ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳንና ሀይማኖተ አበው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ስውሩ አደጋ ካለፈው የቀጠለ

Postby ደብረታቦር » Tue Oct 11, 2005 7:23 pm

ውድ አንባቢዎቼ! ስሞኑን በመጥፋቴ ከይቅርታ ጋር ትረካው ይቀጥላል!

"'ካደግሁባትና የእውቀት ጡቷን ጠብቼ እንጀራዋን በልቼ ለዚህ ከበቃሁባት ቤተ ክርስቲያን መታገዴን የሚናገር ደብዳቤ በየአቅጣጫው ተበተነ:: ደብዳቤው ደግሞ ወጪ የሆነው እኔ ደጅ ከምጠናበት ከጠቅላይ ቤተክህነት ነበር:: በተለይም ከሁሌ አንጀቴን የቆረጠው ለእኔ አጠገባቸው ሆኜ ደጅ ለምጠናው የእገዳዬንም ሆነ የተወገዝኩበትን ደብዳቤ በእጄ ሳይሰጡ ውይም ሳይነግሩኝ አዋሳ ውርደው አባቴ በሚያገለግልበት በአዋሳ መካነ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ማንበባቸው ነበር:: ውግዘቱ እኔ ያስተማርኩትን የስህተት ትምህርት አይናገርም:: ያወገዘኝንም ጉባኤ አይናገርም:: የሚናገረው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት መላኩን ነው:: በኋላም እንደሰማሁት ይህን በከፍተኛ ደረጃ ለማስፈጽም ላይ ታች ይል የነበረው በጊዜው በከፍተኛ የቤተክህነት የሥልጣን እርከን ላይ የተመቀጠው የቀድሞው የአጠቃልይ ጉባኤ አስተባባሪ ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኘ ነበር::
ይህ ውግዘት መላውን አመለካከቴን በቻ ሳይሆን ከዚያ በኃላ ከቤተክርሲያኔ ጋር ያለውንም ግንኙነት ለውጠብኝ:: እንደ ልቤ ቤተክህነት ውስጥ ገባ ወጣ ለማለት መፍራት ጀመርኩ:: "'ያወገዝነው ግቢ ውስጥ ተገኘ ብለው" የቅዱሳን ማኅበር የሚለው ቢያስገድለኝስ ብዬ በመስጋት መቅረብ አልቻልኩም:: በተልይም የትበተነው ደብዳቤ በብዙ መንገድ ስለጎዳኝ ከእኔ ከእውቀት በላይ ልቤን አሸፈተው::

ይቀጥላል: ቀሲስ ከቤተክርቲያን ወጥቶ የት ሄደ?

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ግሩም ነው!

Postby ትትና » Thu Oct 13, 2005 3:52 am

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? በመጀመሪያ ክርስቲያን ተመችቶት ያለፈተና ነው የሚኖረው ያለው ማነው?
ታዲያ እኚህ ሰው (ቀሲስ/ፓስተር መላኩ) (የትኛው እንደሆነ ማመን ስለከበደኝ ነው) እውነት መከራ ቢደርስባቸው ይገርማል? ሀዋሪያቶች ስንት ነገር ነው የደረሰባቸው? እንዲህ እንደ ትልቅ ነገር ይህንን ሁሉ ስትል ገርሞኝ ነው::
ሌላው ብዙም ስለቤተክርስቲያን የውስጥ አሰራር ባላውቅም:: ፓትሪያሪክ መሞት አለበት ሌላ ለመሾም የሚለው ህግ እንደ አስርቱ ትእዛዛት ከእግዜር ነው የተሰጠው ወይስ ለቤተክርስቲያን ማስተዳደሪያ አባቶች ያወጡት ነው? ለምን መሰለህ እንዲህ ያልኩት የሰውን ህግ እግዜር ይሽረዋል የእግዚአብሄርን ግን ማን ይሽረዋል?
ለማንኛውም እንደኔ በእምነት ላለ ሰው ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይላል ቅዱስ መጽሀፍ ስለዚህ የቀድሞው አባት ቦታቸውን መልቀቅ ጥበበ እግዚአብሄር ነበረበት ምክንያቱም አስበው እስቲ ቦታውን ከማስለቀቅ ይልቅ እንደ ደርግ ጊዜ ተገለው ቢሆንስ? ደም ፈሰሰ አይደል? ሌላ ጥፋት!
ግን ደሞ የአቡነ ፓውሎስም ስልጣን መያዝ የእግዚአብሄር ፈቃድ ስለሆነ ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር ያልሾመው ስልጣን አይዝምና:: ለበጎም ይሁን ለመጥፎ አባት ተደርገው ተሹመዋል እኛኛውም አልችልም ብለው ወርደዋል ስለዚህ ማክበር አለብን እንደኔ እምነት:: ስደተኛ ምንምን ከማለት እግዚአብሄር ፈቃዱ ሆነ ማለት የአማኞች አመለካከት ይመስለኛል::
ሌላው አንተ ወያኔ ተሀድሶ ምናምን የምትላቸው ማህበረ ቅዱሳን ዛሬ ለቤተክርስቲያን የሚያደርጉትን ማንም አላደረገም:: ለወጣቱ በሀይማኖቱ መጎልበት እናት ቤተክርስቲያንን ተጠግቶ መኖር, ከአለማዊ ትምህርቱ ጋር መንፈሳዊ ትምህርቱን ጎን ለጎን አካሂዶ ለቤተክርስቲያን በእውቀቱ በገንዘቡ በጉልበቱ አለሁሽ የሚላት አንተ 'አጋንንት" የምትለው ማህበር መሆኑን ቀርበህ ብትመለከት ጥሩ ይመስለኛው ምን አልባት ሰው የጻፈውን ከሆነ የምትገለብጥልን::

አደረህን ደሞ እንደ ናታን ወያኔ/ የማህበሩ ወታደር እያልክ እንዳትጠራኝ እኔ ሁለቱም ውስጥ የለሁበትም ግን ማህበሩ የሰራውን አይቻለሁ! ያየሁትን እውነት መናገር ስላለብኝ ነው;:

እግዚአብሄር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

ይድረስ ለትትና

Postby ደብረታቦር » Thu Oct 13, 2005 9:55 am

ሰላም ላንቺ/ተ ይሁን ትትና!

ወደ ትረካ ከመሄዴ በፊት ጥያቄዎቹን ለመመለስ እሞክራለሁ::
በፈተና ለምን አልጸናም የሚለውን ጥያቄ አሳዳጆቹም የስም ቅዱሳን ግን በግብር የረከሰው ማህበርም የሚጠይቀው ጥያቄ ነው:: መልሱን ከትረካው ከራሱ ከቀሲስ መላኩ ታገኝዪዋለሽ:: በነገራችን ላይ የብእርሽ መዓዛ እንደ ተዋስህያኑ ማህበር ነው::


የፓትያርክን ሹመት በተመለከተ ለጠየቅሽው ጥያቄ በርግጥ የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል አይደለም ሆኖም በሐዋርያት ወንበር በተቀመጡት አባቶች የሊቀ ጳጳሳት ጉባኤ ወይንም ሲኖዶስ የተደነገገ የቤተ ክስርሲቲያን ቀኖና ወይንም ሥርዓት ነው::ይሀው ቀኖና ቤተክርስትያን ፍትሀ ነገሥት በሚባል የቤተክርስቲያንችን መጽሀፍ ላይ የቀደሙት አባቶች አስፍረውልን አልፈዋል:: የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ሁለት ዓይነት ነው አንደኛው ዓለም አቀፋዊ ሲሆን ሁለተኛው ሀገራዊ ነው:: የፓትርያርክን ሹመትን የሚያካታትተው ቀኖና አለም አቀፍዊ ቀኖና ነው:: አለም አቀፋዊ ስንል አምስቱ የኦርቶዶክስ እህትማማቾች አብያተ ክርስቲያናትን ነው:: እነርሱም የግብጽ ኦርቶዶክስ, የአርመን, የህንድ, የሶርያ እና የኢትዮጵያን ማለት ነው በጥቅሉ (Oriental Churches) ይባላሉ:: በመሆኑም አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ቀኖና/ሥርዓተ ቤት ክርስቲያናት አላቸው:: ቀኖናን ማሻሻል ወይም መለወጥ የሚችለው የሊቀ ጳጳሳት ጉባኤ ወይንም ሲኖዶስ ነው በመሆኑም አለም አቀፋዊውን ቀኖና ለማሻሻል ካሰፈለገ የአምስቱም አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶስ ተሰባስበውና ጸልየውበት ተስማምተውበት ብቻ ነው:: ሆኖም ይህን ቀኖና በዘፈቀደ የጣሰ ቢኖር የቤክርስቲያን ሥርኣተ አልበኝነት (spritual anarchism) ማራመድ ይሆናል ማለት ነው:: በመሆኑም ቀኖና የጣሰ ሲኖዶስ ህጋዊነት እና ቅድስናን ያጣል:: ለዚህም የቀሩት እህት አብያተ ክርስቲያናት ለኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እጅግም ክብር የላቸውም በስርዓተ አልበኝነት ይፈርጃቷል:: ሀገራዊውን ቀኖና ደግሞ አገር ባለው ሲኖዶስ ይሆናል ማለት ነው:: ለምሳሌ ያህል ሴት ልጅ በውር አበባ ወቅት ቤተ ክርሲቲያን እንዳትገባ የሚያዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና ነው:: ይህንን ትእዛዝ ማሻሻል ካስፈለገ የኢትዮጵያ ቤ/ክ ህጋዊው ሲኖዶስ ይችላል:: ቀኖና መጣስ ኃጢዓት ነው እንዴ ላልሽው መልሱ አዎ ነው:: ያለመታዘዝ ኃጢአት ነው::

እኚህ በእጃቸው ደም የሚገኝባቸው ፓትያርክ መሾም የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው ካልሽ የመንግስቱ ሀይለማርያም እንዲሁም ሳጥን ገልብጦ መሪ ነኝ የሚለው መለስ ቅድስት አገር ኢትዮጵያን እንዲመሩ የእግዜር ፍቃድ ይሆን? ከሆነማ ህዝባዊ ዓመጽ አያስፈልግማ?

ማህበሩ ታውቀዋልህ እንዲህና እንደዛ ያረገ ነው ላልሽው ጥያቄ መልሱ አዎን በደንብ አውቀዋለሁ:: በነገራችን የኢጣሊያ ፋሺስት መንግስት የአባይ ድልድይ እና ሌሎች ህንጻዎችን ለሀገራችን ስርቶዋልና ጅግኖች አባቶቻችን ዝም አላሉትም:: ኢጣሊያ ያንን የስራው ላገዛዝ እንዲያመቸው ነው:: ብዙዎች የፕሮቴስታንት ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሲሰብኩ እኮ ሆስፒታል ት/ቤት እየስሩ ማልትም ነጻ ህክምናና ትምህርስት እየሰጡ ነው:: ይሄም የእኩያን ማህበር የሥልጣን ጥማቱን ለመወጣት የስላሴን ተክል ክርስቶስ በደሙ የገዛውን ህያው ቤትመቅደስ የሆነው ሰው እየገደሉ ህንጻ ቤተክስርስቲያን ይጠግናሉ::

የዓሣ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ ትልቁ ቀኖና ቤተክርስቲያን ጥሰው "በወያኔነት" መንበረ ፓትርያርኩን ይዘው የቤተክርስቲያን ራስ በሆኑት አባ ጳውሎስ እየተመሩ ራስን "የቅዱሳን ማህበር" ብሎ ስይሞ በአሜሪካ መዝሙር በኦርጋን ተዘመረ ቀኖና ተጣሰ ብሎ በስደት የሚገኙት አባቶች ላይ የጥፉልኝ ዘመቻ ምን ይባላል:: መልሱ "የራሳ እያረረባት የሰው ታማስላለች" ነው:: በመስረቱ በፒያኖ መዘመር የተጅመረው ዛሬ አይደለም በአቡነ ባስልዮስ, በአቡነ ቴዎፍሎስ, በአቡነ ተክለሀይማኖት እና በአቡነ መርቆርዮስ ዘመነ ፕትርክና የነበረ ያለም ነው:: የመዝሙር መሳሪያ እንዲያውም በቀኖና ውስጥ እንካን የሚካተት አይደለም:: ከሀሰት አባታቸው ከዲያብሎስ ያገኙት ነው:: በነገራችን ስለዚህ ማህበ ሳወራ አብላቱን በሙሉ አይደልም:: ብዙዎች የዋሃን ቤተክርስቲያናቸው ከልብ ያግለግሉ እየመሰላቸው በዚህ ማህበር ታቀፈው የሚንቀሳቀሱ አሉ:: እነርሱን ሳይሆን አመራር ያሉትን በስይጣናዊ አጀንዳ የሚንቀሳቀሱትን አባላት እንድሆነ ይታወቅልኝ::
ወገኖቼ ትረካውን ነገ ልመልስበት

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
Last edited by ደብረታቦር on Thu Oct 13, 2005 5:03 pm, edited 1 time in total.
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ቀሲስ መላኩ ከጽዋ ማኅበራት ጋር

Postby ደብረታቦር » Thu Oct 13, 2005 4:44 pm

ስውሩ አደጋ በቀሲስ መላኩ

ከቤተ ክርስቲያን ስታገድ በግል ሕይወቴ ኑሮዬን የምመራበት አንዳች ነገር ስለሌለኝ ለጊዜው ጥግ ይሆኑኝ እንደ እኔው ከየሰንበት ትምህርት ቤቱ በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት የተበተኑት የጽዋ ማህበራት ነበሩ:: በመጀመሪያ እንዳስተምራቸው የጠየቁኝ ከቅድስት ሥላሴ የተበትኑት ልጆች ነበሩ:: እነዚህ ልጆች ከሌሎች ለየት የሚያደርጋቸው በውስጣቸው በእድሜ የበሰሉ ያሉ ሰዎችም የቤተ ክርስትያን ሰዎችም ነበሩበት:: ነገር ግን
ፕሮቴስታንቶች ሰርገው ገብተውበታል የሚል ሃሜታ ስለነበር ብዙም አልተማመናቸውም ነበር:: ሆኖም የማኅበሩ ሊቀመንበር ቤተክርስቲያኑን በጣም የሚወድ ስለነበር ግልጥ አድርጌ ነገሩን ሳጫውተው እውነታውን ነገረኝ:: አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ሾልከው ልጆቹን ለመውሰድ እንደሚሞክሩና የቤተክህነት ባለሥልጣናት ቤተክርስቲያኒቱን ጠቀምን ብለው ለአውሬ እንድሰጣቸው ነገረኝ:: ሁኔታው በአጠቃላይ የሚያሳዝን ነበር:: ከእነርሱ ጋር ሆኜም አልፎ አልፎ ከማኅደር ስብሃት ልደታ ለማርያም የወጡትን ልጆች አስተምራቸው ነበር:: እነርሱ በሚገባ የተደራጁና በተለይም ይመራቸው የነበረው ከፍተኛ የሆነ ባለሥልጣን በመንግስት ድርጅት ውስጥ የነበረው ቤተክርስቲያኑን የሚያፈቅር ሰው ስለሆነ በብዙም ሳይሆን ጥቂቶቹን ከጥፋት ታድጋቸዋል:: እርሱ ይመራቸው የነበሩት እስከ ዛሬ በሃይማኖታቸው ጽንተው አሉ::
ከሐረርም የምሰማው አስደሳች አልነበረም:: ከዚህ በፊት ታሪኩን በሰፊው እንዳነበባችሁት በሐረርም ያሉት በዚያ ሁሉ መከራ የጸኑትን በሐሰት ሰነድ ከቤተክርስቲያን አባረሩዋቸው:: ከቤተክስርስቲያን መባረር ማለት ቀላል አድርገን የምናይ ካለን ምናልባትም በሚገባ የቤተክርስቲያናችንን ታሪክና የቤተክርስቲያን ትምህርት ማስተዋል አለብን:: ከቤተ ክርስትያን ስንባረር የተባረርነው ከአንድ ድርጅት አባልነት አይደለም:: የተባረርነው ጸጋ ከሚገኝበት ሥፍራ ነው:: ያ ጸጋ ነው በሃይማኖት የሚያቆመው::

አንዳንድ ሰዎች ይህን የመክራና የእንግልት ታሪክ ስነግራቸው ለምን አልጸናችሁም ነበር ይሉናል:: ሌላው ቀርቶ የትናንቱ አሳዶጆቼ በቅርቡ በሬድዮ ላይ ለምን እንደ አባቶቹ በመከራም ቢሆን ለምን አልጽናም ለምን ወደቀ ብለውኛል:: ለዚህ ቀጥተኛ መልሴ በመክራዬ ቀን ወደምጸናበት ሥፍራ አላስደርስ አላችሁኝ የሚል ነው:: ያችም ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን ናት:: አበው ይህን ስለሚያውቁ ነው ከቤተክርስቲያን መለየትን የመጨረሻ ፍርድ ያደረጉት:: ቁጥሩም ከሞት ፍርድ ጋር እኩል ነው:: አሁን ግን እድሜ ለማኅበር ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን መለየትን የድርጅት መጠቀሚያ አድርጎታል::

ከተባረርኩበት ጊዜ ጀምሮ ለተወሰነ ጊዜ በሐረር በናዝሬት በደብረ ብርሃን በአዲስ አበባ ተበትነው በነበሩት ወጣቶች ዘንድ በመገኘት መጽሐፍ ቅዱስ ለማስተማር እሞክር ነበር:: ነገር ግን ጥላ የሌለእው ተገን ወጣት ስለነበር ጉዟችንም እንደ ወጣትነታችን ነበር::
ይቀጥላል

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

መልእክቴ ይድረስህ!

Postby ትትና » Thu Oct 13, 2005 10:19 pm

ጊዜህንና ሰአትህን ወስደህ መልስ ስለሰጠህኝ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ::

1ኛ የብዕርሽ መአዛው የነሱን ይመስላል ላልከው:: በመሰረቱ አስቀድሜ እንደተናገርኩት እዚህ ማህበር ውስጥ አይደለሁም:: ብሆን ኖሮ ግን አንተ ስለምትጽፈው ነገር ማህበሩ መልስ ስለሚኖረው እሱን በደንብ አድርጌ እጽፍልህ ነበር:: አይደለሁም ማለቴ አንተ እንድታምነኝ ሳይሆን ስላልሆንኩ ነው ብሆን ኖሮ ግን አላፍርበትም ነበር::

2ኛ ስለፓትሪያሪክ ያልከውን አላውቅም ነበር የነዛ ሁሉ እህት ቤተክርስቲያናት ስምምነት መሆኑን:: አመሰግናለሁ ስለመልሱ

3ኛ ስልጣን ከእግዚአብሄር መሆኑን ሁላችንም የምንክደው አይመስለኝም:: በርግጥ ደርግንስ ኢሀዲግንስ ማን አስቀመጠው ላልከው በርግጥ ካለባለቤቱ(እግዚአብሄር) ማን ያስቀምጣል? እስቲ ልጠይቅህ ሳኦልን ማን ስልጣን ሰጠው? ንጉስ ዳዊትንስ? የግብጹን ፈርኦንንስ? ዮሴፍንስ በአህዛብ አገር ያነገሰ ማነው? ለጥፋትም ይሁን ለበጎ ስልጣንን የሚሰጠ እሱ ባለቤቱ ነው::

አንድ አባት ያሉትን ልንገርህ:-
ንጉስ ሲበድል ሰራዊት ይነሳዋል
ህዝብ ሲበድል መሪ ይነሳዋል
ካህን ሲበድል ሀገር ይጠፋል
የኛ ችግር ግን ከሁሉም ይመስለኛል::

4ኛ የኢትዮፕያ ቤተክርስቲያን ቀኖና ውስጥ አንዱ የሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ወደቤተ መቅደስ መግባት ነው ላልከው:: ምን አልባት አላነበብከው ከሆነ
ኦሪት ዘሌዋዊያን ም12 ቁ 1 ሙሉውን ብትመለከት የቤተክርስቲያኗ ቀኖና እንዳሆነ ትገነዘብ ይሆናል ኩፋሌ 4 ሙሉውን ብታነበው ደሞ ለጠቅላላ እውቀት ይሆንሀል::

5ኛ ስለመዝሙር መሳሪያ ላልከው ደሞ:: ኦርጋኑን በመጀመሪያውኑ ቅድስት ስላሴ ንጉሱን አግባብተው አስገባሁት ያሉት አባት አሁንም እዚህ ወደቤተክርስቲያን እንዲገባ ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ ያሉት አባት ናቸው:: እባክህ ከራሳቸው አንደበት የወጣውን ሌሎችም አባቶች የሚመሰክሩላቸው አባት ናቸውና የድሮዎቹን ያላደረጉትን ለምን ስማቸውን ታነሳለህ?

ስለመዝሙር መሳሪያ በቤተክርስቲያን ምንም አልተባ ለም ላስከው ደሞ እስቲ መዝሙረ ዳዊት 150 አንብበው::

በመጨረሻ የመዝሙር መሳሪያ ተለወጠ ብለው በስደት ያሉትን አባቶች ይረብሻሉ ላልከው:: በርግጥ አንተ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጅ ከሆንክ "መቋሚያው የአይጥ መምቻ ነው" የያሬዳዊው ዜማ ከሰማይ የተሰጠ ቢሆንም ብርሀን የሆነውን ለዚህ ላሉት ልጆች ህይወታቸው የሆነውን ኦርጋን መጠቀም አለብን ከማለት ሌላ ምን እንስማ? እንግዲህ ዋሸሽ በለኝ ባይኔ ያየሁትን:: አየር ለመቀየር ብለው መጥተው አባቶችን ቀይረው ያንን ሁሉ በስደት ያለ ወጣት ከቤተክርስቲያን አስወጥተው የሰደዱት እነማን ይሆኑ? የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው:: ከቤተክርስቲያን ልጆች ይልቅ ኦርጋን የተወደደበት ዘመን::

እስቲ አንድ ጥያቄ አባቶችህን ጠይቅልኝ:: ምነው እንዲህ የፒያኖው ፍቅር ከክርስቶስ ፍቅር በለጠባቸው?
ቅዳሴውንም በፒያኖ....

ግን አንተ አሁን የኚህን ሰው ታሪክ ከምትነግረን ምናለበት የምታውቀውን የእግዚአብሄር ቃል ካለህ ብታስተምረን እንዲህ መወቃቀሱም ምን ይረባናል:: ሁሉም ስለስራው ዋጋውን የሚያገኘው ከሰማይ አባታችን ነው:: ለማህበር ቅዱሳን የሚፈርድ እግዚአብሄር, ለነዚህም ተሰደዱ ተበደሉ ለምትላቸውም የሚፈርድ እግዚአብሄር:: ምናለ እኛ የሚረባውን ነገር ብናወራ::

ከመውጣቴ በፊት በጣም ይቅርታ የሚያስከፋ ነገር ከተናገርኩ እኔ እንኳን እንዲህ አይነት ፖለቲካ መናገር አልወድም ነበር አንተው ስላነሳህው ነው::

እግዚአብሄር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

እኛስ ምን አልን? እንደቃሉ መቀየር መታደስ ያለበት ሲበሰብስ አይደል?

Postby ዲጎኔ » Fri Oct 14, 2005 2:05 am

ደብረታቦር wrote:ሰላም ላንቺ/ተ ይሁን ትትና!


የዓሣ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ ትልቁ ቀኖና ቤተክርስቲያን ጥሰው "በወያኔነት" መንበረ ፓትርያርኩን ይዘው የቤተክርስቲያን ራስ በሆኑት አባ ጳውሎስ እየተመሩ ራስን "የቅዱሳን ማህበር" ብሎ ስይሞ ከሀሰት አባታቸው ከዲያብሎስ ያገኙት ነው::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

መልካሙን አባታችንን ለቀቅ የእናንተን አባ ሀና መሳዮቹን ጠበቅ ይሻላላል

Postby መስቀሉ » Fri Oct 14, 2005 2:20 am

[quote=

ኦርጋኑን በመጀመሪያውኑ ቅድስት ስላሴ ንጉሱን አግባብተው አስገባሁት ያሉት አባት አሁንም እዚህ ወደቤተክርስቲያን እንዲገባ ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ ያሉት አባት ናቸው:: እባክህ ከራሳቸው አንደበት የወጣውን ሌሎችም አባቶች የሚመሰክሩላቸው አባት ናቸውና የድሮዎቹን ያላደረጉትን ለምን ስማቸውን ታነሳለህ?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ

ውድ ወንድማችን ደብረታቦር ስለሰጠህን ወቅታዊ ምስክርነት አምላከ ኢትዮጵያ አምላከ እስራኤል ይባርክህ::እነዚህ ወጣቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን መሰባሰቡ ያቃጠላቸውን ናቅ አድርገህ አልፈህ ትምህርትህን ቀጥልልን::

ከቅድስት ስላሴ ጀምሮ ለቅድስት ቤተክርስቲያን መሻሻልና መጠናከር የሚተጉትን አባታችንን ያቆይልን

ይትባረክ አምላከ እስራኤል ወኢትዮጵያ
መስቀሉ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 675
Joined: Sat Sep 24, 2005 2:08 am
Location: ethiopia

ማስታወሻ

Postby ደብረታቦር » Fri Oct 14, 2005 2:27 pm

ማስታወሻ ለዲጎኒ!

ወዴት ወዴት ወሰድከው ባክህ? ምንም እንካን እድፋችንን በጠላቶቻችን ፊት መታጠብ አግባብ ባይሆንም በስም የቅዱሳኖች ማህበር ቁንጮ ላይ በውስጥ አርበኝነት ለተቅመጡት በታኞችና ከሳሾች የተዋህዶ እምነት ተቆርቋሪ መስለው የአዲስ አበባውን ሲኖዶስና "ብጹእ አባታቸውን" ጋሻና ጦር አድርገው የቢጽ ሀሳውያን ዓላማ በማራመድ ላይ ለሚገኙት መልስ ለመመለስ ተገድጄ እንጂ አንተ የምትለውን ፕሮቴስታንታዊ መንገድ ከምንም በላይ አጥብቄ አውግዘዋለሁ:: ልብ አድርግ የማወራው የነበረው የቤትክርስትያናን አስተዳደር በተመለከተ ነው አንተ ግን ወደ እምነት/ዶክትሪና ለመቅየር ሙክራ ባታረግ መልካም ነበር እና ወንድም ዓለም በመሀከላችን ትልቅ ገደል አለና ብትታረም ልቤ ይፈቅዳል:: እምነት አይታደስም ምናልባት በኃጢአት ከወድክ በንስሀ መታደስ ይቻላል እንጂ

ትትናዬ እስቲ ወደ ውይይት ከመግባታችን በፊት የቤት ስራ ልስጥሽና ከዛ በኃላ እንወያይ ማዘዝ ባይሆንብኝ ለነገሩ ከመስዋእት ብዛት ይልቅ መታዘዝ ይብልጣል ይላል መጽሐፉ አይደል?

የዘሌዋውያንን ነገር ስላመጣሽ ግንዛቤያችን እስቲ በቤትከርስቲያናችን አስተምሮ መሰረት ይፈተሽ
1. ዘሌ 11:39 የሞተ ሰውና የእንሰሳ በድን መንካት እንደ ርኩሰት ይቆጠር ነበር
2. ዘሌ 13:1-5 ለምጽ ያለበት ሰው እንደ ርኩሰት ይቆጠራል
3. ዘሌ15:1-18 በሰውነቱ ቁስልና ፈሳሽ ያለበት ሁሉ እርኩስ ነው
4. የወር አበባን በትመለከተ ያለውን እንዳለ እጽፍዋልሁ (የመርገም ወራት ነው የሚለው)
""ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋ ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን በመርገዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች የሚነካትም ሁሉ እርኩስ ነው የምትተኛበት የምትቅመጥበት ሁሉ እርኩስ ነው መኝታዋንም የሚንካ የምትቀምጥበትን የሚነካ ሁሉ እርኩስ ነው" ዘሌ 15:3-22
አሁን ይህንን በአዲስ ኪዳን ወይንም በወንጌል ስታይው በቤተ ክርስቲያንችን አስተምሮ መሰረት ግንዛቤሽ ምንድነው?
በነገራችን ላይ በብሉይ ኪዳን ሴቶች ብወር አበባቸው ወቅት ከቤት ወጥተው ለሰባት ቀናት ያህል በጎጆ ነበር የሚቆዩት የሚነኩት ሁሉ ስለሚረክስ::አሁንስ ይደርጋል እንዴ ካልሆነስ ዘሌውዋያን ላይ ስላለ ማድርጉ አስፈላጊ ይመስልሻል? የዘመናችን ቢጽ ሀሳውያን በሀመር መጽሄታቸው ሴቶች በወር አበባቸው ወቅት የጽሎት መጽሀፋቸውን እንካን እንዳይነኩ ነው ለአባላቱ የሚያስተምራቸው:; በክርስቶስ ደም ከተቀድሱ በኃላ
እህቶቻችን በወር ስባት ቀን ይረክሳሉ:: ይቅር ይበላቸው::
ሌላ ልጨምር ዘሌ 20:9 ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል
ዘሌ 20:11-21 ወንድም ሆነ ሴት በአመንዝራነት ቢገኙ ፈፅሞ እንደገደሉ"' ይህንንም እና ሌሎችም ካሉ ጨምረሽ መወያየት ይቻላል!
ውድ መስቀሉ! ወደ ትረካው እመለሳለሁኝ እግዘአብሔር ያክብርህ ስለ አስተያየትህ!

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

Postby ኤዶም* » Fri Oct 14, 2005 7:25 pm

ደብረ ታቦር እንደጳፈው/ችው

........ Regarding Kesis Melaku what else do you want to know? ከታላቁ ኦርቶዶክሳዊው አባት ከብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ ቀኖናውና የቅስና ማዐዕረጉን ተቀብሎ ልክ ዕንዳንተ የበደላትን ቤተክርስቲያን በንስሀ ታጥቦ በማገልግል ላይ ይገኛል ::ደብረታቦር ባንድ ወቅት በሌላ ርእስ ስለ ቀሲስ መላኩ እንዲህ ብለህ ነበር.....በተከታታይ ባቀረብከው የቀሲሱ ምስክርነት ደግሞ ከእናት ቤተ ክርስትያናቸው በግፍ በማህበረ ቅዱሳን እንደተባረሩ እንደተደበደቡ እንደሞቱ ነው የምትነግረን.......ታድያ እውነት በማህበረ ቅዱሳን አውጋዥነት በግፍ ተሰቃይተው ተባረው ከሆነ አሜሪካ ሲመጡ በአቡነ መልከ ጰዲቅ መሾምና መሸለም እንጂ በንስሀ መታጠብና ቀኖና መቀበልን ምን አመጣው? እንደተረክክልን ከሆነ ደግሞ በጊዜው አገር ቤት ውስጥ በነበሩበት ወቅት ከአባቶች የተማሩትን የሚያውቁትን እውቀት በቤተክርስትያናቸው ጥላ ስር ሆነው ለህዝብ ለማስተማር ደፋ ቀና ይሉ እንደነበር ነው ...እንዲያውም እንዳንተ አባባል በማህበረ ቅዱሳን ተወግዘውና ተጠልተው ሲባረሩ በቤተክህነት ግቢ ደጅ እየጠኑ ለቤተክርስትያናቸው ያላቸውን ታላቅ ፍቅር በትግስት ሲገልጱ በመጨረሻ በህይወታቸው ሲመጣ ካገር እንደወጡ ነው.....እና የኔ ጥያቄ 'የበደልዋትን ቤተ ክርስትያን በንስሀ ታጥበው በማገልገል ላይ ናቸው' ካልክ የግለሰቡ የቀድሞ ታሪክ ቤተክርስትያንን የሚበድል ነበር ማለት ይመስለኛል ይህ ከሆነ ደግሞ ይቃወሙዋቸው የነበሩት ማህበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስትያኒትዋ የሚቀኑ ነበሩ ማለት ያስችላል......እኔ የምትላቸውን ማህበረ ቅዱሳን አላውቃቸውም...እንደተባለው ሰው የሚገድሉ የሚደበድቡ ከሆነ ቅዱሳን የሚለው ስም አይገባቸውም.... እንዳንተ አባባል ቤተ ክርስትያኒትዋን ሲበድል የኖረ ሰው ቢቃወሙ ግን ወንጀል አይመስለኝም.......

p.s
እንደተለመደው ወያኔ ገለመሌ የሚለውን ስድብ መስማት አልፈልግም አገር ቤት ያሉት አባቶች ጉድፍ ጎልቶ እንደሚታይህ ሁሉ እዚህ በስደት ያሉትም አባቶች የራሳቸው የሆነ ድክመት ስላለባቸው መወቃቀሱ ቢቆይልን ጥሩ ነው
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

ካለፈው የቀጠለ

Postby ደብረታቦር » Mon Oct 17, 2005 7:57 am

ስውሩ አደጋ በቀሲስ መላኩ!

በዚያን ጊዜ ከቤተክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት የወጡትና በስተኍላም በአብዛኛው ወደ ፕሮቴስታንቶችና ልዩ ልዩ የስህተት ትምህርቶች የገቡ ወጣቶችን ታሪክ በዝርዝር ለማቅረብ ባልችልም በአጠቃላይ ግን በነበሩባቸው ማኅበራት ውስጥ የሚከተሉት ነገሮች ይታዩባቸው ነበር::
1. ግብታዊነት: እነዚህ ወጣቶች ከቤተ ክርስቲያን ሲባረሩ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር እልህ ውስጥ መግባታቸውን ነው እንጂ ከየት ወደ የት እንደሚሄዱ አያውቁም ነበር:: ያ ሁሉ ወጣት ተጎዳ:: ዛሬ እነዚያ ወጣቶች ማኅበረ ቅዱሳን ባሳረፈባቸው ዱላ ተመትተው በግብታዊነት ተጋዙ:: ለጥቂት ጊዜ ቢንገታገቱም አቅጣጫ የላቸውም ነበር:: በሐረር ያሉት ግሩማን በሆኑ አባቶች ከለላ ስላገኙ የተረፉት ባለፈው ጊዜ በፍርድ ቤት በተፈረደላቸው ፍርድ መሰረት ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው ተመልሰዋል:: አብዛኛዎቹ ግን በፍርድ ቤቱ የሰባት ዓመት ሂደት ወቅት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ብሎ ራሱን ለሰየመው የናዝሬት ፕሮቴስታንት ድርጅት ቅርንጫፍ ሆኑ::
ከናዝሬት ቅድስት ማርያም የወጡት ለትወሰነ ጊዜ በቀበሌ አዳራሽ ነበሩ:: አንድ ወዳጄ እንዳስቀመጠው
ክሁሉ የሚገርመው ግን በወቅቱ የነበሩት የቤተ ክህነት ሰዎች ሥራ ነበር:: ቁጥራቸው ከአምስት እስከ ስምንት ሺህ የሚደርሱትን እነዚህ ወጣቶች መክሮ ገሥጾ አስተምሮ በፍቅር በእርጋታ እንደመመለስ ያደርጉት ነገር ቢኖር ኦርቶዶክስ አይደለንም ብላችሁ ፈርሙልን ብላችሁ ፈርሙልን ብለው አስተዳደሩ ላይ እነዚያን ወጣቶች መክስሳቸው ነበር:: ይህ ሁኔታ ወጣቶቹን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመራት ያደቡ ለነበሩት በር ከፈተላቸው::

ይቀጥላል
ትትናዬ! ለውይይቱ መልስሽን እየጠብክሽ ነው::
ኤዶም! ጥያቄሽን ትረካው ይመልሳል(ቀሲስ ቤ/ክን በልህ የበደሉት ""የቅዱሳን ማህበር"" ሰለባ ከመሆናቸው በኍላ የሆነ ነው) ወያኔ አትበላቸው ስላልሽው ነገር ይሔ ትረክ በሚቀጥለው ጽሁፌ ስለሚጠቃለል የወያኔ የማህበረ ቅዱሳን ጋብቻ በተመለከተ እመልስበታለሁ::

ይትባረክ አምላክ አበዊነ
ደብረታቦር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Aug 01, 2005 10:49 am
Location: united states

ይድረስ

Postby ትትና » Mon Oct 17, 2005 9:32 am

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

በመጀመሪያ አክብረህ ስለመለስክልኝ እግዚአብሄር ያክብርልኝ!! ሲቀጥል ደሞ ለመልሱ በመዘግየቶ ይቅርታ እጠይቃለሁ::

እኔ ምንም እውቀት የሌለኝ ለጠየከኝ ጥያቄ በቂ መልስ የሌለኝ እንደሆንኩ አውቀዋለሁ! እግዚአብሄር መንፈስቅዱስ ባወቀ ግን ለአባቶቻችን የገለጠላቸው ሚስጥር ቤተክርስቲያናችንን የእውቀት ባለቤት እንዳደረገቻት አምናለሁ::
ቤተክርስቲያናችን ብሉይን ከሀዲስ አስማምታ ለሁሉ መልስ ሰጥታ ልጆቿ ግራ ሳይጋቡባት የምታሳድግ; እሷ ሳትሆን ሁሌም ልጆቿን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ህይወታችንን እየለወጠች (እያደሰች) የኖረች የምትኖር ናት:: ለዚህም እግዚአብሄር ይመስገን!!!

ከፍ ብዮ እንዳልኩት ጌታችን ኦሪትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ ባለው ምክንያት ብሉይን ከሀዲስ አስማምታ ያቀረበችልን ቤተክርስቲያን እንደውቂያኖስ የሰፋ እውቀት ቢኖራትም እኔ ደካማዋ ግን ቅንጣት ታክል እንኳን በማይሆን እውቀቴ ጥያቄህን ለመመለስ እሞክራለሁ ከተሳሳትኩ ወንድም እህቶቼ የቤተክርስቲያን ልጆች እንደሚረዱኝ በመተማመን::

1 ዘሌ 11;39 ስለ በድን (የሞተ) መብላት እንዲሁም መንካት ነው የሚናገረው::
:- በመሰረቱ አሁንም ቢሆን በቤተክርስቲያናችን የሞተ ነገር መብላት እርኩሰት ነው አሁንም:: በአገራችን ከብት የታመመባቸው ሰዎች ከመሞቱ በፊት ባርከውት ሰዉ የከብቱን ባለቤት ለመርዳት ያህል ስጋውን ተከፋፍለው የቻሉትን ያህል ብር እንደሚሰጡት አውቃለሁ:: የሞተ ነገር ከነስሙ እንዳውም (በክት) ነው የሚባለው አይበላም ጸያፍ ነው ወጥቶም ይጣላል::

2 ዘሌ 13:1-5 በአጠቃላይ ለምጽ ስለሚወጣበት ሰው ነው የሚያስተምረው::
በብሉይ ለምጽ የነፍስ ደዌ ምልክት ነበር በአዲስ ኪዳን ግን የስጋ ደዌ እንደሆነ ነው ቤተክርስቲያናችን የምታምነው:: ሱራፌል የነብዮ ኢሳያስን የከንፈሩን ለምጽ በጉጠት እሳት ተኩሰው ሳይጠየፉ እንዳስለቀቁትም አይተናል:: ወንጌል የይቅርታ የንሰሀ ጊዜናትና ሀጢያታችን በፊታችን በግንባራችን አይወጣም::

3ኛና 4ኛ ዘሌ 15:1-18ና 3-22 በአጠቃላይ ስለ ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ ነው የሚናገረው::
:- ከሰውነት ከሚወጡት ፈሳሾች ውስጥ ለምሳሌ እንደወር አበባ እና በብዛት በወንዶች ደሞ (ዝንየት) የሚባለው በሚታይበት ጊዜ አሁንም ቢሆን የተወሰኑ ቀናቶች ወደቤተክርስቲያን አይመጣም ከነዛ ቀናቶችም በኃላ ታጥቦ ንጹህ ሆኖ ነው የሚመጣው::

5ኛ ዘሌ 20:9 አባትና እናት ስለመስደብ
:- ክፉን በክፉ አትቃወሙ በሚለው የጌታችን ቃል መሰረት ቤተክርስቲያናችን በይቅርታ መመለስን በንስሀ መንጻትን ታስተምረናለች:: ከአስርቱ ትእዛዛት ውስጥም በመሆኑ እናትና አባት እንዲከበሩ አጥብቃ ታስጠነቅቃለች በንስሀ በይቅርታ የማይመለሰው ከርስቱ ይለይ/ይወገዝም ስትል ታሳስባለች::

6ኛ ዜሌ 20:11-21 ስለዝሙት::
:- በአጠቃላይ ሰው ከሚስቱ በቀር ወደሌላ የሄደ እንዳውም ያሰበ አመነዘረ ነው::
:-እንዲሁም ከ7ቤት በኃላ ነው ጋብቻን የምትፈቅደው እንኳን እንዲህ አንድጊዜ የተዛመዱትን ቀርቶ::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ትትና » Mon Oct 17, 2005 10:13 am

ሳልጨርስ የላኩት ሳይበር እንዳያጠፋብኝ በመስጋት ነው::

በመጨረሻም በአዲስ ኪዳን የምህረት የይቅርታ የንስሀ ጊዜ በመሆኑ የዘሞተውንም, የገደለውንም በሀጢያት የቆሸሸውንም በንስሀ እንዲታጠብ አጥብቃ ቤተክርስቲያናችን ታስተምረናለች::

መልሴ አጥጋቢ እንደማይሆንልህ አውቃለሁ እስቲ ደሞ ከሌሎች የተሻለውን እንጠብቅ::

ግን ማለት የምፈልገው ነገር አለ:: እነዚህ ሁሉ የምናወራቸው ስርአቶች ናቸው:: ስራቶች ደሞ አምልኮታችንን የአክብሮት የፍቅር መሆኑን እንዲያጠነክሩልን የምንጠቀምባቸው ናቸው:: እኔ በወር አንድ ጊዜ ቤተክርስቲያን አለመግባቴ እግዚአብሄርን ለማክበር ከሆነልኝ እሱ በጎ አስቤ እንዳደረክት ይቀበልልኛል ማለት ነው:: በርግጥ እኔን አላዋቂ የሚያስብለኝ ነገር አለ? ወይም ሀጢያት ይሆንብኛል መግባት እንኳን ብችልና ባልገባ?

የሚበላ የማይበላውን አይንቀፈው የማይበላ የሚበላውን እንደተባለ:: ምናለ ብንቷቷው?

ሁለተኛ:- በስርአት ምክንያት ስንነቃቀፍ የክርስትና ሒወቱን ሳንኖርበት እያለፈብን እንደሆነ አይሰማህም? እኔ እንደዛ ነው የሚሰማኝ::

ሦስተኛ:- ዳቢሎስ ምዕመናን አብረውት እንዲጠፉ ስለሚፈልግ ከቤተክርስቲያን አሳዶ ማውጣት ነውና አላማው:: በፊት ኦርቶዶክሶች መጽሀፍ ቁዱሱን አያውቁትም ብሎ ቢነሳ ቤተክርስቲያን መልሷን አዘጋጀች:: ቀጠለና ቤተክርስቲያን አረጀች ብሎ ለምድ ለብሶ ተነሳ በሱም ሰራዊቶቹ ተጋለጡና ከቤተክርስቲያን ወጡ:: አሁን ደሞ መሪዎቹ ላይ መጣ መሪዎቹ ከተያዙ በጎቹን ቀላል ነው ብሎ እግዚአብሄር ይመስገን አሁንም ተነቃበት:: ደሞ የሚቀጥለው ምን ይሆን? ለማንኛውም ቤተክርስቲያናችን አትጠፋም አትለወጥም:: የሚወጡት ወጥተው ወደአዳራሻቸው እስኪሄዱ መደፍረስ ቢኖርም ሁሉ ለበጎ ነው!

በመጨረሻ:- እስካሁን ድረስ እኔ አውቃለሁ እነሱ አያውቁም ብሎ መከራከርን ትተን እከሌ በደለ እከሌ ተበደለ የሚለውንም ንቀን የተሻለውን ብንነጋገር እንዴት ጸጋው በበዛልን ነበር::
ለምሳሌ:- አይሁድ ጌታን ከሰቀሉት በኃላ እነዛ ሁለት ሰዎች የጌታን መከራ እያወሩ በመንገዳቸው ሲሄዱ በመካከላቸው ጌታቸው ነበር አይናቸው ስላልተከፈተ ግን አላዩትም:: አሁንም የሚያጸድቀንን ትተን እስከመቼ እንደምንነቃቀፍ አልገባኝም::
ሁላችንም በስተመጨረሻ ለመጽደቅ ከሆነ አካሄዳችን የአባታችን ቤት እንደሆን ሰፊ ነው ምን አለ አንዱ ሀይማኖት ሌላውን እምነታቸውን መልካም አድርጎ ይቀበልላቸው ብሎ ጥሩ ነበር መመኜት ቢኖረን?


እግዚአብሄር በአምልኮት ያጽናን!
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

ፕሌቶ ሌላ ክርስቶስ ሌላ

Postby ermiasabe » Fri Oct 28, 2005 12:19 pm

ውድ ትትና

አንቺ እንዳልሽው የእግዚአብሄር መንግስት የምትውረስ በትህትናና በየዋሃት እንጂ እንደነ ዲጎኔ አይነት ተመፃዳቂዎች እንደሚያስቡት በፍልስፍና አይደለም:: እነዚህ ግለሰቦች ወደ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ፀጉር ስንጠቃ ገብተው ቤተክርስቲያንን ወደ ጥፋት ህዝቡን ወደ መበተን የሚመሩ ሆነዋል:: Stoics ይባሉ እንደነበሩ ፈላስፎች ነገርን ሁሉ በአመክንዮ እንመራዋለን ስላሉ የክርስቶስን መንገድ ስተውታል:: ቤተክርስቲያንን አሜሪካ ባዩአቸው ቤተአምልኮቶች አይነት ሊያደራጁ ነው ትጋታቸው:: በቅርቡ "ለሴቶች ክህነት ብንሰጥ ግብረ ሰዶማውያንንስ ብናጋባ ምን እለበት' እንደሚሉ አትጠርጥሪ::
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

በጣም በጣም ታሳዝናላቹህ

Postby ጃንሚዳ » Fri Oct 28, 2005 3:14 pm

ሰላም ወንድሞቼ '''''እውነተኛ የቤተ/ክርስቲያናችን ልጆች ከሆናቹ ክርክራችሁን በግል ብትጻጻፉ መልካም ነው'''''ውሳኔ ላይም ስትደርሱ ለህዝብ ማቅረብ ትችላላቹ'''''የሚያሳዝነው ግን በናንተ ክርክር ስንቶች የዋህ የቤተክርስቲያናችን ልጆችን ዓታጠራጥሩ''''''ማንም ከነኝህ ታናናሾች የሚያስት ቢኖር አንገቱ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ታስሮ ወደባህር ቢጣል ይሻለዋል የሚለውን''''ቅዱሱን ቃል አስቡበትና ውይይታቹ በግል ብትጻጻፉ መልካም ነው''''ይህ መልዕክቴ ለማከብራቹ ወንድሞቼ ለናታንና ለደብረታቡር ትድረስ ''''''በዚህ አጋጣሚ እንደነ ዳጎኒ አይነት ሐሰተኛ የጴንጤ ጀሌ እግዛብሔር አምላክ በናንተ ላይ የሚሰራውን የዘንዶውን ወይንም የቀደመውን እባብ ተንኮል በግርማ መለኮቱ ከቤተክርስቲያናችን ያርቅልን::
ሰላመ እግዛብሔር ይብዛላቹ
ጃንሚዳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 414
Joined: Tue Apr 06, 2004 10:19 am
Location: sao tome and principe

ጃንሜዳው በጭፈራ ታቦት ዙርያ መሳከሪያ እና ermiasabel ከማውገዝ ሀይማኖታችሁን መርምሩ!

Postby ዲጎኔ » Fri Oct 28, 2005 5:14 pm

የክርስቶስ የዋሀት መንፈስ ይምጣልን

እናንተ ሰዎች አሁን የእኔን ስም ጠርታችሁ ካልገዘታችሁ እንቅልፍ የላችሁም? የቀጠለው ርእስ በእራሳችሁ ወገንተኛ የቀረበ የጳጳሳችሁን ቅሌት ቀናውን የሀይማኖት አበውን ስብሰባ አጨናግፎ በቅጥረኛ ዲያቆናቱ ጩቤ አስታጥቆ የሰው ደም አስፈስሶ ፋይሉ በአባታችሁ ተጋዳላይ ጳውሎስ ደብዳቤ በአቃቤ ህግ ፋይሉ የተዘጋውን ለማዘናጋት ወደእኔ ስድባችሁ ተመለሳችሁ?

የድሬደዋውን የኢስቡላ-አክራሪ አይነት ጭፍጨፋና ግድያ በቅርብና በአካል የማውቅ ስሆን እናንተ እንደምትከሱኝ ሳይሆን አሁንም ወደእውነተናይቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን እምነትና ስርአት እንመለስ ነው የምለው:ያላልኩትን መጨማማርና ማወላገድ የአባታችሁ ስራ ነውና አይደንቀኝም!

አሁን የተረዳሁት ደግሞ ተሀድሶ ብዙ መልኩ እንዳለው:በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እነሉተር የጀመሩትን በመጻረረ ጄስዊት የሚባሉት ያካሄዱትን በትምህርተ-መለኮት ልዩነት የሌለውና መሰረታዊ የሆነው ደግሞ ክርስቶስን ብቻውን ያለውን ብቻ እናምልክ እንከተል የሚሉ መኖሩን ሲሆን በዚህኛው ሙሉ በሙሉ የምስማማ በጥገና ተሀድሶ ተመልሼ "መርቆሬዎስ ተሰቀለልኝ ጸሎቴን ይሰማል'እያልኩ በማይገባኝ ግእዝ የማይገባኝን አላመልክም!!!

ግብረ ሰዶምና የሴት ቀሳውስት መቀበሉን ግን እንደነፍስ አባታችሁ አባ ሀና እና የተፈራ በለው ግጥምጥም ስምም እናንተው ቀጥሉበት እንጂ እኛ አሁንም እንደጌታችን የሀጢአተኛው ወዳጅ የሀጥያትና የደብተራ ባለውቃቢ መናፍስትግን ጸር ነን::

"የመላእክትን አምልኮእየወደደ ባላየውም ያለፈቃድ እየገባ በስጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ"(ቆላስይስ 2:18)

ዲጎኔ-ከጃንሆይሜዳ ከመሳከሪያው ማዶ ተሀድሶ አምባ

quote="ermiasabe"]ውድ ትትና

በትህትናና በየዋሃት እንጂ እንደነ ዲጎኔ አይነት ተመፃዳቂዎች እንደሚያስቡት በፍልስፍና አይደለም:: እነዚህ ግለሰቦች
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests