ለወያኔ ገረዶች ዛቻ የመልስ ምት ስነግጥም

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ለወያኔ ገረዶች ዛቻ የመልስ ምት ስነግጥም

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Feb 08, 2019 12:39 pm

ዘራፍ በል አማራ! (በላይነህ አባተ)
February 8, 2019
የቱርክን የግብጥን አንገቱን የቆረጥህ፣
የጣልያን ደንደስ ሁለቴ የሰበርክ፣
እንዴት አይጡ ጃርቱ ከጓሮህ ያስወጣህ?

ዘርህን ለይተው ሲሰልቡ ሲያመክኑህ፣
በቋንቋህ ለይተው ገደል ውስጥ ሲከቱህ፣
ዘርክን እያጠኑ ሲገርፉ ሲሰቅሉህ፣
ከቤጌምድር ሳይቀር ዛሬም ሲያሰድዱህ፣
ከኢዮብ በላይ ትእግስት ምንድን ሊሰራልህ?

እንኳን ጉራ ፈርዳን ጎንደር ከለቀቅህ፣
በህይወት መኖሩ ምን ሊፈይድልህ?

ከአርባ ዓመታት በላይ ታስረህ ተጨፍጭፈህ፣
በስድስት ሚሊዮን ቁጥርህን ቀንሰህ፣
ዛሬም እንደ ትናንት በስብከት ተታለህ፣
ጭራቅ ያሳደገው ፓስተርን ተማምነህ፣
ስንት ሰው እስቲቀር ማተብህ ይሰርህ?

ይቺ ዓለም ከጥንትም በጎን አትፈልግም፣
እንኳን የሰውን ልጅ ሰቅላለች አምላክም፡፡

ስለዚህ አማራ ቅድስናን አቁም፣
ከሰው ከፍ ብትል ከመላእክት አትደርስም፡፡

እንደ እሳት ተንቦግቦግ ተፋጅ እንደ ፍምም፣
ይኸን ላንተ መቼም የሚያስተምር የለም!

ዳይኖሶር እንዳትሆን ጭራሽ ከምድር ጠፍተህ፣
ዘራፍ በል አማራ ልክ እንደ ልማድህ!በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

የካቲት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1516
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ለወያኔ ገረዶች ዛቻ የመልስ ምት ስነግጥም

Postby ክቡራን » Fri Feb 08, 2019 4:54 pm

"የመግጠም እውቀት ያላቸው እነሆ ይገጥማሉ ዝምባሞቹ የሌላን እየገለበጡ ያመጣሉ..."
ካለቃ ኪዳነ ወልድ መጽሃፍ ላይ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ ብዬ ነው፡፡ የዢች ጥቅስ መታሰቢያነት ከዚህ አለም በሞት ለተለየው ለማከብረውና ለምወደው ለዲጎኔ ወንድማችን ይሁንልኝ፡፤
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ለወያኔ ገረዶች ዛቻ የመልስ ምት ስነግጥም

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Feb 08, 2019 5:48 pm

ከሃዲ ወያኔና ገረዶቹ ሰው በቁሙ ገዳዮች
ያልሞተውን ይሞት ዘንድ የገረፉ ከይሲዎች
የወንድና ሴት ብልትን በብረት ጎርጓሪዎች
በሌብነት ትልቅነት በጊነስ ቡክ ላይ ታዋቂዎች
በቁርጥ ቀን ልጆች እንዲህ ይጋለጣሉ ወራዶች

https://www.youtube.com/watch?v=l_o0gzeGEO0 https://www.youtube.com/watch?v=mLyC3Zt2eUI
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1516
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ለወያኔ ገረዶች ዛቻ የመልስ ምት ስነግጥም

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Feb 09, 2019 3:33 pm

ጭራቅ ያሳደገው ፓስተርን ተማምነህ፣
ስንት ሰው እስቲቀር ማተብህ ይሰርህ?

ማንን ይሆን?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests