ኤሉሄ ኤሉሄ ::

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ኤሉሄ ኤሉሄ ::

Postby ARERU » Tue Nov 08, 2005 9:51 pm

ኤሉሄ ኤሉሄ ላማ ሰበቅተና
ችግሩ ስቃዩ በኛ ላይ ሲጠና
የመላእክት አምላክ የጌቶቹ ጌታ
የፍጥረታት ንጉስ የኛ ሁሉ አለኝታ
ምን ነው እረሳህን እንዲህ ስንፈታ
ርሀብ ችግሩ ጭንቁ አልበቃን ብሎ
ህመም መታረዙ ሁሉም ለኛ ተብሎ
እስከመቸ እንኑር ጌታ አንተ እያለህ
አንዴ በለን ባክህ ይብቃችሁ ከንግዲህ
እሚበላ ጠፍቶ እርሀብ እየቆላን
መድሀኒት ጠፍቶ እያየን እየሞትን
እንዴት ለኛ ዱላ የጥጋበኛ እጅ
ወይም በመትረይስ እንቆላ እንፈጅ
እረ ይብቃ በለን
ወይ አንዴ ጨርሰን
ምን ያደርጋል ታድያ ሳንኖር እየኖርን
ለስው ቁጥር መሙያ አንድ ሁለት እያስባልን
እስከመቸ እንኑር ሳንኖር እየኖርን
አንዱ እላይ ሆኖ እየኮረኮመን::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby እሪኩም » Thu Nov 10, 2005 8:05 am

መድሃኒት ነበረ ቀማሚ ጠፋ እንጂ:
አሜሪካ የሚሏት መጥፎ አማላጂ::

እኛ ብንነሳ እየተዘራጠጥን:
ከግቡ ሳንደርስ ወደኍላ ቀረን::

ብሔር ብሔረሰብ አንድ ላይ ከቆመ:
አበባው ያብባል ዓረም ከታረመ::

*****እሪኩም ከቦሩ ሜዳ*****
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

አረሩ

Postby ምርቃና » Thu Nov 10, 2005 11:12 am

እኔ ደግሞ ሄሎዬ ሄሎዬ ስትል የምትወደን ዘፋኝ ቴዲን እየዘፈንክ መስሎኝ ዘው አልኩኝ !!

የተዋጣለት ግጥም እጅ ይባርክ!!
እንዲሁም እሪኩም!!

ሰላም:roll:
Just chat, dont consider it>>>> Love 4 all>>
figaww.
ምርቃና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 211
Joined: Tue Feb 24, 2004 7:23 am

Postby ድራኮላ7 » Thu Nov 10, 2005 12:13 pm

ሠላም ለሁላችሁ : አረሩ: እሪኩም : ምርቃና <<<< ሠላም ለኢትዮጵያ >>>>
ድራኮላ7
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed May 25, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

ድንቅ ሰራ ነው አረሩሻ

Postby ሀዱድ » Thu Nov 10, 2005 2:17 pm

ወሬ ተወረረ መሳርያውም ጠፋ

ምን ተፈጥረ አለ የስንቱ ልብ ለፋ

ሀሳብ አደከመኝ መፍትሄው ቸገርኝ

እኔእዚህ ቁጭ ብየ ሀሳብ አሻፈረኝ

ተነሽ ተነሽ አለኝ ግፉ እየጠና

ምንም የማያውቀው ህጻኑ ሞተና

እናቶች ሲመቱ በሰደፍ ባጣና

ግፉ አንገፈገፈኝ ልቤ አጣ ጤና

ከቤታቸው ማእድ ሳይጠግቡ አቁዋርጠው

ከሞቀ አልጋወስጥ ሳይነጋ ደንግጠው

ከየቤቱ ታፍሶ ወጣቱ ታሰረ

መቻልን አልቻልኩም ቅስሜ ተሰበረ

ልቤ በሀሳቡ ከነሱጋ አደረ

ሀዱድ
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

ኤሉሄ

Postby ARERU » Thu Nov 10, 2005 4:11 pm

ኤሉሄ ኤሉሄ ላማ ሰበቅተና
ችግሩ ስቃዩ በኛ ላይ ሲጠና
ምን ያለ ነገር ነው ነገር ድንግርግር
በዳይ ተቀምጦ ተበዳይ ለአፈር
እረ ተው እባክህ አንተ አንድ በለን
እስከ መቸ እንኑር እንድህ ተሰቃይተን
እሚበላ ሞልቶ እያለ በምድርህ
እንዴት ለህጽን ልጅ ጥይት ታበላለህ
እነሱ ሲቆዩ ድሎት በዝቶባቸው
ወተት ሲያቀረሹ እኒያ ልጆቻቸው
እንዴት የድሀው ልጅ ደም ያቅርሽ ትላለህ
እራሱ ይፈርከስ ብለህ ትፈርዳለህ
ወይ እሪ በከንቱ ሰሚ የለም ለካ
በእር ለያዘ እጅ መትረይስ ሲያሽካክ
ወይ ውረድ ወይ ፈረድ ያሁኑስ ይበቅል
አንዱ በጠገበ ሌላው እንዴት ያልቃል
ተው ፍረድ አባክህ ካንተ ማንም የለም
አንድ ጊዜ ቃል አውጣ ይለይለት ሁሉም::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ARERU » Wed Jan 25, 2006 5:24 pm

ኤሉሄ ኤሉሄ ላም ሰበቅተና
ችግሩ ስቃዩ በኛ ላይ ሲጠና

አምላክ እረ የት ነህ
ተበዳይ በዛብህ

ተመላከት ወደታች አስተውል እባክህ
ጎረምሳ አስቸገረ ህዝብህን ፈጀብህ

ተራነትን ይዞ ይሄ የተራ ልጅ
ማስተዋል አቅቶት ሰው በጥይት ሲፈጅ

መመልከትህ ምን ነው ዝምታህ በዛብን
ወይ እሱን አጥፋልን ወይ እኛን ጨርሰን

እስከመቸ እንደዚህ እኛስ እንኖራለን
የጥገበ ቡጢ እናስተናግዳለን

በክልል በክክል በክክልል ከልሎ
እንደሚመች አርጎ ሁሉን አስተካክሎ

ያሻውን በጥይት
ያሻውን በስር ቤት

አንዱን ለፓርላማ በብጣሹ ጉርሻ
እሱ ሆዱ ሞልቶ ሲተፋለት ቅርሻ

እሚያወጣው መስሎት ወንድሙን ሲከዳ
ነገ ወደ እስር ቤት ረስቶ እንደሚነዳ

ዛሬ እያሳሳቀ እንደህጻን ጨቅላ
ያኛውን ከዛኛው ጭራሽ እያጣላ

እንዳይተማመን አድርጎት ሁሉን ሰው
የቂም መወጣጫ ባንድ ላይ ሲያደርገው

እንዲት ዝም ትላለህ ጌታችን አንድ በል
ኢትዩጵያ ሀገራችን ከምትሆን ሶማል::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ARERU » Thu Jan 26, 2006 4:21 pm

ኤሉሄ ኤሉሄ ላማ ሰበቅተና
ችግሩ ስቃዩ በኛ ላይ ሲጠና

ሰው ተስማማ ተብሎ ገና ሊፋቀር ነው
ይሄ አይመቸንም በጥይት እንበለው

ወገን ከወገኑ ተሳስቆ እንዳይኖር
ያልነበረን ክፋት ከሌላ እንዲበደር

ትግሬ አማራ ኦሮሞ ጉራጌ እያሉ
ያኛውን ከዛኛው በቃላት ሲያጣሉ

አንደኛው ቂም ይዞ ሌላውን ሲበድል
ባለተራው ደግሞ ነገ ጠብቀኝ ሲል

በሻገተ ዜና በማረተ ጭራሽ
ቴድሮስ እንዲህ አለ ምኒሊክ ተከሳሽ

አማራ ነፍጠኛ ኦሮሞ ተጨቁዋኝ ላመታት
ትግራይን ጀግና ነው ሌላው መች አለበት

አበረው ባበሰሩት ሞተውና ቆስለው
ያኛውን የበላይ ይሄን ታች አድርገው

ለነሱ እንዲመች እንዲሆን አስማምተው
እረ ከፋፈሉት ዘርህ ሊጠፋ ነው

ጌታየ እባክህ አንድ ነገር አድርግ
ቃል የገባህለት ህዝብህ ሳይበረግግ

የሰይጣን ቁርጥራች ትናሽ ትላትሎች
ያንተዋን ባለቃል ሳያደርጉ እንዳትመች

ዱላ ሳይናሳ ባንዱ አንዱ ሳይጨክን
የተካበረው ህዝብ ሩዋናዳ ሳይሆን
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ARERU » Thu Jan 26, 2006 5:44 pm

ኤሉሄ ኤሉሄ ላማ ሰበቅተና
ችግሩ ስቃዩ በኛ ላይ ሲጠና

ሰው አልመክር አለ ተለያየ ልቡ
ሆዳም ጢም ብሎ በዝቶ ስግብግቡ

በገና ለገና ብቻ በይሆናል
የሱን ሆድ ሊሞላ ወንድሙን ሲያስገድል

በሱም ቦታ ሌላው እንደዚያ ሲጠቀም
አንዱ ባንዱ ህይወት ትርፍ ሲያቀራርም

እረ ተጨራረስን ምን ነው ጌታ እባክህ
ወይ ውረድ ወይ ፍረድ ያው እዛው ተቀምጠህ

ተጨቁዋኙ ማን ነው ጨቁዋኙስ ማን ይሆን
አንዱ አንዱን ሲከስ አንዱ አንዱን ሲያድን

ሁሉም በየተራ ስልጣን ላይ ሲወጣ
የገባለትን ቃል ህዝቡን ሲያሳጣ

ብቻ ሲያጨካክን ለሁልጊዘ ላይኖር
ሁሉ እያስቀመጠ ቀሪ የቂም ብድር

እኛው እየከፈልን እኛው እያስከፈልን
ወይ ሀገር አትለማ ወይ ሰው ሰው ላይሆን

ሁሌ እራብ ብቻ መጠርያ ስማችን
ላለም መረዳጃ ክፍተን አቅማዳችን

እስከመቸ እንኑር ባክህ ፍረድ ጌታ
ጦርነት እያየን ቀንም ሆነ ማታ
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby shari » Sat Jan 28, 2006 3:56 pm

አረሩ ሰላም አለው ተባረክ ስሜቴን ገዝቶታል.....

ግን.... ወይ ውረድ ወይ ፍረድ ያው እዛው ተቀምጠህ
shari
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Thu Sep 08, 2005 3:08 pm
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests