ከሰረ ዜናዊ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ከሰረ ዜናዊ

Postby eri-drimer » Mon Nov 28, 2005 2:22 pm

አየ አቶ ዜናዊ ብልህ ናቸው ስንል ለካስ ሞኝ ናቸው

ውሼትና ስርቆት መግደልና ቅሚያ የሆነ ኑሮዋቸው

ደጋግመው ደጋግመው የተመላለሱ በወንጀል ስራቸው

ገና ድሮ ድሮ ታሞ ተሰቃይቶ ሞቶ ህሊናቸው

የነበረበቱ ቦታው እንኩዋ ፈርሶ ጠፍቶ ከውስጣቸው

ከወዴት መጥቶ ነው? ወዴትስ ሆኖ ነው የሚፈርድባቸው::


እንግዲያውስ ጌታ ከህሊና በቀር ምን ከንቱ ፈጠረ?
ወይ ከሁሉ አልጠፋ ወይ ከሁሉ አልኖረ
ታዛዦችን ሁሉ በጸጸት ሰንሰለት አስሮ እያስቸገረ
ለማይታዘዙት የግፍ መፈጸሚያ አድርጎ እያኖረ
ለበዳይ ይፈረድ ተበዳይም ይካስ ይቀጣ እንደገና
መቸም ያለም ስራ እብድ እንዳደራው ድር ውትብትብ ነውና


ይህ የወንበዴ አለም የወንበዴዎችን ስራ ተከትሎ

ደካሞችን ረግጦ ሀይለኞችን አዝሎ

ያም ቢጮህ ያም ቢጮህ ይጉዋዝ ዝም ብሎ

ይህ ነው ያለም ስራ ብንወድም ብንጠላ

ይህን ለመቀበል ልቡ የሚኮራ ደሙ የሚፈላ

ታግሎ መለወጥ ነው መንገድ የለም ሌላ ::
eri-drimer
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:56 pm

Postby eri-drimer » Sat Dec 03, 2005 9:39 am

ነገር ግን እንደኛ ደሙ የማይፈላ የረጋ ቀዝቅዞ

አለሙን እንዳለ ከነጉስቅልናው እስከ ግፉ ይዞ

ጥቃት እንዳያስቀጭ ምክኒያት በመፍጠር መንፈስን አቡዞ

ግፍ እንዳያሰቃይ በጌሾዋማ ጠላ ራስን አፍዝዞ

ቀን እየሰሩ ሌቱን እየተኙ መቀጠል ነው ጉዞ

እንዲያ ነው መጠጣት መተኛት ማለምና መስከር

ስካር መልካም ነገር እልም መልካም ነገር

እግዜር የነሳንን ያደርጉናል ታላቅ ያደርጉናል ክብር
eri-drimer
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:56 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests