ጠቤ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጠቤ

Postby ኦኑፈያሮ » Tue Nov 29, 2005 7:17 am

ስደተኛው ጠቤ ካገር ቤት ሲወጣ
ተመችቶት ሊኖር ሊበላ ሊጠጣ

ችግር ደህና ሰንብት ብሎ ተሰናብቶ
በሰው ሀገር ደልቶት ሊኖር ልቡ ጉዋጉቶ
ጉዋዙን ጠቀለለ ጠቤ አገሩን ትቶ

ስደት ቀላል ሆኖ ባገር መኖር ከብዶት
መስሎት ነበር ጠቤ ሊኖር ተመችቶት

ጠቤን እንጠይቀው የስደትን ኑሮ
መልሱን እንዲነግረን እጅግ አሳምሮ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Wed Nov 30, 2005 10:11 am

ሰነፍ በስንፍናው ሲቀርበት ሀብት

ፈሪ በፍራቱ ድል ሲቀርበት

እግዜር እግዚአብሄርን ባያወርድለት

ከየት ይገኝ ይሆን ከቶ ምክኒያት

ሰነፉና ፈሪው ጅሉ እንኩትኩቱ

ምንጊዘም ልማድ ነው እግዜርን ማማቱ

እግዜር ችሎት አርጎ ችሎት አስከትቶ

በድሀ ላይ ሲፈርድ ለሀብታም አድልቶ

አየሁ ሰማሁ የሚል ይኖር ይሆን ከቶ

አየሁ የሚል ካለ ይመስክር ተነስቶ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest