በውቀቱ ስዩም ከድንቅ ገጣሚዎች አንዱ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

በውቀቱ ስዩም ከድንቅ ገጣሚዎች አንዱ

Postby ermiasabe » Fri Oct 28, 2005 1:52 pm

Guys and Gals',

If you have not yet read/heard this poet's work check it out at http://www.addislive.com under "short stories'. I believe he is among the best writters who came into the Ethiopian literature scene. One for the road:

ጣይና አንሺ

ደሞዙን ቢጥል አንስተው ጠጡበት
ባርኔጣውን ቢጥል ወስደው ደመቁበት
ከዘራውን ቢጥል ተመረኮዙበት
በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ
በጣለው ሲያጌጡ በጣለው ሲያተርፉ
እራሱን ሲጥል ግን አይተውት አለፉ::
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

Postby Ellenie » Tue Nov 01, 2005 7:08 pm

ermiasabe የሚገርመው እኔም ከግጥሞቹ ሁሉ የወደድኩዋቸው እቺን ከላይ ያለችውና ስትሥቂ ይሚሉት ""እንኩዋንስ በኔ ልትስቂ... ...የሚሉትን ነበር:: በተለይ ሁለተኛው እንኩዋንስ በኔ ልትስቂ ብሎ የሚጨርሰው በጣም ያሳቀኝና ያስገረመኝ ነው::
Smile
Ellenie
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1000
Joined: Wed Jul 27, 2005 4:36 am
Location: ethiopia

ድንቅ ገጣሚ

Postby ያሙ » Wed Nov 02, 2005 4:59 am

በእውቀቱ ስዮም በጣም ከማደንቃቸው ወጣት ገጣምያን አንዱ ነው::ግጥሞቹ በጣም የተዋጣላቸው ናቸው::ከዚሁ ከጎን ለጎን በጣም ተወዳጅ አጫጭር ልቦለድ ጽሑፎቹ ባለው ልዩ የቃላት አመራረጥና የአተራረክ "ስታይል" በጣም ያዝናናኛል::

እስቲ ከቻላችሁ ያገኛችኋቸው ግጥሞች አስነብቡን::

አመሰግናለሁ
እባካችሁ፡እንደማመጥ..."ሃሳብን በሃሳብ መግደል ይቻላል፡ሃሳቡን የተሸከመው ሰው መግደል ግን አይቻልም"
ያሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Mon Oct 24, 2005 3:03 am
Location: united states

መልክዓ እናት

Postby ermiasabe » Wed Nov 09, 2005 5:39 pm

ምናልባት የገጣሚውን መብት መጋፋት ባይሆን ይህቺን ‘መልክዓ እናት” የምትል ግጥም ከበውቀቱ ስዩም የግጥም ስብስብ እነሆ። ለሁላችንም ትልቅ መልዕክት ሳይኖራት አይቀርም ብዬ ነው ፤ መልዕክቱ እንዳተያያችን ቢሆንም። ስርዓተ ነጥብ ባለመጠበቄ ግን ይቅርታ። መልካም ንባብ።

መልክዓ እናት

ሰላም ለኪ እናታችን ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለአይኖችሽ ከጢስ ጋር ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በሆንኩ ከአይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ
ሰላም ለከንፈሮችሽ ትናንት ለማውቃቸው ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቅት ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴ ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ
ለካ በእርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ
ሰላም ለጣቶችሽ ለሰዎች የቀረቡ ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስ እንጂ መቀበልን ለማያውቁ
ሰላም ለኪ ባለሽበት እንዳለሽ።
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

Postby ermiasabe » Sat Nov 12, 2005 9:35 am

ፍካሬ እውነት

ሰማይ እንዲህ እንደ ዛሬ ርቆ ሳይወረወር
ሁሉ እንዳሻው የሚቆረሰው ሁሉ እንዳሻው የሚጎርሰው ግዙፍ እንጀራ ነበር
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለሁ
ምክንያቱም እወድሻለሁ
አያቴ ሦስት መቶ አመታት ኖሩ
የመቶ አመት ሰው እያሉ ብርቱ ፅኑ ነበሩ
ዝሆን በጥፊ ጣሉ አንድ ጥይት ተኩሰው ሦስት ነብሮች ገደሉ
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለሁ
ምክንያቱም እወድሻለሁ
አባቴ ከሰዎሽ ሁሉ ይለያል
በአይኖቹ ብቻ ሳይሆን በማጅራቱም ያያል
ብለሽ የነገርሽኝን እውነት ነው ተቀብያለሁ
ምክንያቱም እወድሻለሁ
ግና ጅል እንዳልመስልሽ አይደለሁም ተላላ
በርግጥ በጄ ብላሻለች ነፍሴ ሁሉን ተቀብላ
እውነት ማለት ከሚወዱት መስማማት እንጂ አይደለምና ሌላ
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

Postby ሩኒ » Mon Nov 14, 2005 9:56 pm

በእውቀቱ ስዩም ከግጥም ስራዎቹ ባሻገር በተለያዪ ጋዜጦችና መፅሄቶች የሚያወጣቸው አጫጭር መጣጥፎችና ወጎች እጅግ ይማረካሉ.....በተለይም የስእል ችሎታውን በመጠቀም የሚያወጣቸው የካርቱን ስእሎች መልክታቸውም ሆነው አዝናኝነታቸው ግሩም ነው:: የ 'መዝናኛ' ጋዜጣ ቐሚ አምደኛ በመሆኑ አምልጠውኝ አያውቁም::

በእውቀቱ ስዩም የ Psychology' ምሩቅ ቢሆንም የስነ ጽሁፍ ምርኮኛ ይመስልኛል:: በ አ. አ. ዩ. የ ስነ-ሰዕል ት/ቤት ተማሪ መሆኑም በውስጡ ያሉትን ምጡቅ የፍልስፍና ንድፍ ሀሳቦችን ከስነ ጽሁፍ እካይ በረቂቃዊ /abstractive/ የስዕል ዘዬ ለመተረክ ውጥኑን የሚያመላክት ይመስልኛል::

አልፎ አልፎ በወሬዎቹ መካክል ጣል የሚያረጋቸውን ቀልዶች ብታደምጡ ስል እውነት ነው የምላችሁ ያ ዝመተኛው ሰው እንዲህ አይነት ሰው ነው ወይ? ትላላችሁ:: ታዲያ እሱ አይስቅም...
ሩኒ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 108
Joined: Sat Oct 22, 2005 1:56 pm
Location: Wales

...

Postby ዋኖስ » Tue Nov 15, 2005 12:49 am

መልክዓ እናት

ሰላም ለኪ እናታችን ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለአይኖችሽ ከጢስ ጋር ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በሆንኩ ከአይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ
ሰላም ለከንፈሮችሽ ትናንት ለማውቃቸው ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቅት ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴ ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ
ለካ በእርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ
ሰላም ለጣቶችሽ ለሰዎች የቀረቡ ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስ እንጂ መቀበልን ለማያውቁ
ሰላም ለኪ ባለሽበት እንዳለሽ።እያዝናኑ የሚያስተምሩ ኪነጥበባዊ ምክር-አዘል ግጥሞች

ናቸዉና እኒህን ዓይነት ሥራዎቹን ብትጨምሩን

አበጃችሁ ከማለት ወደኍላ የሚል የሚኖር አይመስለኝምና

በርቱ:: ዉድ ገጣሚ በዕዉቀቱ ሥዩምም በዚህ

አጋጣሚ ይህ ዓይነቱ በሳልና እንቁ-ፍሬ-ለበስ ታላቅ

ሥጦታ ተተኪዎቹን ማፍራት እንዲችል ዘንድ ይህን

አጋጣሚ በመገጠም ሌሎች አያሌ በእዉቀቶችን

እንዲያፈሩልን ወደ ዋርካችን ጎራ እያሉ ስልትዎንና ልዩ

ኪነጥበባዊ ተሞክሮዎትን ቢያካፍሉን ደስታዬ የእትዬለሌ

ነዉ::

==== ዋኖስ ከዳሞት ለማጂ-ኪነጥበብ አምባ::===
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ermiasabe » Tue Nov 15, 2005 9:51 pm

ውድ ሩኒ

ከፅሁፍሽ እንደተረዳሁት በውቀቱን በአካል ታውቂዋለሽ። በዋርካ ስር የተጠለሉ ብዙ አድናቂዎች እንዳሉት ብትነግሪውና አንድ ቀን ግጥሞቹንና ሌሎች ስራዎቹን አምድ ከፍቶ ቢያስተዋውቀን መልካም ይመስለኛል።

አመሰግናለሁ
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

Postby ermiasabe » Tue Nov 15, 2005 10:13 pm

አዳምና ጥበቡ

በመጀመሪያ አዳም ሳተ
ከገነትም ተጎተተ
አዳም ከገነት ሲባረር
እነሆ እርቃኑን ነበር
ብርዱ፣ ውርጩ አንዘፈዘፈው
ዶፉ፣ ጠሉ ወረደበት
ይንዠረገገውን አይተው
አእዋፍ አራዊት ሳቁበት
ይሄኔ አዳም ተማረረ
ተማረረና ተመራመረ
ተመራምሮም አልቀረ
ጋቢ መስራት ጀመረ
ጅማሬውን ወደደ
ተጀምሮ እስኪፈጠም
የእድሜውን ግማሽ ወሰደ
ያሳዝናል
ጋቢውን ጨርሶ ሲቋጭ
ገላው ብርዱን ለመደ
ermiasabe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Oct 27, 2005 10:37 am
Location: ethiopia

Postby እቴነሽ » Fri Nov 25, 2005 8:50 am

እ?
እቴነሽ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 91
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:19 am

Postby ሙርጥ » Mon Jan 30, 2006 2:36 pm

ብሩህ ተስፋ ያለው ገጣም, ሰአሊና ፈላስፋ..........

ብዙ እንጠብቃለን
Please learn to live with controversies.
ሙርጥ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Sat Jan 28, 2006 5:22 pm
Location: UK


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests