢንዱስትሪያል ዘመንን መሳሪያውን አስፋፍቶ መጠዛጠዝ ከጀመረ ጀምሮ ይኸው የሰው ልጅ በምድር ላይ ያለው አቀማመጥ የተዛባ ሆኖእል
ለሰው ልጅ ለራሱ ነው ሕክምና የሚያስፈልገው ለሕመማችን ሳይሆን
እስቲ እንስሳትን ተመልከት ለምሳሌ ጥንቸልን ፡ የሰው ልጅ ነው በሽታዋ ፡ አንበሳን ተመልከት የሰው ልጅ ነው በሽታው ፡ ዝሆንን . ጅራፍን ሌሎችንም በምድር በውሃ የሚኖሩትን እንስሳት ተመልከት በሽታቸው የሰው ልጅ ነው ፡ የተፈጥሮን በሽታ ተቁዋቁመው ዝንተ ዓመት አልፈው እዚህ ደርሰዋል ወደፊትም ይጉዋዛሉ የሰው ልጅ ግን ሰለጠንኩ ብሎ በሚያመርተው ዝባዝንኬ እና በተለይም የጦር መሳሪያ ( አቶሚክ ቦምብ ) እንዲሁም የባዮሎጂካል የጦር መሳሪያዎች ራሱን ጨምሮ እያጠፋ ነው ከዛም አልፎ የምንኖርባትን ምድር ባህሩን አየሩን እየተፈታተነው ነው
ዛሬ ቴክኒክ ተብሎ የተሰራ ነገር ነገ አየር ያበላሻል ተብሎ ይወነጀላል
ዛሬ ቴክኒክ ተብሎ የተሰራ ነገር ውሃውን በከለ ተብሎ ይወነጀላል
እስከ እሁን ድረስ የምንኖረው ራሳችን በፈጠርነው በሽታ ማለትም በማያስፈልግ ቴክኒክ እና ስልጣኔ ራሳችንን ለማጥፋት ነው
ሳይንስ ለሰው ልጅ መፍትሄ ሳይሆን ማጥፊያ መንገድ ነው፡፡
የሚያሳዝነው ደግሞ የቴኒካል እድገት ከጸሐይ ፍጥነት በበለጠ ፍጥነት መወንጨፉ ነው
የሰው ልጅ እውነተኛ ችግር አይደለም ለሳይንስ እድገት አስተዋጽኦ ያበረከተው ነገር ግን የሰው ልጅ ለገንዘብ ያለው ስግብግብነት ነው ለሳይንስ እድገት አስተዋጽኦ ያደረገው . ይህንን ስልህ እነ አልበርታንስታይንን እነ ጋሊልዮን እነ ነውተን የመሳሰሉትን እነ ፓይታጎረስን እነ እርኬሚዲክስን እና የመሳስሰሉትን ማለቴ አይደለም
ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንዲሉ የሳይንስ የጥፋት ምስጢሩ በሰውልጅ ባህርይ አማካይነት የተለያየ ነው ነው ፡፡
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4005
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Thu Dec 29, 2016 3:04 am

ቆቁ wrote:ሳይንስ ለሰው ልጅ መፍትሄ ሳይሆን ማጥፊያ መንገድ ነው፡፡


ወዳጄ ቆቁ....ይህን የመሰለ አሳፋሪና የደነዘ አስተሳሰብ ይዘህ ፈላስማ ነኝ የማለት ድፍረትህን ሳላደንቅ አላልፍም፡) የሳይንስን "ጥቅም" እና "ጉዳት" ለአፍታ በአይነ ህሊናህ ጎን ለጎን ደርድረህ ብታስበው ኖሮ ከላይ ያለውን አትከትብም ነበር፡፡ በግድ አሁኑኑ ዋርካ ላይ ጻፍ ብሎ የሚገርፍህ የለ....ምነው አንዳንዴ ቆም ብለህ ብታስብ ወዳጄ?

ወደቤቱ ርእስ ስመጣ....ሳይንስም ሆነ እምነት በአጭሩ የሰው ልጅ ራሱንም ሆነ የሚኖርበት አካባቢ፤ አለምና ዩኒቨርስን መነሻና መድረሻ ለመረዳት የሚጠቀምባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ እምነት ማስረጃ አይፈልግም....ካመንክ አመንክ ነው፡፡ ሳይንስ ግን በአስተውሎትና በተለያዩ መረጃና መጠይቅ ዘዴዎች ይጠይቃል፤ ይመረምራል፤ ያመሳክራል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ጊዜያትና እምነቶች የፈጣሪ ቁጣ ወይንም ሌላ ትርጏሜ ተሰጥቷቸው ይታመንባቸው የነበሩ የተፈጥሮ ክስተቶች በሳይንስ በቂ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው እነዛ እምነቶችና አስተሳሰቦች አሁን ተቀባይነት የላቸውም፡፡ አሁንም ቢሆን ግን ሳይንስ ያልደረሰባቸው የአለምም ሆነ የዩኒቨርስ ክንውኖች አሉ....ወደፊት የሰው ልጅ የእውቀት አድማስና ቴክኖሎጂ የበለጠ ጎልብቶ የጊዜ፤ የአድማስና የመረጃ ማሰባሰብና ማጠናቀር ከቀጠለ "ፈጣሪ" መኖር አለመኖሩን እናረጋግጥ ይሆናል፡) ለማንኛውም እስካሁን ባለው አያያዝ ሳይንስ ከ"ፈጣሪ" የሚያርቀን ይመስላል፡፡ ጠቢቡ ሰለሞንም "ብዙ ምርምር ሰውነትን ታደክማለች" ብሎ በሾርኒ ከሳይንስ እንድንርቅ መክሮናል፡)
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ቆቁ » Thu Dec 29, 2016 5:27 pm

ነፍሱ ዝም ብለህ ነው ዳንኪራ የምትረግጠው
ከላይ በጣም ከላይ የጻፍኩትን በተመስጦ ብታነብ ኖሮ ይህንን ባልቀባጠርክ ነበር፡፡
በጣም ትዘላለህ
1.ስማ ነፍሱ ዩኒቨርስን አወቅህ አላወቅህ
2. በዩኒቨርስ ላይ ሚሊያርድ ቢሊያርድ ኮከቦች ኖሩ አልኖሩ
3. መሬት በጸሐይ ዙሪያ ተሽከረከረች አልተሽከረከረች
4.የሶላር ሲስተም ፡ የሚልክ ዌይ ኖረ አልኖረ
ለሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ ለሚኖረው፡ ለሰው ልጅ እና ለምድር ኑዋሪዎች፡ የምድር እንስሳትና፡ የባህር፡ የሰማይ እንስሳት፡ ምን የሚፈይደው ፡ የሚጠቅመው ነገር አለ ነው እምብርት ጥያቄው፡፡
ነፍሱ የዞረ ድምር ያለ ይመስላል፡፡
ቅዱስ አውግስቲኖስን ጠቅሰህ ለኔ ለፈላስፋው ስለ ዩኒቨርስ ከንቱነት ለማብራራት መሞከርህን ዘንግተህ ይሆን እዚህ የመጣኽው?
ነፍሱ የዛ የለንዶኑ ይሁን የአሜሪካኑ የዩኒቨርስ የጊዜ ተመራማሪ የሰው ልጆች ወደ ሌላ ዓለም መሄድ አለባቸው የሚለው ነገር አሳቀኝ ያልከው ተዘንግቶህ ነው እዚህ የመጣኽው ?
ለመሆኑ እምነትና ሳይንስ በምን ይሆን የሚለያዩት ?
በሌላ አነጋገር
በሳይንስ ምን ታገኛለህ ?
በእምነት ምን ታገኛለህ ?
የሰውን ልጅ የሚያስጨንቀው ነገር አለ፡፡
ይህም ከየት እንደመጣ ለምን በዚች ምድር እንደሚኖር አለማወቁ ነው ፡፡
ማወቅ አለበት ?
የሰው ልጅ ሞትና ሕይወት መኖራቸውን እያወቀ ሞትን ግን በፍጹም አይቀበልም፡፡
በዚች ምድር ላይ ለመኖር ይፈልጋል በዚች ምድር ላይ በመኖሩ በጣም ደስተኛ ነው ፤፤
ድሃው ሐብታሙ በጠቅላላው የሰው ልጆች የሚፈሩት ነገር ቢኖር ሞትን ነው ሌላ ነገር አይደለም፡፡
ታሞ መዳን አለ ተሰብሮ መጠገን አለ የመሳሰሉት
ሞት ግን አንድ ነው፤ ሞት መጣ ማለት እኛ የለንም ማለት ነው ፡ እኛ አለን ማለት ሞት የለም ማለት ነው
ሳይንስ ለዚህ ሞት ለሚባለው ነገር መፍትሄ ይኖረው ይሆናል ብለህ ጠይቀህ ይሆን ?
እንደገና
ሳይንስ ለሰው ልጅ መፍትሄ አይደለም ፡ ለመኖር የሚያስችሉትን መሳሪያዎች መፍጠር ከዛም መጥፊያውን መፍጠር ደግሞ የሰው ልጆች በጎ ስራ ሳይሆን መጥፎ ስራዎች ናቸው ፡፡ የምንፈራውን ሞት በዚህም በዛም በማምጣቱ
ለምን ?
እኛ ጥሩ ብንሆን ኖሮ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆን ነበር ( አጼ ዘርዓ ያእቆብ ) ለጥሩ ነገር በጥሩ ሰዎች የታሰበው የሳይንስ ግኝት በመጥፎ ሰዎች እጅ በመውደቁ
ሳይንስ የሰውን ልጅ ከማሻሻሉ የበለጠ የሰውን ልጅ ማጥፊያ ነገር ነው የሆነው ለዛውም በአንድ ደቂቃ ውስጥ
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4005
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Thu Dec 29, 2016 5:54 pm

አይ ያንተ ነገር ጭራሽ እንደግመል ሽንት ወደኋላ መንጎድ ሆነ፡)

የሰውን ልጅ የማወቅ ፍላጎትና የሳይንስን ፋይዳ በመንደርህና በቀብር ጉድጏድ ከገደብህ ሰውዬ ጋር እንዴት ብዬ ከዚህ በላይ ስለሳይንስ ላውራ? በል ተወው

አንተ የሚያስጨንቅህ ሞት ብቻ ከሆነ ለምን ገዳም ገብተህ ሌት ተቀን አትጸልይም? ይጥቀምህ አይጥቀምህ እርግጠኛ ባልሆነም፤ ለጠበበው አስተሳሰብህ ቀላል መፍትሔ ይመስለኛል....በጸሐይ ጥላ ግን ሰዐት እንዳትቆጥር....ጸሐይ ላንተ ምን ትፈይድልሀለች?፡)
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣûîሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby የተወደደው » Fri Dec 30, 2016 3:43 am

ሠላም ለቤቱ ፣ ዳግማዊ ዋለልኝ ፣ በኔ አመለካከት ብቻ ሳይሆን በብዙዎችም ዘንድ በአማኙም አይን ፣ " እምነት ማለት ዝም ብለን የምናምነው ብቻ ሳይሆን ኢቪደንስ የተሞላበት እውነተኛነትን ተይዞ ነው። "
ለምሳሌ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ከድንግል ማሪያም መወለዱን ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ ማለቱን ፣ በሽታውን መፈወሱን ፣ የሞተ ሰው ማስነሳቱን እንዲሁም እራሱ መቃብር ፈንቅሎ ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ ማረጉነና ምጳቱን ፣ እኛ በዘመኑ ያለን ሰዎች የተረዳነው እና ያወቅነው የተነገረንን ቃል ሰምተን እንጂ በአይናችን አይተን አይደለም። ይህ ለኛ "እምነት " ይባላል ።
ሰለዚህ በአይናቸው ያዩትን በጆሮቸው የሰሙትን ያወቁትን እውነት ነው በታሪክ መልክ ለኛ በዚህ ዘመን ለምንኖረው ያስተላለፉልን።


ይህም " observational fact and Historical facts ይባላል ።

መጰሃፍ ቅዱስን እንደምታጠና ባላውቅም ነገር ሰለ ምናምነው እምነት በኦብዘርቨሺናል እና በሂስቶሪካል መልክ እንደ ተጳፈልን እና እነደተነገረን መጰሃፉ በደንብ እንዲህ በማለት ይገልፅዋል ።


" ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1:14) በተጨማሪም በሌላ በኩል እንዲህ ይላል ።

" የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።"
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:16)
እዚህ ጋር እነዚህን የእግዚአብሔር "ቃሎች " ለመጠቀም የፈለኩበት ምክንያት ኦብዘርቬሽናል እና ሂስቶሪካል ፋክት ስላላቸው ነው ።
እነዚህ የጌታ ደቀ መዝሙሮች ያዩትን ፣የዳሰሱትን ፣ የቀመሱትን፣ እና ያረጋገጡትን ወይም "ኦብዘርቭ" ያደረጉትን "በታሪክ" መልክ ለኛ በዚህ ዘመን ላለነው ሰዎች ይህንን እውነት ጵፈውልናል።
ስለዚህ እምነት ማለት "ኢቭደንስ " ባለው እውነት ላይ የተመሰረተ ነገር እንጂ
ያለ "ኢቭደንስ" የምንረዳው አይደለም ለዚህም ነው የዕብራዊው ጰሃፊ ሰለ እምነት እንዲህ አይነት ድፊኒሽን የሚሰጠው ።

" እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።"
(ወደ ዕብራውያን 11:1)

ማለትም "እምነት " ተጨባጭ ባልሆነ "ኢንፎርሜሽን" ወይም ሀሳብ ሳይሆን " እውነትና እና እውቅና ያለውና በኦቨዘርቬሽን መልክ የተነገረንና ታሪካዊ እውነተኛነት ያለው ማለት ነው።
ሌላው ደግሞ መመልከት የሚገባን "ኢንፎርሜሽን "
ሳይንስ እና እግዚአብሔር ሁለቱም የሚያርፉበት አንድ ነገር አለ ያም "እውነት "
የተባለ ላይ ነው ። ይህ ነገር ሳይንስና ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ለማድረግ ሳይሆን ሁለቱም "እውነት " የሆነ ነገር ላይ እንዴት እንደሚደረስ የሚሄዱበትን መንገድ ለማሳየት ነው። እግዚአብሔር የሚለው "እመነኝ" እውነቱን ታያለህ ወይንም ትደርስበታለህ ሲል፣
ሳይንስ በበኩሉ እውነቱን አሳየኝና "አምንሃለሁ" ይላል ። እንዲህ አይነቱ "ቃል " በጌታ እየሱስ ምድራዊ ዘመን ላይ ተፈፅሞ ነበር ። ቶማስ የሚባል የጌታ ደቀመዛሙርት ጌታ የሞትን ሃይል ሰብሮ ከሞት ከመቃብር በትንሳኤ እንደተነሳ በኢንፎርሜሽን ደረጃ ሰምቶ ነበር ነገር ግን ቶማስ ይህንን የሰማውን "ኢንፎርሜሽን" ማረጋገጫ "ኢቭደንስ" ካላገኘ የሚያምን ሰው አልነበረም ይህንን የውስጥ ሀሳቡን ግን ጌታ ተረድቶት ነበር የሰውን ውስጥ ፍላጐት እና መሻት ማንም ሳይነግረው የሚረዳው ጌታ የቶማስን ጥያቄ መልስ እንዲህ በማለት መልሶለታል።(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 20, 25- 28 )
ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ። ጌታን አይተነዋል አሉት። እርሱ ግን። የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም አላቸው።
ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።
ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።

ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለ።

እንግዲህ በሳይንሱ አለም እንደምናውቀው ከሆነ አስቀድመው "እውነት " አሳየን ከዚያም በድርጊቱ "እናምናለን " የሚሉ የቶማስን አይነት ሰዎች በሚታይ ኦብዘርዠቭ በተደረገ ነገር ብቻ የሚያምኑ ናቸው። ከሳይንሱ አለም ጀምሮ እስከ አላማኙ ክፍል በብዙ የሚቆጠሩም በዚህ መደዳ የሚመደቡ ናቸው ። ይህም የሆነበት ምክንያት ሰው በሚታዩ እና በተጨበጡ ነገሮች ላይ ብቻ ነው እምነቱን የሚጥለው ። በተለያዩ ዘመናቶች ለሚኖሩ ሰዎች ከነርሱ በፊት ለተደረገው ማንኛውም ነገር ለመረዳት " ታሪካዊ ኢቨደንስ" ያስፈልጋል ።
ዛሬ በምድራችን ላይ ያሉት ታላላቅ ሳይንቲስቶች ብዙዎች "ፈጣሪ" አለ የለም አይደለም ጥያቄያቸው ፈጣሪ "person" ነው አይደለም ነው ።
ለዚህም ነው ሳይንቲስቶች በሁለት ካታጎሪ የተከፈሉት ወይም ያላቸው "world view" የተለያየው የሆነው። ያም ፈጣሪ "አለ" ወይም "የለም "
የሚል ነው ። ወይንም "ኤቲስት" እና " "አማኝ " የሚባሉት ናቸው ። ሁለቱም ጉሩፖቹ በኦብቭዘርሽናል ሳይንስ ውስጥ የሚመራመሩ
እና የሚያጠኑ ናቸው ። ይህን ከሕክምና ጀምሮ እስከ ክዋክብት ክምችት ወይም "ጋላክሲ " ብለን የምንጠራውን ድረስ ማለት ነው። ነገር ግን
ፍጥረትን ማን ነው የፈጠረው ሲባል ግን ያላቸው የተለያዩ "ቪው " ነው ያላቸው ።
እንደ ኒውተን ያለ "ግራቪትንን" ዲስከቨር ያደረገ ሰው ዲስከቨር ባደረገው የግራቪቲ ግኝት የሁሉን ፈጣሪ የሆነውን እግዚአብሔርን አምላክ ሲያመሰግን ሌላው ደግሞ እንደ ስቲቪን ሃዋልክስ ያለው "ጄኔራል ሪልላትቪሊቲ እና ኮንተም ግራቪቲ" እንዲሁም ብላክ ሆልን ዲስከቨር ያደረገ ሰው እና እንዲሁም የዘመናችን ዳርዊን የተባለው ሰው ሪቻርድ ዳርክሰንን እግዚአብሔር አምላክ የለም ብለው በመሽምጠጥ በገሃድ መጵሃፍ ጵፈዋል ። እነዚሁ ሰዎች ፣በጋድ ድሉዢን" እና "ግራንድ ዲዛይን " መጰሃአፋቸው ይታወቃሉ ።
በሰው የእውቀት መለኪያ በዘመናታት ሁሉ የሰው ልጆች በእውቀታቸው እና በታላቅነታቸው አንቱ ያላቸዋቸውን
ቅዱስ እግዚአብሄር የሚባል ፈጰሞ የለም ለሚሉት ግን መጰሃፍ ቅዱስ እንዲህ አድርጎ ዲፋይን ያደርጋቸዋል

" ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል ።" (መዝ 1,14)

ይህም ማለት ይህንን ቃል በአንደበቱ የሚናገረው ሰው
እግዚአብሔር እያለ የእርሱን ህልውና የረሳ ሰው ነው። ያም ማለት ይህ ሰው ፈጣሪ ስላለ እንጂ ወደ መኖር የመጣው ወይንም በዚህች ፕላኔት የተፈጠረው አምላክ ባይኖር ኑሮ እሱም በሕይወት አይኖርም ነበር ። ስለዚህ መዝሙረኛው ዳዊት በአምላክ መንፈስ ተመርቶ ቃሉን ሲጵፍ ለማንኛውም የሰው ፍጥረት እንጂ ላወቀው ላላወቀው አይደለም ። በዚህ ዘመንም የቃሉ መልእክት ተመሳሳይ ነው ለተማረውም ላልተማረውም ። እግዚአብሔር አምላክ የሚባል ፈጣሪ የለም የሚሉት እነዚሁ "ኤቲስት" ብለው እራሳቸውን የሰየሙ ሙሁራኖች ትልቁ ችግራቸውከሳይንስ ምርምር እና ውጭ "እውነት " የለም የሚል" ቴኦሪ" አላቸው ስለዚህ በእነርሱ የእውቀት ድምዳሜ በሪሰርቸራው ወይንም በጥናታቸው ገደብ የሰሩት ነገር ከሳይንስ ምርምር ውጭ ሌላ አይነት "እውነት "
መገኛ የለም ብለው ነው ሌላ የእውነት በር መገኛ እንደሌለ ነው የሚረዱት ። ዛሬ በምድራችን ላይ ብዙ ቦታ ስለማንኛውም ነገር ሪሰርች በሚደረግበት ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ላይ ለተማሪዎች ሌክቸር በማድረግ በእግዚአብሔር መኖር የሚያምኑትን ተማሪዎች አስከ አምላክ የለም ክህደት ድረስ ትምህርት አለ። ያም በቴዎሪ መልክ ሳይሆን "ፕራክቲካል"
በሆነ መንገድ ነው።
የተወደደው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Dec 05, 2016 3:31 pm

Re: Faith and Science ሳይንስ ወደ ፈጣûîሪያችን ያቀርበናል ወይንስ ያርቀናል?

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Dec 30, 2016 5:02 pm

የተወደደው wrote:ሠላም ለቤቱ ፣ ዳግማዊ ዋለልኝ ፣ በኔ አመለካከት ብቻ ሳይሆን በብዙዎችም ዘንድ በአማኙም አይን ፣ " እምነት ማለት ዝም ብለን የምናምነው ብቻ ሳይሆን ኢቪደንስ የተሞላበት እውነተኛነትን ተይዞ ነው። "
ለምሳሌ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ከድንግል ማሪያም መወለዱን ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ ማለቱን ፣ በሽታውን መፈወሱን ፣ የሞተ ሰው ማስነሳቱን እንዲሁም እራሱ መቃብር ፈንቅሎ ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ ማረጉነና ምጳቱን ፣ እኛ በዘመኑ ያለን ሰዎች የተረዳነው እና ያወቅነው የተነገረንን ቃል ሰምተን እንጂ በአይናችን አይተን አይደለም። ይህ ለኛ "እምነት " ይባላል ።
ሰለዚህ በአይናቸው ያዩትን በጆሮቸው የሰሙትን ያወቁትን እውነት ነው በታሪክ መልክ ለኛ በዚህ ዘመን ለምንኖረው ያስተላለፉልን።


ይህም " observational fact and Historical facts ይባላል ።


ሠላም የተወደደው፣ ሰፋ ስላለው ማብራሪያህ አመሰግናለሁ፡፡ የሀሳብህ ጭብጥ ከላይ የጠቀስኩት ክፍል ሥለመሰለኝ እሱ ላይ ላተኩርና ጥቂት ልበል፡፡

አራቱን ወንጌላትን የጻፉትም ሆነ ሌሎች የአዲስ ኪዳን መልእክቶችን የጻፉት ሐዋርያቶች ኢየሱስን ያወቁት ሰላሳ አመት ከሞላው በኋላ ነው፡፡ የአዲስ ኪዳን ብዙ መልዕክቶችን የጻፈው ሐዋርያው ጳውሎስ እንደውም ኢየሱስ በምድር ላይ እያለ አያውቀውም፡፡ ኢየሱስ ሲወለድ አልነበሩም፤ በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላም ወስዶ የቀበረው ዮሴፍ የሚባል ባለጠጋ ነው፡፡ በሶስተኛው ቀንም መቃብሩ ባዶ እንደሆነ ያዩት እነመግደላዊት ማርያምና ሌሎች ሴቶች ናቸው፡፡ እርግጥ ሐዋርያቶች የኢየሱስን ተአምራት አይተዋል፤ መስክረዋል፡፡ ዛሬም በምድር ላይ ተአምራትን የሚያደርጉ ቄሶች ወይም ፓስተሮች ወይም ሸሆች አሉ፡፡ኢየሱስም ራሱ የእሱ ተከታዮች እሱ ካደረጋቸው የበለጡ ተአምራትን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግሯል፡፡ ነገር ግን "ፈጣሪ" በሚለው ሐሳብ ላይ ከማመን ውጪ ምን ያዩት ነገር አለ? የአንተን አባባል ልዋስና "ፈጣሪ" ብለህ ለማመን "observational and historical facts" ማቅረብ ይቻላልን?

መልካም ቀን!
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests

cron