00

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

00

Postby ARERU » Mon Oct 17, 2005 3:49 pm

00
Last edited by ARERU on Sat Nov 19, 2011 12:20 am, edited 1 time in total.
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው:በአፍሪቃ ቁ.2

Postby ARERU » Mon Oct 17, 2005 5:39 pm

የቀጠለ:-

የመጀመርያ ስደት::

ስምህ ማን ይባላል ስሜን ተናገርኩኝ
እድሜህስ ስንት ነው እድሜየን መለስኩኝ
ሀገሬ ኢትዮጵያ የመከራ መንደር
እናቴን አባቴን እህት ወንድሞቸን ተናገርኩ በዝርዝር
ምን አመጣህ አለኝ አዘለለህ ሀገር
እኔም አስረዳሁት ያም ሳይቀር ያም ሳይቀር
ስላልቻለ ሆዴ ደም እያየ መኖር
ጣር ሲወራወሩ ላንዱ ላለማበር
ገላጋይ በለለው በወንድሞች ጠብ ውስጥ
አይኔ እያስተዋለ ስላልቻልኩ መቀመጥ
ልገላግል አቅም ልቆጣ ውይ ጉልበት
እንደለለኝ ሳውቀው ዝም ብሎ ከማየት
ይብቃኝ ብየ ወጣሁ ምን ይደረግ ታድያ
እስኪ አንተው ንገረኝ እሚያሻሽል ነገር ካለ ማቃለያ
እሱም ሊከራከር ብዙ ሞካከረ
የጥያቄ መአት ብዙ ወረወረ
እምቢ አልኩት አልሄድም እምቢ አልመለስም
ለወንድሜ አብሬ ወንድሜን አልገልም
ወይ ሲጨፋጨፉ ተመልካች አልሆንም
ወይ መረጋገጫ እሳር ሆኘ አልቀርም
መፍትሄው ይሄ ነው እራቅ ብሎ ማየት
እንደ በግ ባሞሌ ልሶ ከመጎተት
ወይም እንደውሻ ያዝ ብለው እንዳሉት
ስጋ ባየሁ ቁጥር ጀራቴን ከመቁላት
አንገቴን ደፍቸ መኖር የመረጥኩት
አልቻለም ተቆጣ ብዙ ሞካከረ
ወዲህ ወዲያ እያለ ጎዋዶቹን መከረ
አንተ እዚህ እንድትኖር ለመፍረድ ይከብዳል
ወይም ለማስመለስ በጣም ይቸግራል
ዛሬ እንተውና ነገ በሌላ ቀን
እኛም አጢነነው አለቃም አማክረን
ውሳኔውን ይዘን እንመጣልሀለን
ብለው ሰጡኝና ብስኩት የሚበላ
እንዲሁም ብርድ ልብስ ኬንዳንም ለጥላ
ተሰነባበትን አይዞህ አትፍራ አሉኝ
ፈትለክ ፈትለክ አሉ ለኔ ሰው ሰጥተውኝ
ያ ሰው እየመራ እኔ እየተከተልኩ
በጣም ከሚያስገርም ጉድ ውስጥ ጥልቅ አልኩ
የህጻኑ ብዛት ሽማግለው ወጣት
አንዱ ካንዱ አይለይ ወይ እንዲህ መገርጣት
የመቶው የትኛው ወይስ ያንድ አመቱ
ሁሉም ሸምግለዋል ቀረበዋል ለሞቱ
እሪታው ብዙ እለቅሶና ዋይታው
አቃሳቹም እንዲሁ ደክሞት ሚያንኮራፋው
ያካባቢው ሽታ የዝንቡ ግርግር
እንኩዋን ለአዳም ልጅ ለምስለ እግዚአብሄር
ምላሽ አይሆነውም ለዳቢሎስ ብድር
የተቀዳደደ ቡቱቶ ለባሹን
እርቃኑን የቆመው ልብስ አጥቶ ጭራሹን
ጎኑ የሚቆጠር አጥንቱ አንድ ሁለት
ወይ የተጽዳዳው በተጋደመበት
መሬት የሚጭረው አንገቱን ደፋ አርጎ
ወይም ጭልጥ ያለው ባሳብ ውስጥ ተመርጎ
ደስታ የለለበት የሰይጣኖች ቤት
ሮሮና ለቅሶ ባንድ የሚሰማበት
የምድሪቱን ጋነም ባይኔ ዛሬ አየሁዋት::

ይቀጥላል:-
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው በአፍሪቃ

Postby ሰላም ኢትዮጲያ » Tue Oct 18, 2005 3:07 pm

ሰላም እንደምን አላችሁ?

ከላይ ወንድሜ አረሩ ስደተኛው በአፍሪቃ በሚል ርዕስ ስር የፃፈውን አየሁና እኔም የበኩሌን ለማለት ወደድኩ:: ግን ለምንድን ነው ብዙዎቻችን የምንሰደደው ወይም የተሰደድነው? መልሱ ግልፅ ነው:: የተሻለ ነገር ፍለጋ...አገራችን ጥሩ ኢኮኖሚ ስለሌላት...ስራ ማግኘት ከባድ ስለሆነ ቢገኝም ደህና ገንዘብ ስለማይከፈለን...በትምህርት ጥሩ መሠረት (background) ስለሌለን...ብቻ ብዙ ምክንያት መስጠት ይቻላል:: እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት የምዕራቡን አለም ወደን እና ነጭ ለማየት ብለን አይመስለኝም:: እኔ በበኩሌ ያንን ብዬ አልወጣሁም የወጣሁበት ዋናው ምክንያት የተሻለ ነገር በመፈለጌ ነው:: አዎ ይህንን ብዬ ነው::

ለተወሰነ ጊዜ በኬንያ ናይሮቢ ኖሬያለሁ:: እናም ብዙ ነገሮችን ለማየትና ለመታዘብም በቅቻለሁ:: በዚህ አጋጣሚ ከሀገራችሁ በቀጥታ ሌላ ሶስተኛ ሀገር ሳትረግጡ ወድ አለማችሁበት ቦታ መሄድ የቻላችሁ ስዎች ጥሩ እንደገጠማችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ:: አውቃለሁ እዛም ችግር ሊገጥማችሁ ይችል ይሆናል ሆኖም ግን ስደት ለዛውም በ አፍሪካቃ እጅግ ከባድ ነው::

ናይሮቢ ውስጥ የሚገኙውን ኢትዮጲያውያን እና ኤርትራዊያን ብዛት መጀመሪያ ሳይ በጣም ደንቆኝ ነበር:: ኬንያ ጎረቤት ሀገር በመሆኗ ወይም ደግሞ ለ ካናዳ እና አሜሪካ ፕሮሰስ አመቺ በመሆኑ ይመስለኛል ብዙ ሰው ወደዛ የሚያመራው:: ወደ ስደተኛው ስንመጣ ብዙ አይነት ስደተኛ አለ:: ግማሹ ከላይ እንደጠከስኩት የ ካናዳ እና አሜሪካ እንዲሁም አውስትራሊያ ወረቀት አስገብቶ መልሱን እየጠበቀ የሚገኝ..ሌላው ደግሞ በዘመኑ አጠራር ሊያስጨድድ የመጣ (ጨደዳ እንግዲህ በዛ ያለ ገንዘብ ተከፍሎ ወደ ተለያዩ ሀገራት መውጣት የሚቻልበት መንገድ ማለት ነው) ሌላው ለፕሮሰስ ከቤተሠብ የተላከለትን ገንዘብ ጨርሶ ወደ ሀገር ቤት መመለስ አሣፍሮት እዛው ቁጭ ያለ ወ.ዘ.ተ.... በናይሮቢ ስደት ከባድ ነው ምክንያቱም ስደተኛነቱ ከሚያደርሰው ተጸዕኖ በትጨማሪ ሁሉም ስደተኛ ስራ የሌለው መሆኑ ነው:: ልስራም ቢል አይችልም:: ጥቂት ኢትዮጲያውያን ወንዶች bus ላይ እንደ ረዳትነት (ወያላነት) ሲሰሩ ብቻ ተመልክቻለሁ::

አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሚተዳደሩት ከቤተሠብ በሚላክላቸው ገንዘብ ነው:: ግማሾቹ ደሞዝ ሲሉት ሌሎቹ ደግሞ የግፍ ገንዘብ እንዲሁም ጡረታ ይሉታል ይህንኑ በየወሩ መጨረሻ የሚላክላቸውን እና የሚያስተዳድራቸውን ገንዘብ:: ሌላ ቤተሰብ ማለት ማንም የማይረዳው ስደተኛም አለ ከ ዩናይትድ ኔሽንስ በሚያገኘው ምግብ ህይወቱን የሚያኖር... በዚህ ሁኔታ ከ 5 ዓመት እስከ 16 ዓመት የቆዩ ሠዎችን ማግኘት ችያለሁ::

በኬንያ ናይሮቢ የአዲስ አበባን መርካቶ እንዳስታውስ ያደረገኝና ራሱ መርካቶን የመሰለኝ ቦታ አይቻለሁ:: ቦታው ኢስሊ (Eastleigh) ይባላል:: በዚህ ቦታ ላይ የሚሰማው አማርኛ ብቻ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም:: ምግብ ቤቱ .ሙዚቃው..የባህል ዕቃው በአጠቃላይ አገር ቤት ያለሁ እንዲመስለኝ አድርጎኝ ነበር:: ይህ አካባቢ በጣም ቆሻሻና ጭቃ ቢሆንም አብዛኛው አበሻ ግን ኑሮ በአካባቢው ረከስ ስለሚልና ቅናሽ የቤት ኪራይ ለማግኘት ሲል በዚህ አካባቢ ይኖራል::

በናይሮቢ ስደተኞች ላይ ከሚደርሱ ችግሮች ዋነኛው በከተማው ፖሊስ መያዝ ነው:: እነዚህ ፖሊሶች ገንዘብ ከ አበሻ የለመዱ በመሆናቸውና ኢትዮጲያውያንን በመልክ ለይተው ስለሚያውቁ ይዘው ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃሉ:: የተጠየቀው ሰው ያንን ገንዘብም ሆነ ተከራክሮ መጨረሻ የደረሰበትን ካልሰጠ ፖሊስ ጣቢያ መግባቱ ነው ማለት ነው:: ናይሮቢ በገባሁ በ ሁለተኛው ቀን አንድ ፖሊስ ይዞኝ ፓስፖርቴ ላይ valid የሆነ ቪዛ እያየ ፎርጅድ ነው ቪዛሽና ገንዘብ ልትሰጪኝ ይገባል ብሎ ብዙ እንደተጨቃጨቅን አስታውሳለሁ::

በናይሮቢ ቆይታዬ ከነዛ ያስጨድዳሉ ከተባሉት ሰዎች ጋር ተገናኝቼ ነበር:: እንደ ሁኔታው ነው አንዳንዴ ይሳካላቸዋል ብዙ ጊዜ ግን አይሆንላቸውም:: ይህንን ቃል ስጠቀም አዝናለሁ ግና አጭበርባሪዎችም ናቸው:: የሰው ፓስፖርት እጃቸው እስኪያስገቡ እና ገንዘብ እስኪያዝ ድረስ እንክብካቤያቸው ልዩ ቢሆንም ከዛ በሁዋላ ግን ምንም ግድ የላቸውም:: መጀመሪያ ላይ ፓስፖርት ሲቀበሉ በ15 ቀን ግፋ ቢል በ 1 ወር እንዲሁም በሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚያስጨርሱ ቃል ቢገቡም ያንን ባሉበት ቀን መጠበቅ ግን ዘበት ነው:: ገንዘብ ከተቀበሉ በሁዋላ መካድና መጥፋትም በጣም የተለመደ ነው:: ትክክለኛ ቪዛ ነው ብለው ፎርጅድ ቪዛ ፓስፖርት ላይ መተው የሚሰጡም አጋጥምውኛል:: ከዛ ሲያቆዩ ወይመ አልሳካ ሲል ፓስፖርቴን መልስልኝ አልመልስም በመባባል የሚገጥመው አታካሮ እጅግ አስቀያሚ ነው:: ሰው ለወገኑ ግን ለምን እንደዚህ ክፉ እንደሚሆን ግን ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው:: ለዛሬ በዚህ ይብቃኝ:: ተመሳሳይ ተሞክሮና ገጠመኝ ያላችሁ ሰዎች የየበኩላችሁን እንደምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ::

ሠላም ለሁላችሁ ይሁን

...........................................................................
BE GOOD TO EVERYONE
ሰላም ኢትዮጲያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 162
Joined: Mon Oct 03, 2005 1:00 pm
Location: planet earth

ስደተኛው በአፍሪቃ

Postby ሰላም ኢትዮጲያ » Tue Oct 18, 2005 3:11 pm

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Tue Oct 18, 2005 6:54 pm

ቁጥር 3 ከቁጥር 2:- የቀጠለ

በካምፕ ውስጥ

ወይ እሪ በከንቱ ሳይሞቱ ለጋነም
ሁሉም ሀዘንተኛ ዋይታን ሰሚ የለም
እያጉረመረምኩኝ ውስጤ ስላረረ
መናገር አቆምኩኝ አይኔም ማየት ሻረ
በማልሰማው ቁዋንቁዋ በል ና ብሎ ጎቶ
መግባባት እንድችል ሌላ አንድ ሰው ተርቶ
የሰጡኝን እቃ ኬንዳ ምናምኑን
እንዳይሰርቁህ በሚል በምክኒያት ውሸቱን
ጠቀላሎት ሄደ ብስኩት ግን ተወልኝ
እሚበላ ካለኝ ከቃውስ ምን አለኝ
ሆዴን ስለራበው ማሰብ ስላቃተኝ
ብየ ጠየቅኩና ውኅ እንዲሰጡኝ
ዋጥ ዋጥ አረግኩት የብስኩት አበላል
ህገ ወጉ ጠፍቶኝ
ሀበሻ ደግ ነው በተለይ ሲወጣ
ሀገር ባህል ትቶ በባእድ ሲቀጣ
አይልም ወደ ሁዋላ ለመተዛዘኑ
ማካፈል አይቀርም ካለው በመጠኑ
ና ግባ አሉኛና ወደውስጥ ስገባ
ጉዳ አየሁ ሌላ ጉድ በጣም የሚያባብ
ለሁለት የተሰተው ያ ኬንዳ ቱም ብሏል
ሰላሳ ስምንት ሰው ተዛዝሎ ተኝቷል
ሽማግለ ያቃስታል
ህጻኑ ይጮሀል
አሮጊት ጎልማሳው
ኮረዳ ጎረምሳው
ሁሉም አንድ ሆነዋል እንዴት ነው እሚለየው
ይሄውልህ አለኝ ተስፋ ባጣ አባባል
የተከበረው ህዝብ ሀበሻ ተዋርዷል
አንተም አይዞህ በርታ እጣው ወጥቶልሀል
ያዝ አርገው ከንግዲህ ተሰደህ መጥተሀል
መታመም ይኖራል መሞትም እንደዚያው
ከዚህም የከፋ ስለለ ምታየው
ከንግዲህ ሞተሀል
ቀድመህ ተቀበለው
በሁዋላ ከማዘን ከዛሬው እወቀው
ብሎ አስጠነቀቀኝ ቀድሜ እንድረዳው
ድካሙና እራቡ ስለተጫጫነኝ
ጋደም እንደማለት ካንዱ ላይ ተኛሁኝ
እንቅልፍ ሽልብ አርጎ ይዞኝ ጭልጥ አለ
እሰይ አለ አንጎሌ አሁን ሰላም አለ
ሳላስበው ድንገት ጩኽት ሰማሁና
ገና ብድግ ሳልል አንገቴን ሳቀና
ሰው ነው ወይስ አውሬ ያላወቅኩት ነገር
ሲረገጠኛና ወገቤ ሲሰበር
ባንድ ላይ ታወቀኝ አወይ የኔው ነገር
በዛው ልምጥ አልኩኝ ሽምድምድ ሽምድምድ
ጎኔ ስቅዝ ስቅዝ ትንፋሸም ጉምድምድ
ከባድ ጩኽት ሰማሁ ጉሚ የሚልም ቃል
እሷ አልነሳም እሱ ይጎትታል
በጥፊ ደጋግሞ ፊቷን አብልዞታል
ወይ የሚከራከር የለ ሚገለግል
አፈፍ አርጉዋት ሄደ ታቅፎ እንደእቃ
ይሄ ሁሉ ሲሆን እርስዋ ግን ምን አውቃ
ሌላው ደግሞ ገባ ያው ተንጎራደደ
እንደበግ ደባብሶ ሌላዋን ወሰደ
ሌላው ደግሞ መጣ ያው ተንቆራጠጠ
ያምሳ አመቷን ሴት ይዝዋት ፈርጠጠ
ሁዋላማ ጉድ ሆነ ህጻንም አልቀረች ባለ 10 አመቷ
ቀላቅለው ወስደዋት አብረው እንደናቷ
የሚናገር የለ ማን ደፍሮ ይመልስ
መተንፈስ ጀመረ ሁሉ በስስ በስስ
ተረባረቡበት እንደ ቅርጫ ስጋ
ሁሉም በየፈርጁ ከዚህ እዛ እያላጋ
ሴት የትባለች ፍጡር ከዛ የተገኘች
ባለባል ባላባት ባለናት የሆነች
የታመመች ትሁን ለሞት የቀረበች
ከነጉሉኮዝዋ እየተጎተተች
ሁሉን ነገር ችላ ደርሳ ተመለሰች
ጸጥ አለ እንዳልነበር ለቅሶ ሁሉ ጠፋ
ሀበሻ ከሰረ ሁሉ አንገቱን ደፋ
እግዜርን ለመነ ላመጣበት ጣጣ
እንባው ከአይኖቹ ሳይታዘዝ ወጣ
እልቅሶ ተሰማ እሪታው ቀለጠ
ድንኩዋኑ እንደገና ከዚህ እዚያ ተናጠ
ምነው የሚል ጠፋ ሙዋቾቹ በዙና
ያም ያም በየጉያው እሬሳ አቀፈና
እናት ልጇን አጣች ልጅ ደግሞ እናቷን
ወንድም እህት አጣ እህትም አክስቷን
ልድን ብሎ መጥቶ ከሚወርደው ዝናብ
አያሳዝንም ወይ በጎርፍ ሲደበደብ
ከውጭ ሰወች መጡ ጥበቃ ተባዮች
ፍንክች የማይሉ በሀዘን ሰርግኞች
መራርጠው መራርጠው ጎተው ወሰዷቸው
የሚቀብር ዘመድ ሳይከተላቸው::

ይቀጥላል::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ይሁኔ » Wed Oct 19, 2005 6:47 pm

አይ አረሩ ስንቱን ናውራው ብለህ ነው . ስንቱን ግፍና በደል ነው የምንችለው ፕሲኮፓት ሳንሆን መቅረታችን ይደንቀኛል ምናልባትም ባናውቀው ነው እንጅ የመንፈስ በሽተኞች እንሆን ይሆናል ; በዝች ቸት እንኳንስንት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ህክምና እንደሞያስፈልጋቸው መገመት አያቅትም ;; ይኔ በደርግ ዘመን የህዝብ ወ/ር ነበርኩ መንጌም አመለጠ ጦሩም ተበተነ /ምክንያቱን መግለጽ አልፈልግም / እኔም ህይዊቴን ለማትረፍ ስል ከአስመራ ሱዳን ተሰደድኩ . የሱዳን ወታደሮችም ቀላል ምርመራ ካደረጉ በኍላ አስገቡን ድንገት አንዲት የሀገር ልጅ መጥታ እባክህን ሚስቴ ነች በል አለችኝ እኔም ስትጨነቅ በማየቴ ምክንያቱ ሳይገባኝ ባለቤቴ እንደሆነች ተናግሬ ባለትዳር ለሆኑ ሰወች ከተዘጋጀው ድንኳን ሰፈር ቦታ ተሰጥቶን 4 ወር ሙሉአብረን ከረምን /አሁን ከልጅትዋ ጋር ግንኙነት የለንም / በኍላ ስስማ ግን አዘንኩ ለካስ ሱዳኖች ባል የሌላቸው ወጣት ሴቶችን በጉንበት እየወሰዱ ያሳድሩአቸዋልያውም ያለ አግባቡ ይጠቀሙባቸው ስለነበረ ይታመሙ/እየተበላሹ/ ህክምና ይሄዱ ነበር በኍላም /ትዳር በግድ / አግብተው ቀርታተዋል ;; ባጣም ያሳዝናል ያልፍልናል ብለው ወጥተው መሰቃየት የኢትዮፒያ ልጆች እንዲህ ሆነን ቀረን ... አረሩ .. አንተ ብቻም አይደለህ ሁናችንም አረናል ጭሰናል .. ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ
ይሁኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Sat Sep 17, 2005 5:45 pm
Location: india

የአፍሪቃ:ስደተኞች::

Postby ARERU » Wed Oct 19, 2005 8:43 pm

ቁጥር 4 ከቁጥር 3 የቀጠለ:-

እንዲሁ እንደባከን አንድ እንቅልፍ ሳንተኛ
ልተገላግለን ጸሀይ ወጣች ለኛ
ነጋና ጥዋቱ ሙቀቱ ከረረ
ሽንት ቤትም የለ በወግ የታጠረ
ሁሉም በየፊናው መጸዳዳት ጀመረ
እኔም ተላውሸ እንደነገሩ ልል
እየተወላገድኩ ብየ እራቅ ልበል
ተነስቸ ወጣሁ ሄድኩኝ ፈንጠር ብየ
ዛሬም እንደገና ሌላ ጉድ አይኔ አየ
እሬሳው ይጎርፋል የት ይቀበር ይሆን
የሚታየው ከሩቅ ግጥም ብሎ ሞልቷል
አንድ ሁለት አይደለም ለመቁጠር ያዳግታል
ቦታ እስኪቆፈር ድረስ ሄዶ ይቆለላል
መጸዳዳት ትቸ እረስቸው ሁሉን
ማስተዋል ጀመርኩኝ የነገው እጣየን
እንባየ ወረደ በጥፍ በጥፍ ጎርፎ
ዛሬ ሁሉ አለቀ ለነገ ምን ተርፎ
ጉልበቴም እራደ መብረክረክ ጀመረ
ተስፋየ ጠፋብኝ ውስጤ ሁሉ አረረ
አላሳየኝ አለ አይኔ አልመለከት
ተደነባበረ ጥቁር ነጭ ጠፋበት
አይምሮየ ካደኝ የኔ እንዳልነበረ
በምትኩ ገባ እብደት ተጨመረ
እሩጥ እሩጥ አለኝ ቅደደው ልብስህን
አፈትልክ አፈትልክ አድን አንተነትክን
ከዚህ መአት ውጣ ከምድሩ ገሀነም
ላንተ የሚመችህ አንድም ነገር የለም
ተመልስ ሀገርክን ጠብቅ እዛው ሞትክን
እንደወጣህ ቀርተህ ደመከልብ ከምትሆን
ሞክር ተነስ አለኝ ምከርኩ መሰለኝ
ከዛ በሁዋላማ ምኑም አልታወቀኝ::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Wed Oct 19, 2005 9:10 pm

ቁጥር 5 ከቁጥር 4 የቀጠለ:-

ሀኪም ቤት:-

ገላየ ተጋድሟል ካልጋ ይሁን መሬት
ከጀ መርፌ ገብቷል የጉልኮዝ ጅራት
የቆሸሸ ጎጆ ጣራ ይታየኛል
ከጎኔ እንደምርኩዝ አንድ ሰው ቀጥ ብሏል
ዘወር ዘወር ብየ ወደዚህ ወደዚያ
ማስተዋል ጀመርኩን ልክ እንደገበያ
የተጋደመ ሰው ከኮርነር እኮርነር
የሚጮኽውና እንዳበደ ነገር
የሚለፈልፈው አርጎት እንደመስከር
ሁሉም በየፈርጁ ተጋድሞ ተጋድሞ
በሞቱ ያመነው ሞት ሳይመጣ ቀድሞ
ወይ ለጸሎት ሳይደርስ ወይንም ለፍታት
እንደሚሄድ አውቆ መናዘዝ አቅቶት
የት ነው ያለሁ አልኩኝ
ይሰማ አይሰማ በሀይል ግን ጮህኩኝ
አይዞህ ሆስፒታል ነህ ደህናም ትሆናለህ
እኛም ድኮተሮች ነን አለን ልናክምህ
ብቻ አሁን ለጊዜው ማረፍ እንዳለብህ
ወስነናልና ትንች ታገስ ባክህ
ብሎ አለኝና ከጎኔ የቆመው
እጀን ዳበስ ዳበስ አንገቴንም እንዲያ
ዛሬ በጣም ደህና ጭራሽ ተሽሎሀል
ጉሉኮዝ ስትጨርስ ምግብ ይሰጥሀል
እስከዚያ እራስክን አረጋጋውና
ደሀና ትሆናለህ ብሎ አለኝና
ወደዚያኛው ዞረ ከጥጌ ከተኛው
ዳበስ አረገና መሞቱን አወቀው
ምን የቸገረ ነው በዚህም በዛም ሞት
ከዚህስ የከፋ ምን ይመጣል በእውነት
ብየ ተማረርኩኝ ግራ ገባኝና
በሀበሻ ምን ነው እንዲህ ቅጣት ጠና
በቀን አራት ሞቶ አራት ካልተተካ
የጎጆዋ ቆሌ ልክ እንደማትረካ
እሬሳ ሳስገባ እሬሳ ሸኝቸ
እኔም እንደምንም ወጣሁኝ ሰንብቸ
መሄድስ ችያለሁ እንዲያ እንደነገሩ
ሰውነቴ አቁሞ አንዱ አንዱን መምከሩ
እንደአስፈለገው እግሬ እያራመደኝ
እየተንቀጠቀጥኩ እንደምንም ሄድኩኝ
እንዴት እንደደረስኩ ባላውቀውም እንኩዋ
አጋጠመኝ እኔው የሰው በር ሲያንኩዋኩዋ
ግባ አለኝና ገባሁኝ ወደውስጥ
እሬሳ የሆኑ ያልተሰጡ ለምስጥ
ጉዋዶች አገኘሁኝ ተጋድመው ሲያቃስቱ
ጊዜ አልደርስ ብሎ ሰልፍ በዝቶ የሞቱ
ቁጭ አልኩ እንደምንም
መለየት አቃተኝ ማንን ግን ከማንም
ዘርፈጥ እንዳልኩ ቀረው እሚያወራ አጥቸ
እማነጋግረው የውስጤን ፈትፍቸ
ሁለት ሶስት ስአት እንዲሁ ቆይቸ
ድምጽ አናገረኝ ከየት እነደመጣሁ
እኔም ደስ ብሎኝ ዘረዝሬ ተናገርሁ::

ይቀጥላል::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Thu Oct 20, 2005 3:00 pm

ቁጥር 6 ከቁጥር 5 የቀጠለ:-

እሱም ጀመረልኝ ዶክተር አበራ ማሞ
የፈታታውን ሆድ የሚያድብ ገጣጥሞ
የደርሰበትን ባገሩ እዳይኖር ያረገውን በደል
የተገረፈውን በትልትል በትልትል
አላግዝም ባለ አልሆንም ላንደኛው
ከዚህኛው ዱላ ማፋጠጥ ከዛኛ
ተደራርበውበት ሆኖ እንደብቸኛ
ሲቅበዘበዝ ኖሮ አንድ ቀን ሳይተኛ
ታመው የተኙትን ማዳን እየቻለ በጉልበት ተገፍቶ
እንደመጣ አወራኝ ወደሞት ሸኝቶ
ሀገረ ያስተማረኝ ለወገኔ ነበር
ከዝህ እዚያ አጠራቅሞ ለራሳስም ለደብተር
ገበሬው ደክሞ አፈር ገፍቶ አርሶ
መሀንዲሱም ደግሞ ተራራን አፍርሶ
በጉልበቱ አዳሪው ፋብሪካ ውስጥ ያለው
ላቡን አንጠፍጥፎ ጨው እየቀመሰው
ሁሉም በየፊናው እየከፈለ ግብር
እንዲህ ያስተማረኝ እንድረዳው ነበር
ግን ከንቱ ሆነና ከንቱ ዘመን መጥቶ
እንዲኖር ወንድሙ ያው ወንድሙን በልቶ
አፍናጥሮ አወጣኝ አበቃኝ ለስደት
እኔንም ወገኔን መጥቸ አዋረድኩት
ወይ ስራ አይሰሩ ወይ ስራ አያሰሩ
በጠበንጃ ብቻ ሰው እያስፈራሩ
የተዘጋጀውን ልድከም ለወገኔ
እንዳገለገለኝ ላገለግለው እኔ
ያለውን ከልቡ ቅናት አይሉት ክፋት
ጥርግርግ አድርገው የተራረፈውን ለስደት አበቁት
አፈር ውስጥ የገባው አሞራ የበላው
ቀን አልፎ ቀን መጥቶ ጊዜ እስኪቆጥረው
መቸስ ምን ይባላል እግዜር ይማራቸው
ሰው እንደነሱ ሰው ገድሎ ሲጥላቸው
አይናገር አጥንት ከደምና ስጋ ጭራሽ ከተለየ
ቁሞ ሲከራከር ወይ ከድሮ አልታየ
እንዲያው በየመንገድ በጣሻው በዱሩ
ወዳድቀው ወዳድቀው እንደለለ ሁሉ ሰው ሚባል ባገሩ
ቀባሪ አጥቶ ከተወለደበት ካደገበት ምድር
ያውሬ መጫወቻ እንዲህ ሆኖ ሲቀር
ላንተ መጣንልህ ቃል የገቡለቱ
እያስደሰታቸው የሱ እንዲህ መቅረቱ
እነሱ በሻንፓኝ እንደህጻን ሆነው ቀልድ ሲጫወቱ
ያልበቃችው ብሎ መግደሉ መግረፉ
በውሸት ደልለው ወንድም ከወንድሙ እያከፋፉ
ጥርስ እያናከሱ እጅ እያስጨበጡ
አንዱን ከወደላይ አንዱን ከታች አርገው እያረጋገጡ
እንድተመቻቸው እያዘገጃጁ ድራማ እያሰሩ
ወገንን ከወገን እያቀጣቀጡ እያሰባበሩ
እነሱ ብርቱካን ሎሚ እየሸተቱ
ህዝቡን እንቧይ በእንቧይ አረገው ሰነበቱ
ይህ ቀን ያልፍ ወይ ሌላ ቀን ይመጣ
ፍርጥርጥ ሚያደርገው ጉዱን የሚያወጣ
ውሽታሙን በፍርድ አቁሞ እሚያስቀጣ
ወይም በይቅርታ ያለፈን እረስቶ
የበደለው ይቅር ብሎ ተጸጽቶ
ለራሴ ለራሴ መስገብገቡን ትቶ
ያም ከዚያ ያም ከዚያ ተዋልዶ ተጋብቶ
በመጣና ባየሁ ብሎ እንባው አቅሮ
ዝም አለ ጸጥ አለ እህ አለ ሆዱ አሮ::እዚህ ላይ ያለው ዶክተር አበራ ማሞ ለግጥሙ እንዲመች እንጅ ማንም በዚህ ስም ተጠቃሚ የዚህ ጽሁፍ ባለታሪክ አይደለም:: ይቅርታ

ይቀጥላል::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ቀብራራው » Fri Oct 21, 2005 7:40 pm

ውድ ወንድሜ አረሩ:

በጣም ድንቅ ነገር ነው የምትጽፈው:: እውነተኛ ታሪክ ነው ብትልም ግን በፍጹም ማመን ይከብዳል.... በተለይ ስቃዩ የፈጠራ ታሪክ (ስነጽሁፍ) ነው የሚመስለው:: ስቃይ እንዳለው አውቃለሁ...ግን እውነቴን ነው የምልህ እስከዚህ አይመስለኝም ነበር:: እንደውም ብዙው እንደዛ የሚወጡት ...አገር ውስጥ ደብሯቸው...የሆነ ያልሆነውን እያነሱ እየቀባጠሩ/እየዋሹ...የውጭ ሀገር አባዜ አንቀዥቅዦ የሚያወጣቸው ነበር/ነው የሚመስለኝ::

አሁን ግን ያንተን ጽሁፍ ሳነብ ብዛታቸውና ስቃያቸው በጣም ያሳዝናል:: እውነት ግን ስነጽሁፋዊ-ግነት (scale) የለውም?! ለመሆኑ የኬኒያው ነው ወይስ የሱዳኑ ታሪክ?....አሁንስ ያን ያህል ሰዎች አሉ? ስቃዩስ እንዳለ ነው? "ኬንዳ" ምንድን ነው?

ካክብሮት ጋር::
peace for all
ቀብራራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Sun Dec 05, 2004 10:00 am

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Sat Oct 22, 2005 2:44 pm

ቁጥር 7 ከቁጥር 6 የቀጠለ:-

እኔስ አይመስለኝም ይህ ቀን እሚመጣ
ሰው ክፉ ሆኗል ሁሉ አለው ባላንጣ
ከዚህኛው ሳይሆን ከዛኛውም ሳይሆን
በሰላም ለመኖር ማንንም ሳይነካ ለራሱ ብቻውን
ቢያስብ እንኩዋን ቢያልም ለመሆን እራሱን
መቀጥቀጡ አይቀረም እንደባብ መታደን
አ አለ አሉ ያ የደከመው ስው
ጭራሽ የሰለቸ ኑሮ የገለማው
እህህን ለፈረስ ያስተማርኩ እኔ ነኝ
እሱም እሳር ሲያጣ እኔም ሲቸግረኝ
እህህ ለማለት በመቻሉ እሱ
እሱ ያወቀውን ሲመራው ፈረሱ
ከውስጥ የሚያቃጠል የሚነደው እሳት
ቦገግ ብሎ ወጥቶ ጭሱ እንዲሄድለት
ቻለ እህ ማለትን እኛስ መቸ እንበል
እሳቱ እረመጥ ሆኖ ውስት ተቀምጧል
በማናውቀው ነገር ባልመሰለን እኛ
በተጠናወተው በስልጣን መጋኛ
እንያም ሶሻሊዝም እኒም ሶሻሊዝም
ኸረ ብንላቸው የሚያጣላ አይደለም
ከነገረ ቀደም እግዚአብሄርን ክደው
ያን ምቀኝነትን ሳይንስ ነው ብለው
ስለግዜር ሚመክርን አስፈንጥረው ጥለው
በምትኩ ዳግሞ ጋኔኖችን ጠርተው
ወረቀት መለያ ትንሽ ብጣሽ ነገር
የያዘውን ብቻ ተብሎ እንድናከብር
ታላቅ ለትንሹ መቀመጫ ለቆ
ጎምበስ እንደማለት ከላይ ባርኔጣውን በማክበር አላቆ
ያገር ባህላችን ቅጥ አንምባሩ ጠፍቶ
ወንድ በጊዜ ገብቶ ሴት በሌሊት መጥቶ
ተፈጥሮን በጉልበት እንቀየር ተብሎ
ሰው ሚበላው አጥቶ
በጎንደር በትግራይ እንዲሁም በወሎ
ቀኝ እጅ ተንቆ ግራ እጅ ተነስቶ
በጉራ በጩኽት ይሄም ያም አሽካክቶ
መሪ የተባሉት ተደብቀው ገብተው
ተደብቀው ወጥተው
እንደደነገጠ አንደ አፈረ ሰው
የያዙት አድራ ከበድ ሲልባቸው
ከነሱ ያወቀ መስሎ ለታያቸው
ማሳመን ጭራሹን እንደማይችሉ አውቀው
ቀድመው በመትረይስ እራሱን ፈርክሰው
በደሙ ላይ ቆመው ደም እየጠማቸው
ደመ ከልብ አረጉት ምሁር ረክሶባቸው
አወይ አንች ሀገር ምን ነው እንደዚህ ሆንሽ
የተዘራ በቅሎ አይታጨድብሽ
በለጋ በለጋ እየሆነ ድርቆሽ
ወጣ ወጣ ሲባል ዘርሽ አደገልሽ
የልጅ ጣእም ሽታው ማዛው ሳያውድሽ
እሬሳ በሬሳ ሁሌ ሲሆን ምድርሽ
አቻ ወይም መንታ ወይም ዘመድ የለሽ
ልጆችሽ ሲጣሉ የሚያገላግልልሽ
ብቻ ሚቆሰቁስ ጠብ ሚያጫጭርልሽ
አንተ አንተ አባብሎ የሚያገዳድልልሽ
በዘር በሀይማኖት በባህል ሚመስልሽ
ወይንም በቁዋንቁዋ በፊደል ሚጠጋሽ
አንድ እንኩዋን ወይ ግማሽ
እሚሆን ሰው አጥተሽ
ልጆችሽ አለቁ አንችም በጣም ጫጫሽ
እገሌና እገሌ ከሁዋላሽ ተነስተው
ወደፊት ዚጉዋዙ አንችን ሁዋላ ጥለው
አክሱም ፋሲለደስ ላሊበላ ቆሞ
እርጅና ሲጥለው አንድ ባንድ ለቃቅሞ
የነበረሽ ዝና እንደምንም ጠፍቶ
ስምችሽ እንደገና በርሀብ ተተክቶ
ካንች እንዳልበሉ ሳኡዲና ሊቢያ
ዛሬ አንቱ ሲባሉ በአለም ገበያ
ያም ያም ሲጠራቸውታላላቅ እያለ
አንችን እንደህጻን ጥርስ እንዳልተከለ
ለኢትዮጵያ ስጥዋት ለሀበሻዋ ሀገር
የነቀዘም ቢሆን የማረተም ነገር
ብቻ ሆድዋን ትሙላ ማን ሁሌ ይቸገር
መሬትሽ እምቢ ብሎ በግድ ሲያበቅል
እሚጭደው አጥቶ ፍሬው ደርቆ ካፈር ሲቀላቀል
አማካሪ የለሽ ወይ እምያደራድር
ልጅሽ ከመመጽወት ዘር ዘርቶ እንዲያድር
ምን ያለ ነገር ነው እርግማን ነው ቁጣ
ከግዜር የወረደው ወደኛ የመጣ::

ይቀጥላል:-
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Sat Oct 22, 2005 3:31 pm

ቁጥር 8 ከቁጥር 7 የቀጠለ:-

እናት አባት ወልደው ልጅ እንዳይሞሸር
እያዩ ባይናቸው እንደጥንብ ውሻ ተጎቶ ሲቀበር
ወይም ከበራቸው እንደጣሉት ስጋ
ተጋድሞ እንዲውል ዝንብ ወሮት አንድ መንጋ
ክፍያ የጥይት ልጅ የሞተበትን
ለገዳይ ሽልማት ጉራ መንዣ እንዲሆን
እህት ከወንድሙ ጎራ እንዲለያዩ
ከአንድ ሆድ ወጥተው በአይነ ቁራኛ ከምር ሲተያዩ
በበሉበት ወጭት ሲፈረካከሱ
እንገላግል ብለው እነማን ደረሱ
ይህን ተናግሬ ዶክተሩን ሳስተውል
እሱ እንደማሸለብ ጥሎኝ እሩቅ ሄዷል
ወዲያ እንባው ቀረር በስልፍ ወረደ
መናገረ ጀመረ ጎርነን አለ ድምጹ ልክ እንድታረደ
የሚገርመው ደግሞ የሚደንቀው ነገር
ጭራሹን ተሰደን መጥተን ከሰው ሀገር
ለህዝብ የተቆጩ መስለው የሚታዩ
በእየስራቻው ሰው እያወያዩ
አንተ ወያኔ ነህ አንተ ደግሞ ኢዲዩ
ሌላውም ኢህአፓ ቀኙነን ተውና ግራ ግራ እዩ
እየተባባሉ የሰለቸውን ህዝብ
እናድንሀለን እዚህ ከመደብደብ
እራብም አይገባህ ቤትህም ይሞላል
በየሁለት ቀኑ ራሽን ይመጣል
ወደነዛ እንዳትሄድ ጎጆ በዚህ ስራ
የሚቀናህ መስሎህ በውሸት አትመራ
ያለኛ የለህም ነጻ የሚያወጣህ
አንተ ትግሬ አማራ ወይም ኦሮሞ ነህ
ብለው ያናግሩና ያዳመጣቸውን
እራሱ አዙረው ባንድ እሚበላውን
የጎሪጥ ሲተያይ ሲጨካከን ደርሶ
የእነሱ ሞራል ወዲያው ታድሶ
ዝፈን ብለው ሰጠተው ከበሮ እያስመቱ
ጨካኝ አደረጉት ሰውን በእውነቱ
ወደ አንዱ ካልሆንክ ላንዱ ካልተገዛህ
ምንም ቢሆን ምንም እወቅ እንደጠፋህ
ያለም ህዝብ ይረዳል ሲባል እንሰማለን
ካገሩ ለወጣ መርጦ ስደትን
ይሄ ግን ሌላ ነው የሚረዳው ሌላ
የተጠቃለለው በነሱ ከለላ
ነጮች አምነውበት ተቀናቃኝ ላሉት
በገፍ ነው እርዳታው እንደሰማይ ወተት
ታድያ ይገርመኛል የነጩም የጥቁሩ
ለራሳቸው ጥቅም ባንድ ላይ ሲያብሩ
ይሄው እምታየኝ ታምሜ ስሰቃይ
ልሞት ቀርቤያለሁ ህክምና ሳላይ
ለኛ ሁን ለኛ ሁን እንደ ስጋ ቅርጫ
ሁሉም ሲያስገድዱኝ ያለ እኔው ምርጫ
አይሆንም ስላቸው ይብቃኝ ማቃጠሩ
ባደረጉት ነገር ጭራሽ ስላፈሩ
እንድወንጀለኛ በደል እንደሰራ
ሰው እንድልገናኝ ወይ እንዳላወራ
የደርግ ጀሌ ነው ሊሰልል የመጣ
ብለው አስደረጉኝ በህዝብ እንድቀጣ
ብሎ ዝም አለ ትንፋሽም ያው ጠፋ
አረፋ አዳፈቀ ልክ እንደተጋፋ
ብነካካወና ባገለባብጠው
ጠጋ ባደርገውም እጄን ወዳፍንጫው
ጭራሽ ተሰናብቷል ይህችኑ ምድር
ለካስ ለሱ አይሆንም ከደከመ ዶክተር::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Re: ስደተኛው በአፍሪቃ

Postby ተድባበ » Sat Oct 22, 2005 10:16 pm

ሰላም ኢትዮጵያ..... አንቺና አረሩ እያነሳችሁት ያላችሁት ይህ የስደት እንግልት ጉዳይ የብዙዎች የልብ ትርታ ስለሆነ በሰፊው እንድንወያይበትና እንድንጽፍበት እፈልጋለሁ:: የኬንያ ኢስሊን መራራ ህይወት ካዩት ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ:: :( :( :( ባንቺና በአረሩ ገጠመኞች መደመሜ አልቀረም :: ሙሉ በሙሉ በጋራ የምንጋራቸው ገጠመኞች አሉንና በርትተን እንጻጻፍ:: ሌሎችንም እንጋብዝና የካኩማውን, የናይሮቢውን, የኢስሊን, የካሩባንጌን, የኩባ ሙላንጎውን.... ቅቅቅቅቅቅ!.... ገጠመኞቻችንን ሁሉ አስቲ ለህዝብ እናቅርበው....

ልዩ ማስታወሻ ለአረሩ...... ወገን አረሩ በግጥም ስሜትክን ለመግለጽ እየደረከው ያለው ሙከራህ የሚደነቅ ነው:: ሆኖም ግን ይህንን የስደት ገጠመኝህን በተሻለ መንገድ ሀሳብህን አፍታተህ ለመግለጽ እንዲያስችልህ በስድ ጽሁፍ ብታቀርበው የብዙ አንባቢያንን ቀልብ እንደምትስብ ላሳስብህ እወዳለሁ::

ተባባሪያችሁ
ተድባበ
ሰላም ኢትዮጲያ wrote:ሰላም እንደምን አላችሁ?

ከላይ ወንድሜ አረሩ ስደተኛው በአፍሪቃ በሚል ርዕስ ስር የፃፈውን አየሁና እኔም የበኩሌን ለማለት ወደድኩ:: ግን ለምንድን ነው ብዙዎቻችን የምንሰደደው ወይም የተሰደድነው? መልሱ ግልፅ ነው:: የተሻለ ነገር ፍለጋ...አገራችን ጥሩ ኢኮኖሚ ስለሌላት...ስራ ማግኘት ከባድ ስለሆነ ቢገኝም ደህና ገንዘብ ስለማይከፈለን...በትምህርት ጥሩ መሠረት (background) ስለሌለን...ብቻ ብዙ ምክንያት መስጠት ይቻላል:: እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት የምዕራቡን አለም ወደን እና ነጭ ለማየት ብለን አይመስለኝም:: እኔ በበኩሌ ያንን ብዬ አልወጣሁም የወጣሁበት ዋናው ምክንያት የተሻለ ነገር በመፈለጌ ነው:: አዎ ይህንን ብዬ ነው::

ለተወሰነ ጊዜ በኬንያ ናይሮቢ ኖሬያለሁ:: እናም ብዙ ነገሮችን ለማየትና ለመታዘብም በቅቻለሁ:: በዚህ አጋጣሚ ከሀገራችሁ በቀጥታ ሌላ ሶስተኛ ሀገር ሳትረግጡ ወድ አለማችሁበት ቦታ መሄድ የቻላችሁ ስዎች ጥሩ እንደገጠማችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ:: አውቃለሁ እዛም ችግር ሊገጥማችሁ ይችል ይሆናል ሆኖም ግን ስደት ለዛውም በ አፍሪካቃ እጅግ ከባድ ነው::

ናይሮቢ ውስጥ የሚገኙውን ኢትዮጲያውያን እና ኤርትራዊያን ብዛት መጀመሪያ ሳይ በጣም ደንቆኝ ነበር:: ኬንያ ጎረቤት ሀገር በመሆኗ ወይም ደግሞ ለ ካናዳ እና አሜሪካ ፕሮሰስ አመቺ በመሆኑ ይመስለኛል ብዙ ሰው ወደዛ የሚያመራው:: ወደ ስደተኛው ስንመጣ ብዙ አይነት ስደተኛ አለ:: ግማሹ ከላይ እንደጠከስኩት የ ካናዳ እና አሜሪካ እንዲሁም አውስትራሊያ ወረቀት አስገብቶ መልሱን እየጠበቀ የሚገኝ..ሌላው ደግሞ በዘመኑ አጠራር ሊያስጨድድ የመጣ (ጨደዳ እንግዲህ በዛ ያለ ገንዘብ ተከፍሎ ወደ ተለያዩ ሀገራት መውጣት የሚቻልበት መንገድ ማለት ነው) ሌላው ለፕሮሰስ ከቤተሠብ የተላከለትን ገንዘብ ጨርሶ ወደ ሀገር ቤት መመለስ አሣፍሮት እዛው ቁጭ ያለ ወ.ዘ.ተ.... በናይሮቢ ስደት ከባድ ነው ምክንያቱም ስደተኛነቱ ከሚያደርሰው ተጸዕኖ በትጨማሪ ሁሉም ስደተኛ ስራ የሌለው መሆኑ ነው:: ልስራም ቢል አይችልም:: ጥቂት ኢትዮጲያውያን ወንዶች bus ላይ እንደ ረዳትነት (ወያላነት) ሲሰሩ ብቻ ተመልክቻለሁ::

አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሚተዳደሩት ከቤተሠብ በሚላክላቸው ገንዘብ ነው:: ግማሾቹ ደሞዝ ሲሉት ሌሎቹ ደግሞ የግፍ ገንዘብ እንዲሁም ጡረታ ይሉታል ይህንኑ በየወሩ መጨረሻ የሚላክላቸውን እና የሚያስተዳድራቸውን ገንዘብ:: ሌላ ቤተሰብ ማለት ማንም የማይረዳው ስደተኛም አለ ከ ዩናይትድ ኔሽንስ በሚያገኘው ምግብ ህይወቱን የሚያኖር... በዚህ ሁኔታ ከ 5 ዓመት እስከ 16 ዓመት የቆዩ ሠዎችን ማግኘት ችያለሁ::

በኬንያ ናይሮቢ የአዲስ አበባን መርካቶ እንዳስታውስ ያደረገኝና ራሱ መርካቶን የመሰለኝ ቦታ አይቻለሁ:: ቦታው ኢስሊ (Eastleigh) ይባላል:: በዚህ ቦታ ላይ የሚሰማው አማርኛ ብቻ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም:: ምግብ ቤቱ .ሙዚቃው..የባህል ዕቃው በአጠቃላይ አገር ቤት ያለሁ እንዲመስለኝ አድርጎኝ ነበር:: ይህ አካባቢ በጣም ቆሻሻና ጭቃ ቢሆንም አብዛኛው አበሻ ግን ኑሮ በአካባቢው ረከስ ስለሚልና ቅናሽ የቤት ኪራይ ለማግኘት ሲል በዚህ አካባቢ ይኖራል::

በናይሮቢ ስደተኞች ላይ ከሚደርሱ ችግሮች ዋነኛው በከተማው ፖሊስ መያዝ ነው:: እነዚህ ፖሊሶች ገንዘብ ከ አበሻ የለመዱ በመሆናቸውና ኢትዮጲያውያንን በመልክ ለይተው ስለሚያውቁ ይዘው ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃሉ:: የተጠየቀው ሰው ያንን ገንዘብም ሆነ ተከራክሮ መጨረሻ የደረሰበትን ካልሰጠ ፖሊስ ጣቢያ መግባቱ ነው ማለት ነው:: ናይሮቢ በገባሁ በ ሁለተኛው ቀን አንድ ፖሊስ ይዞኝ ፓስፖርቴ ላይ valid የሆነ ቪዛ እያየ ፎርጅድ ነው ቪዛሽና ገንዘብ ልትሰጪኝ ይገባል ብሎ ብዙ እንደተጨቃጨቅን አስታውሳለሁ::

በናይሮቢ ቆይታዬ ከነዛ ያስጨድዳሉ ከተባሉት ሰዎች ጋር ተገናኝቼ ነበር:: እንደ ሁኔታው ነው አንዳንዴ ይሳካላቸዋል ብዙ ጊዜ ግን አይሆንላቸውም:: ይህንን ቃል ስጠቀም አዝናለሁ ግና አጭበርባሪዎችም ናቸው:: የሰው ፓስፖርት እጃቸው እስኪያስገቡ እና ገንዘብ እስኪያዝ ድረስ እንክብካቤያቸው ልዩ ቢሆንም ከዛ በሁዋላ ግን ምንም ግድ የላቸውም:: መጀመሪያ ላይ ፓስፖርት ሲቀበሉ በ15 ቀን ግፋ ቢል በ 1 ወር እንዲሁም በሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚያስጨርሱ ቃል ቢገቡም ያንን ባሉበት ቀን መጠበቅ ግን ዘበት ነው:: ገንዘብ ከተቀበሉ በሁዋላ መካድና መጥፋትም በጣም የተለመደ ነው:: ትክክለኛ ቪዛ ነው ብለው ፎርጅድ ቪዛ ፓስፖርት ላይ መተው የሚሰጡም አጋጥምውኛል:: ከዛ ሲያቆዩ ወይመ አልሳካ ሲል ፓስፖርቴን መልስልኝ አልመልስም በመባባል የሚገጥመው አታካሮ እጅግ አስቀያሚ ነው:: ሰው ለወገኑ ግን ለምን እንደዚህ ክፉ እንደሚሆን ግን ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው:: ለዛሬ በዚህ ይብቃኝ:: ተመሳሳይ ተሞክሮና ገጠመኝ ያላችሁ ሰዎች የየበኩላችሁን እንደምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ::

ሠላም ለሁላችሁ ይሁን

...........................................................................
BE GOOD TO EVERYONE
ተድባበ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:06 pm
Location: ireland

Postby ትትና » Mon Oct 24, 2005 5:28 am

አረሩ መቼም እየነገርከን ያለው የወገኖቻችን አሰቃቂ የስደት ሂወት አሳዛኝ አስለቃሽ ነው:: እስቲ ቀጥልልንና ሀዘናችሁን እንካፈል! ሲናገሩት ቀለል ስለሚል ደሞ እኛም ለመስማት(ለመካፈል) ዝግጂ ስለሆንን በሆድህ ሳታስቀር አውጣና ንገረን::

እግዚአብሄር ጽናቱን ይስጣችሁ!

አክባሪህ
ትትና
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

ለወንድም ተደማም::

Postby ARERU » Tue Oct 25, 2005 12:29 pm

ሰላሙን ሁሉ እመኝልሀለሁ ከዛ በመቀጠል እምለው ነገር ግን ወደፊት ይሄን ታሪክ በስድ ንባብ መልክ እድሜውን ለሁለታችን ከሰጠን መስጸሀፍ ሆኖ ታነበዋለህ እኔም ታሪክን ግጥMም ይናገረዋል ብየ አስቤው አይደለም ነገር ግን ለጊዜው እንኩዋን በሚል ነው ስለዚህ የተዘጋጀ መጽሀፍ አለና ታትሞ ልታነበው ትችላለህ ብዙ ነገሮችን ያዘለ በዛም ላይ እህት ትትናን ሳላመሰግናት አላልፍም::
አመሰግናለሁ
አረሩ::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests