ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳንና ሀይማኖተ አበው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳንና ሀይማኖተ አበው

Postby ደብረታቦር » Sat Sep 03, 2005 10:24 pm

ውድ ኦርቶዶክሳውያን ከዚህ በመቀጠል ግንዛቤያችንን ከፍ በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ለመጠበቅ ይረዳ ዘንድ ቀሲስ መላኩ ባወቀ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ካህን የሆኖት አገልጋይ የቀደመ ተመክሮቸውን ያለፉበትን ውጣ ውረድ መሰረት በማድረግ የአንድ ትውልድ ሮሮ በሚል ርአስ ስውሩ አደጋ በሚል መጻህፋቸው ውስጥ አንዱ ምዕራፍ ሰለ ተሕድሶ ማኅበረ ቅዱሳን እና ሀይማኖተ አበው ማህበር የጻፉትን በዚህ ዐምድ እንወያይበታለን
ስውሩ አደጋ የተባለው መጽሀፍ ለፓስተር ቶሎሳ የድፍረት ንግግር መልስ ሲሆን አንዳ ምዕራፍ ብቻ ግን የአንድ ትውልድ ሮሮ በሚል ርዕስ የወቅቱን ጥያቄ ትመልሳለችና ከመጽህፉ በቀጥታ በተከታታይ በትንሹ አቅርባለሁ::

'" ተሐድሶ ምንድነው?""
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናትን በሰፊው እያነጋገረ ያለው ነገር ቢኖር "ተሐድሶ" የሚለው ቃል ነው:: ቃሉ እንዲህ እንዱህ እንደ አሁኑ ፕርቴስታንታዊ ለሆነ አስተታሰብ ከመዋሉና አከራካሪ ከመሆኑ በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚጠቅሱት ታላላቅ የነገረ መለኮት ቃላት እንዱ ነው:: ንስሐንና ውስጣዊ የሆነ የሕይወት ለውጥን ወደ እግዚአብሔር መመለስን የሚያመለክት ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ ሲኖዶሳዊ የሆነ ለውጥን(መሻሻልን) ሊያመልክት ይችላል ለምሳሌ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታስቦበትና ተመክሮበት ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት ይረዳሉ የሚባሉ መሻሻሎችን ለውጦችንና አዳዲስ ተቓሞችን ሁሉ ይመለከታል:: ከዚህም ታላቁና ቤተክርቲያንን በአስቸጋሪ መክራ ውስጥ መከታ ሆኖ እንድታልፍ ያደረጋት የሰብካ ጉባኤ መቃቃምና የቃለ አዋዲ ድንጋጌ ነው:: ይህ ድንጋጌ ብዙዎች እንደሚያስቡት የሰዎች የአስተሳሰብ ፈሊጥ ሳይሆን የሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔ ነው:: አሁን ግን "ተሐድሶ" የሚለውን ቃል ፕሮቴስታንቱ ዓለም ብቻ ሳይሆን የፖሊቲካው ዓለምም እየተጠቀመበት አስቸጋሪ ቃል ሆናል"" ይቀጥላል

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ተሐድሶ በኦርቶዶክሱ ዓለም

Postby ደብረታቦር » Sun Sep 04, 2005 1:18 am

ካለፈው የቀጠለ(የአንድ ትውልድ ሮሮ) በቀሲስ መላኩ ባወቀ

""ተሐድሶ በኦርቶዶክሱ ዓለም""

ኦርቶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትን የምትጠብቅ እንጂ እምነትን በዘፈቀደ ወይም ባሰኛት መንገድ የምትቀያይር ስላይደለች ዛሬ ኣንዳንዶች ከዚህ ቤተክርስቲያን የወጡ ሰዎች እንደሚናገሩት ተሐድሶ የሚለውን ቃል እምነትን በተመለከተ አታውለውም:: ሀይማኖት ምን ዓይነት መልክ እንዳላት ሐዋርያው ይሁዳ በመልእክቱ ጽፎልናል "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለቅዱሳን የተሰጠች በማለት" ስለሆነም አትበረዝም አትከለስም ወይም ብልየት እርጅና አያገኛትም በሌላ በኩል ግን የክርስቲአያን ሕይወት ዕለት እለት ይታደሳል:: ውስጣዊ የሆነውን የሕይወት ተሐድሶ የሚያገኘውን በንስሀ በጾም በጸሎት ነው:: ይህብ በተምለከተም በብዙ ቦታዎች ቅዱሳት መጻህፍት ይናገራሉ::
በሌላ በኩል ደግሞ አስተዳደራዊ የአሠራር ለውጦችና አልፎ አልፎ ቀኖናዊ ለውጦች ይኖራሉ:: እነዚህም ቢሆኑ የሚከናወኑት በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ስለሆነ ለውጡ ሲኖዶሳዊ ነው እንጂ የአመጽ ውይም የጥቂት ግለሰቦች አይደለም::

ይህም በኦርቶዶክሱ ዓለም የተለመደ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያንችን የከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ለብዙ ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ የተሰማሩትና አያሌ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ሉሌ መላኩ "የቤተ ክድርስቲያን ታሪክ" በሚለው መጽሐፋቸው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ሲኖዶሳዊ ተሐድሶ ሲገልጡ
"""በኮፕቶች(በግብጾች) ዘንድ የተሐድሶ አባት በመባል የሚታወቀው ቄርሎስ አራተኛ(1854-1861) የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ነው:: ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሣው ትምህርትን ማስፋፋት(የማሰራጨት) ሰለነበር በግብጽ ካህናት ዘንድ ሰፍኖ የነበረውን የትማህርት ጉድለት ዝቅተኛነትን ለማሻሻል ካህናት ተግተው እንዲማሩ አደረገ:: ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም ከፍቶ ዓለማዊና መንፈሳዊ ዕውቀት የነበራቸውን በማሰማራት መጻህፍትን በገፍ በማቅረብ ካህናትና ም እምናን የቅብጥ(ኮፕት) የዐረብኛ የእንግሊዝኛ የፈረንሳይኛ የኢጣልያንኛ የቱርክ.. ወዘተ ቃንቃዎችና የትለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እንዲማር አደረገ""'ይሉናል

ይቀጥላል: በሚቀጥለው ኦርቶክስ ተሐድሶ የሚልውን ይዤ እቅርባለሁ

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ማኅበረ ቅዱሳንና ተሐድሶ

Postby ደብረታቦር » Sun Sep 04, 2005 11:02 am

ማኅበረ ቅዱሳንና ተሐድሶ ካለፈው የቀጠለ (በቀሲስ መላኩ)
"የማኅበረ ቅዱሳን በመላው ኢትዮጵያ ዕውቅና ማግኘትና የተሐድሶ መስፋፋት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዊች ናቸው::ማኅበረ ቅዱሳን ያለ ተሐድሶ አሁን የደረሰበት ደረጃ አይደርስም ነበር:: ተሐድሶም ያለ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ያለ መተዋወቅና መስፋፋት አያገኝም ነበር:: አንደኛው የሌላኛው ሕልውና መሠረት ነው::"" ይቀጥላል

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ካለፈው የቅጠለ

Postby ደብረታቦር » Mon Sep 05, 2005 5:03 am

ማኅበረ ቅዱሳንና ተሐድሶ (ካለፈው የቀጠለ)

""ማኅበረ ቅዱሳን ከብላቴ ጦር ሠፈር የተመለሱ ጥቂት የዩኒቨርስቲ ትማሪዎችና በዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ ለሁለትና ለሦስት ወራት ከሰለጠኑ ካህናት የተወሰኑትን ይዞ ሲቓቓም ዓላማው አድርጎ የተነሳው በከፍተኛ ትምህርት ተቅማዋት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የቤተክርስቲያንቸውን እምነትና ሥርዓት ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ያደርጉት እንደነበረው ዶግማን ወይም እምነትን ክቀኖና ቀኖናው ከባህል ባህሉን ደግሞ ከአጉል ባህል እየለዩ ማስተማርን ነበር:: ነገር ግን ገና ከምሥረታውማኅበሩን የረጅም ጊዜ ዓላማ የነበራቸው ስዎች ያሰባሰቡዋቸው ልጆች መቆጣጠርና ለዓላማቸው ማድረግ ጀመሩ:: በተለይም የከፍተኛ ተቅማዋትን በማስተማር አያሌ የቤተ ክርስቲያቱዋን ልጆች ያፈራውን ሀይማኖተ አበውን ልማፍረስ ዕድሜ ልካቸውን ሲያውጠንጥኑ የነበሩት ስዎች አሁን ሀይማኖተ አበውን አፍርሰው ማኅበረ ቅዱሳንን ለመተካት ይማስኑ ጅመር::

ቁጥሩ ከሠላሳ ሚሊዮን ለሆነው የኢትዮጵያ ምእመናን ሁለት የወጣቶች ተቅማዋት ቢያንሱበት እንጂ አይበዙበትም:: ይሁን እንጂ ገና ከጅምሩ የአንዳቸው ሕልውና በአንዳቸው መጥፋት የሚወስን እስኪመስል አንዱ አንዱን እስኪያጠፉ ድረስ ከፍተኛ ግብ ግብ ውስጥ ገቡ:: ይህ ደግሞ ለቤተክርስቲያን ሆነ ሁለቱም ማኅበራት በሥራቸው አቅፈው ለያዙት ህዝብ የሚጠቅም አልሆነም:: ይቀጥላል
ይትባረክ አምላክ አብዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ማኅበረ ቅዱሳንና ተሀድሶ

Postby ደብረታቦር » Mon Sep 05, 2005 9:28 am

ካለፈው የቀጠለ

ማኅበረ ቅዱሳን ከምስረታው ሕዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት የማኅበሩን አቅዋም ወግን በማጥበቅ መጛዝ እንደሆነ ግልጥ አደረገ:: ሴቶቹ ምንም ዓይነት ጥለት ያልገባበት ነጭ ልብስ እንዲለብሱ ነጭ ሻሽ እንዲጠምጠሙ ከጸጉራቸው አልፎ እስከ ግንባራቸው እንዲከናነቡ (ይህ ቅዳሴና ስብሰባቸው ላይ ብቻ ነው) ወንዶቹም እንደዚሁ ነጭ ልብስ እንዲለብሱ ታዘዙ:: በሠርጋቸው ውቅት ከመዝሙር ውጭ ባሕላዊም ሆነ ዘመናዊ ዘፈን እንዳይዘፍኑ ተነገራቸው::

ነገር ግን ይህ ሁሉ መልካም ሆኖ ሳለ ወዲያው ማኅበሩ የሀይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበርን ኦርቶዶክሳዊነት ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ መጠየቅ ጀመረ:: ምንም ሀይማኖተ አበው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነባር ማኅበር እንደሆነ የተቓቓመውም ጀስዊትስ ውይም ኢየሱሳውያን የተባሉትን በዩኒቨርሲቲና በሌሎችም የትምህርት ተቓማት የሚያደርጉትን መስፋፋት ለመከላከል ቢሆንም ንጉሠ ነገስቱ የበላይ ጠባቂ ፓትርያርኩ ሊቀ መንበር ሆነው የሚመሩት የቤተክርስቲያኒቱ አካል እንጂ የተገነጠለ የአግልግሎት ክፍል አለመሆኑ ቢታወቅም ማኅበረ ቅዱሳን ግን ሀይማኖተ አበው የመናፍቃን ማኅበር ነው አሠራሩም አካሄዱም በኑፋቄ የትሞላ ነው እያል ይጽፍ ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ብጹዓን ሊቃን ጳጳሳት በሃይማኖተ አበው ጉባኤ ላይ እየተገኙ ያስተምሩ ነበር:: የሃይማኖተ አበው አባላትም ይህ የማኅበረ ቅዱሳን አካሄድን ለመክላከል ይመስላል አንዳንድ ቃላትን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ መውርወር ጀመሩ:: የቃላት ውርወራውና አምባጉዋሮው ከሁለቱ ማኅበራት አልፎ ወደ ቤተ ክርስቲያንዋ ከፍተኛ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ገባ:: የማኅበረ ቅዱሳን ልጆች መንበረ ፓትርያርክ ጊቢ ይካሄድ ወደነበረው ወደ ሃይማኖተ አበው የሚሄዱትን "መናፍቃን" ሲሉአቸው የሃይማኖተ አበው ልጆች ደግሞ ወደ ምስካየ ሃዙንና ግቢ ገብርኤል የማኅበረ ቅዱሳን ጉባኤዎች የሚሄዱትን "ጋኔን ሳቢዎች መተተኞች" ይሉአቸው ነበር:: በዚያ የልጅነትና ጭፍን የድርጅት ፍቅር የነበረውን መወጋገዝ ዛሬ ያ ልጅነት አልፎ ስናየው እንዴት የሚያሳፍር ነው:: በዚያ ወቅት በዚያ የቃላት ድብድብ ላይ እንሳተፍ የነበርነው የሁለቱም ወገኖች የምናገለግለው የየግላችን ድርጅቶች እንጂ ቤተክርስቲያንን እንዳልነበረ የምናውቅ ስንቶች ነን::

በሚቅጥለው ጽሁፍ የሃይማኖተ አበው መዘጋት የሚለውን ንኡስ ርዕስ ይዤ እቀርባለሁ

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Postby NATHRATHE » Mon Sep 05, 2005 9:52 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አማላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ይህን እርስ ጀምሮ ስለ ተአድሶነት በታአድሶ አራማጆች አመለካከት ከተአድሶች መሪ ከፓስተር መላኩ ባወቀ የተነገረውን እየተረከልን ያለው ወንድማችን ጽሁፉ ፍሬ ነገር የሌለው ተረት ሊሆን እንደሚችል የገመትኩት ገና ፓስተር መላኩን የበግ ለምድ አስለብሶ "ቀሲስ" መላኩ ባወቀ እንደጻፉት ብሎ ሲጀምር ነው::እኔ እንደውም እስከዛሬ ወርካ ላይ እነዚህ የውስጥ የቤተክርስቲያን ጠላቶች አይጽፉም ብዬ ይገርመኝ ነበር::ያው ሌሎቹ Protestant አንዳንዴ እየተሳደቡ አንዳንዴም ለመወያየት ብለው እነሱ የሚሉትን ሲጽፉ ስለማይ እነሱ እየተናገሩልን ነው ብለው ይሆናል ብዬ ገመትኩኝ::ከተነሳ አይቀር እስኪ ስለተአድሶ ሆነ ስለ ፓስተር መላኩ እኔም የተወሰነ ነገር ልበል::በመጀመርያ በተአድሶ ኑፋቄ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ማኅበራትን ስም በመጥቀስ ልጀምር::

የተሐድሶ ኑፋቄ በቤተክርስቲያን የሚያሰራጩ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች
 1. ማኅበረ በኩር:-ይህ ማኅበር የነ መሠረት ስብሐት ለአብ ሲሆን በጣም የሚታወቀው "ጮራ መጽሔትን" በማሳተም ነው::የዚህ ማኅበር አላማ አዋልድ መጽሐፍትን(ድርሳናትን ገድላትን የታምራት መጽሐፍትን) በመተቸት ሕዝቡ እንዲጠራጠርና እንዲክድ ማድረግ ሲሆን ለዚህ አላማው ማታለያ አድርጎ የሚጠቀምበት ደግሞ በመጽሐፍቱ ሽፋን ላይ የቅዱሳን ሥዕል መጠቀም የግዕዝ ጥቅሶችን መጥቀስና ሌሎች ኦርቶዶካዊ ማስመሰያ መጠቀም ነው::
 2. ፍኖተ ሕይወት ማኅበረ መዳኒያለም:-ይህ ማኅበር ዋነኛ አላማው በጽዋ ማኅበራት ውስጥ ሠርጎ በመግባት ወደፕሮቴስታንት ጉባዬ መለወጥ ነው::
 3. የምስራች አገልግሎት ኢትዮጵያ:-በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ገዳማትና ሰንበት ት/ቤቶችን ለመበከል የተቋቋመ ነው::የዚህ ድርጅት ታላቅ ተለኮም የተሳሳቱ መጽሐፍትን ወደ ገዳም እያስገቡ መበከል ነው::ከዚህ ውጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር መሰረታን ነቃቅሎ ለመጣል(ክርስቶስ በደሙ የመሰረታትን ማድረግ አይቻልም እንጂ) ይረዳል የሚለውን መንገድ ለማወቅ ጥናት አስጠንቶ የራሱን ሰዎች ሆነ ሌሎች ተባባሪዎች በማሳተፍ ተግባራዊ ለማድረግ የሚሯሯጥ ድርጅት ነው::ይህ ድርጅት ካስጠናቸው ጥናቶች ለአብነት ያህል አንዱን እንመልከት::መዲና መጽሔት ቁጥር 001 ጥር 1994 ዓ.ም ገጽ29-30 ላይ ጥንቷዊቷን የኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ የተዘጋጀ ምስጢራዊ ሰነድ" በሚል ያወጣው ጥናት ተጠቃሽ ነው::
 4. የተሐድሶ መነኮሳት" ኅብረት:-ይህ ግሩፐ በአንድ ወቅጥ በኢግዚብሽን ማኅከል ተሰብስቦ ያዘጋጀውን የዳንስ ፕሮግራም በVideo የተዘጋጀውን አብዛኞቻችን ስለተመለከትን አላማቸውን ያላያቹ ካሴሱን ፈልጋችሁ ብታዩት ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል::
 5. ሐይማኖተ አበው:-ይህ ቡድን አሁን ስለመኖሩ የማውቀው የለኝም::በመጀመርያ ለበጎ አላማ አባቶች ያቋቋሙት የተማሪዎች ማኅበር ቢሆንም Universalism የሚል አጉል ፈሊጥ አምጥቶ ፐሮቴስታንት የሆኑ ሰዎችን አስገብቶ የፕሮቴስታንት ስራ ሊሰራ ሲል ከቤተ ክርስቲያን የተባረረ የመናፍቃን መጠቀሚያ የነበረ ድርጅት ነው::


ሌሎችም በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያን ተደብቀው እንክርዳድ ሐዋርያት በዘሩት ስንዴ ላይ ለመዝራት የሚራወጡ አልጠፉም::

ለማንኛውም የሚቀጥለው ጽሑፍ ከማቅረቤ በፊት የገሐነም ደጆች የሚለውን ጽሑፍ ያላነበባችሁ እንድታነቡት በመጠቆም እግዚያብሔር የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላቶችን እንዲያስታግስ በጸሎት እንድንተጋ እያሳሰብኩ እሰናበታለሁ::

ይቆየን::
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

መምሬ/ባለውቃቢው ናታርቴ ምነው ቸኮሉ? ወንድማችንኮ ደህና ትንታኔውን አልጨረሰም

Postby ዲጎኔ » Tue Sep 06, 2005 2:30 am

የክርስቶስ ሰላም ለሁላችን ይሁን
መምሬ /ባለውቃቢው ናታርቴ
(ይቅርታ ለመዝለፍ ብዬ ሳይሆን በሌላ አምድ ናታርቴ ውቃቢን በአዎንታዊ ስለጠቀሱና ስለሚያምኑበት ይህንን መጠሪያ አይቃወሙም)

እጅግ የተወደደው ወንድማችን ደብረታቦር በማለፊያ ጭብቶችና ትንታኔ ያሳለፍኩባቸውን ሂደቶች እስከአሁን ድረስ ከጥቂት ቴክኒካዊ ልዩነቶች በቀር አቅርቦ ሳይጨርስ ለለመዱት ዘለፋ ምነው ቸኮሉ በሌላ አምድ እኔን አትቸኩል ይሉ አልነበር::

ወደእርስዎ ዘለፋዊ ትንተና ተመልሼ ጥያቄ ላንሳ ባለውቃቢ ወይም ባለአውሊያም ቢሆኑ የሚያውቁትን ይመልሱና በቃሉና በታሪኩ ፈትሸን እናልፈዋለን

1. ከሁሉ በፊት ተሀድሶን በኢትዮጵያ ከነሉተር በፊት ያካሄዱት የቀድሞዎቹ የቆየጻ ገዳም የነእስጢፋኖስ ማህበር ለምን ተዘለለ? አሁንምኮ በጉንዳጉንዲ እንዳሉና Heretics በኢትዮጵያ ተብለው በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ክርክር ይደረጋልና

2. አለቃ መሰረት ስብሀት ለአብ እንደኑፋቄ በቤተክርስቲያን በይፋ የተወገዙበት ዘመንና ዝርዝር ማስረጃ አልዎት? ኑፋቄ ከተባሉስ ለምን የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም ሆነ ሌሎቹ የዲያቆናት ማሰልጠኛ ተቓሞች መጽሀፋቸውን በይፋ ይጠቀማሉ?

3.የቀድሞው የሀይማኖት አበው ማህበር" የመናፍቃን መሳሪያ በመሆኑ" እያሉ ፍርደገምድል አስተያየት የሰጡበት በሀይማኖት አበው ማህበር ላይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተላለፈ አንዳች ውሳኔ አልዎት?

4.በኦርቶዶክስ በተክርስቲያን የተሀድሶን አስፈላጊነት ያስተማሩ እንደ አቡነ ቄርሎስ ያሉ አባቶች የሰጡትን ትምህርት ያውቃሉ?

በተረፈ መካሪዬና በቅድስት ጥምቀት የተወለድኩባትን እናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኔን በጎ እድገት ዘወትር የምታካፍለኝና ትግሳጽህ የጠቀመኝ ወዳጄ ልቤ ደብረ ታቦር መጣጥፍህ ይቀጥል: ለባለውቃቢዎች ዘለፋ ቦታ አትስጥ እልሀለሁ::

ዲጎኔ የክርስቶስ ባርያ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

የሃይማኖተ አበው መዘጋት

Postby ደብረታቦር » Tue Sep 06, 2005 10:31 am

ከርዕሴ ፈቀቅ ብዬ ከናታርቴ ጋር አተካራ መግጠም ባልፈልግም በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የጠፋው ልጅ ሲመለስ አባቱ ከግቢ ውጭ ድረስ ሄዶ ልጁን እንካን ደህና መጣህ ብሎ ፍሪዳ አርዶ ደግሶ ሲቀበል ወንድሙ ግን ስለስነፈ የጠፋው ውንድሙ በመምጣቱ ደስተኛ ስላልነበረ ወደ ቤት አልገባም አለ:: የዚህ ወንድሜ እና የማህበረ ቅዱሳን ዕጣ ፋንታ ከዚህ ሰነፍ ጋራ ነው በውጭ ነው ያሉት:: እግዚአብሔር የንስሃ ሕይወት ያስተምራቸው ይስጣቸውም! አሜን!!!ውድ አንባቢዎች ወደ ርእሴ ስመለስ የሚቀጥለው የሚሆነው
"የገሞራው ጋዜጣ ጽሑፍ እና የሃይማኖተ አበው መዘጋት" ካለፈው የቀጠለ በቀሲስ መላኩ ባወቀ
""እንዲህ በዚህ ውቅት ነው ማን እንደጻፈው የማይታወቅ ጽሑፍ "ገሞራው" በሚባልና አሁን ከሕትመት ውጭ በሆነ የግል ጋዜጣ ላይ የወጣው:: ጽሑፉ ሰፊ የሆነና የተሐድሶ ማኅበር እንዴት እንደሚንቀሳቀስና ዓላማውም ምን እንደሆነ የሚገልጥ ነበር :: ከሁሉ የሚገርመው ግን ጽሑፉ ሰለተሐድሶ ሆኖ ሳለ ከጽሑፉ ጋር አብሮ የውጣው ግን በጎፋ ገብርኤል ለረጅም ጊዜ ያገለገሉና የኢትዮጵያዊው ስማእት የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ልጅ የሆኑ መነኮሴና እርሳቸው የሚያስተምሩዋቸው የሃይምኖተ አበው ተማሪዎችን የያዘ ፎቶ ነበር::(እኚህ አባት ጋዜጣው በወጣ ማግሥት ያለ ምንም ጥያቄ ከሚያገለግሉበት ደብር እንዲወገዱ ተደረገ:: እምነት ክህደታቸውን የጠየቀ አጥፍተውም ከሆነ በንስሐ እንዲመለሱ የመከረ ማንም አልነበረም :: ማኅበረ ቅዱሳንም አባ እገሌ መናፍቅ ናቸው እያለ ይጽፍ ጀመረ:: ይህ ሁኔታ ቢያዝናቸውና አቤት የሚሉበት ቦታ ቢያጡ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው ከብዙ እንግልት በኃላ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ተፈርዶላቸዋል:: ዛሬ በቤተክርስትያና ውስጥ በታላቅ የሥልጣን ደርጃ ላይ ናቸው:: የጋዜጣው ጽሑፍ መደምደሚያ ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር የተሐድሶ ድርጅት አካል እንድሆነ የሚናገር ነበር::

ወዲያው በግል ጋዜጣ የተጀመረውን ሰፋ አድርጎ ማኅበረ ቅዱሳን ""ስምዓ ጽድቅ"" በሚባለው ጋዜጣው
ላይ አወጣው:: ሃይማኖተ አበውም እንዲዘጋ ጥያቄ አቀረበ:: ለዐርባ ዓመት በቤተ ክርሲቲያን ውስጥ ታላቅ ሥፍራ የነበረውን ብዙ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያኖችን አባት ያፈራ በሃይማኖት ያጸና ማኅበር በአንድ የግል ጋዜጣ ላይ በተጻፈ ጽሑፍና በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት እንዲዘጋ ተወሰነበት:: በየሳምንቱ ቅዳሜ ያሰበሰብ የነበረውም በሺህ የሚቆጠረውንም ወጣት መናፈቅ ስለሆናችሁ በቤተክርስቲያናችሁ ውስጥ ሥፍራ የላችሁም ተብለው አውሬ እንዲበላችው ብውጭ ተጣሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን ጉዳዩን እናጣራ ያለ የእንዚህን ሁሉ ወጣቶች ዕጣ ፋንታ ምንድን ነው ያለ አንድም ሰው አልነበረም:: አምላካችን የአንድ ሰው መጥፋት የሚያሳዝነው አምላክ ነው:: እንዲያውም ወደዚህ ዓለም እኛን ለማዳን የመጣበትን አመጣጡን ሁኔታ የገለጠልን የጠፋችውን አንዲት በግ የጠፋውን አንድ ልጅ የጠፍውን አንድ መሀልቅ የጠፋውን አንድ ድሪም በምሳሌ በማቅረብ ነው:: ለአንዱ የሚገደው ነውና:: ለዚህ ነው ለአንዱ አርዮስ እኒያን የመሰሉ ቅዱሳን አበው ተሰብስበው የለመኑት የመክሩት:: በዚያ ወቅት ግን ለነዚያ ለተበትኑት ልጆች ዕድል የሰጠ እስቲ አንድ ደቂቃ እናነግራቸው ያለ የለም ነበር:: ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ በየሳምንቱ ቅዳሜ በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ ውስጥ ያሰበሰብ የነበረው ሕዝብ ሃይማኖተ አበው መዘጋቱን ያወቀው ቅዳሜ ሲመጣ አጥሩ ልይ ከተለጠፈ ውረቀት ነው::

ይህም ሁኔታ ለማኅበረ ቅዱሳን አመቺ ስልሆነለት በተቻለው መጠን የሃይማኖተ አበውን ስም ማጥፋት ቱን ገፉበት:: ትናንት ከትናንት ውዲያ ሀገሪቱ ካፈራቻቸው ፕሮፌሰሮችን ታላላቅ ምሁራን ጋር ሆነው በአባልነት የደከሙበት ሊቃነ ጳጳሳት ምን እንዳሉ ባላውቅም ማኅበረ ቅዱሳን ግን የሃይማኖተ አበውን ውንጀል ይዘረዝር ገባ:: ከወንጀሎቹ አንዱ የዓለም ተማሪዎች ህብረት ፌደሬሽን አባል መሆኑ ነበር:: አይ አለማወቅ ለንግሥና ሲያበቃ:: የዚህ መጽህፍ ዓላማ አይደለም እንጂ ብዙ ለማለት ይቻል ነበር:: አባልነትን ካነሳን ከአባልነት በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን የስራ አስኪያጅ ውስጥ የነበረችና መሪዎቹ እየመጡ የሚጎበኙን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ምንድን ነው? በእምነት አንድ ስለሆንን አባል የሆነው? አይደለም:: አንድ በሚያደርጉን ሌሎች ነገሮች አብሮ ለመሥራት ነው እንጂ በእምነት ከሆነ የመጨረሻው የስህተት አጋፋሪዎች የሚገኙት በዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ነው::

ሃይማኖተ አበው ምንም እንካን ከመንበረ ፓትርያርክ
ግቢ ውስጥ በግፍ ቢባረርም በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙት አባላቱ በሃይማኖታቸው ጸንተው ሁኔታውን በትግስት እንዲያሳልፉ አሳሰበ:: በሐረር በጅጅጋ በደብረ ብርሀን በባህር ዳርና በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙት አባላቱም ወደ አባቶች አቤት ማለቱን ተያያዙት::

ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈልገው ድግሞ የሃይማኖተ አበውን ስም አጠራር ከምድረ ገጽ አጥፍቶ የርሱን ድርጅት ከዳር እስከ ዳር ማጠናከር ነበር:: ይህ አልሆን ሲለው ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይትወቅ ሁኔታ ሌላ ነገር ማድረግ ወሰነ ያም በጉልበት መጠቀም ነበር::"" ይቀጥላል

በሚቀጥለው በሃይማኖተ አብው ወጣቶች ላይ በድሬዳዋ የተካሄደው ድብደባና ነፍስ ግድያ

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Re: የሃይማኖተ አበው መዘጋት

Postby NATHRATHE » Wed Sep 07, 2005 8:53 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ደብረታቦር wrote:ከርዕሴ ፈቀቅ ብዬ ከናታርቴ ጋር አተካራ መግጠም ባልፈልግም በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የጠፋው ልጅ ሲመለስ አባቱ ከግቢ ውጭ ድረስ ሄዶ ልጁን እንካን ደህና መጣህ ብሎ ፍሪዳ አርዶ ደግሶ ሲቀበል ወንድሙ ግን ስለስነፈ የጠፋው ውንድሙ በመምጣቱ ደስተኛ ስላልነበረ ወደ ቤት አልገባም አለ:: የዚህ ወንድሜ እና የማህበረ ቅዱሳን ዕጣ ፋንታ ከዚህ ሰነፍ ጋራ ነው በውጭ ነው ያሉት:: እግዚአብሔር የንስሃ ሕይወት ያስተምራቸው ይስጣቸውም! አሜን!!!


የዚህ ወንድሜና...እግዚያብሔር የንሰሃ ሕይወት ያስተምራቸው ይስጣቸው!አሜን!!! ላልከው እኔ የኔን አሜን ሁላችንንም ለንሰሀ ሕይወት ይስጠን ብያለሁ::ሰላነሳኸው ማኅበር ኢትዮጵያ እያለሁ አውቋቸዋለሁ::እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናቸው::እነሱን የተመለከተውን በአድራሻቸው ፈልገህ ንገራቸው እኔ ግን ከላይ ለጻፍካት ንግግር መስተካከል ያለበትን ብዬ ያሰብኩትን እነሆ ብያለሁ:-

ንስሀ ምንድን ነው?

ንሰሀ-ነስሐ ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ነው::የቃሉ ፍች ሐዘን ፀፀት ቁጭት ምላሽ መቀጮ ቅጣት ቀኖና የኃጢያት ካሳ ማለት ነው::(የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት):: አንድ ሰው ንሰሀ ገባ ሲባልም ዐዘነ: ተጠጠተ :ተመለሰ: ክፉ ዐመሉን ተወ: ጠባዩን ለወጠ: ማለት ነው::ንሰሐ ማለት ደግሞ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት : ባደረገው ስህተት : በፈጸመው ኃጢያት ማዘኑን መቆርቆሩን መፀፀቱን-ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢያት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው::

አንድ ሰው ንሰሀ ሲገባ በሰማይ ደስታ ይሆናል::ሉቃ15:6 ሰው ንሰሀ ሲገባ ቅር የሚለው ካለ ያ ሰው ክርስቲያን ነው ማለት አያስደፍርም::

ስለንስሀ ለጠቅላላ ግንዛቤ ባጭሩ ከዳሰስኩ :ወደሚቀጥለው ደግሞ ልሸጋገር::

በቤተ ክርስቲያን ስርሀት አንድ ሰው በአርባና በሰማኒያ ቀኑ ለቤዛ ቀን የታተመበትን የእግዚያሔር ቅዱስ መንፈስ ክዶ ሐይማኖቱን ከቀየረ(አይደለም ፓስተር ደረጃ የደረሰ የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ የተመለሰ ቢሆን) በእግዚያብሔር ላይ እንዳመነዘረ (ኤር3:6-10) ስለሚቆጠር በንሰሀ ቢመለስ ምእመን ሆኖ ከማንኛውም ምመን የሚጠበቅበትን እያደረገ ይኖራል እንጂ ወደ ክህነት ደረጃ አይደርስም::

የፓስተር መላኩ ጉዳይ ግን በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም::ሰሞኑን አንድ ጓደኛዬ ይህን ተመልከተው ብሎ የሰጠኝ DVD ላይ ስመለከት ብዙ ሌላ ጥያቄ የሚያስነሱ ነገሮችን ተመልክቻለሁ::በዲቨዲው ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት ፓስተር መላኩ በሚከተሉት ምክንያቶች ካህን ነው ማለት አንችልም
 1. በቤተ ክርስቲያን ስርኃት መሰረት አንድ ሰው ከተጠመቀ በኃላ ሐይማኖቱን ቢቀይር እና ከጊዜ በኃላ ንሰሀ ገብቶ ቢመለስ እንደማንኛውም ምመን የሚጠበቅበትን እየፈጸመ ይኖራል እንጂ ወደ ክህነት ማኅረግ አይደርስም::
 2. DVD ላይ እንደሚታየው ክህነት የሰጡት እራሳቸው ከንኳን ለሌላ ሰው ሊሰጡ እራሳቸውም እመቤታችን ጥንተ ኃብሶ(Orginal sin) አለባት ብለው በማስተማራቸው ከጵጵስና የተሻሩ በመሆናቸው እርሳቸው የሾሙት ፓስተር መላኩ በቤተክርስቲያን እንደማንኛውም ምመን እንጂ እንደ ካህን አይታይም::
 3. በንሰሀ ተመለስኩ ካለ በኃላ የቀድሞ ግብሩን ባለመተው:- እርሱ "ካህን" ተብሎ የሚገኝበት ቤተ ክርስቲያን(እኔ ቤተ ክርስቲያን ነው ማለት ይከብደኛል) በአለማችን ያለ ብቸኛ THE MOST WILD ነው::በአለማችን ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሌለ የቤተ ክርስቲያን ስርህት የሚጣስበት ቦታ ነው::ለምሳሌ አንድ ሁለቱን ልናገር:-
  • ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ህዝብ ጫማ ማውለቅ እንደ ኃላ ቀርነት ተቆጥሮ አድርጎ እንዲገባ ይበረታታል::እስከነጫማቸው የሚገቡ ቃላል አይደሉም
  • የመጨፈር አምሮታቸው ያልቆረጠላቸው ቤተ ክርስቲያን Night Club መስሏቸው የሚዚቃ መሳሪያ አስገብተው(እንደ ፒያኖ አይነቱን) ሲጨፍሩ ይታያሉ::የበግ ለምድ ለብሰው መድረኩ ላይ የቀሙት እነ ፓስተር መላኩ ይህ የቤተ ክርስቲያን ስርዐት ነው:: ሊሎቹ ፋራ ስለሆኑ ነው ይሉናል::
  ሌላም ብዙ መጥቀስ ይቻላል ጊዜ የለም እንጂ::ይህን ሁሉ ስናጠቃልለው በእውነት ይህ ሰው ንሰሐ ገብታል::ከገባ ታዲያ ከቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ስርዐት ውጭ ለምን ይፈጽማል?ያስፈጽማል? ፍርዱን ለእያንዳንዳችን በመተው እግዚያብሔር አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያስታግስልን በጸሎት እንበርታ እያልኩ የዛሬውን ጽሁፊን አበቃለሁ::


ይቆየን::
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

የድሬዳዋው ድብደባና ነፍሰ ግድያ

Postby ደብረታቦር » Thu Sep 08, 2005 8:50 am

ጤና ይስጥልኝ ወገኖቼ!

ወደ ዛሬው ትረካ ከመሄዴ ብፊት ለወንድሜ እንደምልስለት ፍቀዱልኝ:: ይገባኛል ከርዕሱ ፈቀቅ እንድል ነው ሙከራው:: እውነት ታስጨነቃለችና::
ስለ ንስሀ ማብራሪያው መልካም ነው ግን ከዕውቀት ብቻ ይመስላል ማስተዋል ይጨምርበት:: ብዙ ዶክተሮች ሲጃራ ማጨስ የሳምባ ነቀርሳ እንደሚያመጣ ጠንቅቀው ይውቃሉ ሆኖም ግን ይጨሳሉ ማስተዋሉ ስለተውሰዳባቸው:: ያንተ የወንድሜ ሕይወት እንደዛ እንዳይሆን ስጋቱ አለኝ::ክርስትና የሚኖሯት ሕይወት ነች እናም (walk the walk don't talk the talk)

ቀሲስ መላኩ ፓስተር ተብሎ ተሹምም አያውቅም እንዲህ ብለው የሚያወሩትም ማኅበረ አጋንንት ቡድን ነው የክስ ዲቪዲ የሚብትኑትም እነሱው ናቸው ልጅ አባቱን እንደሚከተል የከሳሹ የአባትቸውን የዲያብሎስን ስራ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ በመፈጸም ላይ ይገኛሉ:: ያው በህቡዕ ስለምንተቃሰቀሱ እንጂ ያው አንተም የነሱ እግረኛ ወታደር ነህ:: የቀሲስ መላኩ ሕይወት ውጣ ውረዱ በተመለከተ ቸኮልክብኝ እንጂ በደንብ ይተረካል::

ብጹእ አቡነ መልከጸዴቅ የተወገዙ ናቸው ብለሃል:: ማነው ያወገዛቸው? የትኛው ሲኖዶስ? ለምን? ዓለም አቀፋዊውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና ጥሰው በመንፈቅለ ሲኖዶስ መንበር ላይ ቁጭ ላይ ያሉት አቡነ ጳውሎስ? ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ቁ. 77-78 ""አንድ ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም"' እናም አቡነ መልከ ፄዴቅ ቀኖና ፈርሳል በኚህ ሰው የሚመራው ሲኖዶስ ቅድስናውን ያጣ ነው ስላሉ ሕገ ወጥ የተባለው ሲኖዶስ የሚያወጣው ውግዘት ወፈ ውግዘት ያባላል:: ይልቅ የኔና ያንተ ነገር መሆን ያለበት እነዚህ አባቶቸ በአስተዳደር ጉዳይ የተለያዩበትን ወደ አንድነት እንዲያምጣቸው በጸሎት መትጋት ያለውን ልዩነት ከማራገብ ይልቅ እንድ የሚሆኑበትን ነገር መፈለግ በአሁኑ ሰዓት የፖሊቲካ(የዓለሙ) መሪዎች እንካን ለህገራችን ብሔራዊ ዕርቅ እያለሙላት ነው:: በአባቶች መለያየት የተጠቀመው የጋለሞቶቹ ስብስብ የሆነው ማህበር "ቅዱሳን" አጋንንት ነው;;
ጥንተ አብሶን በተመለከተ አቡነ መልከ ጼዴቅ እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት ብለውም ጽፈውም አያውቁም:: ብለው ከሆነ በየትኛው መጽሀፋቸው በየትኛው ገጽ? ከ18 መጽሀፍ በላይ ጽፈዋል እስቲ መረጃህን? በሌላ በኩል ግን የጥንተ አብሶ ጉዳይ የቤተክርስቲናቸንን ሊቃውንት ሲይወዛግብ የኖረ ጉዳይ ነው:: በቅርቡ በዲሲ እና አካባቢው የሆንውን እስቲ ለአንባብያን ላስረዳ::
በካንሳስ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን እምቤታችንን ከአዳምዊ የሀጢያት ውርስ ነፃ ናት አይደለችም በሚል ውዝግብ ስለተፈጠረ በዲሲ አካባቢው የሚገኘው ማህበረ ካሀናት መፍትሄ እንዲሰጥ ይጠየቃል;; ማህበረ ካህናቱም ኅዳር 16, 1997 በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርሲቲያን ጉባኤ አድርጎ ውሳኔውን በአቡነ ይስሐቅ የማኅበሩ የበላይ ጠባቂ ፊርማ ሸኚነት ተያይዞ በታኅሣሥ 10, 1997 ወጪ የተድረገው ደብዳቤ በአጭሩ ፍሬ ሀሳቡ ከዚ እንድሚክተለውን ነው::

የጉባኤው አባላት
1. ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኃይሌ( ዲሲ ማርያም)
2. ቆሞስ አባ መዓዛ በየነ( ከዲሲ ገብሬል)
3. ሊ.ማ. ዶ/ር አማረ ካሣዬ (ዲሲ ማርያም)
4. መላአከ ብርሃን አስተአየ ጽጌ (ካንሳስ ኪዳነ ምህረት)
5.መጋቢ አእላፍ መክብብ አጥናው(ዲሲ ኪዳነ ምህረት)
6. አባ ሰረቀ ብርሃን ው/ሳሙኤል(ዲሲ ጊዮርጊስ)
7. ሊቀ ኅሩን ከፈለኝ ው/ጊኦርጊስ (ማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ በሰሜን አሜሪካ)

ለውሳኔ ማስረጃነት የቀረቡ መጻህፍት
1. ሃይማኖተ አበው
2.ትርጋሜ ወንጌል
3. መጻሕፍተ ቅዳሴ
4. ግብረ ሕማማት
5. የመላደ ብርሃንተ አድማስ ጀንበሬ መጻሕፍት
መድሎተ አሚን
ኩከሐ ሃይማኖት
6. የአለቃ አያሌው መጻህፍት
የኢትዮጳይ እምነት በሦስቱ ሕግጋት
ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ
7. ከፕሪስተን ዩኒቭርሲቲ የተገኘ የአቡነ ጳውሎስ መጽሀፍ (PHD thesis) NB ሊንክ ፔስት ማረግ ስላስቸገረን ነው የአቡነ ፓውሎስ ቴሲስ ፖስት ምረግ እችል ነበር::
8. የአራቱ እህት አብያተ ክርስቲያናት መጽህፍት ናቸው;; በነዚህ መረጃ መሰረት ጉባኤው "'አንጺሆ ሥጋሃ ኅደረ ላእሌሃ"" የሚለውን ቃል ተቀብሎ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኒቢብ የገቢርና የኅልዮ ኃጢይት ያልነበራትና የለለባት ናት ነገር ግን በአዳማዊ ዘር በኩል ከሚተላለፈው ውርስ መንፈስ ቅዱስ አንጽቶዋታል የሚለውን ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል:: እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ለምን እንደ ኢትዮጳያው misinformation minster በረከት እውንትን ማዛባት አስፈለገ? የወያኔ ታሪክ ምእራፍ ሲዘጋ የማህበር አጋጋንትም አብሮ ይፈጽማል;;

ወደ ትረካው ነገ እመለሳለሁ


ይትባረክ አምላክ አበዊነ


ወግኖቼ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Postby NATHRATHE » Thu Sep 08, 2005 7:06 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ደብረ ታቦር wrote:ብጹእ አቡነ መልከጸዴቅ የተወገዙ ናቸው ብለሃል :: ማነው ያወገዛቸው ? የትኛው ሲኖዶስ ? ለምን ? ዓለም አቀፋዊውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና ጥሰው በመንፈቅለ ሲኖዶስ መንበር ላይ ቁጭ ላይ ያሉት አቡነ ጳውሎስ ? ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ቁ . 77-78 ""አንድ ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም "' እናም አቡነ መልከ ፄዴቅ ቀኖና ፈርሳል በኚህ ሰው የሚመራው ሲኖዶስ ቅድስናውን ያጣ ነው ስላሉ ሕገ ወጥ የተባለው ሲኖዶስ የሚያወጣው ውግዘት ወፈ ውግዘት ያባላል ::


አንተው ማን አወገዛቸው ብለህ ጥይቀህ አንተው በፖለቲካ ምክንያት ነው ብለህ በምክንያት መወጋዛቸውን አምነአል::ዋናው ነጥቤ በምን ምክንያት ተወገዙ ብቻ ሳይሆን መወገዛቸውን መቀበልህ ነው::እኔ ከንዲወገዙ ምክንያት ከሆነው መካከል አንዱ እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት ብለው ማስተማራቸው እንደሆነ እርሳቸው ኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ በዚህ ጉዳይ ሊቃውንት ጉባዬ እንደተከሰሱና መልስ መተው ስጡ ሲባል አሻፈረኝ ብለው ወደ ውጭ ሀገር እንደመጡ በወቅቱ የሊቃውንት ጉባዬ ሰብሳቢ የነበሩት አባት በአንድ ካሴት ላይ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው የሰጡትን መልስ አይቻለሁ::

የተወገዙት በየትኛው ነው ብለህ ጠይቀኻል መልሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ነዋ ነው::ምን አልባት እዚህ አሜሪካ አንዳንድ ጳጳሳት ሲኖዶስ እኛ ነን ይላሉ ሲባል ሰምቻለሁ::ከእሱ ጋር Confuse ያደረገህ ይመስለኛል::ሰው ስለተሰደደ ሲኖዶስ ይሰደዳል የሚባል ነገር አልሰማሁም::አንተ የጠቀስከው ህገ ቤተ ክርስቲያን የሚለውም ፓትርያርክ እያለ ፓትሪያርክ አይሾምም እንጂ ፓትርያርኩ ከአቅም በላይ በሆነ በጠማ እመም ታምሚያለሁ ከአሁን በኃላ መስራት አልችልም ቢል በግድ እስክትሞት ድረስ ወንበሩ ላይ ቁጭ በል አይልም::ፓትሪያርክነት ከቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ ነው::ሰው በጠና ከታመመና ህመሙ መስራት አላስቻለኝም ብሎ ጥያቄ ካቀረበ ጥያቄው ተቀባይነት የማያገኝበት ምክንያት አይታየኝም::

እኔ የቀድሞው ፓትሪያርክ በጣም ከአቅሜ በላይ በሆነ ምክንያት ስለታመምኩ መስራት አልችልም ብለው ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ በመጻፋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቃቸውን ተቀብሎ ግዚያዊ ፓትሪያርክነት የዛኔ ምክትላቸውን የነበሩትን ብጹህ አብነ ዜናን ለተወሰነ ግዜ እንደመረጣቸውና እርሳቸውም ለተወሰነ ጊዜ(ከስድስ ወር በላይ ሳይሆን አይቀርም) ካከለገሉ በኃላ ጥቅላላ የሲኖዶስ ምርጫ ተደርጎ አሁን ያሉት እንደተመረጡ በወቅቱ በቤተ ክህነት አካባቢ ያገለግሉ የነበሩ አባት እንዴት በፓትሪያርክ ላይ ፓትርያርክ ይሾማል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ ሰምቻለሁ::እኔ እንደምገምተው ምርጫው በአብነ ዜና መሪነት መደረጉ ስርሀተ ቤተ ክርስቲያን መጣሱ አይታየኝም::ባይሆን ምርጫ በትክክል ተፈጽማል ወይ የሚለውን እርግጠኛ አይደለሁም::አባታችን ብጹህ ወቅዱስ አቡእ መርቆሮዮስ በእውነት በጠና ታመው ወይስ ሌላ ምክንያት ይኑረው ይህንንም እርግጠኛ አይደለሁም::እኔ ስገምት ምንም ፈተና ቢበዛ በጠና ቢታመሙም እንኳ ሀሳቡ ከሳቸው ካልመጣ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መፍቀድ የለባቸውም ባይ ነኝ::ሰው ላይ ለመፍረድ ሳይሆን አሁን ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል በፓትሪያርክ ላይ ፓትሪያርክ ተሾመ ብለው የሚረብሹ ሰዎች ስላሉ ነው::አንድ ግዜ እኔ ያለሁበት ደብር ተጋብዘው መተው ይህ ጥያቄ ተነስቶላቸው ልጆቼ የጋዛ ሰዎቼ ናቸው ሌላ ማንንም Blam አላደርግም ብለው ብዙም ማብራሪያ ሳይሰጡ ወደሌላ እርዕስ እንደገቡ ትዝ ይለኛል::እኔ ወዳለሁበት City አልፈው አልፈው ይመጣሉ አንድም ቀን እኔ በማይገባ መልኩ ነው የወረድኩት ሲሉ አልሰማሁም::እርሳቸው ዞር ሲሉ የሌለ ታሪክ የሚፈትሩ በሳቸው ስር ተደብቀው ሌላ አላማቸውን ለመፈጸም የሚራወጡ እነ አባ ሀብቴ ፓስተር መላኩ የሚያወሩትን ብዙ ባንሰማቸው ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ጥሩ ነው::እውነት ህገወጥ ሁኔታ ቢኖር እርሳቸው እራሳቸው በአንደኝነት ይቃሙት እኛም እንደግፋቸው ነበር::ቤተ ክርስቲያን ላይ እንክርዳድ ለመዝራት የሚራወጡትን ሰዎች ወሬ ግን አንሰማም::

ሌላው ስለ DC አካባቢ የሚገኙ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በካንሳስ ሲቲ አንዱ ቄስ እመቤታችን ጥንተ ሀብሶ አለባት በማለቱ ሌሎች አብረውት የሚያገለግሉ እንዲሁም ሰንበት ት/ቤቱ እና ህዝብ ስለተቃወሙት መፍትሄ እንዲሰጡ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ተጠይቀው የተሰጠውን ውሳኔ አልቀበለውም በማለቱ ይህንንም መፍትሄ እንዲፈልጉለት የዲሲ ካህናትን ስለጠየቃቸው እነሱ ይህን መወሰን እንደማይችሉና ይህን የወወሰን ስልጣን ላለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ መፍትሄ እንዲሰጥበት ወደ አዲስ አበባ ደብዳቤ ለመጻፍ ተስማምተው ደብዳቤ እንደጻፉ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቀው ነገር ካለ የጠየኩት አንድ ዲሲ አካባቢ የሚኖር ጋደኛዬ ነግሮኛል::በደንብ አላነበብኩትም እንጂ ካህናቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ የላኩትን ደብዳቤ FAX አድርጎልኛል::እንዴት መለጠፍ እንዳለብኝ ስላላወኩ ነው እንጂ የጻፉትን ደብዳቤ እዚህ እለጥፈው ነበር::

ይቆየን
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

ተነቃቅተናል ናቲ

Postby ደብረታቦር » Fri Sep 09, 2005 12:48 am

ብጹእ አቡነ መልኬ ጼዴቅ ተውገዙ የምትለው አንተ ነህ:: ለማንኛውም ለቃላት ጨዋታ ጊዜ የለኝም:: ጥሩ ወያኔ መሆንንህን ተረድቻለሁ:: የወያኔ መንግስት የተቃዋሚው ፓርቲዎች በስደት ላይ ከሚገኘው ህዝብ ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ስለተረዳ ይሄ ህዝብ ደግሞ በአብዛኛው ታቅፎ የሚገኘው በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ስለሆነ ይህን ህዝብ ለመክፋፈል ለሰይጣናዊ ተልእኮ ሁሌ ዝግጁ የሆነው ማህበር ቅዱሳን ክወያኔ ጋር ጋብቻ ፈጽመዋል:: በስደት ላይ የሚገኘውን ሲኖዶስ ላይ አንተ ያልክውን አሉባልታ የሚናፍሱት የጋለሞቱች ማህበር ነው:: ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ
አንተ ያልክውን ብለውም አያቁ ሊሉም አይችሉም:: አለዛም ለምን ሲኖዶሱን በአመት ሁለት ጊዜ ይሰበስቡታል? በወያኔ መንግስት የስኔ ልደታ ቀን በግፍ ለተጨፈጨፈው ህዝብ የተቃውሞ መግለጫ ህዝቡንም የሚያጽናና መልእክት ያወጣው በሳቸው የሚምራው የሊቀ ጳጳሳት ስብስብ(ሲኖዶስ) ነው:: የአቡነ ፓውሎስ አይደለም የሚግረመው ጸሎተ ፍታት እንካን አላኬሄዱም
በመጨረሻ ስለ ውግዘት ስደት በተምለከተ የቤተ ክርስትያን ታረክ መጻህፍትን ብታገላብጥ አይከፋም ካልሆነም ወደፊት እመልስብታለሁ:: እንድ አቡነ ጵውሎስ ምኞትማ አቡነ ዜና ማርቆስ አቡነ ኤልያስ አቡነ መልኬ ጼዴቅ አቡነ ይስሐቅ አቡነ ጎርጎርዮስ(ለንደን ያሉት) ሞተዋል ምክንያቱም በነሱ ስም እንደሞቱ ተቆጥረው ሌላ ጳጳስ በስማቸው ሾመዋል ተሞኙ የወያኔ መንግስት እንደሆነ ያልፋል ማለፉም ነው የእግዚአብሔርን መንግስት መከታ ቢያረጉ መልካም ነበር አልታደሉም ያንተና የማህበርህ የበረከት ስሞኦን አሉባልታ ምዕራፉ ይዘጋል ካንተ ጋራ የሚኖረኝ ውይይት በዚህ ተደመደመ:: የኢትዮጵያ ህዝብ ለተሸነፈ መንግስት አንገዛም በቃኝ እንዳለ እኔም ከአፍቃሬ ወያኔ ጋር አተካራ በቃኝ ወደ ትረካዬ እመለሳለሁ::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

የድሬዳዋ ድበደባና ነፍስ ግድያ

Postby ደብረታቦር » Fri Sep 09, 2005 10:52 am

ካለፈው የቀጠለ( በቀሲስ መላኩ)

በድሬዳዋ ያለው የሃይማኖተ አበው ቅርንጫፍ የተደራጀና በቁጥር በዛ ያሉ አባላት ያሉት ሲሆን ለቤተ ክርስቲያናቸው ቅናኢ የሆኑ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ናቸው:: በግል ጋዜጣ ላይ የወጣውን ጽሁፍ ተከትሎ ዋናው ጽሕፈት ቤት በመዘጋቱና የምኅበሩ ተቃዋሚዎች በየአቅጣጫው በሚያናፍሱት ወሬ አባላቱ በመደናገጣቸው አባላቱን ለማረጋጋት ቅርንጫፍ ማህበሩ ነሐሴ 21 ቀን 1986 ዓ.ም የእመቤታችን ዕለት ታላቅ ጉባኤ ለማድረግ አባላቶችን ጠራ::

ሁኔታው የማኅበሩን መበተን ለማየት የሚጠባበቁትን ስላናደዳቸው ጉባኤው እንዳይካሔድ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አቀረቡ:: በተለይም አቀራረባቸው የዛቻና የዱላ ስለነበረ የአስተዳደር ጽሕፈት ጥያቄያቸውን ውድቅ ከማድረጉም በላይ ጥያቄውን ባቀረቡት ግለሰቦች አማካይነት አንዳች ጉዳት ቢደርስ በኃላፊነት የሚጠየቁ እንደሆነ አስጠነቀቃቸው:: ሆኖም ማስጠንቀቂያውን ወደ ጎን በመተውና ጥቂት የዋህ ምእመናን ሃይማኖትህ ተወረረብህ በማለት እንዲሁም ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን በገንዘብ በመስጠት የኃይማኖተ አበው ተማሪዎች ማኅበር አባላት ወደ ተሰበሰቡበት አዳራሽ መጥተው አዳራሹን ከበቡት::
ዕለቱ የእመቤታችን ቀን ስለሆነ የጉባኤው መክፈቻ ""ወትቀውም ንግሥት በየማንከ ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች"" የሚለው ተሰብኮና ጸሎተ ወንጌል ደርሶ የዕለቱ መምህር የዕለቱን ወንጌል ማስትማር ሲጅምሩ ማኅበረ ቅዱሳን የቀጠራቸው ነፍሰ ገዳዮች አዳራሹን ውረሩት:: ዱላ ጩቤና ሌላም የጦር መሳሪያ ይዘው ስለ ነበረና በቁጥርም የሚበዙ ሰለ ነበሩ ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ:: በድብደባውም ነፍሰጡሮች የተጎዱ ሲሆን በተለይም ለመውለድ ሦስት ቀናት የቀራት ልጅ ""ስለ እመ ብርሃን ልወልድ ሳምንቴ ገብቷል"' ብላ ስትለምናቸው ክፉኛ ደብደበዋት ሆስፒታል ሄዳ በከፍተኛ ችግር ልጁ ወጣ:: ሦስት ልጆች አካለ ጎዶሎ የሆኑ ሲሆን አንድ ወንድማችንን ገደሉት:: በቦታው የነበረውንም ግምቱ መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የመንግስት ንብረት አጠፋ::
ይቀጥላል

ይትናረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

የድሬድዋ ነፍስ ግድያ በማ/ቅ

Postby ደብረታቦር » Sat Sep 10, 2005 9:33 am

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ወገኖቼ[/u]
ካለፈው የቀጠለ( በቀሲስ መላኩ)
ከሁሉ የሚገርመው በጊዜው ለጵጵስና እየተዘጋጁ የነበሩትና በስተኃላም የሐረርን ሰንበት ትምህርት ቤት ያዘጉት መምህር ብርሃነ ሥላሴ በኃላም እዚህ አሜሪካ ባሉት ታላቁ አባት በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ምትክ ዜና ማርቆስ የተባሉት በእነዚህ ልጆች ተንኮል ውስጥ መግባታቸው ነው::
በጊዚው የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ መርስኤ ኃዘን አበበ ለአቡነ ጳውሎስ ባቀረበው ሪፖርት ""የጸቡ ምክንያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር በማለት ራሳቸውን በመጥራታቸው በቤተክርስቲያን ስም መናፍቃን ሊነግዱ አይችሉም በሚል ነው"" ካለ በኃላ ሰለ ሃይማኖተ አበውም ሲናገር ""ራሱን ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር በማለት የሚጠራው አካል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት ውስጥ ባሉት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በቡድን ተደራጅተው ከቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት ውጭ እየንተንቀሳቀሱ በመገኘታቸው በተለያዩ ስንበት ትምህርት ቤቶች እንዲታገዱ ተልጧል"" ይላል:: ከሁሉ የሚያስቀው ደግሞ ማኅበሩ ስብሰባውን የጠራው ""የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር"" በሚል ስም ነው ማለቱ ነው::

ጋዜጠኛው መርስዔ ኃዘን አበበም ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ሀፍረት መሆኑን ዘንግቶት በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ለገዳዮቹ ሽልማት እንዲሰጥ አደረገ::

ይህ መቼም በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አዲስ ክስተት ነበር:: መግደል ንስሐ ያስገባል ያሳዝናል ከሹመት ያሽራል እንጂ አያሸልምም:: የወደምውን ንብረት እንዲከፍል ቤተ ክህነት ስለተጠየቀ ሀላፊነት ውስዶ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ አድርጎ ከፈለ:: በድሬዳዋ የነበሩትን ውጣቶች ቅስም ሰበረ:: በገዛ ወገናቸው የተደበደቡም በደም እንድጨቀዩ በዚያው አምርረው እንደወጡ ቀሩ::


በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ላይ የተጀመረው ዘመቻ

ማኅበረ ቅዱሳን ኃይማኖተ አበውን ካስዘጋና ድሬዳዋን ካስደበደበ በኃላ ማኅበረ ቅዱሳን መንገዴ ላይ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ ያላቸውና በአባልነት ወ እርሱ ጎራ ለመግባት እምቢ ያሉትን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ""ተሐድሶዎች"" ናቸው በማለት ስማቸውን በዝርዝር በጋዜጣ ላይ ማውጣት የጀመረው ውሎ ሳያድር ነው:: አገልጋዮች የሆኑ ካህናትንም ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ የየሀገሩ ስብደት ሥራ አስኪያጆችና ሊቃነ ጳጳሳትን መመውትወት ጀመረ:: በጥቂት ጊዜ ውስጥ ማንም የማያውቀውና እዚህ ግባ የማይባለውን በፕሮቴስታንቶች የተጀመረው ተሐድሶ ተብዬ እንቅስቃሴ ማኅበረ ቅዱሳን ለመላው እትዮጵያ ከማስተዋወቁም በላይ የየእለቱ መነጋገሪያ አደረገው:: በተለይም የማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች ጳጳሳቱም አሉበት በማለት መናገር ሰለ ጀመሩ ሕዝበ ክርስቲያኑ በሙሉ ጳጳሳት ሁሉ ያሉበት ይህ ተሐድሶ የሚሉት ምንድን ነው ማልት ጀመር::

ሁኔታው በኦርቶዶክሳዊትቤ/ክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታይ ሁኔታ በ""ጫካ ሕግ"" የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የተረገጡበት በአላዊቂዎች የተዋረዱበት ነው:: ማኅበረ ቅዱሳን በነዚያ ውቅቶች ያከናወናቸው ድርጊቶች ሁለት ወቅቶችን ያስታውሰኛል:: አንደኛው ቁስጥንጥንያ ውስጥ የተደረገን ነገር ሲሆን ሌላው ካምቦዲያ ውስጥ የተደረገ ነው::
ጊዜው እግዚአብሔር ያስነሳው ታላቁ ፓትርያርክና የሰባክያን መስፍን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መላዋን ቁስጥንጥንያን በትምህርቱ ይገስጽ ይመክር የነበረበት ወቅት ነው:: ትምህርቱ የቁስጥንጥንያ ቤትመንግስት ስዎች ቢጎረብጣቸውም የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የትምህርት ጸዳል ያገለላቸውን ጥቂት ወሮበሎች አስነሡበት:: ከእስክንድርያ ደግሞ የሥልጣን ጥም ያናውዛቸውን ስዎች አመጡበት:: ሌላው ቀርቶ መናፍቃንን በትምህርቱ ይመክት የነበረውን ኤጲፋንዮስን እስኪያሳስቱ ድረስ ""ዮሐንስ አፈወርቅ መናፍቅ ሆናል ድረስልን"" ብለው አመጡት::

ይቀጥላል

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ካለፈው የቀጠለ

Postby ደብረታቦር » Sun Sep 11, 2005 9:41 am

እንካን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ! አዲሱ የስላም የደስታ የፍቅር ያድርግልን:: አገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ እንዲጎበኛት ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን::
ካለፈው የቀጠለ

ቅዱስ ኤጲፈንዮስ ግን ነገሩን አይቶ ቀስ ብሎ ወ ሀገሩ ቆፕሮስ ሲመለስ መንገድ ላይ አረፈ:: ሌሎቹ ግን ያን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ዓይን መናፍቅ ነው ብለው ፈረዱበት:: ከገዛ መንበሩ አጋዙት አንገላቱት በስደት ሳለም ከሕመምና ከእንግልት የተነሳ አረፈ:: የሚገርመው ግን መናፍቅ ነው ብለው የፈረዱበትና ያወገዙት ቤተክርስቲያኒቱን የማያውቁ ጊዜ ያነሳቸው ውሮበሎች መሆናቸው ነው:: አለማወቅ አዋቂነት የሆነበት አዋቂነት ወንጀል የሆነበት ዘመን ነበርና::

ሌላው በዘመናችን የተደረገ ነው:: በካማቦዲያ ውስጥ ኬሚን ሩዥ የተባለው ኮሚኒስታዊ ድርጅት ሥልጣኑን ይዞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የገዛ ውገኖቹን በገደለበት ወቅት ነው:: በዚያ ወቅት በሀገሪቱ እየተፈለጉና እየታደኑ ይገደሉ የነበሩት አሉ የሚባሉት የሀገሪቱ ምሑራን ነበሩ:: በዚያ ወቅት በካምቦዲያ መማር ወንጀል ነበር:: ለመማር መጣጣር የሚያስቀጣ ነበር:: የነሞዛርትን ረቂቅ ሙዚቃ ያሰማምሩ የነበሩ እጆች የምዕራብውያንን ባሕል ልታመጡ ነው ተብለው ተቆረጡ:: የታረክ መዛግብትን የሚመረምሩ ዓይኖች በአብዮቱ ላይ ታሴራላችሁ ተብለው እንዲጠፉ ተደረጉ:: ሊቃውንቱ በቁማቸው ተቀበሩ ገደል ተወረሩ:: ሊቃውንቱ በቁማቸው ተቀበሩ ገደል ትወረሩ:: ማወቅ ወንጀል ይሆነበት ውቅት ነበርና::
ያ ጊዜ ተምልሶ የመጣ የመሰለበት ወቅት አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን አምጥቶልናል:: ሊቃውንቱን በመጀመሪያ የመናፍቅነት ጥላሸት ሊቃውንቱን በመጀመሪያ የመናፍቅነት ጥላሸት ማስቀባት ቢቻል የሆነ የሚከሰስበት ነገር መፈለግ ቤተክርስቲያን መናፍቅ ትበለውም አትበለውም በእነርሱ ጥቁር መዝገብ መናፍቅ እንደሆነ ማወጅ ማሳደምና እንዲባረር ማድረግ:: ከሳሽ ማኅበረ ቅዱሳን ምስክር ማኅበረ ቅዱሳን ፈራጅ ማኅበረ ቅዱሳን ሕግ አስፈጻሚ ማኅበረ ቅዱሳን:: ለዚህ አስዛኝ ሁኔታ ምሳሌ ምሳሌ የሚሆነን በአንድ ወቅት ማኅበሩ በሚያወጣው ጋዜጣ ላይ የከፍተኛ የቴዎሎጂ ኮሌጅን ከምክትል ዲኑ ጀምሮ የኮሌጁን ዋና ጸሐፊ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግዕዝ መምሕር በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግእዝ መምህር በኮሌጁ የቤተክርስቲያን ታሪክ መምህር የኮሌጁን ሥራ መሪና የእንግሊዝኛ መምህር እና ስድስት ተማሪዎችና ጨምሮ ተሐድሶዎች ናቸው ብሎ አውጥቷል:: ይህም የኮሌጁን ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ወደ ቅድስት ሥላሴ የተዛወሩ ሦስት አስተማሪዎች ተሐድሶ ማለቱን ሳይጨምር ነው::ይህ ጸሐፊ እስከሚያታውሰው ኮሌጁ ያሉት አስተማሪዎችከስምንት እስከ አሥር ቢሆኑ ነው::ስለሆነም በማኅበረ ቅዱሳን ሚዛን ኮሌጁ ካሉት አስተማሪዎች ዘጠና በመቶዎች መናፍቃን ነበሩ ማለት ነው::
ይህን ታሪክ ስጽፍ በስሜታዊነት ቢሆን አትፈረዱብኝ::ልቤ እየደማ ነውና የምጽፈው:: ወደማን አቤት ይባላል? ወደ ማንስ ይኬዳል? እግዚአብሔር እንዲፈርድ ከመጥራት ሌላ ማን ይባላል?
ይቀጥላል
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 4 guests