ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳንና ሀይማኖተ አበው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ወዳጄ ልቤ ደብረታቦር ይህውልህ ወንድም አለም የእኔንም ልብ ያደማ የነበረውን ተጋራህኝ

Postby ዲጎኔ » Mon Sep 12, 2005 4:12 am

እንኩዋን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን::
እጅግ የተከበርክ ወንድሜ ደብረ ታቦር እስከአሁን ድረስ በትክክል ያስቀመጥካቸውን የተሀድሶ ትረካዎች በአድናቆትና በመመሰጥ ከሚኮመኩሙት አንዱ መሆኔን ተረዳልኝ :በተለይም ደግሞ በእግዚአብሄር ቤት በሚሰራው ሸፍጥ የልቤን መድማት በመጋራትህ አሁን የልቤን ብሶት ስለተረዳህልኝ ጌታ ይባረክ!

በቀጠለው እውነተኛ ትረካህ ከማሳረጊያህ በሁአላ የምለው ቢኖረኝም ይህ ወንድማችን ቀሲስ መላኩን ለማስታወስ እንዲረዳኝ ተጭማሪ ማብራሪያ እፈልጋለሁ::በሀረር በአንድ በኩል ከአጋንንቱ ማህበር ከማህበረ ቅዱሳን በውጭ ከአሸባሪው IFLO ጋር ሲፋለሙ ከነበሩት ወገኖቼ ጋር ስለነበረኝ ጥቂቷ ትዋጽኦ ጌታ ቢፈቅድ የእኔን ሳይሆን የእኒያን የክርስቶስ የወንጌል አርበኞች ገድል የምዘግብበት ዘመን እንዲመጣ ተስፋ አደርጋለሁ::

በሀረር የነበሩት ቅዱሳን በተለይ በሂርና በገለምሶ በጅጅጋና በድሬደዋ በሚገባ የማውቃቸው ሲሆን በተለይ የሀረሩ ማህበረ ተዋህዶ የመዝሙር ካሴቶቹን በማሰራጨት ያንን የሰደታቸውን ዘመን ልጋራ በመቻሌ ደስ ይለኛል:ስለዚህም ቀሲስ መላኩ ከዚያው ከሀረር ከነበሩት ወገኖች ከሆነ በትክክልም እኔ የማውቀው የኢትዮጵያ መርዶኪዎስ እለዋለሁ

ስለተጠቀሱት ምንደኞችም ያው በህዝባችን ዘንድ በደንብ እንደሚታወቀው በንጉሱ ዘመን አባ ሀና በደርግ ዘመንም አበባው ይግዛው አሁን በወያኔ ደግሞ የመርስኤሀዘን አበበና ታደሰ ውቤን ጉድ በቅርብ ከሚያውቁት አንዱ ስለሆንክ ጌታ ቤቱን ያጥራ ከማለት በቀር ምን እላለሁ::
በተለይ መርስኤሀዘን አበበ ከድሮውም በጨነገፈ የጋዜጠኛ ሙያው እኩይ ተግባር ፈጻሚ እነጳውሎስ ኞኞን የመሰሉትን ከሳሽና አስወጊ ሲሆን ላስቴ ወገኖቼንም የማህበራቸው መሪ ነኝ በማለት እጅግ ደባ የፈጸመባቸው ሲሆን በዚህችው መከረኛ ቤተክርስቲያን ሰርጎ በመግባት የፈጸመውን የማበጣበጥና የማጋደል ወንጀል በተለይም በድሬደዋ የምክር ቤት አዳራሽ የሀይማኖት አበውን ጉባኤ ላይ ስለፈጸመው በህግ የሚጠየቅበት ዘመን ሩቅ አይሆንም

ሌላው የቅድስት ቤተክርስቲያን ምንደኛ ዋሾ በግሌ የኤለመንታሪ የአማርኛ የቀለም አስተማሪዬ የነበረውና አንዳችም መንፈሳዊ ትምህርት ሳይወስድ ድሮ ለነንብረኡድ ኤርሚያስ ከበደ እጅ መንሻ በማቅረብ ከቤተክርስቲያን ሀላፊነት ቦታ የተቆናጠጠው ታደስ ውቤ ባህታዊ ፈቃደ በአባ ተጋዳላይ ጳውሎስ ቦዲጋርዶች በጥይት በተረሸኑበት ወቅት የሰጠው መግለጫ እጅግ ከሀዲነቱን አሳይቷል

ለሀገሬ ኢትዮጵያ የተዜመውም ለቅድስት ቤተክርስቲያኗ ተዚሟል

እምዬ ኦርቶዶክስ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ ያዋረደሽ በላ

ስለዚህ አሁን የባለውቃቢያንና የአባተጋዳላይ ጳውሎስ የጆሮ ጠቢዎችና ምንደኞችን ሳይሆን በእውነት ለቅድስት ቤተክርስቲያን የተገፉትን እውነተኛ ምስክርነት የምንሰማበት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ እጸልያለሁ::
ዲጎኔ ነኝ ከጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተሀድሶ ማህበር
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ቤ/ክን አትናወጥም

Postby ማየት መልካም » Tue Sep 13, 2005 8:34 am

በመድሐኔአለም ክርስቶስ ቤዛነት የታነፀችው ቅድስት ቤ/ክን ፈተናዋ ብዙ ቢሆንም ሁሉንም መከራዋን አሳልፋ እንደወርቅ ተፈትነው ያለፉትን ልጆችዋን ለድል አድራጊውን ጌታ የምታስረክብበት ጊዜ ቶሎ እንዲመጣ እሰልያለሁ::
በመቀጠል የምሰጠው አስተያየት
1. ማህበረ ቅዱሳን :- የፖለቲካ አጀንዳ የሌለው ማህበር ነው: በአሁኑ ሰአት በህገር ውስጥም ሆነ በሌሎች ቦታዎች እየሰራ ያለው ቤ/ክን የምትስፋፋበትን የተለያዩ መንገዶች በመምረጥ ለምሳሌም ትምህርተ ወንጌል በማስተማር: ሥርአተ ቤ/ክንን የተከተሉ የተለያዩ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን በመዘመር: በተለያየ ምክንያት የተጎዱ ገዳማትና አድባራትን በማጠናከር ራሳቸውን ችለው የሚቆሙብትን የልማት ስራዋች በመስራት: ተረስተውና ተዘንግተው ያሉ ወይም በአቅም ማነስ እንክብካቤ በማጣት እየተጎዱ ያሉ ታሪካዊ ቅርሶችን የሚጠበቁበትን ስራና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎትን እየፈስመ ያለ የቤ/ክን ልጆችን ያቀፈ ማህበር ነው::
2.ሌላው ወያኔ በቤ/ክን ውስጥ እጁን በማስገባቱ ምክንያትና በውቅቱም ቤ/ንን ይመሩ የነበሩት አባቶች ህብረት በማጣታቸውና ፈተናውን መከላከል ባለመፈለጋቸው በደርግ የተፈጸመው ጥፋት ተደገመ::በዚህም ይቅርታ ይደረግልኝና ሁሉም አባቶቻችን ጥፋት ፈጽመዋል::
በስደት ካሉት መካክል ዋነኛው ለፓትሪያሪክነት መወዳደራቸውን አስታውሳለሁ:: በበኩሌ መንግስት በተቀያየረ ቁጥር እንደ ሚኒስትር ፓትርያርክ መቀያየር የለበትም ባይ ነኝ :: ለዚህም መፍትሔው መንፈሳዊ ነኝ:ለቤ/ክን እቆረቆራለሁ: የቤ/ክን ልጅ ነኝ የሚል ሁሉ ፐለቲካን-ከሀይማኖት ነጥሎ ማየትና መንፈሳዊ መላ መፈለግ ይኖርበታል እላለሁ::
3. ተሀድሶን በተመለከተ: ሐዋርያዊት:ታሪካዊትና ጥንታዊት የሆነችውን ቤ/ክን እንደአላዋቂ በመቁጠር አዲስ ወንጌል 'ሊያስተምሩ' ሰርገው በገቡ ሀሳውያን:ወይም የእነሱ አፍ በሆኑ የእናት ጡት ነካሾች: በሀሳውያኑ በተማረኩ የዋህ 'ምእመናን' ሲካሄድ የነበረ እንቅስቃሴ ነበር አሁንም አለ:: ሀይማኖተ አበው ሲጀመር መልካም አላማ:ጥሩ አነሳስ ይዞ የተጀመረ ቢሆንም በሁዋላ ላይ ፈሩን በመሳት የቤ/ክንን መዳከም ለሚፈልጉ ሀይሎች መሳሪያ ሆኖ የተገኘ ማህበር ነው:: ይህንንም ስል ቀድሞ የሀይማኖተ አበው ማህበር የነበሩ ሁሉ መናፍቃን ናችው ለማለት አልችልም :: ምክንያቱም ቀድሞም ሆነ አሁንም ቤ/ክንን በእውነተኛ ፍቅር ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉ አባቶችን:እናቶችን:ወንድሞችንና እህቶችን አፍርቷልና!
በመቸረሻም: ምንም እንኩዋን በፖለቲካው ምክንያት ነገሮች ውል ቢያጡም ክርስቶስ የሞተላችውን ልጆቹን ከመጠበቅ አንጻር: በሀሰት ትምህርት እየተታለለ እየሄደ ያለውን ምእመናን ለማዳን : በጥላቻና በተንኮል በመነሳሳት ስም የሚያጠፉ ቢታረሙ: የተሳሳቱት በንስሐ ቢመለሱ: የበደሉ ቢክሱና: የተበደሉ ይቅር ብለው በአንድነት እናት ቤ/ክንን የሚያገለግሉብት መንገድ እንዲመጣ ልንሰራ: እግዚአብሔርንም ልንማጸን ያስፈልጋል::

ረዴተ እግዚአብሔር አይለየን!
የቅዱሳን አምላክ ካለንበት መከራና ፈተና እንድንወጣ ይርዳን::
Let God the almighty save our church!
ማየት መልካም
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Tue Sep 13, 2005 6:17 am
Location: united states

በሊቃውንተ ቤ/የተደረገ ዘመቻ

Postby ደብረታቦር » Tue Sep 13, 2005 10:36 am

""ስውር አደጋ"" በቀሲስ መላኩ ባወቀ

ካለፈው የቀጠለ

""ለመሆኑ የእነዚህ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም አደባባይ የወጣው ቤተ ክርስቲያን መከራበት ነው? ለምናቸው አልቅሳላቸው እባካችሁ ልጆቼ ስህተት አግኜባችሃልሁና ተመለሱ ብላቸው ነው? በፍጹም! ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንካን የእንዚህን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተከሰሱብትን ምክንያት አያውቁም ውንጀሉን የሚያነቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጣ ላይ ነው:: ከዚያም በየቤታቸው እነዚህን ካላባረራችሁልን የሚል ማስፈራራያ ይመጣል::
ለመሆኑ ይህ ሁሉ እወጃ ""ጳጳሳቱ ተሐድሶ ሆኑ"" ቤተ ክርስቲያኒቱ ከነበራት ኮሌጅ ውስጥ ከዲኑ ጀምሮ እስከ አስተማሪዎቹ ድረስ ተሀድሶ ሆነዋል ብሎ ማወጅ ማንን ነው የሚጠቅመው? ለማነው የልብ ልብ የሚሰጠው? የቤታችንን ጉድ ጋዳችን ይዘን ድብቅ አድርገን ተዋቅሰናል? ተላቅሰናል? አረ ለቤተ ክርስቲያን ትምከርበት:: አረ ለቤተ ክርስቲያን የምታስቡ ቆም ብለን እንወያይበት:: የበደለ ቢኖር እንካን አሁን ማኅበረ ቅዱሳን በሚያደርገው ዘመቻ ንስሐ ይገባል ወይ? ይህ እኮ በሕዘብ ላይ የተነጣጠረ ጠላትነት ነው:; ለመሆኑ ይህን ያህል ሰው የለንም ወይ? ይህን ያህል አገር ተፈትቷል ወይ?

ለነገሩ ቤተ ክርስቲያኒቱ ባዘጋጀችው ትምህርት ቤቶች ያላለፉ እነዚህ ወጣኒያን ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ገብቼ እንዚያን ሊቃውንት ላስተምር ሲሉ ቴዎሎጂያን ሆነው በምስጢረ ሥጋዌ ላይ መጽሐፍ ሲጽፉ መምህር እየተባባሉ እርስ በእርሳቸው ሲሞካሻሹ ጎጃም ቅባት ሆናልና እንዳኘው ብለው የጎጃም ሊቃውንትን ሰብሰበው ሲውሎ ከዚህ የባሰ የሀገር መፈታት ምን አለ? አረ ለመሆኑ ""የቅባት ማቅለጫዎች"" የጎጃም ሊቃውንት በስመ ቅባት ማንም ወፍ ዘራሽ ሲሳለቅባቸው ምን አሉ ይሆን? የሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ የሰማእቱ የቴዎፍሎስ የሊቁ የድሜጥሮስ አጽም እንዴት አለ ይሆን? ስንቱ ሊቅ በጥንቃቄ የነገረ መለኮት ኃይለ ቃላትን ሳያማታ ምሥጢር ሳያልፍስ ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጋር በጥንቃቄ እየመተከረበት ሲመልስ የነበረውን ጉዳይ እንዚህ ወጣቶች የሚመልሱት ቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት አጥታ ነው?

ማኅበረ ቅዱሳን ፍላጎቱ አውድማው እንዲህ እዲሆንለት ነው:: የትናንቶቹ አቶዎች ዛሬ ቄስ ተብለው ከዚያም አልፈው ራሳቸውን መምህር አሰኝተው በድግሪ ያጡትን ገንዘብ በቤተክርስቲያን በፖሊቲካ ያጡትን ሥልጣን በቤተ ክርስቲያን ጋሮ በኩል ማግኘት እንዲችሉ ቤተክርስስቲያን ወልዳ ያሳደገቻቸውን ገለል እንዲሉ ምድረግ ነበረባቸው:: እንዚህ የቤተክርስቲያን ልጆች አንዳንዶቹ በማኅበሩ ግፊት ከቤተ ክርስቲያን ከተባረሩ በኃላ በሠሩት ሥራ ተጸጽተው ቤተክርስቲያናቸውን ለበደሉት በደል ለሰደቡአት ስድብ ለሌሎች መሳሳት ምክንያት ለመሆናቸው በሙሉ ንስሐ ገብተው ተጸጽተው ቤተክርስቲያንቸውን ቢጠይቁ ያ ለማኅበረ ቅዱሳን የሞት ሞት ነው::ምክንያቱም ለነርሱ የእንዚህ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አደባባዮች መታየት ለሕልውናቸው አስጊ ነው:: ብሩ ፎቅ ቤት መሥራቱ ሊቀር ነው:; እውነት ሊገለጥ ነው:: እንዲህ ያለ አስተማሪ የት አፍናቹ አስቀምጣችሁ ነበር ሊባሉ ነው:: ስለዚህ ከዚህ ይልቅ እንደምንም ብሎ ማሳደድ አውሬ እንዲበላው ሁኔታዎችን ማመቻቸት ሲጠፉላቸው ደግሞ በአውሬ የተበሉት ራሳቸው ናቸው:: ወደ ጴንጤ የሄዱት ራሳቸው ናቸው ብሎ ማላዘን ይሄ ነው ልማዳቸው:: በ""ወልድ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው"" የሚለውን ለውጠው ""በማኅበረ ቅዱሳን የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው"" ብለው ያመኑ ይመስል ዛሬ በማኅበረ ቅዱሳን እስካመነ ድረስ ከሃዲ ቢሆን ቤተ ክርሲያን የሚዘርፍ ቢሆን ዘማዊ ቢሆን ግድ የለም:: የማኅበሩን ኅልውና አይነካምና::""

በሚቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳን በሰንበት ት/ቶች ላይ የከፈተን ዘመቻ ይዤ እቀርባለሁ::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ማ/ቅ በሰንበት ት/ቤቶች ላይ የከፈተው ዘመቻ

Postby ደብረታቦር » Thu Sep 15, 2005 6:10 am

""ስውሩ አደጋ"" በቀሲስ መላኩ ካለፈው የቀጠለ

ማኅበረ ቅዱሳን ሃይማኖተ አበው ከተዘጋለትና ሥልጣኑን ካደላደለ በኃላ ተሐድሶ የሚለውን ቃል አስፍቶ ማናቸውም በቅድስት ሥላሴ የሰንበት ትምህርት ቤት የአዘማመር ስልት የሚዘምሩ በሙሉ ተሐድሶ ናቸው በማለት አዲስ አንድምታ አበጀለት:: መንበር ጽባኦት ቅድስት ሥላሴ በስጦታ በተሰጠው ኦርጋንና በግርማዊነታቸው ትእዛዝ በሰለጠኑ የቤተክርስቲያኑዋ ልጆች በነ ዶክተር ኢሳይያስ ዓለሜነህ በተዘጋጀው መዝሙር የሚጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ሴቶች ቆመው የዘመሩበት ቦታ ነው::

የቅድስት ሥላሴ መዝሙራት መንፈስን የሚመስጡ የግጥማቸው ስልት ሥርዓትን የጠበቀ ካቴድራሉ ባሉት ምሑራን እየተመረመረ የሚወጡ ስለነበር በአብዛኛው ወጣቶች ዘንድ ተወዳጅነት ነበራቸው:: በዚህም ምክንያት ለብዙ ወጣቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት ከቤተክርስቲያናቸው እምነትና ሥርዓት ጋር መተዋወቅ ምክንያት ሆኗቸው ነበር::

እንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳን በጊዜው ባገኘው ኃይል ተጠቅሞ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴን የአዘማመር ስልት ይከተሉ የነበሩትና በአዲስ አበባ በልደታ ለማርያም በቅድስት ሥላሴ በሳሪስ አቦ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሐረር በስድስቱም አብያተ ክርስቲያናት በአማሬሳ በሒርና በአሰበ ተፈሪ በድሬዳዋ በቅድስት ማርያም በጊዮርጊስ በደብረ ማርቆስ በናዝሬት የሚገኙ የሰንበቱ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንዲዘጉ አስደረገ:: ወጣቶቹንም ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡና በቤተ ክርስቲያን እንዳይሰበሰቡ አሳገደ::

በአሁን ወቅት ከቤተክርስቲያን ስለተባረሩ ወጣቶች ማኅበረ ወጣቶች ማኅበረ ቅዱሳን የሚያወጣቸው ዘገባዎች ፍጹም ሐስትን የተመሉ ናቸው:: ስለ እነዚህ ልጆች ያለው እውነታ የሚከተለው ነው::

1ኛ. ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ አቤቱታም ክስም ለደብር አስተዳዳሪዎችም ሆነ ለህገር ስብከት ሥራ አስኪያጆቸ ያቀርብ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ነው::
2ኛ. እነዚህ ልጆች ከመባረራቸው በፊት በኦርጋን የቅድስት ሥላሴን መዝሙር አትዘምሩ ከሚል ውጪ የተከሰሱበት የክህደት ትምህርት የለም:: በየትኛውም ሥፍራ ጉዳያቸው በስብሰባ አልታየም::
3ኛ. ከቤተክርስቲያን ከተባረሩ በኃላ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ እንዳይስቀድሱ ቢወልዱ ክርስትና እንዳያስነሱ በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪዎች ሰለታገዱ ትንሽ ጊዜ በአዳራሽ በየቤታቸው እየተሰባሰቡ እርስ በእርሳቸው ቢጽናኑም ከማኅበራዊ ኑሮ ግፊት ከፕሮቴስታንቱ ዓለም ማባበልና ከማኅበረ ቅዱሳን የጥላቻና ደብድቡልኝ አባሩልኝ የሚል ጥላቻ ጩሐት በስተቀር በፍቅር የሚመልሳቸው ስላላገኙ ጠፍተው የቀሩ ናቸው:: አንዳንዶቹም የከዳቻቸው ደጅ የወረወረቻቸው እናት ቤተ ክርስቲያናቸው መስላቸው የግለሰቦችን ኃጢአት እና የቤተ ክርስቲያን ቅድስና መለየት አቅቷቸው የቤተክርስቲያን ጠላቶች ሆኑ:: አንዳንዶቹም አጥፍተን ከሆነ ይቅርታ ይደረግልን ቢሉ ማኅበረ ቅዱሳን ግብረ አበሮቹን አሰማርቶ አስደበድባቸው::አንዳንዶቹንም በፖሊቲካ አስከሰሰ አንዳንዶቹንም አሰገደለ:: በድሬዳዋ የሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር አባል ይዞ የነበረውና የሀገር ልብሱን ለብሶ ጭራውን ይዞ የእመቤታችንን በዓል አከብራልሁ ብሎ ወጥቶ ተሀድሶ ነው ተብሎ በማኅበረ ቅዱሳን አባላት የተገደለው ወንድማችን አዳም ከእነዚህ ስማቸውን ከማላውቀው አእላፋት ወጣቶች አንዱ ነው:: የነዚህን ደም የሚጠየቀው ማን ይሆን? ይህ ሁሉ ሲሆን ወደ የት እንድሚሄዱ ግራ የገናቸውን ወጣቶች በግልጥ ያገኘው የፕሮቴስታንቱ ዓለም ወደ የራሱ ጎራ በመውሰድ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ናጩ ስለዚህ ነው ያባረሩአጩ እያለ መስበክ ጀመረ:: በአንዳንድ ከትሞችም ከየቤተ ክርስቲያኑ በማኅበረ ቅዱሳን የተባረሩትና ሰብሳቢ አጥተው የተበተኑትን ወጣቶች ለመንጠቅ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች እርስ በእርሳቸው ከፍተኛና የመረረ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር:: በተለይም ደግሞ ዳግመኛ ወደ ቤተክርስስቲያናቸው እንዳይመለሱ ዳግም በማጥመቅ የእነርሱ ታማኝ ተከታዮች በማድረግ ለዘላለም ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ለይተዋቸዋል::

በሚቀጥለው ስለ ሐረር ሰንበት ት/ቤቶች ላይ የተከፈተው ዘመቻ ይቀርባል::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ!
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Postby የዘመኑ ልሳን » Thu Sep 15, 2005 7:51 am

እኔ አልገባኝም ከመቼ ጀምሮ ነው ደግሞ በቤተ ክርስቲያን በቅድስት ስላሴ አዘማመር ስልት የሚባል የመጣው::እኔ እማውቀው ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ያሬድ ጀምሮ ሲዋረድ የመጣውን ትጠቀማለች እንጂ ማንም አሹልኮ ያስገባውን ልክ ነው ቀጥሉ አትልም::የባሰ ሳይመጣ ሀገርህን አትልቀቅ ይሉኃል ይህ ነው::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ሐረር

Postby ደብረታቦር » Fri Sep 16, 2005 10:29 am

ስውሩ አደጋ በቀሲስ መላኩ ካለፈው የቀጠለ

ሐረር ጥንታውያን ከሚባሉት የኢትዮጵያ ከተሞች አንዳ ከመሆኑዋ በላይ እንደ አሜሪካዋ ቦስተን ለብዙ ሥልጣኔዎች የመጀመሪያዋ በር ከፋችም ናት:: የቀዶሞው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዎ ኃይለ ሥላሴም የተወለዱበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን በዚያ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ ትኩረት ይሰጡ ነበር:: በከትማዋ የሚመደቡት የቤተድርስቲያናችን ሊቃውንትና ሊቃነ ጳጳሳት በእውቀታቸውና በትምህርታቸው ከፍተኛ ተደናቂነት ያላቸው ነበሩ::ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በሊቀ ጳጳስነት ሀገረ ስብከቱን የመሩት ኢትዮጵያዊ ሰማእት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን መጥቀስ ይቻላል:: ከለውጡ በኃላ የቀደመውን የወንጌል አገልግሎት እንዲቀጥል ለማድረግ ሌት ተቀን የሚለፉ የቤተክርስቲያን አባቶች አልጠፉም ነበር:: ከእነዚህም አንዱ የአደሬ ጢቆ መካነ ሥላሴ ደብር አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ሰላም ጴጥሮስ አዘነ ናቸው:: ሌት ተቀን ለጽሎትና ላገልግሎት የማይደክሙት እንደ መላእክት ሰሉጥ የሆኑት ኦርቶዶክሳዊው ሊቅ መልአከ ሰላም ጴጥሮስ አዘነ እያንዳንዱን የቤተክርስቲያናችንን ሥርዓት በተግባር የሚያሳዩ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት ናቸው:: ተንባላት በከበቡአት ምድር ስዓታቱን ቆሞ ስብሐተ ነግሁን አድርሶ ጾመ ድጋውን አድርሶ ውሎ ቅዳሴው አስቀድሶ ማታ ምሕላውን አድርሶ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹን አስተምሮ ውዳሴ ማሪያምን በዜማ አድርሶ ለጥቂት ስዓታት ተኝቶ እንደገና ስዓታት ለመቆም የሚነሳው ስንቱ ነው? መልአከ ሰላም ጴጥሮስ እንዲህ ያሉ ታላቅ አባት ናቸው:: እኒህ አባት ወጣቱ ሃይማኖቱን አጽንቶ እንዲይዝና ከሌሎች የእምነት ክፍሎች ተጸእኖ የጸዳ እንዲሆን ከፍተኛ ትግል ያደርጉ ነበር:: አገልግሎታቸው ፍሬ አፍርቶ በተለይ በ1980 ዓ.ም. ጅምሮ ወጣቶች በብዛት በአጸደ ቤተክርስቲያን መሰብሰብ ጀመሩ:: የእርሳቸውን አርአያነት ተከትለው በተለይ ወጣቶች ማታ በሠርክ ጸሎት ላይ ጠዋት በኪዳን ቤተክርስቲያኒቱን አጣበው ""መሓረነ አብ"" ሲሉ መቆሚያ ሲያቀብሉ ቤተ ክርስቲያን ሲያጸዱ መመልሰት ምንኛ የሚያሰደስት ነበር::
ይህ በመካነ ሥላሴ የተጀመረው ወደ አጸደ ቤተክርስቲያን የመመለስ እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ በሌሎችም አድባራት ቀጠለ:: በመሆኑም በደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሚካኤል በተክለ ሃይማኖት በአቦከር ደብረ ጸሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስና በስተሀላ በተተከለው በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አባቶች እና እናቶች ይሰበሰቡ ጀመር::

በሚቀጥለው የነዚህ ወጣቶች መሳባሰብ አይኑ ደም የለበሰው ማን ይመስላቹኃል? የውጭ ጠላት ወይስ የውስጥ? በሚቀጥለው ትረካ መልሱን ይቀርባል::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ሐረር

Postby ደብረታቦር » Sat Sep 17, 2005 10:32 am

ስውሩ አደጋ (ካለፈው የቀጠለ)
በሐረር ከተማ የነበረው እንቅስቃሴ እጅግ ከሚያስቆጣቸውና ከሚያናዳድቻቸው መካከል በዚያ አካባቢ የሚገኙ ፕሮቴስታንቶች ነበሩ:: ምክንያቱም ወደ እነርሱ አዳራሽ ማንም ሰው አይሄድም ነበር:: በየቦታው የማታ ጉባኤ ሳይጀመር ሐረር በየቤትከርስቲያኑ ታላቅ ጉባኤ ነበር:: ፕሮቴስታንቱን ስላናደደው "'አስተማሪዎቻቸው የእኛ አባላት ናቸው"" እያሉ ማስወራት ጀመሩ:: ባሳለፍካቸው የአገልግሎትና የስደት ዓመታት እንዳስተዋልኩዋቸው ፕሮቴስታንቶች ታዋቂ የሆኑ ህዝቡን የሚያስተምሩ አንደበተ ርቱእ የሆኑ የቤተክርስቲያንን መምህራን በህዝባችን ለማስጠላት የሚጠቀሙበት በዚህ ዓይነት መንገድ ነው:: በሐረር ግን ማኅበረ ቅዱሳን መጥቶ የሃሳባቸውን እሰኪያሟላላቸው ድረስ አልተሳካላቸውም ነበር::

የሐረር ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተሐድሶ መባል::

ፕሮቴስታንቶች አንዳችም ሊያደርጉት ያልተቻላቸውንና በሌሎች ሃይማኖት በተከበበች ምድር አስደናቂ እንቅስቃሴ ያደርግ የነበረውን የሰንበት ትምህርት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ በድርጅታዊ ፍቅር ታውሮ የበታተነው ማኅበረ ቅዱሳን በሚል ስም የተቃቃምው ድርጅት ነበር:: ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ላይ ያለውን የሰንበት ትማህርት ቤቶች እንቅስቃሴ በድፉ ዓይን ማየት የጅመረው አለማያ ግብርና ዩኒሽርሲቲ ውስጥ ገና እግሩን በተከለበት ወቅት ነው:: በዚህ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ማኅበር በሐረር ስሙም የማይታወቅ ስለነበረ በሐረር ያሉ ካህናትም ሆኑ
ምእመናን ቦታ አልሰጡትም ነበር:: ነገር ግን ጥቂት ቆይቶ ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነትና ለሐረርጌ ሀገረ ስብከት አቤቱታ አስገባ:: አቤቱታውም ሐረር ውስጥ ያሉት ሰንበት ትማህርት ቤቶች በሙሉ ተሐድሶ ናቸው የሚል ነበር:: ለጊዜው የሀገረ ስብደቱ ጽሕፈት ቤት የማኅበሩን ክስ አጥብቆ ተቃወመ:: የሀረር ሕዝበ ክርስቲያንም ሁኔታውን ሲስማ አጥብቆ ተቃወመ::

በሚቀጥለው በሐሰት ሰነድ(forge doc) የማኅበረ አጋንንት የፈጠራ ችሎታ የሐረር ሰንበት ት/ቤት መዘጋትና የቀሲስ መላክ ግላዊ ምስክርነት ይቀርባል::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

የሐሰት ሰነድና የሐረር ሰንበት ት/ቤ መዘጋት

Postby ደብረታቦር » Sun Sep 18, 2005 9:33 am

ስውሩ አደጋ በቀሲስ መላኩ

ማኅበረ ቅዱሳንን ሐረር ምድር ላይ ላለማስገባት ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ተጀመረ:: ሁኔታው ያላመረው ማኅበረ ቅዱሳን የሐረር ሕዝበ ክርስቲያንን የሚከፋፈልብትን አንድ ረቂቅ ተንኮል አርቅቆ አወጣ:: ያም በሐረር የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን የተሐድሶ አባላት የሚያሳይ የሐሰት ሰነድ ነበር:: ሰነዱ በቃለ ጉባኤ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን የተሐድሶ አባላት የሆኑ ከመላው ኢትዮጵያ ተሰብሰበው ለሐረር እንቅስቃሴ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጡ ለሐረርም መሪዎችን እንደሾሙ የሚናገርና ስሞችንም የሚዘረዝር ነበር::

በዚህ የሐሰት ሰነድ ላይ መላክ ሰላም ጴጥሮስ አዘነን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱን የመዝገቡ ቤት ኃላፊ ሌሎች ካህናትና ታዋቂ ምእመናን የያዘ ነበር:: በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩት ቀንደኛ የሆኑ ማኅበር ቅዱሳንን አላፈናፍንም ያሉ ሰዎች ነበሩ:: በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት መምህር ብርሃነ ህይወት (አባ ዜና ማርቆስ የተባሉት በስሜን አሜሪካ ባሉት ታላቅ አባት ምትክ የተሾሙት) በደስታ ቸኩለው ተሐድሶዎች ቤተክርስቲያኔን ወረዋል በማለት በሸኚ ደብዳቤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ ካህናቱን የደብር አስተዳዳሪውን ታላቁን ሊቅ መላከ ሰላም ጴጥሮስ ከስራና ከደሞዝ አገዱአቸው:: ቤተክርስቲያኑ ለማንም ወጣት የተከለከለ እንደሆነ አስታወቁ:: በብዙ ሺህ የሚቆጠር የሐረር ህዝብ ሥእለ ማርያምም ይዞ በነቂስ ወጥቶ ውሳኔውን ተቃወመ ለቤተክህነት አቤት አለ:: ሰሚ ገን አላገኘም:: እነዚህ በሐረሩ የሐሰት ሰነድ የተጠቀሱት እንድ አዲስ አበባው ዘገባ
ዘም ብለው አልተቀበሉትም:: ወዲያውኑ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቀረቡ::ፎርጅዱን የሠራው ተያዘ:: ከማኅበረ አባላት አንዱ ይህን እንዲሠራ እንደጠየቀው ተናገረ:: የፖሊስ የምርመራ አባላትም ሰነዱ የሐሰት ሰነድ (ፎርጅድ) እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አስታወቁ:: ጉዳዩ ፍርድ ቤቱንም የሐረርን ሕዝብ አስቆጣ:: ፍርድ ቤቱም የሐሰት ሰነዱን በሸኚ ደብዳቤ የበተኑት ሊቀ ጳጳሱ ስለሆኑ በኃላፊነት እንደሚጠየቁ ወሰነ:: ከሦስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት ሊፈረድባቸው ፍርዱ እየተጠበቀ እያለ የኢሐደግ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ጳጳሱ ይቅርታ እንዲጠይቁና በሐሰት ስማቸው የጠፋውም ክሳቸውን እንዲያነሱና በየስማቸው ከጠላይ ቤተክህነትና ከሀገረ ስበከት ንጹሐን እንድሆኑ ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ተወሰነ:: ሊቀ ጳጳሱም ያሳሳቱኝ ልጆቹ (ማኅበረ ቅዱሳን) ናቸው ብለው ይቅርታ ጠየቁ::

አሳዛኙ ነገር ግን ይህ ውሳኔ የተሰጠው ድርጊቱ ክተፈጸመ ከሰባት ዓመት በኃላ መሆኑ ነው:: በዚህ ሰባት ዓመት "'ተሐድሶ" ናቸው ተብለው ከገዛ ቤተ ክርሲቲያናቸው የተባረሩና ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንዳይደርሱ የተደረጉ በዙህም ተበሳጭተው መሄጃ አጥተው ዓለም የበላቻቸው ደግሞም በስሕተት አረን ቁዋ የሰጠሙ በፕሮቴታንቱ ዓለም የተወሰዱ ስንቶች ናቸው:: ለእንዚህ መጥፋት ተጠያቂውና ኃላፊውስ ማነው?

የቀሲስ መላኩ ምስክርነት ይቀጥላል

ይትባረክ አምላክ አበዊነ!
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ግላዊ ምስክርነት ካለፈው የቀጠለ

Postby ደብረታቦር » Tue Sep 20, 2005 10:47 am

ስውሩ አደጋ ካለፈው የቀጠለ:

ማኅበረ ቅዱሳን ዛሬም ራሱ ያዘጋጀውንና በፖሊስ በፍርድ ቤት ሐሰትነቱ የተረጋገጠበትን የሐሰት ሰነድ በመያዝ እነ እከሌ ""ፓስተር" ናቸው:: ከቤተክርስቲያን የወጡት የመናፍቅነት መንፈስ ይዟቸው እንጂ ማንም አላባራራቸውም እያለ ይጽፋል:: ከእነዚህ በግፍ ከተባረሩት ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ በይቅርታው ወደ ቤቱ ከመለሳቸው አንዱ የዚህ ጽሁፍ(መጽሐፍ) አቅራቢ ነው::

ግላዊ ምስክርነት(የቄስ መላኩ ምስክርነት)

ይህን ታሪክ የምጽፍላችሁ የዚህች አነስተኛ መጽሐፍ አቅራቢ ተወልጄ ያደግሁት በዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው:: ከህጻንነቴ ጀምሮ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ኮትኩተው ያሳደጉኝ የቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያን ፍቅር እንዲኖረኝ በማእረገ ክህነት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳገለግል ያዘጋጁኝ ኦርቶዶክሳዊው ሊቅ መሪጌታ ባወቀ ተረፈ ናቸው:: ገና ደግና ክፉውን ሳላውቅ እጄን ይዘው እርሳቸውና በሚቆሙባት ቅኔ ማኅሌት አጠገብ ከእግራቸው ሥር እንድሆን በማድረግ ፍቅረ ቤተ ክርስቲያንን ፍርሃተ እግዚአብሔርን ተምሬ አድጌአለሁ::
አብዛኛውን የሕጻንነት ጊዜዬን ያሳለፍኩት በደቡቡ የሀግራችን ክፍል ሲሆን በተለይም ባደኩባት በአዋሳ መካነ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ገና ከታናሽነቴ ጀምሮ በስበከተ ወንጌል በመቀጠልም ከብጹዕ አብይነ በርተሌሜዎስ ማዕረገ ዲቁናን ብ1976 ዓ.ም. በመቀበል እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ለአራት ዓመት በዲቁና በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ አገልግያለሁ::

በዚህ ወቅትም በውስጤ ያለውን ፍላጎት ብፁዕነታቸው በቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ራሴን እንዳበለጽግ ከፍተኛ የሆነ አባታዊ ምክራቸውና ቅን ሃሳባቸው አልተለይኝም ነበር:: በትለይም ወደፊት ስለሚኖረኝ ሁኔታ ከወላጅ አባት በላይ ሰለእኔ በማሰብ በአደባባይ ሳይቀር መላኩን አዲስ አበባ ልኬ አስተምረዋለሁ በማለት ለእኔ ያላቸውን የወደፊት ሃሳብ ይገልጡ ነበር::

በተጨማሪም መልአከ ሰላም ኃይለ ኢየሱስ ከበደ መልአከ ምሕረት ጳውሎስ ቀጸላ መምህር ኃይለ ሥላሴ ይግዛው ኦርቶዶክሳዊ የስብከተ ወንገል ምን ዓይነት እንደሆነ በማሳየት አርዓያቸውን ተከትዬ እንዳድግ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ፍቅር እንዲኖረኝ አድርገውልኛል::

በተለይም በቤተክርስቲያን ታሪክ አስተማሪነታቸው ያላቸው መምህር ኃይለ ሥላሴ ይግዛው በአዋሳ የካህናት ማሰልጠኛ በሰጡኝና ቀን በሌት በትጋት ባስተማሩኝ ትምህርት ስለ ቤተ ክርስቲያኔና ስለ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፍቅር እን ዲያድርብኝ አድርገዋል::
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Postby ደብረታቦር » Tue Sep 20, 2005 10:58 am

አንባቢዎች በሚቀጥልው የቀሲስ አግልግሎት በሐረር
ይዤ እቅርባለሁ::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ቀሲስ መላኩ ብሐረር

Postby ደብረታቦር » Thu Sep 22, 2005 10:39 am

ሥውሩ አደጋ ካለፈው የቀጠለ

በአዋሳ ለእምስት ዓመት ካገለግለኩ በኃላ በወላጆቼ መካከል የተፈጠረው መለያየት ስለ አሳዘነኝ በዚያ የወጣትነት ወቅት ተንስቼ ወደ ሐረር ሄድኩ:: ወደ ሐረር የሄድኩት በጊዜው በአዋሳ የማውቃቸው ቀሲስ መዘምር የክፍለ ሀገሩ ሥራ አስኪያጅ ሆነዋል የሚል ዜና ስለስማው ነበር:: በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ኦርቶድክሳዊ አባት አቡነ ሳሙኤል የእድሜዬን አነስተኛነት አይተው ውደ ወላጆቼ ዘንድ እንድመለስ መክረውኝ ነበር:: ነገር ግን ካደጉባት መንደር ስወጣ ወስኜ ስለ ነበር ብጹዕነታቸው በእርሳቸው ሀገር ስብከት እያገለገልኩ መኖር እንደምፈልግ ነገርኩዋቸው::

በሐረር ለመጀመሪያ ጊዜ በዲቁና ያገለገልኩት በደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ነበር:: በዚያም ከአስተማሪ እጦት የተነሳ ተዘግቶ የነበረውን የሰንበት ትምህርት ቤት በአዲስ በማደራጀትና በዲቁና አገለግል ነበር::
በዚህ መካከል ነበር በዚያን ወቅት ሕይወቴን በአያሌው የለወጠው ነገር የተከሰተው:: ይኸውም በየዓመቱ የሚደረገውን የቀዳም ስኡር በኣል ምክያት በማድረግ ብጹዕ አቡነ ሳሙኤልን እንኳን አደረስዎት ለማለት በሐረር ከሚገኙ አድባራት ተሰብሰን ለዕለቱ የሚገባውን ሥርዓት እያደረስን እያለን የመካነ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች ልብ የሚነኩ መዝሙራትን አቀረቡ :: ከመዝሙራቱም መካከል "ፍቅሩ አይለወጥም' "የሞት ላብ አላበው" እና የመሳሰሉት ነበሩ:: መልእክትና ዜማቸው እጅግ የሚነካ ስለነበር በዚያ የተሰበሰብውን ምእመን በሙሉ የሳበ ነበር:: ከዚያም በፊት በሩቅ የማቃቸው የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ጴጥሮስ በአባትነታቸው የሚያከናውኑት ነገር ልቤን ስለነካው እርሳቸውን በግል ማነጋገር እንዳለብኝ ወሰንኩ:: ሳነጋግራቸውም በወጣትነቴ ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ማገልገል እንዳለብኝ መክረውኝ መካነ ሥላሴ ክፍት የዲቁና ቦታ ሳላለ እዛ እንድመጣ ትምህርቴንም እንድቀጥል ነገሩኝ::

በመካለ ሥላሴ ሰንበት ት/ቤቱን ለማደራጀት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስለነበረ በዚያ ወቅት ወጣቶችን በማስተማር በስብከተ ወንጌልና በዲቁና ማገልገል ጀመርኩ:: በዚያም ያለው የሰንበት ት/ቤቱ እንቅስቃሴ ወደ ስድስቱም አድባራት ተቀጣጠለ::

ወደ ቅዱስ ጵውሎስ ት/ቤት መግባቴ

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሐረሩ የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ይህንን እንቅስቃሴ በሚገባ ለማንቀሳቀስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ትምህርት ቤት በሚገባ የተማረ ካህን እንደሚያስፈልግ በማስስተዋል ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት መዝጋጀት ጀመርኩ::

ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ቤትም እንደገባሁ እግዚአብሔር ሁሉን አሟልቶ ከሰጣቸው ከመምህራኖቼ በሃይማኖቴ ላውቀው የሚገባኝን እንደ ካህንነቴም ላስተምረው የሚገባኝን በሚገባ ተምሬአለሁ::

በሚቀጥልው በቅዱስ ጳውሎስ ት/ቤት የተፈጠረውን ክፍፍል እና የድሬዳዋ ሁከትና ግድያ ይቀርባል::
አንባቢዎች መጠቃለሊያው እየታቀረብ ስለሆነ ታገሱኝ ውይይቱ ከዛ በኍላ ይቀጥላል እስከዛም ጥያቄ ቢቀርብ ውይይቱ ላይ ለመመልስ ይቻላል::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

በጳውሎስ ት/ቤት የተፈጠረው ክፍፍል

Postby ደብረታቦር » Fri Sep 23, 2005 10:56 am

ስውሩ አደጋ ካለፈው የቀጠለ

በስዋሰወ ብርሐን ቅዱስ ጳውሎስ የቴዊዎሎጂ ትምህርቴን በምከታተልብት ወቅት እንደ አዲስ የተፈጠረው የቡድኝነት ስሜት ነበር:: ዛሬ ያ የልጅነትና የእልክ ዘመን አልፎ በዚያ ውስጥ ያሳለፍኩትን የአለመብሰል ጊዜ ሳስታውሰው እገረማለሁ:: ለነገሩ ያ የድሮው ስህተት ሳያንስ ዛሬም በማኅበረ ቅዱሳን አባላት መካከል የሚታየው ጭፍን የሆነ ድርጅት ፍቅር ቤተ ክርስቲያን የሚጎዳ እንደሆነ ማን በነገራቸው?

በዚያ ወቅት በትምህርት ቤቱ ውስጥ የነበርነው ደቀ መዛሙርት ለሁለት የተከፈለ አቋም ነበረን:: አንዳንዶቻችን የሃይምኖተ አበው ልጆች በሚሰበሰቡት በመንበረ ፓትርያርክ ስንሰበሰብ ሌሎቹ ደግሞ በግቢ ገብርኤልና በምስካየ ሐዙናን በሚደረገው የማኅበረ ቅዱሳን ጉባኤዎች ላይ ይሰበሰቡ ነበር:: በተለይም በሃይማኖተ አበው ስበስባዎች ላይ በመገኘት አስተምር ስለ ነበር እኔ በማኅበረ ቅዱሳን ጥቁር መዝገብ ላይ ለማስፈር ጊዜ አልወስደባቸውም ነበር:: ነገሩን ለማርገብ የማህበረ ቅዱሳንን ከሚመሩት ጋር ለማነጋገር ሞክሬ ያገኘሁት ምላሽ ከሃይማኖተ አበው ጉባኤ እንዳንሄድና በኦርጋን የሙዚቃ መሳሪያ የሚጠቀሙትንና የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ስንበት ትምህርት ቤቶችን የአዘማመር ስልት የተከተሉትን ሰንበት ት/ቤቶችን እንድናወግዝ ነበር:: ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን እምነትም ሆነ ሕያው የሆነው ታሪኳ ስለማይፈቅድልኝ አልተቀበልኩዋቸውም::

ምንም እንኳን በየአብያተ ክርስቲያናቱ የምሰጠው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተወዳጅ ቢሆንም ማኅበረ ቅዱሳን ግን የእኔንም ሆነ በሃይማኖተ አበው እና በሌሎች ሰንበት ትምህርት ቤቶች የምናገለግለውን በመናፍቅነት ከመፈረጅ ወደ ኍላ አላለም ነበር:: በተለይም አገልግሎታችን እየሰፋ ሕዝቡም ስብከታችን ትምህርታችንን እየወደደ ሲመጣ የኛ በአጸደ ቤተ ክርስቲያን መታየት ለማኅበረ ቅዱሳን ሕልውና አደጋ እንደሆነ እየተቆጠረ መጣ::

እዚህ ላይ መጠቀስ የሚገባው ይህ ሁሉ ሲሆን በእኛ በኩል የመላእክት ባሕርይ ይታይብን ነበር ማለት አይደለም:: በተልይም የቤተ ክርስቲያን አባቶች የሚሉንን አለመስማት ችኮላ የሕጻንነት ባሕርይ አለመብሰል ከጉድለቶቻችን ዋናዎቹ ናቸው::ውጊያችን ለዘመናት የቤተ ክህነቱን ሥልጣን ለመጨበጥ ከሚያዳባና ስንት ሊቃውንትን ሲቻለው በአደባባይ ሳይቻለው በስውር ሲያጠፋ ከነበረ ቡድን ጋር መሆኑን አለማወቃችን በብዙ ጎድቶናል:: ያም ሆነ ይህ የዚህ ቡድን ችሎታ የት ድረስ እንደሆነ የተገነዘብኩት ድሬዳዋ በነበረው ግድያ ነው::

የድሬዳዋ ግድያ ይቀጥላል

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

የድሬዳዋው ግድያ በማኅበረ ቅዱሳን አማካይነት

Postby ደብረታቦር » Sun Sep 25, 2005 9:30 am

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ! አደረሰን

በቅዱስ ጳውሎስ በቆየሁባቸው ዓመታት የክረምትን ወቅት የማሳልፈው በመጣሁበት ሀገረ ስብከት ማልትም ሐረርጌና አልፎ አልፎ ደግሞ በወላጆቼ አካባቢ ነበር:: ሐረር እንደደርስኩም ከድሬዳዋ የሃይማኖተ አበው ተማሪዎች መልእክት ተቀምጦልኝ ነበር:: መልክቱም ነሐሴ 21 ቀን 1986 ዓ.ም ጉባኤ እናከናውናለንና እባክህ መጥተህ ብታስተምረን የሚል ነበር:: በእውነቱ በጣም ነበር ደስ ያለኝ ምክንያቱም እነዚህ ልጆች በብዙ የተገፉ ነበሩ:: በእኔ የልጅነት ሃሳብ የቤተ ክህነት ሰዎች የማኅበረ ቅዱሳንን ውትወታ ሰምተው ከቅጽረ ቤተክርስቲያን በያስወጡአቸውም አንድ ቀን ወደ ቤተከስትያናቸው ሊመለሱ ሰለሚችሉ እነዚህን ማጽናናት ማረጋጋት የገባል የሚል ነበር::

ጉባኤው ወደ ሚደርግበት ወደ ድሬዳዋ የገባሁት አንድ ቀን ቀደም ብዬ ነበር:: በዚያ ያሉ ወጣቶች በሙሉ ልባቸው ለጉባኤው እየተዘጋጁ ነበሩ:: ነገ የሚሆነውን የገመተም ያሰበም የለም:: ሁሉም የሚያስቡት አንድ ቀን ያ የሚወዱት ማኅበራቸው ከተሰደበበት እንደሚነሳ የቤተክርስቲያን አባቶች የእንዚህን ወጣቶች ምኞትና ሃሳብ አንድ ቀን እንደሚያዩት መናፈቅ እንዳይደሉ ነበር:: ይህ የነበር የነዚያ የዋሆች ልብ::

ጠዋት ድሬዳዋ እንደ ልማድዋ ደምቃለች:: እኔም ያደርኩበት ቤት በእንግዶች ግርግር ደምቛል:: ከእንዶቹ ጋር በመሆን ወደ ጉባኤው አዳራሽ ሄድን:: ጉባኤው የሚካሄደው በከተማው አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር:: አዳራሹ ከመቶ ዘጠና እጁ መስተዋት ብቻ የሆነ ውብ አዳራሽ ነበር::

ጉባኤው ምስባክ ተሰብኮ በጸሎተ ወንጌል ሰተከፈተ በኍላ የሃይማኖተ አበው ወጣቶች የሀገር ልብሳቸውን እንደለብሱ የዕለቱን መዝሙር አቀረቡ:: በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ጩኸት ሰማን ወዲያውም የመጀመሪያው ድንጋይ የመጀመሪያው ድንጋይ የተሰበስብነትን አዳራሽ መስተዋት ሲሰብር ተሰማን:: የስዎቹን ቁጥር ቁጥር ለማየት ለሌሎች አዳጋች ቢሆንም ለእኔ በግልጥ ይታየኝ ነበር:: ምክንያቱም በእለቱ ፕሮግራሙን እየመራሁ የነበርኩት እኔ ነኝና::

በመጀመሪያ የመጡት ጥቂት ሰዎች ቢሆኑም "ያዘው! ስበረው!"ጩኸት ያሰሙ የነበሩት ግን ብዙ ነበሩ:: በድንጋይ መስተውቱን አንዴ ሲያደቅቁት በበሩ የነበረው ታጣቂ(ቦታው የአስተዳደር አዳራሽ ሰለነበር ነው) ወደ ሰማይ ለመተኮስ ቢሞክርም አልቻለም:: መጨረሻ ላይ ነፍስ አውጭኝ ብሎ ሸሸ:: ከዚያ በኍላ መራኮት ሆነ:: ''ዋናው እሱ ነው እርሱን ያዙት'' የሚል ጩኸት ብሰማም የማላዋቃቸው ሰዎች መጥተው ሰለሸፋነኑኝ እኔን ለመግደል ለሞከሩት ስዎች አልሆነላቸውም ነበር:: ''ስለ እማምላክ ተዉኝ'' ከምትለው ነፍሰ ጡር ጀምሮ ''እማዬ የት ነሽ'' እያለ እስከሚያለቅሰው ሕጻን ድረስ ታላቅ ጩኸት በአዳርሹ ውስጥ ሞላ::

መግቢያና መውጫውን እነርሱ ሰለያዙት በየትም መውጫ አልነበረም:: የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎች እስኪመጡ ድረስ ሰዎቹ ይዘዉት በመጡት ሁሉ መቱን:: ማን ምን እንደሆነ ለማወቅ ግን አልተቻለም ነበር:: በመጨረሻ የጸጥታ ሰዎች በመጡ ወቅት ግን የተወሰንነው እነርሱን ጥግ አድርገን ለማምለጥ ቻልን:: ከአካባቢው እየሮጥኩ ስወጣ ታክሲ ስላገኘሁ የማልረሳውን ቃል ተናገርኩ-:''ከዚህ ቦታ ወደ ፈለግህበት ውሰደኝ'' ምንም እንኳን ለጊዜው ለባለ ታክሲው የተናገርኩት ቢሆንም በዚያ ወቅት ግን ለአምላኬም የተናገርኩት ነበር:: ''ብቻ ከዚህ ቦታ ወደ ፈልግህበት ውሰደኝ'' ወንድሞቼ በምላቸው የገዛ ወገኖቼ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስንደበደብ ምን ልበል? ካሳደገችኝ ቤተ ክርስቲያን ሽሚዜ በደም ጨቅይቶ እንደሌባ በገዛ ሀገሬ ወገኔ ፊት ስሸሽ ምን ልበል? (በሸፈኑኝም ሰዎች ደም ጭምር ነበር የዳንኩት እነርሱ ለኔ ደሙልኝ) እናም በታክሲ የተቻልኝን ያህል ራቅሁ:: የራቅሁት ግን ሕይወቴን በሙሉ ከስጠሁበትም ቦታ ነበር::

በሚቀጥለው ፍርደ ገምድሉ የአቡነ ጳውሎስ ቤተ ክህነት በዚህ ጉዳይ ላይ ያስትላልፈውን ውሳኔ እና የቀሲስ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መመለስን ይዤ እቀርባለሁ:: የአቡነ ጳውሎስ ካድሬ ይሆኑት ማህበረ ቅዱሳን ተብዬ ቡድኑ ገዱሉ ይህን ይመስላል አሁን በሰሜን አሜሪካ የአቡነ ጳውሎስ ሲኖዶስን አንቀብልም ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ላይ መርዙን በመርጨት ላይ ይገኛል ሆኖም አልተሳክለትም በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት እንመልስበታለን:: (በነገራችን ላይ 95 በመቶ የሚሆኑት አብያተ ክርስቲያናት አቡነ ጵውሎስን ፓትርያርክነት አይቅበሉትም)

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ያልታሰበው ውግዘትና ከት/ቤት መባረር

Postby ደብረታቦር » Wed Sep 28, 2005 4:26 pm

ካለፈው የቀጠለ (ስውሩ አደጋ) በቀሲስ መላኩ

ከድሬዳዋ ድብደባ በኃላ ወዲያው ሐረር ነበር የተመለስኩት በሐረር ሁኔታው ተሰምቶ ስለነበር ሕዝቡ ሁል አንድ ነገር የሆንን መስሎት ነበር:: በሰላም መመላሳችን ደስታ ቢኖርም የእኛን እግር ተከትሎ አንድ አስደንጋጭ ዜና ደረሰን:: ከተደበደቡት መካከል ሦስቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና በተለይም አንደኛው በኮማ ውስጥ እንዳለ ተነገረን:: ሁላችንም አለቀስን:: ሰለ ወንድሞቻችን ሰለ እህቶቻችን ደግሞም በነፍሰ ገዳዮች እጅ ሰለወደቀችው ሰለ ቤት ከርስቲያናችን አለቀስን:: በተልይም በኮማ ውስጥ ያለው አዳም የተባለው ወንድማችን መሆኑን ስሰማ በጣም አዘንኩ:: ብዙ ባላውቀውም በድሬዳዋ በነበረኝ ቆይታ አግኝቼው ነበር:: ቤተ ክርስቲያን የሚወድ የአምቦ ልጅ ነበር::ለህገሩ ለቤተክርስቲያኑ ታላቅ ፍቅር ስላለው የሀገር ልብስሱ በባንዲራና በእመቤታችን ሥነ ሥእል ያጌጠ ነበር:: ያን ኢትዮጵያዊ ነበር አናቱን በድንጋይ የቀጠቀጡት::
የአዳምን ሁኔታም የሌሎችንም ነገር ልማጣራት በተልያየ መንገድ ብንሞክርም ስላልተቻለ በጠዋት እንደገና ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ወሰንን:: ጠዋት ወደ ድሬዳዋ ስንሄድ እንዚያ ሃይማኖተ ጽኑ ልጆች የተዋህዶ ልጆች በለቅሶ ውስጥ ነበሩ:: በኮማ ውስጥ የነበረው የሃይማኖተ አበው ተማሪ ኦርቶዶክሳዊው አዳም አርፎ ነበር:: በስተኃላ እንደሰማሁት የተወሰኑ የመስሪያ ቤት ልጆች ገንዘብ አዋጥተው አስከሬኑ ወደ አንቦ ተልኳል::


ይቀጥላል
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ከስዋሰው ብርሃን መባረርና ያልታሰበው ውግዘት

Postby ደብረታቦር » Sat Oct 01, 2005 11:49 pm

ስውሩ አደጋ ካለፈው የቀጠለ

ከድብደባውና ከመጋፋቱ በላይ እነዚያን ልጆች የወንድማቸው መገደል እጅግ የጎዳቸው ይመስለኛል::በተለይም ገዳዮቹ ራሳቸውን የኦርቶዶክስ ጠባቂ አድርገው የሚያዩት የድሮዎቹ አጠቃላይ ጉባኤዎች የአሁኖቹ ማህበረ ቅዱሳን ሲሆኑ የበለጠ ጥቃት ተሰማቸው:: ከተድብዳዊዎቹ መካከል አጠቃላይ ጉባኤ በ1970ዎቹ ያደረሰውን ድብደባ የሚያውቁ ነበር:: ድብደባውንም በዋናነት የመሩት መምህር ብርሃነ ሥላሴ (አሁን አባ ዜና በታላቁ አባት በአቡነ ዜና ምትክ የተሾሙት) ቀድሞም በልደታ ለፈሰሰው የዲያቆኖት ደም ተጠያቂ እንደሆኑ ይነገር ነበር የብዙዎቹን የብዙዎቹን ወጣቶች አእምሮ በጠበጠው::

በተቻለኝ መጠን ልጆቹን አረጋግቼ ወደ ሐረር ከተመለስኩ በኍላ በሐረር አገልግሎቴን እየሰጠሁ ቆይቼ ትምህርት ቤት ስለ ተከፈተ ስዋሰው ብርሃን ተመለስኩ:: ወደ ትምህርት ቤቱ አደባባይ እንደረገጥሁም ቢሮ እንደምፈለግ ስለተነገረኝ ወደ ብጹእ አቡነ መርሃ ክርስቶስ ጽሕፈት ቤት በቀጥታ ሄድኩ:: ብጹዕነታቸው መስቀል ካሳለሙኝ በኍላ የድሬዳዋውን ነገር እንደሰሙ የኛም የልጅነት ችኮላ እንዳሳዘናቸው አጫወቱኝ:: ነገር ግን ከበላይ ማለትም ከጠቅላይ ቤተክህነት አንድ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ከትምህርት ቤቱ እንደታገድኩ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ትዕዛዝ እንደመጣላቸውና እርሳቸውም ትእዛዙን ከመጸፈም በስተቀር ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ነገሩኝ:: ሁኔታው በጣም ገረመኝ:: የተገደልነው እኛ! የተደበደብነው እኛ አሁን ደግሞ የተከሰስነው እኛ ነበርን:: አባታችን ጉዳዩን በትዕግስት እንድይዘውና ቤተክህነት ሄጄ ደጅ እንድጠና መክረውኝና ጸልየውልኝ መስቀላቸውን ተሳልሜ ከቢሮአቸው ወጣሁኝ::

ሁኔታው በስዋሰወ ብርሃን ለነብሩት ደቀመዛሙርት ድንጋጤ የፈጠረ ቢሆንም ለእኔ ግን እንግዳ አልሆነብኝም:; ነፍስ ለማጥፋት ወደኍላ ያላሉ አሁን ደግሞ የቤተክህነቱን ባለ ሥልጣናት ጥግ አድርገው እኝህን አባት አባርሩ ብለው በያዝዙ አያሰደንቀኝም ነበር:: ከትምህርት ቤቱ ከተባረርኩ በኍላ እገዳዬን ለማስነሳት የቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሆነው አቶ መርስኤ ሐዘን ዘንድ ደጅ መጥናቴን የተያያዝኩት ወዲያው ነበር:: በሦስተኛውም ቀን ወደ እርሳቸው ጽሕፈት ቤት መቅረብ እንደማልችል በጸሐፊያቸው በኩል ተነገረኝ:: ቢሆንም ደጅ ጥናቴን ለአንድ ወር አላቋረጥኩም ነበር:: በዚህ ወቅት ያላሰበኩት ነገር ከሌላ አቅጣጫ ተነገረኝ::
ይቀጥላል

ፍርደ ገምድሉ የአራት ኪሎ ቤትክህነት በደመራው ላይ በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ላይ ያወጣው መግለጫ ኢፍትሀዊ አቋሙ አግጥጦ ታይቷል:: የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነኝ የሚለው ስውር የሥልጣን ጥማቱን አጀንዳ ለመወጣት እጁን በሰው ደም እስከ መንከር ድረስ በእናት ቤተ ክርሲቲያን ውስጥ የሚንቀሳቀሰው "ማህበር ቅዱሳን" ተብዬውም ክወያኔ አብሮ መቆሙን የማስ ሚዲያዎችና እንካን እያገልጡት ነው (ትንሣኤ ሬድዮ 9/26/05 ያዳምጡ)
ማህበር ቅዱሳን ተብዬ እንድ አንድ መንፈሳዊ የወጣቶች ማህበር እንዲያውም ልሳኑን የሚገልጽበት ጋዜጣ እያለው የወያኔ ባለስልጣን (ተፈራ ዋልዋ) ቤተክርስቲያናን እያቃለለ ሲናገር ሰላማዊና መሣሪያ ይልታጠቁ ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ግንባራቸውን እየፈጠፈጠ ሲጣሉ ትንፍሽ አላለም:: በውስጡ የተሰገሰጉት የወያኔ ካድሬዎች ስለሆነ:: ይህን በትመለከተ ትረካ ይለቅና እንመልስበታለን::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 4 guests