በጣም የወደድኩት አዲስ የአማርኛ ግጥም ዌብሳይት

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ውበት አድናቂ » Tue Oct 11, 2005 4:21 pm

ምንም አይደል; ደስ ብሎኛል ስለወደድከው
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

Postby Rick Rider » Thu Oct 13, 2005 9:36 pm

ውቢት: የእሁዱን VOA አማርኛ ፕሮግራም ብታዳምጪ የመጽሀፉ ደራሲ ኢንተርቪው አለ..........በጣም ቆንጆ ኢንተርቪው ነው በኢንተርኔት አዳምጪው;; እኔም መጽሀፉን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው
Rick Rider
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 73
Joined: Fri Aug 27, 2004 6:44 pm
Location: Monaco

Postby ውበት አድናቂ » Fri Oct 14, 2005 6:02 pm

Rick Rider wrote:ውቢት: የእሁዱን VOA አማርኛ ፕሮግራም ብታዳምጪ የመጽሀፉ ደራሲ ኢንተርቪው አለ..........በጣም ቆንጆ ኢንተርቪው ነው በኢንተርኔት አዳምጪው;; እኔም መጽሀፉን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው


አመሰግናለው ሪክሪድር..........አዳምጠዋለው
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

Postby ውበት አድናቂ » Tue Oct 18, 2005 9:45 pm

Rick Rider wrote:ውቢት: የእሁዱን VOA አማርኛ ፕሮግራም ብታዳምጪ የመጽሀፉ ደራሲ ኢንተርቪው አለ..........በጣም ቆንጆ ኢንተርቪው ነው በኢንተርኔት አዳምጪው;; እኔም መጽሀፉን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው


ኢንትርቪ ያልከውን ላገኘው አልቻልኩም;;;;እምቢ አለኝ.........ለምን?
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

Postby Rick Rider » Fri Oct 21, 2005 1:38 pm

ውበት አድናቂ wrote:ኢንትርቪ ያልከውን ላገኘው አልቻልኩም;;;;እምቢ አለኝ.........ለምን?

አንስተውታል ማለት ነው እኔም እምቢ አለኝ
Rick Rider
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 73
Joined: Fri Aug 27, 2004 6:44 pm
Location: Monaco

Postby ወደ ዋርካ ገባ » Tue Oct 25, 2005 3:14 pm

Rick Rider wrote:
ውበት አድናቂ wrote:ኢንትርቪ ያልከውን ላገኘው አልቻልኩም;;;;እምቢ አለኝ.........ለምን?

አንስተውታል ማለት ነው እኔም እምቢ አለኝ


ውበት አድናቂና Rick Rider............የእሁዱን VOA ብታዳምጡት ሁለተኛውን ክፍል ኢንተርቪው ማዳመጥ ትችላላችሁ...........እኔ ፈተናን እያነበብኩት ነው አሁን ገና አልጨረስኩትም ግን እስካሁን እንዳየሁት ድንቅ ስራ ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! አሪፍ ጸሀፊ ነው አቦ!!!!!!!!!!!!! ስንት ጊዜዬ እንደዚህ አሪፍ የግጥም መጽሀፍ ካነበብኩ!!!!!!!!! ቴዲ አሻረኝ ነው የሚባለው!!!!!! አቦ ይመቸው!!!!!!!!!!!!!
ወደ ዋርካ ገባ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Tue Nov 23, 2004 11:11 pm
Location: united states

Postby ውበት አድናቂ » Thu Oct 27, 2005 1:45 pm

ወደ ዋርካ ገባ........አመስግንሀለሁ;;;;;; አዳምጠዋለሁኝ እምቢ ካላለኝ
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

Postby Rick Rider » Fri Oct 28, 2005 1:57 pm

ወደዋርካገባ እኔም ላመሰግንህ እፈልጋለሁ. ቆንጆ ኢንተርቪው ነው
Rick Rider
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 73
Joined: Fri Aug 27, 2004 6:44 pm
Location: Monaco

Postby ወደ ዋርካ ገባ » Fri Oct 28, 2005 10:24 pm

እረ ምንም አይደል!!!!!!! ይመቻችሁ!!!!!!!!!!!
ወደ ዋርካ ገባ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Tue Nov 23, 2004 11:11 pm
Location: united states

Re: በጣም የወደድኩት አዲስ የአማርኛ ግጥም ዌብሳይት

Postby ወሎ ሠፈር » Tue Nov 01, 2005 10:48 pm

ውበት አድናቂ wrote:እናንተዬ: ሌላ የኢትዮጵያውያን ፎረም ላይ የሆነ ዌብሳይት ተመልክቼ በጣም ስለወደድኩት ለእናንተም ላካፍላችሁ:: አይታችሁት ከሆነ በጣም ይቅርታ ካልሆነ ግን http://tewodros.com ሂዱና ተመልከቱት::

ውቢቱ


ውበት አድናቂና ሌሎችም የቴዎድሮስን የግጥም ሥራዎች የምትወዱ ሁሉ:

መጽሀፉን አግኝቼ ትናንትና አንብቤው ጨረስኩ:: ዛሬ ወያኔ የኢትዮጵያን ንጹሀን እየጨፈጨፈ ባለበት ሰአት "ፈተና" ውስጥ የሚከተለውን ግጥም ስላገኘሁና ወቅታዊ ስለመሰለኝ መጽሀፉን አግኝተው ላላነበቡ ሁሉ ከታች አስቀምጨዋለሁ:: የመጽሀፉ ደራሲ እንደማይቀየመኝ ተስፋ አለኝ:: ግጥሙ ልቤን ስለነካኝ ነው ለማካፈል የፈለግሁት::

"እንባሽ ደርሶናል እንባችንን ተቀበይን"
("ፈተና" በሚል ርእስ ከታተመው የቴዎድሮስ አበበ የግጥም መጽሀፍ ውስጥ ገጽ 136 ላይ ያገኘሁትና ልቤን የነካኝ ግጥም)

ለምን አታለቅስ?
ለምን አታነባ?
ተስፋዋ ሲቀጠፍባት ወደ መቃብር ሲገባ
ለምን አታነባ?
ኢትዮጵያ?
ለምንስ ቅስሟ አይሰበር?
በመሪር ሀዘን ተሸንፋ
የዐይኗ ተስፋ የሆነው ወጣት ትውልዷ ሲጠፋ?
ለምን አትከፋ?
እንዴት ጭንቀት አይውጣት ዕንባዋንስ ምን ሊገደው?
የአምባገነን የግፍ ጥይት ተስፋዋን ሲደበድበው?
ለምን አታለቅስ?
ለምንስ አትከፋ?
የገነጠላት ባንዳ ዳግም ተስፋዋን ሲያጠፋ?
ምነው አይከፋት?
ሀዘኗ አይከብድባት
የፈነጠቀውን የድል ብርሀን ወያኔ ሲያጨልምባት
ማሕጸኗን ሲያመክንባት
ድምጿን ሲያፍንባት
ልጆቿን ሲገድልባት
ምነው አይከፋት ለምንስ አታነባ?
ተስፋዋ ሲቀጠፍባት ወደ መቃብር ሲገባ
ኢትዮጵያ
ለምን አታነባ?
ለምን አናነባ?

(ከላይ ያካፈልኳችሁ ግጥም ፈተና በሚል ርእስ በቅርቡ ከታተመው የቴዎድሮስ አበበ መጽሀፍ ውስጥ ያገኘሁትና ልቤን የነካኝ ግጥም ነው:: በተለይ ለዚህች የሀዘን ቀን አግባብነት ስላላት ነው እንዳለ የገለበጥኳት:: የመጽሀፉ ደራሲ ስሜቴን እንደሚረዳ ተስፋ አለኝ ያለፈቃድ እዚህ ስላሰፈርኳት:: ታይፕ ሳደርግ ተሳስቼም ከሆነ ይቅርታ)

ደረጀ
ወሎ ሠፈር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Feb 25, 2004 2:51 pm

Postby Rick Rider » Tue Nov 08, 2005 11:11 pm

እኔ በግጥሙ አልስማማም!!!!!!!! የምን ማልቀስ ነው እሱ????!!!!!!! ወያኔ ንጹሆቹን ወገኖቻችንን በጭካኔ እንደገደለ ከነደጋፊዎቹ በሙሉ ለራሳቸው የሚያለቅሱበት ቀን ሩቅ አይደለም!!!!!!!!! አይዞን!!!!!!!!!!!!!!!!! የምን ማልቀስ ነው!!!!!!!! ለወያኔ ይለቀስለት!!!!!!!!!!!!!
Rick Rider
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 73
Joined: Fri Aug 27, 2004 6:44 pm
Location: Monaco

Postby ወሎ ሠፈር » Wed Nov 09, 2005 6:21 pm

Rick Rider wrote:እኔ በግጥሙ አልስማማም!!!!!!!! የምን ማልቀስ ነው እሱ????!!!!!!! ወያኔ ንጹሆቹን ወገኖቻችንን በጭካኔ እንደገደለ ከነደጋፊዎቹ በሙሉ ለራሳቸው የሚያለቅሱበት ቀን ሩቅ አይደለም!!!!!!!!! አይዞን!!!!!!!!!!!!!!!!! የምን ማልቀስ ነው!!!!!!!! ለወያኔ ይለቀስለት!!!!!!!!!!!!!


ወንድሜ ሪክ: በምትለው ሁሉ እስማማለሁ:: እኔ እንኳን የቴዎድሮስ ግጥም ሀዘኔን በሚገባ ስለገለጸልኝ ላካፍላችሁ ብዬ ነበር እዚህ አምጥቼ የገለበጥኩት እንጂ አንተ እንዳልከው ወያኔ ድራሹ እስኪጠፋ ድረስ እረፍት የሚባል ነገር አያስፈልገንም:: ገጣሚው በግጥሙ ውስጥ ያሰፈራቸውን ቁምነገሮችና የግጥሙን ውበት እንዳደነቅሁ ሁሉ ያንተንም ኢትዮጵያዊ ቆራጥነት በእጅጉ አደንቃለሁ::
ወሎ ሠፈር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Feb 25, 2004 2:51 pm

Postby ውበት አድናቂ » Thu Nov 10, 2005 5:08 pm

ሪክ ሪደርና ወሎ ሰፈር...............ሁለታቹም በምትሉት እስማማለሁኝ ግን ይሄ ቦታው ስላልሆነ ለምን ዋርካ ፖለቲካ መድረክ ላይ አንገናኝም????????? እወዳቹዋለሁ
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

Postby ላቀው » Thu Nov 10, 2005 5:29 pm

"" ለስራ ወሰን አለው ለፍላጎት ግን የለውም""
ላቀው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Dec 02, 2004 10:20 am
Location: united states

Postby ውበት አድናቂ » Thu Nov 10, 2005 5:53 pm

ላቀው wrote:"" ለስራ ወሰን አለው ለፍላጎት ግን የለውም""


ላቀው በፍጹም አልገባኝም!!!!! መልስህ ለኔ ከሆነ ማለቴ ነው
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest