ዋናው wrote:እንደዝባዝንኬዉ አለም ... መልካም ልደት ብየ አልልም ... የልደትሽን ቀን እንዴት ና እንደምን እንደምትቀበይዉ አላዉቅምና !
እንደ ቀጣፊዉና ዋሾዉ አለምም አበባ አለጥፍም ... አበባን አበባ ለማለትሽ የማዉቀዉ ነገር የለምና !
ሻማም አላበራልሽም .... ቁጥሩ በመኖርና ለመኖር በመሞከር ተደበላልቋልና !
ኬክም አልቆርስልሽም .... የኬክ ጣእም አይገባኝምና !
ዳንኪራም አላስረግጥም ... የደስታ ምንጭ መሆኑን አላምንምና !
ሳትፈልጊ በሰዎች ምርጫ መጣሽ ... በዛሬዋ የልደት ቀን ማስታወሻሽ ላይ እስኪ ራስሽን እንደገና ዉለጂ ... አብቢ ... ዳግም ቆንጂ ..ቁንጂት በይ ... እደጊ ...ወደ ጎንም ...ወደ ላይም እደጊ ... እወቂ ... ራስሽን እወቂ ... አለምንም እወቂ ... እመኝ ... ራስሽን እመኝ ... ሌሎችንም እመኝ .... በእጂሽ ባለዉ ማጥፊያ ... የትናንትናዉን አጥፊዉ .... ለራስሽም ...ለአለምም ይቅርታን አድርጊ ... የተሰበረ ልብ ካለም ... ይጠገን ... ዳግም እንዳይሰበር ይሞከር ...
ትናንት ጥሩም መጥፎም ሆኖ ሊያልፍ ይችላል ... ነገን ግን የተሻለች ለማድረግ ሁሉም በእጂሽ ... ሁሉም በደጅሽ ነዉ ... እድሜሽን ከፍለሽ ያመጣሽዉ ትልቁ ንብረትሽ ተሞክሮሽ ነዉ ... ተሞክሮሽን አክብሪዉ ... ተመልከችዉ ... ትናንትን በዛሬ አስተካክይዉ ...
እኔ እስከዛሬ እንደምኖር ባዉቀዉ ኑሮ ለራሴ ትልቅ እንክብካቤ አደርግ ነበር ... ግን የስከዛሬዉንም ያክል ልኖር እችላለሁና እንክብካቤየን ጀምሪያለሁ ... ያለፈ የሚባል ጊዜ የለምና ! አለ እንዴ ? የእብድ ነገር ... ግን ጊዜ ያልፋል ... ይለፋ የራሱ ጉዳይ ... ግን አሁኑኑ ለራስሽ እንክብካቤ ጀምሪ ....
ወንድምሽ
ሙዝ 1
ተፃፈ በሙዘይድ
ሜይ 09 2007
____________________________________________::
I remember this. It's dope!