የሼጋ ግጥሞችናጥቅሶች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የሼጋ ግጥሞችናጥቅሶች

Postby ሼጋ » Mon Dec 12, 2005 12:58 pm

ለውበት ስል ሞቼ
ብቻዬን ተትቼ
ብቻዬን ቀርቼ
የመቃብር አፈር ቦታ ተመርቼ
ለውበት ስል ሞቼ
ለዕውነት ሲል የሞተ አንድ ሰው አገኘሁ
ጎኔ ተቀበረ
ጎረቤቴ ሆነ ከኔ ውሎ አደረ
ለምን እንደሞትኩኝ
ቀስ ብሎጠየቀኝ
"'ለውበት"" ስል አልኩት
ቀጥሎም የራሱን አሟሟት ሲነግረኝ
""ለሞት የብቃሁት
እኔም ለዕውነት ስል አለኝ
ውበትናዕውነት ሁለቱ አንድ ናቸው
እኛም ሁለታችን
ወንድማማቾች ነን
ብሎ መለሰልኝ::
እንደቤተዘመድ ከርሞ እንደተያየ
ድንገት አንድ ማታ እንደተገናኘ
አወራን
አወጋር
ግርግዳ ለይቶን ብዙ ተጫወትን::
ብዙ ተወያየን
አረም ሙጃው በቅሎ
አፋችን ጋ እስኪደርስ
አልፎም ስማችንን
እስኪ ሸፍን ድረስ::
ቸር ያሰማን

ትርጉም """አይ ዳይድ ፎር ቢውቲ;"""
ሼጋ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Sun Jul 25, 2004 7:37 pm

Postby crypto » Fri Dec 16, 2005 6:56 pm

ውብ!!!
crypto
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Tue Dec 13, 2005 7:28 pm

ክብር ስሜ

Postby ሼጋ » Tue Jan 24, 2006 8:21 pm

ክብር ስሜን አትንፈጉኝ
የመለዮ ቁጥር ባይኖረኝ
ምድብ ብርጌድ ባይሰጠኝ
ስም አድራሻ ሀገር ያለኝ
በሀገር ፍቅር የቆሰልኩኝ
በባለ አደራ የታጠርኩኝ
ላደራም ስል የታሰርኩኝ
እይወቴንም ያጣሁኝ ነኝ
እና አደራ.....
ሀውልቴ ላይ....
ማንነቴን ስትቀርጹ
በማላውቀው ባህል ቁዋንቁዋ
ከነስሜ እንዳትቀድሩኝ
በማይጨበጥ ስያሜ
ከሀገሬ እንዳታርቁኝ
ከእናንተ እንዳትለዩኝ
ኢትዮጵያዊ ወታደር
በሚል ስያሜ ጥሩኝ.
ብላችሁም ቅረጹልኝ;;;;
<<ማስታወሻነቱዋ በቅርቡ ለዲሞክራሲ ሲሉ በሀገራችን ህይወታቸው ላለፉት መለዮ አልባ ጀግናዎች>>
ቸር ያሰማን
Last edited by ሼጋ on Wed Jan 25, 2006 7:43 pm, edited 1 time in total.
ሼጋ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Sun Jul 25, 2004 7:37 pm

Postby ሳምቻው » Wed Jan 25, 2006 2:54 am

ጥልቅ ትርጉም ! ቀለል ባለ ዘይቤ የተከሽነ ,ልዩ እና ቆንጆ ነው !

በሴት ድምጽ በኢንስትሩመንት ትራክ-ሳውንድ ተደግፎ በዝግታ እየተስረቀረቀ ቢነበብ ደግሞ ልዩ ቃና ይኖረዋል ::

በርታ !
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

እህስ

Postby አኒታ » Thu Jan 26, 2006 10:55 pm

እኔም ባደንቅልህ. ከምር ድንቅ ስራዎችን ከማንበብ አልቦዝንም ስድብ ካልተቀላቀለ በቀር..
ሳምቻው:- "" ነጻ የጽሁፍ አገልግሎት "" ለማበርከት የተሰበሰብን ሰልፈኞች መስሎ ይሰማኛል . !!
ይህን ብትለንም.. ግን አንባቢዎች እኮ አንጠፋም መቼም... አለ አይደል እንደ ሸግዬ ጸሀፊዎች ባንሆንም የ እናንተ አድናቂ.. :D ሸግዬ ስራዎችህ እጅግ ውብ ናቸው እጥር ምጥን ያለና እንዳንተው ሸጋ ግጥሞች... በርታልኝ..! በምናብ እየሳልኩኝ ነው የማነበው.. ከምር it looks real!
አክባሪህ አድናቂህ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby shari » Sat Jan 28, 2006 3:47 pm

.......ሻጊ ....... ሸጋ ነው::
shari
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Thu Sep 08, 2005 3:08 pm
Location: ethiopia

ለ አስተያየት!!

Postby አኒታ » Sat Jan 28, 2006 10:25 pm

ሸግዬ መቼም ያንተን ምጥን.. ሽክን ያለች ግጥምህ ፍለጋ ጎራ ማለቴ አይቀርም..ብቻ እስኪ ከቻልክ ባለጭ ጊዜ አንዳድ ወርውር .. በናፍቆት ሚጠቁ እንደ እኔ ያሉ አሉና..አድናቆቴን ሳልቆጥብ በመናገር.. እጅግ ድንቅ ስራዎች አሉ.. ወደፊት ለ እትም አብቅተህ ለሀገር ሰው የሚደነቅ ጸሀፊ እንደሚወጣህ አምናለሁ..!
ሳምቻውዬ.. ሁሉን እንዳላካተትክ ይገባኛል.. ምክኒያቱም እንዲህ ቁምነገሬ ብለህ ምትጽፍላቸው አንባቢዎችህን አክባሪ ሰለሆንክ. እኔ መጻፍ ሰለማልችል እንጂ.. ብችልማ በግጥሞች የናንተን ጽሁፍ ባደናነኩት ሰለ እውነት ዘንድሮ በመጽሀፍት ቤቱ ከሚሸጡት ስራዎች በላይ ጥሩ ነገርን ትጽፋላችሁ! ስለ ድንቅ አስተያየትህና ..በጎ አመለካከትህ ..አምላክ ብድሩን በ እጥፍ ይመልስልኝ. ምስጋና ኪስ አይገባምና :wink: ስላንተ ስራም ደግሞ ሰው አይደለም ድንቅ መጣጦችህ ሰውን የሚስቡት ይናገራሉ! የሰው ልጅ ሊመሰክር አይችልም ከ ምግባር በላይ.. ግን ሚናገር ሰለ እውነት .. ስራ (ምግባር) ነውና.. አትዘን! "ስለ ኖቭል አጻጻፍ ቴክኒኮች እና ዘዴዎች ያገኘሁትን አጫጭር ጽህፎች ፖስት ባደርግ አንድም ሰው የጠየኩትን "" ቲፕ - ሬቲንግ " ሊሰጥ ኣልቻለም" ይህ ላልከው.. አንዳንዴ እኮ አመለካከት ይወስነዋል እዚህ ደግሞ ጥሩ ነግረህ አጸፋውን በመልካሙ አትጠብቀውም አለ አይደል.. ሁሉም የየቅል ነው ነገሩ. :lol: ሚጽፈውንም ሚያቅ አንዳንዴ የለም.. ይሁንና የብዙዎች ድንቅ ስራን ሳናነብ አናልፍምና ያንተም መጣጥፎች ሳላነብ አልወጣሁም.. ለዚህም ነው አትኩሮቴን የሳበችኝን ስንኝ መዝዤ ያወጣሁ :wink: ብቻ አታስብ ሁሉም አንድ አይደለም :!: ሁሉም ጣት በአንድ እጅ ይገኛል ግን ከጣት ጣት ይለያያል!
ሁሉም ሰው ቢሆንም.. በአመለካከቱ ይለያያልና.. አንተ የመሰለህን ከማድረግ አትቦዝን.... አጸፋን ሳይሆን የምታገኘው.. ድንቅ ስራዎችህ ታላቅነትህን ያስመሰክርልሀል.. እኔም ታላቅ አክባሪህና አድናቆቴም የላቀ ነው..::.. ልክ እንዳንተም ብዙዎች ድንግ መጣጥፎችን ያሰፍራሉ.. ስንቱን በአድናቆት እንግለጽ.. መገረም አፍ በ እጅ ያስጭን የለም? ግፉበት ነው እንጂ በዚሁ ይብቃ አንልም.. በተስፋም ብዙ ስራዎችን ይበልጥ እንጠብቃለን.. አስተያየቴ በዚህ ይብቃ! ሁላችንንም ቸር ይግጠመን!
አክባሪያችሁ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ!!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 12:39 am

***********
Last edited by ሳምቻው on Sun Jan 29, 2006 1:02 am, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 12:40 am

ገደልሽኝ እሺ :: ! ዋርካ ማለት "" it is a different world "" መልቲ ካልቸር በይው !!

ዋርካ ውስጥ በርከት ያሉ ወንዶች ጨዋ ናቸው :: ያ ደስ ይላል :: ሞራሉ አለ ማለት ነው ::ጥቂቶች ደግሞ ባህል እና ስረአት የጎደላቸው ናቸው :: እነዚህ ምናልባት ካልቸር-ሚክስ የሆነባቸው ፍንዳታ ነገሮች ናቸው :: በጣም ጥቂቶቹ ደሞ ከበድ ያለ እውቀት አላቸው :: የሚያውጣጣቸው ሲገኝ ቮላካኖ ናቸው :: ታድያ የሚያውጣጣቸው ርእስ ከሌለ በቀር ከኛው ጋር ተመሳስለው የሚኖሩ ናቸው :: በአካል የማውቃቸው አሉ :: የእነሱን እውቀት ለመጠቀም ብለን የዋርካ አስተዳደርን " የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ "" አምድ እንዲክፈቱ ብንጠይቃቸው ዘጉን :: እነሱ ከወሰኑ እኛ ላለመቀበል አንገደድም :: "" impossible is noting ! "" የተሰኘው ዝነኛው የአዲዳስ ካንፓኒ ስሎጋን ለኘ ስቲል አዝጋሚ ነው :

ሴቶቹ የዋህ እና ጨዋዎች ናቸው :: በብዛት :: እነሱን የተሻሉ አንባቢዎች እና ታጋሾች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ :: ጥሩ የሚጽፉም አለ :: የማይታለፉ እና የማይረሱ ሴት ጸሀፊዎች አሉ :: ትህትና (ትትና 2 ) በጣም የተዋጣላት ስዊት ጸሀፊ ነች :: ለሷ በድረሰቱ አለም ትልቅ ቦታን እመኝላታለሁ :: መጻፍ ብቻ ሳይሆን አንባቢም እንደሆነች እገምታለሁ :: ደራሲ ደግሞ ካላነበበ ለመጻፍ ባይደፍር ይሻለዋል ::

ሁሉም ሴቶች እና ወንዶች የሚያስቅ ፖስተር ላይ ያተኩራሉ :: ይሄ የዋርካ ታዳሚዎች በብዛት ወጣቶች መሆናቸውን ያሳያል :: እና ያው ሁላችንም መሳቅ እንፈልጋለን ::የሚያስቁ ጽሁፎችም ሞልተዋል :: ለዛ ያለው ቀልድ ከ ቁም ነገር ጋር እወዳሁ :: በተለይ የፖለቲካ ቀለድ እና ካርቱን እኔን ያስደስተኛል ::

ስለ ቁጭራ ላይፍ -ስታየል ዋርካ ነው ያስተማረኝ :: የምተኛው እምየ-ሚኒልክን ጎርጉሬ አውጥቼ አንብቤ ነው :: ዋርካ ሲያባርረው ገማናውን ሳይደብቅ በየዋህነት እየተናገረ እንደገና በሌላ ኒክ ይመለሳል :: ወደ ኮንፈረነሱ አዳራሽ << በ ዩ.ኤን ህግ መሰረት >> እንደገና ሲመለስ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ በኮንፊደንስ ነው :: መሰስ ብሎ እያወራ ወደ አዳራሹ ተስቦ ይገባል :: የሌላውን ባላውቅም እኔን ይሄ በራሱ ከልብ ያስቀኛል ::
Last edited by ሳምቻው on Sun Jan 29, 2006 1:49 am, edited 10 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 12:41 am

አንዳዶቹ ደግሞ የተምታታባቸው ናቸው :: የምትየው አይገባቸውም :: የሚሉት አይገባሽም :: የሁለት አለም ሰዎች ትሆናላችሁ ::

አንዳንዱ ስለሚጽፈውን ነገር የማያውቅ ሲሆን ያላቅሙ ስላልገባው ነገር ሀይለኛ አዋቂ ለመሆን ሲጥር ከአጻጻፉ ትረጂያለሽ !! እና ያ ጥረቱ ትንሽ ፈን ብጤ ኣለው ::

አንዳንዱ የተጀመረው ርእስ ሳይገባው የፈለገውን ነገር አምጥቶ መሀል ላይ ይሰካና ይሄዳል :: ሌላው እየመረጠ ከማሀል ከመሀል ያነብና ሲጨርስ አጀንዳ ይከፍታል :: በአንድ ፎርም ላይ ስንት ዝብርቅርቅ ሀሳብ የሚመጣውም ለዚህ ነው :: ማለት ነው እንግዲህ :: እቤትሽ ሆኖሽ ስራዬ ብለሽ ከተከታተልሽማ የሁሉንም ባህሪ ከአጻጻፉ መገምገም ትችያለሽ :: አንዳንዱ ዘው ከማለቱ የሚጣላውን ሰው ካየ የጽሁፉን ዋና ርእስ ሳትፈልጊ ያሰቅይርሽና የራሱ የግል ጉዳይ ይጀምራል :: ከየትም ዘው ብሎ ገብቶ ከሌላው ጋር ይጋጫል :: መስመር ላይ የሚገናኙ ቂመኞች አንቺ ስለጀመርሽው ርእስ ጣጣም የላቸው :; አንቺን አስቀምጠው ልክ ከህይወታቸው ክፍል እንደ አንዱ አብይ ጉዳይ በመቁጠር በራሳቸው ጉዳይ ላይ አምርረው ይጨቃጨቃሉ :: ርእስ አስቀይሮ ገብቶ ከፈለገ በፈለገው ሰአት ወጥቶ በዚያው ይቀራል :: ሲምፕል ነው :: አሁንም ትስቂያለሽ :: በገዛ ፖስተርሽ ብዙ ልትየው የምትፈልጊው ነገር ገና እየቀረሽ ሽሚዝ ቀይረሽ እስክትመለሺ ኣንዱ ከሌላው ጋር ሲጋጭ ትደርሺያለሽ :: በራሳቸው የግል ጉዳዩ ላይ ወገበቸውን ይዘው ሲጨቃጨቁ ትደርሺያለሽ :: ሲነታርክ ሲነታርክ ከርሞ ሮረሙ ይዘጋል :: ያንቺ ሩም መሆኑን እስክትጠራጠሪ ድርስ ከዳር ሆነሽ ትመለከቺያለችሽ :: የሚጠይቅ የለም :: ስቲል ኖርማል ነው :: ይሄ የዋርካ የምትቀበይው ካልቸር ነው :: እና ደስ ብሎሽ ትቀበያለሽ ::
በሌሎች ፍረሞች ላይ የተለካከፉ ልጆቹ ደንገት ሌላ ቤት ሲገናኙ ዋናው ጉድይ የእነሱ ይመስል በቁምነገር ይወራወራሉ :: የጠላት ስም ካለ ቶሎ ዘው ነው :: ብድር ለመወጣት :. ...ብቻ ወርም ይቆይ ሳምንት የሚያገናኛቸው ቤት ጋር ድንገት ሲደርሱ የፖስተሩን ባለቤት እና ዋናውን ርእስ ወደጎና አስቀምጠው ቤትሽ ገብተው ኣግሮቻቸውን አጣምረው ተደላድለው በመቀመጥ ; እርስ በርሳቸው ይፋጫሉ :: ዋርካ ባህር ነው ::

ሌላው የሚገርመኝ እና የሚያሳስበኝ በሀገራችን ጉዳይ ላይ ያለን ተላላፊ አመለካከት ነው :; ይህንን እንኳ ባልጀመርው ይሻለኛል ::

በይ ደህና እደሪ :: ለመሆኑ አዲስ'አባ ስንት ሰአት ነው አሁን ? በግዜ ተኚ :: this is the unfinished pool !

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Sun Jan 29, 2006 2:03 am, edited 2 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ቅቅቅቅ

Postby አኒታ » Sun Jan 29, 2006 1:45 am

እንዴት እንደደነገጥኩ አትጠይቀኝ.. አዎ ምሽት ነው .. ትንሽ እቅልፍ አልባ ሰለሆንኩ ነው ቁጭ ያልኩት...አለ አይደል ሰው እድሜው ሲጨምር.. ሀሳቡም የተራራ ቁልል ያክል ይጨምራል.. ከማሰላሰል እዚሁ መቃጠል :lol:
"እነዚህ ምናልባት ካልቸር -ሚክስ የሆነባቸው ፍንዳታ ነገሮች ናቸው :: "ፖስተርሽ ብዙ ልትየው የምትፈልግው ነገር ገና እየቀረሽ ሽሚዝ ቀይረሽ እስክትመለሺ ኣንዱ ከሌላው ጋር በግል ጉዳዩ ላይ ወገቡ ይዞ ሲጨቃጨቅ ትደርሺያለሽ :: ያንቺ ሩም መሆኑን እስክትጠራጠሪ ትገርሚያለሽ :: እና ይሄ ሁሉ የዋርካ ካልቸር ነው እና ደስ ብሎሽ ትቀበያለሽ
-----
በቃ ልልህ የፈለኩት ሁሉ ገብቶሀል ከምር :lol: :lol: ልቤ ውስጥ ያለውን ሁሉ ዘርዝረህ ስትጽፈው በጣም አስቆኛል..ከምር በእኩለ ለሊት እንደ እብድ ሳኩኝ .. :lol:ከምር.. ታዝበሀል.. ስንቱ ሰው ይህን ታዝቦልኝ ይሆን.. ከምር እኮ የሆነ ሚከፈተውን ነገር ስራዬ ብለው ለንትርክ ሽቅድድም ይመስላል.. ቦታ ለመያዝ... እረግግ ደግሞ ይህን አይተው እንዳይወርዱብኝ .. አንተና እኔ ከተግባባን ይበቃል.. ትትና2 እና ትትና ብቻ ይምታቱብኛል እንጃ አንድ ይሁኑ ሁለት አላወኩም.. ብቻ የ ብዙዎች ሴቶች ሚደነቅ ስራ አለ እኮ.. በጣም አደንቃቸዋለሁ እጅግ ነው ሚያኮሩኝ.. ሴቶች ሰለሆኑ ብቻ አይደለም.. ብቻ ሴት ደራሲያን የሉም እና አንድ ቀን እነሱም ቢሆኑ የሚል ምኞት አለኝ...ታዋቂ ሴቶች..ያድርጋቸውም አምላክ...
ብቻ አሳከኝ ከልብ.. አቤት ይህቺን አግኝተው ነው.. አሁን አፋቸውን ያሾላሉ.... ወይኔ ጉዳችን..
ሳሚች..አንድ አሿፊ ሰው.. ሰለ ፍንዳታዎች ምን እንዳለኝ ታቃለህ... DAF ምንድነው ብሎ ጠየቀኝ.. እኔም የ አንበሳ አውቶቢሱ ምልክት የሆነውን ትልቁን የ አውቶቢሱን ብራን ስነግረው .. ትክክል አይደለሽም አለኝ.. ምን እንደሆነ ታቃለህ? ዳግማዊ ፍንዳታ :lol: :lol: :lol: ይቺን አባባሌን መቼም እንደምትፈታትና እንደምታነባት አምናለሁ
አክባሪህ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ :wink:
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 2:16 am

Yanni has given us something very wonderful in his instruments by capturing your inner soul in his very energetic and passion of sound rhythms . u will be in a complete silence of heaven


Image
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 2:56 am

*****
Last edited by ሳምቻው on Sun Jan 29, 2006 3:03 am, edited 2 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ውውውውውውውውውውውውው

Postby አኒታ » Sun Jan 29, 2006 2:58 am

thanks sooo much... i love his all albums and i already take this pic. on my desk top it's wonderful.. album i wish everyone could listen to his albums.. by the way i only missed one album of his work..and i got all :D .. I love it so much.. i got great filling when heared it..fill soo.....peacful.. woderful..i am speechless! to say...you got to hear it!
one of his fan
Anita bonita
cheers! zum wohle!(prost) cheers prost!
:wink:
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Re: ውውውውውውውውውውውውው

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 3:04 am

ቅቅቅቅ

አንቺ ልጅ አትተኚም !!?

አሁን እዚህ ፍራንክፈርት ሰአቱ ስንት መሰለሽ 2:42 ማለት በኛ ከለሊቱ 8:42 :: አዲሳባ ደግሞ ለ 11 ምናምን ጉዳይ !! ቆይ መች ልትተኚ ነው ? ነገ ዊክ እኔድ ነው :: ቢሆንም ስዊሚንግ ካለብሽ ወይም ሌላ ነገር ካለሽ , u know ኮንሰንትሬት እንድታደርጊ በግዜ ተኚ ::

እኔ ትንሽ ቼስ ተጫውቼ እተኛለሁ :: yahoo Intermediates ላይ ነው ያለሁት :: የምጫወተው ከታዋቂው የ ያኒ ኢንስትሩመንት reflections of passion የሚለውን እያዳመጥኩ ነው :: ፖመስ እና ቫሰር አጠገቤ አለኝ :: ሲድኒ ሽልደን ሲጽፍ የ'ያኒን ሚዩዚክ ኮምፕሊት ሳይለንስ ባለው ለሊት እያዳመጠ እነደሆነ ሰምተሽ ታውቂያለሽ ?

ኮንፒዩተርሽ ላይ winamp ፕሮግራም ካለሽ ከ 10 MB በታች የሁኑትን ሙዚቃዎች አታች አድርጌ ልልክልሽ እችላለሁ :: የያኒን ማለቴ ነው :: እውነት ስራ ስፈታ ሳይሆን አለ አይደል ...ለሰው ማውራት ግን የለም !!

ቅቅቅቅ ትንሽ ዘብረቅረቅ ያሉ ኮሌክሽን ርእሶች ይታዩሻል እንግዲህ !! ? ቅቅቅቅቅቅ :: ምን ይደረግ ብለሽ ነው ያውም ባለቤቱ ክፍቱን ጥሎት የሔደው ቤት ሲገኝ 'ማ ቻት ሩም እኮ ሆኖ ነው የሚጠብቀው :: የዋርካ ተለጣፊ ቤቶች እንበላቸው ይሁን .....

አሁን ግን ነግሬሻለሁ ተኚ !! ዋ !ጆሮ ቆራጭ ሳይመጣ አምደ -ማቲዮስ የሚባል ጭራቅ ለሊት ለሊት ሰፈራችሁ አለ ተብሏል እኔ ምን ችገርኝ ::


Last edited by ሳምቻው on Sun Jan 29, 2006 2:02 am
Last edited by ሳምቻው on Sun Jan 29, 2006 4:25 am, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests