ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳንና ሀይማኖተ አበው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ይቅርታ

Postby ደብረታቦር » Sat Oct 29, 2005 6:39 pm

ወድ አንባቢያን!

ጊዜ በማጣት ምክንያት ነው የጠፋሁት! ወደ ትረካ የመጨረሻ ክፍል እመለሳለሁ! ቀሲስ እንዴት ወደ ቤ/ክስርቲያን እንደተመለሰ::
ከትትና ጋራ የጀመርነው የመማማር ውይይትም ይቀጥላል::
ከይቅርታ ጋራ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Postby ermiasabe » Sun Oct 30, 2005 6:34 pm

ውድ ዲጎኔ

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያየ አምዶች ላይ የምትፅፈውን እየታዘብኩ ሳልፍ መመፃደቅህ ቢበዛብኝና በቅን ልብ እግዚአብሄርን የሚያገለግሉትን ሁሉ በኑፋቄህ ለማሰናከል የማትተኛ መሆንህን ባይ የፃፍኩትን እንድፅፍ ተገደድኩ እንጂ የካድሬው ጳውሎስም ይሁን የሌላ ማህበር አንጋች አይደለሁም:: እንግዲህ ተገድጄ ከገባሁበት አንድ ነገር እንድጠይቅህ ፍቀድልኝ:: ለመሆኑ የምታምናቸውነንና የማታምናቸውን ነገሮች ለይተህ አውቀሃልን? አልመሰለኝም! በየጊዜው ሳይህ ሃሳብህን የምትቀያይር ከመሆንህ ሌላ (ስለ እመቤታችን ፀሎት ያልከውን አስታውስ) ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጋር ያለህ ችግር ምን እንደሆነ እንኳን ለይተህ መናገር አልቻልክም:: ሲልህ "አስተዳደሩ አስመርሮኝ ነው የወጣሁት" ትላለህ:: ስትፈልግ ደግሞ "ቤተክርስቲያኒቷ ሰው አምላኪ ነች" ትላለህ:: ትዲያ በየቱ ልቀበልህ?

ሌላው የሚያስደንቀኝ ነገር ከላይ እንዳልኩህ ተመፃዳቂነትህ ነው:: ለነገሩ የጵንጠጣው አባዜ የያዛችሁ ሁሉ በዚህ የተለከፋችሁ ብትሆኑም ያንተው ደግሞ በዛብኝ:: "የክርስቶስ ባሪያ" ነኝ እያልክ እራስህን የምታንቆለጳጵስ ሰው "ተው ተሳስተሃል ተመለስ" የሚሉህን ሁሉ "በቃሉ እንሞካከር" እያልክ የትዕቢት አባት የሆነው ዲያብሎስ በቀደደልህ ጎዳና ገፍተህ ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለህ:: ከሁሉ ደግሞ የሚገርመው ሌሎች ሰደቡኝ እያልክ ለማሳጣትና ሰብዕናቸውን ለማኮሰስ ስትሞክር አንተው የስድብ ምንጭ መሆንህ ተጋለጠ:: ተምሬ ጠንቅቄዋለሁ በምትለው የሃይማኖት ጉዳይ ደግሞ ብትፀና መልካም ነበር ወደ ፖለቲካውም መስክ ገብተህ አይመስሉኝም የምትላቸውን ታብጠለጥላለህ:: ሌላው ቢቀር ግን ግጥሙ ይቅርብህ:: ያንተ አይነቱ አገጣጠም ፀያፍ መሆኑን ድሮ አንደኛ ደረጃ ሲያስተምሩን ትዝ ይለኛል::

ያለ አንድ ቀን ሃሳብ ያልሰነዘርኩትን ሰው በማታውቀው ገብተህ የማህበረ ቅዱሳን አባል ነው ብለህ ትወነጅለኛለህ:: ችግሩ ሃሳብ የሌላቸው ሰዎች ዋነኛው ስልታቸው ታርጋ መለጠፍ ነው:: ምናልባት ግን ቢረዳህ ብዬ "ማህበራት" ስለሚባሉት አስተያየቴን ልስጥህ:: እኔ እነዚህ አንተና መሰሎችህ "ጉባኤ" "ማህበር"፣ "ኮንፈረንስ" ወዘተ እያላችሁ የዋሃንን ለማታለል የምትቀፅሏቸውን ቅፅሎች ሁሉ "cult" ብዬ ነው የምጠራቸው:: ለምን ብትለኝ ክርስቶስን ሳይሆን ግለሰብን ወይም የተወሰኑ ግለሰቦችን ማዕከል አድርገው የሚመሰረቱ በመሆናቸው ፍፃሜአቸው መሪው ሲከዳ አብሮ መክዳት መሪው ሲጰነጥጥ አብሮ መጰንጥጥ በመሆኑ ነው:: ለዚህ ምስክር ሌላ ማንንም ሳይሆን አንተኑ በራስህ ቃል ምስክር አደርጋለሁ:: የሃይማኖተ አበው አባል ነበርኩ የምትል ግለሰብ የመሪዎቹ ትክክለኛ ማንነት ሲገለጥ "እኔ የማምነው ክርስቶስን እንጂ ሰውን አይደለም" ብለህ በቤተክርስቲያን ደጅ መቅረት ሲገባህ "አይ እከሌማ ከወጣ እኔም አብሬ ልኮብልል" ብለህ የመናፍቃን ዋሻ ውስጥ ገብተህ ትዋኛለህ:: አሳዛኙ ነገር ደግሞ አሁንም የምትመካው ይህንን ወይም ያንን ግለሰብ በማወቅህ ነው:: ለዚህም ምስክሩ በየፅሁፍህ የሰዎች ስም መጥቀስ ማብዛትህ ነው (ፈረንጆቹ "name-dropping" እንደሚሉት)::

ሌላው በተደጋጋሚ ከምትፅፈው ያሳዘነኝ ለኢትዮጵያውያን ያለህ አመለካከት ነው:: ላንተ የኢትዮጵያ የሆነው ሁሉ የሚጣል የፈረንጅ የሆነው ሁሉ ቅዱስ ነው:: አቡነ ተ/ሃይማኖት "በፖለቲካ ጉዳይ ገብቶ ይፈተፍት የነበረ መሰሪ" ሲሆኑ ሉተር ግን "ገነት እንደገባ ጥርጣሬ የሌለው" ቅዱስ ነው:: በኢትዮጵያዊነትህ ማፈርህ ቢያሳዝነኝም ግን አይገርመኝም ምክንያቱም በደሃ እናቱ የሚኮራ ጥቂት በመሆኑ:: ግን ምናልባት አታውቅ እንደሁ ላንተ ብፁዕ ወቅዱስ የሆነው ሉተር የእርሱን ድጋፍ ተማምነው በመንግስት ላይ የተነሱትን ምስኪን ገበሬዎች ለመንግስት አሳልፎ በመስጠት በሺዎች ያስጨረሰ አረመኔ ነው:: እንዲያውም የክርስቶስን የእኩልነት ትምህርት ክዶ "worldly kingdom cannot exist without inequality of persons" የሚል ሰይጣናዊ አስተምህሮውን ለማስረፅ የሞከረ ከሃዲ ነው:: ከዚህ የከፋው ደግሞ "On the Jews and their lies" ብሎ ያሳተመውና ያሰራጨው ትክክለኛ የሂትለር አባትነቱን ያስመሰከረበት መፅሃፍ ነው:: ስለነዚህ ጉዳዮች መመርመር ከሻትክ የሚከተሉትን ድህረገፆች ተመልከት::
http://www.britannica.com/eb/article-59863?hook=360728
http://www.zum.de/whkmla/military/16cen ... 41525.html
http://www.humanitas-international.org/ ... r-jews.htm
http://www.nobeliefs.com/luther.htm
ግብረ ሰዶምና የሴት ቀሳውስት መቀበሉን ግን እንደነፍስ አባታችሁ አባ ሀና እና የተፈራ በለው ግጥምጥም ስምም እናንተው ቀጥሉበት እንጂ እኛ አሁንም እንደጌታችን የሀጢአተኛው ወዳጅ የሀጥያትና የደብተራ ባለውቃቢ መናፍስትግን ጸር ነን ::
ላልከው በቀላሉ መልሴ እዛው ያለህበት ቦታ መሰሎችህን ፈረንጆች ተመልከት ይሆናል:: የምታወድሳት የሉተር ቤተአምልኮ ይህንን ስትከለክል አላየንም አልሰማንም:: እንዲያውም መስራቿ ሉተር ባፀደቀላት የሁሉም እንዳሻው ይተርጉም ትምህርት ተጠቅማ የግብረ ሰዶምንና የሴቶች ክህነትን ትክክለኛነት በቅዱሳት መፅሃፍት ለማስረገጥ እየሞከረች እንደሆነ ነው የማውቀው:: እናንተስ ዛሬ ብትምሉ ብትገዘቱ ማን ያምናችኃል? ዋናው ጥያቄያችሁ ቀሊሉ የክርስቶስ መንገድ "ከበደን" እስከሆነ ድረስ ነገ ስጋችሁን ማሸነፍ ሲሳናችሁ እነዚህንስ እንደ ፅድቅ ትምህርት እንደማታቀርቡልን በምን እንመን? እንዲህ ስልህ ስጋዬን አስገዝቻለሁ ብዬ እንዳንተ ልታበይ እንዳይመስልህ:: ይልቅስ እኔ አለም ስትበረታብኝ "አልቻልኩም እርዳኝ" እያልኩ ስጋና ነፍስን አስተባብሮ የሚገዛ አምላኬን በፀሎት እጠይቃለሁ እንጂ እንዳንተና መሰሎችህ "ተዋህዶ ሰው አምላኪ ቀንበር አጥባቂ ነች" ብዬ ወደ ነጣቂ ተኩላ ዋሻ አልሄድም::
በመጨረሻ ግን አንድ ያልተረዳሁት ነገር ስላለ ልጠይቅህ እፈልጋለሁ:: እውን በውጭው አለም የምትኖር ከሆነ እንዴት ጊዜ ቢተርፍህ ነው እባክህ በየአምዱ ለመፃፍ የበቃኸው? እባክህ ሥራ መፍታት አገራችንንም አልጠቀማት:: የምታምነውን እያመንክ ሥራህን ሥራ:: ክህነትም እንዳለህ ስብከትህን ቤተአምልኮህ ውስጥ አድርገው:: በዛውስ ላይ አባቶቻችን "አስተምረኝ ሳይሉት ላስተምር የሚል እንደተሳዳቢ ይቆጠራል" ይሉ የለ::
ሰላም ሰንብት
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

የማርቲን ሉተር ድንቅ ጥቅስ

Postby ermiasabe » Sun Oct 30, 2005 7:38 pm

He who loves not wine, woman and song, remains a fool his whole life long.
ወይንን፣ ሴትንና ዘፈን ያልወደደ በእድሜው ቀለደ።
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

በጽሁፍ ያለ ይታወሳል በቃል የሆነው ግን ይረሳል

Postby ዲጎኔ » Sun Oct 30, 2005 7:41 pm

[

ወዳጄ ልቤ ermiasabe

እኔ ከምጽፍ የጻፍከውን እንዳለ አቅርቤአለሁ::
የቀጥለው ርእስ አግባብ ያለው ተሀድሶ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ያስፈልጋት በሚል ሲሆን በተሀድሶው አይነት ከአምዱ ከፋች ጋር የምንስማማበትም የማንስማማበት ቢኖርም በሀሳብ መለዋወጥ መብትና ሀላፊነታችን ያመነውን መጻፍ በአንተ የሚያስነቅፈኝ አልነበረም:እንደምትከሰኝም አይደለሁም::

በተረፈ ጊዜ ወስጄ ስለእምነቴም ሆነ ስለሀገሬ የምጽፈው ለመማርና ለመማማር ነው :ሉተርም ሆነ ማንም ሰው በቅዱስ መጽሀፍ ከተጻፈው የሚጻረር ቢያስተምር አልቀበልም:የሀግሬ ልጅ ባህሌ ብዬም ጽድቅ የሌለበትን ከክርስቶስ እንደሚለይ በተረዳሁት ነገር ላይ የግል ውሳኔ መስጠት መብቴ ነው::

በተረፈ እኔ ጭንጋፉ ብቻውን ያለውን አዳኜንና ጌታዬን ክርስቶስን የምከተል ደካማ ፍጥረት እንጊ ከክርስቶስ መስቀል በቀርአንዳች ትምክህት የሌለኝ ነኝ

ክርስቶስ ጌታ እውነተኛውን የልብ መታደስ ይስጠን!

ያለክርስቶስ የማልረባው ዲጎኔ ከተሀድሶ አምባ

quote="ermiasabe"]ውድ ትትና

አንቺ እንዳልሽው የእግዚአብሄር መንግስት የምትውረስ በትህትናና በየዋሃት እንጂ እንደነ ዲጎኔ አይነት ተመፃዳቂዎች እንደሚያስቡት በፍልስፍና አይደለም:: እነዚህ ግለሰቦች ወደ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ፀጉር ስንጠቃ ገብተው ቤተክርስቲያንን ወደ ጥፋት ህዝቡን ወደ መበተን የሚመሩ ሆነዋል:: Stoics ይባሉ እንደነበሩ ፈላስፎች ነገርን ሁሉ በአመክንዮ እንመራዋለን ስላሉ የክርስቶስን መንገድ ስተውታል:: ቤተክርስቲያንን አሜሪካ ባዩአቸው ቤተአምልኮቶች አይነት ሊያደራጁ ነው ትጋታቸው:: በቅርቡ "ለሴቶች ክህነት ብንሰጥ ግብረ ሰዶማውያንንስ ብናጋባ ምን እለበት' እንደሚሉ አትጠርጥሪ::[/quote]
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ermiasabe » Sun Oct 30, 2005 11:22 pm

ውድ ዲጎኔ

እኔ ያንተንም ሆነ የሌሎችን መብት የመጋፋት ሥልጣኑም ፍላጎቱም የለኝም። እስካሁንም እከታተል የነበረውም እንደው ምናልባት የሚያንፀኝ አንድ ነገር እንኳን ከወገኖቼ አገኝ ይሆናል በሚል ነው። ጉዳዩ ግን አንድም የግለሰብ ገድል ሲልም ቤተክርስቲያንን የግላቸው መጠቀሚያ ያረጉ ፈሪሳውያን ግብግብ ዘገባ ስለሆነብኝ ትረካው ባያልቅም እኔው መከታተሌን ለማቆም ወስኛለሁ። ባይሆን በግል ሳላውቅህ በፅሁፌ ላስቀየምኩህ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ቅን ፈራጅ የሆነ ክርስቶስ ሁላችንንም መተላለፋችንን ሳይቆጥር በቸርነቱ የመንግስቱ ወራሽ ለመሆን ያብቃን። አሜን።

ውድ ደብረታቦር
ምንም እንኳን በግል ባላውቅህ ከፅሁፍህ የእግዚብሄር እና የቤቱ ፍቅር እንደሚያቃጥልህ አያለሁ። ነገር ግን ድፍረት ባይሆንብኝ አንድ ሃሳብ እንድሰጥህ ፍቀድልኝ። በቅድሚያ ይሄ የግል ወንድማዊ አስተያየቴ እንጂ ለማንም ለምንም ተቆርቁሬ የምሰጠው እንዳልሆነ እወቅልኝ። ይልቁንም በቤተክርስቲያናችን አስተዳደራዊ ለውጥ አስፈላጊ ነው ብለው ከሚያምኑ ሰዎች አንዱ መሆኔን ልገልፅልህ እወዳለሁ።
ስገምተው ታሪካችውን የምታትትላቸውን ግለሰብ በቅርብ ታውቃቸዋለህ፤ ለዚህም ይመስለኛል በጥብቅ የምትከራከርላቸው። እኔ በግሌ ስለግለሰቡም ሆነ ስለተነሱት ድርጅቶች በስም ካልሆነ በቀር አንድም የማውቀው ነገር ባይኖረኝም ትንሽ ታሪኩ ላይ ግን ቀዳዳዎችን (loop holes) ለማየት ችያለሁ። ትክክል ልሆንም ላልሆንም ብችል እዚህ አላነሳውም፤ ነገር ላለማራዘም። ነገር ግን ላንተ ልልህ የምፈልገው ነገር እሰቲ ለተወሰነ ጊዜ ከግለሰቡ ወይም ከሚመሩት ማህበር እራስህን ለይና እግዚአብሄርን በግልህም ይሁን በቤተክርስቲያን ለማገልገል ሞክር። ብዙ ጊዜ ለአንድ አስተሳሰብ ብቻ መጋለጥ አደገኛ ነገር ነው። የ Group mentality ታዳብርና የዛ አመለካከት ብቻ አንፀባራቂ ትሆናለህ። ይህ ሲሆን ደግሞ የሰዎች ስህተት ጎልቶ አይታየንም። ስለዚህም እያንዳንዱን ነገር በግልህ በተዋህዶአዊ መነፅር ለመገምገም ሞክር። እንዲህ አርገህ ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ከቻልክ እውነትም ምስክርነትህ ይገባቸዋል። ካልሆነም ካንተ የደበቁትን ማንነታቸውን ትረዳለህ። ዋናው መልዕክቴ ሰዎችን ትተን እግዚአብሄርን ብቻ እንያዝ እላለሁ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣ እኔ የአጵሎስ ነኝ” አትበሉ እንዳለ።
እግዚአብሄር የክብሩ ወራሾች፣ የስሙ ቀዳሾች ለመሆን ያብቃን። አሜን።
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

Postby ደብረታቦር » Mon Dec 19, 2005 7:46 am

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!

በሰሞኑ ህገራችን መከራ ምክንያት ተከታታይ ትረካዬን ወቅታዊ አይሆንም ብዬ ብማመን አቁሜው ነበር:: ከእንግዲህ ይቀጥላል:: ለማንኛውም እስቲ ማህበረ ቅዱሳን በየቦታው እየተጋለጠ መሆኑን የሚሳይ አንድ ሊንክ ልስጣችሁ
http://www.ethioview.com/images/occasio ... 5B1%5D.pdf[/u][/url]
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ሌላ የሚሰራ ሊንክ

Postby ደብረታቦር » Mon Dec 19, 2005 9:29 am

ይቅርታ ያለፈው ሊንክ ጥሩ አይደለም ይህንን ሞክሩ

http://www.ethiomedia.com/fastpress/menfesawi_kaba.pdf
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ድንቅ ሪፖርት

Postby ደብረታቦር » Fri Jan 20, 2006 5:02 pm

ውድ ወገኖቼ!

በቅርቡ በሕዝብ ብሶት የተወለደው የንጋት ሬድዮ የወያኔው ንስሐ አባት የታጋዩ ጳውሎስ እና የካድሬዎቻቸው የማህበረ ቅዱሳንን በውጭ አገር ባሉት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የዘረጉትን ስውር ደባ አጋለጠ:: ሁላችንም ማዳመጥ የሚገባን ፕሮግራም ነው::
http://ethio.info/downloads/negat_radio.wmv
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests