መመንኮስ ኃጢያት ነው ወይስ ጽድቅ ???

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

መመንኮስ ኃጢያት ነው ወይስ ጽድቅ ???

Postby ጩጉዳ » Tue Nov 08, 2005 9:59 pm

በፍጹም ያልገባኝ ነገር ስለሆነ እባካችሁ የምታውቁ በስርዐቱ ታስተምሩኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ::
በአገራችን በተለይ በኦርቶዶክስ አማኞች የተለመደውን ምንኩስና ትክክል ያልሆነ ነው ሲል አንድ ጴንጤ ነገረኝ:: ሰውዬው ያለኝ <መጋባትን የሚከለክል ኑፋቄነት ነው> የሚል ነገር በመጽሀፍ ቅዱስ ተጽፏል:: ነው ያለኝ:: ይህ እውነት ነው ወይ? እግዚአብሄር <ብዙ ተባዙ ምድሪቱንም ሙሏት> ብሎ የተናገረውስ ምንኩስናን አይቃረንም? ወይ? እንዲሁም ሐዋሪያው ጳውሎስ <ሰው ብቻውን ይሁን ዘንድ መልካም አይደለም> ሲልስ ምን ማለቱ ነው:: ሌላው ጥያቄዬ ምንኩስናን የሚያዝ ወይም የሚደግፍ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይኖራል ? የሚነቅፍስ?
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby 4get.this » Wed Nov 09, 2005 12:07 am

General forum ላይ ብትሄድ ብዙ መልስ ልታገኝ ትችል ይሆናል:: ጥሩ ጥሩ አዋቂዎችም አሉበት:: ለማንኛውም: ሁለት ነገር ልበል::
1- የመጀመሪያው አይነት "ጥቅስ" እስካሁን አላየሁም: አልሰማሁም:: እንዲያ የሚል ካለ ቦታው ቢታወቅ መልካም ነው::
2- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሳያገባ እንደኖረ መርሳት የለብንም:: ሐዋርያቱን: እኛን ደግሞ "እኔን ምሰሉ" ብሎ በሕይወታችን የርሱን ፈለግ እንድንከተል አስተምሮናል:: አለማግባት ሀጢያት ከሆነ ... (ጨርሰው)
1ኛ ቆሮ 7ን ብታነበው ብዙ ጥያቄህን ይመልስልሀል ብዬ አስባለሁ:: በተለይ ቁጥር 1 (..ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው) እና 7(ሰው ሁሉ እንደኔ ሊሆን እወዳለሁና ...) እንዲሁም ከ32 ጀምሮ ያለው ጸጋው ለተሰጣቸው አለማግባት የሚሻል መሆኑን ያሳያል::

"ብታገባ ግን ሐጢያት አትሰራም" ቁጥር 28
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ

Postby ዲጎኔ » Wed Nov 09, 2005 3:43 am

" መንፈስ ግን በግልጥ -በሁዋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ሀይማኖትን ይክዳሉ ይላል በገዛ ህሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው እነዚህ ውሸተኞች መጋባት ይከለክላሉ"( 1 ጢሞቲዎስ 3:1-3)

ምንኩስና ወይም የብትውህና ኑሮ ሰዎች ለእግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ ለመሰጠት የሚፈጽሙት የመንፈሳዊ እርምጃ ሲሆን ከመጀመሪያው የመካከለኛው ዘመን ጀምሮ በአለም ዙርያ በኢትዮጵያችንም ጭምር የተጀመረ ጉዳይ ነው::

ጌታ ግን ቃሉን ለተቀበሉት አማኞች (ደቀመዛሙርት) ያዘዘው ግን" ወደአለም ሁሉ ሂዱ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ ነው(ማርቆስ 16:15)::

በገዳማት ግን አያሌዎች በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በአለም ላይ ቅዱስ ቃሉና መንፈሱ ቀስቅሶአቸው እጅግ ጠቃሚ ስራዎችን የፈጸሙ ስላሉ በጥቅሉ መነኮሳት ሁሉ ውሸተኞች ማለትትክክል አይደለም :ነገር ግን እግዚአብሄር የመሰረተውን ቅዱስ ጋብቻ የሚከለክሉ ሁሉ ከተጻፈው አንዳች ሳይጎድል" ውሸተኞች አጋንንታዊያን" ናቸው::

ዲጎኔ ከመነኮሳት ገዳም ማዶ ደቅ እስጢፎ ተሀድሶ አምባ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Wed Nov 09, 2005 7:14 am

ዲጎኔ:-


የመጨረሻዉን ፓራግራፍ እስኪ ማብራሪያ ስጥበት....

አልዋጠኝ ዐለ!!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ብዙ መነኮሳት በበጎ ምግባር የሚታሰቡ አሉ

Postby ዲጎኔ » Thu Nov 10, 2005 5:47 am

ዋኖስ
የትኛውና እንዴት አልዋጥ እንዳለ ባውቅ የአቅሜን እሞክራለሁ: በበጎ ትክክለኛ የክርስትና ቀኖና አስተምህሮ ከሚታወሱ ምንኩስናቸውን እስከመጨረሻ የጠበቁ ያልጠበቁም ብዙ መነኮሳት ነበሩ አሁንም አሉ::
ለምሳሌ
1. አባ ሳቮናሮላ-ፍሎሬንስ ኢጣልያ
2.አባ እስጢፋኖስ- ቆየጻ ኢትዮጵያ
3. ዶ/ር ማርቲን ሉተር- ሳክሶኒ ጀርመን
ሌሎችም ሲሆኑ ስለእነዚህና ስለመሳሰሉት መነኮሳት የተጻፉትን ብዙ ጽሁፎች ማንበቡ የበለጠ ምላሽ ይሰጣል::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ምንኩስና ቅድስና ነው ::

Postby ግሸንማርያም » Wed Nov 16, 2005 6:16 pm

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::የተከበርክ ውድ ወንድሜ ጨጉዳ በመጀመሪያ ይህን የመሰለ ወቅታዊ ጥያቄ ስላቀረብክ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛለህ አሜን :: የጠየቅከውን ጥያቄ ተመልክቼዋለሁኝ :: በዚህ አምድ ላይ ግን ምንም ስለ መጸሀፍቅድስ የማያውቅ ሰው ሌላ ነገር ሲናገር ሳይ ገረመኝ:: መጽሀፍቅዱስ እውርን እውር ቢመራው ተያይዘው ገደል ይገባሉ ያላል :: መጽሀፍቅዱስ አይነ ልቦናችን ያብራልን ::አንድ ጴንጤ ምንኩስና ኑፋቄ ነው አለኝ ላልከው ጴንጤ መጸሀፍቅዱስ አያውቅም :: ይህን እንደ መረጃ መቀበል አልነበረብክም :: ምክንያቱም እነሱ የሚያውቁት ታሪክ የለምና :: እስቲ ጴንጤው ምንኩስና ኑፋቄ ነው አለ :: አንድም የጴንጤው ዘመድ... ምንኩስናን ሲቃወም ነበር ነገር ግን መጸሀፍቅዱስ ስለ ምንኩስና ምን ይላል የሚለውን እንመልከት :: እኔ ሁል ጊዜ ጴንጤዎች የሚሉትን ካየሁኝ ቡሐላ ወደ መጸሀፍቅድስ ነው የምሄደው :: ለማንኛውም እስቲ ከመጸሀፍቅዱስ ውስጥ ማስረጃ እናምጣ ::

ምንኩስና መጸሀፍቅዱሳዊ ነው :: በመጀመሪያ ወደ ምንኩስና ምስጢራት ከመሄዳችን በፊት መነኮሰ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እንይ ::

መነኮሰ ማለት (ግእዝ ነው) ሞተ ማለት ነው :: ይህም ማለት ለዚህች አለም ፍትወት ራሳቸውን የገደሉ ናቸው ማለት ነው :: ይህንን ሲያረጋግጥልን ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ እንዲህ ይላል :

አለም በእኔ ዘንድ የሞተ ነው እኔም በአለም ዘንድ የሞትኩኝ ነኝ ያለው ::

ከላይ እንደግለግለለጽኩት መመንኮስ ማለት ከአለማዊ ግብር መለየትን የስጋን ፈቃድ መግደልና በነፍስ ፈቃድ መመራት ማለት ነው ::

ሮሜ ምህራፍ 6 ቁጥር 2 እንዲህ ይላል "" ለሐጢያት ሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን ?"" በማለት ሐዋርያው ለሐጢያት ስራ ብልቶቻቸውን የገደሉ እነደሆኑ ያስገነዝበናል ::

የድንግልናን ወይንም የምንኩስናን ሕይወት የሚነቅፉ እንደውም ሕገ እግዚአብሄርን እንደመጣስ የሚቆጥሩ አሉ :: አይ መጸሀፍቅዱስን አለማወቅ :: መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ , ቅዱስ ኤልያስ , ወንጌላዊው ዮሐንስ እና ቅዱስ ጳውሎስ እኮ በድንግልና ነው የኖሩት አይ መታወር ሰይጣን አይነ ልኖናቸውን ጋርዶባቸዋል ::

ያአህዛቡ መምህር ቅዱስ ጳውሎስ ድንግል ነበረ እንደውም ሰዎችን ሁሉ እንዲህ ብሏል "1ኛቆሮንጦስ ምህፋፍ 7 ቁጥር 7 ሰው ሁሉ እንደ እኔ እንዲሆን እወዳለሁ "" ተመልከቱ ! ቅዱስ ጳውሎስ ባህታዊ ነው አላገባም ታዲያ ከላይ እንዳየነው ሁሉም እንደ እኔ እንዲሆን እወዳለሁኝ ነው ያለው ::

ዳሩ ግን ይህ (ድንግልና:ምንኩስና) ለሁሉም አይቻልም :: ለተመረጡ እንጂ :: አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምንድነው ያለው ስለ ምንኩስና ማቴዎስ ምህራፍ 19 ቁጥር 11-12 ደቀ መዛሙርቱ:- የባልና የሚስት ስርአት እንዲህ ከሆነ ማግባት አይጠቅምም አሉት (ኢየሱስን) :: እርሱ ግን ይህ የሚሆነ(ምንኩስና) ለተሰጣቸው ብቻ ነው :: በእናት ማህጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ : ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ : እራሳቸን ስለ መንግስተ ሰማያት የሰለቡ አሉ [color=green] አላቸው ::የሰለባቸው አሉ : ስለ መንግስተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ አሉ ::ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው :: ተመልከቱ ወገኖቼ ኢየሱስ እራሱ ስለምንኩስና አስፈላጊነት ተናግሯል ::ነገር ግን ይህ ምንኩስና ለተሰጣቸው ነው :: እናንተ ግን ልትቀበሉት የምትችሉ ከሆነ አቅሙ ካላችሁ ተቀበሉት ብሏል :: አቅምን ማወቅ ትልቅ ነገር ነው ::ማርቲን ሉተር አቅሙን ሳያውቅ ገብቶበት ቡሀላ ላይ ቆቡን ጥሎ ወጥቷል :: አያድርስ ::

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሳቸን ለመንግስተ ሰማያት ጃንደረባ የሚያድርጉ አሉ ብሏል :: ወገኖቼ ይህን እኔ ጭንጉፍ የምሆን ሰው ይህን በአይኔ አይቻለሁኝ :: አንድ መነኩሴ ወጣት ነው : ይህ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ወደ አንድ ገዳም ሄዶ በጾም በጸሎት በስግደት እንደ ቅዱስ ጳውሎስ እራሱን አደከመ :: ነገር ግን የሰውን ቅድስና የማይወድ ሰይጣን ለዚህ መነኩሴ በሴት ልጅ እየተመሰለ የተለያዩ አይነት ሽቶ እየተቀባ መነኩሴውን ሊያሳስተው በዙ ጊዜ ይጥር ነበር :: ይህ ወጣት መነኩሴ ግን በማቴዎስ ምህፍራፍ 19 ቁጥር 12 ላይ እንደተነገረው እራሱን ጃንደረባ አደረገ :: ሰይጣኑ ገዳሙ ውስጥ እየመጣ እንደዚህ በሴት አምሳል ሲፈትነው ይህ ወጣት መነኩሴ የውንድ ዘሩን በጡዋፍ አቃጠለ :: በዚህን ጊዜ ሰይጣኑ የመነኩሴው የወንድ ዘር ሲቃጠል ይጠፋ ነበር:: ይህ መነኩሴ አሁንም በገዳም ተወስኖ የሚኖር ነው :: እግዚአብሔርም ጸጋውን ያበዛለት ወጣት ነው :: እንግዲህ እራሳቸን ለመንግስተ ሰማያት ጃንደረባ ያደርጋሉ የሚለው በአገራችን እየተፈጸመ ነው ::

በገዳም መወሰንና ራስን ለእግዚአብሔር ማስገዛት እንደሚገባ አብነት የሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶ ነው :: ""በማቴዎስ ምህራፍ 4 ቁጥር 1- 11 ስትመለከቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ በዳ ገዳም ለ 40 ቀንና ለ40ሌሊት ጾመ ጸለየ ይላል ""


ይህንን አብነት አድርገው አባቶቻችን በገዳም ንጽህናቸውን ጠብቀው ይኖራሉ :: ይህንን የአባቶችን በገዳም መኖር ሲያስተምር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሏል ሕብራውያን ምህራፍ 11 ቁጥር 37 -38 በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በመጋዝ ተሰነጠቁ በሰይፍ ተገደለው ሞቱ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ አለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳ (ገዳም) ና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ
ይላል ::

ተመልከቱ የበግና የፍየል ቆዳና ሌጦ ለብሰው በዋሻና በምድረ በዳ እንዲሁም በተራራ ተቅበዘበዙ ይላል :: ለዚህም ነው በአገራችን ባህታውያንን መነኮሳት ይህን ህይወት የሚኖሩት ለዚህም ነው በአገራችን ይህንን አብነት አድርገው ባህታውያንና መነኮሳት በገዳም ተወስነው የሚኖሩት :: ይህ ግን ምንኩስናው ማለት ነው ለተሰጣቸው ብቻ ነው :: ለምሳሌ እኔ አቅሙ የለኝም ስለዚህ ሚስት እግዚአብሔ እንደፈቀደልኝ አገባለሁ:: ምክንያቱም ጸጋዬ ምንኩስና አይደለምና :: እንደ ማርቲን ሉተርም መሆን አልፈልግም :: ምክንያቱም እርሱ በመጀመሪያ መነኮሰ ነገር ግን:: የወንድ ፍሬው በጣም ሲፈትነው ጥሎ ወጣ እንደውም ድርጅት አቁዋቁዋመ :: አሁን ይህ ድርጀት እንደውም የእምነት ሆኖ ቁጭ ብሏል ::
ስለዚህ አቅምን ማወቅ ያስፈልጋል ::
ለሌም ደግሞ ንጽህናቸውን ጠብቀው ከአለም ርቀው በደብረ ቅዱስ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት የእግዚአብሔር ልጆች ባልተባሉም ነበር [color=red ]ኦሪት ዘፍጥረት ምህራፍ 6 ቁጥር 1 እና መጸሀፈ ሄኖክ ምህራፍ 2 ቁጥር 1ን ተመልከቱ

ስለዚህ ከአለማዊ ግብር ተለይተው ሐይማኖትን ከምግባር ጋር አስተባብረው ይዘው ከተገኙ ባይሞነኩሱም ፍጹምነት በጋብቻ ላሉም ይሰጣል ለዚህም አብህርሐም : ይሰሐቅ ያእቅብ : እየቦ : እርምያስ : ዳዊት ... ::

ስለሆም ሁለቱም የእግዚአብሔ ናቸው :: መመንኮስን ግን እግዚአብሔር ለተሰጣቸው ብቻ ነው ይላል :: ምክንያቱም ይህ ለሁሉም አልተሰጠምና ::

እንግዲህ ይህን ይመስላል በመጸሀፍቅድስ ውስጥ ::
ውድ ወንድሜ ጨጉዳ ሌሎቹም ትምህርቶች ከተለያዩ ስብከቶችና መጸሀፎች የገኜሁዋቸውን ስብከቶች ዋርካ ጄኔራል ብትገባ "" ግሸንማርያም"" የሚለውን ስም ብታይ የኔ ነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅነ : ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት : ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም : ስለ ቅዱሳን መላእክት ከተለያዩ ስብከቶች ያገኘሁአቸን የቤተ ክርስትያናችን እውነቶች አቅርቤያለሁኝ ሄደክ ጎብኛቸው ::ሌሎች ጥያቄዎች ካሉክም ጠይቀኝ:: እዚህ ላይ መጠየቅ ካልፈለግክም ደግሞ በፕራይቬት/private ልትጽፍልኝ ትችላለክ :: እግዚአብሔር ያቆይክ ::
ያስተማረን እግዚአብሔር ይመስገን ::

የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የጻድቃን የሰማእታት ጸሎትና በረከት የቅዱሳን መላእክት አማላጅነትና ተራዳይነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ::


ምንጭ መራሄ ደህነት( በመምህር ብርሀኑ ጎበና ) የተዘጋጀ መጸሀፍ ላይ የተወሰደ :: መምህራችንን ቃለ ሕይወት ያሰማልን አሜን ::
Last edited by ግሸንማርያም on Wed Nov 16, 2005 10:40 pm, edited 7 times in total.
ግሸንማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 366
Joined: Mon Aug 15, 2005 8:11 pm
Location: ethiopia

ዲጎኔ...

Postby ዋኖስ » Wed Nov 16, 2005 6:22 pm

:roll: ይድረስ ለዲጎኔ በልልኝ ከሥሩ ባክህ!! ከጊዜ ማጠር የተነሳ ልጠይቅ ጀምሬ አልሳካልኝ ብሏል ገላገልከኝ::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests