እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ

Postby እማማ » Fri Nov 11, 2005 2:42 am

አቤቱ አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ብዛት ይቅር በለን:: የመጣውንም መቅሰፍት በምህረትህ መልስልን:: የታወረ አይነ-ልቦናችንንም አብራልን:: በጣም ስር የሰደደና ልንገታው ያልቻልን የተጠናወተንን የዘር ልዩነት መንፈስ አስወግድልን:: ሁላችንም አንድ ሆነን አንተን እንድናመሰግንህ አድርገን አሜን::

እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ (3)

በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ (3)

ኪራላይሶን (3)

ኦ አምላክ (3)

ኦ ክርስቶስ (3)

ያድህነነ ከመዓቱ ይሰውረነ በምህረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ (3)

ስማነ አምላክነ ወመድሀኒኒ (3)

እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረን (2)
እንደ ምህረትህም ይቅርታን ስጠን (2)
ከሀጢያቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ (2)
ለዚያች ክፉ ሀጢያት እንዳልሆናት ሎሌ (3)
እኔም አበሳዬን በደሌን ሳውቀው (2)
ከቶ የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው (2)
አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ (2)
አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ (2)
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን ስማጸን አንተን
መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሀን (2)
አሁን ትባርክ ዘንድ ማህበራችንን ጉባኤያችንን
ፈጥነህ ላክልን ጰራቅሊጦስን መንፈስ ቅዱስን
አሁን ትባርክ ዘንድ ሀገራችንን ሀይማኖታችንን
ፈጥነህ ላክልን ቅዱስ ሚካኤልን ቅዱስ ገብርኤልን::

አቤቱ ቅዱስ አምላካችን ሆይ እንደኛ ሀጢያትና በደል ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ጸሎታችንንና ልመናችንን ስማን::

አሜን
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby ጋርቢቲ » Sat Nov 12, 2005 2:43 pm

እውነት ነው አማማ ባሁኑ ወቅት የሚያስፈልገው: እግዚኦ ብቻ ነው በውነት:

እንደው እማማ እግዚኦ ሲሉ ያንዲት ጉዋደኛዬ አያት ታሪክ ትዝ አለኝና ነው ብቅ ማለቴ:

እኚህ መነኩሴ ሁልጊዜ ከለሊቱ 9 ሰአት የጀመሩ ቆመው ሲጸልሁ ይነጋባቸዋል: እና አንዳንዴ ዳዊት አንዳንዴ የተለያዩ የጸሎት መጽሀፍ ዘርግተው .... እየገለጡ ሲጽልዩ ነው የሚያድሩት: እና ይቺ ጉዋደኛዬ ስትነግረኝ: እንዴ እማማ ምንም ማንበብ እንደማያውቁ በደንብ አውቃለሁ ግን እንዴት ሆነው ነው የጸሎት መጻሀፍትን እያነበቡና እየገጡ የሚጽልዩት ብዬ ሁሌ ይግርመኝ ነበር አለችኝ እና አንድ ለሊት እኔም ተደብቄ እንዴት እንደሚያነቡት ስሰማ አለች........ ጠቅላላውን ጊዜ መጽሀፉን እየገለጡ....
"እንደው አቤቱ እንዴት ታደርገኝ ይሆን,አቤቱ እንዴት ታደርገኝ ይሆን....አ አ አ አቤቱ እንዴት ታደርገኝ ይሆን.........."
ብቻ ነው የሚሉት አለችኝ:: እንደው ግን አይገርሙም ሌሊቱን ሙሉ አቤቱ እንዴት ታደርገኝ ይሆን" እያሉ ስያነጉት ?? እኔ በጣም ነበር የደነቀኝ: እሳቸውማ መቼም ይህኔ አሙዋሙታቸው እያሳሰባቸው ይሆናል : ነገር ግን እውር አሞራን በጫካ የሚመግብ አምላክ ፍላጎታቸውን ተረድቶ የሚያስፈልጋቸውን ያደርግላቸዋል::

አገራችንን የነዚህ የየዋሆቹ አምላክ ይጠብቅልን::

መልካም ቀን
ጋርቢቲ ነኝ::
ጋርቢቲ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Thu May 06, 2004 9:38 am


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests