የተማሪው.ደብዳቤ ከተማሪው ለመምህሩ ከኢል ፊሊዩ( ካነበብኩት)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የተማሪው.ደብዳቤ ከተማሪው ለመምህሩ ከኢል ፊሊዩ( ካነበብኩት)

Postby ዳኒቦይ2002 » Sat Nov 12, 2005 10:08 am

ውድ መምህር ሆይ:ይህችን አነስተኛ ደብዳቤ ስፅፍልህ ከራሴ ብዙ ተሟግቼ ነው.....በዚህ መሰል አስተሳሰቤም የሀይማኖት አስተማሪዬን አስቀይሜ ይሆን? ርጉም ተማሪ ሆኜ ይሆን እያልኩ እተክዛለሁ....ይሁን እንጂ እፅናናለሁ....የሀይማኖት መፃሕፍቶች ሁሉ የተፃፉት በሰው ልጅ ብዕር አይደል?ደግሞስ በሰው አድሮ ጥበብ የሚሰጥ የልዑል እግዚአብሔር መንፈስ አይደል?አሊያማ ብቻችንን የሰው ልጆች ምንድር ነን?ፈረንሳዊ ፈላስፋ ፓስካል እንዳለው ደካማ ሰንበሌጥ እንጂ::
ውድ መምህሬ
ለፅሁፌ የሰጠሁት አርዕስት <<የሰው.አፈጣጠርና.የአዶከበሬ.ቡጊ.አጀማመር>>የሚል.ነው::
ሰፋ ያለ አእምሮም ተቀዳጅተህ በጥሞና እንድታነብልኝ እለምንሃሎህ:: እንደአንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ውግዘትን ብቻ አታስቀድም:: ደግሞስ ቅዱስ ዻውሎስ እንዲህ ብሎ የለ <<ስለዚህ አንተ በሌላው አገልጋይ ላይ መፍረድ አይገባህም.... እንዲያውም ጌታው ሊያቆመው ስለሚችል ፀንቶ ይቆማል >>ተገነዘብከኝ መምህሬ: በሰው መፍረድ አይገባም ::
መምህሬ ሆይ
ኦሪት ዘፍጥረትን /ምዕራፍ1 ቁጥር2 - 6 ዋቢ እያደረግህ <<ሰው በእግዜር መልክና አምሳያ ተፈጠረ>> እያልክ ስታስተምረኝ ለማመን ቢከብደኝ ይህችን ፃፍኩልህ ::
ነገሩ እንደዚህ ነው
በአንድ በኩል ፈጣሪ /በተለይም ከክርስቶስ ልደት ቦሀላ የተነሱ ሰዓሊዎች በስዕል እንዳቆዩልን/ንፁህ,ብሩህና.ደስ የሚል መልክ አለው ሰው ግን ዕለት በዕለት እንደምናየው መልኩ አንዳንዴ በቅሎ አንዳንዴ አህያ አንዳንዴ ደግሞ ጉመር ዝንጀሮ ይመስላል:: በሌላ በኩል ደግሞ ፈጣሪ /እንደ ሃይማኖት መፅሕፍቶች/ደግ ርህሩህ አዛኝ ለችግር ፈጥኖ ደራሽ ነው :: ሰው ግን ዕለት በዕለት እንደምናየው ምግባረ-ብልሹ ጨካኝ ዋሾ ዘራፊ ሀሜተኛና አጭበርባሪ ነው ::ታድያ ሰው በፈጣሪ አምሳያና መልክ ተፈጠረ እንዴት እንበል ? ይከብዳል :: እኔ እንደሚመሰለኝ የሰው አፈጣጠር በዚህ መልክ ነው :: ይህ አስተሳሰቤን ከአንድ ሺህ ኣመት በፊት በድንጋይ ወይ በብርና ላይ ፅፌው ቢሆን ኑሮ /አይነዶ/ ዛሬ ስንት ሚሊዮን ሰዎች ወይ መጣጥፍ ኢል ፊልዩ ዲ ብኤልዜቡል እንዳለው እየተባለ በተጠቀስሁ ነበር :: ይቀጥላል አስተያይታችሁን አትንፈጉኝ
No body is Perfect only "PERFECT"
ዳኒቦይ2002
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Tue Jun 22, 2004 11:11 am
Location: sudan

Postby ቁም ነገር2 » Sat Nov 12, 2005 7:46 pm

ሀይ ዳኒ ተመችተሽኛል እንዳታቋርጪ በርቺ :!:
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Postby ዳኒቦይ2002 » Mon Nov 14, 2005 8:32 am

ቁም ነገር አመሰግናሎ :lol:
No body is Perfect only "PERFECT"
ዳኒቦይ2002
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Tue Jun 22, 2004 11:11 am
Location: sudan

Postby ቁም ነገር2 » Mon Nov 14, 2005 8:50 am

አይ የልጅ ነገር አማርኛህ ነው ያሳቀህ :?: እኔ እንኳን በቃላት ግድፈቶችህ ሞራልህ እንዳይነካ ብዬ ነበር :?
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Postby ቀበሌው » Wed Nov 16, 2005 9:24 pm

:roll: እንዳታቁዋርጥ ደስ ይላል አጀማመርህ::አሪፍ ነ በርታ ዳኒ
that is good
ቀበሌው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Mon Feb 09, 2004 4:29 pm
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests