ሠላምታ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ሠላምታ

Postby eri-drimer » Mon Nov 28, 2005 6:05 pm

ቼ ቢሉት ቼ ቢሉት የማይሰማ ፈረስ
አለንጋው ተሰማ ጉባላፍቶ ድረስ

አላ ገዶ በታች ባለው መካኒሳ
በሶስቱ ስላሴ እንዳንረሳሳ

በሶስቱ ስላሴ ባርባው ነጋሪት
አላን ተሻገርኩት ባንድ ቀን ሌሊት

ከአላማ ወዲያ ስሙ ነው እናውጋ
ቆርኬን አቆራርጦ ታቹን በውላጋ

መርሳ አባ ጌትየ ሊብሶን ወረድ ብሎ
ውርጌሳ ከተማው ያለህው መለሎ

ሰላሜ ይድረስህ ባለህበት ቦታ
ሁሉም ይሳካልህ ይከተልህ ጌታ

ጤናዳም ናትራው ሪኩም ሽታህ
eri-drimer
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:56 pm

Postby ድራኮላ7 » Tue Nov 29, 2005 8:58 pm

እሪኩም ያገር ልጅ እንዴት ከርመሀል ከላይ ያለው ግጥም ላንተ ይመስላል !!
ድራኮላ7
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed May 25, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

Postby እሪኩም » Wed Nov 30, 2005 1:04 am

ሠላም Eri-Drimer!

እንደዚህ ነው እንጂ ጨዋታና ግጥም:
አብሮ አደግ መከታ ቁምነገርህ ሲጥም::

ውርጌሣና ሊብሶ መርሣና ሥሪንቃ:
ጥቁር ውኃን ሳናልፍ ዬት አለች ሣንቃ::

ደብረ ገሊላ ላይ ኑሩ ሲያጫዉተን:
ሸሁ ብቅ ብለው ሳንቡሳ ሲሰጡን:
እንፀልይ ነበር አብረን ተሰባስበን:
መቼ እንመለስ እኛ ውጭ ቀርተን::

ጊዜው አላፊ ነው እስቲ እንቻል:
መቻሬ ሜዳ ላይ ብቅ ብቅ እንበል::

ጥሩ አባባል ነው ወንድም አፈላለግ:
አመሰግናለሁ በአገራችን ወግ::

ዋርካ እየታደስ ብዙ ቢያቆየን:
ሊመጣ ይችላል ገና ደርሶልን::

ሠላም ድራኮላ!

ድራኮላ ወንዱ ከቶ እንደምናለህ:
ድምፅህን አሰማ ውድበን ላይ ሁነህ:
እኛም እንመጣለን አንተን ልናጅብህ::

**********እሪኩም ከቦሩ ሜዳ**********
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby eri-drimer » Wed Nov 30, 2005 9:22 am

እሪኩም ገላየ ማሬ ወለላየ
አንተ የወንዜ ልጅ ኩራት መመኪያየ
የናፍቆት ሰላምታ ለዘመድ የሚሆን

የድሮው ትዝታ ሊሆን የጻፍክልን
ደርሶን አነበብነው በደንብ አጣጥመን
አመሰግናለሁ እግዚአብሄር ይስጥልን
******

ሀገር ቀውጢ ሆኖ ወገን ተቸግሮ
መነጋገሪያችን ዋርካችን ተሰብሮ
ቅርንጫፍ ሳይኖረው ግንድ ብቻውን ቆሞ

ሄሎሂ ዋይታችን የሚሰማው ጎልቶ
ዋርካው ሲኖር ነበር የሚታይ በርቶ
ቀኖች ተንከባለው ወራት አስቆጠሩ

ሌት ተቀን ሳይሉ ሳይበሮችም ሰሩ
የዋርካን መመለስ ቀልጥፈው ሊያበስሩ

ላይቀር መመለስህ !
ምነው መዘግየትህ !
eri-drimer
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:56 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron