ፀሀይ ትወጣለች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፀሀይ ትወጣለች

Postby አልምጠው ጀለሴ » Mon Nov 07, 2005 3:30 pm

ለምን በፖለቲካ አታደርገውም ማለታችሁ አይቀርም ግን በፍቅር ብዙ ሰው ስለሚሳተፍ ነው እና እስኪ አንቡት

<B>ፀሀይ ትወጣለች</B>

በጨለማ ገብተው በጸሀይ የሚገጥሙ

ጫካ ውስጥ ተወልደው ጫካ ውስጥ ያደጉ

በብሶት ተወልደው በቀን ያዘኑ

በጠመንጃ አፈሙዝ ወገንን የሚገድሉ

የሰው ዘር እንዳንል አዕምሮ የላቸው

መስራትን አያውቁ ማፍረስ ተግባራቸው

በየትኛው ቃላት እንዴት ልግለጻቸው

የጭራቅ ክፋዮች መናፍስት ናቸው

ለጊዜው ብትጠፋም እውነት ተደብቃ

አትኖርም ብቻዋን ከወገን ርቃ

ዛሬ በስራቸው በግፍ ለፈጇቸው

ጸሀይ ትወጣለች ተጠያቂ ናቸው

ጸሀይ ትወጣና ደምቃ ታበራና

ሀሰት ሀሰት ሁኖ እውነት ትነግስና

ስንዴው ከእንክርዳዱ በደንብ ይለይና

የእጃቸውን ዋጋ በቀኑ ያገኛሉ

ከህዝቡ መካከል ወዴት ይሄዳሉ

መግደል ማሰቃየት ሆኗል ዓላማቸው

ግን ዞር ብለው ቢያዩት ሂትለርም አልበጀው

ጸሀይ ትወጣና ወያኔ ፍርድ ቤት በቅርብ ይቀርብና

የአስከፊ ተግባሩን ምሱን ያገኝና

ሰላም እና እውነት በሀገራችን ሰፍኖ

ብሔር ብሔረሰብ ሁሉ እኩል ሁኖ

ጸሀይ ትወጣለች እውነት ታብባለች

ጎጠኛ ወያኔን ታቃጥለዋለች

ቢገድሉና ቢያስሩ እንዲያው ለጊዜው ነው

የማታ የማታ ድሉ የህዝብ ነው

የማታ የማታ ድሉ የኢትዮጵያ ነው

<B>ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ</B>
አልምጠው ጀለሴ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Wed Jul 27, 2005 3:49 pm

ቆንጆ ግጥም

Postby ጌታ » Mon Nov 07, 2005 3:45 pm

አልምጥዬ ወቅታዊና አሪፍ ግጥም ነች:: እኔም የናፈቀኝ የወያኔ ለፍርድ መቅረቢያ ቀን ነው:: ከሰው የእግዚአብሄር ፍርድ ይበልጣልና እስቲ እንመልከት::

አሁን በቅርቡ!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

አምልጠው ጀለሴ

Postby Monica**** » Mon Nov 07, 2005 4:35 pm

አሜን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
በስፈሩት ቁና መስፈር አይቀርም ይሉ የለ አባቶቻችን ሲተርቱ!!!
Judgment day እንደሆን እሩቅ አይደለም!!
ስላምና ፍቅር ለኢትዮጵያችን ይሁን!!!!!
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

ድንቅ ስነግጥም ለውድ ኢትዮጵያ

Postby ዲጎኔ » Mon Nov 07, 2005 7:12 pm

አልምጥዬ ተባረክ
እውነትም እንዳልከው እንዲህ ልድገመዋ!
የማታ ማታ ድሉ የጌታ
ኢትዮጵያ ግፈኞችን ረታ
እናያታለን በሁሉ በርትታ
አሁን በያለንበት እንበረታታ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests